አቡጊዳ- ባላገሩ ከተሜዉ በአንድነትና መኢአድ መቀራረብ ተደሰተ !

May 30th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

አቡጊዳ – ግንቦት 22 2001 ቀን 2001

ግንቦት 20 ቀን የቃሌ ምሽት በተሰኘዉ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን በግፍ መታሰር የሚያስታወስ ምሽት ላይ፣ በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጽ/ቤት፣ የተከበሩ ኢንጂነር ኃያሉ ሻወልና በርካታ የመኢአድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ተገኘተዉ ለክብርት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ያላቸዉን ሶሊዳሪቲ እንዳሳዩ አወደ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ የሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች ማህበር መዘገቡ ይታወሳል።

በአዲስ አበባና በክፍለ አገራቱ የዚህ የቃሌ ምሽት ክስተት እንደ ትልቅ አብይ ዜና፣ ሰዉ ለሰዉ፣ በአፍና በሞባይል የተሰራጨ እንደሆነ የነገሩን አዲስ አበባ ያሉ ዘጋቢዎቻችን፣ ባላገሩ ከተሜዉ ሁሉ እጀግ በጣም እንደተደሰተና እንደፈነደቀ ገልጸዉልናል።

በአንጻሩም ደግሞ የወያኔ ካድሬዎች የአቶ ኃይሉ ሻወል ከነኢንጂነር ግዛቸዉ ጎን መቆምና ከነርሱ ጋር በወንድማማችነት አብሮ መተቃቀፍ ከቶዉኑ ያልጠበቁትና ያስደነገጣቸዉ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል።

በመላዉ የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትና በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ መካከል የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነት እምብዛም እንደሌለ፣ በነዚህ ሁለት ድርጅቶች ዉስጥ ያሉትም ከፍተኛ የአመራር አባላት በብዛት በጋራ በቅንጅት ዉስጥ ይሰሩ የነበሩና አብረዉ በግፍ በወያኔ በቃሊቲ የተሰቃዩ እንደነበረ ይታወቃል። ነገር ግን በጥቃቅን ትናንሽ ነገራት፣ ሰይጣን በመሃከላቸዉ ገብቶ፣ በመለያየታቸዉ ለሕዝቡ የሐዘን ለወያኔ-ኢሕአዴግ ደግሞ የደስት ምክንያት ሆነዉ መቆየታቸዉ የማይካድ ነዉ።

በቅርቡ አይጋ ፎረም የተሰኘዉ ድህረ ገጽ ትላንትና የመኢአድን ፕሬዘዳንት ሲያቀልና ሲሰድ እንዳልነበረዉ ሁሉ፣ አሁን የመኢአድ ደጋፊ በመመስል፣ ሆን ብሎ መኢአድን ጥላሸት ለመቀባት፣ ከሌሎች እንደ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጋር የበለጠ ለማራራቅ እኩይ ተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱ ይታወሳል።

በሕዝቡ ዉስጥ የነብረዉን ሃዘን፣ ይህንንም የአይጋ ፎረም ተንኮል የተመለከቱ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ «የመኢአድና የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባላት በአንድ ላይና በጋራ መቆማቸዉ ወያኔ በነአይጋ ሲሸርበዉ የነበረዉን ተንኮል እንደካሸፉት የሚይሳያ ነዉ» ሲሉ በቃሌ ምሽት የሆነዉን ክስተት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠዉ ገልጸዋል። ሕብረት መፍጠር፣ በጋራ መስራት ምንጊዜም ከባድ እንደሆነ ያስረዱት እኝህ የፖለቲካ ተንታኝ፣ የአንድነትም ሆነ የመኢአድ አመራር አባላት፣ ወደፊት ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ አንዳንድ ኃያላት እንዳሉ በመረዳት፣ ካለፈዉ ስህተቶቻቸዉ ተምረዉ ታሪካዊ ሃላፊነታቸዉን በጥንቃቄና በማስተዋል፣ በመቻቻልና የአገርን ጥቅም በማስቀደም፣ በትህትናና በቅንነት መወጣት እንዳለባቸዉ አስገንዝበዋል።

