እኛ እንተባበር-ይህን ሕግን የሚንቅ ሥርዓት ማስወገድ እንችላለን !(ግርማ ካሳ)
ግርማ ካሳ (ቺካጎ) - muziky68@yahoo.com / ታህሳስ 24 ቀን 2001
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ዋሽንግተን ዲሲ የአንድነት ፓርቲ ልኡካን ቡድን አባል ሆነዉ ለኢትዮጵያዉያን ንግግራቸዉን ሲጀምሩ በጸሎት ነበር የጀመሩት። «አምላክችን ሆይ ኢትዮጵያ ተችግራለች። እኛም ተችግረናል።
እባክህ ፍቅርን ስጠን» ብለዉ እግዚአብሄርን ሲማጸኑ ከአይኖቼ እንባ ፈሶ ነበር። በኢንተርኔት ብቻዬን እከታተል ስለነበረም ድምጼን ከፍ አድርጌ «አሜን !» ብዬ ጮህኩኝ።
ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከቃሊቲ እሥር ቤት በተፈቱ ጊዜ በጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ጋር ያደረጉት አንድ የማልረሳዉ ቃለ መጠይቅ ነበር። «ስላሰሯቹህ ስዎች ምን ትላላቹህ። እንደጠላት ነዉ ወይ የምታይዋቸዉ ?» ተብለዉ ሲጠየቁ «ቅንጅት የሰዉ ጠላት የለዉም» በማለት ነበር እርሳቸዉና አብረዋቸዉ የታሰሩ ጓደኞቻቸው በጥላቻና በቂም በቀል ያልተሞሉ ከራሳቸዉ ጥቅም ይልቅ በኢትዮጵያ መረጋጋት ሰላምና እርቅ እንዲመጣ የሚፈልጉ መሆናቸዉን ያሳዩን።
የቀድሞ ቅንጅት አሁን አንድነት አመራር አባላት በዳያስፖራ ካሉ አንዳንድ አካላት ከፍተኛ ተቃዉሞ እየደረሰባቸዉም ቢሆን «ወያኔ ጠላት አይደለም። የምናደርገዉ ትግል ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያን ለመጥቀም አላማዉ ያደርገ ትግል እንጂ ጸረ ወያኔም ሆነ ጸረ ማንም ትግል አናደግርም።» እያሉ በድፍረት ሕዝቡን አስተምረዋል።
እኛም የነዚህን ሰላማዊ የዲሞክራሲ ጀግኖች ጥሪ ተከትለን አብረናቸዉ የሰላም የእርቅ የወንድማማችነትና የፍቅር መልዕክት ስናስተጋባ ቆይተናል። «አሁን በስልጣን ላይ ካሉት ጋር መነጋገርና መወያየት ያስፈልጋል። እነርሱን መለወጥ እንችላለን» በሚል ነጩን የሰለም ባንዲራ አዉለብልበናል። ምላሹ ግን መሪዎቻችንን በሰደፍ መደብደብና በግፍ ቃሊቲ ማወረድ ሆነ።
አዎ መስሎን ነበር በአራት ኪሎ ያሉ ባለስልጣናት የሚሰሙን። መስሎን ነበር አይሞሮና ልብ ያላቸዉ። መስሎን ነበር ከዚህ በፊት ከሚሄዱበት መንገድ ሊመለሱ የሚችሉ።
ከጊዜ ወደ ጊዜ የምናየዉ ግን ተስፋ የምናደርገዉን ሳይሆን አንገታችን የሚያስደፋዉን ነዉ። ልባችንን በደስታ የሚሞላ ሳይሆን ዉስጣችንን የሚያቆስል ነዉ። ፍቅርና ይቅርታን የሚያወሩ እነ ቴዲ አፍሮ በግፍ ሲታሰሩ፣ የሰላምና የስብዓዊ መብት መከበር ሐዋርያ የሆኑት እነ ፕሮፌሰርን መስፍንን ወልደማሪያም ሲደበደቡ፣ ለፍትህና ለኢትዮጵያ አንድነት የቆሙ እነ በርቱካን ሚደቅሳ ወህኒ ሲጣሉና የጭካኔ የዛቻ የትዕቢት የዉሸትና የሸፍጥ ፖለቲካ እየበዛ ሲሄድ ነዉ የምናየዉ።
