የአስመራ ትዝታዬ ግርማ ካሳ muziky68@yahoo.com

May 28th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

zenawi_issayas_victimsበጠቅላይ ሚኒስትር መለስዜናዊ ወይንም በፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በግፍ የታሰሩ ሰላማዊ ወገኖቻችን መካከል በጥቂቱ ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ ፣ ፓስተር ሃይሌ ነዕዝጊ ፣ ፓስተር ዶር ክፍሉ ገብረመስቀል ፣ ፓስተር ተስፋጽዪንሃጎስ ፣ አርስቲስት ቴዎድርሶ ካሳሁን (ቴዲአፍሮ) ከግራ ወደቀኝ ስዘረዝራቸዉ።

በቅርቡ የኢትዮጵያ ሪቪዉ ዋና አዘጋጅ አቶ ኤሊያስ ክፍሌ በድህረ ገጻቸዉ ላይ አሥመራ ሆነዉ የተነሱትን ፎቶግራፎች ተመለከትኩኝ። የአስመራ ዮኒቨርሲቲ ተማሪ የነበሩኩኝ ጊዜ በዚያ ያሳለፍኩትን አመታት አስታወሰኝ።

ብዙ ጊዜ በፖስት ካርድ ላይ የምናየዉ፣ ዘንባባዎች በዳርና በዳር ያሉበት መንገድ የሚያልፈዉ፣ ፒያሳ ወይንም ኮምፖሽታቶ በሚባለዉ ሰፈር ነዉ። በዚያ መንገድ ብዙ ኬክ ቤቶችና ቡና ቤቶች ነበሩ። ትዝ ይለኛል በአምሳ ሳንቲም አንድ ኬክና ምን የመሰለ ካፑቺኖ እናዝ ነበር። በተለይም ሲመሽ ከመብራቶቿ ጋር ከተማዋ በጣም ታምራለች።

ከከተማዉ ዉበት ባሻገር የማልረሳዉና በዉስጤ የተተከለ አንድ ሌላ ነገር ቢኖር የሕዝቡ ፈሪሃ እንግዚአብሄርነትና ደግነት ነበር።

እስቲ አንዳንድ ያጋጠሙኝ ላጫዉታቹህ። አንድ ቀን በዮኒቨርሲቲ ዉስጥ ወዳለዉ ካፍቴሪያ እራቴን ለመብላት እየሄድክ ሳለ ጓደኞቼ አገኙኝና «አትሄድም እንዴ ? » አሉኝ። «የት ?» አልኳቸው። «ንግደት» አሉኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ያንን ቃል የሰማሁት። ጓደኞቼ ነገሩን ያወቁ ነበርና ምን እንደሆነ በኋላ አስረዱኝ።

ያን ቀን በአስመራ በሰሜን ምዕራብ በኩል ቪላጆ የሚባል ሰፈር፣ የሚካኤል ይሁን የገብርዔል ቤተ ክርስቲያን አለ። (የቱ እንደሆነ አሁን አላስታወስም)። የዚያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት የሚወጣበት ቀን ነበር። ታዲያ ቤተ ክርስቲያኗ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ታቦቱ በነገሰበት ቀን ግብዣ አድርገዉ በአካባባዉ ያሉትን ሁሉ ይጋብዙ ነበር። ይሄ ስርዓት ነዉ እንግዲህ ንግደት የሚባለዉ።

ያኔ መኪና የለንም። በእግራችን ከአንድ ሰላሳ ደቂቃ በኋላ በቪላጆ ደረሰን። አራት ተማሪዎች ነበርን። በሰፈሩ ስንሽከረከር «ኑ ግቡ» ብሎ የሚጠራን ሰዉ አጣን። ለካ ኑሮ በጣም ስለተወደደ እንደድሮ በየመንገዱ እየቆሙ «ብሉልን ጠጡልን» ማለት ቆሟል። «መቼም የዩኒቨርሲቲ ካፍቴሪያ ምግባችንን ትተን ባዶ ሆባችንን አንመለስም» ብለን ወደ አንዱ ቤት አመራንና አንኳኳን። «እንኳን አደረሳቹህ ? » ስንል ፣ አንዲት ያኔ ወደ አርባ አመት የሚጠጋት እናት፣ በእጇ አንድ ሕጻን ልጅ ታቅፋ ወጣችና «ግቡ፣ ግቡ » አለችኝ በፈገግታ። የቤቱ በር ጠባብ ነበር። ጎንበስ ብለን ገባን። የነበረችዋን ጠረቤዛ ከበብናት። በትልቅ ትሪ እንጀራ ቀረበልን።፡ከዚያ ሴትየዋ ድስቱን አመጣችና ወጡን እንዳለ እጀራዉ ላይ ደፋችዉ። ብዙ ጊዜም አልፈጀብንም ትሪዉን ጠረግነዉ። ከዚያም በትላልቅ ጣሳዎች ጠላ አመጣች። ምን ልበላቹህ ምን የመሰለ መስተንግዶ ተደረገልን።

