መሬት የመቸብቸቡ ጉዳይ! – ኩችዬ (kuchiye.blogspot.com)

May 29th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

“ችስታ” የመታቸው አገሮች ሰፋፊ መሬታቸውን ለውጭ መንግሥታት በገፍ የመቸብቸባቸው ፈሊጥ በዓለም መድረኮች አነጋጋሪ ሆኗል። በኛው አካባቢም ብዙ ንትርክና ቁጣ እንደጫረ ተረዳሁና ጉዳዩን መመርመር ጀመርኩ። ሳያጣሩ ወሬ ሳያነቡ መምሬ መሆን አጉል ነውና በመጠኑም ቢሆን አንብቤ ያገኘሁትን ላካፍላችሁ።

ፍሬ ነገሩ እንዲህ ነው። በቂ መሬትና ምርት የሌላቸውን እንደ ሳኡዲ፤ ኤሚሬት፤ ኳታር፤ ኩዌት፤ ግብጽ፤ ሊቢያ፤ ቻይና፤ ደቡብ ኰርያና የመሳሰሉትን አገሮች የእህል ዋጋ ሰማይ እየነካ መሄዱ የምግብ ሴኪውሪቲ እያሳጣቸው ነው። ባዮ-ፊውል ለማውጣት ሲሉ ፈረንጆቹ ለዓለም ገበያ የሚቀርበውን እህል መቀነሳቸውም ሼኮቹን ያስደነቀ አይመሰለኝም።

ይሁን እንጅ እንደ ሳኡዲ ያሉትን የናጠጡ ሀብታሞች ያሳሰባቸው ከላይ የተጠቀሰው ብቻ አይደለም። ሳውዲዎች በማይታመን ዋጋም ቢሆን እህል በበረሀ ውስጥ ያመርታሉ። የሳውዲ እርሻዎች ለብሔራዊ ኩራት ምንጭ ሆነው ይቆዩ እንጅ በከርሰ-ምድር ያለውን የውሀ ክምችት ክፉኛ በሟሟጠጥና አካባቢን በመበከል ረገድ ጋውፋህ (የተሲያት እንቅልፍ) የሚነሱ ዓይነት ሆነውባቸዋል። በኢትዮጵያው ኮንትራት የተመረተው ሩዝ በታላቅ ሥነ-ሥርዓት ታጅቦ ለሳኡዲው ንጉሥ ሲቀርብላቸው በፈገግታ የተሞሉት ያለምክንያት አልነበረም። ለምን አይሞሉ? ርስቱ ከወንዝ ባሻገር፤ የተገኘው በነፃ፤ የኤክስፖርት ታክስ አይከፈልበት፤ የሚሟጠጠው የሌላ አገር ውሀ፤ የሚመረዘው የሌላ አገር መሬት።

ከወዲሁ ላስጠንቅቃችሁና የውጭ ኢንቬስትመንት ለዕድገት እጅግ አስፈላጊ ግብአት ነው ከሚሉት ወገን ነኝ። ስለሆነም የመሬቱን ኮንትራት የማየው በ “ጠርጥር” መነጽር ተጋርጄ አይደለም። ለዚህም ነው አዲስ ዓይነት “የጅ-አዙር ቅኝ አገዛዝ” ወዘተ የሚለውን ዝባዝንኬ ክርክር የማልስማማበት። አገርም ግለሰብም የሚፈርሙትን ውል በቅጡ ካሰቡበትና ጥቅማቸውን ለማስከበር በቂ ጥንቃቄ ካደረጉ የጅ-አዙርም የሌላም ዓይነት ቅኝ አገዛዝ ሰለባ አይሆኑም። ደ!

