ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል በአንድነት ጽ/ቤት፣ በቃሌ ምሽት ላይ ንግግር አደረጉ !

May 29th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ልዩ ዘገባ – አወደ ኢትዮጵያ
ግንቦት 21 ቀን 2001 ዓ.ም

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ፣ የፓርቲው ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በግፍ ለአምስት ወራት ለእስር የተዳረጉበትን ዕለት በማስመልከት የሚያዘጋጀው «ቃሌ የሻማ ምሽት» በትላንትናዉ ዕለት ሐሙስ ግንቦት 20 ቀን 2001 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ግቢ ውስጥ አካሂዷል። ጽ/ቤቱ በታዳሚዎች እጭቅ ከማለቱ የተነሳ ቦታ በጣም ጠብቦ እንደነበረ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

ይህ «ቃሌ የሻማ ምሽት» በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያሉትን ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እያሰባሰበ ያለ የሰላማዊ ፖለቲካ እንቅስቃሴና በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍ በስፋት ከሚያጋልጡ ዝግጅቶች አንዱ ነዉ። በየወሩ አዳዲስ ክስተቶችን ይዞ የሚመጣው ይህ የ«ቃሌ ምሽት» በግንቦት ሃያ ቀን አንድ አዲስ ተሳታፊ ይዞ ነው የመጣው።

እንደተለመደው ፕሮግራሙ ከቀትር በኋላ በ11.00 ሰዓት እንደሚደረግ ነበር ጥሪ የደረሰዉ። ጥሪውም በስልክና በቃል ከመተላለፉም ባሻገር በሚወጣ ዕለታዊ የግል ጋዜጣም እንደዜና ተዘግቦ ተላለፈ። የዚህ የምሽት ጥሪ አንዱ ተባባሪ የቴሌኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ነበር። የኢሕአዴግን የግንቦት ሰባት በዓልን ለማድመቅ ሳያዉቅ የፈቀደው የ24 ሰዓት የነጻ የሞባይል የመጻጻፍ መልዕክት የቃሌ ምሽትን ጥሪ ለማሰራጨት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጎ ነበር።

ተሳታፊው ለፕሮግራሙና ፕሮግራሙ ለቆመለት አገራዊና ሕዝባዊ ጉዳይ ካለው አክብሮትና ወገናዊነት የተነሳ ወደ ግቢው የገባው አስቀድሞ ነበር። በዚህ ምሽት ፕሮግራም ላይ ጨርሶ ለመተያየት እንኳ የማይታሰቡት የሁለት ፓርቲ ቤተሰቦች በአንድ መድረክ ላይ ተሰለፉ።

የመኢአድ ፕሬዜዳንት ኢንጅነር ኃይሉ ሻውልና የመኢአድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሻለቃ ጌታቸው መንግሥቴ፣ ዶክተር በዛብህ ደምሴ፣ አቶ ገብረጻድቅ፣ ዶ/ር ታዴዎስና ሌሎችም የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት በፕሮግራሙ ላይ ለመገኘት ወደ ግቢዉ ሲመጡ በዚያ የነበረዉ ሕዝብ እልልታዉና ጭብጨባዉን አቀለጠዉ። ብዙዎች እጆቻቸዉን ወደ ሰማይ ሲዘረጉ ይታዩ ነበር። (ፈጣሪን ለማመስገን)

ይህ በቃሌ ሻማ ማብራት ዝግጅት የታየዉ ክስተት በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰር ሳቢያ፣ ለመፈታቷ፣ አብረው ለመቆምና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሕብረት ሊፈጥሩበት የቻሉት አንድ ሃይል እንደሆነ ያሳየ ዝግጀት ነበር፡፡

የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው በቅድሚያ እንግዶቹን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ነበር ፕሮግራሙን የከፈቱት። በመክፈቻ ንግግራቸዉ «አንድ አላማ ይዘን አብረን ስንጓዝ የነበርና በተለያዩ ምክንያቶች የተለያየን ፣ ኢሕአዴግ ነጻ አወጣኋቹህ በሚልበት በአሥራ ስምንተኛ አመቱ፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በግፍ በታሰረች በአምስት ወሩ፣ ዛሬ ግንቦት 20 ቀን በአንድ ላይ መገናኘታችን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ለፍቅር፣ ለሰላም፣ ለአንድነት ያሳየችዉ ቁርጠኝነት ኢትዮጵያውያንን አንድ የሚያደርግ ትልቅ ኃይል ነዉ» ሲሉ ኢንጂነር ኃይሉ ሻወልንና አብረዋቸው ያሉትን በማያታቸው ደስታቸዉን የገለጹት።

የእለቱ የክበር ተናጋሪ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ነበሩ። ፕሮፈእሰር መስፍን «ሠላማዊ ትግል በኢትዮጵያ» በሚል ርዕስ ያቀረቡት ንግግር፣ በጣም ጥልቀት ባለው መንገድ በሃገራችን ያለውን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ንግግር ነበር። ፕሮፈሰሩ ሰላማዊ ትግል የሚፈራዉ የአቶ መለስ አገዛዝ በሰራዊቱና በጡንጫዉ ተማምኖ መንገዶችን ለመዝጋት ቢሞክርም ፣ ሕዝቡ እየመጣበት ያለዉን ሁሉ በመመከት ላይ እንደሚገኝና ተስፋ እንዳልቆረጠ ገልጸዋል።

ርእዮት ዓለሙ የሚባል ወጣት «ልክ ነዎት አባቴ» እንዲሁም «የብርቱካን ፊሬ» የሚሉ ሁለት ወቅታዊ ግጥሞችን አቅርቧል። በተለይ ‹‹ልክ ነዎት አባቴ›› የሚለዉ ግጥም ለፕሬዜዳንት ግርማ የተገጠመ፣ «ብርቱካን ትፈታ» በሚል አዲስ አበባ በተደረገዉ የሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የተጻፈላቸውን ደብዳቤ አልቀበልም ያሉበትን ሁኔታ ያገናዘበ ግጥም ነበር።

ሌላዉ ወጣት ገጣሚ ስለሺ ሃጎስም ‹‹መታሰር ምንድን ነው›› የሚል ግጥም ከማቅረቡም ባሻገር የእለቱ ፕሮግራም መሪ አቶ ደበበ እሸቱም ሁለት መናብቦችን አቅርቧል። የመጀመሪዉ ንባብ «አድባርና ብርቱ» የሚለው ሲሆን ሌላው ደግሞ «ጥቂት ሰአታት በቃሊቲ ከብርቱ ጋር» የሚለው ነበር።

በፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ በአክብሮት የተጠየቁት የመኢአድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል አጭር ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸው ላይ «ወሬውንና አሉባልታውን ወዲያ ጥለን አረሞችን በመንቀል አብሮ ከመሥራት ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም» በማለት የ«አብረን እንስራ» መልእክት አስተላልፈዋል። በግቢው የነበረው ታዳሚም ይህን መልእክት ሲሰማ ከፍተኛ አድናቆቱን በጋለ ጭብጨባ ገልጾላቸዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የተካተተው ዝግጅት በቅደም ተከተል እየቀረበ ሳይጠገብ ያለቀ ፕሮግራም ከመሆኑም ባሻገር በዚያ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላትን የመኢአድ አመራር አባላት ከፊታቸዉ የደስታ ጮራ እየፈነጠቀ በመተቃቀፍ ሰላምታ ተሰጣተዋል።

 1. አንድንት
  | #1

  አሜን አሜን አሜን ብለናል

  ይዘገያል እንጂ በአንድ ላይ በርትቶ መቆም የማይቀር እውነት ነው በርቱልን

  አቡጊዳዎች ይህን ታላቅ ዜና ስላበሰራችሁን እግዜር ይስጥልን

  አሜን አሜን አሜን

 2. እንግዳ
  | #2

  ይሄ በጣም የሚያስደስት ነገር ነው:: ተቃዋሚዎች በህብረት ቆመው ቁርጠኝነታቸውን ለህዝብ ማሳየት አለባቸው:: አርቆ ማሰብ በጣም አስፈላጊ ነው::

