የኢትዮጵያ ህዝብ የገባበት አጣብቂኝ መነሻው፣ መዘዙና መፍትሄው - እስከ ነጻነት

December 25th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ኢትዮጵያውያን እንደ ህዝብ በመሪ ሳንተዳደር በገዥዎች ቀንበር ተጠምደን ስንማቅቅ ብዙ፣ በጣም ብዙ ጊዜ ያለፈን መሆኑን መናገር ለቀባሪ ማርዳት ስለሆነ መዘርዘር አያስፈልግም: የአስተዳደር ስርአታችን ምህዋሩን ለቆ መጓዝ ከጀመረ ብዙ አስርተ አመታት አልፈዋል: ይህም የሐገሪቷ ምህዋር መልቀቅ የሚያሳስባቸው፣ የሚያስጨንቃቸው ዜጎች አቅጣጫውን ለመቀየርና ወደ ተገቢው ተፈጥሯዊ የአስተዳደር ምህዋር ለመመለስ ደፋ ቀና ማለታቸው የማይካድ ሐቅ ነው: ወደ ምህዋሩ መመለስ የምችለው እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ በሚል ሁሉም የበኩሉን ሐሳብና እቅድ ነድፎ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከሚደረገው እሽቅድምድም በተጨማሪ አንቱ ለመባል ስምና ዝናን ለማትረፍ ንብረትም ለማካበት አጋጣሚውን ለመጠቀም የሚራወጡ ቁጥራቸው ቀላል እንዳልሆነም እንገነዘባለን::

እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ ግን እንኳን ለውጤት ያበቃ ቀርቶ የተቃረበ እንኳ ለማየት አልታደልንም: በ1997 ምርጫ ለውጤት ተቃርበን ነበር ግን በመሪ ማጣት ወጤቱን ድሉን ተነጥቀን እንደ ገና ለዳግም ባርነት ተዳርገናል::

ለመሆኑ ይኽ ሁሉ ድርጅት እያለና ይኽ ሁሉ ጥረት እየተደረገ ለውጤት ያልበቃነው ለምንድነው? የሚለው ጥይቄ የሁላችንም ነው ብዬ አምናለሁ:

የችግሩ ምንጭ እንደኔ እምነት ከሆነ የመጀመሪያው ለመሪ ያለን እይታና ግንዛቤ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የሐገሪቷ የጂኦግራፊ አቀማመጥ የሩቅና የቅርብ ጠላቾችን የሚስብ መሆኑ ይመስለኛል: ሰለሁለተኛው ምክንያት አሁን ልለፈውና ስል አንደኛው ሰለ መሪ ችግር በዚህ ጽሑፌ ለመዳሰስ እሞክራለሁ::

ስለመሪ ያለን ግንዛቤ መሪ ነን ብለው ራሳቸውን በሚያቀርቡትም ሆነ ተመሪ ነን ብለን በምንከተላቸው ህዝቦች በኩል እኩል የተሳሳተ ግንዛቤ እንዳለ ይታየኛል: በመጀምሪያ ግለሰብ መሪ በጣም አስፈላጊ ነገር መሆኑን ማስረዳት ያለብኝ አይመስለኝም: ያለ ግለሰብ መሪነት ምንም እንቅስቃሴም ሆነ ውጤት ሊገኝ አይችልም: ትክክለኛ መሪ በፍርሃት ቆፈን የተጨማደደን፣ ዙሪያው ገደል ሆኖበት ተስፋ የቆረጠን ህዝብ ወደ ፍርሃት አልባ ጀግና፣ ልበ ሙሉ አልደፈር፣ አልገብር ባይነትና ብሩህ ተስፋ አላሚነት መቀየር የሚችል አካል ነው: አንድ ምሁር የትክክለኛ መሪን አስፈላጊነት ሲገልጹ እንዲህ አስቀምጠውታል: እጠቅሳለሁ “በአንበሳ የሚመራ የበጎች ሰራዊት ሁልጊዜም በበግ የሚመራ የአንበሶች ሰራዊትን ያሸንፋል” መሪ ተብዬው በግ ለአንበሳው ሰራዊት የሚያስተላልፈው መልእክት የፍርሃት፣ የመሸነፍ የመደንገጥ እና አቅልን አላማን ግብን የመሳት መልእክት ነው: በዚህም ምክንያት ወደ ጦርነቱ ሲገቡ መሸነፋቸውን አምነው ስለሚሆን ውጤቱም የጠበቁት ይሆናል: በአንጻሩ የበጎቹ መሪ አንበሳው ደግሞ ለበጎቹ የሚያስተላልፈው መልእክት የድፍረት የአሸናፊነት፣ የድል አድራጊነት ስለሆነ የበጎቹ ሰራዊት ወደ ጦርነቱ ሲገቡ በሙሉ ልብ ድል አድራጊነት ስለሚሆን እንደ ሓሳባቸው ይፈጸማል:

መሪነት ጥበብ ነው: መሪነት እንደ ሰዓሊነት፣ ደራሲነት የሚታደሉት ተስጦ እንጂ እስኪ ልሞክረው ተብሎ የሚገባበት የስራ ድርሻ አይደለም: መሪነት በትምህርት፣ በዘር፣ በአካል ብቃት ወይም በሐብት ብዛት የሚገኝ አይደለም: መሪነት በውስጥ ማንነት የሚገለጥ፣ የተፈሮ የአመራር ችሎታ የሚታከልበት፣ ያም ደግሞ በትምህርትና በምርምር፣ በልምድ የሚዳብር የጥበብ ዘርፍ ነው:

ምንም እንኳ መሪነት በተፍጥሮ ለሁሉም የሰው ልጆች የተስጠ ጸጋ ቢሆንም ከውስጥ ፈንቅሎ የሚወጣው ግን በተውሰኑ ሰዎች ዘንድ ብቻ ነው: እንደዚያ ባይሆን ኖሮማ እስካሁን መሪ ነን እያሉ ስንት የፖለቲካ ድርጅት ያቋቋሙ ሁሉ ለመሪነት ስልጣን በበቁ ነበር: መሪ ከተከታዮች የተለየ አስተሳሰብ ባህሪይ (attitude) ያለው/ላት ሰውን የማሳመንና በዙሪያው ለማሰለፍ ብቃትና ችሎታ ያለው ነው/ነች:

ትክክለኛ መሪ ልክ ሰዓሊ የሚስለውን ስዕል ሸራው ላይ ከማሳረፉ በፊት በአእምሮው ያለቀ፣ የተጠናቀቀ ቅርጽ እንደሚታየው ሁሉ መረም በአእምሮው ተቀርጾ የሚታየው የተሻለች አገር፣ የኑሮ ደረጃው ከፍ ያለ ህዝብ፣ ከበሽታ፣ ከጉስቁልና፣ ከመሃይምነት የተላቀቀ ህዝብ፣ ህጻናት በፍራቻ ሳይሆን በደስታ የሚቧርቁባት ሐገር የፍርድ ስርአቱ የተስተካከለባት፣ የህዝቦች መብት ጥያቄ ውስጥ የማይገባባት፣ ህዝቧ ዛሬን ምን ልብላ ሳይሆን ለተተኪ ትውልድ ምን አፍርቼ ልለፍ የሚልባት ሐገር ሰው በዘሩ፣ በቋንቋው፣ በኃይማኖቱ፣ በቆዳው ቀለም ሳይሆን በሰብአዊ ፍጡርነቱ ብቻ የሚከበርባት፣ በአለም አቀፍ መድረክ የችግር፣ የረሃብ፣ የቸነፈር፣ የበሽታ፣ የድንቁርና ተምሳሌት ሳይሆን የእድገት፣ የብልጽግና፣ የባለታሪክነት፣ የተስተካከለ አመራር ተምሳሌት የምትሆን አገር ምስል ነው:

መሪነት እንደ ማንኛውም የጥበብ ዘርፍ ልክፍት ነው: ትክክለኛ መሪን ገንዘብ፣ ጥሩ ኑሮ፣ ድሎት፣ ስምና ዝና አያረካውም: የሚያረካው ህልሙ፣ ራዕዩ እውን መሆን ሲችል ብቻ ነው:

ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ፣ ሁሉም ተነስቶ ከጭንቀት ወይም ከተለየ አላማ በመነሳት፣ እኔ ልምራችሁ ተከተሉኝ ብሎ የሚነሳው መሪ ሁሉ ይህ ተሰጦ ስላልነበረው፣ ስለሌለው የመሪነት ብቃቱን ራሱ እንኳ ሳያምንበት እየገባበት ለቁም ነገር ሳይበቃ እንደ ዋለ ቀርቷል: እኛም ልምራችሁ ብሎ የተነሳ ሁሉ መሪ የሚሆን እየመሰለን ስንከተል ገደል አፋፍ ላይ እያደረሱን እንኳን እኛን ሊመሩ ቀርቶ እነሱም አቅጣጫው ጠፍቶባቸው የሞት የሽረታቸውን ሲንደፋደፉና ጠላት ጎራ ሲመሰጉ በተደጋጋሚ አይተናል::
መሪ ነኝ ያለ ሁሉ መሪ አይደለም አይሆንምም::

ሌላው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ መሪ ነኝ ባይ እንዲመለክ እንዲሰገድለት ስው ሁሉ እንዲሽቆጠቆጥለት ይፈልጋል: እኛም ተመሪዎች ወይም ተከታዮች መሪዎችን እንደ ተለዩ ፍጡሮች የማየት፣ አላግባብ የማክበር ጎንበስ ቀና በማለት ባህል ተጠፍረን የተያዝን ነን: መሪ በመሰረቱ ለህዝብ አገልጋይ እንጂ በህዝብ ተገልጋይ አይደለም መሆንም የለበትም: ስለዚህ መሪ መባል ያለበት አንተ ወይም አንቺ ነው: ወደ ስልጣን ከሚያደርገው ጉዞ ጀምሮ በስልጣን ላይም እያለ ህልውናው የሚቆመው በኛ በዜጎች ወይም በተከታዮች የህይወት፣ የጉልበት፣ የእውቀት እና የገንዘብ መስዋእትነት ስለሆነ፣ አመራሩም ካልጣመን ልናስወግደው የምንችለው እኛው ህዝቦቹ ስለሆንን፣ እርሶ፣ አንቱ መባል ያለብን እኛ ነን እንጂ መሪዎች አይደሉም: አገልጋያችንን አንቱ ማለት አስፈላጊ አይደለም: እርሶ ካልተባልኩ የመሪነት ስልጣን አልፈልግም የሚል ካለ በኔ በኩል በደስታ እቀበለዋለሁ: እኔ ከአሁን ሰአት ጀምሮ መሪ ነኝ ብሎ የሚነሳን ሁሉ አንተ/አንቺ ብዬ የምጠራው መሆኔን ውድ አንባቢዎቼ እንድታውቁልኝ እጠይቃለሁ: ይህን ስል እንኳን ታላላቆቼን፣ ባለስልጣናትን ቀርቶ ወላጅ አባቴን እንኳ አንቱ፣ እርሶ ብዬ ያደግሁ ሰው አሁን ተነስቼ መሪዎቼን አንተ/አንቺ ብዬ መጥራት ምን ያህል ስቅቅ እንደሚያደርገኝ ሳልገልጽላችሁ ማለፍ አልፈልግም: ነገር ግን መሆን ያለበት ነው ብዬ ስለማምን ባህላዊ ግርዶሼን ቀድጄ ጥየዋለሁ: አብሮት የነበረውን የባህል ዲሪቶ ሁሉ አውልቄ መጣል ብቻ ሳይሆን አቃጥየዋለሁ: ተመልሼ ልደርበው ብል እንኳ የለም አላገኘውም: እመራሃለሁና ተከተለኝ ብሎ የተነሳን/ችን ለመከተል ፈቃደኝነቴን ወይም አክብሮቴን ከመቸሬ በፊት ትክክለኛ የመሪነት ብቃት ያለው ያላት መሆኑን ማጣራት ተቀዳሚ ስራዬ ይሆናል::


ለመሆኑ ትክክለኛ መሪ በምን ይገለጻል፧ ወይም በምን ይለያል?

ትክክለኛ መሪ የተለዬ ስነ አእምሮ (attitude) ያለው ነው

1. ትክክለኛ መሪ በራሱ የአመራር ችሎታ የሚተማመን፣ ደፋር፣ ለበ ሙሉ፣ የሚታየው ሽንፈት ሳይሆን ድል፣ ውድቀት ሳይሆን ስኬት፣ ጨለምተኝነት ሳይሆን ብሩህነት፤ ጥላቻ ሳይሆን ፍቅር፣ በቀል ሳይሆን በፍትህ ላይ የተመሰረት ይቅር ባይነት ነው:

2. ትክክለኛ መሪ እንደ ሀውልት የጸና ባህሪይ የሚታይበት ነው: ሐውልት በዝናብ በጸሐይ፣ በብርድ በሙቀት፣ በብርሃን በጨለማ እንደማይቀያየር ሁሉ የመሪ በህሪም እንደዚሁ በድልና በሽንፈት፣ በስኬትና በውድቀት፣ ተቀባይነት በማግነትና በማጣት ጊዜ አይቀያየርም: ባጭሩ በድል፣ በስኬት አይፈነጥዝም፣ በሽንፈት ጊዜ አይሸበርም፣ ተሰፋ አይቆርጥም፣ በተከታዮቹ ተቀባይነቱ በበዛ ጊዜ አይፈነጥዝም፣ ተቀባይነቱ ሲቀንስ አያኮርፍም አይነፋነፍም: አቅሉን አይስትም: በአቋሙ እንደ ጸና ይኖራል::

3. ትክክለኛ መሪ የቀድሞ ስህተቱ ወይም ውድቀቱ በወደፊት ራእዩ ላይ አያጠላበትም ካለፈ ስህተቱ ወይም ውድቀቱ ተመክሮ ወስዶ ለቀጣይ ግቡ በጥንካሬ የሚጓዝ ነው:

4. ትክክለኛ መሪ በቀለኛ፣ ቂመኛ አይደለም ይቅር ባይ ነው (forgiveness) እዚህ ላይ ይቅርታ ስል ወንጀለኛ ወንጀሉ ይሰረዝለታል ማለት እንዳልሆነ ልብ ልትሉልኝ ይገባል: ይቅርታ ማለት በቀልን በራስ እጅ አልመውሰድ ለህግ አሳልፎ መስጠት ማለት ነው: ይቅርታ በጽኑ የህግ ስርአት ላይ እስካልተመሰረት ደረስ ዘለቄታ አይኖረውም::

5. ትክክለኛ መሪ ተከታዮችን በተከታይነት ይዞ የሚጓዝ ሳይሆን ተተኪ መሪዎችን የሚያፈራ ነው:

6. ትክክለኛ መሪ በቅርብ እይታ ወይም በአይነ ስጋ አይን አድማስ አይመራም ይልቁንም በአይነ ህሊናው ራእይ የሚመራ ነው:

7. ትክክለኛ መሪ ለአብዛኛው ህዝብ የኑሮ መሻሻል፣ ለልጅ ልጅ የሚወረስ ቅርስ ለማዘጋጀት፣ አይን ከሚያየው ርቆ ለተቀመጠ፣ በአይነ ህሊና ብቻ ለሚታይ ራእይና ግብ ለመድረስ እንደ ንስር አሞራ የሚመነጠቅና ወገኖቹንም ከወደቁበት ዘርፈ ብዙ አረንቋ መንጥቆ ለማውጣት በራሱ የሚተማመንና የህዝብ አመኔታን ማትረፍ የሚችል ልዩ የአመራር ጸጋ የተቸረው ነው:

8. ትክክለኛ መሪ የማያምንበትን አይናገርም የተናገረው ቃሉ፣ ቃል ከዳኑ ነው: በቃሉ የጸና በእምነቱ የጠነከረ ነው: አላማውን ከግብ ለማድረስ ለሚያደርገው ጉዞ ችግር፣ እስራት፣ እንግልት፣ ስቃይ አያግደውም: የመንገዱ ጠመዝማዛነት፣ እሾሃማነት፣ ወጣ ገባነት አይገድበውም: እንዳውም የበለጠ ያጠነክረዋል ያጸናዋል:

ትክክለኛ መሪነት እንግዲህ ከላይ ከሞላ ጎደል ከላይ የጠቃቀስኳቸውን መስፈርቶች የሚያሟላ ግለሰብ ነው::