በነገራችን ላይ በመሬት ችብቸባው ንግድ የተሰማራችው ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ሱዳን፤ ዛምቢያ፤ ታንዛኒያ፤ ኮንጐ፤ ሞዛምቢክ፤ ካምቦዲያ፤ ዩክሬን፤ ሰርቢያና የመሳሰሉት ጭምር ናቸው። ሩስያ አውስትራሊያና ብራዚልን የምያካክሉ የዳጎሰ ኤኮኖሚ ያላቸው ሳይቀሩ ከነሳኡዲ ጋር ሽር ጉድ እያሉ ነውና ያዲሱ ዓለም የኢንቬስትመንት ቄንጥ ይህ እንደሆነ እንወቅ። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያም ድርሻዋን ለማግኘት ብትሯሯጥ ልንገረም አይገባም – ኢንቬስትመንት ካፒታል እንደሷ የሚያስፈልገው አገር የለምና።

ታዲያ ችግሩ የት ላይ ነው? በጣም ጥሩ ጥያቄ። ችግሩ ያለው መሬት የሚቸበችቡት አገሮች ግልጽነትንና ተጠያቂነትን በማያውቁ መንግሥታት ሥር የሚተዳደሩ መሆናቸው፤ አኮናታሪዎቹም ተኮናታሪዎቹም ሙስናን ባህል ያደረጉ መሆናቸው፤ የውል ዝርዝሩ ድብቅ መሆኑ፤ ኢንቬስተሩ ያመረተውን እህል ሙልጭ አድርጎ ወዳገሩ ወይንም ወደ ዓለም ገበያ የመውሰድ መብት እንዲኖረው መደረጉ ይገኙበታል። ይህ ብቻ አይደለም! ውሉ ስለከባቢ ዓየር መበከል፤ ስለብሔራዊ የውሀ ቋት መሟጠጥ፤ ስለነዋሪው ሕዝብ መፈናቀል ከመጨነቅ ይልቅ የኢንቬስተሩንና የውል ሰጨዎችን ኪስ በማሟሸት ላይ የተጣደፈ ነው የሚሉም ይበዛሉ። እኔ ማነኝና ነው አዋቂዎች የሚሉትን ላስተባብል የምሞክረው? እንቀጥል…

ከኢንቬስተሮቹስ ምን ይጠበቃል? ይህም ሌላ ጥሩ ጥያቄ ነው። ኢትዮጵያን በሚመለከት ከሳውዲ ኢንቬተሮች ጋር የተፈረመው ውል በምስጢር ስለተያዘ ምን ዝርዝር እንዳለው አይታወቅም። ይህ ነው እንግዲህ ግልጽ ያለመሆን ጣጣ። ኢንቬስተሮቹ የሚሉት የሥራ ዕድል፤ ምርጥ ዘር፤ አዲስ ቴክኖሎጅ፤ ዘመናዊ ማኔጅመንት፤ ትምህርት ቤቶች፤ ክሊኒኮች፤ ይዘን እንመጣለን ነው። ከተጠቀሱት ጥቅሞች ኢትዮጵያ ምን ያህሉን እንዳገኘች የሚያውቅ ሰው ካለ ይንገረንና የትኞቹ ዕውንት የትኞቹ ደግሞ ባዶ ተስፋ እንደሆኑ መለየት እንችላለን።

እስከዚያው ድረስ ግን ከሌሎች አገሮች ያገኘነውን ተመክሮ መሠረት አድርገን መወያየቱ ክፋት የለውም። ሌሎች አገሮች ውስጥ የተቋቋሙ የ “መንግሥት-ለመንግሥት” ወይንም የ “መንግሥት-ግል” የርሻ ኮንትራቶች ብዙ ፋይዳ አሳይተው እንደማያውቁ ያለም ታሪክ ይመሰክራል። ለነገሩ መንግሥት የሚይዘው ነገር የት ቦታ ነው ፈይዶ የሚያውቀው? ባንጻሩ ደግሞ የውጭ የግል ኢንቬስተሮች ካገሬው የግል ኢንቬስተሮች ጋር የሚጀምሯቸው ፕሮጀክቶች ብዙ ውጤት ታይቶባቸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ሁሉን በጄ ከሚለው አባዜ እስካልተላቀቀ ድረስ የሳውዲውም ሌሎችም ፕሮጀችቶች ብዙ ዕድሜ እንደማይኖራቸው ከወዲሁ መመስከር ይቻላል።