አሰመራን ሳስብ፣ የአስመራ ነዋሪዎችን ሳስብ ያቺን ሴት አስባለሁ። ለእግዚአብሄር ፍቅር ስትል፣ እንግዳን በደስታ የምትቀበል ! ችግረኛ ናት ፣ ነገር ግን ከፊቷ ውስጣዊ ሰላም ያላትና ሰዉን የምትወድ ትልቅ ሴት ነበረች!! ያኔ በትግሪኛ አይደለም ያናገርናት። «የኔ ዘር ናቸዉ» ብላ አልነበረም ያስተናገደችን። ነገር ግን ትልቅ ሴት በመሆኗ እንጂ።

የማያልፍ ነገር የለምና የዪኒቨርሲቲ ትምህርታችንን አጠናቀን የምረቃችን ቀን ደረሰ። ባጽእ (ምጽዋ) በሕዝባዊ ሀርነት ኤርትራ ግንባር ሥር ከወደቀ በኋላ በምጽዋና በአስመራ መሃከል ከሚገኝ አንድ የከፍታ ቦታ፣ «ግራፒ» እንለዉ የነበረ ከሩቅ የሚተኮስ መድፍ በየጊዜው አስመራ ከተማ ላይ ያርፍ ነበር። በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ መብረሩን አቁሞ ነበር። (የጦር አይሮፕላን ግን ማረፉን አላቆመም)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለማይበርም ቤተሰቦቻችን ለምረቃችን ከአዲስ አበባ ሊመጡ አልቻሉም። ስለዚህ የምረቃ ስነ ሥርዓታችን ብዙ አልጓጓንለትም ነበር።

የምረቃችን ስነስርዓት ቀን በወንዶች ሽንት ቤት ዉስጥ ትልቅ ፈንጂ ፈነዳ። ያን ሰዓት ትልቅ ድንጋጤ በዩኒቨርሲቲ ጊቢ ዉስጥ ለጥቂት ደቂቃዎች ተፈጠረ። ወዲያዉ ሻቢያ የደስታ መግለጫ መልዕክት ማስተላለፉ ነዉ ብለን ቀልደን አለፍን። ከሩቅ በሚተኮስ መድፍ በግራፒ ተምሮ በፈንጂ መመረቅ ይሉታል ይሄ ነዉ።

ያ ቀን ከፈንጂ ፍንዳታዉ ሌላ የማልረሳዉ፣ በጣም ልቤን የነካና ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ዘላቂ ፍቅር እንዲኖረኝ ያደረገ አስደናቂ ነገር ሆነ። ቤተሰቦቼ ከአዲስ አበባ ስላልመጡ የምረቃ ልብሴን አዉልቄ ወደ ዶርሚተሪ ለማምራት እየተዘጋጀሁ ሳለ ድንገት፣ አንዲት ሴትዮ አበባ ይዘዉ ብቅ አሉ። ትዬ ዘይዳ ነበሩ። ትንሽ እንደቆየዉ ደግሞ አንዲት አሮጊት ሴትዩ ሌላ እቅፍ አበባ ይዘዉ መጡ። አደይ ጸሃይቱ ነበሩ። ሁለቱም አይተዋወቁም። በአራት አመት የአስመራ ቆይታዬ የተወዳጀኋቸዉ እናቶች ናችዉ። ያኔ ብቻዬን የሆንኩኝ መስሎኝ ነበር። ግን ከአንድም ሁለት እናቶች እንደ እናቴ ሆነዉ አበባ ይዘዉ በምረቃዬ ተገኙ።

እነዚህ ሁለት እናቶች ዶሮ አርደዉ ቤታቸዉ ድግስ አዘጋጅተዉ ነበር። ሁለቱም ወደ ቤታቸዉ እንድመጣ ፈለጉ። ግራ ገባኝ። በኋላ አንዳቸዉ ጋር ምሳ ሰዓት ፤ ሌላኛዋ ጋር ደግሞ ሲመሽ ሂጄ ከጓደኞቼ ጋር የተዘጋጀልኝን ድግስ ተካፈልኩ።

አስመራን ሳስብ፣ የአስመራን ሕዝብ ሳስብ ትዬ ዘይዳና አደይ ጸሃይቱን አስባለሁ። እነዚህ እናቶች በስጋ እናቶቼ አይደሉም። እንደነርሱ ትግሬ አይደለሁም። እንደነርሱ የኤርትራ ተወላጅ አይደለሁም። ነገር ግን የእነዚህን እናቶች የዋህነት፣ ፍቅርና ያላቸዉን ፈሪሃ እግዚአብሄር አናያለን። የእነዚህ እናቶች ደጎችና ለዘር ቦታ የማይሰጡ መሆናቸዉን እናያለን። እነዚህ እናቶች ባይወልዱኝም እናቶቼ ናቸው ! እግዚአብሄር ባሉበት ቦታ ያክብራቸዉ።