 3. ድንቅ
  | #3

  መሰረታዊ ጥያቄዎች ሳይመለሱ የነሱ ባንድ ጣራ ስር መሰብሰብ ጥቅሙ ምንድን ነው? ከዚህ በፊት ባንድ ጣራ ስር አልነበሩ እንዴ? ጣራውን በጣጥሰውት; እግረ መንገዳቸውንም የኛን ተስፋ በረቃቅሰውት ወጡ እንጂ::

  እኔ መሰረታዊ ጉዳይ የምለው እነሱን ያጣላቸው ጉዳይ ተቀርፏል ወይ ለማለት አይደለም; ባይገርማችሁ! ከዛም የባሰ ጠለቅ ያለ ችግር አለ:: ይህም – የወያኔን እየበረታ የመጣ አፈና ለመጋፈጥ አዳዲስ ሃሳቦች አሏቸው ወይ? ወኔውንስ አላቸው ወይ?

  ከዚህ በተጨማሪም; ኢንጅነሩን ከዚህ በኋላ ማመን ቂልነት ነው::

 4. ሎሎ
  | #4

  ያሳዝናል በጣም ገና ብዙ ይቀረናል::ኢንጅነር ሃይሉ እና ፓርቲያቸው ይህን ለማድረግ ብዙ ጊዜ ወሰደባቸው:: ደጋፊዎች በነገር
  ከመቛሰላቸውና በጠላትነት ክመተያየታቸው በፊት ይህ እርምጃ ቢወሰድ ከስንት ውድቀት በተረፍን ነበር::ነገር ግን ይህም ቢሆን መጥፎ እርምጃ አይደለምና የተፈጠረውን ገደል ለማጥበብ ባንድነት ለመሰራት መሞከር ነው::

 5. belew
  | #5

  i dont trust hailu shawel anymore, he had killed the biggest struggle in a favor of weyane and eprp homeless gangesters that histroy wont forget it.

  anyway, if hailu would like to work under the adminstration of udj, that would be good otherwise if he still want to gain his dream power interest, he better remain with his destructive groups.

 6. ሰላማለው
  | #6

  በአጠቃላይ ሲታይ ትግሉ እንዳሁኑ መስመር የያዘበት ፖለቲከኞቻችን ብልጠት ያለበት የሸናፊነት ብለሀት እየገባቸው ያለብት ጊዜ የለም:: ድል እየቀረበ ነው:: ተመስገን

 7. Ethiopia first
  | #7

  to defeat weyane we have to stand together.but i don’t trust Eng. Hailu , because it is fail.maybe they lost poplarity that is why they came in UDGP meeting.UDGp have to work carfully with those guys we don’t give the 2nd chance to kill Ethiopian struggle.

 8. ወሎ ሰፈር
  | #8

  በጣም ድንቅ ነው በርቱ ተበራቱ ኢንጂነሩ እንዳሉት በመሃል ገብቶ የነገር ድርቆሽ የሚያሰጡ ሰዎች ቆም ብለው እንዲያስቡ መልእክት የሰጣል የኢንጅነሩ አባባል ;; የመሂህድ ደጋፊ እየመሰሉ ልዩነት እያራገቡ ድብቅ የወያኔ አጀንዳ ለማራመድ የሚዳክሩ ብዙ ናቸው ።በተረፈ ከሰሃን አጠባ መልስ ፓል ቶክ ላይ እየተጣዱ የታገሉ የሚመስላቸው ደነዞች ደሞ በዘፈናቸው ይቀጥሉ ይሄን የፓል ቶክ ማይክ እንደ ጀላቲ እየላሱ
  ድርጅቶች ተቀራርበው እንዳይሰሩ ድቤ ሚመቱ በእየ ሩሙ ብዙ ናቸው ፡፡ ደግነቱ እውርተው ሲደክማቸው ይተኛሉ ለተግባር አልተፈጠሩም ፡፡ ደሞ ሚገርመው አንድ አይነት ፓርቲ እየደገፉ እርስ በእርስ የሚባሉ ውሾች ናቸው ፡፡

