የብርቱካን ሚደቅሳን መታሰር በመቃወም የሻማ ማብራት በመስቀል አደባባይ እንዳይደረግ ኢሕአዳግ መከልከሉን በተመለከተ የወጣ መግለጫ ! –

December 29th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ
 1. ብሄራዊ እርቅ ከመለስ መጠበቅ ከ እባብ ዕንቁላል ጫጩት መጠበቅ
  | #1

  መለስ ብሔራዊ አጀንዳ እንደሌለው እየታወቀ ከርሱ ቢሔራዊ እርቅ መጠበቅ የሚያስፈልግ አይመስለኝም።ይልቁንስ ተቃዋሚው በመሀሉ ያለውን ልዩነት እያጠበበ ለመሄድ መጣርን ዋና ተግባሩ ማድረግ አለበት።
  ይህ የብርቱካንን ፎቶ የያዜው ቲ-ሸርት በመላ ሀገሪቱ እንዲሠራጭ ማድረግ መቀጠል አለበት።መረሳት የሌለበት ጉዳይ ግን የመለስ ጋሻ ጃግሬዎች ይህንን ለማስቆም የሚጠቀሙባቸውን ቀዳዳዎች ሁሉ መድፈን መቻል ነው።ሕዝቡ ሕገ-መንግሥቱን በተጻረረ መንገድ ተቃዉሞውን እንዳይገልጽ በጥንቃቄ እንቅስቃሴውን ማከናወን ያስፈልጋል። ለውሃ ቀጠነ ባዮቹ ሁሉ መንገዱን ጠመዝማዛ በማድረግ ሰላማዊዉን ትግል ወደ ሕዝቡ ማስገባት ነው።ሚሊዮኖችን የሚያስርበት እስርቤት የለውም መለስ።