ወደማጠቃለሉ ላምራ። ከላይ እንደጠቀስኩት የውጭ ባለካፒታሎች በደሀ አገሮች ውስጥ የእርሻ ሥራ ለማስፋፋት መሺቀዳደማቸው የዘመናችን ክስተት ነውና ልናቆመውም ልንሸሸውም አይገባም። ጥያቄው ኢንቬስተሮች ይግቡና አይግቡ ከሚለው ላይ አይደለም – ይህ ብዙ አያከራክርምና። ፍሬ ነገሩ ያለው እንዲህ ያለው ውል ሁለቱንም ወገን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ የሚጠቅም ነው አይደለም ከሚለው ላይ ነው። ለዚህ ደግሞ የግልጽነት ጥያቄ ወሳኝ ይሆናል። ያገሬው ኢንቬስተር ተሳታፊነት ወሳኝ ይሆናል። ብሔራዊ ጥቅም የማስከበሩ ጉዳይ ወሳኝ ይሆናል። ተገቢው የኤንቫይሮንሜንት ሕግ መውጣቱና ማስከበሪያ መሣሪያዎቹም መደራጀታቸው ወሳኝ ይሆናል። የውጭው ካፒታል የሚንቀሳቀስበት የሕግ ዳር-ድንበር መከለሉ ወሳኝ ይሆናል። ስለሚፈናቀለው ገበሬና በከብት-ርቢ ስለሚተዳደረው ሕዝባችን እጣ-ፈንታ በቅጡ ማሰብ ወሳኝ ይሆናል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ የዴሞክራሲ የመልካም አስተዳደርና የሕግ የበላይነት መስፈንን የግድ ይላል።

እነዚህ ሳይሆኑ ቀርተው የመንግሥት ቢሮክራቶች በግብታዊነትም በሌላ ተነሳሺነትም የሚያደርጉት ውሳኔና የሚፈራረሙት ውል የሚያስገኘው ጥፋትና ኪሣራ ነው። በቆቃ ሀይቅና በወንዞቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ሁኔታ አሳዝኖን ከሆነ ይኸኛው ደግሞ ከትውልድ ወደትውልድ የሚተላልፍ የሀዘንም ሀዘን ይሆናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የውሎቹን ዝርዝር የማወቅ መብት አለው።

Kuchiye@gmail.com

———-
(እንግሊዝ ለሚቀናችሁ፡ “The Economist” May 23, 2009 አንብቡ። ብዙውን ያገኘሁት ከዚያ ነው)

