የሞት ፍርድ ለማን ፤ የሞት ፍርዱስ ለምን? – ሥርጉተ ሥለሳሌ

December 30th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ
  1. ጉያ
    | #1

    እረ ምን አበሳ ነው ጃል! የወያኔ ወያኔነት ያነሰን ይመስል እኚህ ባልቴት የቃላት ክምር – ቅርጽ የሌለው ክምር – በክምር ላይ ክምር አጠረቃቅመው መለጠፋቸው መጣጥፍ የሚሉት ነገር መሆኑ ይሆን? ነገር ማካረሩ መሆኑ ነው ግማሹ አረፍተ ነገር ተሰምሮበት ሌላው ተሰምሮበትም ጎልቶ እንዲታይ መደረጉ አይማርክ አያስተምር :: ጉዱን- መጨረሻውን ልየው ተብሎ እንደኔ ተታሎ ካላነበበው በስተቀር ጊዜው – ለማንበብ የሚባክነው ጊዜ ይቆጫል:: ያናድዳል:: እንዲያው ሲታሰብ ግን “ሰው ያለውን ከወረወረ ፈሪ አይባልም” እንደሚባለው እንዲወሰድላቸው አልያም በወያኔ ላይ “ቆራጥ አቋም ያላቸው ባልቴት” ለመባል ተፈልጎ ከሆነ ይሁን:: እሱም ቢሆን በየመሃሉ “ዘራፍ”ን ቢጨምሩበት ባማረላቸው ነበር:: ተቃዋሚውን ግን የሚያስንቅ አቀራረብ ነው:: ወያኔ እንደነዚህ አይነቶቹን ባዶ ቅሎች – በባዶ ዘራፌዎች ንቆ እንደግፈዋለን የሚሉትንም ድርጅቶች ደጋፊዎቻችሁን አየንላችሁ እያለ በማፌዝ ላይ ነው:: ያ ባይሆንማ ኖሮ መች እንዲህ ጥሬ አር ይታራብን ነበር?
    ወያኔ በራሱ ቲያትር እየሰራ ይመስለኛል:: የዚህ አይነቱን ፌዝ (ፍርድ ብሎ መጥራቱ በፍርድ መቀለድ ይሆናልና) ትኩሳት መለኪያው አድርጎታል::በዚህ ላይ መተቸቱ በራሱ ቀልድ ይሆናል:: በተባበረ የኢትዮጵያውያን ክንድና ስልት ወያኔ ይንኮታኮትና እንፈራረዳለን እንጂ ለዛቢስ መጣጥፍ ተብየዎች ሲለቀለቁ ቢውሉ ምንም አይፈይዱም:: ይልቁንም አንባቢን ያናድዳሉ!

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።