በሺሆች የሚቆጠሩ በመርካቶ የመድረክ/አንድነት ስብሰባ አጣበቡ ! አዳራሹና ጊቢዉ ሞልቶ ብዙዎች ተመለሱ !
አቡጊዳ የካቲት 21 ቀን 2002 ዓ.ም
በመርካቶ አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት አዳራሽ፣ መድረክ ትላንት ቅዳሜ የካቲት 20 ቀን 2002 ዓ.ም ፣ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ አደረገ።
የትምህርት ቤቱ አዳራሽ መያዝ ከሚችለዉ በላይ በሰዉ ተጨናንቆ የነበረ ሲሆን ከአዳራሹ ዉጭ ቁጥሩ እጅግ በርካታ የነበረ ሕዝብ እንደነበረም ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያመለክታል። ሁለት ሺህ ሕዝብ የሚይዘዉ አዳራሽ በመሙላቱና ጊቢዉ ዉስጥም መቆሚያ በመጥፋቱ፣ የትምህርት ቤቱ ዘበኞች የመድረኩን ስብሰባ ለመካፈል የመጡ በርካታ ሌሎች ኢትዮጵያዉያንንም ለመመለስም ተገደዋል።
በስብሰባዉ የተገኘዉ ሕዝብ ብዛት ከጠበቁት በላይ የሆነባቸዉና ሕዝቡ ያቀርብ በነበረዉ አስተያየት የተደነቁት ፣ የመድረኩን ስብሰባ የመሩትና በመርካቶ አካባቢ መድረኩን ወክለዉ ለፓርላማ የሚወዳደሩት፣ ወ/ሮ ላቀች ደገፋ፣ «በቅንጅት ጊዜ የነበረዉን አይነት የሕዝብ ግለት ነዉ ያየሁት» ሲሉ ስብሰባዉ፣ ሕዝቡ ለለዉጥ፣ ለሰላም፣ ለአገሩ አንድነትና ለነጻነቱ ያለዉን ቁርጠኝነት በግልጽ ያንጸባረቀበት ታላቅ ስብሰባ ነዉ ሲሉም አስተያየታቸዉ ገልጸዋል።
በሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን በተገኙበት በዚሁ የመርካቶ የመድረኩ ስብሰባ፣ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆነችዋ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ በግፍና በጭካኔ በወያኔ/ኢሕአዴግ የታሰረችበትን አሥራ አራተኛ ወር የታሰበ ሲሆን፣ ሕዝቡም በዚህ አጋጣሚ ለወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ያለዉን ክብርን ፍቅር በሚያስደንቅ ሁኔታ መግለጹን ከስፍራዉ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
«የመድረኩ የምርጫ ምልክት የአምስት ጣቶች የሰላምታ ምልክት ሳይሆን የብርቱካን ምልክት መሆን ነበረበት፤ አንድነት/መድረኩ ይህ አይነት ስብሰባ ለማድረግ መዘግየት አልነበረበት፣ አይዟቹህ እኛ ከጎናቹህ ነን። መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተናል …. » የሚሉ ጠንካራና ወኔ የሞላበት አስተያየቶች ይሰጡ የነበሩ ሲሆን፣ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላትም በሕዝቡ ስሜት እጅግ መበራታታቸዉና መደሰታቸዉን ከስፍራዉ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ስም ሲነሳ ሕዝቡ በጭብጨባና በፊጩት ስሜቱን ሲገልጽ የተመለከቱ ያነጋገርናቸዉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ፣ የመርካቶዉን ስብሰባ «አስደናቂ» ሲሉ ከገመቱትና ከጠበቁት በላይ እንደሆነ አስረድተዋል።
«ወያኔ የቅንጅት መሪዎችን ለሃያ ወራት ርካሽ በሆነ በዘር ማጥፋት ወንጀል አሰረ። ቅንጅትን አፈራረሰ። የቅንጅትን ስም ለአየለ ጫሚሶ ሰጠ። ብርቱካን ሚደቅሳ የሕዝብን አደራ ሳትበላ ፣ በዉጭ አገር የስደትንና የምቾትን ኑሮ አልፈልግም ብላ፣ መብቱ ከተረገጠዉ ሕዝብ ጋር አብሬ እታገላለሁ የሚል ዉሳኔ ወስና፣ በወያኔ ዱላ የተበታተነዉንና የፈረካከሰዉን ቅንጅት እንደገና አሰባስባ፣ በአንድነት ስም መንቀሳቀስ ጀመረች። ከቀድሞ ቅንጅት ክልል በማለፍ የቀድሞ ቅንጅት ያላቀፋቸዉን በብሄር ተደራጅተዉ የነበሩ ወገኖቻችንን በኢትዮጵያዊነት ጥላ ሥር ማሰለፍ ቻለች። መድረክ እንዲቋቋም ቁልፍ ሚና ተጫወተች። በዚህም ምክንያት ወያኔ የበቀልና የጭካኔ እርምጃ ወሰደባት።» ሲሉ ከዚህ በፊት የተደረጉትን ጥረቶችና የተከፈሉትን መስዋእተነት ያስታወሱት እኝሁ የፖለቲካ ተንታኝ « እንደዚያም ሆኖ ግን፣ ወያኔ እንደተመኘዉ አልሆነለትም። ሕዝብ ለነጻነቱ፣ ለመብቱና ለአንድነቱ ያለዉ ጥማትን የሚያመለክተዉ የቅንጅትን መንፈስ ሊያጠፋ አልቻለም። የቅንጅት ፓርቲዉን ሰርተፊኬት ሊወስድ፣ ስሙን ሰርዞ ለሌላ ሊሰጥ ይችላል። ነገር ግን መንፈሱን ግን ሊያጠፋ አይችልም። ብርቱካንን ሊያስር ይችላል። ብርቱካን የታሰረችለትን የነጻነትና የፍትህ እሳትን ግን ማዳፈንና ማሰር አይችልም። በመርካቶ የተደረገዉ ስብስባ ይሄንኑ ነዉ በገሃድ ያሳየዉ። » ሲሉም ወያኔ በጠመንጃና ገንዘብ አብላጫ ቢኖረዉም በሃሳብና በሕዝብ ድጋፍ ግን የተሸነፈ መሆኑን ያስረዱት።
