ቃሌ - ብርቱካን ሚደቅሣ

December 27th, 2008 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

«ቃሌ»- ከወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ /December 27, 2008

ታህሳስ 14 ቀን 2001 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ጽ/ቤት ተገኝቼ ማስጠንቀቂያ ሲነገረኝ እና ያዉ መልእክት በኢትዮጵያ ቴለቭዥን ሲተላለፍ ስመለከት ያደረብኝን ስሜት ለመግለጽ ያዳግተኛል።

ምንም እንኳን ይህን ሁኔታ ለመለወጥ፣ ከማዉቀዉና ከማምነዉ ነገር ዉጭ የምናገረዉ ነገር ባይኖርም ጉዳዩ በሕዝብ ዘንድ ጥያቄዎችን ማጫሩ አልቅረምና በጉዳዩ ላይ ግንዛቤን ለመፍጠር ይቺን ጽሁፍ ለመጻፍ ወስኛለሁ። ምን አልባትም የመጨረሻ ቃሌ ይሆናል።

በሽምግልናዉ ልጀመር። የሽምግልናዉ መሰረታዊ መንፈስ፣ ሁለቱንም የሚያግባባ ስምምነት አምጥቶ እና የእርቅን መንፈስ ፈጥሮ የፖለቲካ ሂደቱን ማስቀጠል ነበር። ይህም በመሆኑ ነዉ ሂደቱ በርካታ ወራትን ሊወስድ የቻለዉ። በዚህም ዉስጥ ምርጫ 1997 ዓ.ም ተከትሎ የተፈጠረዉን ችግር በተመለከተ፣ የአገር ሽማግሌዎች «አንዱን አጥፊ አንዱን ንጹህ በማድረግ ሳይሆን እያንዳንዱ ወገን በወቅቱ ለተፈጠረዉ ችግር ህዝቡን ይቅርታ ጠይቆና እርስ በርሱም ተጠያይቆ በመሰረታዊ ጉዳዮችም ያለዉን የፖለቲካዊ አመለካከት ቁርጠኝነትን አረጋግጦ ፣በእርቅ መንፈስ ወደፊት በጋራ ለመቀጠል» በሚል አላማ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸዉ ያሏቸዉን ነጥቦች፣ ለሁለቱም ወገኖች ሲያቀርቡ ሃሳባችንን ሲያለዋዉጡና በተቻለም መጠን ለማለዘብም ሲሞክሩ ቆይተዋል።

ከዚህም የተነሳ በመንግስት ፈቃደኝነት ብቻ ሳይሆን በእኛም ተሳትፎም ጭምር፣ በሀገር ስማግሌዎች ሲደረግ የነበረዉ ሽምግልና ሁለቱም ወገኖች ሰጥተዉና ተቀብለዉ የሚያመጡት ማስማሚያ ሃሳብ /Negotiated Deal/ በመድረስ ላይ ያተኮረ ነበር።

በሂደቱ መንግስትም ለሕገ መንጋሳትዊ ስርዓት ያለዉን ታምኝነት እንደገና እንደሚያረጋገጥ፣ እና በ1997 ዓ.ም ምርጫ ጋር በተያያዘ በተፈጠረዉ ችግር ጉዳት የደረሰባቸዉ ዜጎችን እና ቤተሰቦችን ለመካስ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ዉይይቱ እየቀጠለ ዜጎችን እና ቤተሰቦችን ለመካስ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም፣ ዉይይቱ እየቀጠለ ሊሄድና የፍርድ ቤቱ ክርክር ወደ ብይን በሚቃረብበት ወቅት በሽማግሌዎች አስተባባሪ አማካይነት አንድ አሳዛኝ ሁኔታ ተነገረን።

ይኸዉም ሌላኛዉ ወገን፣ እኛ ታሳሪዎች ከሕዝብ እና ከመንግስት ይቅርታ ከምንጠይቅበት ነጥብ ዉጭ በተለይም መንግስትን የሚመለከቱ የወጡት ነጥቦች ላይ መስማማት አይፈልግም የሚል ነበር። ይሁን እንጂ በዚህም ደረጃ የዉይይቱ አቅጣጫ የተመሰረተበት የእርቅ መንፈስ አልተቀየረም ነበር። ስለሆነም ሽማግሌዎቹ ሌሎች የመግባቢያ ሐሳቦችን ወደኋላ የተተወ ቢሆንም በአገራችን ባህል ይቅር በመባባል መንፈስ የተቃኘዉን ያንን ሰነድ ብንፈርም ጉዳዩ ባለበት ደረጃ እንደሚቆም ፋይሉም እንደሚዘጋ ገልጠዉ ሽምግልናዉን ገፉበት። ቃል በቃል በመግልጽም ጠቅላይ ሚኒስትሩ « ይህ ሰነድ ከተፈረመ የሥራ አስፈጻሚ ስልጣኔን ተጠቅሜ ክሱ እንዲቋረጥ አደርጋለሁ» እንዳሉ አረጋገጡልን።

ከዚህ ጋር በተያያዘም « በአገሪቷ ዉስጥ ከቅንጅት ጉዳይ ጋር በተያያዘ የታሰሩ እስረኞች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚፈቱ በመንግስት እና በቀድሞዉ ቅንጅት መሪዎች መሃከልም የፖለቲካ ዉይይት በቀጥታ እንደሚጀመር የፓርቲዉ መሪዎች ያለ ምንም ገደብ የፓርቲዉን ሥራ እንደሚቀጥሉ» ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር።

በተጨማሪም ይህ ሰነድ በማንኛዉም መንገድ ለምንም አይነት የፖሮፖጋንዳ ጥቅም ለሁለቱም ወገኖች ጥቅም በሁለቱም ወገኖች እንደማይዉልና ሰነዱም የሚፈረመዉ ለሽማግሌዎች እንደሆነ፣ ሽማግሌዎችም በዚያ ላይ ተመስርተዉ የራሳቸዉን ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚጽፉ በሽማግሌዎች የተረጋገጠ መሆኑ ታሳቢ ሆኖ ሰነዱ ተፈረሟል።

በርግጥም በዚህ ሰነድ ላይ እኔም እንደ አንድ ታሳሪ መፈረሜን ክጄ አላዉቅም። በሽማግሌቹም የእርቅ መግባቢያ መንፈስ መሰረት፣ በፖለቲካ የተቀሰቀሰዉን ክስ ፖለቲካዊ እልባት ለመስጠት በማሰብ ለእርቅ ስል ከሌሎች የፓርቲዉ መሪዎች ጋር ተስማምቼ ሰኔ 11 ቀን 1999 ዓ.ም በተጻፈዉ ሰነድ በሽማግሌዎች አማካኝነት መንግስትንና ሕዝብን ይቀርታ ጠይቂያለሁ። ይህ ብፈልገም ልለዉጠዉ የማልችለዉ ሀቅ ነዉ።

ከዚህ ስምምነት በኋላ ይጠበቅ የነበረዉ፣ ጠቅላይ ሚኒስቱ ለሽማግሌዎቹ አረጋግጠዉ በሰጡት ቃል መሰረት የክሱ መቋረጠና የፋይሎ መዘጋት ቢሆንም ሂደቱ ሌላ አዲስ መልክ ያዘ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የአቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ክሱን ሳያቋርጥ ቀረ። ይልቁንም ተከሳሳቹ እድሜ ልክ ቅጣታችንን ተቀበልን። ከዚህ በኋላ እንግዲህ ታሪኩ በእኛ ስምምነት ሳይሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈቃድ የተቃኘ ነዉ። ጉዳዩም ብሎ ብሎ የአገሪቱ ፕሬዘዳንት ለታሳሪዎች በሰጡት ይቅርታ እኛ ከእሥር በመፈታታችን ተገባደደ።

እንግዲህ እንዲህ ያለ የተዥጎረጎረ መልክ ያለዉን ዉስብስብ ሂደት በመደበኛዉ የሕግ የይቅርታ አቀራረብ ስነ ስርዓት እንደቀረበም በዛዉም አግባብ እንደተደመደመ ጉዳይ ብቻ ለማየት መሞከር አንድም እራስን ማሞኘት ነዉ፤ ሌላም አለማወቅ።

አንድ ተከሳሽ በሕጉ መሰረት የይቀርታ ጥያቄ ማቅረብ ያለበት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይሆን ለይቅርታ ቦርድ ነዉ። በኛ ጉዳይ ለአገር ሽማግሌዎች የፈረምነዉን ሰነድ ለይቅርታዉ ቦርድ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸዉ። ይቅርታዉንም የጠየቁት እርሳቸዉ ናቸዉ ብሎም መከራከር ይቻላል። ሆኖም ግን በሕጉ አግባብ የይቅርታ ጥያቄ ማረብ የሚችለዉ ባለጉዳዩ ጠበቃዉ ወይም በተዘመድ እንጂ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አይደለም።

ጥያቄዉ መቅረብ የሚችለዉም በጉዳዩ ፍርድ ቤት ፍርዱን እና ቅጣቱን አጠናቅቆ ከወሰነ በኋላ እንደሆነ በሕጉ ተመላክቷል። በእኛ ጉዳይ ከመነሻዉ ጉዳዩን የየቅርታ /Pardon/ የመጨረስ ስምምነት ስላልነበረን ለሽማግሌዎች የተፈረመዉ ሰነድ የተፈረመዉ ፍርድ ቤት በጉዳዩ የቅጣት ዉሳኔ ከመስጠቱ በፊት ነዉ።

ስለዚህ ከዚህ እዉነታ በመነሳት በዚሁ በሕግ በተሰመረ አግባብ የይቀርታ ጥያቄ አላቀረብኩም። ሆኖም ግን በመጨረሻ በፕሬዘዳንቱ ለተሰጠዉ ይቅርታ ጥያቄ መሰረት የሆነዉን የአገር ሽማግሌዎች ለእርቅ ሲሉ አግባብተዉ ሰኔ 15 13 1999 ዓ.ም ያሰፈረሙንን ሰነድ ከነይዘቱ አልካድኩም ብሎ መናገሩ የቱ ላይ ነዉ ስህተቱ የቱ ላይ ነዉ ወንጀሉ ?

