ቫንኩቨር፡ ብርቱካን ሚደቅሳ የታሰረችበትን አንደኛ አመት አከበረች – ሰፊ ውይይትም ተደገረ

December 29th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

በቫንኩቨር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን፡ በታህሳስ 20 2001 ዓ.ም. በወያኔ ወታደሮች ያለአግባብ ተይዛ ቃሊቲ እስር ቤት የተወረወረችውን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ መሪ፡ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የታሰረችበትን አንደኛ ዓመት አክብረው ዋሉ። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር፡ ቅዳሜ ታህሳስ 27፡ ከቀኑ አራት ሰዓት እስከ 7 ተኩል ሰዓት በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ ላይ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን፡ ነዋሪነታቸው በሲያትል የሆነውና የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል የካርታ ስራ ባለሙያ፡ አቶ ዘውገ ፈንታ ንግግር አቅርበዋል። አቶ ዘውገ ፈንታ፡ ብርቱካን አንደኛ እውቅናን እያገኘች በመምጣቷ፡ ሁለተኛ አቶ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ህዝብ ንቀት ስላላቸውና ህዝቡን ለማስፈራራት፡ ሲሉ እንደታሰረች ተናግረዋል። የብርቱካን እስራትም የኢትዮጵያን ህዝብ እስራት እንደሚያሳይ ጨምረው ተናግረዋል። አቶ ዘውገ አስከትለውም፡ ሰው ለማሸነፍ የግድ ይታሰር ማለት ባይቻልምና ወያኔ ብርቱካንን ያሰራት ሞራሏን ለመስበርና ለመርታት ቢሆንም፡ ብርቱካን ግን ከእያንዳንዱ በእስር ቤት ከምታሳልፈው ሴኮንድ፤ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ፡ ያስር ዓመት ክብር እንደምታገኝ ተናግረዋል።

አቶ ዘውገ በተጨማሪም፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አፋኝ ስርአት፡ ጸረ-ኢትዮጵያ ከመሆኑ የተነሳ፡ የኢትዮያን ድንበር ለሌሎች አገሮች አሳልፎ እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። የመጀመሪያውን ባለቀለም የኢትዮጵያንና የአዲስ አበባን ካርታ የሰሩትና፡ በልጅነታቸው ላገራቸው ባበረከቱት ከካርታ ጋር የተገናኘ ስራ በጃንሆይ ዘንድ ቀርበው የተሸለሙት፤ በኋላም የትምህርት እድል አግኝተው ወደአሜሪካን የመጡት አቶ ዘውገ ፈንታ፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ፤ በወያኔ ለሱዳን አሳልፎ የተሰጠውን በሰሜን ምእራብ ከተሰነይ እስከ በጎንደር ሁመራ አልፎ እስከ ኦሜድላ የሚደርስ መሬት ተዘዋውረው እንዳጠኑና ካርታውንም እንደሰሩ፡ የወያኔው መሪ አቶ መለስ ባንድ በኩል ኢትዮጵያ ምንም መሬት ለሱዳን አልሰጠችም ብለው በሌላ ቀን ደግሞ ከሱዳን የወሰድነውን መሬት መልሰን ሰጥተናል ማለታቸው ርስ በርሱ የሚቃረን መሆኑን ጠቁመዋል። አቶ ዘውገ በተጨማሪም፡ ኢትዮጵያ አሁን የምትመራበት ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝም ለኢትዮጵያ የማይበጅና ከፋፋይ መሆኑን ጠቁመው፡ እሳቸው ለኢትዮጵያ ይበጃል ስለሚሉት የመሬት አቀማመጥንና ታሪክን መሰረት ያደረገ የአስደዳደር አወቃቀር ተናገርዋል።

ከአቶ ዘውገ ንግግር በተጨማሪም፡ በብርቱካንና በድንበር ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጐ፡ የእለቱን ዋና ጉዳይ የብርቱካንን መታሰር መሰረት ያደረገ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅተም ተደርጓል። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በሰፊው በመንቀሳቀስ የሚታወቁት አቶ ከበደ ሀይለማሪያም፡ የብርቱካንና የልጇ ምስል ያለባቸውን የቡናና ሻይ ኩባያዎች አቅርበው፡ ሁሉም ተቸብችበው ገቢው ለብርቱካን ሚደቅሳ ቤተሰቦች እንዲላክ ሰጥተዋል። በእለቱ አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን የኢትዮጵያን ህዝብ መንገፍገፍ የሚጠቁሙ አልባሳትን ለብሰው ተስተውለዋል። ከኢትዮጵያ ተሰደው ነዋሪነታቸው በካናዳ የሆነው ወ/ት አለምጸሀይ ዳምጤ “በቃ” የሚውን ካኒቴራ ለብሰው የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ምን ያህል እንደተንገፈገፈ ተናግረዋል።

ነጻ ተመልካችና ዘጋቢ፡ ከቫንኩቨር፡ ታህሳስ 27፡ 2009 ዓ.ም.

