ቾቼስኮ እንደ መለስ፤ ኤሌና እንደ ሀዜብ ፤ ትንቢተ ሮማኒያ፡ መልእክተ ኢትዮጵያ – ልጅ ተክሌ

December 31st, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

1989 ዓ.ም. ነው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር። ታህሳስ፡ 1981 ዓ.ም. እንደ ኢትዮጵያ። በዚያ የሆነው በ20?? የሚሆነውና ያሳያል እነሆ በሮማኒያ የተከሰተውን ታሪካዊ ክስተት ማተት ፈቀድን። በዚያም ግዜ እንዲህ ይሆናል። ከዚያ አስቀድሞ በሆነ ግዜም፡ ኒኮላ ቾቼስኮ አላደመጠም ነበር። ነቢያት ሁሉ ሲተነብዩ የሚሰማ መሪ የሚያደምጥ አምባገነን የለም። ኤሌናና፡ ቾቼስኮም አላደመጡም ነበርና፡ ያ አስቀድሞው የሮማኒያ ወይንም ሌሎች ነቢያት የተነበዩት በነሱ ደረሰ። የሮማኒያ ፍርድ ለኢትዮጵያ ትንቢት ነው። ለማይሰሙት መለስና ሀዜብ፡ እንዲሁም ተከታዮቻቸው ይሆን ዘንድ እነሆ የሮማኒያን ፍርድ።

የ1989 ልደት፡ ለሮማኒያ ህዝብ እውነተኛ ልደት ነበር። የታህሳስ 21 አመጽ፡ ለ15 አመታት እና ከዚያም በላይ አምባገነን ሆኖ የኖረውን ኒኮላ ቾቼስኮን ገልብጦ ጣለ። ኒኮላ መለስ ነበር። ኒኮላ ገዳይ ነበር። ኒኮላም አፋኝ ነበር። ኒኮላ አምባገነን ነበር። ሚስቱም፡ ኤሌና እንደዚያው። ሀዜብ ነበረች። አታውቅም። ግን አለባበስ እውቀት የሚመስላት፡ ከታጋዮች ሻይ አፍይነት ወደ ቤተመንግስት እመቤትነት ያደገች ጥጋበኛ ነበረች። በነ እቴጌ ጣይቱና በነ ምንትዋብ ወንበር የተቀመጠች አምባገነን ሴት ነበረች። የሮማኒያ ህዝብ መረረው። ታህሳስ 1989 አመጽ ተነሳና ገለበጣቸው። አመጹን ሌላ ግዜ እንመለስበታለን። አሁን ግን የኒኮላና ሚስቱን የፍርድ ሂደት እንመለከታለን። ያ ለኛ ትንቢት ነውና።

ባንድ የጦር ፍርድ ቤት፡ ዝግ ችሎት ኒኮላና ጠበቆቹ እንዲሁም አቃብያነ ግግ ተቀምጠዋል። ጥቂት ተመልካቾችም ነበሩ መሰል። ችሎቱ ዝግ ይሁን እንጂ፡ የተወሰነው የችሎቱ ሂደት በቀጥታ በቲቪ ይተላለፋል (http://www.ceausescu.org/ceausescu_texts/revolution/trial-eng.htm) ።

አቃቤ ሕግ፡ “መልስ እንጂ? መልስልን?”

ኒኮላ ዜናዊ ወይም መለስ ቾቼስኮ፡ “አልናገርም። እኔ የማውቀው፡ የተወካዮችን ምክርቤት ብቻ ነው። ለተዋካዮች ም/ቤት ወይንም ለጠቅላይ ፍ/ቤት እንጂ፡ ለሌላ ለማንም ቃሌን አልሰጥም። ከተወካዮችና ከፌዴሬሽን ም/ቤት ፊት ብቻ ነው ልቀርብ የምችለው። ማንም በኔ ላይ ስልጣን የለውም? አልናገርም።” አለ።

አቃቤ ህግ፡ “ትናነት ከህዝቡ ጋራ አልነጋገርም ብሎ እምቢኝ እንዳለው፡ ዛሬም ከኛ ጋር ልነጋገርም ብሎ ማመጹ ነው።” (ይቅርታ፡ በሮማኒያንኛ አንቱታ የለም መሰል። በኢትዮጵያንኛ ግን አንቱታ አለ። እኛ እንደመለስ አይደለንም። ማለቴ መለስን ጥለን የምናቋቁመው ፍ/ቤት የነመለስ አይነት ዘርጣጭና ባለጌ አይደለም። አንቱታ የሚያውቅ ነው። አንተና አንቺ ብቻ ያለበት የታጋዮች ፍ/ቤት አይደለም)