በዉጭ አገር በጉዳዩ የተናገርኩትም ይህንኑ የሚገልጽ እና የሚያብራራ እንጂ ሌላ ምንም የተለየ ይዘት አልነበረዉም። ምን አልባት የተናገርኩት አላግባብ ተተረጉሞ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ።

ይህ የእኔ አንጋገር የተዛባ ነዉ ቢባልስ ፖሊስ ጣቦያ በመጥሪያም ያለመጥሪያም ለመመላለስ ያበቃል ? በፍጹም ያስጠይቃል ቢባልስ በአገሪቱ ፕሬዘዳንት የተሰጠን ይቅርታ የሚያስነሳዉ እንዴት ይሆን ? ይቅርታን የሚያስነሳ ቢሆን ፌደራል ፖሊስ በየትኛዉ ሕጋዊ ስልጣኑ ነዉ በጉዳዩ ምርመራ የሚያደርገዉ ? ማስጠንቀቂያስ የሚሰጠዉ ?

ታህሳስ 1 ቀን 2001 ዓም የፌደራል ፖልሲ ኮሚሽነር የወረዳ 12 ፖሊሲ አባላት የሆኑ ሁለት ፖሊሶችን ቤቴ በመላክ ቢሯቸዉ ድረስ እንድመጣ ሲጠሩኝ ስለ ፓርቲያችን ስለአንድነት ለመወያየት ሊሆን ይችላል በሚል በጽ/ቤታቸዉ ተገኝኔ የተጠራሁት ለይቅርታዉ ጋር በተያያዘ መሆኑ ሲነገረኝ መጀመሪያ የጠይኩት ጥያቄ «ፖሊስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ስልጣን አለዉ» የሚል ነበር። ምላሾቹ ግን በመነደቅ ፈገግታ የታጀበ «ይሄ እኮ የአካዳሚ ዉይይት አይደለም፤ እንዲሁ አይነቱ ጥያቄ ብትተይ ይሻላል» የሚል ምላች ነበር የሰጡኝ። ለእነርሱ ያስፈገጋቸዉ ያስገረማቸዉ ጉዳይ ግን እኔን ሁሌም የምኖርለት የምቆምለት እንዳንዴም የምታሰርበት እና የምፈታለት ታላቅ ቁም ነገር ነዉ። የሕግ የበላይነት ወይም ሐግ መንግስታዊነት ።

ሕገ ወጥነትን ማናለብኝነትን መቼም አልለምደዉም፤አልተባበረዉም። ስለዚህ ነዉ ታህሳስ 15 ቀን 2001 ዓ.ም ፖሊሲ ኮሞሽነሩ በድጋሚ ያለ ሕጋዊ መጥሪያ በመልእክተኛ ወደ ቢሯቸዉ ሲጠሩኝ በወቅቱ ሳልሄድ የቀረሁት። በእለቱ ከሰዓት በኋላ የሕግ መጥሪያ በደረሰኝ ጊዜ ወደ ቢሯቸዉ ለመሄድ ደቂቃም አላጠፋሁም። በኮሚሽነሩ ቢሮ ስደርስ የጠበቀኝና መጥሪያዉ የሚገልጸዉ ለየቅል ቢሆንም።

ኮሚሽነሩ በላኩልኝ መጥሪያ ላይ እንደተጠቀሰዉ ጥያቄ ሳይሆን ያቀረቡልኝ መመሪያ ነክ ማስፈራሪያ ነበር። ስዊድን የሰጠሽዉን ቃል በሥስት ቀን ወስጥ ካላስተባበልሽ መንግስት ይቅርታዉን አንስቶ እስር ቤት ይከተልሻል የሚል።

«ይቅርታዉን ማንሳት የሚችሉት እኮ የአገሪቱ ርዕሰ ብሄር እንጂ እርስዎ መንግስት የሚሉት የሥራ አስፈጻሚ አካል አይደለም። ለዛዉም እርሱም ቢሆን ስርዓት አለዉ። የ«ይቀርታ ይነሳ» አቤቱታ ቀርቦ፣ በ20 ቀናት ዉስጥ ለባለጉዳዩ ደርሶ፣ ቦርዱ ካመነበት ጥያቄዉ ለፕሬዘዳንቱ ቀርቦ፣ ያኔ ይቀርታዉ ሊነሳ ይችላል …» እያልኩ ለኮሚሽነሩ ላስረዳቸዉ አስቤ ነበር፤ አላደረኩትም። ንግግራቸዉን መጨረሳቸዉን አረጋግጬ ያለ ምንም ቃል ቢሯቸዉን ጥዬ ወጣሁኝ።

በእኔ እምነት ይሄ ሁሉ ከሕግ የወጣ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰብን ያለዉ ስለ ቃላት ጨዋታ ወይም ስለ ተዛባ እዉነት ወይም ስለተጣሰ ሕግ አይመስለኝም። መልእክቱ ግልጽ ነዉ። ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሰላማዊ ታጋዮች። «በሰላማዊና ሕጋዊ ማእቀፍ ዉስጥ የፖለቲካ ትግል ማድረግ የሚቻለዉ በሕገ መንግስቱ በተሰመረዉ መሥመር ሳይሆን ገዢዉ አካል ወይም ግለሰቦች በፈቀዱት ብቻ ነዉ » የሚል ነዉ። ለዚህም ደግሞ እሺ ወይንም «አዎ» ማለት ለእኔ እጅግ ከባድ ነዉ።

የሽማግሌዎቹ ስም ዝርዝር

1. Prof. Ephraim Isaac,
2. Pastor Daniel Gebre Sellassie,
3. Ambassador Bekele Endeshaw
4. Athlete Haile Gebre Sellassie,
5. Judge Tamiru Wondimagegnehu,
6. Abune Merha Kiristos
7. Aba Kidanemariam Gebray,
8. Dejazmach Zewde Gebre Sellassie,
9. Like Tiguhan Astatke Abate
10. Woizero Tsion Andom,
11. Judge Taddese Gurmu,
12. General Solomon Beyene
13. Engineer Woldeloul Kassa,
14. Ambassador Zewde Otoro,
15. Dr. Haile Wolde Michael
16. Dr. Dawit Zewde,
17. Dr Yacob Bekele,
18. Woizero Rahel Mekuria
19. Fitawrari Amede Lemma,
20. Like Siyuman Dimitros Woldu,
21. Dr. Mussie Hailu
22. Ato Fesseha Asres,
23. Ato Amha Wolde,
24. Dejazmach Woldesemayat Gebrewold
25. Ato Zewge Gedlu,
26. Shiek Arage Mohamed,
27. Prof Jemal Abdulkadir,
28. Ato Mamo Wudineh

ጽሁፉን በፒዲፌ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

  1. lukas
    December 27th, 2008 at 12:04 | #1

    Brilliant.

    Keep the good job our queen.

  2. Yikerbelen
    December 27th, 2008 at 12:33 | #2

    God bless you Birtuyeeeeee. Keep on the good job. weyane is above the law.this arrogants should be punished by any means. ethiopians should stand up. S our fathers and forefathers had punished their band’s fathers, we should punish those bands.

  3. ጎሳየ
    December 27th, 2008 at 12:44 | #3

    አረ ለማን ነወ አቢት የሚባለው!!!!

  4. Andinet
    December 27th, 2008 at 12:47 | #4

    Lets stand together and say together about Birtukan!!! they are going to put her in jail again. What is the silent about!!! You know this dictator will do whatever he wants to do. There is nobody to say him “enough is enough” from the westerns. Lets try to get a solution by ourselves!!!

    Please God keep our country in peace

  5. Anonymous
    December 27th, 2008 at 12:51 | #5

    የአሁኑ ይባስ የሚባል ተረት አለ/
    የብርቱካን ቃል ይሰቀጥጣል. ዕርቁ ጉዳይ /የአንበሳ ልመና ጋማ ጭውብጦ/ እንደሆነ ማንም ያውቀዋል.
    ጀግናዋ ለማብራራት የምትሞክረው የእርቁን ህጋዊ ይዘት ነው. ግን ቕንቕው ዱላና እስራት ከሆነ አካል ጋር ስለ ህግ ማውራት ከነፋስ ጋር እንደ መወያየት ነው. ወገኖች ለወያኔ ጉዳይ ቤየለቱ እንግዶች እየሆንን ማላዘኑ ይብቃን. ምንም የምንከፍልበት ስለሌለ አንድ እንሁን. የእኛ ነገር ለሰሚም እያስቸገረ ነው. ውድ ቡርቱካን ጥናቱን ብርታቱን ይስጥሽ.

  6. Ewnetu
    December 27th, 2008 at 12:51 | #6

    Brothers and Sisters in USA!!! Look our brothers in Ethiopia even do not have the access to get what Birtukan has said. But we have the information and the right to express our opinion. Are we waiting from home something to come?!! We have lost many already by Woyane/EPRDF. Lets speak out on behalf of our brothers and sisters!!!

  7. ክዳነ
    December 27th, 2008 at 12:52 | #7

    ምንዉ የዚች ሃገር መከራዋ በዛ!!!!

  8. Suffa
    December 27th, 2008 at 12:54 | #8

    Everyday detention, Everyday intimidation, harassment, beating, killing!!! When will Ethiopian will be citizens in their own country!!!

    Let stand together. Lets put our minor differences and struggle for the lasting solution!!!

  9. Hagere
    December 27th, 2008 at 13:02 | #9

    This is a very serious issue that requires urgent action from us. When Bertukan - this brave young leader of ours - says “maybe this will be my last word” we have to take it literally to mean we might loose her for good. Because they cannot silence her throug intimidation, the monster Meles may not allow her to utter a word from now on.

