በቀለ ጂራት ተፈቱ - ብርቱካን ጠ/ሚኒስትር መሆን የምትችል ናት አሉ ዶ/ር ቡላቻ
አቡጊዳ / ጥር 27 ቀን 2001 ዓ.ም
የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ አቶ በቀለ ጂራታ ዛሬ በዋስ ተለቀቁ። «ከኦሮሞ ነጻ አዉጪ ግንባር ጋር ግንኙነት አለህ» በሚል ክስ ገዢዉ ፓርቲ ሕግ ወጥ በሆነ መልኩ እኝህን የሰላማዊ ትግል አካል የሆኑትን ኢትዮጵያዊ ለወራት ማሰሩ ከኢትዮጵያዉያን ዘንድ ከፍተኛ ተቃዉሞ ማስነስቱ ይታወሳል።
በተለይም በአለም አቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያዉያን በተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች አቶ በቀለ ጂራታ እንዲፈቱ ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ሲሆነ የተለያዩ የፖለቲካና የሲቪክ ማህበረሰብ በግልም ሆነ በጋራ ጠንካራ መግለጫ በማዉጣት እኝህ ሰላማዊ ታግይ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታና በአስቸኳይ እንዲፈቱ መጠይቃቸዉ በሰፊዉ ተዘግቧል።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ፓርቲ ሊቀመንበር የተከበሩ አቶ ቡላቻ ደመቅሳ በአቶ በቀለ ጂራታ መፋታት በጣም የተደሰቱ እንደሆነ ለሮይተርስ የገለጹ ሲሆን «አቶ በቀለ መጀመሪያዉኑ መታሰር አልነበረበትም። ምንም ጥፋት አላደረገም » ሲሉም ገዢዉ ፓርቲ የወሰደዉን እርምጃ አዉግዘዋል።
ዶ/ር ቡላቻ ሌላዋ አንጋፋ የፖለቲካ መሪ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳም በአስቸኳይ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ የጠየቁ ሲሆነ « ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ያሰሯት ጠቅላይ ሚኒስተር መሆን የምትችል ጠንካራ መሪ እንደሆነች ስላወቁ ነዉ» ሲሉ ለወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ያላቸዉን ትልቅ ግምትና ክብር ለሮይተርስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ገልጸዋል።
በቅርቡ የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ባለሥልጣን ካርተር ፊሊፕስ አዲስ አበባን ጉብኝተዉ ከአቶ መለስ ዜናዊና ለተቃዋሚ መሪያዎች ጋር መነጋገራቸዉ ይታወሳል። የአቶ በቀለ ጂራታ መፈታት ከዚሁ ባለሥልጣን ጉብኝት ጋር የተገናኘ ነዉ የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች ሕወሃት በቅርብ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳንም ሊፈታ እንደሚችል ይናገራሉ።
ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ጠበቃቸዉን ያነጋገሩ ሲሆን ያሉበት ሁኔታ እጅግ የከፋ ቢሆንም በመንፈሳቸዉ በጣም የጠነከሩና የበረቱ እንደሆነ ከአዲስ አበባ ለመረዳት ችለናል።



አሳሪም ፈችውም መለስ ከሆነ ህጉ የተጻፈውብ ለማን ነው?
ሰልፉን እንዳይወጥዓ ምንም አታመጥዑም ላሉትና ወደፊትም ለሚሉት ትልቅ ለውጥ ነው አሳረና ፈቺ የሆነውን ወያኔ ማንነቱን ማጋለጥ አሁንም ይቀጥል ብርቱካን እስክትፈታም ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እስኪፈታ የምንችለውን ሁሉ ባለን አቅም እንበርታ::
አቡጊዳዎች በታም እናመሰግናችሁል::ወያኔ ሕዝባችንን ለማሰቃያት የሚያደርገው ጥረቶች ሁሉ በ ህዝባችን ትግል ይከሽፋል!!!
አይመስለኝም ወያኔ መሰሪ ነው ሰውይውን የፈታው ብርቱካንን እዛ ለማቆየት ነው በአቶ በቀለ መታሰር ትልቅ ነገር ሆኖ ችግር ስለፈጠረ ነው ለወያኔ አቶ በቀለ ምንም የማይጎዱ መሆናቸው ይታወቃል ወያኔ የፈራው ብርቱካንን ነው
I think Ato Bulcha is not a Doctor. So, the editor should check the title.
Dr Bulcha or Ato Bulcha? Need correction! The news is encouraging!
Thanks!
የአቶ በቀለ መፈታት አስደሳች ነው:: ይህ ግን ክፍሌ እንዳለው “የኢትዮጵያ ሕዝብ እስኪፈታ” ከምናደርገው ትግል ሊያዘናጋን አይገባም::
80ው ሚሊዮን ገና አልተፈታምኮ!
በገዛ ሀገሩ በክክልል:በቋንቋ ተገድቦ ይኖራልኮ!