የመጨረሻ አመት ተማሪ እያለን በአንድ ሃይ ስኩል፣ ለሶስት ወር ማስተማር ነበረብን። ባርካ ተብሎ በሚታወቅ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመደብኩኝ። የተመደብኩበት ክፍል አስተማሪ ክፍሉ በጣም ረባሽ ክፍል እንደሆነ አስጠነቀቀኝ። በጣም ፈራሁ። ነገር ግን ማስተማሩን ስጀምር የተካሁት አስተማሪ ከነገረኝ የተቃረነ ሁኔታ ነዉ ያየሁት። ተማሪዎቹ በጣም የሚያዳምጡ፣ በአክብርት ከታያዙ ብዙ ሊሰሩ የሚችሉ ሆነዉ ነበር ያገኘኋቸዉ። አስተማሪያቸዉም ብሆን ጓደኞቼም ሆነዉ ነበር የተለያየነዉ። ያኔ ከተማዋ ችግር ላይ ነበረች። እንደዚያም ሆኖ ግን ከፊታቸዉ፣ ከሁኔታቸዉ ያየሁት ፍቅርንና ደስታን ነበር።

አሰመራን ሳስበ፣ የአስመራን ሕዝብ ሳስብ ያኔ ወርቃማ ዩኒፎርም ለብሰዉ የማስተምራቸዉን ያዳምጡ የነበሩትን ፣ ሳስረዳቸዉ ፊቴን ያዩ የነበሩትን የባርካ ተማሪዎችን አስታወሳለሁ።

እርግጥ ነዉ ብዙ የሚያሳዝኑ ነገሮች በአስመራ አይቻለሁ። እርግጥ ነዉ ከተማዋ ያኔ መለስተኛ ጦር ግንባር ነበረች። እርግጥ ነዉ በየጊዜዉ ሳይታሰብ በሻቢያ የሚተኮስ መድፍ ባልተጠበቀ ቦታ ያርፍ ስለነበረ ብዙ ሰዎች አልቀዋል። እርግጥ ነዉ በደርግ ወታደሮች የተሰሩ ብዙ ግፎች ነበሩ።

ነገር ግን እንደዚያም ሆኖ ግን የሕዝቡ ፍቅር አሸንፎኝ ነዉ የጦር መሳሪያ በተሸከመ የጦር አይሮፕላን፣ መሳሪያ ላይ ተቀምጬ ከተማዋን የለቀኩት። አሁንም ለአስመራ ትልቅ ፍቅር አለኝ። አሁንም አሰመራን ከአዲስ አበባ ቀጥሎ እንደከተማዬ ነዉ የማያት። አሁንም ያንን ሕዝብ እንደ ሕዝቤ ነዉ የማየዉ። አሁንም ኤርትራዉያንን ከተቀረዉ ኢትዮጵያዊ እንደተለዩ ተደርጎ ሲታይ አያስደስተኝም።

በዚህ ምክንያት ነዉ የኤርትራን መገንጠል አጥብቄ የትቃወምኩት! አሁንም የምቃወመዉ። ለዚህ ነዉ ከመረብ ደቡብ ይኖሩ የነበሩ ወደ ኤርትራ ፣ ከመረብ ሰሜን ይኖሩ የነበሩ ደግሞ ከኤርትራ በግፍ እንዲባረሩ መደረጉ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነዉ የምለዉ። ለዚህ ነዉ የባድመ ጦርነት የወንድማማቾች የርስ በርስ ጦርነት እንጂ ከዉጭ ኃይላት ጋር የሚደረግ ጦርነት አይደለም የምለዉ።

በአዲስ አበባና በአስመራ ዲሞክራቲክ መንግስት ቢኖር፣ በፍቅር በዉይይት ለሁሉም በሚጠቀም መልኩ የኤርትራ ችግር ይፈታል የሚል ሙሉ እምነት አለኝ። ኤርትራም ከኢትዮጵያ ጋር ትዋሃዳለች። በሳባ ስቴዲየም ቺፖሊኒና ጊዮርጊስ ይጫወታሉ። በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሞሽን ፊት ለፊት ከአስመራ የመጡ እንደ ተስፋጋብር አይነት ብስኪሌተኞች የብስክሌት ጥበባቸዉን ያሳዩናል።

ስለዚህ ትኩረት በኤርትራዉያንና በተቀረነዉ መሃከል ያለዉን ያለፉት አሳሳኝ አስራ ሰባት አመታት የፈጠሯቸዉ ጠባሳዎች ላይ መሆን የለበትም።