የአሜሪካን ድምጽ ሬዲዮ ባልደረባ አቶ ሰለሞን ክፍሌ ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ሳዳምጥ ሐዘን ብቻ አልነበረም የተሰማኝ ሐፍረትም እንጂ። ተሸማቀኩኝ። «ኢትዮጵያዊ ናቸዉ። የኔ ወንድሞች ናቸዉ» የምላቸዉ ወገኖች እንዲህ አይነት ሥራ ሲሰሩ ሳይ «ምን አይነት ትዉልድ ሆነናል!» ብዬ አዘንኩኝ።
እስቲ አስቡት ! የሰባ ስምንት አመት አዛዉንትን በሰደፍ መደብደብ ስብዕና ይባላል ? አዉሬነት እንጂ። እስቲ አስቡት ! አንዲትን ሴት በአራት መኪናና በአሥር ደህንነቶች እያዋከቡ እያንገላቱና እየገፉ መንዳት ሕግን ማክበር ይባላል ? ውንብድና እንጂ።
ኢሕአዴግ ዉስጥ ጥሩ ልብ ያላቸዉ ፓርቲዉን ወደ ቀናዉ መንገድ ሊመሩት የሚችሉ ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ተስፋ ነበረኝ። አሁንም እነዚህ ሰዎች አሉ ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን በዚህ ሳምንት ከታየዉ አሳዛኝ ሁኔታ አንድ በግልጽ የደረስኩበት ድምዳሜ አለ። እርሱም ኢሕአዴግን ወደ ጥሩ አቅጣጫ ሊወስዱ የሚችሉ ኃይላት በፓርቲዉ ዉስጥ ምንም ለዉጥ ሊያመጡ እንዳልቻሉና በነርሱ ተስፋ ማድረግ ከአሁን በኋላ የሚያዋጣ እንዳልሆነ እየታየኝ ነዉ።
«ታዲያ ምንድን ነዉ የሚያዋጣዉ? » ብላቹህ ብትጠይቁኝ በቀዳሚነት አንድ ነገርን አጉልቼ እናገራለሁ። መፍትሄዉ የሚያዋጣዉ በአንዲት ኢትዮጵያ የምናምን በአገራችን ዲሞክራሲ እንዲሰፍን የምንሻ ሁሉ በቅንነት እርስ በርስ ከመጠቃቃት ተቆጥበን በሚያስማሙን ነገሮች ላይ መተባበሩ ብቻ ነዉ።
ለዚህም እንዲረዳ የሚከተሉትን ነጥቦች ለፖለቲካ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችና ለሜዲያ ግሩፖች በአክብሮት አቀርባለሁ፡
1. እያንዳንዱ ድርጅት ሌላዉን ከመንቀፍ ተቆጥቦ በሚሰራዉ ሥራ ላይ ያተኩር። በሥራዉ ዉጤት የሚያመጣ ድርጅት ምንም በሌሎች ቢተችም በሕዝብ መደገፉ አይቀሬ ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ወሬ ሳይሆን ወጤት ነዉ የሚፈልጉት።
2. በሌሎች ድርጅቶች የድጋፍ ካልሆነ የጥቃት መግለጫ ማዉጣት፣ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን መሳደብ ይብቃ።
3. በመግለጫዎቻችን በሜዲያዎቻችን የምናወጣቸዉ በእዉነት ላይ የተመሰረቱ ያልተለጠጡና ያልተጋነኑ ይሁኑ ! የሰለጠን ስብእና ያለን ጨዋ ኢትዮጵያዋያን መሆናችንን በዚህ እናሳያለን።
4. «የሰላማዊ ትግል አይሰራም፤ የትጥቅ ትግል አይሰራም» እያልን መከራከራችንን እናቁም። እኔ ሰላምዊዉ ትግል የሚበጅ አማራጭ ነዉ እላለሁ። ይህ አቋሜ ይከበርልኝ። «አይ ወያኔ በጠመንጃ ካልሆነ አይቻለም» የሚሉ ደግሞ እነርሱ ይዘናል ባሉት መንገድ ይቀጥሉበት። አቋማቸዉ ይከበርላቸዉ። «ይሄ ይበጃል ያ ይበጃል» የሚለዉን ክርክር ሂደት የሚወስነዉ ይሆናል።