 1. በለው
  | #1

  “ችስታ የመታቸው ሀገሮች” በቡጢ,በቃሪያ ጢፊ,ወይስ በሾኬ ?በአነበቡት ላይ የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖርዎት ” የግሎባላይዜሽን ውጤቱ- ያበጠው ሲፈነዳ- ሕብረተሰቦች ሲተረማመሱ-ለእኛም ሲትርፈን” ክቡር አቶ ፈቃዱ በቀለ የተጻፈውን ያንብቡ..fekadubekele@gmx.de
  “ኢንቨስተመንት ለዕድገት አስፈላጊ ግብዓት ነው” ያሉት.. ሳንቲም ተዘርቶ በዶላር ዛፍ ሥር ቁጭ ብሎ መፅሐፍ መግለጥ ነው” ” የመሬት ኮንትራት በሕጉ ከመቶ ዓመት ባልበለጠ ነው” በዚህም ማዳጋስካር ለ99 ዓመት በመፈረሟ ሦስት ትውልድ መስራት እንደማይችልያልተወለደውም በኪራይ መሬት እንደሚኖር ያሳያል ካስፈለገም የኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥር 2020 የሚደርስበትን ትንበያ ማገናዘብና ዕጣ ፋንታቸውንም የሕገ-መንግስቱን ትንታኔ ማንበቡ የተሻለ ይመስለኛል::
  በክሊንተን አስተዳደር ክብርት ኦልብራይት በአፍሪካ ጉብኝታቸው ፎቶ እየተነሱ እንዳሉት
  “ተመልከቱ የአፍሪካ ወጣት መሪዎች አፍሪካን ለመለወጥ ቆርጠው ተነስተዋል” በአራዳው ቋንቋ
  ፉገራ, ጥገራ, ሽርደዳ,ወይስ ተመልከተኝ ገደል ስገባ እንዳለው ይሆን ?
  “የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ” ዝባዝንኬ ያሉት (መሬት መቸብቸብ) ሰው መሸጥ ቀርቶ ሉዓላዊነትን
  ማፍረስና ከቤት ባለቤትነት ተከራይ መሆንን አበክረው ይደግፋሉ::? “የዓይን አፍዝዝ የእጅ አደንዝዝ የሥነ-ልቦና ጦርነት ወይስ የትውልድ መርዝ ብለን እንሠይምልዎ ?
  “የኢትዮጵያ ሕዝብ የውሎችን ዝርዝር የማወቅ መብት አለው” ማን ሰው አለሽና” “የብሔር-ብሔረሰብ ህዝቦች በአንድ አላማ በአንድ የፖለቲካ ጥላ ስር ሆነው በጋራ ይኖራሉ”(…)
  ተቀናቃኝ ፓርቲም አያስፈልግም በሚወጣልህ መመሪያ እየተዳደርክ የመናገር በብት ሲኖርህ
  ለመደመጥህ ግን ዋስትና የለውም ትጠይቃልህ እንጂ አትወስንም:: ልብ ያለው ልብ ይበል!!!!!!
  ከምስጋና ጋር (ከካናዳ)

 2. ዓቢይ
  | #2

  ለመሆኑ ትምህርት ቤት የሚከፍቱት ለማን ነው? ምን ለምስተማር ነው? አስተማሮቹስ እነማን ናቸው?
  ትምህርቱስ ምንድር ነው? መስጊድ መስራትስ አይፈልጉም? እጅ አዙር ወረራው ይሀ ነው. ቀልድ!!!

 3. Mes
  | #3

  ወንድሞች ከሁሉ የሚያሳዝነው የአገሬው ሰው እርሻውን አርሶ ምርቱንም አምርቶ ልክ ለሽያጭ ሊያቀርብ ሲል ሆን ተብሎ በእርዳታ እህል ለህዝቡ ወይም ለአካባቢ ላለው ህዝብ ይሰጣል: ያ ያመረተው ገበሬ ልፋቱ ሁሉ ከንቱ ይሆናል ሰዉም በነጻ ሲያገኝ ግዢውን ይተዋል:: ያም ገበሬ ያመረተውን ወይ መንግስት አይገዛው ወይ ህዝቡ አልገዛው ያመረተው እንዲሁ መና ይቀርና ከጥቅም ውጪ ይሆናል:: እንግዲህ ይህ የሆነበት ያገሬው ገበሬ ምን ብሎ ለሚቀጥለው ግዜ በመሬቱ ያምርት? እሱም እንደ ተጡዋሪው ማምረቱን ትቶ እርዳታውን መጠበቅ ጀመረ:: የውጪም ረጂዎች ልክ ገበሬው ማምረቱን ሲተው አውቀው እርዳታ ይቀንሳሉ ወይም ያቆያሉም ያቆማሉምም; ከዛ ነው እንግዲህ ድርቁም ብቅ የሚለው:: አንዴ በኦጋዴ አካባቢ የሆነውም እንደዚሁ ነበር ገበሬው ሩዙን አምርቶ ሊሸጥ ሲል ከየት መጣ የማይባል እርዳታ በነጻ ሃገሬው ህዝብ ታደለ ያ ለፍቶ ያመረተው ገበሬ ካለምንም ጥቅም ሩዙን ገደል ከተተው ግማሹን በነጻ ከስሮ እርም እንዲል አደረጉት:: የወያኔም መንግስት አውቆ ገበሬው አሰነፈው “ያመረተውን እንኩዋን ምናለበት ቢገዛው?” ያንን ግን አይፈልግም ያው ከላይ ለተጠቀሱት መሸጥ ስለሚፈልግ እንደዚህ አይነት ኬኦስ መፍጠር ስላለበት:: ወይ አገራችን ተጫወቱባት!

