አልቆርጥ አለ አንጀቴ - የምስራች ከአቡጊዳ
ጎኔ አላንቀላፋ
በቅሎ ስላላየሁ የዘራሁት ተስፋ
ስላልተመለስ ጥያቄየ የኔ
ወይ ፍንክች አጅሬ
ተስፋ አልቆርጥም እኔ ::
አውቃለው ሁሉንም
ለልጄም አንድ እናት
ለናቴም አንድ እኔ
ሁለቱም አይተኩኝ አያገኙም ሌላ
እነሱም አይችሉት ጸብ ከመጣ በኔ
ይግረማቸው እንጂ የራሴው ጭካኔ
በንባ እያጠብኩአቸው በልጦብኝ ወገኔ::
ይህም ብቻ አደለም ብዙ አይቱአል ይህ አይኔ
ፍትህ እስኪወለድ እምባ አርግዞ ሆዴ
ፀንቼ እጉአዛለሁ አያልቅም መንገዴ
ነፃ እስክንወጣ ካለንበት እስር
ምን አል ባይጠጣ ምን አል ባይጨፈር
ያሰብነው ተሳክቶ በደስታ እስክንሰክር::
እስኪ ልንገራችሁ አለኝ አንድ ሚስጥር
በታንክ ተከቦ ታጅቦ በወታደር
ለሊት ዘብ ተቁሞ ሲጠበቅ ዳር ድንበር
ግንቡና መሬቱ በሽጉጥ ሲታጠር
ፍራቻ አስጨንቆ እንቅልፍ ሲያሳጣ
የሰሩት ግፍ በቀል በህልም እየመጣ
ሲባንኑ ማደር በቅዥት ፈጣጣ
እሱ ነው እስር ቤት
ኡ ኡ ታ ለቅሶ የበዛበት ጣጣ::
እኔ ግን ነጻ ነኝ
ልክ እንደ ጲላጦስ
እጄን የታጠብኩኝ
ግን ፍትህ የጠማኝ የተንገበገብኩኝ
እውነቱን ልናገር እነሱም አልተዉኝ
እኔም አልተዋቸው
ነጻነት ሳይቀምሱ ከስር ሳልፈታቸው ::
የምስራች ከአቡጊዳ



የምስራች እናመሰግናለን
እንኳንም ይህንን ድምጽሽን ለመስማት አበቃን
አዎን እነሱም ከተከኔቸሩብት ዪፈቱ:: እኛም አንተዋቸው
እንደሻማ ቀልጣ የምታበራዋ የነጻነት ሻማችን ….
እኔም አልተዋቸው
ነጻነት ሳይቀምሱ ከስር ሳልፈታቸው ::
የምስራች ጥሩ ብለሻል በግጥሙ; ብስለት የተሞላበት እውነት ነው የተናገሽው:: ባጣም እናመሰግናለን;;