የደብረማርቆስ እርሻ ኮሌጅ ተማሪዎች በግፍ ተባረሩ

May 26th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም

ደብረ ማርቆስ በሚገኘዉ የእርሻ ኮሌጅ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊስ መከበባቸዉን ዘግብነ ነበር።፡ከደብረ ማርቆስ የደረሰን ዜና እንደሚጠቁመዉ ተማሪዎች በጠመንጃ ኃይል እየተደበደቡ ከኮሌጁ ጊቢ በግፍ ተባረዋል።

ደብረ ማርቆስ የሚገኘው የእርሻ ኮሌጅ በየዓመቱ ተማሪዎቹን ለጥናትና ምርምር ተግባር ወደ ገጠር የሚልክ ሲሆን ተማሪዎቹ ወደ ገጠር በሚሰማሩበት ጊዜ ከመኖሪያ ቅጥር ግቢያቸው ርቀው ስለሚሄዱና ተጨማሪ ወጪም የሚያስከትልባቸው በመሆኑ ትምሕርት ቤቱ ለዚህ ማካካሻ የሚሆን የውሎ አበል የመክፈል አሰራርባ ልማድና ነበረዉ።

ዘንድሮም ተማሪዎቹ ለተመሳሳይ ተግባር ለመሄድ እንዲዘጋጁ ተነግሯቸዉ። የሚያስፈልገዉን ዝግጅት ካደረጉ በኋላ ጉዙ እንዲጀምሩ መመሪያ ይሰጣቸዋል። ለጉዞዉ የሚያስፈልገዉ የጉዞው የውሎ አበል ያልተከፈላቸው በመሆኑ ተማሪዎቹ እንዲከፈላቸው በተማሪዎች ማሕበር ተወካዮች በኩል፣ ሕጋዊና የትምህርት ቤቱን ህግ ደንብ በጠበቀ መልኩ ጥያቂያቸዉን ያቀርባሉ። የኮሌጁ አስተዳደር ጥያቄውን ተቀብሎ መልስ በጊዜዉ ሳይሰጠቸው በመቅረቱ፣ ለምርምር ሥራዉ ደግሞ አለ ወጪ መጓዝ ስላለሚያስቸግር፣ በትምህርት ቤቱ ደንብ መሰረት የውሎ አባል የማይከፈል ከሆነ ባሉበትና በሚኖሩበት የኮሌጁ አካባቢ ምርምሩን እንዲያካሂዱ ሃሳባ በማቅረብ ሳይጓዙ ይቀራሉ።
ተማሪዎቹ አሁንም ላቀረቡት ጥያቄና ላቀረቡትም ሃሳብ መልስ ሳያገኙ ቆይተው በድንገት ዛሬ ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም ጥያቄውን ያነሱት የኮሌጁ የእርሻ ተማሪዎች በሙሉ፣ ታጥቀው ግቢውን በድንገት በወረሩት የፌዴራል ፖሊስ አባላት በመገደድ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ይደረጋሉ። ይህን ያዩ ሌሎች የትምሕርት ቤቱ ተማሪዎችም አብረው ግቢውን ለቀው ወጥተው አሁን በአንዲት ቤተክርስቲያን ገረገራ ስር ተኮልኩለው ይገኛሉ።

ምንም የሌላቸው ምስኪኖችና ከኮሌጁ ውጪ ማንንም የማያዉቁ በመሆናቸዉ ተማሪዎቹ ተባረው ሲወጡ የት ሄደው እንደሚጠጉ፣ የት እንደሚያድሩ፣ ምን እንደሚበሉ ጨርሶ አያወቁም። የአካባቢዉ ባላሥልጣናት በሰለጠነ መልኩ ተማሪዎች ማነጋገር ሲገባቸዉና የተማሪዎችን ጥያቄ እንደ ሰዉ መመለስ ሲኖርባቸዉ በድንገትና በእብሪት ይህን አይነት አረመኒያዊ ድርጊት በዜጎች ላይ ማድረጋቸዉ ምን ያህል በአገራችን የሰፈነዉ ስርዓት ለስብእና ክብር የሌለዉና ሕዝቡን የናቀ እንደሆነ ያሳያል ሲሉ ነበር በስፍራዉ ያነጋገርናቸዉ ዘጋቢዎች የገለጹልን።