 9. ሙስ
  | #9

  i just want to say something um happy that the division happened in the past….most of u may not like my idea but just take a time and think abt it…. ስለ እውነት ያተረፍነውን ያህል አልተጎዳንም…. ተጠናከርን እንጂ አልተልፈሰፈስንም…መማር ከቻልን ያ ለኛ ትልቅ ትምህርት ነው !!!isn’t it ?????

 10. ትንገርቱ
  | #10

  ታላከ ሰራኢንጅነር ሃይሉየተፈጠረውን ገደል ለማጥበብ ባንድነት ለመሰራት መሞከር ነው::

 11. ትንገርቱ
  | #11

  ታላከ ሰራኢንጅነር ሃይሉየተፈጠረውን ገደል ለማጥበብ ባንድነት ለመሰራት መሞከር ነው

 12. koster
  | #12

  Both G7 and Andinet are meant to weaken the nationalist group led by engineer Hailu Shawel. Unity is for sure strength and if we are really interested to build an Ethiopia free from tyrany and poverty, the right path is a united struggle of like-minded, well-devoted Ethiopians than will shorten the tyrany of Meles/Woyane

 13. ደበደ
  | #13

  በርእግት ኢንጅነርኅይሉ ከልባችው ከሆነ በጣም ደስ ይላል ግን ግለሰቡ ካላቸው ጸባይ አንጽኣር አስተማማኝ ናችው ብየ ለማመን ቤያሰችግርም ፈታሪ ለእትዮፐያ ይረዳት

 14. አቢይ፡ኢትዮጵያዊ
  | #14

  )))))))))))))ደስፈቅ የሚያደርግ ሀሳብ ነው።((((((
  ዕውነት ነው፤በተፈጥሮ ሆኖ “አጠገቡ ሲታረድ የሚያመነዥግና ተራውን የሚጠብቅ በግ ብቻ ነው።”ብለው ያስገነዘቡን ሎሬት ፀጋዬ ትዝ አሉኝ፤ነብሳቸውን ይማረውና።በሬእንዃ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል በደም ትግሉ።እናም አጠገባችን ስንቱ በሕቡዕ ታረደና ስንቱስ ባደባባይ ተቆላ??ይህንን እያወቅን አገራችንን ለማዳን ካልተዘጋጀን፣ከሕሊናችን በስተቀረ ማንም መጀመሪያ አይወቅሰንም።
  ፅሁፉ የተግባር መነሻ ነውና፣ደስፈቅ አድርጎኛል እንጠብቃለን።

  የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቃታል።

 15. ዓቢይ
  | #15

  እንጅኔር ህይሉ “አሉባልታውን ትተን አረሙን እንንቀል” ብለዋል. በዚያላይ እናተኩር. ውይይቱን ይግፉበት. ከዚያ ውጭ ወዳጅንም ጠላትንም በጀምላ “የማርያም ጠላት” ማለቱ ይብቃ. በሀገር ያሉት ሲቀናጁ ነው ውጤት ይየታየው. አህንም ይቻላል, ይቻላል, ይቻላል እንበል.