5. ሕብረት መፍጠሩ ጠቃሚ ቢሆንም በችኮላ ሕብረት መፍጠሩ ጉዳት ሊያመጣ ይችላል። ሕብረት መፍጠሩ ላይ አሁን ከማተኮር ቢያንስ ቢያንስ በጋራ የሚሰሩ ሥራዎች ላይ አብሮ የመስራትን ባህል ማዳበር ይጠቅማል። የጋራ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎችን ለማድረግ፣ የጋራ መግለጫዎችን ለማዉጣት ያስችል ዘንድ ከሁሉም ወገን የተወጣጣ አንድ ግብረ ኃይል፣ የዲፖሎማሲዉን ሥራ በቅንጅት የሚሰራ ሌላ ግብረ ኃይል በአስቸኳይ እንዲቋቋም ያስፈልግሃል። ሥራዉ አንድ አይነት ሆኖ በአሥር ገመድ በተለያዩ ድርጅቶች መጎተት የለብንም። አሜሪካኖች አዉሮፓዊያኖችም ቢሆኑ ከሃያ ድርጅቶች መስማት አይፈልጉም። በአንድ ድምጽ ካልተናገርን ይንቁናል።
ዉድ ኢትዮጵያዉያን እነብርቱካን ሚደቅሳ በቃሊቲ እየተሰቃዩ ነዉ። እነ ፕሮፌሰር መስፍን ሰደፍ አርፎባቸዋል። ያለፉትን ልዩነቶቻችን አቻችለን ከዚህ በፊት ለተነጋገርነዉና ለተቀያየምነዉ ይቀር ተባብለን ለአንዲት ኢትዮጵያ በጋራ ለመስራት ክብራችን መዋጥ ያቅተናልን ? አያቅተንም። እንችላለን።
ትንሹ ዳዊት ግዙፉን ጎሊያድ ጥሏል። እኛ ከተባበርን እኛ ከተደጋገፍን የማንወጣዉ ተራራ የለም። እኛ እንተባበር ፤ በርግጥ ይህ ሕግን የሚረግጥ ሥርዓት ሲወገድ እናያለን። ጥያቄው «እንችላለን ወይ? » አይደለም ? ጥያቄዉ «ፍላጎቱ አለን ወይ? » የሚል ነዉ።



ይህ አሳብ ከስከነ ልቦና የወጣ ስለሆነ ሊደገፍ ብሎም ሊደመጥ ይገባል:: በሆነ ባልሆነው እርስ በርስ ከመሰዳደብ ይላቅ ዋናው ችግር ላይ ትኩረት ሰጥቶ በአንድ ላይ በመቆም በኢትዮጵያ ሃገራችን ህልውና እንዲሁም በልጆቹአ የመጣውን ጠላት መጋፈጡ ይመረጣል:: በዋና ሃሳቡ ላይ ሰው እስከ ተስማማ ድረስ በትንሹና በማይጎዳው ልዩነት ላይ ማተኮር የኢሃደግን ዘመን ለመጨመር ብቻ ነው::
ይህ አሳብ ከስከነ ልቦና የወጣ ስለሆነ ሊደገፍ ብሎም ሊደመጥ ይገባል:: በሆነ ባልሆነው እርስ በርስ ከመሰዳደብ ይልቅ ዋናው ችግር ላይ ትኩረት ሰጥቶ በአንድ ላይ በመቆም በኢትዮጵያ ሃገራችን ህልውና እንዲሁም በልጆቹአ የመጣውን ጠላት መጋፈጡ ይመረጣል:: በዋና ሃሳብ ላይ ሰው እስከ ተስማማ ድረስ በትንሹና በማይጎዳው ልዩነት ላይ ማተኮር የሚጠቅመው የኢሃደግን ዘመን ለመጨመር ብቻ ነው::
Ato Girma,
You are right. I knew that you were one of the individuals strongly attacking Ginbot7 for choosing different approach for the struggle. Are you ready to say sorry for the public? Atleast we have to start to admit our mistakes.
