የኢሕአዴግና የተቃዋሚዎች ድርድር አንድነት ባነሳዉ የስብሰባ አካሄድ ጥያቄ ለነገ ተላለፈ!

August 31st, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

አቡጊዳ – ነሐሴ 25 ቀን 2001

የምዕራባዉያን አገሮች ባደረጉት ከፍተኛ ግፊት ምክንያት የፊታችን 2002 የሚደረገዉን ምርጫ በተመለከተ ኢሕአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር ለመወያየት የጠራዉ የዛሬ ነሐሴ 25 ቀን 2001 ስብሰብ፣ የስብሰባዉን አካሄድ በተመለከተ የአንድነት ፓርቲ ባቀረበዉ ጥያቄ እንደተቋረጠና ለነገ ነሐሴ 26 ቀን 2001 እንደተላለፈ ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያለመክታል።

በስብስበባዉ፣ የኢሕአዴግን አራት ድርጅቶች ወክለዉ አቶ በረከት ስሞን፣ አቶ ሙክታር፣ አቶ አስመላሽ እና አቶ ኅያለማሪያም የተገኙ ሲሆን ከተቃዋሚዎች ወገን ደግሞ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ደርጅት(መኢአድ)፣ የአንድነት ለዲሞክራሲን ለፍትህ ፓርቲ እንዲሁም በመድረክ ዉስጥ የሚገኙ ድርጅቶች በሙሉ ተገኝተዋል።

ሶስተኛ አማራጭ ይዞ የሚንቀሳቀሰው በአቶ ልደቱ አያሌዉ የሚመራዉ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ እንዲሁም በአቶ አይለ ጫሚሶ የሚመራዉና እራሱን ቅንጅት ብሎ የሚጠራዉ ተቃዋሚ ነኝ ባይ አካልም መገኘቱን ዘጋቢዎቻችን ከአዲስ አበባ ገልጸዉልናል።

የአንድነት ፓርቲ ያስነሳዉ የአካሄድ ጥያቄ ፣ ፓርቲው መሪው የታሰረችበት እንደመሆኑ፣ ከሌሎች ድርጅቶች የተለየ ጥያቄ እንዳለዉ በማሳሰብና ኢሕአዴግ ከድርጅቶች ጋር የተለዩ ጥያቄዎቻቸዉ እልባት እንዲያገኙ፣ በግልም መወያየት እንዳለበት በመጠየቅ ነበር።

የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በፖለቲካ እምነቷ ምክንያት ኢሰብአዊና ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንድትታሰር መደረጉ፣ በተለያዩ ጊዚያቶችም ፓርቲዉ የሚያደርጋቸዉን እንቅስቃሴዎች ለማዳከም፣ ገዢዉ ፓርቲ በሚቆጣጠራቸዉ የክልልና የወረዳ ካድሬዎቹ አማካኝነት ከፍተኛ እንግልትና ወከባ በአንድነት አባላት ላይ እየፈጸመ እንደሆነም ይታወሳል።

  1. ትንገርቱ
    | #1

    መሰርታዊ የሆኑ የፖልቲካ ዪትየኩ እስረኖተ የፈቱ የ ፕረሰእ ነሳነተእ የፈከደ

  2. Anonymous
    | #2

    No dialoge with TPLF untill Birtukan is free.

  3. Anonymous
    | #3

    No Dialoge with TPLF at all man! What are you thinking? We should see them in the court and that is when the dialoge is needed.

  4. ግሩም ተሾመ
    | #4

    እንደአንድነት ቆራጥ መሆንን እና በእውነት ስለ እውነት ቆሞ መታገልን ኢትዮዽያን እና ኢትዮዽያዊነትን ለሚወድ በሙሉ ፈጣሪ ይከተለው!
    * UDJ * እስከመጨረሻው ለመታገል ፈጣሪ (አላህ)ብርታቱን እንዲሰጣቸው በዚህ በተቀደሰ የረመዳን ወር ፀሎት(ዱዓ) እየደረግን ሰለሆነ በርቱ ::
    ሁልግዜም ምንግዜም እውነት, የህግ የበላይነት አሸናፊ ነው!
    መልካሙን ያሰማን : ቸር ያሰንብተን ::

  5. ሙስ
    | #5

    በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው…ቅድሚያ የሚገባውን ቅድሚያ እንስጠው

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።