የ2010 ምርጫና ቻቻታው! – ኩችዬ

October 29th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ከ2010 ምርጫ ጋር በተያያዘ ፊት-ለፊትና በሠያፍ የሚወረወሩት ትችቶች ብዛታቸውም ግለታቸውም እየጨመረ መሄዱ በመሀላችን የሰፈነውን የመረበሺና የጥርጣሬ ስሜት ያመለክታል። ስጋቱ ማንንም ከማን የለየ አይደለምና ትንሺ ልተችበት ፈለግሁ።

በኢሕአዴግ ልጀምር…

“ነገሮች በቁጥጥሬ ሥር ናቸው!” የሚል ገጽታ ማስተጋባት የሚፈልገው ኢሕአዴግ ውስጣዊ ጭንቀት እንዳለበት የፖለቲካን አቡጊዳን ለዘለቀ ሁሉ ስውር አይደለም። በ2005 ምርጫ ያደረሰው ጥፋት፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ለማዳከም የሚያካሂደው ቅጥ ያጣ ዘመቻ፤ ሕዝብ የማስተባበር ችሎታ ያላቸውን መሪዎች ማሠሩና ማሳደዱ፤ ነጻውን ፕሬስ ማዳከሙ፤ ፍትሀዊ የምርጫ ሜዳ የለም ብለው ተቃዋሚዎች ባይካፈሉ የሚደርስበት ኪሣራ፤ ብቻውን ሮጦ አሸነፍኩ ቢል የውጭ መንግሥታት የገንዘብም የዲፕሎማሲም ድጋፍ ለመስጠት የመቆጠባቸው ጣጣ፤ የተዛባ ምርጫን ተከትሎ ሊመጣ የሚችል ቀውስ……እነዚህ ሁሉ ኢሕአዴግን ማስጨነቃቸው እርግጥ ነው።

የጠቀስኳቸው ዝርዝሮች በቂ አይደሉም የምትሉ ከሆነ ደግሞ ጥቂት ላክልበት እችላለሁ – በአሜሪካው ፀረ-ሺብር ዘመቻ ውስጥ ኢሕአዴግ የነበረው ተፈላጊነት መመንመኑ፤ ባፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ “ንብረትና ዕዳ” ሚዛን መዝገብ ላይ ኢሕአዴግ በዕዳው ዘርፍ መፈረጁ፤ ሀገሪቱን እያጥለቀለቀ ያለው የኤኮኖሚና የረሀብ ግሽበት፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በዓለም መሪዎች መድረክ ላይ ቀዝቃዛ ትከሻ እያገኙ መሄዳቸው….እነዚህ ሁሉ ኢሕአዴግን እንቅልፍ መንሳታቸው ከቶውንም አያጠራጥር። ቁንጮ ላይ ያሉት ባለሥልጣኖች ደፍኖባቸው ቢሆን እንኳ አንዳንድ አስሊ ፖለቲከኞቻቸው ይህን አይስቱትም።

ወገኖቼ! ከላይ የተዘረዘሩት ጭንቀቶች ናቸው ኢሕአዴግን ከተቃዋሚዎች ጋር እንዲደራደር ያስገደዱት። ተቃዋሚዎችም ወደ ድርድሩ ያመሩት የመንግሥቱን አጣብቂኞች ከግምት አስገብተው፤ የፖለቲካ ኮንሴሺኖች እንደሚኖሩ አምነው፤ አጋጣሚው የነርሱን ራዕይ ልዑዋላዊነትና የኢሕአዴግን ፕሮግራም ክስረት ለማሳዬት ያመቻል ብለው ነው። በየትኛውም የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ሚዛን ላይ ብናስቀምጠው ተቃዋሚዎቹ ማለፊያ ስሌት አድርገዋል።