Regards,
E.
Ato Girma,
Please be strong man and stand firm. It is better to ask Satan(devil) than woyane for mercy.
Just be a man and fight woyane, the group of subhumans.
Thanks
እንተባበር
እንከባበር
እንማማር
I was following Eng. Hailu today on http://www.ethiolion.com and he was asked if his organization took stand on the jailing of Birtu Kahen/Birtukan the leader of UDJP. He said they are working on it and it will be public soon.
I understand why they did not come quick to defend Birtukan because they do not want to give an ammunition for those hyenas to lock them up before any understanding is reached between AEUP and UDJP.
Both faced the same enemy that would like to kill them separately and they need each other for survival. There is no war and will not be any between AEUP and UDJP.
I hope the diaspora AEUP and UDJP support group start following their leaders back home and bring the needed unity with difference immediately.
I commend Wondem Girma for his honest assessment and recommendation.
Kaleshe Kalachene
መልካም ነው አባባሉ ሁሉ ድንቅ ነው በርግጥ ዬኛ ትብብር ማጣት ነው ወያኔን ያናጠጠው:: አንድ እንሁን ማለት ለኢትዮጵያችን ሲሉ እንግልት ለመደርስባቸውም ሁሉ እኩል እናልቅስ ማለት መሆኑንስ ተገንዝበናል ወይስ በሀሳብ የሚስማሙን ብቻ ሲመቱ ነው የሚያመን? የመኢአድዋ ወ/ሮ መሶብወርቅ ሲታሰሩ ምነው አልተናገርን አንድ እንሁን ማለት እኮ ለሁሉም እኩል እንጩህ ማለት መሰለኝ:: ብርቱካንን የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቅልን:: ለኛም ልቦና ይስጠን በተለያየ ድርጅት ውስጥ ሆነው ከወያኔ ጋር የተናነቁትን ሁሉ በተለይ ውጪ ያለነው በአንድ አይን እንያቸው ያን ጊዜ ነው አንድነቱ የሚመጣው እንጂ እኛን ሲመቱን ብቻ እናንተም ጩሁ ቢባል በቂ አይመስለኝም:: አመሰግናለሁ::
እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያ ሕገራችንን ይጠብቅልን::
Dear Girma (Muzikye),
Please lead by example by stopping your constant attack on Eng. Hailu Shawel.
አቶ ተድላ አስፋው,ወያነም ሆነ የወያነ
አላማ መቃወም ሌላ ነው.መብትዎም
ነው.ስለ ቴዲ መታሰሩ ህጋዊ አይደለም
ሲሉ ሲከራከሩለት ስለዘላለማዊ ሙዋቹ
ደጉ ምንም አላሉም አዎን ድሃ በመሆኑ ሊሆን ዪችላል. ሁለተኛ,ወይዘሮ
ቢርትኩዋን ለበደልኩት ህዝብና መንግስት ይቅርታ እጠይቃለሁኝ,በዲየአለህ ብላ ስትወጣ
መካድዋ አግባብነት አለው እያሉ ነው.
ለክህደት ማበርታታት ምን አመጣው.
ብዙ ግዜ ጽሁፎትን አነባለሁኝ የተማሩ ይመስሉኛል ለማንም ይሁን ለማንም ሲሳሳት ኖ ተሳስተሃል ብሎ መናገር ለሚወዱት ሰውና የፖለቲካ ድርጂት ጥንካሬ እንጂ አያደክመዉም.በእውነት ለሰላምና ለፍቅር ከቆሙ.ግን አይመስለኝም ባይ ዘወይ መንገዱ ጨርቅ ያርግላቹህ.