በቡድን አመራር ወደ ግብ መቃረብ ይቻላል ለድል ለመብቃት ግን የግድ የተናጠል ወይም የግለሰብ መሪነት ያስፈልጋል: የ1997 ምርጫም ለመጨንገፍ ካበቁት ምክንያቶች አንዱ ይህ የትክክለኛ መሪ የማጣት ጉዳይ ነው ብዬ አገምታለሁ::
እያንዳንዱ ሰው የራሱ ተሰጦ አለው ሁሉም መሪ አይሆንም ሁሉም ተመሪ አይሆንም: እያንዳንዱ እንደ ተሰጦው ለሐገሩ ለወገኑ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ: ማንም ሰው ደግሞ ለራሱ ከሰጠው ግምት ባላይ ሊሄድ አይችልም: እያንዳንዱ የሚደርስበት የኑሮ ደረጃ ለራሱ ብቃት ካለው ግንዛቤ ሊዘል አይችልም: የያንዳንዱ ግለሰብ ተግባር የስነ ልቦናው ነጸብራቅ ነው:

በዚሁ መሰረት እያንዳንዱን ፖለቲከኛ ሰነ ልቦና (mind setup) መመልከትና መተነተን ይቻላል:

ሁሉንም ፖለቲካኛ ነኝ ወይም የፖለቲካ ድርጅት መሪ ነኝ የሚሉትናን በሐገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን (ከሐገር ውጭ ያሉትን በሌላ ጊዜ ስለምመለስበት ነው) መመርመርና መፈረጅ የሚቻል ቢሆንም የአንባቢን ጊዜና የግል አስተሳሰቡንና የአድማስ ገመዱን መገደብ ወይም የሐሳብ አቅጣጫው ላይ ተጽዕኖ ማድረግ እንዳይሆንብኝ፣ አንባቢዎቼ ስለ እያንዳንዱ የፖሊቲካ መሪ የአመራር ብቃት፣ የሐገሪቱን በትሪ ስልጣን ተረክቦ ሊያስተዳድር፣ ህዝቡን ወደተሻለ የኑሮ ደረጃ ለማሸጋገር ብቃቱ፣ ተሰጦው፣ የስነ ልቦና ዝግጅቱ፣ የተፈጥሮ የአመራር ችሎታው፣ አለው ወይ ብላችሁ ወደ ራሳችሁ ድምዳሜ እንድትደርሱ ጋብዤ አልፈዋለሁ:

በኔ በኩል የአመራር ተሰጦ፣ ችሎታ፣ እውቀቱ፣ የስነልቦና ዝግጅቱ፣ ራእዩ አላት የምላት መሪ አንድ ብርቱካን ሚደቅሳ ብቻ ነች::

የተቀሩት ሐገራቸውን በተለያየ የሙያና አገልግሎት ዘርፍ የማገልገል ብቃቱና ችሎታው ያላቸው መሆኑን እያመንኩ፣ በዚያም በተሰጣቸው ጸጋ ሐገርና ህዝባቸውን ከማገልገል አልፈው መራሄ መንግስቱን ከመለስ ነጥቆ፣ ተረክቦ ለማስተዳደር ብቃቱ አለው ብዬ የማምነው ግለሰብ ግን የለም:

መለስ በካርተር ማእከልና በእንግሊዝ መንግስት የተተከለ የውክልና ገዥ መሆኑን ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነይ: ጂሚ ካርተር ለኖቬል ሽልማት ያበቃውን የግብጽና የእስራኤል ስምምነት ሲያፈራርም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም አሳልፎ ለመስጠት መማለጃ ማድረጉ ልብ የማይል ያለ አይመስለኝም: ይህም ወያኔ ወዲያው ስልጣን እንደያዘ እ. አ. አ. 1993 የመጀመሪያውን የሐገር ህልውናና ጥቅም አሳልፎ የሰጠበትን ናይል ፍሬም ወርክ አግሪመንት (Nile Framework Agreement) ከግብጽ ጋር መፈራረሙን ማስታወስ ያስፈልጋል: መለስ ዜናዊ የቆላ እባብ (የኮብራ) ጭንቅላት ያለው ሰው ነው: አሳቡ ሁሉ አጠገቡ የተገኙትን፣ ለስልጣኑ ያስጋኛል የሚላቸውን አስደንግጦ የማባረር እንዲያም ሲል መርዞ የመግደል ባህሪ ያለው ፍጥረት ነው: ከአረጋዊ በርሄ ጀምሮ የተባረሩትና አድራሻቸው የጠፉ እጅግ ቁጥራቸው የበዛ ዜጎች ለዚህ ባህሪው በቂ ምስክር ናቸው: ስልጣን ከያዘ በኋላም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ከአረካ እልቂት እስከ ትናንቱ የነ ጄነራል ተፈራ ማሞ ፍርድ ድረስ ምን ያህል ህዝብ እንደፈጀ ፀሀይ የሞቀው፣ ማወቃቸውን መናገር ባይፈልጉም አለም ያወቀው ጉዳይ ነው::
የመለስን መርዝ በሰላም የበዘምባባ ዝንጣፊ ተከላክላ በህግ ባላ አንገቱን ጠምዝዛ መርዙን ወደራሱ ልታስተፋ የምትችል ብቸኛ ሰው ድግሞ ብርቱካን ነበረች:ይህንን ድግሞ ወያኔ ብቻ ሳይሆን የምእራብ አጋሮቹ ጠንቅቀው ሰለሚያውቁት፣ አዳኝ ውሻቸው ከስልጣን እንዲባረርባቸው ስለማይፈልጉ ብርቱካን እንድትታሰር ወያኔን መክረዋ የሚል ጽኑ እምነት አልኝ:

የአንድነት መሪዎችም (የነ ኢንጂነር ግዛቸው ቡድን ማለቴ ነው) መታሰሯን ፈልገውት ነበር ለማለት ባልደፍርም መታሰሯ ግን እንዳላስከፋቸው ጥርጥር የለኝም: ይህም በተለያዬ ጊዜ ከድርጅቱ ቃል አቀባይ ጀምሮ የሰጧቸው ቃለመጠይቆች እሷን ለማስፈታት የሚደረጉ አገም ጠገም እንቅስቃሴዎች ዋቤ ናቸው:

ማጠቃለያ:

• ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ የድርጅት መሪዎች መካከል የመሪነት በትረ መንግስትን ለመረከብና ሐገሪቱናን ህዝቡን ለመምራት የተዘጋጀ፣ ችሎታውና ተሰጦ አለው የምለው ሰው አላገኘሁም :

• አንድ መሪ ብትኖር ለጊዜው አካሏ እስር ቤት ነው መንፈሷና ራእይዋ ግን በአለም ሁሉ እየተናኘ እየተሰራጨ ነው ይሰራጫልም:

• መለስ ዜናዊ ከዘረኛ አምባገነንነቱ በተጨማሪ የካርተር ማእከልና የእንግሊዝ ተወካይ ባንዳ እንጂ ኢትዮጵያዊ ገዥ አይደለም:

• ኢትዮጵያ በሰላምና በብልጽግና እንድትኖር የማይፈልጉ ዘርፈ ብዙ ጠላቶች ያላት ሐገር ነች: ለአላማቸው ማስፈጸሚያ ደግሞ አሁን ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችቶላቸዋል:

• ከአንድነት ድርጅት ቃርመን ልናስቀር የምንችለው አላማውን፣ ህገ ደንቡን፣ ህዝቡንና ብርቱካንን ብቻ ነው የሚል ጽኑ እምነት አለኝ:

• ከዚህ ሌላ ነጻ ሊያወጣኝ የሚችል መሪ አለ ብዬ ጊዜየንም ጉልበቴንም የማባክንበት ምክንያት የለኝም:

አሁን ጥያቄውም ውሳኔውም በያንዳንዳችን እጅ ነው

1. በካርተር ማእከልና በእንግሊዝ ተወካይ ባንዳ በዘረኛ አምባ ገነን በባርነት፣ ገበያ ለማረጋጋት ወንዝ የሚጨምሩትን ፍርፋሪ እየጣሉልን ያውም ለመለስ ደጋፊዎች፣ የማንደግፍ ደግሞ ዉሃ፣ ውሃ እህል፣ እህል እያልን አልቀን ልጆቻችንን አገር አልባ ባሪያ አድርገን እናልፋለን?
ወይስ

2. ነጻነታችንን አስከብረን ለልጆቻችን ነጻ ሐገርና ነጻነትን አውርሰን የሰላም እንቅልፍ እናንቀላፋለን?

መልሱ ለያንዳንዳችን

ውጭ ስለሚኖረው ወገናችን ስነ አእምሮ (mind setup} በሚቀጥለው እመለስበታለሁ

አመሰግናለሁ

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

እስከ ነጻነት

  1. ነቢዪ ከበደ
    December 25th, 2009 at 14:27 | #1

    ትክክል ነው በታም አደንክሃለሁ

  2. ተሰማ
    December 25th, 2009 at 14:33 | #2

    No author nothing!