ስለ ስሌት ካነሳን ዘንድ የኢሕአዴግ አመራር ፍጹም ወጥ የሆነ አመለካከት አለው ብሎ መደምደም ስህተት እንደሆነ ሳላመላክት አላፍም። መንግሥት ከህዝብ ጋር እየተራራቀ መሄዱና ባጠቃላይ አገሪቱ ያለችበት አሳዛኝ ሁኔታ የሚያሳስባቸውና ለውጥ ማየት የሚሹ ግለሰቦች/ቡድኖች መኖራቸው ሊያከራክር አይገባም። ጥያቄው ቁጥራቸውና የኃይል ሚዛናቸው ተፈላጊውን ለውጥ ማምጣት ከሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል አልደረሰም ከሚለው ላይ ብቻ ነው። ኢሕአዴግ በጥቅል ሲታይ ጫካውን ከዛፉ ለይቶ ማየት የተሳነው፤ የፍልስፍና ችኮነትና የ “ስኬታማነት” እብሪት ጠላቶቹ የሆኑት መንግሥት ይመስለኛል። እነዚህ ሁለቱ ደግሞ የብዙ መንግሥታት መጥፊያ (ወተርሉ) ለመሆናቸው የኛም ያለም ታሪክም ይመሰክራሉና ኢሕአዴግን ከንቅልፉ የሚያነቃው “ደብል-ኤስፕሬሶ” ያስፈልገዋል እላለሁ።

ወደ ተቃዋሚው ልሸጋገር?

ተቃዋሚው ወገን በሁለት ጎራ ሊከፈል የሚችል ይመስለኛል። ጎራ-አንድ “ኢሕአዴግ ከመሣሪያ ትግል ውጭ አይሞከርም፤ የሠላማዊ ትግሉ ምዕራፍ አክትሟል፤ ገዥው መንግሥት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያካሂዳል ማለት ዘበት ነው” የሚለው ነው። የሳይበር ደጋፊዎቹ ቻቻታ አስተማማኝ መለኪያ ይሆናል ብንል ይህ ጎራ “ሠላማዊ ትግል” ብሎ አገር ውስጥ ለሚንቀሳቀሰው ወገን ብዙም አድናቆት ያለው አይመስልም። በጎራ-አንድ ደግፊዎች እይታ ያገር ውስጦቹ ፓርቲዎች ወይ ባንዳዎች ናቸው ወይንም ደግሞ ባንዳ ለመሆን የተሰለፉ ናቸው። እንዴ! ይሄ ፍረጃ የሚባለው ነገር ጊዜው ያለፈበት ርካሺ የግራ ፖለቲካ ቅሪት መስሎኝ? ያሁኑን ዘመን ፖለቲካ እኮ በነጭና በጥቁር ብቻ ፈርጀው የሚያዩት አይደለም። “እኔ ልክ አንተ ስህተት” የሚባልበትም አይደለም። እመሀል ላይ ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበት መስክ መፍጠር ነው አሸናፊ ፖለቲካ የሚባለው። ስለዚህ ተቃዋሚው ወገን ዓይን ላይን መተያየትን ሊለምድ ይገባል፤ ሊከባበር ያስፈልጋል፤ አንዱ የሌላውን ስብራት ለማገም በጎ ፍቃድ ማሳየት አለበት። እዚህ ላይ የመሪዎቹ ምሳሌ መሆን እስከታች የሚዘልቅ መልዕክት ያስተላልፋልና የመጀመሪያውን ርምጃ ሲወስዱ ማዬት እንፈልጋለን። “ሁሉም ዜሮ ዜሮ” ዓይነት ፖለቲካማ ይብቃን።

