አልነጋም- ገና ነው! - ዳግማዊ ዳዊት

January 19th, 2010 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

የሰማይ ኮርኔሥ ሆኖ- ማቅ የመሰለ ደመና
ከታችም አውሎ ነፋስ- ፉጨቱን እያሰማ
አቧራውን አሥነስቶ- ዛፍ ቅርንጫፉን እያሾረ
ዛሩ እንደወረደ ባለአውሌ- አለመጠን እያስጨፈረ
አይን ቢወጉ በማያሳይ- ጥቅጥቅ ባለ ጨላማ
ወዴት ነው መድረሻችን- ጉዟችን የሚያቀና?

ትናንት እንዳስቆመን ዝናብ- ሊዘንብ ሰማዩ አግቶ
ወዴት ነው የምንሄደው- በትናንቱ ምን ታይቶ?

ትርምስምሳችን ወጥቶ- ጨቅይቶ ሳለ መንገዱ
ለይምሰል አይሆንምወይ -ደግመን ዛሬ መሄዱ?

ትናንት መካሪ ጠፍቶ- ሌሊቱ ገና እናዳልነጋ
ጉዞው መርዛም-እሾክ በዝቶበት- ስንቱ ነው የተወጋ?

እኔስ አልምክርውም- የዛሬውን መንገድ
እስኪነጋ እቆያለሁ- ካልሆነብኝ የግድ
አልነጋም ገና- ጨለማ ነው ሌሊት
እነሱንም ንገሩዋቸው- መጓዙን ይተውት
ተከታያቸውን በመሉ- የአውሬ ቀለብ አያርጉት።

ዳግማዊ ዳዊት
Ethio_dagmawi@yahoo.com
ጥር 2002 ዓ.ም.

  1. ሞገስ አመስ
    February 1st, 2010 at 11:57 | #1

    ዳግማዊ አድናክሃለሁ

  2. ሞገስ አመስ
    February 1st, 2010 at 11:59 | #2

    ዳግማዊ አድናክሃለሁ አዳማ ዩንቭርሲቲ

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።