ትኩረቱ ፣ በአዲስ አበባና በአስመራ ህዝብን የሚያከበሩ፣ ለሕግ የበላይነት የሚገዙ መንግስታት እንዲዘረጉ ማድረጉ ላይ መሆን አለበት። አቶ መለስ ዜናዊና ድርጅታቸዉ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳንና ቴዲ አፍሮን የመሳሰሉ የሕሊና እሥረኞችን በመፍታት፣ የሕዝብን ጥያቄ እንዲያከብሩ፣ አቶ ኢሳያይስ አፈወርቂ ደግሞ የቀድሞ የአስመራ ዩኒቨርሲት የተፈጥሮ ሳይንስ ዲን የነበሩት ዶር ክፍሉ ገብረ መስቀል፣ ፓስተር ሃይሌ ነእዝጊ፣ ፓስተር ተስፋጽዮን ሃጎስ የመሳሰሉ በእምነታቸዉ ምክንያት የታሰሩትን በመፍታት፣ ከግትርና ከእልህ ፖለቲካ ወጥተዉ ለሕዝብ ጥያቄ ቅድሚይ እንዲሰጡ ማድረጉ ላይ ትልቅ ግፊት መደረግ አለበት እላለሁኝ።

«ከአቶ ኢሳያስ ጋር መነጋገር ያስፈልጋል» የሚሉ ወገኖችንን አልቃወምም። ሻቢያም ሆነ ኢሕአዴግ አንድ ናቸዉ። ሁለቱም በእናት አገራችዉ ላይ ትልቅ ጥፋት እያደረጉ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ። (እነርሱ አይደለንም ሊሉ ይችላሉ።ነገር « ኢትዮጵያዊ መልኩን ነበር ጅንጉርጉርነቱን ይቀይራልን? » እንደተባለ ኢትዮጵያዊነት ፓስፖርት በመለወጥ ወይንም በመጣል የሚጠፋ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የዉስጥ የሆነ ማንም የፖለቲካ ስርዓት የማይለወጠዉ ማንነታችን ነዉ።)

«ኢሕአዴግን እናነጋገር» እንደምንለዉ ሁሉ ከሻቢያ ጋር መነጋገሩን እደግፋለሁኝ። በአንዳንድ ድህር ገጾች እንደምናነበዉ አሰመራ በሮ መሄድ ወንጀል አይደለም። ከኤርትራዉያን ጋር መወያየት የኢትዮጵያን አንድነት መጉዳት አይደለም። ከኤርትራ መሪዎች ጋር ዉይይት የሚያደርጉትን ከመቃወም ይልቅ፣ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ እንዲኖር እንታገላለን እስካሉ ድረስ፣ በኤርትራ ያለዉን አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ትልቅ ቦታ እንዲሰጡት ማሳሰቡ ይበጃል እንጂ።

ያ ካልሆነ ግን ኤርትራ ያሉ ወገኖቻችን በላያቸዉ የግፍ ቀንበር ተጭኖባቸዉ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ለተቀረዉ ኢትዮጵያዊ መፍትሄ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነዉ።

 1. ነጋድራስ-1
  | #1

  አቶ ግርማ!
  ለምን አስመራ አትገባም? ማምታታት አይሰለችህም? እባክህ ተወን!!!

 2. ሰሎሞን
  | #2

  ያለንበት 21 ክፍለዘመን ስለሆነ ሰፋ አድርገህ ብታስብ ይመረጣል መለስና ኢሳይስን ማወዳደር ትክክል አይደለም ሐቅ ሆሉግዚ ሐቅ ነው ስለዚህ የመለስን እንደ ቂጣ እያገለበጠ የሚያወራውን ሰምተህ አትታለል ስለዚህ ለወደፊት አስብ

 3. ሁሉ በእርሱ ሆነ
  | #3

  ይህ ወቅታዊ ትዝታ ነው መሪዎቻችን እንዶት እነደሚያዩት አላውቅም!

 4. God Bless Ethiopian
  | #4

  የሀን የሳፍከው ሰው <<< God belss you ኤኜም አሥመራ ነበርኩ
  ፊከር ነው የሚያሰፈለገን , ግን ብዙ ሰዎችሀ አሉ ሰላምን የማየፈልጉ
  የ ትኩኡር Nazi .
  እነ በቻ ልኑሩ የሚሉ , ለ ሰው ልጀ ሰላም ያማይሰቡ
  እንድዝሂ አይተ የ ትኩኡር Nazi እጊዛብሀር ይታርካችሀው
  በ ሰው አገር በ ሰደት የኖሩ , የ Ethiopia and Etria ሰላም የማይፈልጉ አሉ
  ይሀ ነው የ እጃ ችግር , ሰላም እና ፊከር ለ Ethiopia and Etria ሀዝብ ኣመን
  God belss Ethiopia and Etria

