ከዚህ በሁዋላ ለወያኔ ተጨማሪ ዕድሜ ከተሰጠው፣ ከወያኔ በላይ ወንጀለኛ የሚሆነው ተቃዋሚው ነው። (ከመኮንን ተድላ)

December 4th, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ
 1. Anonymous
  | #1

  ከወያኔ በላይ ተቃዋሚው ተጠያቂ መሆኑን ከተገነዘብን ቆይተናል

 2. አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ.
  | #2

  እንዴታ በታሪክ የተመዘገበው ዘመነ-ቅንጅትም አይረሳም::እናም በቃ ለማለት ተጨማሪ ዓመታትን በመፈለግ ሰላምን ከፍትሕ ይልቅ ሙጥኝ ማለት ብልህነት አይደለም::እናም በቃ ልንል ይገባል::

  ሁሉም ይበል በቃ።”
  ***********
  የምታውቁ ሁሉ፣…
  እንደ ተቀሰፈ የሰው ወቸገሉ:-
  በጉጅሌ ጫንቃም እንዲያ ተመክቶ፤
  ለሥጋው ሲያደላ መፈሳዊን ትቶ፤
  ሐውልት አላፈርስም እኔው ነኝ ሲኖዶስ፤
  ያለው በአንዴ ፈርሷል ያ!አባ ዲያብሎስ፤”
  እናም ዝም ጭጭ ምጭጭ በሉ፣
  የ”ሰላም ትግል ነው፣”የምትሉት ሁሉ:-
  እናም ባደባባይ ታፈሱም ይባላል፤
  የዋሁ ሕዝብ ግን፣በባንዳ ይገደላል።
  በዚህ የትግል ጎራ፣ጊዜውም ይሮጣል፤
  ጉጅሌም በጊዜው፣ቅጥረኞች ይመርጣል።
  ዛሬስ ለትግላችን ከመረጥነው ዘዴ፤
  በሰላም መረገጥ አያበቃም እንዴ?
  አማራጩ የለም?ጉጂሌው እስኪነቃ?…
  እናም ለነጻነት አንልም ወይ በቃ???
  የትግራይ ጉጂሌው አለበለዚያ ግን፤
  አዲስ ጅብ ያመጣል ራሱን ሲጠግን።
  “እሽሽሽሽሽ…ዝም በሉ፣”
  ባንዳ ጅቦች ናቸው የሚቆረጥሙን።
  “ይህም ጊዜ ያልፋል”ይልቅ እኛን ስሙን።
  ፍጹም አትበሉ ሰላማችሁ ይንቃ፤
  ለፍትሕ ይነሳ፣
  ሁሉም ይበል በቃ።
  እንየው ማለቱ በየግል አብቅቶ፤
  ማየት እንሻለን ወያኔ እጁን ሰጥቶ።
  በግል ሳንወስን ገና እንይ ስንል፤
  ጊዜውን ሲሰርቀን”ሰላም”ብሎ ትግል፤
  ለጉጅሌ ዓይነቱ ቋንቋው ለማይገባው፤
  ምንድነው ማሸርገድ ማነው የሚያነባው?
  ለነፃነታችን ዛሬም አንነቃም?. . .
  በየተራ ሲገድል እሺታው አይበቃም???
  እነሱም ይክረሙ የዋሁም ይገደል???
  በሰው ቁስል እኛ ልንል አለመታደል።
  የሚያመነዥጉት በጎች ብቻ ናቸው፤
  ከሚታረደው ደም የማይከረፋቸው።
  እኛስ እንደበጎች
  በቃላት ስን-ጠቃ፤
  ማመንዠጉን ትተን
  አንልም ወይ በቃ???
  “እሽሽሽሽሽ…ዝም በሉ፣
  የሚቆረጥሙን።”
  እኛን ስለሆነ
  በጸጥታ ስሙን።”
  ፍጹም አትበሉን ሰላማችሁ ይንቃ፤
  ለፍትሕ ይነሳ
  ሁሉም ይበል በቃ።

 3. Anonymous
  | #3

  Ato Mekonen
  I agree with you is time to stop blaming Wouane for everything & we should blame the dead opposition
  A) G7 == Fake arned struggle, ma be they are firing bullet n Cyber lol
  B) EPPF ==== Kkkkkkkkkk thy are still training in Asmara lol
  C) UDJ=== well all top UDJ leaders are back in School, I guess we all should stop the struggek and weight Nteworkun they graduate lol

 4. አንድነት ብርሃኔ
  | #4

  አቶ መኮንን ተድላ ሁልግዜ ድርጅቶችን መውቀስ የተለመደ ነው ነገር ግን መጀመርያ ራሳችንን ብናውቅ ሌሎችን ማወቅ በተቻለን ነበር (how to understand others by understand yourself)እያንዳንዳችን የተለየ አስተሳሰብና መንገድ እንዳለን ሁሉ: ሕብረተሰቡ የትግሉ ዋነኛው በመሆኑ እትግሉ ተዋንይና አታጋዮችን ማበረታታትና ወደፊት መምጣት እሚገባው ምክንያቱም ያስተዳደር ብልሹነት በታጋዮች ተወስኖ የሚመራ መሆን አይገባውም እውነት ነው የትግል ድርጅቶች ድካም ቢኖራቸውም የትግሉ ምህዳር እንዲጠብና ያላቸውን ጠንካራ የትግል ስልት ለሀገርና ለህብረተሰቡ እንዳይደርስ ኢሓዼግ ለሀያ አንድ አመት በህዝብና በሀገር ለመቀለድ የተጠቀመበት አሻጉሊት ተቃዋሚ ድርጅቶች በማቋቋም እውነተኛውን የትግል መስመር ውጤት እንዳይኖረው የተጫወተው ሚና ሕዝቡም በፍርሃት ቆፈን በሆድ አደርነት ትግሉ ውጤታም እንድይሆን አስተዋጾ አድርግውል:ይህንን ስል እኔንም ጭምር ለመወቀስ እንጂ ሌላውን አላደረግም ለማለት አይደላም: ምክንያቱም እያንዳንዳችን ጠንካራና ደካማ ጎን አለን ስለዚህ እንደኔ ጠንካራና ደካማ ጎን ያለው ሊኖርም ላይኖርም የሚል አመለካከት አለኝ; ወያነን የምንሰጠው ጥንካሬ በተቃዋሚው ብቻ ሳይሆን በውስጥም በውጭም ያላነው ዜጎች የሚያስጠይቀን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ያልቻልንበት ከተጠያቂነት ለመሸሽ የምናደርገው በትግል ድርጅቶች ድክመት መሆን አይገባም: ምክንያቱም ትግሉን ለማፋፋም ቀድምት ሆነው ክቡር ሕይወታቸውን የቤኤተሰብ ኃላፊነታቸውን እውቀትና ሀብታቸውን በመስጠት በእስር በእንግልት ያሉትን ብርቅዮ የኢትዮጵያ ልጆች ማጣጣል ሆኖ ስለሚሰማኝ አሁንም በትግል ላይ ያሉ አቅማቸውን የተቻለውን ባለው በጠበበና መፈናፈኛ በሌላው በእምባገነን መሃል ትግል የሚያደርጉ ወገኖቻችንን ወቀሳና ማጣጣል ተገቢነት የለውም ምክንያቱም የትግሉን እንቅፋት የሆኑትን ለትግል ያልቆሙ በወያኔ ተለጣፊነት ያሉትን ነጥሎ መተቸትና ወደ እውነተኛ እትግል መስመር እንዲመጡ አልያ በተመሳሳይ ከወያኔ ባልተለየ መንገድ እነሱንም መታገል እንዳለብን ሕዝቡን ማንቃትና ትግሉ ያለህዝቡ ተሳትፎ ውጤታማ እንዳልሆናና: ሳይታገልና ዋጋ ሳይከፍል ነጻነት እንደሌለ ማስገንዘብ ይጠበቅብናል:ሌላው ሁላችንም ወያነን በስልጣን ተቆናጦ እንዲቆይ ያደረግነው ግልጽ ተግባር ሳንሸፍን በግልጽ የተደርጉና የሚደረጉ ወገንተኛነት መንጽብረቅ በማቆም ሁሉም ዜጎች በኢትዮጵያዊነት ተጣምረው የወያነን የዘር ፖሊሲ በማፍረስ ሁሉም በእኩልነት ለአንዲት ሀገርና ሕዝብ መታገል እንዳለብን ይህንን የዘር ነቀርሳ ከላያችን በማስለቀቅ በአንድ ብሄራዊ አንድነት በመታቀፍ አታጋዮች ሳንፈልግ በየችሎታችንና አቅማችን በፈቀደው ሀገራችንን ከጥፋት ሕዝባችንን ከደረሰበት የመብትና የነጻነት እጦት ከረሃብና ከእንግልት ለማውጣት በጽናት እንነሳ

 5. aha!
  | #5

  I fully agree with the assertion of the author about the aligment of the parties along ethnic rather than national agenda as the major cause for not coming together, but above all their implicit support of ethnic federalism, secessionism and totaliarinism as the major cause for not coming together with common goals for unity, territorial integrity, sovereignity of Ethiopia and Ethiopians, where the last item has to do with individual freedom, liberty and equality to supecede ethnic rights and secessionist rights, where the now the teletafi (ethnic federalist) parties within TPLF/eprdf regime are scrambling for the top position, eventhough all positions are nominal, except for TPLF Politbeurro, and are ethnic not national oriented to begin with.