አቃቤ ሕግ ቀጠለ፤ “ስለዚህ አቶ መለስ ትናንት ህዝቡን እምቢ እንዳሉት ዛሬም እኛን እምቢ አላናግርም ማለታቸው ነው። ራሳቸውን የህዝቡ አንደበት አድርገውና ለህዝቡ እንደሚናገሩለት የተወደዱ የህዝብ ልጅ እንደሆኑም አድርገው ነበር የሚያክቱት። ግን ህዝቡን ሁሌም እንደጨቆኑ ነበር። በዓል በመጣ ቁጥር በቤተ መንግስትዎ ቅልጥ ያለ ድግስ ይደግሱ ነበር። ዝርዝሩን አገር ያውቀዋል። የተከበረው ፍ/ቤት፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች፡ በህዝብ ገንዘብ፡ ከውጭ አገር የማያመጡት ወድ ልብስና ምግብ አልነበረም። በዚህ ረገድ፡ ከቀድሞው የሮማኒያና የኢትዮጵያ ነገስታት የባሱ ነበሩ። ባንድ በኩል ህዝቡ፡ በቀን ከሁለት መቶ ግራም ያልበለጠ ሬሽን ነበር የሚሰጠው። እነዚህ ሁለት ሰዎች ግን፡ ኒኮላና ኤሌና፡ መለስና ሀዜብ እንደማለት ነው፡ ህዝቡን ዘረፉት። ቀሙት። ያ ሁሉም ሆኖ፡ ዛሬ ተናገሩ ሲባል ፡ መልስ አይሰጡም። ቦቅቧቆች ናቸው። ስለያንዳንዱ ወንጀላቸው ማስረጃ አለን። ቀጥሎ ጠቅላይ አቃቤ ህጉ፡ የክሱን መዝገብ እንዲያነብልን እጋብዛለሁ።”

ጠቅላይ አቃቤ ህግ፡ “የተከበሩ ሰብሳቢ ዳኛ፡ ዛሬ በነዚህ የሚከተሉትን ወንጀሎች በፈጸሙት፡ ሁለት ወንጀለኞች ላይ (ይቅርታ፡ ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ፡ እኛ ወንጀለኞች አንልም። ፍርድ ቤቱ ወንጀለኛ ይበላቸው። እኛ በነሱ ቋንቋ አንናገርም። እነሱ ናቸው ሰውን አስቀድመው ወንጀለኛ የሚያደርጉት። ከሰው፡ ፈርደው፡ ገድለው ፍርድ ቤት ያቀርባሉ) ፍርድ መስጠት አለበት። ከሰው ልጅ ክብርና ማህበረሰባዊ አስተሳሰብ ጋር የማይጣጣም ወንጀል ፈጽመዋል። እንመራዋለን የሚሉትን ህዝብ አጥፍተዋል። ወንጀል ፈጽመውበታል። ጨቁነውታል። ገድለውታል። አስረውታል። በድለውታል። አገር ከፋፍለዋል። ሉአላዊነታችንን ሸርሽረዋል። ኢትዮጵያን ክደዋል። በዚህ በህዝብና በአገር ላይ በፈጸሙት ወንጀል ምክንያት፡ በተበዳዮቹና በአገሪቱ ስም፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች በሞት እንዲቀጡልን እንጠይቃለን። (ኖ ኖ፡ እኛ ቀድመን አንቀጣም። መጀመሪያ ጥፋተኞች መባል አለባቸው። ካመኑ መልካም፡ ካላመኑም፡ እናስመሰክርባቸዋልን። መረጃ ይቀርባል። እኛ መለስን ጥለን መለስ ላይ እንዲፈርድ የምንመኘው ፍርድቤት እንደ ለመስ ያለ ፍርድ ቤት አይደለም)። የክስ መዝገባችን የሚከተሉትን ወንጀሎች ይዟል። አንደኛ፡ በአንቀጽ ? ? ? መሰረት፡ የዘር ማጥፋት ወንጀል። አምቦ ይናገር። አኝዋክ ይመስክር። አዋሳ፤ ጌዴዎ፡ አማራው፡ ኦሮሞው፡ ሶማሊው ይናገር። ሁለተኛ፡ በአንቀጽ ? ? ? መሰረት፡ በአገሪቱና በህዝቡ ላይ የጦር ወንጀል በመፈጸም። አመጽ እናስቆማለን ብለው፡ ህዝቡን ተኮሱበት። ገደሉት። (አይገርምም? በሮማኒያና በኢትዮጵያ የሆነውና የሚሆነው አንድ ነው)። ሶስተኛ፡ በአንቀጽ፡ ? ? ? መሰረት፡ የህዝብን ተቋማትና ህንጻዎች፡ በማውደም፡ የአገሪቱን ብሄራዊ ምጣኔ ሀብት በማጥፋት፡ የኢኮኖሚውን ሂደት በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በታማኞቻቸው እንቅስቃሴ በማኮላሸት ወንጆለች ተከሰዋል። (አይገርምም፡ ዝቅ ብለን እናየዋለን፡ ግን ሀዜብና ኤሌና፡ መለስና ቾቼስኮ ያደረጉት አንድ ነው። ባዶ ኪሳቸውን አዲስ አበባ የገቡ ምስኪኖች፡ እነሆ ባስር ዐመት ታላላቅ ህብታሞች ሆኑ። ያም ባልከፋ፡ ስንቱን በሰበብ አስባቡ ከስራና ቢዝነስ ውጪ አደረጉት። እነ ኤፈርትን አስቡ። ሀዜብ። ኤሌና።)