 1. Abiy Ethiopiawe
  | #1

  ))))))ነፃ አስተያየት ለመረረ ትግል፤ከአገር ቤት ባሕር-ማዶ።((((((
  ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሐገሩ በጎ እና ቀና ከማሰብ ያቆመ የለም ፤ከአጋዚያን ሠይጣናዊ ድርጊት በስተቀር።በሕዝብ መሃል እርቅ ይደረግ ሲባል፤”እኛ ባለ ጊዜ ነን”ብለው እምቢ ያሉ ባንዳ-አጋዚያን ናቸው። በሃቅ የሕዝብ ምርጫ ይደረግ ሲባሉ፤”በጡንቻችን እኛ አሸንፈናል”ብለው ግድያ የሚፈጽሙ ባንዳ-ወያኔዎች መሆናቸው ያደባባይ ሚስጥር ነው።
  ታዲያ ምን ይደረግ ቢባል???ኃላፊነቱን የሚስህከሙት እንደዚህ በተናጠል ሳይሆን፤ቀድሞ የተደራጁት ፓርቲም ሆነ
  ቡድን የሕዝብን አስተያየት ወዲያው አጥንቶ በየድጋፍ ሰልፉ ወደተግባር መለወጥ ነው።አለበለዚያ ፓርቲነታቸው ወይም የቡድን አፈጣጠራቸው ምን ይፈይዳል???ትግሉ ለዓመታት ያዘግማል፤እኛ የምንፈልገው በጣም የሚያታግለን እንጂ በየአደባባዩ እየጠሩ ይችን ያዛት ወይም ጮክ እንበል እያለ የሚጎተጉተን ግለሰብ አንሻም።
  በጣም ብልህ(Smart)አስተባባሪዎች ናቸው በፍጥነት የሚያስፈልጉን።በግድ የፓርቲ ወይም የቡድን አባል መሆን አያስፈልግም።እኔ ደጋግሜ ለተቃውሞ አደባባዮችና የስብሰባ ቦታዎች ተገኝቻለሁ።አንዳንዱ የብርዱን እሳት ችሎ ንፍጡን መቆጣጠር እስኪያቅጠው፤ላንቃው እስኪሰነጠቅ ጩኸቱን ሲያሰማ፤ሌላው አብሮት ሆኖ በዝምታ ቆሞ አይን አይኑን ሲያዩት፤የአስተባባሪዎች የቀበሌ ሰልፍ አስተሳሰብ ሆኖ እንጂ የመጣው ተካፋይ ቸልተኝነት አይደለም።
  ውጤቱም ምን ይሆናል እንደወያኔ-ባንዳ ቁጥሩን በመጨመር መዋሸት ይቀጥላል።በሚቀጥለው ጊዜም ቁጥራቸው እያነሰ ግራ ያጋባል፤የተወሰንን ብቻ ስንሆን።ዕውነቱ ይሄ ነው።መደረግ ያለበት፤
  1/ከተፈቀደላቸው (ጥሪውን ካዘጋጁት)በስተቀር ምንም ዓይነት የፎቶግራፍ ማንሳት መኖር የለበትም።
  2/ማስታወቂያዎች ተሳታፊው ይዘዋቸው ሊመጡ(ሰንደቅ-ዓላማ፡ፎቶግራፍ፡መጻፊያ ማርከር ወይም ፖስተር፡ፊሽካ የመሳሰሉትን)የሚችሉትን አብሮ ማሳወቅ።
  3/ቀጣዩን የትግል ቀን ማዘጋጀትና በእለቱ ማሳወቅ
  4/ የማንንም አድራሻ ያለፍላጎት አለመውሰድ ወይም አለመመዝገብ፤ስንት ሰው እንደተገኘ በፆታ ቢቻል በእይታ የእድሜ ግምት መረጃዎችን ሁሉ ማዝ።
  5/ከሚባሉ ከሚዘመሩና ከሚታዩ በተጨማሪ የሚበተኑ በራሪዎችን ማድረግ
  6/ዋናውና አስፈላጊው በእለቱ ብቻ ለምሳሌ የብርቱካን እስር ቤት ናሙና(Model)በሕዝብ እንዲጎበኝ በማድረግ የፈለገ እንዲረዳ ማቀናጀት።
  7/የወረቀት ላይ ነብር የሆነ ሁሉ በተግባርም እንዲሳተፍ ማመቻቸት።
  የመጨረሻውና በጣም አስፈላጊው ውጭ ለሚኖሩ ሁሉ፤
  ከድጋፍ ሰልፉ በኋላ ባንዳ-አጋዚያንና ባንዳ-ወያኔዎች በቡድን እንደመጡና እኛ ተበታትነን ወደየቤታችን ስንሄድ በሰላዮች በተናጠል እንዳንጠቃ ለእኛ ዋስትና እንዲኖረን በፊዚክስ ራሳችንን መጠበቅ(አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ያዥ) ይገባናልና (ቢያንስ ሁለት ሆነን) በዚህ የሞት ሽረት የመረረ ትግል ልንዘጋጅ ይሁን።
  ወያኔ-ባንዳዎች እና ባንዳ-አጋዚያን አብደው በአገር-ቤት ሕዝብ እየነከሱ መግደል ከጀመሩ አመታት ተቆጥሯልና ባሕር-ማዶ ያለነው ብዙነገር ልንማር ይገባናል።በትንሹ ማንበብና መፃፍ እንኳ የማይችሉ ግለሰቦች በወያኔ-ባንዳዎች ሆቴል ቤቶችና ሱቆች ተቀጥረው የሚሰሩ አላያችሁም?ለመሆኑ ምን ይሰራሉ ከስምንት ሰዓት በኋላ?ተራ በተራ ባንዳዎች እስኪንጠባጠቡ ጊዜው የለንም።በባንዳነት አሁን ያሉት እንደገቡበት መውጫን አጥተው ነው።
  ኢትዮጵያውያን ሆይ! ትግሉ የምር ነውና ኢትዮጵያን እናድን።በዚህ የምርጫ ግርግር እኛን ለስደት ፤አገራችንን ለባርነት ቀን ከሌት ከዲያብሎስ ጋር እየሰሩ ነውና በፀሎትና በትግል ኢትዮጵያን እንጠብቃት እላለሁ።

  የኢትዮጵያ አምላክ ከእኛ ጋር ይሁን፤አሜን።

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።