የሌባ ተረት – ብርዞ ፍራንክፈርት

June 22nd, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

የ አቦይ ስብሃት ግብና አባባል
የሚያቅለሸልሽ ጥሬ ግንፍልፍል
የመዋህለ ነዋይ ተንታኝ ርዕሰ ሊቅ
የካፒታሊዝም ጽንሰ ሃሳብ ዱዳ አባ ዘብርቅ
የመለስ ጆሮ ጌታ የውሸት ግርፍ
የማፍያ መሃንዲስ አባ መንትፍ

ተቃውሞ ሳይገጥመን ገዛን ባይ
አይነ በላ ቀጣፊ አታላይ
የማይጸጸት አረመኔ ልበ ድንጋይ
የአስር አፈና ቀያሽ ነፍሰ ገዳይ

ማሰቢያ አልባ ሃፍረተ ምንም
ዘረኛ ከንቱ የ ዜጋ አረም
የመጮሙማ የአህምሮው ስባት
ስሙም ይመስላል በራሱ አንደበት
ከዋሾ መንጋ ከልጋግ በረት
የወያኔ ንግድ የሌባ ተረት
አቦይ ድሪቶ የታሪክ ዝተት
እጅህ ወደ ሁዋላ፡እስከሚቁዋጠር
አስበህ ተንፍስ ከመቀባጠር
ትን እንዳይለን በውሸት፡ዲስኩር
ለካድሬ ቁንጮ ምሑር ስባት
ዓይን አንጨፍንም ለሌባ ተረት

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።