 16. Be Ewunetu
  | #16

  አንድነት ማለት በቅድሚያ ጥፋተኛው ተለይቶ ጥፋቱን አውቆ በይፋ ይቅርታን ሲጠይቅና ለወደፊቱም ለሕግ የበላይነት፣ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እኩልነትና ነፃነት መቆምን የሚያሳይ ግልጽና ተግባራዊ አቋም ሲኖር ብቻ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ ግን ለእይታና ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ መገኘት ብቻውን አንድ የመሆን ዋስትና አይሰጥም። የመኢአድ መሪዎች በቅድሚያ ከቅንጅት መርህ ውጭ የወሰዱትን ህገ ወጥ እርምጃ አምነውበት ይቅርታ ሲጠይቁና በህግ እንመራለን የሚል ዳግማዊ ቃል ኪዳን በይፋ ሲገቡ ብቻ ነው አንድ እንሁን የሚለውን ጥሪአቸውን የምንቀበለው።
  በአመራር አካላቱ ብቻ ሳይሆን በደጋፊዎቻቸውም ያለው ልዩነት ቀላል እንዳልሆነ ማወቅና የተለያየውን የቅንጅት ቤተሰብ አንድ ለማድረግ አርያነታቸውን በተግባር በግልጽ ያሳዩን።ከዚህ ውጭ ግን አንድ እንነሁን የሚለው የሽንገላ ጥሪ ዛሬ በበርቱካን መታሰር ወቅት ሳይሆን ሁሉም አመራር አካላት በ እስር ቤት ከነበሩበት ወቅት ጀምሮ የሚዘመርና የሚሰተጋባ የገደል ማሚቶ ስለሆነ እንደ አዲስ አናየውምና „ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት…“ እንዳይሆን ጠንቀቅ እንበል ለማለት ነው።

  እውነተኛው የኢትዮጵያ አምላክ እውነተኛውን አንድነት ያምጣልን!!! ብርቱዬንም ያስፈታልን!!!

 17. በለው
  | #17

  አሁንስ ከቀድሞው ትንሽ ተስፋ ታየ
  ወሬኛና አስመሳይ በተግባር ተለየ
  መልካሙ መሀንዲስ ቀየሰው ቀናውን
  አሁን ልናየው ነው ሰጪ ተወባዪን
  እስቲ አትጥለፍለፉ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ
  የግራና ቀኙ እንዲለካ አቅሙ
  የምላስ እርዝመት ከተት አድርጋችሁ
  ተቆልቶም ተንጣጥቶ የት አደረሳችሁ ?
  አቃቂርና አሽሙር የትም ላይወስዳችሁ
  እስቲ አትቻኮሉም ምጥም አይያዛችሁ
  ኳሷ ተቀምጣለች ከመሀል ለሁሉ
  አመታትን አጥኑ አትንከባለሉ
  ሁሉ አዋቂ ሆኖ ቤታችን እንዳይፈርስ
  ጥሩ ረዳት አምጡ ካላችሁ መሐንዲስ
  ከቶ የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል
  በዚያች ድሀ ሀገር ፍቅር ይወለዳል
  ያጠፋው ተምሮ ሕልም እውን ሆና
  አዲስ ዕቅድ ስፍኖ ተከብሮ ሕልውና
  ሕዝባችን ይድረሰው ሰላምና ጤና ::(ሞ.ካናዳ)

 18. al
  | #18

  ‘Mesenbet deg naw’ i don’t ve sny trust in Ato Hailu. Its not only about trust, he is incapable of providing balanced judgement with regard to complicated political issues. Sorry, thats what I learnt from the past. Humans do learn and change, but changes need to be evaluated according to merit and past results. Hailu has been destructive through all his political carier… All Amhara and now AEUP, no credibility

 19. አካሉ
  | #19

  Engineer Hailu is doing his best and taking a leadrship move and obligation for sake of the Ethiopian people peaceful struggle. What is needed now is to live aside our diffrences and unite as one and be ready to win the the coming election. Please! we have to stop finger pointig to each other and becoming obstacles. Leave politics for the professional policticians,lwayers, historins, and the likes. (Sew ketesmara endeye muayaw) is a good poem to listen and to comprhend. Guys! Ethiopia’s problem is so complex.