ጎራ-ሁለት ደግሞ “ሠላማዊ እንጅ ትጥቅ ትግል ለማካሄድ አመች አገራዊና ዓለም-አቀፋዊ ሁኔታ የለም” ባይ ነው። በተጨማሪም ኢሕአዴግን መግጠም በሠለጠነበትና በተካነበት የመሣሪያ ትግል ሳይሆን ፍጥጥ ብሎ የሚታየውን ደካማ ጎኑን ዕለት ተለት በማጋለጥ፤ ደንጊያ እንደምትሰብረዋ የዝናብ ጠብታ ያልታከተ የፖለቲካ ሥራ በመሥራት ነው ይላል። በሁለቱ ተቃራኒ አቋሞች ላይ ብዙ ስለተጻፈ በዝርዝር አላሰለቻችሁም። ስለ ግል አመለካከቴ “ሠላማዊ ወይስ ጥጥቅ – እንካስላንቲያዎቹ” በሚል ርዕስ የጻፍኩትን ማንበብ ትችላላችሁ።

የጎራ-ሁለት ደካማ ጎን አምስት ዓመት እንኳ ዕድሜ ያላስቆጠረ ብላቴና መሆኑ ነው። ስለሆነም የልምድ ማነስ ቢታይበት ልንበረግግ አይገባም። የዚህ ዓይነቱ ትግል አራማጆች ፈተና ብዙና ውስብስብ ነው። የሚመሩባቸውን ሰነዶች የማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን ግልጽ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ደጋፊያቸው በሰቀቀን ኑሮ ውስጥ የሚገኝ ነውና ዛሬውኑ ውጤት ውለዱ ይላቸዋል። ሥራቸው ፊትለፊት ነውና ለነቀፋ፤ ለሴራና ለወከባ የተጋለጡ ናቸው። የሚጋፉት ካዝናውንም ወታደሩንም ሚዲያውንም ፍርድ ቤቱንም የግሉ ካደረገ መንግሥት ጋር ነው። በየድርጅቶቻቸው ውስጥ ሊመሠርቱ የሚሞክሩት የዴሞክራሲ ባሕል ለብዙዎች ባይተዋር ስለሆነ የግጭትና አንዳንዴም የመሰንጥቅ ጣጣ ያመጣባቸዋል። ከሥራው ጠባይ ጋር አብሮ የሚጓዝ መሰናክል ስለሆነ እንዴት እንደሚዘሉት ብቻ ነው ማሰብ የሚችሉት። ሊያስወግዱት ግን አይሆንላቸውም። እንዲህ ዓይነቱን የኃላፊነት ፈተና ለመቀበል የቆረጡ ወገኖቻችንን መደገፍ ባንችል እንዴት ልናከብራቸው እንቸገራለን?

የ “አንድነት” እና የ “መድረክ” ጉዳይስ?

“ቻተር” ይሉታል ፈረንጆቹ። የተሻለ ትርጉም የሚነግረኝ እስኪመጣ ድረስ “ቻቻታ” ብየዋለሁ። የሳይበሩ ሕብረተሰብ በአንድ ጉዳይ ላይ የሚያደርገው ቻቻታ ከተጧጧፈ ያ ጉዳይ አሳስቦታል ማለት ነው። ያሳሳቢነቱ ደርጃ የሚለካው ደግሞ የተወሰኑ ቃላቶች ድግግሞሺ ሲበዛ ነው። የሀበሻውን ድረ-ገጽ ላንዳፍታ ብትቃኙት “አንድነት” “መድረክ” እና “ምርጫ” የሚሏቸው ቃላት ድግግሞሺ ጣራ ነክቷል። ለምን? ማለት ጥሩ ነው። እስቲ “ምርጫና አንድነትን” እንዲሁም “አንድነትና መድረክን” ላንዳፍታ እንመርምራቸው።

