ቀደምት፡ምሳሌዎች – ብርዞ ፍራንክፉርት

May 26th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ባላቸው፡ተሰጥዎ፡መኖር፡እየቻሉ
ገንዘብ፡የሚያዘውን፡ቅንጦት፡ነገር፡ሁሉ
ግን፡እውቅናቸውን፡ለሃገር፡ያዋሉ
ቀደምጥ፡ምሳሌዎች፡ለዜጐች፡በሙሉ
ርህሰ፡ሃኪም፡ፕሮፈሰር፡አስራት
በስራ፡ያሳለፉ፡ወገንን፡በመርዳት
ወያኔ፡ሲጀምር፡ማፍረስ፡ሃገሪቱን
ባንዲራ፡ማጣጣል፡ሲጀምር፡ንቀቱን
በእረፍትና፡በቤተሰብ፡በጡረታ፡ፋንታ
የሃገር፡ጉዳይ፡መጣ፡የማይሰጥ፡ፋታ
ወያኔን፡ታገሉት፡ተጋፍጠውት፡ከፊት
ሃገሬን፡አትበትን፡ነጻነቴን፡አሉት
የለፉላት፡ሃገር፡ሙሉ፡ህድሜያቸው
ሰርጾ፡በገባው፡ህውን፡ፍቅራቸው
ዳግም፡ልትቆረስ፡ሳያዩ፡ይህን፡ውርደት
አርሓያ፡ሆኑ፡ከፍለው፡ውድ፡ህይወት
ይብቃን፡አንዳለፈው፡ብሎ፡ይሁን፡ሰላም
ለአዲስ፡ምህራፍ፡ምኞት፡መድረኩን፡ቢጠቀም
ወህኒ፡የወረደው፡ያከያኒ፡ወጣት
ለብሩህ፡ህይታው፡ለአንድነትዋ፡ጽናት
ነበረ፡ምሳሌ፡ለነአቶ፡ዝምታ
ተሰልፈው፡ያሉ፡በታዋቂ፡ተርታ
መብት፡ተደፍጥጦ ህግ፡አልባነት፡ሰፍኖ
መግረፍና፡መግደል፡ተራ፡ነገር፡ሆኖ
በደም፡ግፍ፡ተሳክሮ፡ወያኔ፡አበደ
ብሐራዊ፡ስሜት፡ሃገር፡እየናደ
ሴራ፡ጐነጐነ፡መርዝን፡አሰናዳ
የድንበሩ፡ለጋሽ፡አባመስጠት፡ባንዳ
በማለዳ፡አውቀው፡ይህን፡እኩይ፡ስራ
ጠመንጃ፡አምላኩ፡የጨካኞች፡አውራ
ትልሙ፡እንዳይሰምር፡እየተናነቁ
ትናንት፡የወደቁ፡ዛሬም፡የሚወድቁ `
የህሊና፡እስር፡ጭቆና፡ባርነት
ታግለውት፡ያልፋሉ፡ዳግም፡ላያወርሱት
የብርቱካንና፡የብዙሺ፡እስረኞች
የአዋሳ፡ጋምቤላ፡የአርባምንጭ፡ሰማህቶች
በግፍ፡ለተፈጁት፡የኢትዮጵያ፡ሊጆች
ለደማቸው፡ፍትህ፡እንጩህ፡ወገኖች
በምድርዋም፡ሆነ፡የምትኖር፡በውጪ
ወገንህ፡ከፍሎዋል፡ለህውቀትህ፡ምንጭ
ሲገፋ፡ሲዋከብ፡ሲታጐር፡ጨለማ
መቼ፡ልትደርስ፡ነው ጥሪውን፡ካልሰማ
ስንቱ፡ቤት፡ሲዘጋ፡ለመብቱ፡ሲጋደል
ተመልክቶ፡አልፎ፡ነገ፡ሊደላደል
የዜጋ፡መሆዶ፡አደራ፡የረሳ
ራሱን፡ይጠይቅ፡ሰው፡ነው፡ወይ፡እንሰሳ
ሃገርን፡ታደጋት፡መላበል፡በጊዜ
ሃገሬ፡ቅበሩኝ፡የሚባል፡ኑዛዜ
በሃገር፡ለተዋለ፡ግን፡ላገር፡ላልዋለ
ይቅለለው፡የሚባል፡አፈርስ፡የታለ
ሰንደቅዋ፡ከፍያለ፡በዜጐችዋ፡ታፍራ
በልጆችዋ፡አንድነት፡የምትኖር፡ተከብራ
ለዜጐችዋ፡እኩል፡የሆነች፡መመክያ
ትጠበቅ፡በሁሉም፡እናት፡ኢትዮጵያ

