በቦስተን ከተማ ተዘጋጅቶ የነበረው የአዲስ ዓመት ዝግጅት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑ ሲገለጽ፤ በትግራይ ኮሚኒቲ የተዘጋጀው የአዲስ አመት በዓል ዝግጅት እስካሁን እንድቀጠለ መሆኑ ታወቀ፤

September 8th, 2016 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

“የኢትዮጵያ እንቁጣጣሽ በቦስተን የድጋፍ ማህበር፤ ከቦስተን ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር በየዓመቱ የኢትዮጵያን አዲስ አመት በጋራ እና በኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንደሚያከበሩት ይታወቃል። በ፪፻፱ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በተለይ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ሐዘን ምክንያት በዓሉን ሻማ በማብራት፤ የሕሊና ጸሎት በማደርግ በሕብረት ከወገኖቻችን ጋር ለማክበር በዝግጅት ላይ ነበርን፤ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት አገራችን ያለችበትን ሁኔታ በማጤንና እኛም የሕበረተሰቡ አካል በመሆናችን ዝግጅቱ ላልተወሰነ ግዜ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፤ የድጋፍ ድርጅቱ ወደፊት ዝግጅቱን አጠናቆ ጥሪ የሚያደርግ መሆኑን፤ ለቦስተን እና አካባቢው ሕብረተሰብ ከታላቅ ከይቅርታ ጋር እናስታውቃለን። ትኬት የገዛችሁ ወገኖች ትኬታችሁ ወደፊት በምናዘጋጀው ዝግጅት ላይ ሙሉ ዋጋ ያለው መሆኑን እንገልጻለን።” ሲሉ የድርጅቱ ድጋፍ ድርጅት ለዝግጅት ክፍላችን አስታውቋል።

ይህንኑ ዝግጅት አስመልከቶ የዝግጅት ክፍላችን የኢትዮጵያውያን እንቁጣጣሽ በቦስተን ድጋፍ ማህበር ቦርድ ሊቀ መንበር የሆኑትን አቶ መሰለ ክፍሌ አነጋግረን በሰጡን ምላሽ የድጋፍ ማህበሩ አትራፊ ያልሆነ ድርጅት እና በማሳቹሴትስ ስቴት ሕጋዊ እውቅና ያለው ማሕበር፤ መሆኑን በመግለጽ የድጋፍ ማሕበሩ ባለፉት አመታት በቦስተን ከተማ የሚኖሩትን ኢትዮያውያንን በማሰባሰብ ባዘጋጃቸው ዝግጅቶች ፍጹም ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ፤ ሁሉም ኢትዮጵያውያኖች በፖለቲካ፤ በሃይማኖት፤ በዘር እና በብሄር ሳይለያዩ፤ የእኛ የኢትዮጵያውያኖች ብቻ የሆነውን አዲስ አመት ዝግጅት በጋራ የሚያከብሩበት፤ ኢትዮጵያዊነት የሚወደስበት፤ ታዳጊ ወጣቶች ባህላቸውን ማንነታቸውን እንዲያዉቁ የሚደርገበት፤ ኢትዮጵያውያንም ከአገራችው ውጭ አገራቸውን ወደኋላ ዞር ብለው የሚያስታውሱበት ሲሆን፤ ይህንኑ ዝግጅት አሁን አገራችን ላይ ባለው ሁኔታ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ፤ ቦርዱ እና ባህላዊ ዘፋኞቹ ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ዝግጅቱ ላልተወሰነ ግዜ እንዲራዘም የተወሰነ ሲሆን ይሕ ዝግጅት ዋናው ዓላማው ሕበርተሰቡን በማቀራረብ በምንኖርበት አካባቢ ማህበርሰቡ የራሱ የሆነ ማዕከል እና ኢትዮጵያዊ እሴቶችን እና ባሕሎችን ለመጬው ትውልድ ማስተላለፍ መሆኑ ይታወቃል።
በዝግጅቱም ታዳጊ ወጣቶች ከሚያቀርቡት ባህላዊ ዝግጅት በተጨማሪ፤ በቦስተን እና አካባቢ ጊዜያቸውን ገንዘባቸውን እና ጉልበታቸውን ሳይሰስቱ ሕብረተሰቡን ያገለገሉ ሰዎችን እውቅና በየዓመቱ የመስጠት ዝግጅት በዚህ ዓመትም በመቀጠል ለ፪ኛ ግዜ የ፪፻፱ ዓ.ም አሽናፊ ለሚሆነው የቦስተን የአመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት ለመስጠት ታስቦ ነበር፤ በመዝናኛ በኩል ታዋቂው የባህል ተጫዋች ድምጻዊ ይሁኔ በላይ፤ ግዛቸው ሃ/ማርያም እና በተጨማሪም ተጋባዥ ድምጻዊት ሕይወት አያሌው በዕለቱ የባህል ጨዋታዎችን ይዘው ለመቅረብ በዝግጅት ላይ የነበሩ ሲሆን አሁን በአገሪቷ ያለችበትን ሁኔታ በማጤን ዝግጅቱን ላልተወሰነ ግዜ ያስተላልፈ ሲሆን፤ የድጋፍ ድርጅቱ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ዝግጅቱን አጠናቆ ጥሪ የሚያደርግ መሆኑን ለቦስተን እና አካባቢው ሕብረተሰብ ከታላቅ ከይቅርታ ጋር እንጠይቃለን በማለት በዝርዝር አስረደትዋል።

