የተቃውሞ ሰልፎች እየቀጠሉ፣ የብርቱካን ትፈታ ድምጽ እየበረከተ ነዉ ! -የካናዳ ሰልፍ

May 26th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

በቶሮንቶና በኦታዋ ከበርቱካን መታሰር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰልፍ ይደረጋል-

ግንቦት 18 ቀን 1፡00 AM

ግንቦት ሰባት 2001 ዓ.ም፣ በተለያዩ የአለማችን ከተሞች ኢትዮጵያዉያን በወያኔ-ኢሕአዴግ ላይ ያላቸዉን ተቃዉሞ ሲያሰሙ እንደነበረ በሰፊዉ ተዘግቧል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ አንጋፋዉ የኢትዮጵያዊነት አቀንቃኝ ቴዲ አፍሮ እንዲሁም ሌሎች በርካታ የፖለቲካ እሥረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ የሚጠይቁ መፍክሮችን እያሰሙ ለትግሉ ያላቸዉን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ነገ ግንቦት አስራ ስምንት ቀን በኦንቶሪዮና ኬቤክ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወያኔ-ኢሕአዴግን በመቃወም፣ ከነ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ጎን መቆማቸዉን ለማረጋገጥ በካናዳ ትልቁ ከተማ በሆነችዋ የቶሮንቶ ከተማና፣ በካናዳ ዋና ከተማ ኦታዋ ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደርጋሉ።

የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶች እርስ በርስ በነበራቸዉ አለመስማማት በቶሮንቶና ኦታዋ ብዙ መኖር የነበረበት ትልቅ እንቅስቃሴ መኖር እንደነበረበት ያለልነበረ እንደሆነ የታወቀ ነዉ። ነገር ግን አሁን በቶሮንቶና ኦታዋ ያሉ ኢትዮጵያዉያን በአንድነት መሰባሰባቸዉና መተባበራችዉ ለትግሉ ትልቅ ድል ለወያኔ-ኢሕአዴግ ደግሞ መርዶ እንደሆነ የሚያሳይ ነዉ የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ።

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ አሁንም በግፍ በጨለማ ቤት ዉስጥ የምትገኝ ሲሆን፣ ገዢዉ ፓርቲ ፍቃዷንን ቁርጠኝነቷን ለመስበር ብሎም በመንፈስ እርሷን ለማበርከክ በነፍሰ ገዳዮች ላይ ሁሉ ያልደረሰ ግን እየፈጸመባት ነዉ፡፡ ወያኔ መሰለዉ እንጂ በብርቱካን ላይ እየወሰደ ያለዉን እኩይ ተግባር በቀጠለ ቁጠር፣ እራሱን እየጎዳና እየገደለ እንደሆነ የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም።

«ለወያኔ የፖለቲካ ክስረት ከማምጣቱም በተጨማሪም፣ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰር ኢትዮጵያዉያንን አንድ እያደረገ እንደሆነ በቶሮንቶና በኦታዋ የሚደረገዉ ሰልፍ ያሳያል» የሚሉ ተንታኞች፣ «ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከታሰረች ጀምሮ አለም አቀፍ እዉቅናዋ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ ያደገ ከመሆኑም የተነሳ፣ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ ከቀድሞ ተቃዋሚዎቿ ሁሉ ሳይቀር አክብሮትና ፍቅርን እያገኘች እንደሆነ በሰፊዉ እየታየ ነዉ» ያላሉ።

የካናዳዉን ሰልፍ በሁለቱም ከተሞች ከ 12፡ እስከ 1:30 የሚደረግ ሲሆን፣ ዜናዎች እንደደረሰን በሰፊዉ እንደምንዘግብ እየገለጽን እንድትከታተሉ ጥሪ እናቀርባለን።

 1. አቢይ፡ኢትዮጵያዊ
  | #1

  )))))))))))የብርቱካን፡እሳት!!!(((((((((((
  ተንኮልን፡ያልጫረ፤
  ደም፡ያልተነከረ።
  ዕውቀት፡የቋጠረ፤
  ለሰላም፡ያደረ።
  ይፋጃል፡በጠዋት፤
  የብርቱካን፡እሳት።
  እሳት፡ነው፡የፋመ፤
  ውስጥ፡ውስጡን፣
  የጋመ።
  በቀላል፡የማይነድ፤
  በትዕግስት፡አመድ፤
  ተዳፍኖ፡የረመጠ፤
  ትግል፡እያማጠ፤
  እያማጠ፡ፍቅር፤
  ለኢትዮጵያ፡ሲያዘምር፤
  ይፋጃል፡በጠዋት፤
  የብርቱካን፡እሳት።
  ገና፡ገና፤
  ይለበልብና፤
  አልነደደም፡ሲባል፤
  ሐቅንም፡ያግታል።
  ትናንትና፤
  ቀን፡ተቆጠረና፤
  በእድሜአቸው፡ቢጠሩ፤
  እንዲመሥክሩ፤
  ሽማግሌ፡ሆነው፡መናገሩን፡ፈሩ፤
  ከነማተባቸው፡በየጓዳ፡ቀሩ።
  ግና!!!!
  ግፍ፡አይቀርምና።
  ደም፡ያልተነከረው፤
  ዕውቀት፡የቋጠረው።
  ለሰላም፡ያደረው፤
  አሳዶ፡ ‘ማይምረው።
  ይፋጃል፡በጠዋት፤
  የብርቱካን፡እሳት።
  ሰማን፡ትናንትና፤
  በድንገት፡ሆነና።
  አመፁ፡በርክቶ፤
  ፈነዳ፡መርካቶ።
  ፈነዳ፡በዓለም፡ላይ፤
  ሕዝብ፡ወጣ፡አደባባይ።
  ለእነቴዲም፡ጮህን፤
  ለእስረኞች፡በሙሉ፤
  ሰሚ፡ጠፋ፡ግና፣
  ይቀጥላል፡ትግሉ።
  እናም!!!
  ፈሰሰም፡አልፈሰሰም፤
  በፍትሕ፡ዓለም፤
  ደም!!!
  ሙት፡አይደለም።
  ዝግጁ፡ነው፡በግልፅ፣
  ሰንጥቆ፡ለማጋት፤
  ለብልቦ፡ያሳምናል፣
  የብርቱካን፡እሳት!!!

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።