 20. ግሩም ተሾመ
  | #20

  ምን ይባላል ሁሉም እስተያየቶች ላይ እኔም አለሁበት የአንባቢ አስተያየቶቹ ሁሉ ጥሩ ናቸውና
  ሁሉንም ለአገራቸው የቆሙ ያልታደሉ ምሁሮቻችን አባቶቻችን ውንድሞቻችን እባካችሁን ተስፋ መቁረጥን ከውስጣችሁ አውጡ ጥሩው ጊዜ ይመጣልና::ነብዩ መሀመድ(ሰ.ዓ.ወ)ትውልድ ቦታቸውን (መካን)ለቀው ተሰደዋል ተባረዋል እኮ…..ያውም በገዛ ጎሳቸው ቤጎቶቻቸው ጉዋደኞች….
  ጥንካሬውን አላህ ይስጣችሁ!

 21. ከካምፖ
  | #21

  አንጅኔር ሀይሉ ህበብ የገደሉበትን ብትር ለመርዙ ስሉ አብረው ክሬሳው ጋር ይጥሉታል ይባለል

 22. ከካምፖ
  | #22

  ከካምፖ[ብቸና] ወያኔ ማለት በህጅ የተከሉት ድንች መዳዳቅያ ይሰብር

 23. ከካምፖ
  | #23

  ከካምፖ[ብቸና] ለሆድ አደር ሆዳ ዘመዳም ዘመድ ዬለውም ይባላል

 24. Andenet
  | #24

  I am surprised by some of the comments on this article. Why dont you like the move of Eng. Hailu? He could be one of the reasons for the down fall of CUD, but is he the only person out there? I dont think so! All of them share the blame. So why dont Andinet work with Eng. Hailu having the same national agenda than Beyen Petrose, or Gebru Asrat? I belive AEUP is more organized and headache for Woyane than the so called people who gathered in Medrk, who are not challenging woyane at this time.
  God Bless Ethiopia

 25. ሃኢለ
  | #25

  ዲንኪነው ዲንኪነው ያስገሪማል .ሌትሂኦፒአ የሚበጃት .አንዲነት ቢችሃ ነው .አቢሮ መታገል ናው.

 26. ሃኢለ
  | #26

  fourty and more ethiopian airlines top executives were summarily dismiseed for only opposing the government not to reorganize the airline for safety ,efficiency ,profitability and competitive nesss reason .thse officials were denied of their pension and ticket priviledgeges after serving their airlines during rain and sunshine for the last 40 years .the government has later on acknowleged that the opinion of the dismissed is valid and had to reorganize it back to where it was before .unfortunately the ticket priveledges is still denied considered as a priviledge and not a right of the employee .most of these employees awaiting that the government will reinstate thie hardly earned right to a free ticket have passed away and what a great agony for the families of the deceased and the good moral of all ethiopians.the chairman of the board will be the only authority to make a difference and lift the embargo on the living to get their tickets to visit their children whereever they may be .ethiopian airlines is what it is to day by the dedication,forward looking and managemnet skill of its employees and management staff .

 27. Anonymous
  | #27

  እህ በታም ትሩ ነው ሁላችህን እንበርታ

 28. Anonymous
  | #28

  when people work togther, there is collective power that always take to a victory to the people or a contry. this is what we see now and we the people of that country need to support it and encourage it, not talk about negative connitation about it.
  thank you

 29. ድሪባ
  | #29

  እባካችሁን ድረገጹ የጸረ አንድነት የወያኔና የአፍራሾች መትፊያ አታድርጉት::

 30. ስመኘው
  | #30

  ብርቱካን በታስረቸብት ወቅት ለሎች የፓርቲ መሪዎች መግልጫ ሲያውጡ መግልጫ ያላወጡት የመኢአዱ ኢንጅነር ሃይሉና የኢድፓው ልደቱ ነበሩ:: ይህ ደግሞ ኣቶ ሃይሉን ፖለቲካሊ ምን ያሀል እንደጎዳቸው ያደባባይ ሚስጥር ንው:: አሁን ሳይታስብ ብቅ ያሉትና ነገ በተግባር የማያውሉትን ቀባጥረው የኽዱት የራሳቸውን ፖለቲካል ኢሚጅ ለማስትካከል እንጅ ለዘላቂው ትግልና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታስቦ አይደልም; ይህማ ቢሆን ኖሮ ትናንት በየቦታወ እያለቅስን ስንለመናቸው ጀሮ ሰጥተው ባዳመጡን ነበር:: ካንባ ገነኑና ከግትሩ ኢንጅነረ ሃይሉ ጋር (ያውም አሁን በአጥፊው ኢሕኣፓ እየተጋልበ) የሚደረግ ስምምነት የለም::