ምርጫና አንድነት። አንድነት ከመነሻው ሠላማዊ ትግል አካሂዳለሁ ብሎ ያወጀ ድርጅት ነውና ስለ2010 ምርጫ ቢያወራ፤ መግለጫ ቢሰጥ፤ ከመንግሥትና ከመንግሥታት ጋር ቢደራደር፤ ስትራቴጅያዊና ታክቲካዊ ጥቅም ባየበት ቦታ ከሌሎች ጋር ቢሻረክ ፍጹም መብቱ ነው። የሚጠበቅበትም ነው። ከነዚህ ተግባሮች ሊታቀብ የሚችለው ሥርዓትን በተከተለ መልክ በአባሎቹ በሚደረግ ውሳኔ ብቻ ነው። የሠለጠነው አገር አሠራርም የዴሞክራሲ ወግም ከዚህ የተለየ አይደለም። በሌሎች ፓርቲዎች ውስጥና ዙሪያ የተሰባሰቡ ግለሰቦች በአንድነት የፖለቲካ ምርጫዎችና ውሳኔዎች ላይ ተጽእኖ የማድረግ ሕጋዊም ሞራላዊም ሥልጣን እንደሌላቸው ቢረዱ ጥሩ ይመስለኛል። እነዚህ ፓርቲዎችና ደጋፊዎቻቸው የራሳቸውን ቤት የማጠናከርና የማሳመር ብርቱ ኃላፊነት እያለባቸው ስለሌላው ቤት ለምን እንደሚጨነቁ ግራ የምጋባበት ጉዳይ ነው።

አንድነትና መድረክ። ተሳስቼ ከሆነ እታረማለሁ እንጅ በመድረክ መቋቋም ፀጉራቸውን ሲነጩ የማየው በሰላማዊው ትግል ዙሪያ ያሉ ፖለቲከኞች አይደሉም። “አንድነት ፓርቲ የብሔር ቅኝት ካላቸው ድርጅቶች ጋር ትብብር መፍጠሩ የስህተትም ስህተት ነው” እያሉ የሚደሰኩሩትም ከጥቂቶቹ በስተቀር የፓርቲው አባል ያልሆኑ፤ በደጋፊነት ደረጃ ተመዝግበው እንኳ የገንዘብም የሀሳብም አስተዋጽኦ የማያደርጉ ናቸው። ራስህን ዋቢ አደረግህ አትበሉኝ እንጅ በዚህ ርዕስ ላይም የጻፍኩትን http://kuchiye.blogspot.com/2009_07_01_archive.html ማየት ትችላላችሁ። ዘርዘር አድርጌ እንዳልተች በራሴ ላይ የጣልኩት የገጽ ገደብ ይዞኛልና በቅርቡ እመለስበታልሁ።

አንድ ነገር አስተውላችኋል? ልብ ብሎ ለተመለከታቸው ጥያቄዎች ብዙውን ጊዜ መልሳቸውንም አዝለው ነው የሚጓዙት። እስኪ በተረፉኝ መስመሮቼ ጥቂት ጥያቄዎች አንስቼ ልሰናበታችሁ።

1. በቅርብ ዘመን ታሪካችን ድርጅቶችና ፓርቲዎች ሕብረት፤ ጥምረት፤ መድረክ መፍጠራቸው ትዝ ይለናል። የውጤታማነታቸውን ነገር ለጊዜው ወደጎን ብንተወው በመተባበራቸው ምክንያት ደም ፈሶ አይታችኋል?
2. መተባበር ቀርቶ መነጋገርን አሻፈረን ያሉ ድርጅቶች ጦር በመማዘዛቸው ትውልድ እንዳለቀ ረስተነው ይሆን?
3. የመድረክ መቋቋም የተራራቁ አቋሞችን ለማቀራረብ፤ የጥርጣሬ ቀዳዳዎችን ለመዝጋት፤ የርስበርስ መተማመንን ለማዳበር ከመርዳት ሌላ ምን የሚያስከትለው ጠንቅ አለ?

Kuchiye@gmail.com.