    The many agazis that are following all her moves will not refrain from silencing her by ending this young and promising life. Killing is nothing to their master Meles as he has done it throughout his political life. We have to take this situation as there is a real death threat against her. And we should act fast in exposing this. It will serve no purpose to cry after the fact. It is also important that we should remind ourselves about the fact that what we do outside of Ethiopia has a significant influence on what course of action Meles and his gangs will take.

    Meles knows that his days are numbered. If we do our work to expose this monster, for sure he will end up in the international criminal court facing charges for all the crimes against humanity that he orchestrated. So let’s start our work now.

    We should contact our mosques, churches, politicians, the media, NGOs, international organizations,…whoever will listen to us without being discouraged by lack of immediate support to our cause.

    We cannot leave Bertukan and others who are fighting for our freedom to face this inhumane regime alone. Let’s mobilize our resources to free our people.

    Hagere

  10. Ethiopia first
    December 27th, 2008 at 13:16 | #10

    Ato Girma kassa(moziky68)
    have you read what brave leader W/rt Birtukan response for weyane machinary police? this is weyane & for you good answer. shame on you. you need to ask apologize , to benifat for weyane in poloticaly,. are you close for UDJP leaders than G7 leaders? i don’t think so , you have a problkem with G7 because you love to much weyane than UDJP, G7 & AEUP. please don’t waste time no body read your artical. pls, Abugida info, think twice before to post somebody artical hate propaganda.

  11. Ewnetu
    December 27th, 2008 at 14:03 | #11

    Dear Ato Girma, I don’t understand exactly what you want to say but it seems against Birtukan. How can we bring change to this country by division. As we are different, we might have different ideas. But we need recognition to each other. the main point should be freeing Ethiopians from an open jail. We shouln’t argue about peaceful struggle or military is better. We can even make friendship with satan if he can help us to remove this devilish regime. We should understand the moral and physical torture our fellow brothers and sisters are facing. It is not time to argue “my idea is correct and yours is wrong” issue. We should act to free our country.

  12. አርቤክስ
    December 27th, 2008 at 14:05 | #12

    ወገኔ, መሪዬ, እህቴ ብርቱካን;

    አምናለሁ አቅዋምሽ በእዉነት ላይ ነው; ክርክርሽም ህግን መሰረት ያደረገ እንደሆነ አልጠራጠርም. ከቃልሽ መረዳት እንደቻልኩት አቶ መለስ ተራ የመንደር ዱርዬ ተንኮል ሰርተዋል. ይህም መገለጫ ባህርያቸው እንደሆነ ይታወቃል. ሰዉዬ ከደደቢት እስከ አራት ኪሎ በክህደት ቁልቁለት እየተጣደፉ ሃገርን በማፍረስ ተልእኮ እድሜቸዉን አገባደዋል. ስለሆነም ስለ ፍቅር, አንድነት, ሰላም, እርቅ እና ትብብር የሚሰራ ሁሉ በጥላትነት ይፈረጃል. ያንችም ሆነ የቀድሞ ቅንጅት መርዎች እና ደጋፊዎች ወንጀልም ለ ሃገር አንድነት መቆማችሁ ብቻ ነው. ይህን ያልተገነዘበ ኢትዮጵያዊ አለ አልልም (ከ ጥቂት ወደ-አደር አሽከሮች በቀር).

    ስለሆነም በዚች መከረኛ ሃገር እና በነዚህ መከራ ፈጣሪ ጉዶች ዘመን, ህግ መከራከርያ የሚሆነዉ የነሱን ግላዊ ጥቅም እስካልነካ ድረስ ለመሆኑ ካንቺ የበለጠ የተረዳዉ አይኖርም. ከዚህ መሰረታዊ የማሌሊት ባህሪ እና ተልእኮ አንጻር ታድያ የቱንስ ያክል ህግን መሰረት አድርገሽ ብትናገሪ እና ብትንቀሳቀሽ ምን ዋስትና አለሽ? እኔ ስጋቴ, ባንድ በኩል እነዚህ ሰዎች ልባቸዉ በትእቢት ከመጠን በላይ በተወጠረበት, ለህዝቡም ያላቸው ንቀት የትዬለሌ በሆነበት; በሌላ በኩል ደግሞ ፓርትዉ በደንብ ተደራጂቶ ሰፊ ህዝባዊ ድጋፍ በደንብ ባልያዘበት ባሁኑ ሰአት ከነዚህ ተኩላዎች ጋር መጋፈጡ ጉዳቱ አያመዝንም ወይ የሚል ነዉ. እንደኔ እንደኔ የጠየቁትን በመመለስ ከንጃበበው አደጋ ለግዘዉም ቢሆን ማምለጥ ከተቻለ ብታደሪው ትርፉ ላንቺ ብቻ ሳይሆን እንደ ህዝብ ለሁላችንም ነው.

    በተርፈ የነዚህ አገር አጥፊ አዉሬዎች ትንኮሳ እና ማስፈራርያ ሳይበግራችሁ ክቡር እና ፈታኝ የሆነዉን ሃገር የማዳን ስራ ዳር ለማድረስ በትጋት እየሰራችሁ ለምትገኝት ላንቺ እና ለባልደረቦችሽ እጂግ በጣም ታልቅ ክብር አለኝ.

    እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!! የተኩላዎቹንም ጥርስ ያቁልቅ!

  13. December 27th, 2008 at 14:06 | #13

    ብርቱካን ሚደቅሳ መልሷን ሰጥታለች:: እዉነታዉን እንዳለ አስቀምጠዋለች:: በተለይም እነ ዶ/ር ብርሃኑና ሙሉነህ እዮ’ኤል ይህ ብርቱካን የነገረችንን እነርሱ ቀደም ብለዉ ቢነግሩን ኖር ጥሩ ነበር:: እዚህ ስለሆነ ያሉት የሚያስፈራቸዉ ነገር ምንም አልነበረም::

    አሁንም ዝምታቸዉ አጠያያቂ ነዉ ? ብርቱካን እንዳደረገችዉ በግልጽ ያለዉን ሁኔታ የተደረገዉን ነገር እንዳለች ቢነግሩን ጥሩ ነዉ::

    በዚህ አጋጣሚ ዉጭ አገር ያሉ ዝም ብለዉ ብርቱካን እንደዚህ ለእዉነትና ለፍትህ መቆሟ በኔ ዘንድ ትልቅ አክብሮት አስጥቷታል::

    ይህን ብዬ ብዙ በቃ በትግሉ ላይ ወደፊት ማተኮር ያለብን ይመስለኛል:: ከአንድ አመት ተኩል በፊት በሆነ ነገር ጊዚያችንን አናጥፋ:: ወ/ት ብርቱካ ቃሏን ሰጥታለች:: ነገሩ ተደምድሟል:: አሁን ሕዝባዊዉንና ሰላማዊዉን ትግል የምናትየናክርበትን ሁኔታ ላይ መስራት ነዉ የሚጠበቅብን::

  14. Asfaw
    December 27th, 2008 at 14:14 | #14

    WOW, i always thought about her as the person who raised to the occasion, when it matters she is there, our hero!
    i am proud of you, Birtukann M.

  15. ሊሊ
    December 27th, 2008 at 14:56 | #15

    እስቲ ስለ ወያኒና ስለተቀሩት የኢትዩጲያ ሀዝብ አንድ አንድ ነገሮችን እንይ አንድ ለወያኒ አደገኛ የሁነ ፖለትከኛ ሲፈጠር ወይም ማንኛውም የተቃዋሚ ፖለትከኛ አደገኛም ሆነ አድገኛም አልሆነ በወያኒ በኩል ስለዛ ፖለትከኛ ከፍተኛ ጥናት ይካሂዳል ያ ጥናት በህይወት ዘመኑ ሲያካሂዳቸው የነበሩት ነገሮች በጥንቃቂ ይጠናሉ በዝህ ውስጥ ሊያስከስስ ያሚችል ነገሮች ካሉ ተጠንተው ሊያስከስስ እንዲያመች ተደርገው በፋይል ተያይዘው መክሰስ በሚያመች ጊዚ ወይም መክሰስ በሚያስፈልግ ግዚ ልክስ ያቀርቡታል ማለት ነው የሚያስከስስ ነገር ካልተገኘበት ያልሆነ ነገር ወደፊት እንዲሰራ ተደርጎ ይገባል ማለት ነው ለዚህ ምሳሊ ቲዲ አፍሮና መሰሎቾ ናቸው
    እስቲ ስልጣን ላይ ስላሉት እንገምግም ስልጣን ላይ ያሉት ኦሮሞዎችን እንመልከት ምንም እራይ የሊላቸው ያለፈውን ታሪክ እያነሱ በጥላቻ የሚነዱ ምንም ተስፋ የሊላቸው ስለ መብላታቸው ብቻ የሚያስቡ ኢትዮጲያ ስለምትባል ሀገር የማያስቡ ለማንም ያማይሆኑ ለራሱም ለወያኒ የማይጠቅሙ ወያኒም በደንብ የሚያውቃቸው ናቸው::
    ስለ አማራው እንመልከት ስለ አኢትዮጲያ የሚያስቡ ግን ስልጣን ላይ ያወጣቸው ወያኒ ስለሆነ እሱ የሚለውን ብቻ የሚቀበሉ የሚያደርገው ትክክል እንዳልሆነ እያወቁ ለሆዳቸው ሲሉ የተሸነፉ ይህንን ስልጣን ስላገኙ ወያኒን የሚያመሰግኑ ለትንሽ ሁዳቸው ሲሉ ክብራቸውን የሸጡ ከዚህ በላይ ማሰብ የማይችሉ የሚሞቱ የማይመስላቸው ናቸው::