«ከዚህ በፊት እንደዚህ .. እንደዚይ.. ተደርጎ እንዴት አሁን በጋራ ይሰራል ? ለሚሉ ምን አስተያየት አልዎት» ያልናቸዉ አንድ የእድሜ ባለጸጋ፣ ከመጽሃፍ ቅዱስ የእዮብን መጽሃፍ በመጥቀስ «ጻደቅ ሰባት ጊዜ ወድቆ ፣ ይነሳል» ሲሉ ቁም ነገሩ «ስህተት ለምን ተሰራ? ለምን ተወደቀ ? » የሚለዉ ላይ ሳይሆን ከስህተት ተምሮ ወደፊት ስህተትን ላለመሥራት መሞከሩ፣ ወደቆ ደግሞ መነሳቱ ላይ እንደሆነ በመግለጽ የአባትነት ምክራቸዉ አስተላልፈዋል። ሲያክሉም እኝህ አባት «ደግሞ ተሳሳቱ የተባሉ ሰዎች እኮ ሰዎች ናቸዉ። የሰሩት ስህተት ላይ ብቻ አተኩሮ እነርሱን ለመቀበል ግጥር ከመሆን ከዚህ በፊት የሰሩት ጥሩ ነገራትንም ማሰብ ቢቻል እኮ የበለጠ ፍቅርን ያጠነክራል። ከአሁን በኋላ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ መመልከት አያስፈልግም» ሲሉ አስትያየታቸዉን ሰጥተዋል።

ሌላ ያነጋገርናቸዉ አንዲት እናት «ይሄ ሁሉ የሆነዉ በዚች ልጅ መታሰር አይደለም ? እነ አቶ መለስ በራሳቸዉ ላይ እሳትን ነዉ የለኮሱት ። ይኸዉ ስንት ነገር ተሞክሮ ሊቀራረቡ ያልቻሉ ፣ ወያኔዎች በዚህ ሴት ላይ ግፍ ሲሰሩ አምላክ ለጥፋት ያሰቡትን ለመልካም አደረገዉ። ለኢትዮጵያ አንድነት የቆመዉ ኃይል የበለጠ ተጠናከረ» ሲሊ ነበር የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰር የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመብቱ፣ ለነጻነቱና ለአገሩም አንድነት የሚያደርገዉ ትግል ላይ ትልቅ አስተዋጾ እያደረገ እንዳለና የወይዘሪት ብርቱካን መታሰር የትግሉ ማእዘን እንደሆነ የገለጹት።

 1. ዘንድሮ
  | #1

  ይዋል ይደር እንጂ እውነት ተቀብራ አትቀርም::መቀራረባቸው እረፍት ከሚነሳቸው ወዳጅ መሳይ ጠላቶች እንደተለመደው ወሬ በማመላለስና አሉባልታ በመንዛት ተለያይተው እንዲቀሩ የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደማይኖር ከወዲሁ መተንበዩ አያዳግትም: በተለይም በመከፋፈላቸው የአንድነት ድጋፍ ድርጅት- የመኢአድ ድጋፍ ድርጅት አውራ ነን ባይ ነፈዞችን ነቅቶ መጠበቅ ነው::
  ከዲያስፖራ የኢትዮጵያን የወደፊት የነጻነት እቅጣጫ መዘወር እንደማይቻላቸው ማወቅ ይገባቸዋል::
  ኢንጂነር ሃይሉ መልካም ጅምራቸውን ገፍተውበት ብርቱካን እስክትፈታ የጋራ ትግሉ መቀጠል ብሎም ውህደቱ እንደሚከተል ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ::
  አውራሪስ ዘብሄረ ኢትዮጵያ

 2. Meyisaw
  | #2

  Woyne is done great tric in the eye by the cleaver kinjit fellows. They thought they have managed to disintegrate kinjit, but it has become now like kind of biological propagation by fragmentation with multicaceted front. One part gun totting Heroes of Ginbot 7, the other playing cat and mouse on the nose of woyane. No way for woyane except to surender either peacfully or at point of gun