 5. God Bless Ethiopian
  | #5

  ግርማ ካሳ ትሩ አሰትሳሰብ ነው ያልሀ .. በዝሂ ከትለበት
  ለ ትኩኡር Nazi ትሩ ተመሀርት ይሆናል በይ አሰባልሁ
  ያንተ አስተያይት …..ግርማ ካሳ God Bless you
  በ ፓልቶክ ብሁ ሰዎችህ አሉ ሰራ የፈቱ
  ሙሉ ከን ብላ ብላ የሚሉ ለ Ethiopia and Etria ሀዝብ ሰላም እና ፊከር የማይፈልጉ
  ሰራ ፈቶች .. ለ እንሱ ተመሀርት የሆናለ በይ አሰባልሁ ያንተ አስተያይት

 6. Amazing Weight Loss Story
  | #6

  Thanks for writing, I very much liked reading your most recent post. I think you should post more often, you evidently have talent for blogging!

 7. ድሪባ
  | #7

  ወንድሜ ግርማ እኔም አሥመራ ውስጥ እንዳንተው ነበርኩ::ካንተ ትንሽ ቀደም ባሉ አመታት::የህዝቡ ደግነት የከተማዋ ዉበት አይረሳኝም:; ነገር ግን ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያዊያን የአሥመራን ህዝብ ደግነት አያውቁም::

 8. አሌክስ
  | #8

  የኤርትራን ሉአላዊነት ለመንጠቅ የሚደረግ ከንቱ ሙከራ!

 9. dima
  | #9

  I wonder what is going on these days among Eritreans.An articles that was not read on the internet for the last 18 years since the independent of Eritrea
  Ethiopia is diffrent country Eritrea is another country.
  What is needed now.
  Ethiopia need only Assab(sea Port)from Eritrea.And seen survived existed without sea port for that matter Eritrea fail to be a country contrary to Ethiopia.
  NOW If Eritreans need to be an Ethiopian or live together ,it is up to them drop Eritreawinet and aquire Ethiopiawinet by removing Isayas and unified Eritrea to Ethiopia.

  Oterwise you are telling Jokes bla bla while Sahbea is on the verge of collapse.do that first and the rest will as follows.
  It is something that cannot be happen just by the talk..

 10. ሰላማዊ
  | #10

  ጥሩ ትዝታ ኤርትራን ግን እርሳት ሰላምዋን አግኝታለች. ድል ለጀግናው መሪ
  ኢሳያስ ይሁን

 11. kazahabesha
  | #11

  በጣም ጥሩ አቀራረብ ነው ነገር ግን ኢሳያስን እና መልስን በአንድ አይን ማየትህ ስህተት ነው!!!!!!!! ዬሁለቱ ህዝብ ወንድምነት ለዘላለም ይኖራል ብየ አምናለሁ that doesn’t includ (………..)

 12. እውነቱ
  | #12

  ትዝታህ ባልክፋ ነገር ግን ያልገባህ ብዙ ነገር አለ ወይ ክሁአላህ ነገር አለ ለለላ አሰተያየት ጊዘ የለም;;;;;;;;

 13. ቢኒ
  | #13

  ዋንድማ ገርማ አሰታየተህ በታም አሪፈ ነው አንድ ሰው ለ2 ሀዝብ እናሰብ

 14. ቢኒ
  | #14

  ተከከል

 15. maru
  | #15

  ኣቶ ግርማ
  ምን ታለቃቅሳለህ.ሂድና አስመራ ተቀመጥ. ለአደይ ዛይድ እና ለአደይ ጸሃይቱ ደሞ ቡና ገዝተህ ላክላቸው. አሁን በኢሳያስ አገዛዝ ተቸግረዋል.
  What the fuck are you crying here. Go and live in Asmara if you like. Old bitch

 16. Anonymous
  | #16

  ሁሉንም ኢትዮኤርትራው እንዳንተ እንድናስብ አላህ ይርዳን!እዚህ ላይ ግን ሀይማኖት ያለንም እንሁን የሌለን ሰዎች ምድርዋን (Glob)ን የሚያስተዳድራት ባለቤት እንዳላት አንዘንጋ::ቁም ነገሩ ግን በሚፈጠሩት ክስተቶች ውስጥ የራስን ጥሩና በጎ ስራ ከራስ ለራስ ማበርከቱ ላይ ነው::….ይችን ምድር መቼ ውስጧ ገብተን እንደምንደበቅባት ማንም አናውቀውምና…………ዛሬ….ነገ…ወይስ ሀሙስ?….
  እንመልከት ተወዳጁን ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰን ….ለምን ? ኢትዮዽያ….ለፋሲካ…ለህክምና….ለመደበቅ…እኮ..ለምን?….መልሱን ለአንድየው ብቻ እና ብቻ እተወዋለሁኝ::
  ጥሩ ያሰማን..አሜን!

 17. John
  | #17

  I am Eritrean. I prety much like your article. You don’t support Eritrean independence, thats is ok, all i can say is , that is just your opinion. We don’t need ethiopians to believe in Eritrea’s independence anyway.