  16. ጀብጀብ
    December 27th, 2008 at 15:16 | #16

    ይገርማል! መለስ ያለ እውቀት በደመ-ነፍስ የሰራው ስራ እውቅዋ የህግ ባለሙያ መልሱን ሰጥተዋለች::መለስና ግልገሎቹ እየሰሩት ያለ ተራ የውንብድና ተግባር ግን አገሪትዋ ምን ያህል በጫካ ወንበዴዎች እስከአሁን እንደምትተራመስ ያሳያል:: መለስ በዚህ እድሜው አጭበርብሮአቸዋል::ለ ጊዜው ህዝቡን ለማጭበርበር ሞክርዋል::እውነቱ ግን ሌላ ነው::እርግጠኛ ነኝ ወያኔ ይህንን መግለጫ ካየ ቆሽቱ የባሰ እንደሚያር:: እነ ብርሃኑ ነጋም ስለተፈረመው ሰነድና :ከእስር አፈታታቸው : እውነተኛውን ነገር የበለጠ ለህዝብ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል::

  17. አዳሙ
    December 27th, 2008 at 15:27 | #17

    እንዳንቺ ያለ አስተዋይ ህግ አዋቂ ቅን አሳቢ ሰው አክባሪ የፖለቲካ ድርጅት መሪን መንካት ህዝብን መድፈርና መናቅ እንጅ ሌላ ሊሆን አይችልም::ነጻ ጋዚጠኞች ለመሆኑ የፖሊስ ኮምሽነሩ ስም ማነዉ? እስኪ ጠይቁት በየትኛው የህግ አግባብ ነዉ የሚመራዉ:: ዋ ያቺ ቀን ስትመጣ ታዝዠ ነው ያሰርኩት የገደልኩት ማለት አያዋጣም::”ፖሊስ” የታጣቂ ብቻ ሳይሆን የሙያ ሥራ ስለሆነ ብታስብበት ይበጅሃል በሉት::

  18. ህይማኖት
    December 27th, 2008 at 15:38 | #18

    ዋው!!!!!! “የተማረ ይግደለን” ትል ነበር እናቲ. ዋው!!!! ብርቱካን የወያኒን ደደብ አጋዚ የህግ የበላይነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ነገረችው. መትረየስ የታተከውን አጋዚ መሳቂያ መሳለቂያ አደረገችው ዋው!!!!!!!! መለስ አሁን ጫት ግዝቶ ህግ ሲያተና ያድራል. እረ ወያኒዎች እራሳችሁን አታስድቡ ማፍሪያዎች

  19. Ewnetu
    December 27th, 2008 at 15:55 | #19

    Dear All,

    I have enjoyed the prompt response with fellow brothers sisters but we need also a concrete action. Atleast we ca go out for peaceful demonstration. Ethiopians at home are not capable of doing anything under the woyane regime. The trauma is still in the people mind. Imgine we are living in others country as a first citizen but Ethiopians at home are living as second citizens. they can not be employed, though qualified, unless be a member of TPLf/EPRDF. You cannot get anything from kebele unless you are in the woyane forums. So we should cry for them!!!

  20. amazing.woyane
    December 27th, 2008 at 15:59 | #20

    I’am proud of the smart leader pm melles zenawi zemenawi. the world knows very well how zenawi is good enough for the ppl of ethiopia but there are still few neftegnas dreaming to rule our country again what shame. pls neftegnas go and wash your dirty car leave ethiopia for real ethiopians we are fed up of your arrogace.
    god bless wodi zenawi axumawi zemenawi. death to the power mongers neftegnas and thier faty ass supporters.

  21. agazi
    December 27th, 2008 at 16:02 | #21

    I am 100% with you my brother amazing woyane. pls keep it up the good worck. god bless woyane.

  22. COMANDO
    December 27th, 2008 at 16:05 | #22

    pls guys can you delet the piuctur of
    teddy azmariw? i don’t like to see him in my comment. thank’s and god bless agazi and it’s strong & smart leaders.
    death to narrow neftegnas and thier puppet supporters.

  23. abel
    December 27th, 2008 at 16:08 | #23

    I am really proud of our future leader. I would say she is a charismatic and knowledgeable leader our country has ever had in history. She will definitely lead us for victory. The renegade and retarded Hailu and his EPRP accomplices, back off please. Let our shining star do her job.

    Long live the unity of ETHIOPIANS
    Death for WOYANES & OPPORTUNISTS

  24. ወንድሙ መኮንን
    December 27th, 2008 at 16:15 | #24

    ወይዘሪት ብርቱካን
    የአንድ ትልቅ ፓርቲ ሊቀመንበር በመሆንዎ: በቆራጥነትዎ ትልቅ ዕምነት ስላለኝ: በአንቱታ ነው አስተያተቴን የምሰጠው::
    ከዚህ በፊት: የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ሲሉ በዚህ ለጋ ዕድሜዎ ከሥራዎ በፈቃድዎ ከመሰነበት አልፈው ለዚሁ ለቆሙለት የሕግ የበላይነት ሲሉ እስከመታሰርና መንገላታት ድርስ መስዋዕትነትን ከፍለዋል:: ከዚህ በፊት ሳገኝዎት እሱ ለማያከበረው ሕግ እስዎ ምን ገድዎት ነው ያሚያከብሩልት ስልዎት: “ሁሉም ሕግ ከጣሰ እንዴት ይሆናል” ነበር ያሉኝ:: አሁንም መስዋዕትነትን ለመክፈል እንደተዘጋጁ አያለሁ:: በዚህ በሕገ አራዊት በመገዛን ገዥ ሥር ምንም ሕግ እንደሌ ከርስዎ በፊት ለታሰሩት ስታገል ገና ከጠዋቱ ተረድቼዋልሁ:: አሁን ግን ልልዎት የምፈልገው: ቀኑ ሲመጣ በቁርጠኝነት ካለሁበት አገር ከኋላዎ ቁም ድምጼ ከማሰማት ወደ ኋላ እንደማልል ብቻ ነው:: እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥዎት:: ለኛ ብለው ሲታሰሩ እኛም ከጎንዎ እንድለን ይወቁልን::

    ወንድሙ ከሎንዶን

  25. አለቃ ብሩ
    December 27th, 2008 at 16:55 | #25

    መጥፎ ነገር ከመጣ በምችለው ሁሉ አቅሜ ብርቱካንን ለመደገፍ ቆርጫለሁ::

    ሁሉም ለእውነት ክብር ይስጥ:: በዚህ ጉዳይ የኢሀዴግ ደጋፊዎች እንኳን ሳይቀር ከብርቱካን ጎን ሊቆሙ ይገባል:: ለዴሞክራሲ ቆመናል የምትሉ ከሆነ የፌደራል ፖሊስ በፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ ሲገባ መፍቀድ የለባችሁም::

  26. Biri
    December 27th, 2008 at 17:08 | #26

    In agreement with brother Wondimu Mekonnen’s comments and the last comment, I hereby declare that this is a principle issue and that we will harass Meles Zenawi and his regime to the grave-they cannot get away with killing off any hopes Ethiopia might have by imprisoning credible leaders such as Judge Birtukan Midekssa.
    We in the UK have a proud track record of standing up for good causes and exposing the mercenary TPLF/EPRDF regime. Birtukan’s is one such a cause!
    Although I never believed that the TPLF regime would allow a peaceful means of participating in the political process, nevertheless, this harassment and possible imprisonment of Birtukan has gone way too far and cannot stand unchallenged.
    We will fight alongside Birtukan. It is a grave misunderstanding if Meles and co. believe that the end of 2008 is the same as the end of 2005!
    They better leave Birtukan alone!!

    Regards
    Biri

  27. Be Ewunetu
    December 27th, 2008 at 17:16 | #27

    የሀገር ፍቅር ለህሊናዋ ዕረፍት የነሳት እህታችን ብርቱካን ስለወገን፣ ስለሀገር፣ ስለ ነፃነት፣ እኩልነት፣ስለፍትህ ብላ ብርቅዬ ህይወትዋን አሁንም ለመስዋትነት ማዘጋጀቷን በዚህች “ቃሌ…” መጣጥፏ ዳግም ቃል ገብታልናለች። እኛስ….? ? ?
    ምን ለማድረግ ወይም በየሴኮንዱ ለሚደዉልብን የህሊና ወቀሳ ምን ዓይነት ምላሽ ለመስጠት ተዘጋጅተናል? ? ?….. የቃሌ -ብርቱካን ሚደቅሳ ተጨማሪ ደወል እና ጥሪ አፋጣኝ መልስ እንድንሰጥ ያስገድደናል። እና … ምላሹን በተግባር ፣ በአፋጣኝ ይለናል የብርቱካን ቃሌ…መልዕክት።
    የኢትዮጵያ አምላክ ብርቅዬ እህታችንን ይጠብቅልን!!! ስለ ሀገሯ እና ወገኗ የምታደርገው ትግል ለፍሬ እንዲበቃ የተቻለንን ሁሉ ለመርዳት ሁላችንንም
    በአንድነት ያነሳሳን።አሜን።

  28. derbabaw
    December 27th, 2008 at 18:59 | #28

    Birtukan’s choice of ‘peaaceful’ struggle is not what woyanes consider as peaceful. Obviously, the only group woyanes consider peaceful is kidetu and beyene who pose no single threat at all and are categorized as legal oppositions. Diplomats are fooled by the mere presence of kidetu as MP from the opposition. Any type of opposition outside of what kidetu is pracising is “non peaceful” as far as woyane is considered. One has to serve woyanes interest as legal opposition or teletafi. It is not in woyanes dictionary that a party as popular as UDJP drawing such a huge crowd at short notice in AA to condemn the actions of the ruling pary would be “peaceful”. That is why woyane continues to harass birtukan and UDJP leaders, members and supporters. Woyane doesnt want UDJP exist as an opposition as they see more of a threat than an opportunity. They would, probably, prefer the Hailu group as they think AEUP is gravely incapacitated.
    Anyways. no matter what woyanes are upto, we must stand firm against dictatorship