 3. Anonymous
  | #3

  Now is time for the alliance to the armed political groups – EPPF OLF ONLF TPDM and G7

 4. AGERE_ETHIOPIA
  | #4

  መልካም ጅምር ነው::

 5. Anonymous
  | #5

  ወያአነ አንድ ለናቱ የሆነው የጎተራው ድሊዲይ ይፈለገውን ሰምይስተው እኝዓ
  ethiopia ውያን ግን በወዱ DR አርቲስቲ ጥላሁን ገስስ ሥምስይመነዋል
  DR አርቲስቲ ትላአሁን ገሰሰ መንገድ (ወይም አደባባይ) dokmas k.s.a

 6. አቢይ፡ኢትዮጵያዊ
  | #6

  ))))))))))))ከቀረ ያረፈደ ይሻላል::((((((((((((
  ሽማግሌዎቹም ቀሩ
  እንዳይሞቱም ፈሩ::
  በታሪክ ግን ሲጠሩ
  የደም ይሆናል ምስክሩ::
  እናም የመኢአድ ቃል
  ለትግል ብቻ ይበቃል::
  ተቃዋሚ ስንት አለ
  ለዓላማ የማለ::
  ግና
  አልተነኩምና::
  ተራቸውን መጠበቁ
  ስለማያደርጋቸው ንቁ
  የብርቱካንን
  የጋራ ነጻነት ዕምነትን::
  እንደምን አዩት ይባላል?
  እነሱ ቢቀሩም እንኳ
  ያረፈደ ግን ይሻላል::
  በርቱ
  በርቱ!!!!!

 7. ፍቅር
  | #7

  በጣም ጥሩ እና አበረታች ጅምር በመሆኑ እባካችሁ አይዞአችሁ በርቱና በጋራ ስሩ!
  አንድ ስንሆን ሰይጣንም ሆነ ወያኔ ያፍራሉ!

  ጌታ ይባርካችሁ!
  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

 8. Anonymous
  | #8

  @ፍቅር
  ያስረፈዱት ወጣት
  ሲቀስሩ አንዽን ታት
  አራቱን አይረሱት
  ወደ እርሶ ያዙሩት
  እኒሀ አዛወንቶች
  የቁርጥ ቀን ልጆች
  ለራስ መኖር ወደ ጎን
  የሕዝብ በደል እሮሮን
  መታሰር መገደል መታፈንን
  በቃኝ በል በማለት ሊት ተቀን
  ሲያደራጁ በመላዋ ኢትዮጵያ

  መኢአድ አርፍዱአል እንዲ ታድያ?

  MEAD ለቅንጅቱ መሰረት ምሰሶ
  ሕዝብን አስተባብሮ ለድል አድርሶ
  በአጋዚ ወያነ ተቀማ ደሙን አፍሥሶ
  ሊያተፉት ቢጥሩ ቢያቅቶት እርሶ

  የብርቱካንን
  የጋራ ነጻነት ዕምነትን::
  እንደምን አዩት ይባላል?
  እነሱ ቢቀሩም እንኳ
  ያረፈደ ግን ይሻላል::
  ከነአስተዋይ መሪው አይጥፋ መኢአድ
  ስሙም አንድነት ነው ሳያረፍድ የሚነጉድ
  ለወ/ሪት ብርቱካን ትፈታ
  አብሮ ለመታገል የታሰሩትን ወያነ እንዲፈታ
  ኢንጅነር ሀይሉ ሻውል በመገኝታቸው
  አንድንት ወዳጆች እንኩአን ደስ አላቸው::
  መኢአድ UDJ እንዲሁም ሌላው
  በኢትዮጵያዊነት ቁምስቅሉን ለሚያየው
  መፈናፈን አቅቶት በቁም ለታሰረው
  በዘር እና በቁአንቁአ በእምነት ሲክፍለው
  ለከፋፍለህ ግዛው ለሱ እንዲመቸው
  ሕዝብ እንዲተላለቅ ሊቀጥል ዘረፋው
  መፍትሔው አንድነት እጅ ለጅ መያያዝ ነው::