 2. Abiy Ethiopiawe
  | #2

  ))))))ነፃ አስተያየት ለመረረ ትግል፤ከአገር ቤት ባሕር-ማዶ።((((((
  ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሐገሩ በጎ እና ቀና ከማሰብ ያቆመ የለም ፤ከአጋዚያን ሠይጣናዊ ድርጊት በስተቀር።በሕዝብ መሃል እርቅ ይደረግ ሲባል፤”እኛ ባለ ጊዜ ነን”ብለው እምቢ ያሉ ባንዳ-አጋዚያን ናቸው። በሃቅ የሕዝብ ምርጫ ይደረግ ሲባሉ፤”በጡንቻችን እኛ አሸንፈናል”ብለው ግድያ የሚፈጽሙ ባንዳ-ወያኔዎች መሆናቸው ያደባባይ ሚስጥር ነው።
  ታዲያ ምን ይደረግ ቢባል???ኃላፊነቱን የሚስህከሙት እንደዚህ በተናጠል ሳይሆን፤ቀድሞ የተደራጁት ፓርቲም ሆነ
  ቡድን የሕዝብን አስተያየት ወዲያው አጥንቶ በየድጋፍ ሰልፉ ወደተግባር መለወጥ ነው።አለበለዚያ ፓርቲነታቸው ወይም የቡድን አፈጣጠራቸው ምን ይፈይዳል???ትግሉ ለዓመታት ያዘግማል፤እኛ የምንፈልገው በጣም የሚያታግለን እንጂ በየአደባባዩ እየጠሩ ይችን ያዛት ወይም ጮክ እንበል እያለ የሚጎተጉተን ግለሰብ አንሻም።
  በጣም ብልህ(Smart)አስተባባሪዎች ናቸው በፍጥነት የሚያስፈልጉን።በግድ የፓርቲ ወይም የቡድን አባል መሆን አያስፈልግም።እኔ ደጋግሜ ለተቃውሞ አደባባዮችና የስብሰባ ቦታዎች ተገኝቻለሁ።አንዳንዱ የብርዱን እሳት ችሎ ንፍጡን መቆጣጠር እስኪያቅጠው፤ላንቃው እስኪሰነጠቅ ጩኸቱን ሲያሰማ፤ሌላው አብሮት ሆኖ በዝምታ ቆሞ አይን አይኑን ሲያዩት፤የአስተባባሪዎች የቀበሌ ሰልፍ አስተሳሰብ ሆኖ እንጂ የመጣው ተካፋይ ቸልተኝነት አይደለም።
  ውጤቱም ምን ይሆናል እንደወያኔ-ባንዳ ቁጥሩን በመጨመር መዋሸት ይቀጥላል።በሚቀጥለው ጊዜም ቁጥራቸው እያነሰ ግራ ያጋባል፤የተወሰንን ብቻ ስንሆን።ዕውነቱ ይሄ ነው።መደረግ ያለበት፤
  1/ከተፈቀደላቸው (ጥሪውን ካዘጋጁት)በስተቀር ምንም ዓይነት የፎቶግራፍ ማንሳት መኖር የለበትም።
  2/ማስታወቂያዎች ተሳታፊው ይዘዋቸው ሊመጡ(ሰንደቅ-ዓላማ፡ፎቶግራፍ፡መጻፊያ ማርከር ወይም ፖስተር፡ፊሽካ የመሳሰሉትን)የሚችሉትን አብሮ ማሳወቅ።
  3/ቀጣዩን የትግል ቀን ማዘጋጀትና በእለቱ ማሳወቅ
  4/ የማንንም አድራሻ ያለፍላጎት አለመውሰድ ወይም አለመመዝገብ፤ስንት ሰው እንደተገኘ በፆታ ቢቻል በእይታ የእድሜ ግምት መረጃዎችን ሁሉ ማዝ።
  5/ከሚባሉ ከሚዘመሩና ከሚታዩ በተጨማሪ የሚበተኑ በራሪዎችን ማድረግ
  6/ዋናውና አስፈላጊው በእለቱ ብቻ ለምሳሌ የብርቱካን እስር ቤት ናሙና(Model)በሕዝብ እንዲጎበኝ በማድረግ የፈለገ እንዲረዳ ማቀናጀት።
  7/የወረቀት ላይ ነብር የሆነ ሁሉ በተግባርም እንዲሳተፍ ማመቻቸት።
  የመጨረሻውና በጣም አስፈላጊው ውጭ ለሚኖሩ ሁሉ፤
  ከድጋፍ ሰልፉ በኋላ ባንዳ-አጋዚያንና ባንዳ-ወያኔዎች በቡድን እንደመጡና እኛ ተበታትነን ወደየቤታችን ስንሄድ በሰላዮች በተናጠል እንዳንጠቃ ለእኛ ዋስትና እንዲኖረን በፊዚክስ ራሳችንን መጠበቅ(አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ያዥ) ይገባናልና (ቢያንስ ሁለት ሆነን) በዚህ የሞት ሽረት የመረረ ትግል ልንዘጋጅ ይሁን።
  ወያኔ-ባንዳዎች እና ባንዳ-አጋዚያን አብደው በአገር-ቤት ሕዝብ እየነከሱ መግደል ከጀመሩ አመታት ተቆጥሯልና ባሕር-ማዶ ያለነው ብዙነገር ልንማር ይገባናል።በትንሹ ማንበብና መፃፍ እንኳ የማይችሉ ግለሰቦች በወያኔ-ባንዳዎች ሆቴል ቤቶችና ሱቆች ተቀጥረው የሚሰሩ አላያችሁም?ለመሆኑ ምን ይሰራሉ ከስምንት ሰዓት በኋላ?ተራ በተራ ባንዳዎች እስኪንጠባጠቡ ጊዜው የለንም።በባንዳነት አሁን ያሉት እንደገቡበት መውጫን አጥተው ነው።
  ኢትዮጵያውያን ሆይ! ትግሉ የምር ነውና ኢትዮጵያን እናድን።በዚህ የምርጫ ግርግር እኛን ለስደት ፤አገራችንን ለባርነት ቀን ከሌት ከዲያብሎስ ጋር እየሰሩ ነውና በፀሎትና በትግል ኢትዮጵያን እንጠብቃት እላለሁ።

  የኢትዮጵያ አምላክ ከእኛ ጋር ይሁን፤አሜን።

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።