  What the author should not forget, that there are opposition parties aligned along the national agenda, intent on ratifying the constitution, I presume with respect to Article 1, about the flag, Article 46, Article 39 (1), Article 8 and individual freedom, liberty and equality to supercede ethnic and secessionist rights and resoting to the original provincial political boundries of federated states instead of ethnic federalism and maintain the territorial integrity of the Ethiopia.

  The legacy of TPLF/eprdf regime of ex-liberation fronts, spearheaded by TPLF in the pretext of oppression of nations and nationalities by the previous regimes, but not for class struggle has created a constitution with the ideologies of ethnic federalism, secessionism and totaliarinism built into it, which precludes individual freedom, liberty and equality, free market capitalism to the silent majority of Ethiopians that living under abject poverty under the TPLF/eprdf regime, run by TPLF Politbeurro with its secutiy forces, Military and federal police forces and the Killil mengistat administrators with narrow nationalist mentality together with exploitation, political, economic starangle hold of the countries reources by TPLF/EFFORT, TPLF affiliated enterprises, cadres and foreingn corporations, to say the least about rampant coruptions and inflationary pressures over the countries resources and the silent majority of Ethiopians.

 6. እሳት ምን ሆኖ ነዉ እዚህ ያቀረቡት?
  | #6

  ወንድም መኮንን ተድላ!”ከዚህ በሁዋላ ለወያኔ ተጨማሪ ዕድሜ ከተሰጠው፣ ከወያኔ በላይ ወንጀለኛ የሚሆነው ተቃዋሚው ነው።” ሲሉ ራስዎን ከዬትኛዉ ወገን መድበዉ ነዉ? “ተቃዋሚዉ” እርስዎ የሚሉትን/የሚፈልጉትን ተግባር አልፈጸመም::” እንበል:: ማን ነዉ በወንጀል የሚጠይቀዉ? እርስዎ እንደሚሉት ስልጣን ላይ ያለዉ ቡድን ደካማ ነዉ እንበል::ተቃዋሚዉም ደካማ ነዉ ከተባለ ነገሩ ግራ የሚያጋባ ነዉ::ችግሩ ዬት ላይ ነዉ?
  አቶ መኮንን! ጣትን ወደሌላዉ ከመቀሰር በፊት እያንዳንዱ ዜጋ ራሱን ቢመረምር መልካም ነዉ-ትናንት ምን ሰራሁ? ዛሬስ ምን እየሰራሁ ነኝ? ከዚያ ነዉ ሌላዉን ማየት::ረያንዳንዱ ድርሻዉን መወጣት እና እንዳስፈላጊነቱ ሌላዉን ማስተባበር;መምራት;ማሳወቅ…ከሩቅ ሆኖ መተቸት ብቻ ጥሩ አይመስለኝም::”ተቃዋሚዉ” ራሱን ችሎ በሀገሪቱ ፖለቲካ ዉስጥ ይህ ነዉ የሚባል ሚና ሊጫወት ያልቻለዉ በምን ምክንያት ነዉ? “ደካማ ስለሆነ ነዉ::” የሚለዉ መልስ አይደለም::የድክመቱ መሰረት በዉል ሊጤን ይገባዋል::ደርግ አንድ ትዉልድ አጥፍቶ ነዉ ያለፈዉ-ብዙ ጠባሳዎችንም ትቷል::ስልጣን ላይ ያለዉ ቡድን እርስዎ እንደሚሉት ደካማ አይመስለኝም::ቢያንስ ቢያንስ ኢትዮጵያዊነትን የሚሸረሽሩ በርካታ ተግባራትን ፈጽሟል-እየፈጸመም ነዉ::

  ታሪኩ አባዳማ “የማይደማመጠዉ ያ ትዉልድ” በሚለዉ መጣጥፋቸዉ (እዚሁ ድህረ-ገጽ ላይ)”አለመደማመጥ” አይነተኛ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ችግር እንደሆነ ነግረዉናል:: ምንም እንኳ ይህ ሀሳብ ባያረካኝም እንደ መነሻ ነጥብ ሊወሰድ ይችላል::ለምንድ ነዉ የማንደማምጠዉ? -ብለን መጠየቅ ከቻልን::

 7. ጆን
  | #7

  ሁሉንም አነበበኩት ግን የሚገርመው ሁሊም የምታቀርቡት ሃሳብ ወያኔ ወያኔ የሚል ንው እናተስ ምን ሰራችሁ ምን ለውጥ አምታ ችሁ

 8. Anonymous
  | #8

  ወያኔሰድሜው ካጠረ ተቃዋሚወች በጎራ ከፋፍለው ያፋጁናል:: ስለዚህ የወያኔን እድሜ ያርዝም:: ከተቃዋሚወች ይሻላል:: ተቃዋሚወች ገና ያልበሰሉ ጮርቃ ልጆች ናቸው:: እንደፓርቲያቸው ሁሉ ካልመሰላቸው አገሪቱንም ብትንትን ነው የሚያደርጓት::

 9. በለው !
  | #9

  “ከዚህ በሁዋላ ለወያኔ ተጨማሪ ዕድሜ ከተሰጠው፣
  ከወያኔ በላይ ወንጀለኛ የሚሆነው ተቃዋሚው ነው። ይህ ምንም ጥርጥር ለውም ተፎካካሪ ሳይሆኑ ተባባሪ ናቸው!!
  -”ብታምኑም ባታምኑም ሞተናል! ተንቀናል! ተዋርደናል!” ነበር ያሉት እኛ “የአብዮታዊ ሠራዊት ጠቅላይ አዛዥ” በእርግጥ ይህ ታይቷቸው? አስቀድሞ ገብቷቸው? ነበር ማለት ነው።

  “የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ” ጠቅላይ አዛዥ መመንመንና መምነን በኋላ ሥልጣን የምታርፍበት ቦታ አጥታ፣በአውላላ ሜዳ ላይ በቆመችበት ወቅት፣ እኔ አለሁ የሚላት ተቃዋሚ ወገን ጠፍቶ፣ይኸውና በሙት መንፈስ(ራዕይ) አገርና ሕዝብ ይገዛል። አገርና ሕዝብ ሞቶ በመንፈስ የመገዛቱ መንስዔ ደግም የወያኔን ጥንካሬ ሳይሆን፣የተቃዋሚውን ድክመት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
  -የአቅመ ሥልጣን ያላቸውም ይሁኑ ለአቅመ ሥልጣን ያልደረሱ ፀሐፊያን ተራኪያን አረጋዊያን፣ ወጣታዊያን፣ ምሁራዊያን ፣ተማሪያን፣ የጋዜጣ ባለሀብቶች፣ አንባቢያን፣አምራቾች፣አከፋፋዮች፣ ተቀባይ ሌቦች፣ ፣ ተሸካሚያንና ሻጮች፣ ሁሉ በጋራም ይሁን በተናጠል ተደራጅተውም ታቅፈውም ተቃቅፈው ሲያደነቁሩን ሰነበቱ።ከሚያለቅሰው መሀረብ የሚሸጠው በዝቶ ከሚያዝነው የሚሳቀቀው ቁጥሩ ከፍ ብሎ አባት ባለቤቱን እናት ልጆቿን የመፎጋገር በመተዛዘብ እና በግርምት ላይ የተመሠረተ በፍጥነት ያደገ ትዕይንት አየን!ጉድ አልን ታዲያ እኔ የተሻልኩ ነኝ ለውጥ አመጣለሁ ወንበሩም መንበሩም ይገባኛል ያለ ጠፋ ጭራሽ ለኢህአዴግ የሚበጀውን የብሔር ተወካይ ሊ/መንበር ለማፈላለግ ለመተንበይ ማራቶን ተያያዘን!ጠ/ሚኒስትሩ ከትግራይ ካልሆነ ፅቡቅ ብለን ጮቤ ረገጥን ኢህአዴግ አለቀለት ወያኔ ተበተነ ዕድገትና ብልፅግና መጣ ከመለስ በኋላ ሀገር አንድ ሆነች!! ተባለ ተቃማሚው ሥራውን ጥሎ ድንኳን ጣለ “የሜዳ አህያ ዥንጉርጉርነቱን ወያኔ ሌብነቱን አልተወም(አለቀቀም)አሰላለፉን ቀይሮ ጠ/ሚኒስትሩን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኮምንኬሽን ሚኒስትሩን ረዳት ጠ/ሚኒስትር ከሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር ጋር ደርቦ ደራርቦ (ተወቃን በደቦ)ከመልስ የብሔርና መንደር ስብስብ አመራር ‘group Leadership’ ወደ ኃይለመለስደስአለኝ አዲሱ ከፊትም ከኋላም ያሉ ሁሉ መሪዎች ናቸው ‘collective Leadership’አመራር ጋር አብረን እንጨፍራለን!!
  በተወጠነው የአምስት ዓመት ዕቅድ ዕራይ “ትግራይን የእንዱስተሪ መር ክልል የማድረግ ውርስ” ኋላቀሪት ታጋይ አዜብ መስፍን አብስረውናል።አቦይ ስብሐት “አማራና ኦርቶዶክስ ሥልጣን አበቃለት”አሉ ኃይለመለስ ደስአለኝ መልስዜናዊና ኢሳያስ አፈውርቂ የጠበቀ ግንኙነት እንደነበራቸው አቶ መልስ ፶ ጊዜ እንደለመኗቸው አሁንም የመለስን ራዕይ ለማስቀጠል አቶ ኀይሌ አስመራ ድረስ ሄደው አቶ ኢሳያስ እግር ላይ እንደሚወደቁ ተናግረዋል አለዚያማ አስመሳዩ ብአዴን(ሻቢያ) እንደሚገለብጣቸው አሰፈራርቶአቸዋል!