  The people of asmara did alot of good things to ethiopians. In 1991, Eritrea was liberated. EPLF captured hundereds of thousands of ethiopian soliders. The people of Eritrea fed their enemy! we send them all witout harm!!
  Pilot bezabh petros is good example.He was piolot for mengistu. EPLF shot his plane in 1980s, he was set free.He was set free, he saied”he is sorry to eritreans” He came to bomabard asmara in 1998 . i was in asmara at that time. I saw when his plane was hit by missile of patriot eritrean defence forces. I saw him his hand chained ,disgraced .
  It is time for ethiopians to recognise..enough is enough! Let it go for good.. We can co-exist as people in the horn of africa. We can live in peace and harmony.

 18. ወያኔም ይወድቃል የኢትዮጵያ ህዝብም አንድ ቀን አርነት ይወጣል
  | #18

  አቶ ግርማ ምንም በመልክ ባላውቅወት ባስመራ ትዝታወ እኔም ትዝታ አለይ
  የኤርትራ ህዝብ እና የኤትዮጵያ ህዝብ አንድ ሃይማኖት አንድ ባህል አንድ ህዝብ መሆኑን
  ማንም የሚያውቀው ነው በፋሽሽቶች ጠንቅ ለዚህ በቃን እንጂ
  ምን መሰለህ ከረን አንዲት አክስት አለችኝ እሷን ለመጠየቅ እኔም በ1990 ሚያዚያ 27 ቀን
  ወደሷ ጉዞየን አደረግሁ ስሄድ በኦምሃጀር ነበር የሄድኩት ተሰኔ ስገባ የህዝቡን ኑሮ ሳየው
  ኤርትራውያንን እና እትዮጵያውያንን መለየት በጣም አትችልም እኔም ሳየው በጣም ተደሰትኩ
  ወደ ከረን ስደርስ እንደ አደይ አበባ ነው የፈካሁት ምክንያቱም ካክስቴ ጋራ ስገናኝ የአካባቢዋ ጎረቤቶች አቀባበል ሲያርጉልይ ባዬሁት ትዝታየ ነው
  ነገር ግን እሾህን በሾህ እንደሚባለው ሆነ እና አቶ መለስ እና አቶ እሳያስ ህዝቡን በሰላም ቢያስተዳድሩት ከስልጣናቸው እንደማይቆዩ ሲገነዘቡት ህዝቡን በምን አጋጭተን ስልጥኣናችን
  እናቆየው በማለት አንዲቱን ጸጉር ከሁለት ሰነጠቋት እንጂ እውነት ከተባለ የባድሜ ድንበር
  ሁኖ ነው እውነት እግዚአብሀር ይፍረድ እንጅ
  እኔም ሚያዚያ ሃያ ሰባት እንደገባሁ ግንቦት አራት እና ስድስት ቀን ጀምሮ ያሁሉ ህዝብ ያሁሉ ወጣት ያለቀበት እና የተፈናቀለበት ዘመን ነበረች እኔም በጦርነቱ ምክንያት ወደ ሃገሬ ለመመለስ ጉዞየን ቀጠልኩ ልክ ተሰኔ ስደርስ ካውቶቢስ ስወርድ የኢሳያስ ደህንነት ነበር የተረከቡይ
  ከዚህ በኋላ ምኑን ላጫውታችሁ እንዳልሆነ አርገው ተውኝ እንጂ አንተ የወያኔሰላይ ነህ ተብየ የገባሁበት አንደር ግራውንድ እንኳንስ የሰው ልጅ ይቅር እና አውሬ በዝያ ውስጥ

 19. ወያኔም ይወድቃል የኢትዮጵያ ህዝብም አንድ ቀን አርነት ይወጣል
  | #19

  አይቀመጥም
  ከዚያ በኋላም እንደገና ወደሰሃል በርሃ ከሳዋ ሃያ አምስት ኪሎ ሜትር እርቀት ባለው በርሃ አውሻይት
  ከሚባል ቦታ3000 ሶስት ሺህ ንጹህ ወጣት ወስደው እንደፍየል ካሽዋ ላይ በግራር እሾህ አጎሩን ከዚያ በኋላ ያለውን ምኑን ልንገራችሁ አይነገር ይቅር 3000 ሶስት ሺህ ወጣት ገብቶ የወጣው 2000 ሁለት ሺህ ብቻ ነው እንደተኩላ ነጣቂ ሌሊት ነጥቀው በሉት 1000 አንድ ሺህ ወጣት አውሻይት ላይ ተበልቶ የቀረ ወገኔን እንዴት ልርሳው እንዴት ልተወው
  ደግሞም ወገን አለይ አገር አለይ ብዬ ከዚአ በርሃ ጠፍቸ 27 ሃያ ሰባት ቀን ትጉዠ ሁመራ ገባሁ ወያኔ
  ደግሞ አንተ የአርበኞች ሰላይ ተብዬ እንደገና ወልቃይት ቃፍታ ባዶ ሽድሽተ ከሚባል ጨለማ ገባሁ አንድ አመት ማንም ሳይጠይቀይ ቆየሁ እኔም ከመኖር መሞት ይበልጥኣል ብየ አምልጨ ውጣሁ ደስ ይበላችህ አሁን ያለሁ ሱዳን ነው አሁንም ቢሆን በመፈለግ ነው ያለሁ ባላወቅሁት ነገር ሻቢያ እና ወያኔእንደኳስ ተቀባበልይ