 1. ደበበ
  | #1

  ራሱን ቄሲስ እያለ የሚጠራው አቶ አስተርአየ የተባለው ግለሰብ ዛሬም የለጠፈውን አነበብሁትና እጅግ ገረመኝ

  ደብረ ሊባኖስ ገዳም ውስጥ ዳቤ ሲበላ መክረሙንና የሊቃውንቱን ስም ስላወቀ ብቻ ሊቅ የሆነ እየመስለው የባጥ የቆጡን ይቀባጥራል ::

  የጥጽሑፉ ሁሉ ዋና አላማ የሚጠላውን ግለሰብም ይሁን ቡድን ለመወረፍ ካልሆነ በቀር : ምንም አይነት ትምሕርት ሰጪ ፍሬ ነገር አይገኝበትም ::

  ቆሞሳት : መጨኔዎች ናቸው : እንጀራ ቆጣሪዎች…እያለ ባልተገረዘ ደፋር አንደበቱ የሚያዋርዳቸው ቆሞሳት አባቶች የታላላቅ ገዳማት አበ ምኔቶች የሆኑና በእውቀታቸውና በመንፈሳዊ ህይወታቸው የተመሰከረላቸው ናቸው ::

  ሰውዬው ግን በተገኘበት ኑፋቄ ክህነቱ ተገፎ ስለተባረረ ብቻ : ቂሙን ለመወጣት በማሰብ ብቻ ጧት ማታ : በተከበሩ አባቶቻችን ላይ የስድብ ናዳ ያወርድባቸዋል ::

  እግዜር ይቅር ይበልህ ::
  መጨኔ ማለት እኮ : በቤተ ክርስቲያን ውስጥ : በማኅሌት ጊዜ ከሊቀ ጠበብቱና ከአጋፋሪው መመሪያ እየተቀበለ ማስተናበርና : እንዲሁም ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣውን ምግብ በስርአት ሆኖ እንዲስተጋድ ማድረግና ማስተናበር ነው ::

  ቆሞሳት ማለት ደግሞ : ለማመንኮስና አዳዲስ ቤተ ክርስቲያን ሲተከል ከጳጳሱ እየተላከ የሚባርክ ነው ::
  ለቆሞሳቱ : ከዚህ ያለፍ ስልጣንም ሆነ ሃላፊነት የላቸውም :
  አንዱን ከአንዱ እያማቱ በባዶ ሜዳ አዋቂ መምሰልና : ስለ ሃይማኖቱ ብዙ የማያውቀውን ህዝብ ግራ ማጋባት : ቤተ ክርስቲያኗንም ሰድቦ ለሰዳቢ መስጠት : የተከበሩ አባቶችንም ብስሉን ከጥሬው ሳይለዩ በጅምላ መጨፍጨፍ ስርየት የሌለው በደል ነው ::

  “ሰውን የሰደበ ኃጢአቱ ይሰረይለታል : መንፈስ ቅዱስን የሰደበ ግን ኃጢአቱ አይሰረይለትም” የሚለው የቃሉ ፍርድ ይጠብቀዋል ::
  ቅዱስ ያዕቆብ “በአሐቲ ቃል ንሴብሖ ለእግዚአብሔር : ወበአሐቲ ንረግሞ ለወልደ እጓለ እመሕያው” እንዳለው :: የእግዚአብሔርን ቃል በግዕዝ ጠቅሶ በስድብ የሚተረጉም አደናጋሪ ግብዝ ግለሰብ ነው ::

  የዛሬውን አንብበናል : የሚቀጥለውን ሳምንታዊ ርግማን ደግሞ በምሬት እንጠብቃለን ::
  ከክፉ ሰው : የክፋትን ክፉነት መማር ከተፈለገ : አቶ አስተራየ በቂ የክፋት አስተማሪ ነው ::

 2. ከካምፖ
  | #2

  ከካምፖ ከዘጠና ሰባቱ ምርጫ ወዲህ ማንንም አይወክሉም በተደረገው ምርጫ ወድቀዋል ሆኖም ህያዩ ስልጣን አያስረክቡም አንድ አባባል አለ ጅብ ሌሊት የሠራውን ስለሚያውቅ ቀን ከሰው ይሻሸል

 3. ከካምፖ
  | #3

  ከካምፖ ወያኔ የ ሕዝብ ን ስልጣን አስረክቦ መሄድ ስገባው ሕዝቡ ን በመፍጃት ላይ ነው ስልጣንን ህንደ ማር ጭናት ብንወስድ የማር ጭናትን ሁሉም ሰው አይደለም ከቦታ የሚያደርሳው ወያኔ የማሩን ጭናት ክቦታ ሳያዳርስ መንገድ ላይ ጨረሳው

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።