መድረኩ - በብርቱካን ላይ እነ መለስ የሚነዙትን ቅስቀሳ አወገዘ !

February 21st, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

አቡጊዳ / የካቲት 15 ቀን 2001 ዓ.ም.
መድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ ትላንት ባወጣዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የታሰሩት ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ እንደሆነ በድጋሚ አረጋገጠ።

መድረኩ « የወ/ት ብርቱካን ዳግም መታሰር በሽምግልና ተፈቷል የተባለለትን ጉዳይ ወደ ኋላ የሚመልስ፣ ሃሳብን በነሳ የመግለጽ መብትን የሚጥስ እና ሕግንና ስርዓትን ያልተከተለ እርምጃ መሆኑን በድጋሚ ይገልጣል» ሲል ነበር በመግለጫዉ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ጉዳይን እንደ ትልቅ ዋና አጀንዳ አደርጎ ያቀረበዉ።

በቅርቡ አቶ መለስ ዜናዊ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰር የሕግ የበላይነትን ማስጠበቅ እንደሆነ ሲናገሩና ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እራሳቸዉን መከላከል በማይችሉበት ሁኔታ ከአምሳ ቀናት በላይ ጨለማ ቤት በግፍና በጭካኔ እንዲቀመጡ አስደርገዉ የርሳቸዉን ስም በአደባባይ በትዕቢት ሲዘልፉ መሰማታቸዉ ይታወሳል።

መድረኩ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ጥፋተኛ ለማድረግ በአደባባይ ርካሽ ቅስቀሳ ለሚያደርጉ ለእንደ አቶ መለስ ዜናው ላሉ ግለሰቦች በሰጠዉ ምላሽ « የእርሳቸዉ (ወ/ት ብርቱካን) ቃል በታፈነበት ሁኔታ እርሳቸዉን ጥፋተኛ ለማሰኘት እየተደረገ ያለዉን ቅስቀሳም ያዉገዛል» ሲል በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ የተከፈተዉን ጸረ-ዲሞክራሲና ሕገ ወጥ ድርጊት አጋልጧል።

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ አሁንም በጨለማ ቤት ሰዉ እንዳያገኙ ተደርጉ ኢሰብአዊ በሆነ መንገድና በጭካኔ የታሰሩ ሲሆን ሕገ መንግስቱ እንደሚፈቅደዉ ጠበቃ፣ ሃኪም ፣ መንፈሳዊ አባት የማየት መብታቸዉ እስከአሁን መነፈጉን ለማወቅ ችለናል።

ወ/ት ብርቱካን መታሰራቸዉ አግባብ እንዳልሆነና ጉዳያቸዉ ፍርድ ቤት መዉሰድ እንደሚፈልጉ ከዚህ በፊት መጠየቃቸዉ ይታወሳል። የአቶ መለስ አገዛዝ ግን አሁንም ሕገ መንግስቱ የሚደነግገዉን መብት እየገፈፈና ሕግን በራሱ እጅ እንደፈለገ እየጨፈላለቀ፣ እዉነት ከኔ ጋር ነዉ የሚሉት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ፍርድ ቤት እንዳይቀረቡ ከልክሏል።

መድረኩ በመግለጫዉ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ጉዳይ አንስቶ በርሳቸዉ ላይ እየተደረገ ያለዉን ግፍ በድፍረት ማወገዙ ተገቢና አስፈላጊ እንደሆነ የገለጹልን ያነጋገርናቸዉ የፖለቲካ ተንታኞች ፣ ወደፊት መድረኩ በሚያደርጋቸዉ እንቅስቃሴዎች የእኝህን ቆረጥ ሴት መፈታት ቀዳሚና አብይ ትኩረት ሰጥቶት መጓዝ እንዳለበትም ይናገራሉ።

  1. Dama
    February 21st, 2009 at 07:12 | #1

    መድረኩ ሊጠናከር ሊበረታታ ይገባዋል::