E, you wrote ” I knew that you were one of the individuals strongly attacking Ginbot7 for choosing different approach for the struggle. Are you ready to say sorry for the public? Atleast we have to start to admit our mistakes.”
You are right . I criticised Ginbot 7 a lot. However my criticism was not because they chose whatever struggle strategy they plan to use. IT IS ALL THEIR RIGHT. The problems I had is with the campaign from their part to discredit the peaceful struggle and what the UDJ is doing back home. When we see misinformations we had to make sure it was corrected. That may seem an attack against Ginbot 7 but as they say the peaceful struggle does not work we have to rebut and defend against those lines of tought by presenting also our case.
That is why among my recommendation that we stop argue about struggle strategies. I have hope that Ginbot 7 will be careful and use its influence to make sure we avoid distructive comments and propoganda from its supporters like Awramba Times.
Let Ginbot 7 does what it plans to do. Let those who are waging peaceful struggle do the same. This way there will be no contention between us. (EPPF , EPRP , OLF , ONLF …there are many armed groups who are engaged in arfmed struggle. Kinijit or the UDJ never had problems with these groups. I have never heard these groups also saying the peaceful struggle does not work. These groups are doing their jobs in the fields in their own way…So we want Ginbot 7 to be like that as well.)
Once we have stopped fighting and arguing on petit matters we can focus working together on items that we agree on.
As to AEUP, as Ato Tedla wrote there is no reason why they do not at least coordinate their efforts. Basically their political programs and objectives are the same. Their type of struggle is the same. I am hopeful some real success also will be seen in this regard.
My recommendation is for each one of us including Ginbot 7 and AEUP to do a rethinking in the way we deal with others. I have listened Dr BErhanu NEga. I have also listened Ato hailu Shawel. Both seemed to be outraged by what is happening on their former Kinijitites Prof Mesfin and W/t Birtukan. I liked what they have they said so far. I am sure these two leaders will do their best to bring Ethiopians together again.
Mistakes were made in the past by all of us. PLEASE LET US NOW FOCUS ON THE FUTURE.
Mr Girma:
You were advising ethiopians to stop insulting and disrespecting TPLF system lead by meles zenawi the very first enemy of the nation many Ethiopians concluded. Now, you seem to came back to your sense. Which is good. next time stop driven with delusion. politic doesn’t build by delusion. Start to say a spade spade, then your way will be clear to where you will beading. This time, you seem to came back to the what you call it normal sense. thansk any way. We have so many of them like you who simply were driven with emotion trying to be deplomat to a dangerous beast like the hyena that is eating Bertikan and many million opposition leaders before her. Those who were victims of these hynas should have been lesson to many of you who were advocating not to disrespect the hyna. But, time is good, every one will learn from time.
ethiopiansemay.blogspot.com
አቶ ግርማ አስተያየትዎን አከብራለሆ የግል ኣመለካከትሆ ስለሆነ:: ነገር ግን ማለት የምፈልገው ባለፈው ባቀረቡት ጽሁፍ ላይ ግንቦት7ን በተመለከተ የስጡትን ኣስተያየት አቀራረቡ ገንቢ ያልሆነ ነው በጣም ግን የገረመኝ ግንቦት7 በኣንድነት የሚካሄደውን የሰላማዊውን ትግል (discredit) ያደርጋል ብለዋል ከዚሁም ጋር በማያያዝ ደጋፊው ኣውራአምባ በስጠው ኣስተያየት በማለት ድርጅቱን ሀላፊነት እንዲወስድ ኣደረጉ በመጨረሻ ደግሞ ዶ/ር ብርሃኑ ከኣሁን በሆላ ኢትዮጵያን አንድ እንዲያደርጉ አሳስበዋል እስከአሁን ያደረጉትን ትግል ጥያቄ ውስጥ ማስገባትዎ ይሆን ?