  ለመሆኑ እኝህ የምስራቅ አፍሪካን ቀጣና የሚያተራምሱ በዓለም አሸባሪ ጥቁር ነጥብ የተጣለባቸው እና ማዕቀብ የተደረገባቸው መሪ እንዴት ወዳጅነት ፈጠሩ? እንዴትስ ሌሎች ንፁሐን ዜጎች በኢሳያስ ዳፋ ሊታሠሩ ቤት ንብረታቸው ሊወረስ ቻለ?የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትሮች ከአሸባሪ ጋር አብሮ የመብላት የጠመጠጣት ልዩ ፍቃድ አላቸው ማለት ነውን? ለመሆኑ ተፎካካሪው የሚጠብቀው ምን ይሆን? ሁለት ፊት ያላቸው ፀጉረ ልውጦች በዝተው ይሆን?በእርግጥም የኢትዮጵያ ህዘብ አማራጭ ያጣ ልጉም ሆኖ በዓለም መሳቂያነቱን ያንፀባርቃል እንቢኝ በሀገሬ! እንቢኝ በነፃነትና ክብሬ! እንዳይል ተኮላሽቷል?ተፎካካሪው ሁሉ ከየግል ማዕቀፉ ወጥቶ፣ለወል በሚበጅ ገዥ ሀሳብ ዙሪያ ተሰባስቦ ማረፊያ ለምትፈልገው ሥልጣን መቅደስ መሆን ካልቻለ፣ከወያኔ በበለጠ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ዋና ጠላትና ወንጀለኛ ሆኖ በትውልድ
  የሚቆጠረው ተቃዋሚው ወገን እንደሚሆን መጠራጠር አይቻልም። አዎን! አይቻልም በፍፁም! በጭራሽ! በለው!! ከታላቅ የአክብሮት ምስጋና ከተድላ ጋር ከሀገረ ካናዳ>>>>>>>>>>>

 10. መልካሙ
  | #10

  ሁላችንም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የየድርሻችንን እንደ ደረጃው ለሀገራችን ችግር ፈጣሪና የመፍትሄ አካል መሆናችንን በጥሞና መረዳትና ማመን አለብን፡፡ስለዚህም እዚህ ላይ ልክ እንደ ምፅዓት የመጨረሻው ቀን ባለው አይነት የፍርድ ቀን አንተ ሃጥእ አንተ ፃድቅ ብሎ የመፍረድ የእውቀት የሞራልም ሆነ የስልጣን መሰረት የለንም፡፡እንደዚሁም ለመልካም ነገር በቀናነትና በእውነት ላይ ተመስርተን ካልሆነ በስተቀር ሌላ የተደበቀ ተልእኮ አንግበን እንዲያው በከንቱ በመሰሪነትም ሆነ በግብዝነት መወዳደሱና መሸነጋገሉም ሆነ በተቃራኒው ባለው በከንቱ መረጋገሙና መወቃቀሱ ከጥፋትና ከውድቀት ውጪ ለዘለቄታው ብዙም የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ስለዚህም የተቃዋሚውም ጎራ ከሌሎች የሚሰነዘርበትን አንተ የእኔ ውድቀትና ጥፋት ምንጭ ነህ ብሎ በከንቱ የማውገዝንም ሆነ አንተ ትልቅ ስራና ለውጥ ያመጣህ ታላቅ ሃይል ነህ ብሎ በከንቱ የማወደሱንም ጫፍና ጫፍ የረገጠውንና ያልተመጣጠነና ያልሰከነ አስተያየት መቀበል የለበትም፡፡አዎ የተቃዋሚው ጎራ በውዳሴ ከንቱ በቀላሉ የሚኮፈስ እንደዚሁም በሰላ ገንቢ ትችት በቀላሉ የሚበረግግና የሚያኮርፍ መሆን የለበትም፡፡ከዚህ በፊትም በዚህ አቡጊዳ አምድ ላይ በምሰጠው ተደጋጋሚ እረጅም አስተያያት ላይ እንደተለመደው ተቃዋሚውን በሰላ ትችት(ለእኔ ገንቢ እንደሆነ በሚሰማኝ) ሳብጠለጥል በነበረበት ወቅት ተቃዋሚውን እራሱን ከተቸሁበት አንድ የማልረሳው ነገር ድምፅና ድጋፍ ለማግኘት ብቻ በማሰብና በማስላት ለጊዚያዊ ለፖለቲካ ትርፍ ተብሎ ሁልጊዜ ህዝብን ያልሆነውን እንደሆነ አድርጎ በከንቱ መሸንገል ይቁም እንደዚሁም ህዝብ ስለራሱ ያለው ነባራዊ ሁኔታ እውነቱ ይነገረው ብዬ ነበር፡፡
  አዎ ዲሞክራሲ ሰብዓዊ መብት የፕሬስ ነፃነት ወዘተ በሚሉ በቅጡ ያልጠሩ መጤና ባእድ የዘመናችን ቃላትና ፅንሰ-ሃሳቦች በጥራዝ-ነጠቅነት እየተመራንና እያራገብን ለህዝብ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ አይነት ግዴታውን ጭምር ሳይሆን መብቱን ብቻ እየነገርነው ያልሆነ የቅዠት አለም ውስጥ አንክተተው ብዬ ነበር፡፡አዎ የዲሞክራሲን የነፃነትን የፍትህን የአንድ ሳንቲም ገፅታ እንጂ በተቃራኒው ያሉትን የዚህኑ የሳንቲም ገፅታዎች ለማሳየትና ለማሳወቅ የተቃዋሚው ጎራ የረባ ስራ አልሰራም፡፡
  ይህ የሆነው ደግሞ በዋናነት የተቃዋሚው ጎራ እመራበታለሁ የሚለው በሰከነ ምክንያታዊ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ግልፅ የሆነ የሕይወትና የፖለቲካ ፍልስፍና ስለሌለው ነው፡፡ላፉት 21 ዓመታት የተቃዋሚው ጎራ የተያያዘው ነገር የምርጫ ዲሞክራሲ የሚባለውን ነገር ተቀዳሚ ግብ ከሆነው ከተራ የስልጣን ምንጭነት ጋር በማያያዝና በዚህ ስሜት በመስገብገብ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው አይነት ከሱፐር ማርኬት ተዘጋጅቶ የሚሸጥ ያለቀለት ምግብ አሙቆ ለመብላት ከመፈለግ ከማሰብ ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ነገር ግን የሚበላውን ምግቡን በአስተማማኝ ለማግኘትና ለመጠቀም ግን ለም መሬት የእርሻ መሳሪያ የሰው ሃይል ቴክኖሎጂ ወዘተ ተጠቅሞ መሬቱን ማረስ ማለስለስ መዝራት ውሃ ማግኘት መኮትኮት መንከባከብ ሰብሉን ማጨድ መሰብሰብ መውቃት እንደገና ምርቱን ከገለባው መለየት ምርቱን እንደገና መስበሰብ ……………. እህሉን ወደ ዱቄትነት መፍጨት ማቡካት መጋገር …….. መብላት የሚለው ብዙ ሂደት እንዳለ ግምት ውስጥ አልገባም፡፡ይህ ሁሉ ሂደት ብዙ የሰው ሃይልና ሌላም የቴክኖሎጂ ግብአቶች እንደሚያስፈልጉት የታወቀ ነው፡፡ሀገር መመስረት መገንባትና መምራትና ከትወልድ ትውልድ ማስቀጠል ደግሞ እንግዲህ ይህንንም ከሆድ ጋር በተያያዘ ያለውን ምግብ የማግኘት ሂደት ጨምሮ ብዙ ሌሎች ተመሳሳይና ተጨማሪ ውስብስብ ነገሮች የሚጨምር ነው፡፡የተቃዋሚው ጎራም ለዚህ በእውቀት በአቅም በታሪክ በስነ-ልቦና በሞራል ወዘተ የተደራጀና የተዘጋጀ እነበረም፡፡ይህ ስለሆነ የተቃዋሚው ጎራ ሙሉ ለሙሉ ተጠያቂና ጥፋተኛ ነው ለማለት ግን አይደለም፡፡ምክንያቱም የተቃዋሚው ጎራም በራሱ ከህዝብ አብራክ የወጣ እንጂ ከሌላ ቦታ የመጣ ወይንም በተአምር የተፈጠረ ስብስብ አይደለምና፡፡ያልዘራነውን ለማጨድ ማሰብ እንዳይሆንብንም ከተቃዋሚው ጎራ ቀድሞውን ያልተሰጠውን ነገር መልሶ ለእኛ እንዲሰጠን መጠበቅ የለብንም፡፡
  ስለዚህም ተቃዋሚ በአንድ በኩል ህዝብ በሌላ በኩል የሚከልል የለየለት በነጭና በጥቁር የሚለይና ተቃዋሚውን ጥፋተኛ በተቃራኒው ደግሞ ህዝብን ትክክለኛ አድርጎ የሚፈርጅና የሚለይ ግልፅ መስመር የለም፡፡ሁላችንም እትብታችን በዚህች ሀገር የተቀበረና የዚህችን ሀገር አፈር ፈጭተን ጭቃ አቡክተን ወዘተ ያደግንና እርስ በርስ እንደ ድር የተሳሰረ ማንነት ያለን ህዝቦችና ዜጎች ነን፡፡አስተሳሰባችን ሞራላችን ስነ-ለቦናችን ባህላችን ታሪካችን ሃይማኖታችን ንቃተ-ህሊናችን በአንድ የተወሰነ ተቀራራቢ ማእቀፍ ውስጥ ያለ ነው፡፡ስለዚህም እያንዳንዱ ትችትና ሙገሳ የየራሱ እውነተኛነትና ተቀባይነት የሚያሰጠው ድንበርና ማእቀፍ(domain of truth and righteousness) ያለው እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡ለምሳሌ ቢያንስ ቢያንስ በአደርባይነት የጥፋት ተባባሪ አለመሆን በራሱ አንድ አዎንታዊ እርምጃ ከመሆኑ አንፃር ወያኔ በግዴለሽነትም ይሁን በአደርባይነት ፈቃደኛ የጥፋት ተባባሪ ካላገኘ እንዴት ይህንን ሁሉ ጥፋትና መከራ በራሱ ሃይል ብቻ ሊያከናውንና ሊያመጣ ይችላል የሚለው ቸል ሊባል የሚችል ጉዳይ አይደለም፡፡ስለዚህም ትችትና ፍርድ ከሌላ ከራሳችን ውጪ ካለው በባሰ በራሳችን ህሊና ውስጥ ጭምር የሚመዘንና የሚዳኝ ነገር እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ስለዚህም እይንዳንዳችን ለችግሩም ሆነ ለመፍትሄው አካል የሆነ ነገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እኔ ምን አደርግሁ የሚለውን ወደ ውስጥ እንመርምር፡፡ወቀሳና ሙገሳ ከዚህ ቢጀምር ለመግባባት ብዙም ባልከበደን ነበር፡፡በህይወት ውስጥ ትርጉም ያለው ውድቀትም ሆነ ስኬት በተአምር በአንድ ጊዜ የሚመጣ ነገር አይደለም፡፡ህይወታችን እለት ተእለት እንደሆነው ሁሉ በተቃራኒው ያለውንም ሞታችንንም እየሞትነው ያለነው እለት ተእለት እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡ስለዚህም ችግሩና ቀውሱ አንድ ጊዜ እንዳልተፈጠረው ሁሉ መፍትሄውም እንደዚሁ ነው፡፡
  ወደ መፍትሄው ስንመጣ የሚከተሉትን የሚሰማኝን ማለት እፈልጋለሁኝ፡፡