  እናም ወገን መጎሻሸሙ ብዙ አስተምሮናል
  ትግሉ አሁንም አንድንትን ይሻል
  ያለፈው ኩደታ ለታሪክ ተመዝግቦ አልፉአል
  ያመታውም መዘዝ የሕዝብ ትግል አዳክሙአል::
  ያስረፈዳችሁት በስደት ለግል እውቅና ለጥቅም ብላችሁ
  የትናንቱ እንዳይደገም ይሰብሰብ አፋችሁ
  መኢአድን ከማዳከም ና ትችቶች ወታችሁ
  ሀገርና ሕዝብ ሲሞትና ሲተፋ እያያችሁ
  ሽማግሊ አሮጊት ስትሉ ስንሰማችሁ
  እናንተን በተግባር የትም ሳናያችሁ
  ከመቅዳት ማፍረስ በሻገር ሳታሳይ ሰርታቹ
  ከአምባገነኑ ወያነ እና ሻብያ ምኑን ተሻላችሁ??
  ይልቁስ ከተራው ጉሽምሽም ወታችሁ
  እናንተም በርቱ እና ይፍረድ ምግባራችሁ::
  ስህ

 9. ben
  | #9

  GOOD JOB UNIT IS ??????PPPPPPPP

 10. Anonymous
  | #10

  ወያነ በራሱ ላይ የለኮሰው እሳት እየለበለበው ነው ዋናው የጝ መተኒከር ነው ግንቦት ሰባትን በመርዳት ወያነን በማንቀትቀት በውሰት ደሞ አንድነትን በመርዳት ወያነን ጉሮሮውን አንቆ ወደገነቡአቸው ኢስር በቶች ማጋዝ ነው

 11. አትዮጽያ
  | #11

  may god be with u!!!
  god bless ethiopia!!!

 12. Alebachew Taye
  | #12

  Its Obvious for Millions of Ethiopians that MR. Shawel Arrogant personality and Personnal Eggo Contributes tremendously for dismatling and divisions of KINJIT 2 yrs ago .Even if it took him 2 yrs its a good gesture to come to his sense and admit unity and not personal eggo Will lead us to Democratic Ethiopia

 13. አበበ
  | #13

  መቀራረቡ የሚያስደስት ነው ሆኖም ሊያራርቃቸው የቻለውን መንሰሄ አብጥረውው በማውጣት በሰከነ ሁኔታ ተውያይተው መፍታት ካልቻሉ ለጊዜው ሕዝቡን ያስደስት ይሆን እንጂ ዘለቄታ የሚኖረው አይሆነም በሺታውን የደበቀ መዳህኒት አይገኝለትም ይላሉ አበው

 14. መዪሳው
  | #14

  I personally am a strong believer in reconciliation ,and everyone who is involved in Ethiopian politics must adopt such a gesture.But,what we are lacking is an admittance of guilt on the part of the so called political figures in our country.I strongly believe Engineer Hailu and his blind supporters are responsible for dismantling and disintegration of the only hope of the Ethiopian people “KINIJIT”.After two years he has realized the truth and is coming to his sense,which I think is a good thing but how can we trust this guy in the future?We Ethiopians lack a fundamental principle of admitting mistakes and apologizing for what we did.We should start this noble culture of transparency and accountability for our actions,otherwise it will be a big sum ZERO game again and again.ታጥቦ ጭቃ ይሆናል!!!!!

 15. አስራት
  | #15

  አስራት :
  ነገሩ ጥሩ ይመስላል
  እኔ ግን መራረባቸውን የማየው በጥርጣሬ አይን ነው
  ምርጫ 2002 ስለቀረበ እንደ ምርጫ 97 ሁሉ በጋራ ለመቀስቀስና ለማሸነፍ ለማሰብ መስሎ ታይቶኛል መቀራረባቸው
  ይህን መከረኛ እንደለመደበት ያስጨርሱና እነሱንም ወያኔ ስብስቦ ቃሊቲን ያጉራቸዋል ::

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።