አየ የናንተ ነገር እግዝአብሂር እንደሆነ አገሩ ትግራይ,ዘውድ ከሆነ ያው ቤቱ ትግራይ ነው,ሱሬም ሌላ ኣገር የለውም እስኪ የአማራ ብሔር ሌላውን ለመግዛት ሲሞክር ያሳያችሁ;; 150 ኣመት ወደሁዋላ ሃገሬ ኣስኼዳችሁ ኣሁን ሜዳ ላይ ጅብ እንዳይበላቹህ አርፋቹ ተቀመቱ ዋዋዋዋዋዋዋዋዋዋ
የኛ አገር ፖለቲከኞች እና አደራጅ ወይም(support group) ነን ባዮች አቶ ግርማን ጨምሮ ለብዙ ጊዜ የታዘብኩት ችግር አለባቸው:: ይሔዉም አቁማቸዉን በየጊዜው የሚቀያይሩ መሆናቸው ነው:: አንድ ሰው በሃገሩ ጉዳይ ላይ ለመሳተፍ ሲነሳ በቅድሚያ ለራሱ ቋሚ መመሪያ ወይም መመሪያዎች ሊያወጣ ዪገባዋል:: ለምሳሌ- የአንድ ተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ልሆን የምችለው ካልደገፍኩም ደግሞ እንደጠላት የማልቆጥረው ድርጅቱ ቢያንስ ቢያንስ በምን ላይ የተመሰረተ ሲሆን ነው ወይም ምን ምን ሲያሙዋላ ነው::
እንደምሳሌ ከላይ የጠቀስኩትን እንደ ቋሚ መመሪያ ያደረገ ሰው የፈለገዉን ያህል በማንኛዉም አመራር ወይም አመራሮች መሃከል ግጭት ሆነ መነታረክ ቢፈጠር የሚፈልገዉን የሚያቕ ደጋፊ ስለሆነ በየጊዜው የመዋዥቅ ምልክት አይታይበትም:: መሪ-ነን ባዮች እንደፈለጉ የሚሽከርክሩት ሳይሆን የሚፈልገዉን የሚነግራቸው ሆኖ ይገኛል ማለት ነው:: ስለዚህም አንድነት የመሻቱ ጉዳይ በድርጅቶች መሃከል ሳይሆን በደጋፊዎች መሃከል ዪሆናል ማለት ነው::
ለዚህ ማጠናከሪያ ምሳሌ የሚሆነው: ግንቦት ሰባት ሲመሰረት አንዳንድ ደጋፊዎች ከላይ ለምጥቀስ እንደሞከርኩት “ልደግፈው የሚቻለኝ ድርጅት ነው ወይ? ወይስ ደግሞ እንደጠላት እንዳልቆጥረዉ ሚኒመም የምላቸውን መመሪያዎቼን ያሟላል ወይ?ወይስ ጠላት ነው ወይ?” የሚለውን ጥያቄ ከመጠየቅ ይልቅ: ቢዙዎቹ ፖለቲካ ወዳጅ ብዮች ግንቦት ሰባትንና አንድነትን(ቅንጅትን) በማይገባው በማነጻጸር የሁለቱም ደጋፊዎች አላስፈላጊ አታካራ በመግባት ትግሉን አዳክመዉታል::
ታዲያ በጭንቅላታቸዉ ውስጥ የሚዘዋወር ኬሚካል ያለ ይመስል አንድ ነገር ሲፈጠር አንድ እንሁን እያሉ ያወራሉ! ይታያችሁ! መጀመሪያ ማነው አንድ እንዳንሆን ያደረገው? መቼ ነውስ የሚማሩት? በደጋፊ ስም በደላቸዉን እርስ በራሳችን ማናቆሩን ይተዉን እንላለን!!