በሌላ በኩል የዝግጅት ክፍላችን በደረሰው መረጃ በቦስተን ከተማ በተመሳሳይ ቀን እና ሰዓት በትግራይ ኮምዩኒቲ የተዘጋጀ ሌላ የኢትዮጵያ አዲስ አመት በዓል እንደሚካሄድ በደረሰው ጥቆማ መሰረት “ማህበረ ምትሕግጋዝ ተጋሩ ቦስተን” “የትግራይ ኮሚዩኒቲ በቦስተን” የሚባል ድርጅት “አመታዊ አሸንዳ እና የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት በዓል” ዝግጅት ጥሪ ማድርጉን እና በዓሉም በተመሳሳይ ሰዓት እና ቀን መሆኑን አረጋግጠናል። የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በየዓመቱ በቦስተን ከተማ እንደሚዘጋጅ እየታወቀ ለምን የትግራይ ኮሚዩኒቲ በተለየ መልኩ ራሳቸውን ከሌላው ኢትዮጵያዊ አግልለው ማክበር አስፈለገ ለሚለውን ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ሞክረን ምላሽ የሚሰጠን አካል ማግኘት አልቻልንም፤ በተለጠፈው ማስታወቂያም ላይ ስልክም ሆነ አድራሻ የሌለው በመሆኑ ሙከራችን አልተሳካም። በሌላ በኩል አንዳንድ ያነጋገርናቸው የቦስተን እና አካባቢው ነዋሪዎች እነሱ ኢትዮጵያዊያን አይደሉምን? ለምን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው መገንጠል አስፈለጋቸው? ወይስ ሌላ አላማ አላቸው? የሚል ጥያቄ ያስነሳ ከመሆኑም በላይ በቦስተን ያሉ ኢትዮጵያውያኖችን እጅጉን አስቆጥቷል። የዝግጅት ክፍላችንም በተለይ በስደት ግን በነጻነት በምንኖርበት በምድረ አሜሪካ እንዲህ አይነት ክፍፍል በመፍጠር ሕበረተሰቡን ለመከፋፈል ጥረት የሚያደርጉት የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎችና ወኪሎች መሆናቸው የታወቀ ሲሆን ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰበ፤ ሌሎች የትግራይ ተወላጆችም ይህንን አይነት የመከፋፈል ድርጊት በማውገዝ እና ዝግጅቱን ቦይ ኮት በማድርግ ከሌላው ወገናቸው ጋር በመተባበር ዝግጅቱን በአስችኳይ እንዲሰርዙ የአቡጊዳ ዝግጅት ክፍል ይህንን ጥሪ እና ማስጠንቀቂያ ጭምር ያስተላልፋል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

 1. ራስ አሉላ
  | #1

  ከዚህ በፊት ሲከበር ምንም ያላላቹህ አሁን ክፍፍል ለመፍጠር አይነተኛ ምክንያት ሆናቹህ::

 2. Anonymous
  | #2

  ዘመኖች አለፉ ታሪክም ተሰራ
  መስሎን እኮ ነበር የናድን ተራራ
  ሰው በጭስ አፈኖ በሳተ ማቃጠል
  አሰቕቆን ነበር ያለፈው ዘመን
  መተንፈስ ሲያቕተው ነፍሱ ሲጨነቅ
  ማምለጫ ስያጣ አየር ሲፈልግ
  በጥይት ገደሉት ያን ሓገር ወዳድ
  አንገቱን ደፋ አርጎ ትምህርት በትማረ
  መብት ይጤበቅ በሎ በተከራከረ
  ወገን ሳይለያይ አንድ እንሁን ባለ
  ብረሃን ነበረ የወደፊት ተስፋ
  አለፈች ህይወቱ እንዲሁ እንደለፋ
  መቸ ነው በ ኢቲዮጵያ መብት የሚጠበቀው
  በሙሉ ነጸነት በደስታ የምንኖረው????

  የተመረጡ እለት የግቡትን ቃል
  አልክድም ብለዋል አላወላወል
  መልሱን ያዘጋጁ ጠክላይ ሚንስትር
  ወገን የገደለው የርሶ ወታደር
  አንተ ሰው ተጠንቀቅ ጭካኔን አታብዛ
  የብቅል እንጀራ የበላል ቀዝቃዛ

 3. ጀንጀበር
  | #3

  ዘመኖች አለፉ ታሪክም ተሰራ
  መስሎን እኮ ነበር የናድን ተራራ
  ሰው በጭስ አፈኖ በሳተ ማቃጠል
  አሰቕቆን ነበር ያለፈው ዘመን
  መተንፈስ ሲያቕተው ነፍሱ ሲጨነቅ
  ማምለጫ ስያጣ አየር ሲፈልግ
  በጥይት ገደሉት ያን ሓገር ወዳድ
  አንገቱን ደፋ አርጎ ትምህርት በትማረ
  መብት ይጤበቅ በሎ በተከራከረ
  ወገን ሳይለያይ አንድ እንሁን ባለ
  ብረሃን ነበረ የወደፊት ተስፋ
  አለፈች ህይወቱ እንዲሁ እንደለፋ
  መቸ ነው በ ኢቲዮጵያ መብት የሚጠበቀው
  በሙሉ ነጸነት በደስታ የምንኖረው????

  የተመረጡ እለት የግቡትን ቃል
  አልክድም ብለዋል አላወላወል
  መልሱን ያዘጋጁ ጠክላይ ሚንስትር
  ወገን የገደለው የርሶ ወታደር
  አንተ ሰው ተጠንቀቅ ጭካኔን አታብዛ
  የብቅል እንጀራ የበላል ቀዝቃዛ

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።