  2. አንበሴ
    February 21st, 2009 at 08:20 | #2

    በመጀመሪያ ነገር ወያኔን አምኖ በዚያ ፓርላማ አዳራሽ ከጫካ የመጡ ስታሊኖች መሆናቸውን ረሳችሁና እነርሱን አምኖ የቁራ ጩኸት ማሰማት በኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ ዲሞክራሲ ያለ አስመሰለ: የአለም ሃገሮችም እውነት መሰላቸው: እውነቱን የምናውቀው ግን እኛው ኢትዮጵያውያን ብቻ ነን:: አይናችን እያየ ነውኮ ሃገር የተገንጠለው: አይናችን እያየ ነውኮ ንጹሃን እየተገደሉና እየታሰሩ ያሉት:: ወያኔን ለማስወገድ እነርሱ በሚመጻደቁበት ሁሉን አቀፍ ትግል ነው አማራጩ:: በፓርላማ ውስጥ መቀመጥና ማጀብ አሁንም ቢሆን ወያኔን በርታና ግረፈን ግደለን አሰቃየን የማለት ያህልና በዚህ በድህነት አረር የሚሰቃየውን ህዝብ ዝም ብለህ ተገዛ ተከፋፈል ተገነጣጠል የማለት ያህል ነው:: በወይዘሪት ብርቱካን ላይ የሚደረገው አሳዛኝ ድርጊት በበለጠ ሁኔታ በየእስር ቤቱ እንደሚደረግ ነው የሚታወቀውና ማውገዙ ብቻ ምንም ፋይዳ የለውም:: መላው ተቃዋሚ ድርጅት ወያኔን በፓርላማ ማጀቡን ትቶ ሁሉን አቀፍ ትግል ከሚያደርጉት ተቃዋሚ ድርጅቶች የግንቦት7 ንቅናቄ ጋር ዛሬ ነገ ሳይሉ እንዲዋሃዱና የሃገራችንን ህዝብ በአንድነት በቆም ወያኔን መንግለን እውነተኛ የኢትዮጵያ ህዝባዊ መንግስት እናቋቁም:: ወያኔ የስታሊን አራማጅና ጭካኔያዊ መንፈስን በጫካ አዳብሮ የመጣ የወንበዴዎች ስብስብ መህኑን ዘንግታችሁ በፓርላማ የምታጅቡ ሁሉ ልትገነዘቡ ይገባል እላለሁ::
    ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!!!

  3. በቃ
    February 21st, 2009 at 09:41 | #3

    ፍረድ በወ/ት ብርቱካን ላይ ለመፍረድ ቀርቶ ፍርድ የሚባለውን ወያኔ የሚያውቀው ቢሆን ይሄንን ሁሉ ባልን የደቡብ አፍሪካ ከንጻነት በፊት ዞሮ ካፍሪካ እንዳይወጣ በአፍሪቃ ቀንድ ባቶ መለሰ በኩል ነግሶአል ለዛውም በገዛ ዜጎቻቸው ላይ ታዲያ እኝህ ሰው ሰው ናቸው ወይንስ ሰይጣን ዘር ሳይኖራቸው አይቅርም ከዲያብሎስ ማለቱ ሳይቀል አይቀርም የአኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ተነሳ እንደ 66ቱ ባንድላይ ትመም አስውግደው ነው የምልህ ዲሞክራሲያዊነት በትግላችን በድማችን ይረጋገጥ እንደ ኬነያ ና ዚንቡአቤ ተነስ !!!!!

  4. ፊሊ
    February 21st, 2009 at 10:20 | #4

    እንኳን ደስ አልሽ መስረት

  5. Great appreciation to the well-determined and principled leaders of UJDP. Keep it up together with the people of Ethiopia !!!
    February 21st, 2009 at 12:33 | #5