የ2010 ምርጫና ቻቻታው!
ኩችዬ – ኦክቶበር 29 2009 ዓ/ም
www.kuchiye.blogspot.com

  1. ጀርቦሰ
    | #1

    ኩቹዬ የምትጽፋቸው ቁምነገር አዘልና ትምህርታዊ መጻጽፎች ያስደስቱኛል!
    ለምሳሌ ካደነቅኩልህ መጣጥፎች ጥቂቶቹን ብጠቅስ:- “አውራ የሌለው ምንም የለውና” “ግልገል ጊቤና የላምዋ ታሪከ”
    ሁላችንም በአንክሮ ልንመልክታቸው የሚገባ ምጣጥፎች ናቸው::
    ወደ ዛሬው ጽሁፍህ ስመለስ ደግሞ ወቅታዊና ሁሉም አራሱን አንዲመረምር የሚያስችል አስተዋሽ ጽሁፍ ነው :: “በቻቻታችን”
    አኔ በጫጫታችን አለዋለሁ :ምክንያቱም በወቅቱ ፖለቲካ በየቦታው የምናደርገው ውይይትና ግንኙነት ሁኔታዎቸን ያላገናዘበና ክመቅጽበት ክሚጠፋ ስሜታዊነት ተነስተን ስለሆነ ነው :: ሰልዚህ ለአኔ ጫጫታ የሚለው ቃል ተስማሚ ይመሰለኛል::
    ሆነም ቀረ ማለት የፈለግኩት የምንደግፈውንም ሆነ የምንነቀፈውን ነገር ጭብጥ አወቀን በጥናት ላይ የተመሰረተ ትችት ወይም ድጋፍ አስካልሰጠን ድረስ ሁሉም ክቻቻታ/ጫጫታ አልፎ ለትግላችን ሚዛን የሚደፋ ለወጥ አያመጣም::ስልዚሀ ከጫጫታ በተሻለ መልክ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ግንዛቤ የሚሰጡ ለምሳሌ አንደ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደና አነደ ኩቹዬ አይነት ጽሁፎችን በመጻፍ በማንብበና በመወያይት ትግላችንን መልክ በማስያዝ መልክ ያለው ለውጥ በሃገራችን ማምጣት አንችላለን::
    በወቅቱ ፖለቲካ የአንድነት ፓርቲ በሚወስዳቸው የፖለቲካ አቁዋሞች ወይም ስልቶች ቀድሞ የሚንጫጫውና :ወሳኝ ነኝ ብሎ ቡራ ከረዩ የሚለው :የአንድነት ደጋፊ ያለሆኑና አንደውም የፓርቲው ተቅዋሚዎች ናቸው::
    ልብ በሉ ጎርቤታችሁ መጥቶ ሳትጥይቁት የቤታችሁን አቃ አንዲህ አንዲህ አድርጉት ቢላችሁና ቢያስገድዳችሁ ከዛ ሰው ጦርነት አትገጥሙም?
    ጦር የምትለው ቃል ፈንጠር ብላ ብትገባ በቅርብ አንድ ድሕረ ገጽ ላይ ስለ ኡጋዴን ግንባር መሪና ስለግንባሩ አቁዋም አንብቤ ደነቀኝ:: የግንባሩ መሪ የሱማሌ አድሚራል የነበረና በሰይድ ባሬ ዘመን ኢትዮጵያን የወጋ ነው ::ኡጋዼን የአረብ ግዛት ነው የሚል በሰጠው ቃለ ምልልስ ይነበባል:: ይህ ድግሞ አማራ በቅኝ ግዛት ያዘኝ በማለት አሁንም ከወያኔ ባልተናነስ መልኩ በአማራ ላይ ጥላቻ ማስፋፋት አንደ ትግል ስልት ክሚወስደው ክኦነግ አቁዋም የተለየ አይደለመ:: ታድያ የመድረክን የፖለቲካ ስልት የምትቃወሙ የትጥቅ ትግል ደጋፊዎች ይሄን ግንባር ለኛ ይበጃል ብላችሁ ክሱ ጋር ተቀናጅተን ወያኔን ጥለን የምንመኛትን ዲሞክራሲ የሰፈነባት ያልተክፋፈልች ኢትዮጵያን አንመሰርታለን ከሚል ቅዠት ሳትወጡ የመድረክ ስልት የሚያብሰለስላችሁ ለምን ይሆን?
    አምንደግፈውን አንወቅ! አላልሁ
    አንበርታ!
    ጀርቦስ

  2. አዛርያ
    | #2

    ኩችዬ እግዚአብሔር ይባርክህ/ይባርክሺ!