 4. በለው
  | #4

  ዓቢይ :
  ለመሆኑ ትምህርት ቤት የሚከፍቱት ለማን ነው? ምን ለምስተማር ነው? አስተማሮቹስ እነማን ናቸው?
  ትምህርቱስ ምንድር ነው? መስጊድ መስራትስ አይፈልጉም? እጅ አዙር ወረራው ይሀ ነው. ቀልድ!!!

  “ከእጅ አዙር ቅኝ ግዛት” “የስነ-ልቦና ጦርነት” ፀሐፊው ያላነበበውና ያልተረዳው..አመሰግናለሁ!

 5. በለው
  | #5

  Mes :
  ወንድሞች ከሁሉ የሚያሳዝነው የአገሬው ሰው እርሻውን አርሶ ምርቱንም አምርቶ ልክ ለሽያጭ ሊያቀርብ ሲል ሆን ተብሎ በእርዳታ እህል ለህዝቡ ወይም ለአካባቢ ላለው ህዝብ ይሰጣል: ያ ያመረተው ገበሬ ልፋቱ ሁሉ ከንቱ ይሆናል ሰዉም በነጻ ሲያገኝ ግዢውን ይተዋል:: ያም ገበሬ ያመረተውን ወይ መንግስት አይገዛው ወይ ህዝቡ አልገዛው ያመረተው እንዲሁ መና ይቀርና ከጥቅም ውጪ ይሆናል:: እንግዲህ ይህ የሆነበት ያገሬው ገበሬ ምን ብሎ ለሚቀጥለው ግዜ በመሬቱ ያምርት? እሱም እንደ ተጡዋሪው ማምረቱን ትቶ እርዳታውን መጠበቅ ጀመረ:: የውጪም ረጂዎች ልክ ገበሬው ማምረቱን ሲተው አውቀው እርዳታ ይቀንሳሉ ወይም ያቆያሉም ያቆማሉምም; ከዛ ነው እንግዲህ ድርቁም ብቅ የሚለው:: አንዴ በኦጋዴ አካባቢ የሆነውም እንደዚሁ ነበር ገበሬው ሩዙን አምርቶ ሊሸጥ ሲል ከየት መጣ የማይባል እርዳታ በነጻ ሃገሬው ህዝብ ታደለ ያ ለፍቶ ያመረተው ገበሬ ካለምንም ጥቅም ሩዙን ገደል ከተተው ግማሹን በነጻ ከስሮ እርም እንዲል አደረጉት:: የወያኔም መንግስት አውቆ ገበሬው አሰነፈው “ያመረተውን እንኩዋን ምናለበት ቢገዛው?” ያንን ግን አይፈልግም ያው ከላይ ለተጠቀሱት መሸጥ ስለሚፈልግ እንደዚህ አይነት ኬኦስ መፍጠር ስላለበት:: ወይ አገራችን ተጫወቱባት!

  “ታመርታልህ አትሸጥም” “ትሰራልህ አታተርፍም” “ትኖራልህ ግን ባለቤት አደልህም”
  መንግስት እንደአስፈላጊነቱ ጣልቃ ይገባል(…) ጠ/ሚ መልስ “ገበሬው በነጻ ገበያ ምርቱን
  በፈለገው ጊዜና ዋጋ የመሸጥ መብቱ ነው መንግስት በተመጣጣኝ ዋጋ ከውጭ ስንዴ ገዝቶ በቅናሽ
  ይሸጣል” አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ አጣች::ለምን ? ስንዴ ስለሸመትን::
  “የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት” ካልተስማማው “የእጅ አደንዝዝ” በሀገሩ ሁለተኛ ዜጋ”አመሰግናለሁ!!!!