    Aluta continua!! The struggle continues - የኢትዮጵያ ህዝብ ያቸንፋል!!!!!!
    UDJP will guarantee us the ultimate victory

  29. gutema
    December 27th, 2008 at 19:47 | #29

    comando agaziw redicules woyane malet chiraq new ke tigray ye wetu chirakch sew bella agazi yesimint amat lij be tiyit ye hamsa amet arogit ye migadil sew aydellem awre inji silezih comanto agerbet hidina ke meles gara yesew siga bila tinish shali yilehal ezih ye diasporan lijoch meblat atchlim ye sow dem inde temah bushti vampire neh

  30. gutema
    December 27th, 2008 at 20:13 | #30

    let me tell u somthing man ihave never seen u giving agood comment about diaspora i think u have avery deep hate for amhara oromo all ethiopian except tigray so be it u are very narrow minded person the way u sond on evrey web site u write the same shit saying god bless agazi and meles u never say god bless ethiopia b/c u are not ethiopian u are slave of shabia u vampire go drink some blood with meles u are very theirsty for human belood chirak hllu

  31. wereb
    December 27th, 2008 at 20:20 | #31

    Birtukan told us the truth and she is ready to face whatever Meles and his government planned to do on her. I am willing to give whatever needed to farther her objective. Now it is our turn to stand beside Birtukan. When we said we stand beside her we have to support her struggle and make sure it is stronger than any other time and should be powerful to force Meles and his friends to respect people power. Our diplomatic and lobbying work has to intensify and should have fast and quick result. We have to save our time and money to support her friends and families. Birtukan you are my perfect example politician.

  32. Tsimona
    December 27th, 2008 at 21:08 | #32

    Dear All,

    I don’t know where to start. The letter is brilliant. Both very brave and politically astute. She doesn’t fail to surprise. Is this the one people? - our Mandela or our version of Barrack Obama? Anyway, just to sound my deepest respect and amazement at the feat she continues to achieve. Simply Brilliant! Now the main thing here is what the government will do next. If they continue as anticipated i.e. to inarcerate her, it will mean either of two things: that they completely look down on the public or that they have low comprehension. I don’t think they have either. I don’t think they are interested in turning this into a major sticking point - it has cost them dearly already. I think they (Meles) will deflect this into some sort of public dialogue or debate and will bide their time before they get back at her for this. But anyway, I am following it keenly and will indeed do what is required of me to stand up to any further arrogance - if it shall befall this remarkable woman (my GOD, I can’t still rub off the awe and admiration!).

    But also, would like to say something to my fellow diaspora: I don’t normally get involved in diaspora politics for a number of reasons: uncoordinated, uninformed, undisciplined, uncommitted and lacking leadership such as Birtukan’s… Take for example the protest against the improsenment of Teddy Afro (my God, another Hero by the way). What was that guy leading the slogans saying? Does he know what he was doing? And the organizers allowing all that trash? You will fail to win many self respecting Ethiopians’ hearts if you do not dissociate from irrational, unfocused, sensational dispays of anger and hatred. Some like myself in the past would actually find themselves wishing that EPRDF remain in power just dreading the possibility of this form of opposition taking power. So, organize rallies, even to preempt any action by the government and I, and I am sure a lot more Ethiopians, will be there. The first mention of slandering and ‘yemender’ slogans, I am out of there and I am sure this will be the case for many others. When we do it, let’s have it as Birtukan would like it orgnized - full of civility and rationality so that it makes impact with our audience i.e. the international community. Let’s not try to be leaders and dominate the dialogue just because we are the ‘diaspora’ and earn more than what our compatriots incountry do. Let’s do things because we know and are commited for the cause and look for direction when we don’t know.

    By the way, I say this with all respect and love!

  33. ራስ
    December 28th, 2008 at 01:57 | #33

    ወያኔን ለመታገል መጀመሪያ ኤትንክ ፌደራልዝምን እንዴት የመንግስት ቁልፍ መሳርያን መዋጋት ይቻላል በማለት ማስተማር. ማንን? አንድ አንድ እንሁን የሚል የማሞን ቂሎን ባልት እናቁም

  34. ፈሪ ለናቱ
    December 28th, 2008 at 03:05 | #34

    አቶ ራስ እባክህን አትበጥብጥ ማውራት የምትፈልገውን ብቻ ብታወራ መልካም ይመስለግኛል:: በብርቱካን ልበ ቆራጥነት እጅግ በጣም ተደንቄአለሁ እሳቱ አጠገብ ሆና በውጭ ለምትኖሩትና መተባበር አቅትዋችሁ እርስ በርስ ለምትናቆሩት የአንድ እናት ልጆች ሆናችሁ እየተባላችሁ ላላችሁ ሁሉ ትልቅ ምሳሌ ናት::አንድነት ሃይል ነው አንድነት በጋራ መስራት ካልተለመደና ባህል ካልሆነ ኢሃዴግ የፈለገውን እንዲያደርግ መፍቀድ ነውና ከሁሉም በፊት እስቲ በውጭ የምትኖሩ ነጻነት ባለበትና በዲሞክራሲ እየኖራችሁ እርስ በርስ እየተሰዳደባችሁና አልስፈላጊ ነገሮችን ከምትነጋገሩ አንድነትንና ፍቅርን እስቲ ለማምጣት ሞክሩ?ያኔ ውጤቱን እናያለን:አሁንም አንድነት ሃይል ነው!!!ልበ ሙሉ ለሆነችው እህቴ ብርቱካን ሚደቅሳ እግሂአብሄር ይጠብቅልን ዘንድ የዘውትር ጸሎቴ ነው በጣም እንዎድሳለን

  35. ሊነጋ ሲል ይጨልማል
    December 28th, 2008 at 05:32 | #35

    ከወያኔ ጋር ስለህግ ፍልስፍና ማውራት ወያኔን እንደመንግስት መቁጠር ነው
    ወያኔ ለመግዛት የሚገለገልበት መሳሪያ
    ጥቅም “ጥቅም ጥልቅ ሀይል ነው .የተፈጥሮ ሳይንስ ያረጋግጠውን ሃቅ እንኾን ያስክዳል”
    ዘረኝነት” በዘር የተያዘ ሃእምሮ ከዘር ውጭያለን እውነት የሚቀበልበት ጥቂት ስፍራ የለውም”
    ህገወጥነት”ህግ ባይኖር ኖሮ ሌብነትን የመሰለ አትራፌ ንግድ በአለም ላይ በአልተገኘ ነበር”
    መለስ ከፈለገ ብርቱካንን ያስራታል .መለስ ብርቱካን ከወንበሩ[ከስልጣኑ] ጋር እንዽ ከህግ ጋር አያነጻጽራትም.

  36. ዘይገርም
    December 28th, 2008 at 09:27 | #36

    ብርቱየ! ወያኔን በማይፈልጉት መንገድ ስለመጣሽባቸው መንገዱን ሁሉ ለመዝጋት የሚቻላቸዉን ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸው ጠንቅቀሽ እወቂ :: ምንም እንኳ ፈሪ : ሆዳምና ወላዋይ መሰናክል ሊሆኑብሽ እንደሚችሉ ከወዲሁ ለመገመት ባያስቸግርም ሰፊው ህዝብ ግን ካንቺ ጋር ነው:: ቃልሽንም ያምናል:: የጀመርሽውን ትግል ዳር ታደርሽ ዘንድ አ ደ ራ : አ ደ ራ : አ ደ ራ ይላል::
    የግፍ ተቀባዩ ህዝብ አምላክ ይጠብቅሽ::

  37. ወሰን
    December 28th, 2008 at 09:32 | #37

    በጣም ከሚገርመው የኢትዮዽያን ሪቭው አዘጋጅ አቶ ኤልያስ ስለ ብርቱን በድህረ ገጡ ላያ ያወጣው አንዳችም ነገር የለም :ሊላ ነገር አውራ ወይም ቦጭቅ ቢሉት ይፈተፍት ነበር
    hard headed i like him but ያልዘራውን ማጬድ የሚፈልግ ሰው ነው በተለይ በብርቱካን ላይ ያለው ጥላቻ ይህ ነው አይባልም አሁንፍስ ከየትአኛው ወገን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻልም
    are you with Eyassu/Dr.Taye Woldesemait?