  1ኛ)የማሰብ ሃይላችንን ተጠቅመን እንደ አንድ ሙሉ ሰው በሰከነ መንገድ በጥልቀትና በስፋት በምክንያታዊነት አስተሳሰብ እናስብ፡፡ምክንያቱም የነገሮች ሁሉ ቁጥር አንድ መነሻ ነጥብ ይህ ነውና፡፡ይህ የማከብረውና የማደንቀው የዶ/ር ፍቃዱ በቀለ አባባልን የሚመሳሰል ነው፡፡

  2ኛ)የተቃዋሚው ጎራና ሌላውም ኢትዮጵያዊ ምሁርና ፖለቲከኛ ግልሰባዊ የየራሱን የህይወትና የፖለቲካ ፍልስፍና ቅድሚያ ለራሱ ግልፅ ያድርግና ከዚያም በዚህ መነሻነት እርስ በርስ በሰከነና በመከባበር በቀናነት መንፈስ ይወያይ ይከራከር፡፡ድንገተኛ እሳት ከማጥፋት በዘለለ ትርጉምና ፋይዳ ያለው የፖለቲካ ፓርቲ በዘለቄታዊነት ለመመስረትና የፓርቲ ፖለቲካ ጨዋታ በስኬት ለመጫወት የሚቻለውም ከዚህ ቀጥሎ ነው መሆን የነበረበት፡፡ለምሳሌ ባልንጀራህን እንደራሰህ ውደድ እንደዚሁም ለአንተ/በአንተ እንዲሆን የምትፈልገውን/የማትፈልገውን ነገር በሌሎች እንዲሆን ፈልግ/አትፈልግ እና ቅድሚያ እኛ የሚለው ለአንዱ የህይወት መመሪያ ሆኖ ሲያገለግል ለሌላው ደግሞ ቅድሚያ እኔና እኔ ብቻ የሚል የጥሎ ማለፍ ስራ ለሌላው የህይወት መመሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ነገር ግን አሁን ባለችው ኢትዮጵያችን ውስጥ ዲሞክራሲ ሰብዓዊ መብት ነፃ-ፕሬስ ወዘተ በሚል ጭንብል ውስጥ ተደብቀው ሁለቱንም ተቃራኒ የሕይወት መመሪያ የሚከተሉ ስብስቦችና ሰዎች የጋራ ጠላት ወያኔን መዋጋት በሚል ሽፋን ብቻ እንደ እድርና እቁብ በቀለለ መንገድ ተሰባስበውና የፖለቲካ ፓርቲ መስርተው ህዝብን ያደናግራሉ እርስበርሳቸውም ይሻኮታሉ፡፡ለምሳሌ ሊበራል-ዲሞክራሲ ሊበራል ኢኮኖሚ(ነፃ-ገበያ) ሰብዓዊ መብት ነፃ-ፕሬስ ወዘተ እያልን እንደወረደ ብናቀነቅንም ነገር ግን ይህ የምናቀነቅነው አስተሳሰብ በዋናነት የመነጨበት የምእራቡ አለምን ስልጣኔ መሰረት ያደረገውና በዘመነ ግሎባላይዜሽን እየተስፋፋ የመጣው ደንበር ዘለል ግሎባል ካፒታሊዝም የተመሰረተበት የህይወትና የፖለቲካ ፍልስፍና ምንድን እንደሆነ ብዙዎቻችን ገና በቅጡ መርምረን አልተረዳነውም፡፡ዛሬ በሀገራችን ለጥቂቶች የምድር ገነትና ለብዙሃኑ የምድር ሲኦል ያህል ልዩነትን በሚፈጥር ሁኔታ እየተፈጠረ ያለው ኢ-ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልና ማህበረሳበዊ አዲስ መጥ አወቃቀር(Social Restructuring) እና ይህንንም ተከትሎ እየተፈጠረ ያለው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተፈጥሯዊ ቀውስ ምንጩ ምንድን ነው?ኢትዮጵያዊ ገበሬ ብሄሩና ዘሩ እየተመረጠ ሀገር እንደሌለው እንደ መጤ ከመሬቱ ተፈናቅሎ በተቃራኒው ግን መሬቱ ለውጪ ባእዳን እየተቸበቸበ ያለበት ሁኔታ ከምን የህይወትና የፖለቲካ ፍልስፍና የመነጨ ነው?እውን ይህ አይን ያወጣ ግፍና በደል የአብዮታዊ ዲሞክራሲ እውነተኛ የህይወትና የፖለቲካ ፍልስፍና ስለሆነ ነውን?