ለተማሪዎች የተመደበውን ገንዘብ፣ ገዢው ፓርቲ በሌሎች ክልሎች እንደሚያደርገው ሁሉ ምርጫውን ለማሸነፍ እንዲረዱት ከእያንደንዱ ክፍል አሥር አሥር ተማሪዎች በመምረጥና በካድሬነትና በመልማይነት በመመደብ በየቀኑ ሰላሳ ሰላሳ ብር እየከፈለበት እንደሆነ ተማሪዎች ለዘጋቢዎቻችን ገልጸዋል።

ይህ በተማሪዎች ላይ የሚደርሰዉ በደል እስከ ምርጫዉ መጠናቀቅ ድረስ የሚቀጥል እንደሆነ የሚናገሩት በስፍራዉ ያሉ ተማሪዎች ገዢዉ ፓርቲ እንደሚለዉ ለትምህርት መስፋፋት ፣ ለእድገት ለዜጎች ደህንነት የቆመ ሳይሆን ለራሱ ርካሽ የፖለቲካ ጥቅምና ስልጣን ማራዘሚያ የቆመ ነዉ ሲሉ ድርጊቱን አዉግዘዉታል።

 1. be safe my brother ans sisiter
  | #1

  we need peacful struggle any way

  Thank

 2. ይሁን
  | #2

  በርታ ጨምርበት በበደል ላይ በደል፣
  ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል:

 3. ጞዳየ የደንቃቸው
  | #3

  ስላምታ ክ ደበረማርቆሰሰሰሰሰሰ

  ግደይ ነኘ

  ጉንበት 2001

 4. Meyisaw
  | #4

  Lela ako aydelem, yaw teregteh tegeza wey kindihin ansa new negeru

 5. ሰናይ
  | #5

  አቶ ተስፋዬ ገብረ አብ (የጋዜጠኛው ማስታዎሻ በሚለው ድርሰቱ) እንደነገረን

  ወያኔ : ኦነግን ለማስፈራራት በሚል ፈሊጥ ታዋቂ የኦሮሞ ተወላጆችን : በካድሬዎቹ አማካኝነት በጠራራ ፀሀይ ሲያስገድል ከረመና ያ በግፍ ያፈሰሰው ደም አስክሮት ይመስላል :

  አሁን ደግሞ አፈ ሙዙን ወደ አማራው አዙሯል
  ዛሬ : ደብረ ማርቆስ : ከዚያም ጎንደር : ወሎ : ደብረ ብርሃን………. እያለ የዘር ማጥፋቱንና ትውልድ የማጥራቱን ሴራ ሊቀጥልበት እንደተነሳ ከዚህ መረዳት ይቻላል ::

  የሚገርመው ግን ኦሮሞውም ሆነ አማራው በራሱ ባንዳ ልጆች ሲረሸን ከዚህ አስከፊ ህይወት ለመላቀቅ በጋራ የሚያሰማው ድምጽም ሆነ የሚወስደው አቋም አለመኖሩ ነው ::

  “አንድ እግር በርበሬ መንቀል አቅቷችሁ
  አንድዶ ለብልቦ አቃጥሎ ይጃችሁ”

  አለች አሉ : በቴዎድሮስ ጊዜ የነበረች አንዲት አስለቃሽ

 6. አየ ማልከሰ
  | #6

  አሁንስ ለአነባቢወ የሰለችህል አዳመ መን የተበካል የአመሪካ ወታደር መቶ ሊዋግለት አየ ከለድ

 7. ከበበው
  | #7

  @be safe my brother ans sisiter
  there is no peacful struggle u r talking about ወያኔ

 8. ቶክቻው
  | #8

  እኔን የሚገርመኝ የጊዜው ባለስልጣን ነን ባዮች በወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው ላይ ግፍ ሲፈጽሙ ዘላለማዊ የሚሆኑ መስሎአቸው ይሆን? በሰፈሩት ቁና መሰፈሩ እንደማይቀር የሚያዩበት ቀን ሩቅ አይሆንም…. ሌላው ነገር when do we start the struggle face to face to overthrow this shit narrow minded’s regime? We shouldn’t wait till our people become senseless and lack his motherland love. Ginbot 7, Let’s start the fight… we are waiting for whom?

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።