    You blame everyone including the opposition politicians. What do you want them to do? What good things did you do first? You better mind what comes from your mouth…I am sure either the Europeans or opposition leaders are happy because Birtukan was arrested. How can you speak of such kind of allegation with no evidence? I advise you not to write such kind of lopsided fiction that blames everyone. I suspect you are one of those woyannes.

  3. ቶክቻው
    December 25th, 2009 at 15:53 | #3

    በእሳት የተፈተነ መሪ ለማግኜት እግዚአብሔር ይርዳን!

  4. tk jinka
    December 25th, 2009 at 16:24 | #4

    ይህ ነው እውነቱ !!!!

  5. Shagi
    December 25th, 2009 at 17:51 | #5

    I think you have meditated very well and I appreciate that, but dont limit yourself saying only Birtukan, there are also others who can make things better. Try to encourage them instead of discouraging. We should not limit our selves coz that is the way Meles also thinks. He thinks that he is the only lider no body else can be. so try to open your horizon and give hope to the new generation. May God bless Ethiopia.
    I also encourage you to write more.

  6. ETHIOPIAN
    December 25th, 2009 at 20:13 | #6

    TO ESKE NETSANET

    The first statement of your conclusion that asserted “that you did not find a qualified opposition leader who can hold state power and lead” is an offensive as the comment of (professor?) Mesfin Woldemariam’s who said same statement in joining UDJ. As one commentator had put it in his small page article in this website a couple days ago, under the title PROFESSOR MESFIN YETEYEK (in Amharis) professor Mesfin alleged that he joined UDJ not because he believed UDJ is a good party but he has no other political parties he trust and depend upon. So are you a spokesman of Mesfin repeating the same joke or are you a Weyane’s cadre living to benefit for the service you are performing ??????

  7. gezaw
    December 25th, 2009 at 21:00 | #7

    I coudn’t understand your last statement about udj leaders who are fighting at home. Shame on you.

  8. መሪ ከሰማይ አይወርድ
    December 25th, 2009 at 22:25 | #8

    እስከ ነጻነት (የመጣጥፉ ባለበእት) ገና ከመጊቢያው ያደናግሩናል:: በመጀመሪያ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን የመሰረቱ ሀገሮች ብዙ የ’ዕድገት ደረጃዎችን አልፈው ነው::መገዛት በኢትዮጵያ ብቻ የተከሰተ አይደለም:: ሁለተኛ ስላለፈው ሥር’ዕአት ለአዲሱ ትዉልድ ማስተማር/ማሳወቅ ምን ክፋት አለው? ይልቁንስ ችግርዎት በማስረጃ ማስደገፍ ካልሆነ በቀር::እናም የሚከተለው አባባልዎትን አልቀበለውም::
    1. “…ኢትዮጵያውያን እንደ ህዝብ በመሪ ሳንተዳደር በገዥዎች ቀንበር ተጠምደን ስንማቅቅ ብዙ፣ በጣም ብዙ ጊዜ ያለፈን መሆኑን መናገር ለቀባሪ ማርዳት ስለሆነ መዘርዘር አያስፈልግም:…”
    የሚከተለው ደግሞ አንዳንድ እውነቶችን ያዘለ ቢመስልም እኔ እንደመሰሪ አስተያየት ነው የማየው::ተቃዋሚው ከራሱ ድክመት (እርስዎ እንደሚሉት መሪ በማጣቱ) ድል ከ’እጃችን አፈተለከች ሲሉን መለስን ከማወደስ ምንም አይለይም::

    2.”…በ1997 ምርጫ ለውጤት ተቃርበን ነበር ግን በመሪ ማጣት ወጤቱን ድሉን ተነጥቀን እንደ ገና ለዳግም ባርነት ተዳርገናል::…”
    የመሪን አስፈላጊነት ማንም ባይስተውም የሕዝቦችንም ሚና መዘንጋትን ግን አይዘንጉ::
    መሪ ያጣነው ስለመሪዎች ያለንን የተሳሳተ አመለካከት እንደሆን አበክረው ነግረውናል::የዘነጉት ነገር ግን እንዴት ይህንን አመለካከት እንዳዳበርን ነው::ማነው ተጠያቂው ለዚህ? እንዴትስ እናስወግደዋልን (እርስዎ እንዳሉት ከሆነ)?

    ይህ የአማሪኛው ታይፒንግ ስለአስቸገረኝ እዚሁ ላይ አቁመእ ከተስተካከልልኝ እመለሳለሁ::
    የሚገርመው አቡጊዳዎች ድህረ-ገጿን መርሳታቸው ነው!

  9. መሪ ከሰማይ አይወርድ
    December 25th, 2009 at 22:37 | #9

    ቡጊዳዎች አንድ በሉኝ::
    በማሪኛ ስ’ጽፍ እምጽፈው ነገር አይታይም::ብሳሳት ወይንም የጻፍሁትን ለመለወጥ ብፈልግ አልችልም::ምክንያቱም ታይፕ ሳደርግ እማየው የሆኑ ብሎኮችን ብቻ ነው::የመጣ ይምጣ ብዬ አስተያየተእን ስልክ ነው ምን እንደጻፍሁ እምረዳውና መፍትኼውን ንገሩኝ::
    ወይንም አስተያየታችንን ለማረም የሚያስችለን ዘደእ ፍጠሩልን እንደናዝረእትዶትኮም!

  10. ታሪክ
    December 26th, 2009 at 01:27 | #10

    የቀረበው መጣጥፍ ሸጋነቱ የጎላ ቢሆንም
    በአንድ ሰው ላይ ብቻ መተማመንንን ግን እንደ ትክክለኛ መፍትሄ አድርጎ ለማየት የሚከብድ ይመስለኛል

    አዎ ብርቱካ ሚደቅሳ የመጀመሪያዋ ምሁርና የእንሰት ደፋር ፖለቲከኛ መሆንኗን ሁላችንም እንስማማለን

    “”"እሷ ብቻ ናት መሪ ልትሆን የምይችለው : ሌላ የሚታመን የለም”"” ብሎ መደምደም ግን ትክክለኛ አባባል አይመስለኝም
    አንገት የተፈጠረው አዙሮ ለማየትም ጭምር ነውና : ነገሮችን ረጋ ብለን ካየናቸው
    ሌሎችም ብዙዎቹ እንዳሉ ማስተዋል እንችላለን

    እንዲያውም አንዱና ዋና ችግራችን “”ይህ በአንድ ሰው ላይ የመተማመን አባዜ”" ይመስለኛል

    መንግስቱን ኃይለ ማርያምን ተከትለን “”ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባርን”" አብረን ስንፎከር ኖርን :
    አይተ መለስም አንዳንዴ በሚደሰኩሯቸው አስመሳይ የዱርዬ ቃላት ጎበዝ ምናምን እያልን ነበር… ሌላም ሌላም መጥቀስ ይቻላል

    ዕገሌ ብቻ ነው ትክክል ከሚለው ግለሰባዊ መሞገስ ወጥተን አገርን ማዕከል ያደረገ ራዕይ ላይ ብናጣጥርና : በአንድ ሰው ትክሻ ላይ ሳይሆን በተባበረ ሕዝባዊ ሰላማዊ ትግል ሊመጣ በሚችል ለውጥ ላይ ብንመክር የሚሻል ይመስለኛል

  11. F.M.W.
    December 26th, 2009 at 01:56 | #11

    ይህ ነው እውነታው

  12. በለስ
    December 26th, 2009 at 06:27 | #12

    ይህ ጽሑፍ ሰፊ እውቀትን የያዘ ነው:: መቋጫው ግን ጠባብና ሃሳቡ ተደላድሎ እንዳይቆም ስላደረገው ትንሽ ያሳዝናል::
    ይህ ጽሑፉን ከግል ፍላጎት ጋር ላማያያዝ የተደረገ ሙከራ የፈጠረው ስህተት ሲሆን ሃስቡም ጎደሎ እንዲሆን አድርጎታል:: እውነተኛ መሪዎች ከሚመሩት አካል አብራክ ነው የሚወጡት:: ብርቱካን ምንም እንኳን አስተዋጽዖ የማድረግ ችሎታው ቢኖራትም የቅንጅት መሠረት ከነበሩት ኢዴፓና መኢአድ አብራክ ባለመውጣቷ ትልቁ ደካማ ጎንዋ ነበር:: ጸሓፊው የራሱን ጽሑፍ ሎጂክ ቢከተል የተጠቀሱትን መስፈርቶች በተሻለ ሁኔታ የሚያሟላ መሪ ልደቱ አያሌው ነው:: ሌሎች መስፈርቱን ማሟላትና በሕዝብ ቀልብ ውስጥ መግባት ያልቻሉ መሪዎች በሃሰት ስም ማጥፋት ጠልፈው ጥለውት እንጂ. መስፈርቶቹን በከፊል ያሟላል ያልኩበት ምክንያቱም ራሱን ከመጠለፍ መከላከል መቻል ስለነበረበት ነው::