ከላይ በጻፍኩት ጽሁፌ “መመሪያ” በሚለው ምትክ “መስፈርት” ቢተካ የበለጠ የሚገባ መሰለኝ:: ይቅርታ የችኮላ ጽሁፍ ስለሆነ ነው::
Ato Girma,
I do respect your personal ideas. However, i just can not understand why you can not understand the SIMPLE FACT that peaceful struggle does not work in Ethiopia. Let me tell you once again; IT JUST DOES NOT WORK WITH TPLF!!!! I just do not think that it is necessary to list the reasons behind this simple fact all the time. It is time to advocate the only option left on the table to remove the cannibal regime; Armed struggle.
Ato Girma,
Once again - my advise to you is that first admit Woyannie is a formideable enemy. Second pls. regonize the fact that the TPLF is too much for one party only. In that case you may have to stop attacking the AEUP & Eng. Hailu Shawel. Like it or not the AEUP is the only genunie strong party - with 5 million membership and a well established leadership. One way or the other - we need the AEUP to be the backbone of any movement in Ethiopia. Stop being hostile to the AEUP. That goes to Abugida.com, Ethiomedia and Ethiozare. They are serving the enemy by attacking the AEUP and praising Siyie Abraha, now they are all left alone.
We have to unite to fight for the release of Birtukan and other poltical prisoners.
Dear musiku nothing is new ,we have said this for a
long long time , thx God at
last u oppend your eyes and saw the reality.U have the right to belive in what u think ,but we tell u again again weyane must be forced by any means to kneel dawn for the will of the ppl.we can not get our freedom as a gift from the weyane ethnic dictators. wish u the best and i hope next year u will see the reality more and join the struggle with all your heart.
Dear musiku nothing is new ,we have said this for a
long long time , thx God at
last u oppend your eyes and saw the reality.U have the right to belive in what u think ,but we tell u again and again weyane must be forced by any means to kneel dawn for the will of the ppl.we can not get our freedom as a gift from the weyane ethnic dictators. wish u the best and i hope next year u will see the reality more and join the struggle with all your heart.
አቶ አርዓዶም (አር…)የ አቶ ግርማን ጽሁፍ አንብቤዋለሁ
ነው ያልከው? አላማቸው ጥፋት ለሆነ እና ለወያኔወች የቁልቐልፍሬ እንደመብላት አይቀላቸውም…እርግጠኛ ነኝ …ይገባሃል
አቶ አርአያ ሱሪ የሚጠቅመው ምርቱ የተነሳ አውድማ ለመጥረግ ከሁነ ፤ አወ የለንም
አቶ አርዓዶም የሹሩባ ሰሪ ልጅ ነህ እንዴ ያልተባለ ትገምዳለህ
I see only one enemy for all Ethiopians and our country, which is TPLF. Why we are discredited each other, enstead stand to fight TPLF by united our resources. Please, do not down each other. Bring good ideas how we can stand together and fight for the survival of our beloved country.
“የኛ አገር ፖለቲከኞች እና አደራጅ ወይም(support group) ነን ባዮች አቶ ግርማን ጨምሮ ለብዙ ጊዜ የታዘብኩት ችግር አለባቸው:: ይሔዉም አቁማቸዉን በየጊዜው የሚቀያይሩ መሆናቸው ነው:: ”
የአንድነት የድጋፍ ድርጅቶች አንድ ግልጽ አቋም አላቸዉ:: ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረጉትን ሰላማዊ ትግል ይደግፋሉ:: ሁልጊዜ በኢትዮጵያ ሰላም ዲሞክራሲ እርቅ እንዲመጣ ይታገላሉ:: ይህ አቋማቸዉ አሁንም አቋማቸዉ ነዉ:: የአቋም ለዉጥ የለም የኔ ወንድም::
“ሰላማዊ ትግል አይሰራም:: አቶ ግርማ አይገባህም ወይ” ብላቹህ ለጻፋቹህ ምላሽ አልሰጥም:: የሰላማዊ ትግል አካል ነኝ:: የትጥቅ ትግል ካላቹህ ግርማ ወይንም እንደ’እኔ ያሉ ወገኖች አልያዝናችሁም:: ባካቹህ ተዉን:: ስራችሁን ስሩ ; ዉጤት አሳዩ:: እኛም ስራችንን እንስራ::
በመጨረሻ መጠቀስ የምፈልገዉ አሁንም ወደ ፊት እንድንመለከት ነዉ:: የህውላዉን እያነሳን እንነጋገር ከተባለ ጎበዝ እኛም ልናወጣቸዉ የምንችላቸዉ ፋይሎች አሉ:: ነገር ግን አይበጅም:: ልዩነተቻችን የሚያጣላን ነገር እያነሳን ወደ ታች አንቀበር ነዉ የምንለዉ::
ሥራ ላይ የወደፊቱ ላይ እናተኩር::
እግዜር ይስጥልኝ !