ራበኝ!ጠማኝ! ማለት እንኳ ወንጀል በሆነበት ሀገር ነውኮ የሚኖረው
ሰዎች ሲያረጁ ኣስታራቂና መላ የሚፈልጉ መሆን አለባቸው:: ምነዉ ታዲያ አቶ ቡልቻ (ዶክተር)ባይዘብርቁ:: ስልጣን ሀገር መምራት የምቻለዉ በምርጫ ንዉ::
አቶ ቡልቻ አልዘባረቁም;;መሪ የመሆን ችሎታ ማለት:-ሳትመረጥ ትሆናለች ማላታቸው እንደወያኔ እዳይመስልህ;;
Anonymous, ምነው የዴሞክራሲው ነገር በጣም ስለገባዎት ከአንጎልዎ አልፎ ሄደ እንዴ?? kkkk
Opposition leaders
Dr. Birhanu, Dr. Merara, Dr. Beyene, Dr. Yakob, Dr. Negaso, Dr. Hailu, then …..Dr. Bulcha…… tomorrow Dr. Birtukan….. ????????
አቶ :ቡልቻ :ምነዋ!! ማሞ:ሌላ : መታወK ያው :ሌላ::እየተሰተዋለ:!!!!!!!
-ሊሊ what about opposition leadres
Eng. Hailu, Eng. Eayssu,,Eng.Bedru , Eng(dr.)Taye, Eng. Lidetu(Kidetu), Eng.Mosebwork…………….kkkkkkk,
እባካችሁ አንዱን ከሌላው ከማበላለጥና ከተምታታ የፖለቲካ ግምገማ ውስጥ አንግባ. የአሜሪካ መልክተኛ እገሌን አስፈታው እገሊትን ተዋት ማለት ምን ማለት ነው? ምን ማስረጃ አለህ?
አሜሪካን ባለበት እንተወውና የኛን ትግል እናጠናክር. መዘላለፍ ይቅር. ቡርቱካን ትፈታለች!!!!
ሊሊ ዎያነ መምበር prmate mellese baghdad bob bereket old gangster aboy sebhat criminal abay tsehai looter seyoum mesfin illitrate aba dula las but not least cowboy with pistol aba gebre medin
ይህ ዶክተር ማንትሶ ኢንጂነር ማንትሶ የሚባል ቅጽል ስም ከፊውዳሉ ስርአት የተቀዳ ይመስላል::ለመሆኑ ዶክተር ማንትሶ ስንል ምን ለማለት ፈልገን ነው? ሃኪም ወይስ የትምህርት ደረጃ ለማመልከት? አሜሪካ ውስጥ ሰዎች በቅጽል ስም ሳይሆን የሚጠሩት በተጸውኦ ስም ነው::የእኛው አጠራር የሁዋላ ቀርነት ጠቁዋሚ ይሆን? ወይስ ገበሬ እከሌ ሸማኔ እከሌ ጠንቁዋይ እከሌ ወዘተ እንድንል ሊዳዳን ነው?
ዶክተር ማንትሶ ኢንጅነር ምንትሶ ለሚሉት ለተባለው እንደወያኔ ሰውን ለማሥፈራራት ሳይሆን,ሃሳቸውን በአካዳሚክ ፍሪደም እዲተበይኑ ነው ;;ሌላው ምንጆ ጃንቦ ነው በ እውነት;;
ውድ ወገኖቼ:- በሰለጠኑት አገሮች ሰዎች እንደ እኛ ሰዎቻቼውን በትምህርት ባገኙት ማእረግ አበክረው አይጠሩም:: በእኛ አገር
ግን የበዛ የሰለቼ ነገር እየሆነብን ነው የመጣው:: ወንዱን አቶ ሴትዋን ደግሞ ወይዘሮ/ወይዘሪት በማለት መጥራት ይገባናል::
አሥፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ግን እንደ ፈረንጆቹ አጠራር :- አቶ ዶክተር/ወይዘሮ ወይንም ወይዘሪት ዶክተር እግሌ/እገሊት ብለን
ልንጠራ ይገባናል:: ይህ የትምህርት ደረጃ ማእረግ የመነጨውም ከእኛ ሳይሆን ከውጭ አገሮች ነው:: ይህን ጉዳይ በተለይ ማስ ሚዲያውና ትምህርት ቤቶች ትኩረት ሊሰጡት ያስፈልጋል:: በተረፈ ሁሉም የህሊና እስረኞች ሊፈቱ ይገባል:: በጋራ እንቁም ልጋራ አላማ::
ኣስኪ ወጎነቸ ወያነ ምን ሊሆን ነው የሚፈሊገው ለምን የኣትዮጵያን ሕዝብ ምን በደለው
ይሀ መንግስት የኣትዮጵያ ጠላት ነው::
ኣቶ በቀለ መፈታታቸው ደስ ብለውናል:: ነገር ግን 40 ሺህ ህዝብ አሁንም እስር ላይ ነው:: ቀሪው ደግሞ ነጻ እስክ ወጣ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል !!!
እናሸንፋለን እንበርታ ወገኖቼ !!!!!