    መክብብ 3- 1- 10
    ለሁሉም ጊዚ አለው , ለመሳቅ , ለማልቅስ , ለመታስር , ለመልቀቅ , መልካም ተግባር ለማድረግ , ለማፍረስ , እናም ወ / ሪት ቡርቱካን ላይ እየተደረገ ያለው ሥነ ምግባር በጎደላችው ና በዙሪያችው ለሆዳችው ባደሩ ካድሮች የሚሆነው ነገር ለጊዘው ይሆናል , ግና ግን ያቺ ቀን ታልፋለች , ለ 400 ዓመታት የተግዙት እሥራዓላዊያን ቀንበራችው እንደተስበረ ሁሉ ምድራችንም አሁን በእ/ር ፊት ታልቅስ , የምዕራቡ , ወይም የአማሪካኑ ሕዝብ እኛን ነጻ ሊያወጣን ኣይችልም ገና የሚመዝብሩት ነገር ስላላቀ ተልካችው ወያነው ዕድማ ማራዝም መሆኑን ልናስተውል ይገባናል , ስለዚህ ሀገራችንን ነጻ ማውጣት ያለብን መስራት ያለብት ሥራ ተባብርን በመሥራት ስለሆነ እኛም እንደ ነህሚያ 2 - 20 የስማይ ዓምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተንስተን እንሥራለን , ምድራችንን ተነስተን የምንሰራብት ጊዛ ሩቅ እንደማይሆን እር በጸሎታችን እንትጋ

    ካንሽ / ከአውርፓ

  6. ዓቢይ
    February 21st, 2009 at 14:48 | #6

    በመድርክ የተሰባሰቡት የጀግናዋን እህታችንን ጉዳይ ማንሳታቸው ግድ ነው. ነግ በራሴ ነውና.
    ዛሬ በኢትዮ መዲያ ፎረም የወጣውን ጽሁፍ ያላነበበ ካለ, በግድ ማንበብ አለበት. ይሽምግልናውን
    እርቅ ሁኔታ መስታወት ሆኖ ያሳያል.የ”ቁጭበሉ መለስንና ይሽማግሎችን” ጉዳይ ስታንብቡ,
    ምነው እንደዚህ አይነት መልቲ ከተፈጠረበት አገር ባልተፈጠርሁ ያሰኛል. ወደፊትም የዚህን ተራ ቀጣፊ አስተዳደር ተማምኖ በሰላም እታገላለሁ ማለት የራስንም የደጋፊዎችንም ጊዜ መግደል ነው.
    ተራ አጭበርብሪው መለስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማታለሉን አምኖ,ይቅርታ ጠይቆ ወይ.ብርቱካንን እስካልፈታ ድረስ በሰላም እታገላለሁ እያለ ራሱን የሚያታልለው ሁሉ መንገዱን በጊዜ አስትካክሎ
    አማራጭ ለለው ፍልሚያ መዘጋጀት አለበት. ከዚህ የወውጣው ጊዜ ማባከን ነው.አራት ነጥብ.

  7. ታዘበ
    February 21st, 2009 at 14:53 | #7

    አሁንም እንደ ትናንቱ የሕግ የበላይነት ላይ እየተንጫጫን ነው::መች ይሆን ከጫጫታ ወደ ተግባር የምንሽጋገረው? በአንድነት መቆም ምላሽ የሚሰጥ መሆኑ እንዴት አይገባንም? የሕግ የበላይነት ጥያቄ ማንሳት የሚቻለው በሕዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ መንግስት ሲኖር ነው::አሁን እንደሚታየው ከሕዝብ ፍላጎት ውጭ ያለ መንግስት ነው::መፍትሔ እንጂ የነገር ስንጠቃ የትም አያደርስ::

  8. ታዘበ
    February 21st, 2009 at 14:56 | #8

    አሁንም እንደ ትናንቱ የሕግ የበላይነት ላይ እየተንጫጫን ነው::መች ይሆን ከጫጫታ ወደ ተግባር የምንሽጋገረው? በአንድነት መቆም ምላሽ የሚሰጥ መሆኑ እንዴት አይገባንም? የሕግ የበላይነት ጥያቄ ማንሳት የሚቻለው በሕዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ መንግስት ሲኖር ነው::አሁን እንደሚታየው ከሕዝብ ፍላጎት ውጭ ያለ መንግስት ነው::የጋራ መፍትሔ እንጂ የነገር ስንጠቃ የትም አያደርስ::