    የመሪ ዋናው መገለጫ የሚፈልጋቸው ፍላጎቶች ወይም ራዕዩ ሳይሆን ይህንን ራዕይ ተግባራዊ በሚደረገው ጉዞ ላይ የሚያስመዘግበው ውጤት ነው:: ልደቱ የአገሪቱን የፖለቲካ ባህል; አሰራር; ሂደት ወደኋላ እንዳይመለስ አድርጎ ቀይሮታል:: ከሱ በፊትም ሆነ ከሱ ውድቀት በኋላ መሪነቱን የጨበጡ ተመጣጣኝ የሆነ ውጤት ያስመዘገበ የለም::

    ምናልባት ልደቱ ከውድቀቱ ተነስቶ ተጨማሪ ውጠቶችን ያስመዘግብ ይሆናል:: ወይም እንደወደቀ ሊቀር ይችላል; ጠላቶቹ ለትና ቀን እየሰሩ ስለሆነ:: የተሻለ ድርጅት አደራጅቶ; የላቀ ህዝብ አስከትሎ የተሻለ ውጤት የሚያስገኝ መሪ እስኪመጣ ድረስ በመሪነት ሚዛን ቅዳሚ ስፍራ ይዞ መቆየቱ አይቀርም::

  13. ASHENAFI
    December 26th, 2009 at 11:16 | #13

    የተከበሩ አቶ በለስ ….. ምንም እንኳ ግለሰባዊ ነቀፌታን የማልደግፍ ቢሆንም የሰጡት አስተያየት በጣም ጎጂ ሆኖ አግኝቼዋለሁ:: የኢትዮጵያን ህዝብ በአፈ-ጮሌነት ማንም ሊያድነው አይችልም :: ጥሩ የአነጋገር ተሰጥኦ ለአንድ መሪ ጥሩ መመዘኛ ሊሆን ይችላል :: ይሁን እንጅ ጥሩ ተናጋሪዎች ጥሩ መሪዎች ናቸው ማለት ትክክል አይደለም :: በርስዎ አገላለጽ ልደቱን የሚያክል መሪ ሊኖረን አይችልም ነው ? በጣም ተሳስተዋል ::የልደቱን አቋም ገና ከመነሻው ጀምሮ ብዙዎች ለመገመት አልተቸገሩም :: ግለሰቡ ራሱን” ወደስልጣን ጥመኛ ” ዝቅ ከማድረጉ በፊት የወያኔ ተወካይ መሆኑን ሁሉም ሰው ካነጋገሩ ለመረዳት ችለናል :: እውነት ነው ኢትዮጵያ መሪ አላገኘችም እስከዛሬ ! ይህ ማለት በአገሪቱ መሪ የሚሆን ሰው አልተፈጠረም ማለት አይደለም :: ችግሩ መሪና ተመሪ አልተገናኘንም ::መሪዎች ሊሆኑ የሚችሉ ብሩህ አእምሮ ያላቸው ድንቅ ዜጎች በአምባገነኖች ተፈልገው ስለሚረሸኑ :: ሁሉም ሰው በተለያየ ዘርፍም ቢሆን የመሪነትን ጸጋ ተሞልተን ነው የተፈጠርነው :: ልዩነታችን እድሉ በሚገኝበት ጊዜ ራሳችንን አለማዘጋጀታችን እና በገኘነውም እድል ጸንተን ባለመቆማችን ነው የመሪነቱን ትርጉም እያጣመምን ያለነው :: እግዚአብሄር ለኢትዮጵያ መሪን ይስጣት ::

  14. በለው!
    December 26th, 2009 at 14:10 | #14

    የዚህ ፅሁፍ ባለቤት ትንሽ ቁጠኛ ናቸው ሐሳቡ ከሌላ ቋንቋ ላይ የተተረጎመ ይመስላል ሆኖም
    የልባቸውን እንደ ኢትዮጵያ ቡና እንደወረደ አቅርበውታል ጥሩ ፀሐፊ ጥሩ አንባቢ ሲገጥመው
    ተገቢውን አስተያየትም ሲያገኝ መቀበል ከቻለ የመሪነት ሚዛን አንዱ ክፍል ነውና…
    አቶ ተሠማ, ኢትዮጵያ , ታሪክ የተባሉት የሠጥዎትን ምክር ለሚቀጥለው ይጠቀሙበት::
    አስተዳደር(መሪ),ባሕል,ሀገር,ፖለቲካ…. ሲቧቀሱ!
    “መሪ ነኝ ያለ ሁሉ መሪ አደለም አይሆንም”
    ” መሪ በመሰረቱ ለሕዝብ አገልጋይ እንጂ በሕዝብ ተገልጋይ አደለም መሆንም የለበትም”
    ” አገልጋዮችን አንቱ ማለት አስፈላጊ አደለም”
    “ባሕላዊ ግርዶሼን ቀድጄ ጥዬዋለሁ አብሮት የነበረውን የባሕል ድሪቶ ሁሉ አውልቄ መጣል ብቻ
    ሳይሆን አቃጥዬዋለሁ” እራቁቱን የቆመ መሪ …
    ትክክለኛ መሪ….1. በራሱ የአምራር ችሎታ የሚተማመን>ለመሆኑ ችሎታው በማን ይረጋገጣል?
    2. እንደ ሀውልት የፀና ባሕርይ የሚታይበት>አንድ መሪ አንድ ፓርቲ የሕገ-መንግስቱ ጽሑፍ ?
    3. ካለፈው ስሕተቱ ተምሮ ለቀጣዩ ግቡ በጥንካሬው የሚጓዝ>ኢህአድግ ስሕተቱን አይደግምም?
    4. በቀለኛ ቂመኛ ያልሆነ ይቅር ባይ> መቻቻል?የመከተል እንጂ የሐሳብ ልዪነት ማንጸባረቅየለም?
    መጠየቅ,መልስ ማግኘት,ማመን ማሳመን,መወያየት,መከራከርና ታሪክ መጥቀስ ነውር ናቸው?
    5. ተተኪ መሪዎችን የሚያፈራ> አርዓያ የሚሆን ለማለት ነው? የተከታዩ ደስተኛ መሆን በሥርዓት
    በግብረገብ መታነፅ ለለውጥ ተነሳሽነት እንጂ መሪ በመሪ የሚሠራ የሽክላ ውጤት ነው?
    6. በዓይነ ሕሊናው ራዕይ የሚመራ> የማፍረስ,የመገንባት,አፍርሶ የመስራት,የማጥፋት..ራዕይ?
    7. የህዝብ አመኔታን ማትረፍ የሚችል> በምኑ ?የሰው ማንነቱ የሚገምተው ተቀምጠው እስኪነሱ
    ነበር አሁንማ ከተቀመጡብን በሗላ የተደፈጠጥን አይምስልዎትም?
    8. በቃሉ የጸና በእምነቱ የጠነከረ> ታርአለህ ትበግናልህ ትቃጠላለህ ምን ታመጣልህ?
    እንደቃልህ ይደረግልህ ሳይሆን እንደሕዝባችን ዕውቀት,ባህል, ቋንቋ ታሪክና እምነት ሰንደቅ ዓላማዋን ዳር ድንብሯን የሚጠብቅ መሪ እንጂ መሰሪ እንዳይገጥማት ምክርዎን ቢለግሱ
    አይሻልም? በቸር ይግጠመን መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁልን::ከምስጋና ጋር!(ከካናዳ)

    ጥንታዊ ያልተደፈረች ኢትዮጵያ ሰንድ

  15. በለው!
    December 26th, 2009 at 14:46 | #15

    መሪ ከሰማይ አይወርድ :
    ቡጊዳዎች አንድ በሉኝ::
    በማሪኛ ስ’ጽፍ እምጽፈው ነገር አይታይም::ብሳሳት ወይንም የጻፍሁትን ለመለወጥ ብፈልግ አልችልም::ምክንያቱም ታይፕ ሳደርግ እማየው የሆኑ ብሎኮችን ብቻ ነው::የመጣ ይምጣ ብዬ አስተያየተእን ስልክ ነው ምን እንደጻፍሁ እምረዳውና መፍትኼውን ንገሩኝ::
    ወይንም አስተያየታችንን ለማረም የሚያስችለን ዘደእ ፍጠሩልን እንደናዝረእትዶትኮም!