  3ኛ)ጊዚያዊና ዘለቄታዊ ችግሮችን እንመርምርና እንለይ ከዚህ በመነሳትም ጊዚያዊና ዘለቄታዊ መፍትሄዎችን እናስቀምጥ፡፡ለምሳሌ ወያኔን ከስልጣን ማስወገድና ከዚያ ስርዓቱን በሚፈለገውና መሆን በሚገባው መንገድ መቀየር የሚሉት ነገሮች የየራሳቸው የጊዜ ሰሌዳ እንደ ቅደም ተከተል ሊቀመጥላቸው እንደሚገባ የሚታወቅ ነው፡፡ከዚህ እይታ አንፃር ሀገር በስርዓት የሚመሰረትበትንና የሚመራበትን እረጅም የጊዜ ሰሌዳ በሰከነ መንገድ ማዘጋጀት ተገቢ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡
  የኢትዮጵያ ታሪካዊና ተጨባጭ ችግር የምርጫ ዲሞክራሲ ችግር አይደለም፡፡አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያም ሆነች ሌላው የተቀረው መላው ታዳጊው አለም ምእራቡን አለም በተለይም አሜሪካንንና እንግሊዝን ማከል ያደረገው የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራልና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት ተግበራዊነትን ያተኮረ ከፍተኛ የተፅእኖ መዳፍ ስር ነው ያለው፡፡በተለይ ኢትዮጵያ ደግሞ በፀረ-ኮሎኒሊዝም ግንባር ቀደምና ፋና ወጊ ታሪኳ የተነሳ በባእዳን ሃይሎች ዘንድ ጥርስ የገባች ሀገር ስለሆነች በመለስ/ወያኔ እና በኢሳያስ/ሻእብያ ቅጥረኛነት የተነሳ ቁጥር አንድ ሰለባ ሆናለች ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ወያኔንም ሆነ ሻእብያን አሁን ባለው ሁኔታ ስንታገል ይህንን ዘለቄታዊ ችግርና ትልቅ ስእል ግምት ውስጥ ማስገባት ብልህነት ነው፡፡በትግሉ ውስጥ ጥልቀትና ስፋት ያለው ውስብስብ የሃይል አሰላለፍ መረዳት ተገቢ ነው፡፡ይህንን ስንረዳ ደግሞ ላለፉት 21 ዓመታት በአስከፊና በአሳዛኝ ሁኔታ በውክልና ተዘዋዋሪ ቅኝ ግዛት(Surrogate Neo-Colonialism) ስሌት እየረገጠ እየዘረፈና እርስ በርስ እያናከሰ እየገዛን ያለውን ወያኔን ከመዋጋትና ከመጣል በዘለለም በራሱ ቀድሞውንም ወያኔ እንዴት ስልጣን ላይ ሊወጣ ቻለ የሚለውን በጥሞና መተንተንና መረዳት ወደፊት ተመሳሳይ ሃይሎች በነፃነት ተጋዳላይነት ሽፋን ስልጣን ላይ እንዳይወጡና ተመሳሳይ ችግር ውስጥ እንዳንገባ ይህንን መረዳቱ እጅግ ተገቢ ነው የሚሆነው፡፡ድንገተኛ እሳት የማጥፋት አካሄድ አንዳንድ ጊዜ ለሌላ ዘለቄታዊ መከራ የሚዳርገውም የፊት የፊታችን ብቻ በማየት ቶሎ የሚደርስ የሰኬት ፋስት ፉድ ለመብላት የምናደርገው ችኩልና ጠባብ አካሄድ ነውና ደርግን አምባገን ወዘተ እያሉ የሚራገሙና ውድቀቱን ይመኙ ነበሩ ሃይሎች ሁሉ በቀጣይ የሚመጣውን ሃይል ምንነት በጥሞና አልተረዱም ነበር ለማለት እደፍራለሁኝ፡፡ስለዚህም የችግሮችና የመፍትሄዎችን አቅጣጫ የሚያመላክት ጊዚያዊና ዘለቄታዊ ብሎ የሚክፈል አንድ ትልቅ የጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀትና በዚያ ላይ መወያየት ተገቢ ነው፡፡ብዙዎቻችን ግራ ከመጋባታችን የተነሳ የፊት የፊታችን ብቻ በማየት ቶሎ የሚደርስ የሰኬት ፋስት ፉድ ለመብላት በመቸኮል ተግባራዊ እርምጃ እያልን እኔንም ጨምሮ እናወራለን፡፡ነገር ግን ቅደም ተከተል ያለውና ያለንን ውስን Resource and Capacity በተገቢው መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል ተግባራዊ እርምጃ የምንወስድበት አንድ ትልቅ የጊዜ ሰሌዳ ሊኖረን ግድ ይላል፡፡እንደዚሁም ስለነገሮች የሚኖረን ጥልቅና ሰፊ የሆነ ግንዛቤና እውቀት በራሱ አንድ ትልቅ ሃይል እንደሆነና ለምንወስደውም ማንኛውም ተግባራዊ እርምጃ ዋና መነሻ ነጥብ ሆኖ እንደሚያገለግል መረዳትና ማመን አለብን፡፡ስለዚህም ከምን ጊዜም በላይ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እውቀትም ሆነ ጠብ-መንጃ ሁለቱም እንደ አየሩ ሁኔታ(ጊዚያዊ/ዘለቄታዊ) በአግባቡ ልንጠቀምበት እንደሚያስፈልገን መረዳት አለብን፡፡