 31. ፓስው
  | #31

  @ድሪባ
  በጣም ደሰ ይላል ቀጥሉበት::

 32. ምግባር
  | #32

  አዪ የኛ ነገር …..ሳይከካ ተቦካ? አሁን ምን አየን ብለን ነው ይህ ሁሉ ትንተና? ማን ነው አረሙ ማንስ አረም ነቃይ? አረ ፖለቲከኞችን አናባልጋቸው እንደተመቻቸውም አይጋልቡን:: ለቅሶ የደረሰ ሁሉ እኮ ሀዘንተኛ አይደለም::

 33. Yikerbelen
  | #33

  Unity with out responsibility and accountability is the same as a sandish house. who is responsible for the destruction of ethiopia’s people struggle? what is our garuantee in the future ? is eng hailu’s brain from feudalist’s outlook? has he issolated him self from shaleqa admasse and other weyane’s agents?

 34. ተፈሪ
  | #34

  እንግዲህ ወያኒ ብርክ ይይዘዋል

 35. ኢተዮፒያ
  | #35

  መሞከሩ መልካም ነው ደግሞም ሰው ባንሳደብ መልካም ነው ይህ የኢትዮፒያዊ ስንምግባር አይደለምና
  አግዚአብሂር ኢትዮፒያን ያስባት

 36. ነጋድራስ-1
  | #36

  ኢን. ሃይሉ በወያኔ ለታሰረ መቆማቸው ህብረት ፈጠሩ ማለት አይደለም!! መኢአድ እንደገና አይጋለብም
  የመድረክ መንገድ እንደማያዋጣ በግልጥ አማርኛ ትናግሮአል::UDG ደግሞ የመድረክ አባል ነው!!!

 37. ይነጋል
  | #37

  ማን ኢንጂነሩንና ፕሮፈሰሩን ያምናል; ሁለት በእድሜ የከበዱ ግን ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ የማይታወቁ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሰንካር የሆኑ ግለሰቦች; የፖለቲካችንን አቅጣጫ እየተከተሉ የሕዝብን እርምጃ አደናቃፊዎች;; እባካችሁ በቅርብ የምታውቋቸው እንዳላችሁ ምን እያሰባችሁ ነው ብላችሁ ጠይቁልኝ:: የኢትዮጰያ ሕዝብ አላምን ብሏል እናንተን በሉልኝ;; ገዳም ግቡና ፀልዩ በሉልኝ
  ሁለት በማይታወቅ ድርጅት ፔይ-ሮል ላይ ያሉን ግለሰቦች መሃከላችን አስቀምጠን እየቀለድንም እየተቀለደብንም ነው
  Ethiopians, we can’t aford to have another disintigration some-where on the way. We have to open our eyes and watch the Engineer (Hailu) and the Progfessor (Mesfin). Look their biography. Learn from what they did in the past in Ethiopian Poletics.

 38. ይህን በለው
  | #38

  ይነጋል :
  ማን ኢንጂነሩንና ፕሮፈሰሩን ያምናል; ሁለት በእድሜ የከበዱ ግን ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ የማይታወቁ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሰንካር የሆኑ ግለሰቦች; የፖለቲካችንን አቅጣጫ እየተከተሉ የሕዝብን እርምጃ አደናቃፊዎች;; እባካችሁ በቅርብ የምታውቋቸው እንዳላችሁ ምን እያሰባችሁ ነው ብላችሁ ጠይቁልኝ:: የኢትዮጰያ ሕዝብ አላምን ብሏል እናንተን በሉልኝ;; ገዳም ግቡና ፀልዩ በሉልኝ
  ሁለት በማይታወቅ ድርጅት ፔይ-ሮል ላይ ያሉን ግለሰቦች መሃከላችን አስቀምጠን እየቀለድንም እየተቀለደብንም ነው
  Ethiopians, we can’t aford to have another disintigration some-where on the way. We have to open our eyes and watch the Engineer (Hailu) and the Progfessor (Mesfin). Look their biography. Learn from what they did in the past in Ethiopian Poletics.