    ችግሩ ከድሕረ ገጹ አዘጋጅ አልመሰለኝም
    የግዕዝ ፊደሎች የመጻፊያዎ(keyboard layout/IME is set to “US”or “Geez Unicode”
    START>>>>SETTING>>>>>>CONTROL PANEL>>>>>>KEYBOARD
    you can also view or change the language setting of your keyboard by
    right clicking on the Geez icons (at any status) and selecting
    (left clicking) keyman configuration and selecting the language tab.
    ይህንን መጀመሪያ Microsoft word ላይ ይሞክሩት በስህተት ኪቦርድዎን ዘግተውታል::
    ወይም በኮፒተርዎ ሰዓት መቁጠሪያ አጠገብ ኪቦርድ ምልክት ካለ ተጭነው ፎንቱን ያረጋግጡ
    ከረዳዎ መልካም ፅሑፍ ያቅርቡልን መልካም ገና እመኝልዎታልሁ ሌላ ስጦታ አላዘጋጀሁም!

  16. zina
    December 26th, 2009 at 16:01 | #16

    አቶ በለስ ምነው የበላወን ባታክ እክካም ነህ ብለህ ብለህ ልደቱን ክብርቱካን ጋር ማነጻጸር ጀመርክ ለነገሩ ከናንተ ክዝህ ሌላ ምን ይጠበቃል ግብስብስ ነህ!ክልደቱ ጋር ገደል ግባ የምትረባ ባንዳ መቸ እንደምትማሩ አይገባኝም ይህንን ደካማ አስተሳሰብን ለመቀየር ልትተጋ ይገብሃል!!

  17. በለስ
    December 26th, 2009 at 22:33 | #17

    @ASHENAFI
    በቅድሚያ ይሰጠሁት አስተያየት ዋቢ ያደረገው ጽሑፉ በሰጣቸው መስፈርቶች ላይ ነው:: የልደቱን አስተዋጽዖ በተጨባጭ ማሳየት ይቻላል:: በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዋር ያመጣው ለውጥ ከፍተኛ ነው:: ይህንን ስል ሌሎች ጥረት አላደረጉም ማለቴ አይደለም:: ለምሳሌ ፕሮፌሰር መስፍን ልደቱ ያራመደውን ፖለቲካ በማካሄድ ብዙ ዓመታትን አሳልፈዋል:: እንዲያውም ፋና ወጊ ናቸው ማለትም ይቻላል:: ነገርግን በተጨባጭ ያሳዩት ውጤት በጣም ትንሽ ነው:: ይህ እንግዲህ ከላይ ጸሓፊው ከጠቀሰው የመሪዎች ተፈጥሮዋዊ ባህሪ የመነጨ ሊሆን ይችላል:: ይህ ተፈጥሮዋዊ ባህሪ አብረው የሚወለዱት እንጂ በትምህርት የሚያገኙት አይደለም::
    ልደቱን የሚያክል መሪ ሊፈጥር አይችልም የሚል አልወጣኝም:: የሚበልጥ መሪ እንደሚመጣ ምንም ጥርጥር የለኝም:: እሱ ራሱ ካሁን ቀደም ካስመዘገበው ውጤት የበለጠ ያስመዘግብ ይሆናል:: ይህ ካልሆነማ አገሪቱ ባለችበት ትቀራለች ማለት ነው:: ይህንን ደግሞ አላምንበትም:: የልደቱ ቀዳሚ ቦታ መያዝን ያሳረፍኩት እስካሁን በተሰሩት ስራዎችና በተገኙ ውጤቶች ላይ ነው:: ንግግርማ ሁሉም ይናገራል: ዋናው ውጤቱ ነው::
    የልደቱን አቋም ከመጀመሪያ ጀምሮ ከላይ ከጠቀስኩት ውጭ ለመገመትም ሁነ የወያኔ ተወካይ እንደሆነ እስከ ዛሬ ድረስ ያየሁት መረጃ ስለሌለ የርስዎን ሃሳብ መጋራት ያስቸግረኛል:: የስራውን ውጤት ግን ባይኔ በብሌኑ አይቻለሁ:: ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት ሲታሰር, ሲደበደብ, በሽተኛ ሲሆን ግን አይቻለሁ:: ለህሊናችንና ለማተባችን መመስከር ያለብን ያየነውን ነው:: እርስዎ ያዩትን ከሆነ የሚናገሩት መቼም ተቃውሞ የለኝም:: ያላዩትን በወሬ በወሬ ከሆነ ወቀሳው የህሊናዎት ነው:: ዋናው ነገር ግን ሰው ያየውን ነገር ከህሊናው ጋር ተማክሮ ለመናገር መብት ማግኘቱ ላይ ነው::
    ልድቱ ስህተት የሰራባቸው ጊዜያቶች እንዳሉ የማምንበት ነው:: ለምሳሌ የቅርብ ጊዜውን ለዶር ያዕቆብ የሰጠውን መልስ ብንመለከት ከነዚህ ከሚሰራቸው ስህተቶች አንዱ ነው ብዬ አምናለሁ:: ዶር ያዕቆብ ይቅርታ በመጠየቅ ልደቱ በከፊልም ቢሆን በሃስት የጠፋ ስሙን አጽድተውለት ነበር:: ለዚህ ትልቅ ድርጊት አምስግኖ በማለፍ ፋንታ በማይረባ እንኪያ ሰላንቲያ ጽሑፍ ያንን አርዓያነት ያለው የዶር ያዕቆብን ድርጊት አረከሰው:: እንግዲህ ኋላ ዶር ያዕቆብ የጻፉትን ጽሁፍ ከተመለከትን ውጤቱ ምን እንደሚሆን ማወቅ ይቻላል:: እሳቸው አንድ ደረጃ ከፍ ሲሉ እሳቸውን ተከትሎ አንድ ደረጃ ክፍ ማለት ሲገባው ጉዳዩን ዝቅ አደረገው:: በሚቀጥለው ጽሑፋቸው እሳቸው ደግሞ ከሱ ዝቅ አድርገውት አረፉት:: እንግዲህ የሄ ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አንዱ የሰራውን ሰራ አንዱ ለማፍረስ እየሞከረ እዚህ ደረጃ የደረስነው::
    ልደቱ የሰራውን ሰራ መካድና እንዳልነበር ማድረግ ምናልባት ልደቱን ሊጎዳ ይችላል:: ከልደቱ በላይ ግን በረሃብና በጥማት የሚሰቃየውን የኢትዮጵያን ህዝብ ሰቆቃ ያራዝማል::
    መሻሻልም እድገትም የሚገኘው ሰው የስራውን ሲያገኝ ነው:: የሰራ ሰው የላቡን ከተቀማ ለውጥም እድገትም አይመጣም:: ከሰራተኛ ይልቅ ሌባና ቀጥፊ ሃይልና ስልጣን ይኖራቸዋል::

  18. በለስ
    December 26th, 2009 at 22:46 | #18

    ኣቶ አሸናፊ
    አንድ ነገር መጨመር ፈለግሁኝ:: አንድን መሪ መሪ ከሚያደርጉት መስፈርቶች አንዱ ራሱን አላስፈላጊ ካልሆነ መስዋዕትነት መጠበቁ ጭምር ነው:: ይህ ማለት የራሱን ነፍስ ማዳን ዋናው ተግባሩ መሆን አለበት ማለት አይደለም:: ለዓላማው ቅድሚያ መሰጠት ያለበት:: ነገር ግን እሱ መስዋዕት ከሆነ በኋላ ዓላማው ግብ ሳይደርስ የሚቀር ከሆነ ይህ ሰው ጥሩ መሪ አልነበረም ማለት ነው:: በሌላ በኩል የሱ መስዋዕነት ለዓላማው መሳካት ወሳኝ ከሆነ አይኑን ሳያሽ መስዋዕትነቱን በጸጋ መቀበል ይኖርበታል::

  19. Analyst
    December 27th, 2009 at 11:56 | #19

    -Good leader cares for his flag…. National anthem….
    -Good leader cares for history
    -Good leader takes defeat as learning and good opportunity.
    …….