  4ኛ)የተቃዋሚው ጎራ ተጨባጭ ሃይል እንዲኖረውና ሀገርንም በዘለቄታው ትርጉም ባለው መንገድ ለመምራትና ለማስተዳደር ከፈለገ ቢበዛ ከአራት ባልበለጠ ቡድን ተሰባስቦና የፖለቲካ ፓርቲ መስርቶ መቅረብ አለበት፡፡በኢትዮጵያችን ውስጥም ሆነ በሌላው ታዳጊው አለም ውስጥ ያለው አንዱ ታሪካዊና ተጨባጭ ማህበረሰባዊ ዋና የልዩነት ምንጭ አንድ ከዘር/ከብሄር/ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ሲሆን ሌላው ደግሞ ኢኮኖሚውን በዋናነት መሰረት ባደረገ መንገድ ከመደብ ክፍል(Social Class) ጋር በተያያዘ ያለ ነው፡፡ላለፉት 21 ዓመታት ወያኔ ከዘረጋው የብሄር ብሄረሰብ ቅኝት ጋር በተያያዘ ብሄርን መሰረት ያደረገው ነገር ተጋኖና ገዝፎ ቢወጣም ቅሉ ግን ኢኮኖሚውን በዋናነት መሰረት ባደረገ መንገድ ያለው የመደብ ክፍል(Social Class) ሁኔታ ግን ተገቢው አትኩሮት ተነፍጎት ተደብቆ ያለ ነገር ነው፡፡አሁን ባለችው ኢትዮጵያችን ግን እውነታው እየወጣ ያለው ግን ብዙሃኑ ድሃ ህዝብ አርተፊሻል በሆነ በዘር/በብሄር/በሃይማኖት/በፆታ በጥቂት ሀገራዊና አለም አቀፍ የግሎባል ካፒታሊስት ኤሊቶች እንዲከፋፈልና እንዲዳከም ቢደረግም ቅሉ ግን ድሃው ህዝብ እራሱ ተመሳሳይ የሆነው ኢኮኖሚያዊ ድህነቱ ያመጣበት እርሃቡ እርዛቱ ስደቱ መፈናቀሉ በሽታው ወዘተ አንድ ሊያደርገው የሚገባው ነገር መሆን ነበረበት፡፡ብዙዎቻችን ያልተረዳነው ነገር ጥቂቶች የላይኛው ክፍል ሀገራዊና አለም አቀፋዊ የግሎባል ካፒታሊዝም ልሂቃኖች ታዳጊውን አለምና ብዙሃኑን ድሃ ህዝብ የተፈጥሮ ሀብቱንና ኢኮኖሚውን እንደፈለጋቸው ለመመዝበርና ዘመናዊ ባርነት ውስጥ ለመክተት እንዲመቻቸው ሲሉ የታችኛውን የህብረተሰብ ክፍል አርተፊሻል በሆነ በዘር/በብሄር/በሃይማኖት/በፆታ እንደሚከፋፍሉትና እንደሚያናክሱት ነው፡፡ከዚህ እይታ አንፃር ከዚህ በፊትም እንዳልኩት አብዛኛው የተቃዋሚ ጎራ ፖለቲከኛና ምሁር በትክክል የቆመለትን የመደብ ክፍል (Social Class) አለየም፡፡ይህ የሆነው ደግሞ የተቃዋሚ ጎራ የሚመራበትና የሚታመንለት የጠራ የህይወትና የፖለቲካ ፍልስፍና ስለሌለው እንደሆነ ይሰማኛል፡፡በአንድ በኩል የግሎባል ካፒታሊዝምን ኒዎ-ሊበራል አስተሳሰብ እየደገፉ በሌላ በኩል ደግሞ ደንበር ዘለል ግሎባል ካፒታል ባመጣው ጣጣ ገበሬ እየተፈናቀለ መሬት ለምን ለባእዳን ይሸጣል ለምን የመንግስት የልማት ድርጅቶች በርካሽ እየተቸበቸቡና ብዙሃኑ ህዝብ የኢኮኖሚ መሰረቱና ህልውናው እየተናጋ ህዝብ ለምን በድህነት ይሰቃያል ማለት እጅግ ግራ የሚያጋባ እርስ በርሱ የተምታታ ጥራዝ-ነጠቅ ፖለቲከኛነት ነው፡፡አብዛኛው የቃዋሚው ጎራ ዲሞክራሲ አምባገነን ሰብዓዊ መብት ነፃ-ፕሬስ ወዘተ ከማለት ውጪ የግሎባል ካፒታሊዝምን ታሪካዊና ተጨባጭ አሰራርና ባህሪ በቅጡ ገና አልተረዳም፡፡እውነተኛ የኢኮኖሚ ነፃነት የሌለው ህዝብ እውነተኛ የፖለቲካ ነፃነት ከቶ ሊኖረው እንደማይችልም ገና በቅጡ አልተረዳንም፡፡We are so confused to discern the difference between “Fantasy of the day” (bogus Democracy) and “Order of the day” (Global Capitalism).ዘርፈ ብዙ ትግሉ መስዋእትነቱ መታሰሩ መሰደዱ ሁሉና ወያኔንም መታገሉና ከስልጣን ማስወገዱ በስተመጨረሻ ምን አይነት ስርዓት ለመመስረት ታስቦ ነው?ነፃነት ዲሞክራሲ ፍትህ ወዘተ ሁሉ ጥቅል ሃሳቦች ናቸውና ማንም እነዚህን እሴቶች አሰፍናለሁኝ እንጂ እቃወማለሁኝ የሚል ሃይል መቼም ከዚህ በኋላ አይመጣም፡፡ሰይጣንም ቢሆን ይህንን አደርጋለሁኝ ብሎ ነው የሚመጣውና ማለት ነው፡፡ነገር ግን ግሎባል ካፒታል አለምን እንደባሪያ እየገዛ ባለበት ወቅት እነዚህ እሴቶች በእለት ተእለት ህይወታችን ውስጥ በዝርዝር እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆኑ ግን ብዙም ገልፅ አይደለም፡፡በአጭሩ ግን ለማለት የፈለግሁት የፖለቲካ ፓርቲዎች ትርጉም ያለው ስራ ፈልገው ሊደራጁ የሚገባቸው ከሆነ በብሄርና በመደብ ክፍል ቢሆን እንኳን ከአራት ፖርቲ እንደማይበልጥ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ፡፡የኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ እንደ ሀገር ከመቀጠል ህልውና ጋር የሚያያዝና ለድርድርም የሚቀርብ ስላልሆነ አንድነት ወዘተ እያሉ ፓርቲ መመስረቱ ለጊዚያዊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ብዙም ለዘለቄታው ትርጉም ያለው ነገር አይደለም፡፡ስለዚህም በመደብ ክፍል ስንሄድ በግርድፉ ሁለት የፓርቲ ክፍፍል ማለትም ሶሻሊስት እና ካፒታሊስት የሚል የኖራል ማለት ነው፡፡በብሄር ስንሄድ ደግሞ በሄርን የሚያቀነቅንና የማያቀነቅን ተብሎ እንደዚሁ በግርድፉ በተመሳሳይ ሁለት ፓርቲ ይኖራል ማለት ነው፡፡አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በሀገራችን የሚኖረው ሴኩላር መንግስት ነው ብለን በማሰብ የሃይማኖትን ጉዳይ ለጊዜው ወደጎን መተው እንችላለንና ይህ የፓርቲ ምስረታው ላይ እንደ ዋና መለኪያ መስፈርት ሆኖ መግባት ያለበት መስሎ አይሰማኝም፡፡ከዚህ መነሻ ሃሳብ ስንነሳና ከሌላውም አለም አሰራርና ተሞክሮ ስንነሳ በሀገራችን የሚታየው 60 ያህል የፖለቲካ ፓርቲ እንደ እንጉዳይ መፍላት እጅግ የሚያሳዝንም የሚያስገርምም የሚያሳፍርም ነው ማለት ነው፡፡ይህ አይነት መላቅጥ የጠፋው አሰራር የዲሞክራሲን ጥልቅና ሰፊ የሆነ ፅንሰ ሃሳብ በቅጡ ካለመረዳትም ጭምር የሚመነጭ ነው፡፡አዎ ዲሞክራሲ በአንደኛው የሳንቲም ገፅታ ያለው መብት ነፃነት ወዘተ ብቻ ሳይሆን ሃላፊነት ግዴታ ተጠያቂነት ስርዓት ተአማኒነት ወዘተ ጭምር የሚሉትን የሌላኛውን የሳንቲሙን ገፅታ ፈፅሞ ያልዳሰሰ ነው፡፡ዲሞክራሲም ቢሆን በራሱ ከስነ-ልቦናዊ ከባህላዊ ከማህበራዊ ከሃይማኖታዊ ከፖለቲካዊ ከኢኮኖሚያዊ ከተፈጥሯዊ ደንቦችና ህግጋት ውጪ ዝም ብሎ በራሱ መንገድ በመፃነት የሚንቀሳቀስና የሚሰራ ነገር አይደለምና የእነዚህ ሁሉ ተፅእኖ ያረፈበት ነው፡፡And that is why I raised the issue of “Fantasy of the day” (bogus Democracy) and “Order of the day” (Global Capitalism).ስለዚህም የተቃዋሚው ጎራ እንደ እድርና እቁብ በቀለለ እይታ ዝም ብሎ በቅርርብና በስሜት ብቻ እየተመራ የሚመሰርተው የፖለቲካ ፓርቲ አንድ በህይወትና በፖለቲካ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባዋል ሁለተኛ ሃላፊነት ወስዶ ሀገርንና ህዝብን ከመምራትና ከማስተዳደር አንፃር የሚመራበት የሰከነ ዲሲፕሊን ሊኖረው ይገባዋል፡፡ይህንን ሁሉ እያልኩኝ ያለሁት በቀናነትና በእውነት ለተነሱት ተቃዋሚዎች እንጂ በአደርባይነትና በመሰሪነት ለተሰለፉት ለወያኔ ተለጣፊዎች አይደለም፡፡