አቃቤ ህግ ተመለሰ፡ “ክሱንሰማችሁ? ተረዳችሁትስ? (የእኛ ፍ/ቤት እንደናንተ ፍ/ቤት አይደለም። ባልተረዳችሁትና ባልገባችሁ ክስ አይፈርድም። ባይገባችሁም፡ እንዲገባችሁ ለማድረግ ጥረት ያደርጋል። ያንን ነው፡ የመሪያችን የብርቱካን መንፈስ እንድናደርግ የሚያዘን። እነሆ በ20??፡ እነ መለስ ለፍርድ ሲቀርቡ ብርቱካን በሕይወት ላትኖር ትችላለች። ይገድሏታል። ያ፡ እንዲሆን የምንመኘው አይደለም። እነዚህ ሰዎች ግን፡ እንደ ብርቱካን ያለ ጀግና አይናቸው ስር እንዲያድግና፡ በአመታት እስር ገኖ፡ ከብሮ እንዲወጣ አይሹም። ስለዚህም ያጠፏታል)። ወደ ፍርድ ቤቱ እንመለስ።

መለስ ቾቼስኮ፡ “መለስ አልሰጥም። አልናገርም። መናገር የምፈልገው ከአብዩ ብሄራዊ ሸንጎ ፊት ብቻ ነው። ይሄንን ፍ/ቤት አላውቅም። ክሱ ሀሰት ነው። ስለዚህም አንድም መልስ አልሰጥም። (አይገርምም፡ ለዚህ ፍ/ቤት እውቅና አልሰጥም። እናንተ መቼ ነው የህዝብ እውቅና ያገኛችሁት? ያለእውቅና አይደለም እንዴ ይሄንን ያህል ዓመታት የገዛችሁን? አረ ይሄ አያስኬድም። ስልት ለውጡ።)”

አቃቤ ሕግ፡ “የተከበሩ አቶ መለስ ቾቼስኮ፡ በክስ መዝገብ የሰፈሩትን ክሶች አልቀበልም ብለዋል።”

ቾቼስኮ ቀጠለ።ምንም አይነት ሰነድ አልፈርምም።

አቃቤ ሕግ፡

ብትፈርሙስ ባትፈርሙስ ምን ለውጥ አለው። “ይሄ አገር ያወቀው ጸሀይ የሞቀው ነው። አገሪቱ የገባችበት መቀመቅ ዓለም ያውቀዋል። (ፈረምክም አልፈረምክም ለውጥ የለውም። ይቅርታ አንተ አልኩኝ። እርሰዎ። ክቡርነትዎ።) መራባችንን አገር ያውቀዋል። በያመቱ አስር ሚሊዮን ሕዝብ የምግብ ርዳታ ካልተሰጠው እንደማይኖር፡ ሕጻናትና ሴቶች በምግብ እጦት እንደሚያልቁብን ማን የማያውቅ አለ። እስከ ታህሳስ 22 ጠንክሮ ይሰራ የነበረ የሮማኒያ ዜጋ ሁሉ መድሀኒትና ምግብ እንዳልነበረን፡ ኤሌክትሪክና ሙቀት እንዳልነበረንና በዚህም ብዙ ሺህ ህጻናትን እንደጨረሳችሁ የታወቀ ነው። ሰቆቃችንን እኛ ብቻ አይደለንም፡ ዓለምም ያውቀዋል።”