  38. ኪብሮም
    December 28th, 2008 at 09:47 | #38

    i’m from Tigrai region but i don’t support Meles because he never been eleceted by Ethiopian people he just took power with gun
    so,he doesn’t represent Ethiopian people he is just kind of የጅቦች /ኢህድግ አንጃዎች እና ጥርቅሞች መሪ ነው ለትግራይ ሕዝብ እንክዋን የፈጠሩለት አንዳችም ቁምነገር የለም ስለዚህ ይዋል ይደር እንጅ መባረራቸው አይቀርም
    የኢድሜ ፅጋ ያድርገን ለማየትም ያብቃን

  39. አወቀ
    December 28th, 2008 at 11:30 | #39

    አርአዶም
    መጠጊያ ያጣህ ትመስላለህ
    ወያኔ የወደቀ እለት መቀሌ ካልሆነ በስተቀር ሌላ መግቢያ እንደሌለህ ማወቅ አለብህ.ማየትም የምፈልገው እንዳተ አይነቱ አጬብጫቢ አፍቃሪ ወያኔ የት እንደሚገባ ማየት ነው የምፈልገው በተለይም የኢሕአድግ ቡችሎችና የፍርድ ቤት ዳኞች

  40. ሊነጋ ሲል ይጨልማል
    December 28th, 2008 at 12:05 | #40

    አርኦዳም
    አንተ ሻቢያነህ የምትሸውድ እራስህን ነው የእናንተ ጉዳይ የተዘጋ ፋይል ነው.የኛ [ማስተር ማይንድ] ወደ አረብ ጉዳይህ በተረፈ አደይን ልብዳልህ እግዚያብሄር ምን አርገነው ነው ከትግሬ ጋር የፈጠረን

  41. የኢትዮ ጌጥ
    December 28th, 2008 at 12:58 | #41

    አቦጊዳ እወዳችሁ ነበር አሁን ልንጣላ ነው:: ምነው የሰጠሁትን አስተያየት ሰረዛችሁት እባካችሁ እውነትን አንፍራው እንጋፈጠው የድል ባለቤት ለመሆን ከተመኘን : አልያ ምኞት ብቻ ሆኖ ይቀራል::

  42. Anonymous
    December 28th, 2008 at 13:26 | #42

    fyi
    From: Biri Yaya
    To: Ethiopians-Forum@yahoogroups.com
    Sent: Sunday, December 28, 2008 6:11:51 PM
    Subject: Re: [Ethiopians-Forum] Re: Birtukan Mideksa In Her Own Words

    Dear wondem Tedla,
    I am very much encouraged by your change of heart and seeing that Birtukan Midekssa is the best hope for those who would like to see a siginificant role for a centrist democratic party in Ethiopia.
    I have made the same assessment after appraising the circumistances.
    Even if we have some reservations, we should overlook minor differences in the interests of what is best for our country in the long term.
    That means holding hands across the web and globe to defend Birtukan who by all accounts comes across as the most courageous and genuinely for the good of our country.
    We should gear up for concrete actions(lobbying, financial supports…) and making sure that Birtukan does not become another forgotten victim of Meles Zenawi’s outlaw repressive regime!

    With Barack Obama in the White-House and the world leaning towards conflic resolution, we have a very good opportunity to expose the mercenary regime and to cut it out dry!!
    With appreciation,
    Biri!

    From: tedla asfaw
    To: Ethiopian Email Distribution Network
    Cc: ethiopians-forum@yahoogroups.com; cudethiopia@yahoogroups.com
    Sent: Sunday, December 28, 2008 2:04:47 PM
    Subject: [Ethiopians-Forum] Re: Birtukan Mideksa In Her Own Words

    Dear friends, we should rally behind her and call for the former Kinijit leadership back home to stand as one or else face extinction sooner or later. I posted this, the moment the news broke early yesterday on http://www.quotero. net

    Enberta,

    — On Sun, 12/28/08, Sultan R wrote:

    From: Sultan R
    Subject: Re: Birtukan Mideksa In Her Own Words
    To: EEDN@HOME.EASE. LSOFT.COM
    Date: Sunday, December 28, 2008, 1:13 AM

    Dear Alemayehu,

    Thank you so much for sharing the letter from Birtukan which addresses the hub-hub the panicking Woyane has created recently. I am so much encouraged that Birtukan is standing firm — on behalf of Andinet/Kinijit as well as the rest of us. I am glad she did not give in to Woyane as she had been urged by the cowards among us and even among the leadership of Andinet. With her at the helm, I am not worried about who is picking up the struggle where Kinijit left it off. I am also grateful to those who saw the potential in her and decided to put her over Kihdetu as the 1st deputy of Kinijit. At that time I was among those who were displeased when Kihdetu was passed over. I am glad we have no longer to rely on the erratic one to take the fight to the Woyane. We now know who is wearing the pants and who the skirt when facing Woyane. Moreover, we now know whom Woyane fears the most.

    Sultan

    Date: Sun, 28 Dec 2008 00:21:42 -0500
    From: allakew@GMAIL. COM
    Subject: Birtukan Mideksa In Her Own Words
    To: EEDN@HOME.EASE. LSOFT.COM

    “ቃሌ”- ከወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ

    Saturday, 27 December 2008 22:58

    W/t ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የሽምግልናውን ጉዳይ አስመልክቶ የሰጡት ቃል

    ታህሳስ 14 ቀን 2001 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ጽ/ቤት ተገኝቼ ማስጠንቀቂያ ሲነገረኝ እና ያው መልዕክት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሲተላለፍ ስመለከት ያደረብኝን ስሜት ለመግለጽ ያዳግተኛል።

    ምንም እንኳን ይህን ሁኔታ ለመለወጥ፣ ከማውቀውና ከማምነው ነገር ውጭ የምናገረው ነገር ባይኖርም ጉዳዩ በህዝብ ዘንድ ጥያቄዎችን ማጫሩ አልቅረምና በጉዳዩ ላይ ግንዛቤን ለመፍጠር ይቺን ጽሑፍ ለመጻፍ ወስኛለሁ። ምናልባትም የመጨረሻ ቃሌ ይሆናል።

    በሽምግልናው ልጀመር። የሽምግልናው መሰረታዊ መንፈስ፣ ሁለቱንም የሚያግባባ ስምምነት አምጥቶ እና የዕርቅን መንፈስ ፈጥሮ የፖለቲካ ሂደቱን ማስቀጠል ነበር። ይህም በመሆኑ ነው ሂደቱ በርካታ ወራትን ሊወስድ የቻለው። በዚህም ውስጥ ምርጫ 1997 ዓ.ም. ተከትሎ የተፈጠረውን ችግር በተመለከተ፣ የሀገር ሽማግሌዎች “አንዱን አጥፊ አንዱን ንጹኅ በማድረግ ሳይሆን እያንዳንዱ ወገን በወቅቱ ለተፈጠረው ችግር ህዝቡን ይቅርታ ጠይቆና እርስ በርሱም ተጠያይቆ በመሰረታዊ ጉዳዮችም ያለውን የፖለቲካዊ አመለካከት ቁርጠኝነትን አረጋግጦ፣ በዕርቅ መንፈስ ወደፊት በጋራ ለመቀጠል” በሚል ዓላማ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው ያሏቸውን ነጥቦች፣ ለሁለቱም ወገኖች ሲያቀርቡ ሃሳባችንን ሲያለዋውጡና በተቻለም መጠን ለማለዘብም ሲሞክሩ ቆይተዋል።

    ከዚህም የተነሳ በመንግሥት ፈቃደኝነት ብቻ ሳይሆን በእኛም ተሳትፎም ጭምር፣ በሀገር ሽማግሌዎች ሲደረግ የነበረው ሽምግልና ሁለቱም ወገኖች ሰጥተውና ተቀብለው የሚያመጡት ማስማሚያ ሃሳብ /Negotiated Deal/ በመድረስ ላይ ያተኮረ ነበር።

    በሂደቱ መንግሥትም ለሕገመንግሥታዊ ሥርዓት ያለውን ታማኝነት እንደገና እንደሚያረጋገጥ፣ እና ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ችግር ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን እና ቤተሰቦችን ለመካስ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም፤ ውይይቱ እየቀጠለ ሲሄድና የፍርድ ቤቱ ክርክር ወደ ብይን በሚቃረብበት ወቅት በሽማግሌዎች አስተባባሪ አማካይነት አንድ አሳዛኝ ሁኔታ ተነገረን።

    ይኸውም ሌላኛው ወገን፣ እኛ ታሳሪዎች ከህዝብ እና ከመንግሥት ይቅርታ ከምንጠይቅበት ነጥብ ውጭ በተለይም መንግሥትን የሚመለከቱ የወጡት ነጥቦች ላይ መስማማት አይፈልግም የሚል ነበር። ይሁን እንጂ በዚህም ደረጃ የውይይቱ አቅጣጫ የተመሰረተበት የዕርቅ መንፈስ አልተቀየረም ነበር። ስለሆነም ሽማግሌዎቹ ሌሎች የመግባቢያ ሃሳቦችን ወደኋላ የተተወ ቢሆንም በሀገራችን ባህል ይቅር በመባባል መንፈስ የተቃኘውን ያንን ሰነድ ብንፈርም ጉዳዩ ባለበት ደረጃ እንደሚቆም ፋይሉም እንደሚዘጋ ገልጠው ሽምግልናውን ገፉበት። ቃል በቃል በመግልጽም ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ይህ ሰነድ ከተፈረመ የሥራ አስፈጻሚ ሥልጣኔን ተጠቅሜ ክሱ እንዲቋረጥ አደርጋለሁ” እንዳሉ አረጋገጡልን።

    ከዚህ ጋር በተያያዘም “በሀገሪቷ ውስጥ ከቅንጅት ጉዳይ ጋር በተያያዘ የታሰሩ እስረኞች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚፈቱ በመንግሥት እና በቀድሞው ቅንጅት መሪዎች መሃከልም የፖለቲካ ውይይት በቀጥታ እንደሚጀመር የፓርቲው መሪዎች ያለምንም ገደብ የፓርቲውን ሥራ እንደሚቀጥሉ” ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር።

    በተጨማሪም ይህ ሰነድ በማንኛውም መንገድ ለምንም አይነት የፕሮፖጋንዳ ጥቅም በሁለቱም ወገኖች እንደማይውልና ሰነዱም የሚፈረመው ለሽማግሌዎች እንደሆነ፣ ሽማግሌዎችም በዚያ ላይ ተመስርተው የራሳቸውን ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚጽፉ በሽማግሌዎች የተረጋገጠ መሆኑ ታሳቢ ሆኖ ሰነዱ ተፈረሟል።

    በርግጥም በዚህ ሰነድ ላይ እኔም እንደ አንድ ታሳሪ መፈረሜን ክጄ አላውቅም። በሽማግሌቹም የዕርቅ መግባቢያ መንፈስ መሰረት፣ በፖለቲካ የተቀሰቀሰውን ክስ ፖለቲካዊ እልባት ለመስጠት በማሰብ ለዕርቅ ስል ከሌሎች የፓርቲው መሪዎች ጋር ተስማምቼ ሰኔ 11 ቀን 1999 ዓ.ም. በተጻፈው ሰነድ በሽማግሌዎች አማካኝነት መንግሥትንና ህዝብን ይቅርታ ጠይቄአለሁ። ይህ ብፈልግም ልለውጠው የማልችለው ሐቅ ነው።