  “ይነጋል ያልከው ጭለማን ፈርተህ
  ሻማን ያበራህ ለታቦት ተስለህ
  በኅይሉ ፅና እንዲሆን ተማምነህ
  እኛም ፀሎት አለን ያሰብከው እንዲሆን
  ለዚያች ድሀ ሀገር የተሻለው ይሁን
  መጠንቀቅ ያሻናል ደግሞ አጀብ አንዳይሆን”!!

 39. ዳቆን ሀይለማርያም
  | #39

  ስላም ለመላው ኢትዮጵያኖች ጋዚጠኞች በሙሉ የማንኛውንም ስርጭት እከታተል አለሁኝ ዚናቹህን እርግጥ ነው ይነጋል ያልከው በህልምህ ምናዪህ ነቢዪ ከሆንህ ? ጨለማም ፈርተን ማለት በናአቅጣጫ ወስድከው በሊብነት ነው ? እርግጥ ጨለመ አርፎ መተኛት መልከስከስ የለበትም ? እርግጥ ነው ሻማን ያበራህ ለራስህ ምሳሊ ነው ለታቦት ተስልህ አይደለም ያላዪህውን ጨለማ ስለነበርህ ማብሪያትህ አይንህ ምስክር የሆህ ምልክት የሰጠህ ለአይንህ ነው ? ያም በሀይሉ ጸናህ አይተህ ብላ አይተህ አምብብ አይተህ ፍራ ? አይተህ ተናገር እነዚህ ም መንፈሳዊ ያን ጋዚጠኞች ና መጽሂትም የነበረ የታወቀ በወር በቀን በአመት ባማካኝ ከአምሳ እስከ ሰባህት ሺህ ቅጂዎች ብቻ አይበቁም ቢታተሙሙ አንባቢ አላቸው የላቸውም አላማዊ ሃሳባቸው ጋዚጦኞች ምንድነው ? አድሎ ማድረግ ያላዩትን መነናግር ያልሰሙትን ማውራት ግን ምሳሊ ዘጠኝ መቶ ሰባሁልት ሺህ ቅጂዎች ታትመው ለስርጭት ይበቃሉ ማለት ጥራት የላቸውም ? የኒ በትር ትንሽ ? ያንተበትር ትልቅ ? ሁሉም በትር ናቸው? እስላም ያመጣው ጣጣ የኒ እምነት ጥሩ ቅዱስ የሚለው ስተቱን አይታቹህ በትሩን መዝኑት ? 1ኛ ምሳሊ ሱማሊ ያለው ተጽኖ መሪት የግዚአብሂር መሆኑን እያእቁ ክርስቲያን መኖር መስራት መጸለይ አይችልም የሚሉት በሱማሊ መሪት መልስ ለመስጠት ይህነው በአለም እስላም ክርስቲያን አብረው ይኖራሉ ሱማሊ የብቻው ምድነው ይዘቱ ሀሳባቸው ? ስይርባቸው ያገኘህውን ብላ ይላሉ ?
  ክርስቲአን ቢሰጥም ይበላሉ አይተናንም እየበሉ ይረግም አሉ ትርፉ ምንድነው የሚታዘን እላቸው ? ጥቁር ነጭ ቅይ አይሉም በህዱበት ሁሉ ጥቅም ይፈልግ አሉ ጉቦ ለምን ? ትያቂው ሀይማኖት የላቸም ነው ?

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።