  9. ትእግስት
    February 22nd, 2009 at 01:21 | #9

    መድርኩ ጥሩ አስተዋጾ እያደረገ ነው:: እነ “ኢ ህ አ ፓ” እስከአሁን ስለ ው/ሮ ቡርቱካን መታሰር ያደረጉት ተቃውሞ የለም:: እነ ዶክተር ታየ: እነ አቶ ኃይሉ ሳወልስ ምን ነው ዝምታ ዋጣችሁ? ለሁሉም ሁላችንም በያለንበት ድርጅት እንደ ወ/ሮ ቡርቱካን የመሰሉ መሪ ሲታሰር: ተቃዎማችንን ማሰማት ይኖርብናል::

  10. ኣንበሴ
    February 23rd, 2009 at 07:55 | #10

    ከግንቦት7 ንቅናቄ ጋር በአንድነት ሁሉን አቀፍ ትግላችንን እናድርግ በሚችሉት መንገድ ወያኔን የመመንገል ትግልዎን ያድርጉ ሃሳብ መጻፍ ብቻ በወያኔ ፓርላማ መቀመጥና ጩሀት ብቻ ምንም ለውጥ አያመጣም ወያኔዎች እየሳቁብንና እያላገጡብን ህዝባችንን እየገደሉ እያሰሩ ነውና የሃገራችንን ህዝብ ነጻ ለማውጣት እንረባረብ:: ወያኔዎች ቀድሞ የጥፋት ውጊያ ሲያደርጉ የኢትዮጵያን መበታተን የሚፈልጉ የውጭ ሃገር ሰዎች የገንዘብ እርዳታ ያደርጉ ነበር:: እርስዎ ታዲያ በጽሁፍና በኢንተርነት ሃሳብ መስጠት ብቻ ነው ወይስ ሃገርዎን ወደ ግብታዊ ትግል ለማድረግ ምን እያደረጉ ነው? ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

  11. ዋልያ
    February 23rd, 2009 at 17:56 | #11

    መድረክ አሁንም በርቱ ማለትም ..የነ ስየ አብረሀ ወይም የአቶ ገብሩ አስራት ..ቡድን አሁንም ልክ እንደ አንድነትና እንደ ግንቦት 7 የትግራይን ህዝብ በሰፊው ስለ ኢትዮ አንድነት ..ፍክር ሀይማኖት..ያስተሳሰረው ….ለአንድ ጉሩፕ…ወይም ለእነ መለስና በረከት ብሎ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ከ 65 ሚልዮን ህዝብ ጋር መለያየትና መኮራረት..እንደ አይትና ድመት በጎሳ መለያየት ህዝቡን ባከባቢው ሀደው መከስከስና …ያለበትን ፍርሃት አብረውት መታገል አለባችሀው…..እስካሁን በታም ትሩ ነው እየሰሩ ያሉት ,,,ግን ወያነ አደጋ ስለሆነ የትግራይ ህዝብ ደጋፊ ነው….ድጋፉን ካኮመ….ወያነ ፐንዱለም ነው ……መለስ ዘናዊ በሰማይ አማላድ አይሆንም….ለራሱ ሀይማኖት የለውም ……..የትም ሂዱ ማንም መሪ ንግግር ሲፈትሰሙ አገሩንና አምላኩን ያመሰግናል…..መለስና …..በረከት…ባፋቸው ያራሉ..ኧሁን የወያነ ካድረን ከ ግንቦት 7 ጋር ሆነን መብታተን ነው ከ አንድነት ጋር ድጋፋችን ..ከ ግንቦት ሰባት ጋር የበለተ መሳተፍ ….ክህድያን ዘር ሳንለይ አማራ ትግረ ኦሮሞ ደቡብ ,,,ሳንል ወያነ የሆነ ባከባቢያችሂን ባጋተመን ምችሁ ሁነታ መታገል አለብን …..እግዛብሀር ኢትዮ ይተብክልን ….መለስና በረከት በራሪ ትይት ይብላችሀው አመን ……

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።