  እና ምን ልል እንደፈለግሁ የኤርትራ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ሱዳን ሃገር እንደማየው በመከራም ሆነ በደስታ አብረው ተድጋግፈው አንድ ቤት ተከራይተው እንደ ሚኖሩ ለመናገር ብየነው ሁለቱ የጭቃ ሾህ ተነቅለው ከወደቁ ዛሬም ነገም ሁለቱ አንድ እንደሚሆኑ በማህብራዊ ኑሮ አልጠራጠርም ሁለቱም አንድ ናቸው እና

 20. bekele
  | #20

  I wish all the best for ethiopia &eritrea as good neighbours.

 21. Tigist
  | #21

  I was so touched when I read Ato Girma Kassa’s Asmera recollecton. My dad used to work in many parts of Eritrea, as well, back in the day. He used to tell us a lot of things about Asmera, Keren, Nakfa, Akurdete and other parts of Eritrea. I have never been there, but growing up hearing what my dad used to tell me and the whole understanding of the fact that Eritrea is a part to Ethiopia is still in me. I agree with the idea that the people to people communication needs to be widening among Ethiopians and Eritrean and let the natural course takes its place. Especially, for those Ethiopians and Eritrean that are living in US and Europe, should not be difficult to see how diverse the westerns are and still mange to live together. Take a look the diversity of the US population as example and the success that they achieve. Take a look the worst of ethnicity in Somalia and choose your pick. Which one is better and practical?

 22. Yekajemawue Giorgies
  | #22

  You the people of Abyssinia!!!

  WE are the people. Back in the 80s, I was an air borne (Berari Neber)major assigned in Eritrea to kill the innocent people.I REFUSED THE MISSION AND DEFECTED WITH 20 SOLDIRES. WE WENT TO SUDAN AND NOW LIVE IN EUROPE. i AM MARRIED WITH A BEAUTIFUL ERITREAN LADY ENJOY A GOOD LIFE BEING A FATHER OF 6 CHILDREN.MY HOME TOWN IS DEBRE ZEIT AND AM A TYPICAL AMARA. I AM NOT A DIE-HARD AMARA.I LOVE ERITREANS AS MY BROTHERS AND SISTERS. THEY ARE KIND PEOPLE.

 23. ይህን በለው
  | #23

  ነጋድራስ-1 :
  አቶ ግርማ!
  ለምን አስመራ አትገባም? ማምታታት አይሰለችህም? እባክህ ተወን!!!

  ሰሎሞን :
  ያለንበት 21 ክፍለዘመን ስለሆነ ሰፋ አድርገህ ብታስብ ይመረጣል መለስና ኢሳይስን ማወዳደር ትክክል አይደለም ሐቅ ሆሉግዚ ሐቅ ነው ስለዚህ የመለስን እንደ ቂጣ እያገለበጠ የሚያወራውን ሰምተህ አትታለል ስለዚህ ለወደፊት አስብ

  maru :
  ኣቶ ግርማ
  ምን ታለቃቅሳለህ.ሂድና አስመራ ተቀመጥ. ለአደይ ዛይድ እና ለአደይ ጸሃይቱ ደሞ ቡና ገዝተህ ላክላቸው. አሁን በኢሳያስ አገዛዝ ተቸግረዋል.
  What the fuck are you crying here. Go and live in Asmara if you like. Old bitch

  bekele :
  I wish all the best for ethiopia &eritrea as good neighbours.

  “ምነው እስከዛሬ ዝም ማለታችሁ
  በመወለጃው ቀን ገና ማርገዛችሁ
  ንፋሱ ሲነሳ እሳት መጫራችሁ
  እናንተ ስትጽፉ እኛም ታዘብናችሁ
  ጥሩ ተመልካቾች ይሄውላችሁ”
  ህዝቦች በተጻፈው ሳይሆን በታሪካቸው
  እና እንደአስፈላጊነቱ በመከባበር በጎረቤትነት እንዲኖሩ እንመኛለን
  ምርጫቸውን ካገኙ ሕልውናችንንና ከብራችንን በወደብ አንሸጥም ::