ethiopia ye tigray mefencha ke honech senbitalech engidih wond yehone yimokiren blewal enna gizew ruq aydellem lezyach ken ennizegaj be kum ke memot ye jegninet mot yimerretal gobez is kemeche new gotegnochin ishirur yibka
አቶ ክፍሌ የሹርባ ሰሪ ልጅ አልከኝ አመሰግናልሁኝ,ብሆንም ምን ችግር አለው ስራ ነው.የተቃዋሚዎች ወይም ፖለቲከኞች ነን የሚሉ ሰዎች ያው እንዳንተ የመሳሰሉት ችግሩ እኮ ይሄ ነው.አንተን ይዞ ጉዞ ለድል ያደርሳል .
ባሻ ቅጣው ምንም አያምርብህም,ያው የሆንክ ቀዳዳ ነገር ትመስላለህ ባልገባህ
ነገር ትዘባርቃለህ.ፖለቲከኛ ለመምሰል
ነው እምትሞክረው ሳይህ ግን ዘሮ በስሜት የምትነዳ ማንም አዋቂ ነኝ ብሎ የሆነ መፈክር ካሰማ ከሱ ጋር የምትነጉድ ፉጥር ነህ በተለይ እንግሊዝኛ ከተናገረ አበቃልህ.አያርግልህ እንጂ እንደ ሰልሞን ተካልኝ ሳታቀዉም ትበራልህ.
))))))))))ተብሎ ያለቀለት ነው።(((((((((((((
ሕግ ለምን በማን እንደተጣሰ በግልፅ የሚታይ ነው።አቶግርማ ብዙ የሚያሳዝኑ ድርጊቶች በኢትዮጵያ ምድር የተፈፀሙና እየተፈፀሙ ናቸው።እባክዎ ይህንን ችሎታዎትን ወደሌላ ተግባር መፈፀም የሚያስችል አዳዲስ ሃሳቦች ላይ እናውለው።በተለይም ለእነ”አርዓዶም” በጥብጠው ብናጠጣቸው ሐቁን እንዲቀበሉ የማያደርጋቸው ሁኔታ አለና በጊዜዎ ባይቀልዱ ይበጃል።
ይልቅ አዳዲስ የግልና የጋራ ተግባራዊ ነገሮችን ለማድረግ ቆርጠው ይነሱና እኛም እንካፈል።
የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቃታል።ላክ ይጠብቃታል።
ሰለሞን ነው ያልከኝ?አቶአር..፤ማን ነበር.ር.ር
ዐ.ዐ ትዝ አለኝ አርቆይ እሱ ሰውየ ክንፍ አወጣ! ነው የምትለኝ?
ዋ! ሰዉየዉ ከክንፍም ጭራ አለዉ እሱ ጅብ ነዉ እንኽን ሔደልን::
ጝርማ,
You have destroyed one unity and now you are trying to form another. What a useless person you are. Death to Meles. And shame on the likes of Girma
አርአዶም:- እዚህ ውስጥ አንተን ምን አገባህ?
የሚወያዩት በሙሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው:: አንተ ምን አንደሆንክ ከቃላት አጠቃቀምህ ያስታውቃል:: ተነቅቶብሃል!
አፍህን ዝጋ::