 6. dire
  | #6

  this a very superficial and misguided piece. I think the writer wasted his time reading a lot ( as he claims). the land deal has a wider social, ecological, economical and cultural degradations. It obviously has negative imact on Ethiopia and its people. we will write about in detail soon.

 7. ከካምፖ
  | #7

  ከካምቦ ወያኔ ስልጣን ላይ ክወጣ ሃያ ሀመት ሊሆነው ነው በዚህ ረጅም ግዜ አገሪቷን ማሳዳግ ይችሉ ነበር በማሳደግ ፈንታ ቀበሯት አንድ አባባል አለ ይሀውም ዝንጃሮ የአንበሳን ሚስት ተዋውቆ ከዚያ በኋላ የአንበሳን መሞት ወሬ ሰምቶ ወደ አንበሳ ቤት ይሄዳል ቤት ከገባ በኌላ የአንበሳ አልጋ ላይ ወጥቶ ቁጭ አንዳለ አንበሳ ስለ ነበሪ ዘሎ ዝንጃሮ ስይዛው በአንበሳው ሀይን አፈር በትኖ ያመልጣል ዝ ንጃሮውም ደሙን አየዘራ ስመለስ አናትዮው አይተው ችኩል ልጄ ክመቼው አረድክ ስትለው አረዱኝ አላረድኩም ወደ መጠሽበት ተመለሽ

 8. ይህን በለው
  | #8

  ከካምፖ :

  >መጣም የሚገርመው(የሚያሳዝነው)ይህን የኮሚኒስት መፅሐፍ እንዴት ቢያነቡት ነው
  አንደኛው “እያመርትን እንዋጋለን” ሲል ሌላው “እያፈረስን እንሰራለን” ይላል ከ17 ዓመት በኋላ
  ተነስተው ዛፍ ከመትከል ስልጣን ከያዙ ጀምሮ በቅንንንት ቢሰሩ በ19

  dire :
  this a very superficial and misguided piece. I think the writer wasted his time reading a lot ( as he claims). the land deal has a wider social, ecological, economical and cultural degradations. It obviously has negative imact on Ethiopia and its people. we will write about in detail soon.

  ዓመት ጊዜ ውስጥ ዛፉ ተተክሎ በነበርና ዛሬ ወጣቱ ዛፉ ሥር ተቀምጦ መፅሀፍ ባነበበ ሕፃናት ኩኩሉ በተጫወቱ ነበር
  ችግሩ “ያልታደለች ያዢ ያጣች ሀገር” መሆኗ በ90% የልመና ኑሮ 11.2% ዕድገት ባልተቀለደብን
  በጣም አሳዛኝ እና አሳፋሪ የትውልድ ጠባሳ “እየሳቁ መሞት”

 9. ከካምፖ
  | #9

  ከካምቦ ወያኔ ለረዥም ግዜ ስልጠን ላይ ብቆዩም ያች የጫካ ባሕር አላቃቀቸውም ለመጥቀስ ያህል የቆቅን ህንቁላል ከጫካ አምጥተዉ ዶሮን ቢያስተቅፏት ጫጩቶችን ትፋላፍላሌች ሆኖም ካደጉ በኋላ በራው ወደ ጫካ ይመለሰሉ ምክንያቱም የጫካ ባሕር አይለቀቸውም

 10. ከካምፖ
  | #10

  ከካምፖ ወያኔ በየሀመቱ የ ህካኖሚ ሕድገት አሳየን በማለት በማዝራፍ በተራባ ሕዝብ ያሾፋል ቀድሞስ ኮራፖት ከሆነ ምን ሕድገት ይጠባቃል ጅብ በማየውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ሆኖ ነው ህንጅ

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።