  5ኛ)እንደ ግለሰባዊ አስተያየቴ የሶሻሊዝም መልካም እሴቶች እንደገና ማንሰራራት መቻል አለባቸው፡፡ሶሻሊዝም ማለት ደርግ ማለት ነው ሶሻሊዝም ማለት እስታሊን ማለት ነው አይነት የተንሸዋረረና የጠበበ ውሃ የማይቋጥር ጥራዝ-ነጠቅ አስተሳሰብ መገታት አለበት፡፡ምናልባትም አሁን ያለው አብዛኛው የተቃዋሚው ጎራ እየሰራው ያለው ከፍተኛ ስህተትና ጥፋት አንዱ ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፡፡በደርግ ዘመን ሶሻሊዝምንም ሆነ አሁን በዘመነ ወያኔ ኒዎ-ሊበራል ግሎባል ካፒታሊዝምን ወደን ሳይሆን እንደ ድንገት በቅጡ ሳንመክር በላያችን ላይ እንደ ዱብ እዳ ተጭኖብን የሁለቱም ስርዓት መልካምና መጥፎ ልምድና ተሞክሮ አለን፡፡ጫፍና ጫፍ በረገጠ መንገድ ነገሮችን በነጭና በጥቁር ከመሳል ይልቅ ከዚህ ምን ታሪካዊ ትምህርት እንማራለን?በሶሻሊዝም ውስጥ ካፒታሊዝም አለ በካፒታሊዝምም ውስጥም ሶሻሊዝም አለ፡፡ዋናው ቁም ነገር ግን ጋሪውንና ፈረሱን መለየትና በየትኛው መሰረት ላይ የቱን አይነት ቤት እንገንባ የሚለው ጭምር ነው፡፡ለምሳሌ ካፒታሊዝም በወሬ ደረጃ በዲሞክራሲና በነፃ-ገበያ መርህ ላይ ነው የተመሰረተውና የሚመራው ቢባልም ቅሉ ግን በተግባር ሲታይ ግን ከነፃ-ገበያ መርህና ውድድር ባፈነገጠ መንገድ ኢፍትሃዊ አካሄድ ተከትለው ጥቂቶች ልሂቃን የራሳቸውን ሶሻሊስታዊ የመደብ ክፍል በራሳቸው መንገድ ለራሳቸው በሚስማማ መንገድ ቀርፀው በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ መስርተው በሌላው ብዙሃን ህዝብ ስቃይ የራሳቸውን ምድራዊ ገነት እየኖሩ ነው፡፡That is what is called as socialize risk and loss but privatize profit and advantage. And such schemes are implemented through austerity measures and bank bailouts. And even we have to know that there is indeed command economy and planed economy in capitalism in such a way that it is comparatively advantageous for minority few capitalist elites.እንደዚሁም ስለ ሶሻሊዝም ብዙዎች የሚያስቡት ሶሻሊዝም ማለት ፈፅሞ ዲሞክራሲ የሌለበትና ተንቀሳቃሽ ካፒታል ፈፅሞ እንደማያስፈልገው ሰርዓት አድርገው ነው፡፡ነገር ግን እኔ እያወራሁት ያለሁት በደርግ ዘመን ስላለው ገና ያልበሰለ ጨቅላ ሶሻሊዝም ሳይሆን ለዘመናችን የሚስማማ የሰለጠነና ሰብዓዊነትን የተላበሰ ሶሻሊዝምን ነው፡፡In short it is the sort of Socialism with a sense “First-We” than “First-Me” mentality in a way that is coherent with the resources on earth, laws of nature and social norms and values based on the very real essence of humanity.አሁን ባለው ሁኔታና አካሄድ ተራ የፖለቲካ እስጥ አገባውን ትተነው ከዚህ በዘለለ ከተፈጥሮ ህግና ከአጠቃላዩ መድራዊ የተፈጥሮ ሃብት ሁኔታ ጋር በተያያዘ ካፒታሊዝም በዚህ አካሄድ ብዙም መቀጠል የማይችልበት ደረጃ ላይ ነው የደረሰው፡፡ማለትም የተቀረው ብዙሃኑ ህዝብ እንደማይጠቅም ውዳቂ ነገር ተቆጥሮና የጠፋው ጥፍቶ ጥቂት ምርጦቹ ብቻ በዚህች ምድር ላይ ይኑሩ ካልተባለ በስተቀር እውነታው ይህ ነው፡፡እንደዚሁም ከካፒታሊዝም በተሻለ ሶሻሊዝም የብሄርን የሃይማኖትን የአንድነትን የፆታን ችግር ሁሉ በተወሰነ በአንፃራዊነት እንደሚፈታና የታችኛውን የተከፋፈለውን የህብረተሰብ ክፍል አንድ እንደሚያደርገው ይሰማኛል፡፡በዚህ የተነሳም ነው ሶሻሊዝምን ያነሳ ውሾ ይሁን እየተባለ ሶሻሊዝም ማለት ደርግ ማለት ነው ሶሻሊዝም ማለት እስታሊን ማለት ነው እየተባለ የሚወገዘው፡፡ለህዝብ ቆመናል ለህዝብ እንታገላለን እያልን በተቃራኒው ሶሻሊዝምን የምናወግዝበት እይታ ግን ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ዝም ብሎ እንደ በቀቀነ በል የተባለውን እየተቀበለ ዝም ብሎ የሚያራግበው ተላላኪ ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛና ምሁር ካልሆነ በስተቀር እራሳቸው ከፍተኛው የግሎባ የካፒታሊስቱ ኤሊቶች እንኳን ለድሃው ህዝብ ህልውናና ደህንነት የሚጠቅመው ስርዓት ሶሻሊዝም እንደሆነ ውስጣቸው አሳምሮ ያውቃል፡፡ነገር ግን እነዚህ በግለሰባዊ ነፃነት ሽፋን የግል ምድራዊ ገነት ምቾታቸውና ጥቅማቸው ስብእናቸውን ተብትቦ ስለያዘው የሶሻሊዝምን መጥፎነት በወኪሎቻቸው ፖለቲከኞች ምሁራን ሚዲያ ወዘተ አማካኝነት ነው የሚያስተጋቡት እንጂ እነሱ በቀጥታ ብዙም አያወግዙም፡፡ግለሰባዊ የፓርቲ ፖለቲካውን ትተነው ቢያንስ ቢያነስ አሁን ባለው አካሄድ የምድራችን የተፈጥሮ ሀብት ውሱን ስለሆነ ካፒታሊዝም በዋናነት እየተመራበት ላለው Money Capital Accumulation through Money Capital Sequencing የ Business Cycle ብዙም መቀጠል የማይችልበት ደረጃ ላይ ነው የሚደርሰው፡፡ስለዚህም ከእዝ ኢኮኖሚ (Meticulously Ordered and planned Social Economy)ውጭ ባላ አካሄድ ማንም ዝም ብሎ በዘፈቀደ አንድ ነገር ለግል የቅንጦት ፍላጎትና ለትርፍ ብቻ ሲባል አንድን ምርት ማምረት የማይችልበትና የማይገባው ደረጃ ይደረሳል ማለት ነው፡፡So when we talk about Capitalism, Socialism and Democracy we have to view it not only from the perspective of narrow and unbridled mere personal desires and ambitions but also from the perspective of collective survival issues as human beings and the associated life support systems in general.

  6ኛ) ሌላው በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ላላው አጠቃላይ ቀጣናዊ ችግር የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ከፍተኛ አትኩሮት ሊሰጠው የሚገባ ነገር ነው፡፡ቀናነትና ፍትህ እስካለ ድረስ የባህር በሩን ጉዳይ ኤርትራን ብቻ ሳይሆን ምናልባትም እንገነጠላለን የሚሉትን የወያኔዎችን የትግራይ ትግሪኛ መንግስት ፍላጎት ጭምር ባገናዘበ መንገድ ሁሉም የየድርሻውን የባህር በር መውጫ ማግኘት የሚችልበትን መንገድ መፈለግ ይቻላል ብቻ ሳይሆን ተገቢም ነው እላለሁኝ፡፡አንዳችን በሌላኛችን ጥፋትና ስቃይ ለማትረፍ እስከፈለግንና እስከተንቀሳቀስን ድረስ ግጭትና አለመረጋጋት መቼም ሊቆም አይችልም፡፡ይህ ኢትዮጵያን የባህር በር የማሳጣት ሴራ ደግሞ የባእዳን ሃይሎች እጅ ጭምር ያለበት ነው፡፡ስለዚህም ኤርትራም ብትሆን በእውነት የምትፈልገው ነፃነትንና ሰላምን ከሆነ ሰላምህን በውድ ዋጋ ግዛው እንደሚባለው 90 ሚሊዮን የእናት ሀገር ህዝብ ጉሮሮ አንቄና የባህር በር መውጫ አሳጥቼ በዚህ የባህር በር ኪራይ እየሰበሰብኩኝ በሳለም ለዘለቄታው ተረጋግቼ እኖራለሁኝ ብላ ማሰብ አጉል ግብዝነትና ሞኝነት ነው፡፡ይህ የመለስ/ወያኔ እና የኢሳያስ/ሻእብያ አጉል የብልጣብልጥ ስሌት ነው፡፡ስለዚህም ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍትሃዊ ሞራላዊ ተፈጥሯዊ ታሪካዊ መሰረት አላት፡፡ከእስራኤሎች መዳፍ ስራ ወጥታ ገና እንደ ሙሉ መንግስትና ሀገር የማትታየው ፍልስጤም እንኳን ካርታ ላይ ልብ ብለን ካየን በሚገርም ሁኔታ የባህር በር መውጫዋን ያመቻቸች ሀገር ናት፡፡
  ስለዚህም የኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ ታሪክና ትውልድ ላለፈውም ሆነ ለወደፊቱ ፈፅሞ የማይዘነጋው ክስተት እንደሆነ ነው የሚቆየው፡፡