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዱዋለም አርጌ በሚወዳደሩበት የሰሜን ማዘጋጃ አካባቢም ያለፈዉ ሳምንት እሁድ የካቲት 14 ቀን 2002 ዓ.ም ፣ በድል በር ትምህርት ቤት ተመሳሳይ ሕዝባዊ ስብሰባ የተደረገ መሆኑን በዚያ በርካታ ህዝብ ተገኝቶ ከመድረኩ አመራር አባላት ጋር መወያየቱ ይታወቃል።
በመርካቶና በሰሜን ማዘጋጃ የተደረጉት ሕዝባዊ ስብስባዎች በተከታታይ በሃያ ሶስቱም የአዲስ አበባ ወረዳዎች የሚደረጉ ሲሆን መድረኩም ለሚቀጥሉት አራት ወራት ህዝቡ ከፍርሃት ተላቆ ለመብቱ የሚነሳበት ጊዜ እንደሆነ በማሳሰብ የተጧጧፈ ቅስቀሳዎች የሚያደርግ እንደሆነም የመድረኩ አመራር አባላት ይጠቁማሉ።



Don’t limit the dynamic actions of your people.MEDREK’s public meetings and rallies should not be confined to school halls.Why do you return the people away who come to hear you,support you and show you their love and solidarity for lack of enough space of assembly?Shouldn’t you instead need stadiums and other open spaces for such vital and mass actions? In other words,shouldn’t you,through a creative and visionary leadership,help the struggle expand,gather momentum,go into new territories? Why do you have to constrain the potentials?
The people are ever ready.Are their incumbent leaders really ready to lead them to victory?
Bravo residents of Merkato! I salute you for your support of Birtukan!
ምን ዋጋ አለው ? ምንም ይሁን ምን ወያኔ ስልጣኑን በምርጫ ለመልቀቅ ፍላጎቱም ሆነ ሃሳብ የለውም:: ሕዝቡ አቅም አጣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ከተሰበሰቡበት አዳራሽ ውጭ የሚያመጣው ለውጥ እምብዛም ነው:: ነገር ግን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከምንም ይሻላል;;
ሎሎ ዋጋ የሌለው ያንተ አመለካክት ነው ህዝብ ከተነሳ እንኩዋን ወያኔ አምላክ አያቆመውም::
ታዛቢ!
የመሰብሰቢያ ቦታዎች በሙሉ በኢሕአዴግ መልካም ፈቃድ ብቻ እንደሚገኙ ታውቃለህ? ያ ባይሆን ኖሮ መድረክ በመስቀል አደባባይ ሕዝቡን ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሁሉ ይከሽፍ ነበር? በ6ኪሎ የስብሰባ ማዕከል ከ1000 ሰው በላይ ማስገባት አትችሉም ተብሎ የተሰረዘውን ስብሰባ ታሪክስ ሰምተሃል?
እባካችሁ: ሃሳብ ከመሰንዘራችሁ በፊት ትንሽ ተዘጋጁ - በጉዳዩ ላይ አስቡበት::
ዋናው ነገር በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ ከሕዝብ ጋር መገናኘት ነውና ያለውን ዕድል በሙሉ ለመጠቀም በሚያደርገው ጥረት መድረክ ሊበረታታ ይገባዋል:: ባለፈው ምርጫ ከታዩት ስህተቶች አንዱ ትናንሽ ከተሞችን የመዘንጋት (ቸል የማለት) ጉዳይ ነው:: በዚህኛው ዙር እስከተቻለ ድረስ ወደታች ለመውረድ መሞከር ተገቢ ይመስለኛል:: የጊዜና የገንዘብ እጥረት ለዚህ ዓላማ እንቅፋት ሊሆኑ እንደሚችሉ ቢገመትም የተቻለንን ሁሉ ከማድረግ ግን ወደ ኋላ እንዳንል ለማስገንዘብ ያህል ነው::
በርቱ!
@ሎሎ
አድስ አበባን በአንድ ድምት አስለቅቀነው ዐንደነበር አሁን ደግሞ በአንድነት ከመላ አገረ ግዛት ላ