    ከዚህ ስምምነት በኋላ ይጠበቅ የነበረው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሽማግሌዎቹ አረጋግጠው በሰጡት ቃል መሰረት የክሱ መቋረጠና የፋይሎ መዘጋት ቢሆንም ሂደቱ ሌላ አዲስ መልክ ያዘ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የዓቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ክሱን ሳያቋርጥ ቀረ። ይልቁንም ተከሳሳቹ ዕድሜ ልክ ቅጣታችንን ተቀበልን። ከዚህ በኋላ እንግዲህ ታሪኩ በእኛ ስምምነት ሳይሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈቃድ የተቃኘ ነው። ጉዳዩም ብሎ ብሎ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ለታሳሪዎች በሰጡት ይቅርታ እኛ ከእስር በመፈታታችን ተገባደደ።

    እንግዲህ እንዲህ ያለ የተዥጎረጎረ መልክ ያለውን ውስብስብ ሂደት በመደበኛው የሕግ የይቅርታ አቀራረብ ስነሥርዓት እንደቀረበም በዛውም አግባብ እንደተደመደመ ጉዳይ ብቻ ለማየት መሞከር አንድም እራስን ማሞኘት ነው፤ ሌላም አለማወቅ።

    አንድ ተከሳሽ በሕጉ መሰረት የይቅርታ ጥያቄ ማቅረብ ያለበት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይሆን ለይቅርታ ቦርድ ነው። በኛ ጉዳይ ለሀገር ሽማግሌዎች የፈረምነውን ሰነድ ለይቅርታው ቦርድ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው። ይቅርታውንም የጠየቁት እርሳቸው ናቸው ብሎም መከራከር ይቻላል። ሆኖም ግን በሕጉ አግባብ የይቅርታ ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው ባለጉዳዩ፣ ጠበቃው ወይም ቤተዘመድ እንጂ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አይደለም።

    ጥያቄው መቅረብ የሚችለውም በጉዳዩ ፍርድ ቤት ፍርዱን እና ቅጣቱን አጠናቅቆ ከወሰነ በኋላ እንደሆነ በሕጉ ተመላክቷል። በእኛ ጉዳይ ከመነሻው ጉዳዩን የየቅርታ /Pardon/ የመጨረስ ስምምነት ስላልነበረን ለሽማግሌዎች የተፈረመው ሰነድ የተፈረመው ፍርድ ቤት በጉዳዩ የቅጣት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ነው።

    ስለዚህ ከዚህ እውነታ በመነሳት በዚሁ በሕግ በተሰመረ አግባብ የይቀርታ ጥያቄ አላቀረብኩም። ሆኖም ግን በመጨረሻ በፕሬዝዳንቱ ለተሰጠው ይቅርታ ጥያቄ መሰረት የሆነውን የሀገር ሽማግሌዎች ለዕርቅ ሲሉ አግባብተው ሰኔ 15 ቀን 1999 ዓ.ም. ያስፈረሙንን ሰነድ ከነይዘቱ አልካድኩም ብሎ መናገሩ የቱ ላይ ነው ስህተቱ? የቱ ላይ ነው ወንጀሉ?

    በውጭ ሀገር በጉዳዩ የተናገርኩትም ይህንኑ የሚገልጽ እና የሚያብራራ እንጂ ሌላ ምንም የተለየ ይዘት አልነበረውም። ምናልባት የተናገርኩት አላግባብ ተተረጉሞ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ።

    ይህ የእኔ አንጋገር የተዛባ ነው ቢባልስ ፖሊስ ጣቢያ በመጥሪያም ያለመጥሪያም ለመመላለስ ያበቃል? በፍፁም ያስጠይቃል ቢባልስ በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የተሰጠን ይቅርታ የሚያስነሳው እንዴት ይሆን? ይቅርታን የሚያስነሳ ቢሆን ፌደራል ፖሊስ በየትኛው ሕጋዊ ሥልጣኑ ነው በጉዳዩ ምርመራ የሚያደርገው? ማስጠንቀቂያስ የሚሰጠው?

    ታህሳስ 1 ቀን 2001 ዓ.ም. የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር የወረዳ 12 ፖሊሲ አባላት የሆኑ ሁለት ፖሊሶችን ቤቴ በመላክ ቢሯቸው ድረስ እንድመጣ ሲጠሩኝ ስለ ፓርቲያችን ስለአንድነት ለመወያየት ሊሆን ይችላል በሚል በጽ/ቤታቸው ተገኝኔ የተጠራሁት ከይቅርታው ጋር በተያያዘ መሆኑ ሲነገረኝ መጀመሪያ የጠይኩት ጥያቄ “ፖሊስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ሥልጣን አለው?” የሚል ነበር። ምላሾቹ ግን በመነደቅ ፈገግታ የታጀበ “ይሄ እኮ የአካዳሚ ውይይት አይደለም፤ እንዲሁ አይነቱ ጥያቄ ብትተይ ይሻላል” የሚል ነበር። ለእነርሱ ያስፈገጋቸው፣ ያስገረማቸው ጉዳይ ግን እኔን ሁሌም የምኖርለት፣ የምቆምለት፣ እንዳንዴም የምታሰርበት እና የምፈታለት ታላቅ ቁም ነገር ነው። የሕግ የበላይነት ወይም ሕገመንግሥታዊነት።

    ሕገወጥነትን፣ ማናለብኝነትን መቼም አልለምደውም፤ አልተባበረውም። ስለዚህ ነው ታህሳስ 15 ቀን 2001 ዓ.ም. ፖሊስ ኮሚሽነሩ በድጋሚ ያለ ሕጋዊ መጥሪያ በመልዕክተኛ ወደ ቢሯቸው ሲጠሩኝ በወቅቱ ሳልሄድ የቀረሁት። በዕለቱ ከሰዓት በኋላ የሕግ መጥሪያ በደረሰኝ ጊዜ ወደ ቢሯቸው ለመሄድ ደቂቃም አላጠፋሁም። በኮሚሽነሩ ቢሮ ስደርስ የጠበቀኝና መጥሪያው የሚገልፀው ለየቅል ቢሆንም።

    ኮሚሽነሩ በላኩልኝ መጥሪያ ላይ እንደተጠቀሰው ጥያቄ ሳይሆን ያቀረቡልኝ መመሪያ ነክ ማስፈራሪያ ነበር። ስዊድን የሰጠሽውን ቃል በሦስት ቀን ውስጥ ካላስተባበልሽ መንግሥት ይቅርታውን አንስቶ እስር ቤት ይከተልሻል የሚል።

    “ይቅርታውን ማንሳት የሚችሉት እኮ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር እንጂ እርስዎ መንግሥት የሚሉት የሥራ አስፈጻሚ አካል አይደለም። ለዛውም እርሱም ቢሆን ሥርዓት አለው። የ”ይቀርታ ይነሳ” አቤቱታ ቀርቦ፣ በ20 ቀናት ውስጥ ለባለጉዳዩ ደርሶ፣ ቦርዱ ካመነበት ጥያቄው ለፕሬዝዳንቱ ቀርቦ፣ ያኔ ይቀርታው ሊነሳ ይችላል …” እያልኩ ለኮሚሽነሩ ላስረዳቸው አስቤ ነበር፤ አላደረኩትም። ንግግራቸውን መጨረሳቸውን አረጋግጬ ያለ ምንም ቃል ቢሯቸውን ጥዬ ወጣሁኝ።

    በእኔ እምነት ይሄ ሁሉ ከሕግ የወጣ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰብን ያለው ስለ ቃላት ጨዋታ ወይም ስለ ተዛባ እውነት ወይም ስለተጣሰ ሕግ አይመስለኝም። መልዕክቱ ግልጽ ነው። ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሠላማዊ ታጋዮች። “በሠላማዊና ሕጋዊ ማዕቀፍ ውስጥ የፖለቲካ ትግል ማድረግ የሚቻለው በሕገ መንግሥቱ በተሰመረው መስመር ሳይሆን፤ ገዢው አካል ወይም ግለሰቦች በፈቀዱት ብቻ ነው” የሚል ነው። ለዚህም ደግሞ እሺ ወይንም “አዎ” ማለት ለእኔ እጅግ ከባድ ነው።

    ብርቱካን ሚደቅሣ

    ታህሳስ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. / December 27, 2008

    Life on your PC is safer, easier, and more enjoyable with Windows Vista®. See how

    __._,_.___
    Messages in this topic (1) Reply (via web post) | Start a new topic
    Messages | Files | Photos | Links | Database | Polls | Members | Calendar
    Important Disclaimer - This Ethiopians-Forum Members and Supporters Discussion forum is un-moderated. The content of this forum is simply a collection of opinions with no editorial or factual checking. The information posted is assumed to be the opinion of the author alone and does not represent the beliefs or opinions of their respective organization nor those of the Party.

    To unsubscribe from CUD group, send an email to:
    Ethiopians-Forum-unsubscribe@yahoogroups.com

    MARKETPLACE
    From kitchen basics to easy recipes - join the Group from Kraft Foods
    Yahoo! Groups
    Change settings via the Web (Yahoo! ID required)
    Change settings via email: Switch delivery to Daily Digest | Switch format to Traditional
    Visit Your Group | Yahoo! Groups Terms of Use | Unsubscribe
    Recent Activity
    Visit Your Group
    Cat Groups

    on Yahoo! Groups

    Share pictures &

    stories about cats.
    10 Day Club

    on Yahoo! Groups

    Share the benefits

    of a high fiber diet.
    Yahoo! Groups

    Special K Challenge
    Join others who

    are losing pounds.
    .