  7ኛ)ሌላው የብሄራዊ እርቅ ጉዳይ ነው፡፡በግጭት ውስጥ ለተፈጠረ ቅራኔ ጥፋትና መከራ ይቅርታና እርቅ አስፈላጊና ተገቢ ቢሆንም ቅሉ ግን ዝም ብሎ በብልጣብልጥነትና በችኮላ አንዱን አሸናፊ ሌላውን ተሸናፊ የሚያደረግ ይቅርታና እርቅ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ለጊዚያዊ ስግብግብ ስልጣን ተብሎ የሀገርና የህዝብ ዘለቄታዊ ህልውና ደህንነት ጥቅም ተላልፎ ሊሰጥ አይገባም፡፡የተቃዋሚው ጎራም ለጊዚያዊ ስግብግብ ስልጣን ብሎ በመቻቻል በይቅርታና እርቅ ሽፋን በደልና ግፍ ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ ታሪካዊ ወንጀልና ክህደት ነው የሚሆነው፡፡ይቅርታ ማለት የተፈጠረውን ነገር እንዳልተደረገ አድርጎ መካድ ማለት አይደለም፡፡ይቅርታ ማለት ከሰሩት ጥፋት ከተጠያቂነት ማምለጥ ማለት አይደለም፡፡ይቅርታ ማለት ምንም ሳይሰጡ ዝም ብሎ ምህርት የሚቀበሉበት ብቻ አይደለም፡፡ይቅርታ ማለት ሰጥቶ መቀበል ያለበት ውስብስብ ነገር ነው፡፡የምንሰጠውና የምንቀበለው ነገር አይነቱ ግን ሊለያይ ይችላል፡፡ወያኔ በስተመጨረሻ ተገዶ ለድርድር ከቀረበ የሚፈልገው የብሄራዊ እርቅና የይቅርታ አይነት ከላይ ካናት ያለውን ተራ የፖለቲካ ስልጣንን ለስልጣን ሰግብግቦች አስረክቦ በተቃራኒው ግን የገናባውን ትልቅ የኢኮኖሚ የሚሊታሪ የደህንነት የቢሮክራሲ ወዘተ በዘረኛነት ላይ የተመሰረተ ኢምፓየርና መዋቅር እንደተጠበቀ ሆኖ ላለፉት 40 ዓመታት ያህል ከሰራውና አሁንም እየሰራ ካለው ሀገር አጥፊ ወንጀልና ጥፋት ከደሙ ንፁህ ነኝ ብሎ ከማንኛውም ተጠያቂነትና ካሳ ለመራቅ ነው፡፡የመለስን ራእይ እናሳካለን አንዱ ዋና መሰሪ አካሄድና ነጠላ ዜማም ይህንን አደገኛ ሀገራዊ ጥፋት ለዘለቄታው ለመሸፋፈንና ከማይቀረው ተጠያቂነት ለመሸሽ የታቀደ ስልት ነው፡፡ስለዚህም ብሄራዊ እርቅ ዝም ብሎ ከአናት ባለ የስልጣን ልውውጥ ብቻ በችኮላ የሚከናወን ነገር አይደለም፡፡ስለ ብሄራዊ እርቅ ስናነሳ ወያኔን ብቻ ላደረሰው ጥፋት የሚወነጅል ብቻ ሳይሆን ሌላውንም የተቀረውን ኢትዮጵያ ህዝብና ዜጋ ተቃዋሚ ይህ ሁሉ ጥፋት ሲፈፀም ለምን ዝምታንና ተባባሪነትን መረጠ የሚለውን ጭምር ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት፡፡በስነ-ልቦና ጠበብበት እይታ ከሆነ በእኛ ላይ ለሚፈፀም በደልና ጭቆና እኛው እራሳችን ጭምር ለበዳያችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተባባሪ የምንሆንበት ብዙ አጋጣሚዎች እንዳሉ ነው፡፡So we need to have this deepest sense of honesty responsibility and wisdom when we talk about any sort of abuse and the other corrective and restorative side of ensuing forgiveness.ይህ ሲሆን ነው እውነተኛ ይቅርታና ስርየት በዚህች ሀገር ላይ ሊመጣ የሚችለው፡፡ወያኔዎችም ዛሬ ስልጣናቸውና ሃይላቸው ያመጣላቸውን የበላይነትና አራጊ ፈጣሪነት እንጂ ነገ ከነገ ወዲያ የሚያመጣባቸውን ተጠያቂነት በይቅርታና በመቻቻል ግርግር እንሸፋፍነዋለን ብሎ ማለት እንደ ኖህ ዘመን ሰዎች ባለን ጊዜ አሸሸ ገዳሜ ብለን በተቀረው ጊዜ ንስሃ እንገባለን አይነት አደገኛ የጥፋት መስመር መከተል ይመስላል፡፡

  8ኛ)ተቃዋሚው ብቻ ሳይሆን ህዝቡና ዜጋው ጭምር በራሱ ተጠያቂና ተወቃሽ ጭምር ነው፡፡ህዝብ ፍትህን ነፃነትንና ዲሞክራሲን እንደ ምግብ ቤት ሜኑ አቤት ምን ልታዘዝ እያሉ ተቃዋሚዎች ብቻ እየተንቀሳቀሱ ዝም ብለው ህዝብ ያለበት ያለመንቀሳቀስ የምቾት ቦታ ላይ የሚያቀርቡለት አድርጎ መታሰብና መቅረብ የለበትም፡፡ሁላችንም የምንታገለው ቅድሚያ ለራሳችን ህልውና ጭምር መሆኑን መረዳትና ማመን አለብን፡፡ወያኔም ዛሬ እያደረገ ያለው እኔ መስዋእትነት በከፈልኩበት እናንተ የድሉና የጥቅሙ ተሳታፊ መሆን አትችሉምና እኔ ነኝ እንደፈልግሁ የማስተዳድራችሁ እያለን ነው፡፡ስለዚህም ህዝብ ተቃዋሚ ብቻውን ታግሎ ዲሞክራሲ ነፃነት ፍትህ በየደጁና ቤቱ ድረስ እንዲሰጠው መጠበቅ የለበትም እራሱም የድርሻውን መታገል አለበት፡፡
  9ኛ)ሌላው ታሪካዊውና ተጨባጩ ሀገራዊው ጉዳይ ከአለም አቀፋዊው ታሪካዊውና ተጨባጩ ውስብስብ ግሎባል ፖለቲካል ኢኮኖሚ ጋር በእጅግ የተቆራኘ እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡አሜሪካንንና እንግሊዘን በዋናነት ማእከል ያደረገው የግሎባል ካፒታሊዝም እና ከቀዝቃዛው ጦርነት ጋር የተያያዘው የሶሻሊዝም ጉዳይ እንደቀልድ አፈር የለበሰ ጉዳይ አይደለም፡፡አለም አቀፍ የሃይል ሚዛን አሰላለፍ በሀገራችን ፖለቲካ ላይ የራሱን ከፍተኛ ተፅእኖ እየተጫወተ እንደሆነ ማመን አለብን፡፡ስለዚህም ከመለስ/ወያኔ እና ኢሳያስ/ሻእብያ ጀርባ ምን አይነት የሃይል አሰላለፍ እንዳለ መጥሞና መመርመር አለብን፡፡

  ለማንኛውም የሚሰማኝን ማውራቱ በዚህ መንገድ ላብቃ፡፡

  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!

 11. አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ
  | #11

  … በተለይ የተቃዋሚውንም ሆነ የሚታገሉትን ወኔ የሚሰልቡ
  ተከታታይ የቁጭ-በሉ ትያትርን በማሳየት የተግል አቅጣጫ ጠምዛዦች
  ፊልሞችን በወሲብ እያስታከኩ በመቅረጽ በርካሽ የሚያሰራጩ
  ከሕንድና ከቻይና መጥተው በሚታገዙ ርካሽ ቀራጮች
  በዕፅ በበለጸጉ አንዳንድ የጃማይካ ደላላ ኢትዮጵያዊነትን የደረቡ ጉደኞች
  ባጠቃላይ ኢትዮጵያን ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ነፃነቷን የሚሰርቋት ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እያንዳንድችሁን ጠንቅቆ ያውቃልና ማንነታችሁን ብትደብቁ ይሄውና ፈተናው::
  ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች::
  ባንዳ ላይ ይትፉና!!!

  የምን ጠጋ ጠጋ የምን ልጥፍ ልጥፍ:-
  የምን መተሻሸት የምን ውትፍ ውትፍ::
  የምን መልመጥመጥ ነው
  የምን ደፋ ቀና:-
  የሚፈሰው ደሙ መቼ ደረቀና::
  ድንጋይ ያቀበሉ ስንሞት ትናንትና:-
  እስኪ ዛሬ ያሳዩን ባንዳ ላይ ይትፉና::
  እኮ ምን ተገኝቶ አጨብጫቢዎቹ
  በዚህ በዚያ ገብተው እዚህ ተከማቹ???
  ይቅርታን ነፍገው ሕዝብን እንደናቁ
  እንዴት ባደባባይ ለመታየት በቁ?????
  ቀረ’ኮ ይሉኝታ ቀረ’ኮ መደበቅ:-
  በጉጅሌ ጉያ ሕዝብ ላይ መሳለቅ::
  መሓሙድም ሆነ እነአስቴር አወቀ:-
  ሕሊናቸው ትናንት የተጨማለቀ:-
  ምን እንዳደረጉን ሕዝቡ እያወቀ
  እንዴት ባንዲት ጀንበር ግፋቸው ተፋቀ???
  ዛሬም እነሱን አይተው የሚጨማለቁ
  የሕዝብ እንዲሆኑ
  እውነቱን እንዲያውቁ:-
  ድንጋይ ያቀበሉ
  ስንሞት ትናንትና:-
  እስኪ ዛሬ ያሳዩን
  ባንዳ ላይ ይትፉና::

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።