  3. danial351
    | #3

    እነዚህ ወያኔዎች ለራሳቸው የሚበሉትና ህዝቢ የሚጨፈጭፉ ቅጥሮኞጭ
    እኔ ዳኒኤል ገብረሚካኤል ሓድጉ ከሰግላት
    እነዚህ ኣምባገነኖች የኢትዮጵያ ሃገራችን መሪዎች የሚባሉ በእውነትና በትክክል ለሃገራችን ኢትዮጵያ የሚመሩና የሚያስታዳድሩ መሪዎች ኣይደሉም፣፣

    ታድያ እንዚህ መሪዎች ለራሳቸው ብቻ ለሆዳቸው የሚበሉትና ህዝባችን ኢትዮጵያ በረሃብ እየተሳቃየ እዋለ እያደረ ለራሳቸው ብቻ የሚስተዳደሩ መሪዎች ብቻ በመሆናቸው ለህዝባችን ኢትዮጵያ ከረሃብና ከድርቅ የሚረዱት መሪዎች ኣይደሉም፣፣

    እነዚህ ኢሃኣዴግ መሪዎች ለህዝባችንና ለሃገራችን የቆሙ ሳይሆኑ ከነርሳቸው በጥቅም የሚጋዙት ሃገራችን ወደ ሱዳን ይሁን ሌላ ኣገር ቆርሶ ለጥቅሙ ሲል ታይቶ የማይታወቅ ገበን በሃገር ክህደት ወያኔዎች ገበን እየፈፀሙ ይገኛሉ፣፣ መሬታችን ለሱዳን በመስጥት ወጎኖቻችን እዛ የሚኖሩት የነበሩት ህዝባችን ብሃይል የኛ መሬት ኣይደለም በማለት ከሱ ቦታ ኣልቅቖ ከችግር ሜዳ ላይ ይገኛሉ፣፣

    እኔ መልእክት የሚያስታላልፎው ለጭቁኑ ህዝባችን ኢትዮጵያ ወያኔ ለ2002 ዓ/ም መረፃ ህዝባችን እንዳትታለል ኣደራ ወደ ስልጣን እንደገና እንዳይወጣ ድምፅህን ከጨህ ጥሩ ነው ሰላማዊ ምርጫ ወያኔ ያካይዳል ብለህ እንዳትምን፣፣

    ስለ ሆነ እጅህን ኣጣምረህ ቁጭ ብለህ ማየት መፍትሄ ኣይደለም ጭቁኑ ህዝባችን ኢትዮጵያ ወያኔ በሰላማዊ የሚያምን ስርዓት ኣይደለም በሃይል ወደ ላይ የተሰቀለ ስርዓት በሃይል ማውረድ ስለ ሆነ ሁላችንም ብሄር ብሄርሰቦች ህዝባችን ኢትዮጵያ ለወያኔ ለመገርሰስ ኣብረን ሊንነሳ ነው የሚለው በሃይል የሚያምነው ስርዓት በሃይል መውረድ ስለ ሆነ ኣማራጭ እዚ ነው፣፣

    በህዝብ የተመረጠ መንግስት መትከልና እኛ የምንፈልገው ኣንዲትና ዴሞክራስያዊት ኢትዮጵያ ለመገንባትና ለመመስረት ስለ ሆነ ጭቑኑ ህዝባችን ኢትዮጵያ ኣብረሃ ተባብረህ ተነሳ፣፣