    __,_._,___

    From: Biri Yaya
    To: cbogale@yahoo.com; fekaduteshale@yahoo.com; nc-belaynal2@netcologne.de; zaude.hm@chello.se; yitu@npaid.org; wyi@broadpark.no; workeneh@freenet.de; tilahun@arcor.de; tensae.support@gmail.com; teka@unicc.org; christodoulou_spyros@yahoo.com; soloted2000@yahoo.com; sintayehu.tsehay@chello.at; shimelesfetene31@hotmail.com; Selam2005@aol.com; SamuelMe@web.de; sammyg32@hotmail.com; nesibu@yahoo.de; Negussieali@aol.com; nberhanu@hotmail.com; mzelalem@gmail.com; mulualemad@yahoo.com; mistre@bluewin.ch; mhs2005@bluewin.ch; eshetu@mekonnen.de; MamoYihune@aol.com; mail@et-eueom.org; leon19020@yahoo.com; kshewaye@yahoo.com; kiyaye2003@yahoo.com; kinfuassefa@gmail.com; KebedeF@aol.com; kassa50@yahoo.de; joseyhunfeld@yahoo.com; inegussie@spiderbusiness.com; indalk.negussie@free.fr; hostmaster@comserver.net; hollynight@arcor.de; hanamariam@online.de; ourgessa@yahoo.com; GHABTE12@aol.com; Getachew.wanna@gmail.com; Getachew.wanna@telia.com; geert.guenet@worldonline.nl; fisshaw@hotmail.com; fisseha.worku@gmail.com; fekadu@t-online.de; fekadu2000@hotmail.com; ethiosara@yahoo.com; ethiosara@gmail.com; ethiosaea@gmail.com; Ethiogermany@gmail.com; eth_market@yahoo.gr; Eshetuali@web.de; ehtiosara@gmail.com; editor@ethiomedia.com; demelash@web.de; aldebebe@yahoo.com; merened1@yahoo.com; Bselame@aol.com; berhanu_78@yahoo.com; bemnet@gmx.net; belaywondafrash@yahoo.de; belay1973@yahoo.de; Bekkelle@aol.com; behager1@yahoo.com; andenetadmin@andenet.com; atsege@hotmail.com; alemayehu@netcologne.de; belaynal2@netcologne.de; aethiopien@bluewin.ch; Ameshesha@aol.com; g_ethiop@yahoo.com; lebened@hotmail.com; lu_bek_y@yahoo.com; msibhat@sbcglobal.net; teodros@sbcglobal.net; henoketh@yahoo.com; Dlemma60716@aol.com; meskerem68@yahoo.com; lubek73@fastmail.fm; Drgejere@aol.com; DELNISSAW@HOTMAIL.COM; Wondimu.Mekonnen@BTInternet.com; serahbezu@hotmail.co.uk; olf_fr@earthlinks.net; ABULE2002@YAHOO.COM; a.endeshaw@wlv.ac.uk; info@abugidainfo.com; assefa_feyisa@yahoo.com; AENDESHAW@BROOKES.AC.UK; GETACHEW@BTINTERNET.COM
    Sent: Saturday, December 27, 2008 8:17:45 PM
    Subject: ”MY WORDS/STATEMENT”: UDJP CHAIR-PERSON[BIRTUKAN] PROVIDES OUTLINE OF MEMORANDUM OF UNDERSTANDING WITH ELDERS…AND UPDATE ON HARASSMENT/IMPLICATIONS BY M ZENAWI’S REGIME

    http://www.abugidainfo.com/amharic/?p=311

    ”MY WORDS/STATEMENT”: UDJP CHAIR-PERSON[BIRTUKAN] PROVIDES OUTLINE OF MEMORANDUM OF UNDERSTANDING WITH ELDERS…AND UPDATE ON HARASSMENT/IMPLICATIONS BY M ZENAWI’S REGIME

  43. ይናገሩ
    December 28th, 2008 at 13:30 | #43

    አይ አቶ መለስ እስየን ፈታችብዎ አሁን ደግሞ የእርቁን ሃሳብ እራስዎ አረቀቁት አለችዎ ይችን አንበሳ ቢተዋት ነው ጥሩ ካልሆነ ገና ጉድ ታፈላለች.

  44. Teshome S
    December 28th, 2008 at 14:31 | #44

    Our brave leader, Birtukan Mediksa, has said in clear and plain language on how she was released from the prison along with her colleagues. She has also put her words in the context of the legal framework. This is the truth which is very hard to swallow by the Woyane regime.
    When are we going to have our freedom of expression? For how long are we going to allow Meles to arrest, torture and kill us? We all have to come together and join hand in hand and fight this regime. This intimidation and harassment on our leader has to STOP NOW!

  45. Bruk
    December 28th, 2008 at 16:46 | #45

    አንድ ለማትረባ ሰው ይህን የሚያህል ሰአት ማትፋት ምን ያህል የአኢትዮያ ፖለቲክስ አንደረከሰ ያስረዳል.
    Woyanne strictly knows she is waging a low profile politics this time after she killed the Ethiopian people struggle during Kinijit split.
    So talking about Birtukan politics is a very minor thing for the government and moreover it is a game.
    Folks, dont waste your time on wasteful politics.

  46. Biri
    December 28th, 2008 at 17:14 | #46

    fyi
    From: Biri Yaya
    To: Ethiopians-Forum@yahoogroups.com
    Sent: Sunday, December 28, 2008 6:11:51 PM
    Subject: Re: [Ethiopians-Forum] Re: Birtukan Mideksa In Her Own Words

    Dear wondem Tedla,
    I am very much encouraged by your change of heart and seeing that Birtukan Midekssa is the best hope for those who would like to see a siginificant role for a centrist democratic party in Ethiopia.
    I have made the same assessment after appraising the circumistances.
    Even if we have some reservations, we should overlook minor differences in the interests of what is best for our country in the long term.
    That means holding hands across the web and globe to defend Birtukan who by all accounts comes across as the most courageous and genuinely for the good of our country.
    We should gear up for concrete actions(lobbying, financial supports…) and making sure that Birtukan does not become another forgotten victim of Meles Zenawi’s outlaw repressive regime!

    With Barack Obama in the White-House and the world leaning towards conflic resolution, we have a very good opportunity to expose the mercenary regime and to cut it out dry!!
    With appreciation,
    Biri!

    From: tedla asfaw
    To: Ethiopian Email Distribution Network
    Cc: ethiopians-forum@yahoogroups.com; cudethiopia@yahoogroups.com
    Sent: Sunday, December 28, 2008 2:04:47 PM
    Subject: [Ethiopians-Forum] Re: Birtukan Mideksa In Her Own Words

    Dear friends, we should rally behind her and call for the former Kinijit leadership back home to stand as one or else face extinction sooner or later. I posted this, the moment the news broke early yesterday on http://www.quotero. net

    Enberta,

    — On Sun, 12/28/08, Sultan R wrote:

    From: Sultan R
    Subject: Re: Birtukan Mideksa In Her Own Words
    To: EEDN@HOME.EASE. LSOFT.COM
    Date: Sunday, December 28, 2008, 1:13 AM

    Dear Alemayehu,

    Thank you so much for sharing the letter from Birtukan which addresses the hub-hub the panicking Woyane has created recently. I am so much encouraged that Birtukan is standing firm — on behalf of Andinet/Kinijit as well as the rest of us. I am glad she did not give in to Woyane as she had been urged by the cowards among us and even among the leadership of Andinet. With her at the helm, I am not worried about who is picking up the struggle where Kinijit left it off. I am also grateful to those who saw the potential in her and decided to put her over Kihdetu as the 1st deputy of Kinijit. At that time I was among those who were displeased when Kihdetu was passed over. I am glad we have no longer to rely on the erratic one to take the fight to the Woyane. We now know who is wearing the pants and who the skirt when facing Woyane. Moreover, we now know whom Woyane fears the most.

    Sultan

    Date: Sun, 28 Dec 2008 00:21:42 -0500
    From: allakew@GMAIL. COM
    Subject: Birtukan Mideksa In Her Own Words
    To: EEDN@HOME.EASE. LSOFT.COM

    “ቃሌ”- ከወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ

    Saturday, 27 December 2008 22:58

  47. በለው
    December 28th, 2008 at 19:20 | #47

    ኢትዮ ጌጥ ደህና ብለዋል….ለነገሩ ስውን ስንተች እንጂ እኛ ለመተቸት ዝግጁ ስላልሆን ዲሞክራሲን መተግበር ሳይሆን መጻፍ ያስቸግረናል የማይጽፉ እጆች ያጠፋሉ!!!!
    ከቤታችሁ ሁሉ ቀፎ ሞልቶላችሁ
    የኛ ልመናችን ተማሩ ነው ያልናችሁ !!!!!!!!!

  48. ድል ድል ለ ኢትዮጰያ
    January 5th, 2009 at 18:16 | #48

    እኅኅኅኅኅኅኅኅኅ………………………..
    ቃሌ ነዉ ብላለች ብርቱካን ሚደቅሳ!
    እዉነትን እያየች እንዲያ ስትገፋ
    ዝም ብላ ላትሄድ እራስዋን ሽፍና
    ቃል አባይ ላትሆን ሆድ አዳሪ ሆና
    ያኔ የገባችዉን ማላዋን ሳትረሳ
    እውቀትዋን ጊዜዋን ለሰላም ሰውታ
    ለህዝባዋ እራርታ አለሁልህ ብላ!
    እምምምምም…………………………
    ጀግናን የወለደች ትናገር ላገርዋ
    ማንንም ሳትፈራ እውነት ተመርኩዛ!

  49. Mamo
    January 14th, 2009 at 21:37 | #49

    We need democracy in Ethiopia! Freedom of speech
    Check out! How Ethiopians create such a master peace in the country of freedom!
    http://www.commemoration2009.com
    Peace to Ethioia

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።