 24. ደምበጫ
  | #24

  ግርማ
  ከጽሁፍህ ውስጥ ያነሳኽው ሚካኤል ሌላ ነገር አጭሮ ምፅዋ እዳጋ ወደ ባህር ኃይል ከሚወስደው መንገድ (ሳሊና አጠገብ) ያለው ትዝ አለኝ:: እንደፈረንጆቹ 1978 ምፅዋን ለመያዝ ሻቢያ ሲራወጥ አስተኳሽና ከባድ መሳሪያ የት ነበር የመስለህ ሚካኤል ቤተክሪስቲያን ታዲያ የባህር ኃይል ባልደረቦች እንዴት ቤተክርስቲያን እንመታለን ብለው ምን ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚያውቁ ያውቁታል አጭር መልስ ዝርዝር ከፍለግህ እራስህ አግኘው:: ሁለተኛው ደግሞ ንግደት ነው ያልከው በጣም ጥሩ ስም ነው ይገርማል ሳይታወቅ የልቦና ሲነገር ስለዚህ በኋላ እመልሳለሁ ስለሰው እውነተኛ ቸርነት ላጫውትህ ቦታው አንጎለላ ይባላል በየአመቱ የጥር እግዚሃራብ እለት መንገዱ ህላ ድግስ ነው ታቦት ከሚወጣበት ስፍራ:: ከዚያ ታቦት ሲገባ በየቤቱ ተደግሶ ቁጥሩን መናገር የሚያዳግተኝ ህዝብ በግድ እየተለመነ ነው በጥቂት ገበሬዎች የሚጋበዘው አሁንም ኣጭር መልስ:: እንደዚሁ ጋሾጥ እግዚሃራብ ይደረጋል ሌላም ልበልህ ደብረብርሃን የታሕሳስ ሥላሴ የሐምሌ ስላሴ እንደዚሁ:: እመለስበታለሁ ስላልኩት አጭር ልበልህ ለመሆኑ ስንት ለሃገራቸው የተስለፋ ጀግኖችን በተለይ ሴቶች ሽኳረይ እያሉ እንዴት እንዳስገደሉ አታውቅም እንደሚገባኝ አንተን የተውህ በምን እንደሆን መርምረው:: ቀና ለሚያስብ አንዳንዱ አባባልህ ልክ ነው: ግን ስታዝንለት ራስህ ላይ ሊጨፍር ለሚሞክር አይሰራም (ተግባባን)

  ሞት ለገንጣዮችና ለተባባሪዎቻቸው::

 25. ወርቁ ከቬጋስ
  | #25

  ወንድም ግርማ ስለ ህዝቡ ጥሩ ተናግረሃል ፖለቲክኞችን ግን እንዲት እረሳህ? ስለደርግ ግፍ ካየህ ህዝባዊ ብሎ ራሱን ከሚጠራ ቡድን የሰውን ልጅ እንደ እንሰሳ ሲያርዱ ዐይንህን ምን ሽፈነው .

 26. ኤርትራዊ
  | #26

  “ኤርትራ…ን ኤርትራውያን,,,ብ ኤርትራውያን”

 27. Anonymous
  | #27

  አየ ገርማ አንተን የምናወክ እናውካለን ዛረም አታርፈም ያለፈወን ተፋተሀን መለሰህ አስታወስ ዛረም ህዘቡንዋ አከበር እባከህ እርፈ የበካህ ገርማ your frend from germen

 28. ስላም ለሁሉም
  | #28

  ኣቶ ግርማ ጽሁፍህ በጣም ጥሩ ነው እናመ የበዙ ሰላም ፈላጊ ሀዝቦህችን ድጋፈ እና ፍላጎት የመስላል
  እና እዝሂ ላይ ሃሳቦችህ ሁሉ በፍላጎት ብቻ አይሳኩም ማለት ሃሳብብ መጀመርያ ቢሆነም ሃሳብ በቻወን
  ሃሳብ ሆኖ እንዳይከር ከልብ የሆነ ይከርታ እናም ያለፈ ነገር ኢያነሱ ለመጭው ተውለድ በከለን ማኮየት መብካት አለበት ይሀነን አስተያየት እንድሰጥ ያነሳሳጝ ምክንያት ኢትዮጵያ የለች የዎንደማችን ሚስት እና ከሁለቱ የሚወለዱ ሁለት መንታ ልጆችን ሳሰብ እሱ ኢትዮጵያዊ እርስዋ ገን ቢተሰቦችህዋ ኤርትራውያን በምሆናችው በግምት ከሰላሳ አመት በላይ የኖሩበተን ሃገር ጥሎ መሰደድ ምን ያሀል እንደሚሰማ እናም ኢትዮጵያ ለከረችው የዎንደማችን ሚሰት ከዛ አልፎ ልጆቻችው አደገው ነገሮችን መረዳት ሲጀመሩ ያ ያይውርሰ ጥላቻ እንዳየደገም እግዝያብሀር የርዳን

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።