    እዛ ከትግራይ ክልል የሆነች ከተማ ፋፂ ኣከባቢ ዛላንበሳ የሚትገኝ ታስሮ የሚገኙ ጋዶኜቼ እግዚኣቤሄር ይማር፣፣ ኣክሊል መዝገቦ ——— ከሰግላት
    ሃይለ ለገሰ ———– ከሰግላት
    ኣብርሃም ወለኣነንያ ——— ከሰግላት
    ሄኖክ ጋይም ———– ከዛላንበሳ እነዚህ ጋዶኞቼ በሂወት ካላቹ ሰላም በሉልኝ፣፣ እኔ እንካን ለወያኔ ለመገርሰስ ከትግል ሜዳ ነው የሚገኘው፣፣ ጋዶኞቼ እኔ የት ቦታ እንዳለሁት ኣያውቁም እሱርቤት ውስጥ ካሉ ጋዶኞቼ ነው እኔ ወደ በርሃ ወደ ትግል ሚዳ የሄዱኩትና፣፣ እኔ በርሃ ላይ የወጣሁት እንደምሃነይ ከሰሙ ወዴ እኔ እንደሚመጡት ርግጠኛ ነኝ ግን ማን ይንገራቸው፣፣ ግን ከእሱር ይወጣሉ ብየ እንካን ኣላምንም፣፣

    እነዚህ ጋዶኞቼ ቦዜኔዎች ተብሎችዋል ነው የታሰሩ፣ ግን ቦዜኔዎች ኣይደሉም የ10ኛና የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች በጣም ትህትናና የዋህነት ያላቸው ሰዎች ናቸው፣፣ ያደረጉት ገበን የለም፣፣ እዛ ውስጥ ከተማ ፋፂ የሚረቡሹ ተብሎ ነው በጥርጠራ የታሰሩ፣፣ ግን ከወያኔ መኖር እስከ መቼ ከወያኔ ጨቓኝ ሞኖር ኣይቻልም ዝምብሎ ህዝቢ እየጨፈጨፈ ህዝቢ በረሃብ እየገደለ ከወያኔ መኖር ማለት ከሴት ጅብ ሰፈር መተኛት ማለት ነው፣፣
    ፃህዋ የሚትገኝ ከባቢ ዛላንበሳ ሓዳስ ሓድጉ፣
    ኣስመራ የሚትገኝ ለምለም ሓድጉ
    ዛላንበሳ የሚትገኝ ለተብርሃንና ገብረሚካኤል ሓድጉ ሰላም በሉልኝ፣ ሰላም ቅሳነት፣ ርግበ፣ ኣፈወርቂ፣ ኣደስ ኣበባ የሚገኝ በየነ ገረፃድቕ (ወዲ ኣበሓበሽ)ሁሉም ጭቁኑ ህዝባችን ኢትዮጵያ ሰላም በሉሉኝ እግዝኣቤሄር ከወያኔ ያድነህ፣ ሰላም ሰላም፣ ዓወት ንውፅዓት!!

    ድል ለጭቁኖች ከት.ህ.ዴ.ን (ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ)

    ለመለስ ዜናዊ ሰላም በሉሉኝ በእጃቹ ኣይደለም በካራ ነው ሰላም የሚትሉት ጋዶኞቼ እንዳትሳሳቱ፣ እጁ እንደ ጅብ ነው ወደ ጉድጋድ ስቦ እንዳይበላቹ እንዳትገቡ ጠንቀቅ ብላቹ ነው በስክሪቲ በካራ ሰላም የምትሉት፣፣ በካራ የሚወደው መለስ ደግማቹ በደምብ ሰላም በሉልኝ፣፣ ራሴ ከገኛሁት ችግር የለም በደምብ ሰላም እንደሚለው ጥርጥር የለም በካራና ብሽጉጥ በተላያየ ሰላም ይላሉህ ለሌቦች ሌባ መለስ፣፣

    ተጋይ ስዊት ወይ ዳኒኤል ገብረሚካኤል ሓድጉ ከሰግላት

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።