  20. Anonymous
    December 27th, 2009 at 12:28 | #20

    @zina
    በመጀመሪያ በሰለጠነና በሰከነ መንገድ መናገርን ተማር:: ከዚያ በኋላ ትወያያለህ:: እስከዚያው ድረስ ግን ዝም ባለ አፍ ዝምብ አይገባበትም ይባላልና….

  21. fool
    December 27th, 2009 at 12:53 | #21

    ስለ ብርቱክን ብዙ ሥስፉ አይችሃለሁ. ጊን ሁሉም አዛዝን ሰዎችህ ናችህው በታም ደካማ ንችው. ወያን ተዝህ ያበኩት እኮ እንድ ቢርቱካን ናቸው. ወያን አኪም የለውም ምስግና ለ እነ ቢርቱችን.ምርቻ,ሰላማዊ ትግለ,እያላቹ ወያነ ጊዚ አገነ. አሁኒስ ሚን የከራቹ አለና የሃን ያሀል ቺግረ ለዳረጉን ሚስጋና እባካቹ እንድ ሰው አሲቡ. ካለፈው ተማሩ.

  22. zina
    December 27th, 2009 at 15:24 | #22

    ለ#21; ለሚገባው ሰው አንድ ቃል በቂው ነው ይግባህ ,የሚገባህ ክሆነ እንደአንት አንድን ህሳብ ለመግለጽ ቅኔ መደርድሩ አስፈላጊ ስላልሆነ እሱን ላንተ ትቸዋሉ 18 አመት ሙሉ ከማውራት ተራ አሉባልታ ከመደርደር ውጭ የስሩት ነገር ይኖር ይሁን?የሰክኑ የኛ የወሬ ምሁር ከብዙ ማውራት ቀነስ አርገው ለተግባር እንዲያውሉ አለበልዝያ አይተርተሩ!

  23. እስከ ነጻነት
    December 28th, 2009 at 15:10 | #23

    የሞነጫጨርኳትን ጽሑፍ ላነበባችሁልኝ፣ አስተያየት ለሰጣችሁኝ ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ: የምቀበላቸውን አስተያየቶች ተቀብዬ ያልጣሙኝን ደግሞ እንደ ግል አስታያየታችሁ ቆጥሬ አልፈዋለሁ: ሁላችሁንም ግን ሳላመሰግን አላልፍ:
    አንዳንዶቻችሁ በሰጣችሁኝ አስተያየት ግን ጥቂት ማለት እፈልጋለሁ:

    መሪ ከሰማይ አይወርድም:

    “መገዛት በኢትዮጵያ ብቻ የተከሰተ አይደለም” ያሉት ትክክል ነው: ግን አንድ መዘንጋት የለለበት ነገር ኢትዮጵያ እኮ በአለም መንግስት የሚባል ሳይኖ ስርአተ መንግስትን በመመስረት ቀደምት ሐገር ነበረች፣ እና አሁንም በግፍ በመገዛት ላይ ነች: እኔ የምለው ይህ አልበዛም ወይ ነው::
    ሌላው “መሰሪ” ብለው ያቀረቡት ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ካልሆነ በስተቀር ሁሉንም ያውቁታል: “የህዝቦችን ሚና መዘንጋት የለበትም..:” ህዝብ ከሌለ እኮ አገርም የለም: የኢትዮጵያ ህዝብማ ድርሻውን ተውጥቷል፣ ምረጠን ተባለ መረጠ፣ ሲቪሉ፣ ፖሊሱ፣ ጦር ሠራዊቱ ጭምር መረጠ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ውጣ ተባለ፣ ከባሌ ሮቤ ድረስ ፈረሱን ጭኖ በሶውን ሰንቆ አዲስ አበባ ድረስ መጣ፣ ወያኔ በፖሊሱም ሆነ በጦር ሰራዊቱ ስላልተማመነ ስብእናቸው ተገፎ ወደ አውሬነት በተቀየሩ በትግራይ ተወላጆች ብቻ በተዋቀረ የአጋዚ ጦር አዲስ አበባን ሲያስወርር፣ የቅንጅት መሪ፣ የሐገሪቷ መሪ ይሆናሉ ተብለው የተመረጡት ግን ለፖሊስ ሰራዊትም ይሁን ለጦር ሰራዊቱ ያደረጉት ጥሪ አልነበርም: ብዙ ማለት ይቻል ነበር ግን….::

    ታሪክ: shagi,
    በመሰረተ ሐሳቡ እስማማለሁ: ነገር ግን በአሁኑ ሰአት ሌላ አይታየኝም ነው: ወደፊት ሌሎች መሪዎች አይፈጠሩም፣ ማለቴ እንዳልሆነ እንዲረዱልኝ እፈልጋለሁ:

    አቶ በለስ:
    በርሶ አስተያየት መሪ መሆን ያለበት “…” ብለው አስቀምጠውታል: ያ የኔ እምነት አይደለም: መሪ ከየትም ለወጣ ይችላል: ከገበሬው፣ ከወጣቱ፣ ከተማሪው ከየትም: ስለዚህ መሪ ሁሌም ከፖለቲካ ድርጅት ብቻ ነው የሚወጣው የሚል እምነትም እይታም የለኝም:

    አቶ በለው
    “……. ጥሩ አንባቢ ጥሩ ፀሐፊ ሲገጥመው…” ሲሉ አንብቦ የመረዳት ችሎታየን ዝቅተኝነትና የብእሬን ዱልዱምነት ነግረውኛል: እኔም የተባሁ ብእረኛ ነኝ ያልኩ አይመስለኝም ለሐገሬ ለወገኔ ይጠቅማል፣ እኔ የወቅሁትን ሌላው ወገኔ ይወቀው ብዪ የማምንበትን በዚሁ ጎልዳፋ ብእሬ መሞንጨሬን ግን አላቆምም::
    ወደ አስተያየቶቹ ስገባ እርሶ ከምን ተነስተው ጽሑፌን ከኢህአድግ ጋር እንዳቆራኙት አልገባኝም፣ ራእዩንም የማፍረስ፣ የማጥፋት እያሉ እንዴት እንደተነተኑት አልገባኝም: ምናልባት ዱልዱም ብእሬ ስላልጣሞት አላነበቡት ይሆናል እንጂ እኔ የትክክለኛ መሪን ራዕይ ያስቀመጥኩት እንደዚህ ነው

    “ትክክለኛ መሪ ልክ ሰዓሊ የሚስለውን ስዕል ሸራው ላይ ከማሳረፉ በፊት በአእምሮው ያለቀ፣ የተጠናቀቀ ቅርጽ እንደሚታየው ሁሉ መረም በአእምሮው ተቀርጾ የሚታየው የተሻለች አገር፣ የኑሮ ደረጃው ከፍ ያለ ህዝብ፣ ከበሽታ፣ ከጉስቁልና፣ ከመሃይምነት የተላቀቀ ህዝብ፣ ህጻናት በፍራቻ ሳይሆን በደስታ የሚቧርቁባት ሐገር የፍርድ ስርአቱ የተስተካከለባት፣ የህዝቦች መብት ጥያቄ ውስጥ የማይገባባት፣ ህዝቧ ዛሬን ምን ልብላ ሳይሆን ለተተኪ ትውልድ ምን አፍርቼ ልለፍ የሚልባት ሐገር ሰው በዘሩ፣ በቋንቋው፣ በኃይማኖቱ፣ በቆዳው ቀለም ሳይሆን በሰብአዊ ፍጡርነቱ ብቻ የሚከበርባት፣ በአለም አቀፍ መድረክ የችግር፣ የረሃብ፣ የቸነፈር፣ የበሽታ፣ የድንቁርና ተምሳሌት ሳይሆን የእድገት፣ የብልጽግና፣ የባለታሪክነት፣ የተስተካከለ አመራር ተምሳሌት የምትሆን አገር ምስል ነው:” ከላይ ይመልከቱት

    ሁሉን አስተያየቶን በዚህ መሪ ላይ ተመስርተው ቢያስረዱኝ ባለውለታዬ ይሆናሉ:

    በተረፈ ሁላችሁም ለሰጣችሁኝ አስተያየት በድጋሚ አመሰግናለሁ

    እስከ ነጻነት

    እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

  24. መሪ ከሰማይ አይወርድም::ከመሀላችን እንፍጠርው…
    December 29th, 2009 at 02:15 | #24

    እስከ ነጻነት
    በቅድሚያ ላመሰግኖት እወዳለሁ::እርስዎ ከጥቂት ጽሁፍ አቅራቢዎች መካከል አንዱ ነዎት የቀረበበትን አስተያየት የሰጡት::ይህ ደስ ይላልል::
    እኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰቆቃው ሳይሰማኝ ቀርቶ አይደለም ያንን ያልሁት:: እርስዎ ግን አሁንም ስለቅንጅት መፍረስ የመሪዎችን ድክመት ነው ያሳዩት:: ቅንጅት አንድ ወጥ ድርጅት አለመሆኑን እያወቁ ስለመሪ ሚና ያንን ያህል ማጋነንዎ አሁንም አልገባኝም:: ለቅንጅት መፍረስ ማንን መጠየቅ ወይንም መመርመር እንዳለብን አልገባኝም::ወደ ኋላ ተመልሰን ታሪኩን መመርመር ግድ ሊለን ነው:: የሚገርመው አሁም ትምህርት አለማግኘታችን ነው:: አዎን ስላልለፈው በቅጡ አላወቅምና! እንዴት ትምህርት እንቀስማለን?ከምንስ ነው ትምህርት የንቀስመው?
    ቀጥሎ ባስቀመጥሁት ይርስዎ አስተያየት ላይ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል:: ይህ የትይፒን ስልት ችግር ስለፈጠረብኝና አንድ ነገር ብቻ ለማለት እፈልጋለሁ::ሕዝብ ና ውጣ ይህንን አድርግ! ሲባል ብቻ የሚወጣ አይደለም::ሀሳቡን ራሱም አፍላዊና አስፈጻሚ ሲኖን ነው መሪውም መሪነቱ የሚሰራው:: ሕዝባችን የመሪነቱን ሚና ነስተነዋል ወይንም ተነፍጓል::እርስዎ የሚዘነጉት ይህንን ነው::መሪዎች ህዝብ በሙሉ ልቡ ከጎኑ መሆኑን ማመና ማወቅ አለባቸው::…ጠንካራ ሕዝብ ጥንካራ መሪ ብቻ ሳይሆን መሪዎች ይኖሩታል::የሕዝቡን ልብ የሰረቀው ኃይል ላይ ነው መረባረብ;…
    “…የኢትዮጵያ ህዝብማ ድርሻውን ተውጥቷል፣ ምረጠን ተባለ መረጠ፣ ሲቪሉ፣ ፖሊሱ፣ ጦር ሠራዊቱ ጭምር መረጠ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ውጣ ተባለ፣ ከባሌ ሮቤ ድረስ ፈረሱን ጭኖ በሶውን ሰንቆ አዲስ አበባ ድረስ መጣ፣ ወያኔ በፖሊሱም ሆነ በጦር ሰራዊቱ ስላልተማመነ ስብእናቸው ተገፎ ወደ አውሬነት በተቀየሩ በትግራይ ተወላጆች ብቻ በተዋቀረ የአጋዚ ጦር አዲስ አበባን ሲያስወርር፣ የቅንጅት መሪ፣ የሐገሪቷ መሪ ይሆናሉ ተብለው የተመረጡት ግን ለፖሊስ ሰራዊትም ይሁን ለጦር ሰራዊቱ ያደረጉት ጥሪ አልነበርም: ብዙ ማለት ይቻል ነበር ግን….::”

  25. መሪ ከሰማይ አይወርድም::ከመሀላችን እንፍጠርው…
    December 29th, 2009 at 02:26 | #25

    እስከ ነጻነት
    ይህ ከዚህ በታች ያስቀመጥሁት የርስዎ መረጃ በዉነት ስለመፈጸሙ መረጃ ካለ የቅንጅት መሪዎች ሊመሰገኑና በታሪክም ሊመዘገቡ ይገባል:: ጦር ሠራዊቱ የማን ሆነና ነው ይህንን የሚሉት? ጶሊሱስ? እኔን አስተያየት እንድጭር ያደረገኝ የርስዎ አካሀእድ ወይንም ነገሮችን በስፋት አለመመልከትና በማስረጃ አለማስደገፍ ነው::አንዳንዶቹ እንደሚሉት ሕዝቡ ለሰልፍ በያቅጣጫው ቢወጣ ያልቅ የነበርን ሰውና የንብረት ውድመት ያገናዘቡ አይመስሉኝም:: ከርስዎ አስተያየት መገመት ካልተቻለ ወይ እኔ የጻፉትን አልተረዳሁም ወይንም ሌላ ምክንያት ጋርዶናል መሰለኝ:: …የጫርሁት ስለማይታይና ወደኅውላ ሄጀእ ለማረም ስለማልችል እዚሁ ላብቃ መሰለኝ::
    “…ወያኔ በፖሊሱም ሆነ በጦር ሰራዊቱ ስላልተማመነ ስብእናቸው ተገፎ ወደ አውሬነት በተቀየሩ በትግራይ ተወላጆች ብቻ በተዋቀረ የአጋዚ ጦር አዲስ አበባን ሲያስወርር፣ የቅንጅት መሪ፣ የሐገሪቷ መሪ ይሆናሉ ተብለው የተመረጡት ግን ለፖሊስ ሰራዊትም ይሁን ለጦር ሰራዊቱ ያደረጉት ጥሪ አልነበርም: ብዙ ማለት ይቻል ነበር ግን….::”

  26. መሪ ከሰማይ አይወርድም::ከመሀላችን እንፍጠርው…
    December 29th, 2009 at 02:53 | #26

    ስለትብብርዎ በጣም አመሰግናለሁ::
    ችግሩ ግን አሁንም አልተፈታም:: ቀደም ሲል ይሠራ ነበር::ኢንተርነእት እክስፕሎረር8ን መጠቀም ስጀምር ነው ችግሩ የተከሰተው:: አቡዎች!አላችሁ እንዴ? እንዲህ ስላሉ ጉዳዮች የምታውቁት ነገር አለዎይ?
    እኔ ድህረ-ገጻችሁን መጠቀም ባቆም ምንም እንደማልጎዳ አውቃለሁ::ዝምታችሁ ግን ያስፈራል::ባህላችን መፍትሀእ መፈለጋለመሆኑን እገነዘባልሁ;;

    በለው! :

    መሪ ከሰማይ አይወርድ :ቡጊዳዎች አንድ በሉኝ::በማሪኛ ስ’ጽፍ እምጽፈው ነገር አይታይም::ብሳሳት ወይንም የጻፍሁትን ለመለወጥ ብፈልግ አልችልም::ምክንያቱም ታይፕ ሳደርግ እማየው የሆኑ ብሎኮችን ብቻ ነው::የመጣ ይምጣ ብዬ አስተያየተእን ስልክ ነው ምን እንደጻፍሁ እምረዳውና መፍትኼውን ንገሩኝ::ወይንም አስተያየታችንን ለማረም የሚያስችለን ዘደእ ፍጠሩልን እንደናዝረእትዶትኮም!

    ችግሩ ከድሕረ ገጹ አዘጋጅ አልመሰለኝምየግዕዝ ፊደሎች የመጻፊያዎ(keyboard layout/IME is set to “US”or “Geez Unicode”START>>>>SETTING>>>>>>CONTROL PANEL>>>>>>KEYBOARDyou can also view or change the language setting of your keyboard byright clicking on the Geez icons (at any status) and selecting(left clicking) keyman configuration and selecting the language tab.ይህንን መጀመሪያ Microsoft word ላይ ይሞክሩት በስህተት ኪቦርድዎን ዘግተውታል::ወይም በኮፒተርዎ ሰዓት መቁጠሪያ አጠገብ ኪቦርድ ምልክት ካለ ተጭነው ፎንቱን ያረጋግጡከረዳዎ መልካም ፅሑፍ ያቅርቡልን መልካም ገና እመኝልዎታልሁ ሌላ ስጦታ አላዘጋጀሁም!

  27. እስከ ነጻነት
    December 29th, 2009 at 20:51 | #27

    መሪ ከሰማይ አይወርድም፡
    ይህንን የታይፒንግ ችግር ለማቃለል እኔ የምጠቀመው MSword ላይ ከጻፍኩ በኋላ copy and paste እጠቀማለሁ
    እስኪ ይህንን ይሞክሩት

  28. መሪ ከሰማይ …..
    December 30th, 2009 at 22:50 | #28

    አመሰግናለሁ:: የሚገርመው ለብዙ ጊዘእ እዚሁ ላይ ስጠቀም ቆይቸእ አሁን አልሠራም ያለበትን ምክንያት ለማወቅ አለመቻለእ ነው::
    @እስከ ነጻነት

  29. Analyst
    December 31st, 2009 at 14:45 | #29

    ዋናው መፊቲሀው ሆዳም አለመሆን ነው !ለአሚሮ መኖር !

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።