የአፍሪካ አባት አጼ ኃ/ስላሴ እንጂ ክዋሜ ንክሩማ አይደሉም ከያዕቆብ ኃይለ ማርያም (ዶ/ር)

February 3rd, 2012

አፍሪቃውያን በአረቦች እየተፈነገሉ ለነጮች ተሽጠው ባህር ሲሻገሩ ንብረታቸውም ወደ አውሮፓና አሜሪካ ሲጋዝ ብዙ ምዕተ ዓመታት እንዳስቆጠሩና ከሃያ ሚልዮን ያላነሱ አፍሪቃውያን በዓለም ዙሪያ እንደተበተኑ ታሪክ ዘግቦአል፡፡ እነዚህኑ አፍሪቃውያን ባህር ማዶ ለማሸጋገር፣ በመርከብ ውስጥ ከታጨቁበት ቀን አንስቶ የተለያዩ ግብታዊ አመጽ ቢያካሄዱም ወደ ካሬ ቢያን የተጋዙት ባሮች እንዲሁም ዘግይተው ነፃ የወጡት ተሳብስበው በ18ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ መላው ጥቁር አቀፍ የነፃነት እንቅስቃሴ (PANAFRICANISM) ጀመሩ፡፡ ይቀጥሉ…

ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ቁጥር 27 ከዜናና ልዩ ልዩ መጣጥፍ ጋር

February 2nd, 2012

ግልጽ ደብዳቤ ለፀሐይ አሳታሚና ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ በክፍሌ ሙላት

February 2nd, 2012

ሲሞላልኝ በሳምንት ካልሆነልኝ ደግሞ በአስራ አምስቱ ሰላምታዬን ካሉበት የማደርሳቸው ወዳጆች አሉኝ። ለአገር ምድሩ ሳይሆን በጣት የሚቆጠሩ። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሙያ ባልደረባዬ ኤልያስ ወንድሙ ነው። ትውውቃችን የመንገድ ላይ አይደለም። የኔዎቹ የነፃ ፕሬስ አባላትና የሃገሬ ሰላም ወዳድ ኃይሎች በግፈኞቹ የሕወሃት አባላትና ሹመኞች የሚሰደዱበት የሚታሰሩበት ብሎም የግፍ ፅዋ የሚቃመሱበት በእነዚያ የትግል፣ የፈተናና የፍልምያ ዓመታት የልብ ወዳጅና ለእውነት የቆሙ በመብራት በሚፈለጉበት የወያኔ የግፍ ዘመናት። ዛሬም ይህ ሐቅ ገሃድ ነው። ይቀጥሉ…

አንድነት በሊዝ አዋጅ ላይ የጠራውን ስብሰባ ለመጪው እሑድ አስተላለፈ (ሪፖርተር)

February 1st, 2012

- መድረክ የአደባባይ ስብሰባ እጠራለሁ እያለ ነው

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ባለፈው እሑድ የሊዝ አዋጅን ለመቃወም የጠራው ስብሰባ ሳይካሄድ ቀረ፡፡ ነገር ግን ይኼንኑ ስብሰባ የፊታችን እሑድ ለማካሄድ ዕቅድ ይዟል፡፡ ፓርቲው አዲሱ የሊዝ አዋጅ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ በሚመለከት ከምሁራን ጋር ለመምከር በእየሩሳሌም ሆቴል ስብሰባ መጥራቱ ይታወሳል፡፡ ይቀጥሉ…

በመከላከያ በተተኮሰ ጥይት ሶስት ሰዎች ሲገደሉ ሁለት ቆሰሉ (አኢጋን)

January 31st, 2012

ፍትህ – የፍትህ ጋዜጣ ከወቅታዊ ዘገባዎቿ ጋር

January 30th, 2012

የፍትህ ጋዜጣ አገር ዉስጥ የምትታተም ነጻ ጋዜጣ ናት። የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዮት አለሙ ፣ የፍትህ ጋዜጣ ዘጋቢ ሂሩት ክፍሌ፣ ለአሥራ አራት እና ለአሥራ ዘጠኝ አመታት ኢሰብዓዊና ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ መሰረተ ቢስ በሆነ የሽብር ተግባር ተሰማርታችኋል በሚል በቃሊቲ እሥር ቤት እየተሰቃዩ ነዉ። ይቀጥሉ…

ፍትህ ጋዜጣ ርዕስ አንቀጽ – በኤርትራ ጉዳይ መመካከር ያስፈልጋል

January 30th, 2012

የአለም አቀፍ ግንኙነት ፖለቲካን የሚያጠኑ ምሁራን በሁለት ሀገራት መካከል ስለሚኖር ግንኙነት ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ ‹‹በአለም አቀፍ መድረክ ዘላቂ ወዳጅም ይሁን ዘላቂ ጠላት የለም›› ፡፡ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በአንድ የታሪክ አጋጣሚ በተመሳሳይ ስም በአንድ ገዢ የሚተዳደሩ አንድ ወጥ በሆነ የፖለቲካ ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ የነበሩ ወንድምና እህታማች አገራት ነበሩ፡፡ አሁንም በአንድ የታሪክ አጋጣሚ አንዱ ራሱን ቅኝ ተገዢ ሌላው ቅኝ ገዢ አድርጐ በመቀጠር ላልተፈለገ ጦርነት ተዳርገው መጨረሻውም የሚታወቀው ሆነ፡፡ ይቀጥሉ…

ጩኸቴ!! (አሥራደው ከፈረንሳይ)

January 30th, 2012

መድረክ የሊዝ አዋጁን የሚቃወም ሕዝባዊ ስብሰባ እጠራለሁ አለ (ሪፖርተር)

January 30th, 2012

ከመቼውም ጊዜ በላይ ከአገሪቱ አነጋጋሪ ጉዳዮች በላይ የሊዝ አዋጁ አወዛጋቢነት ተፋፍሞ በቀጠለበት ወቅት፣ የኢሕአዴግ ዋነኛው ተቀናቃኝ ነኝ የሚለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፣ በሳምንቱ መገባደጃ ላይ በአዋጁ ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞ ይዞ ቀርቧል፡፡ ይቀጥሉ…

የጎጠኝነት አጥሩ እየተሰበረ የአገር አንድነት የሚያስከብር የተስፋ ጎህ እየቀደደ ነው!! በዳኛቸው ቢያድግልኝ

January 30th, 2012