(ይሄ ሁሉ በቲቪ ይተላለፋል። ኒኮላና ኤሌና፡ ሀዜብና መለስ መሆናቸው ነው፡ ይንሾካሾካሉ፡ የለም ይሄንን ክስ አንቀበልም ይላሉ። ኖ ኖ ጭራሹኑ አንመልስም ነው እንጂ። ሌላም ጥያቄ ቀረበላቸው? የቲምሶራን ደም መፋፈስ ያዘዘው ማነው? የናዝሬትን ግድያ ትእዛዝ ያስተላለፈው ማነው እንደማለት ነው። ወይንም የአምቦን። ወይም የአዋሳን። የድሬዳዋን። የባህርዳርን። የመቀሌን ለጊዜው ማስረጃ የለንም። ምናልባት ግን እዚያም “ሳይለንት” ግድያ ይኖር ይሆናል።) ሁሉንም ካዱ እነ ቾቼስኮ። እነ ዜናዊ።

አቃቤ ህግ መጣ፡ ለምሳሌ፡ ማነው የቡካሬስቱን ግድያ ያዘዘው? (ቡካሬስት የሮማኒያ አዲስ አበባ መሆኗ፡ነው። አመጹ ሲቀሰቀስ፡ ብዙ ሺዎች፡ ወይም መቶዎች፡ ወይም አስሮች ተገድለዋል። ቁጥር ምን ለውጥ ያመጣል። 193? 1093? አንድስ ነፍስ ቢሆን?)። እና ማነው ያዘዘው፡ ጦሩን በሕዝቡ ላይ እንዲተኩስ? (አግአዚን መሆኑ ነው)”

መለስ ቾቼስኮ፡ አሁንም መልስ አልሰጥም አለ። ገና ወደፊትም ይላል። መልስ አልሰጥ እንዳለም፡ የጁን ያገኛል። አቃቤ ሕግ ግን ደግሞ ጠየቀው፤ እኛ እንደነሱ አይደለንምና። “ማነው ወደ ሕዝቡ እንዲተኮስ ትእዛዝ የሰጠው።” (ነገሩ እኮ ግልጽ ነው። ትዝ ይላችኋል? በምርጫ 97 ማታ፡ መለስ ቾቼስኮ የጦር ሰራዊቱና የፖሊስ ሰራዊቱ ባንድ እዝገብተው፡ በቀጥታ በኔ ቁጥጥር ስር ይሆናል ሲል። ከነገ ጀምሮ ምንም አይነት ሰልፍ አይደረገም ሲል። ሌላ ቀን ደግሞ፡ ወላጆች ተጠንቀቁ፡ ልጆቻችሁን ጠብቁ፡ ልጆቻችሁ በፈንጂ ወረዳ ክልል ውስጥ ከገቡ እንገድላለን ሲል። ነገሩ ግልጽ ነው። ግን ትክክለኛ ሕግ እንደዚህ ነው የሚሰራው፡ ሁሉም ነገር በማስረጃ በደንብ መረጋገጥ አለበት። እናም ግልጽ ቢሆንም፡ እናስመሰክራን ማስረጃም እናቀርባለን) (ያ ብርቱካን የተሰዋችለት የምትሰዋለትም ፍትህ አካሄድ ነው)።

በዚህ መሀል ያቺ ሙጢ፡ ኤሌና መጣች። ለኒኮላ ሹክ አለችው። ሀዜብ መሆኗ፡ነው። “ባክህ እርሳቸው፡ ከነዚህ ጋር ማውራት እርባና የለውም”) አለች። ሚስት ብሎ ዝም። ዛሬም አያርማትም።

አቃቤ ሕግ ቀጠለ፡ “ለጦር ሰራዊቱ ወደ ሕዝቡ እንዲተኩስ ስለተሰጠው ትእዛዝ የምታውቀው ነገር የለም? አሁንም ከውጭ ተኩስ ይሰማል። እነዚህ ያንተ ቅጥረኞች፡ አሁንም ወደ ሕዝቡ እየተኮሱ ነው። ሲተኩሱ አይመርጡም። ሕጻናት፡ ሴቶች፡ ወደመኖሪያ ቤቶች፤ ዝም ብሎ ማንደቅደቅ። ማናቸው ለመሆኑ? የህዝብ ናቸው ወይንስ አንተ ቅጥረኞች።”

መለስ ቀጠለ፡ “አልመልስም። ምንም አይነት ጥያቄ አልመልስም። አንድም ጥይት ከቤተ መንግስት አደባባይ አልተተኮሰም። ማንምም በጥይት አልተመታም። (እኔ አላውቅም አይነት ነገር ነው። አልመልስም ይላል። ግን ይመልሳል።)”

አቃቤ ሕግ፡ “እስካሁን፡ 34 ሰው ሞቷል። (ያ ግን ሮማኒያ ነው። ያ ኢትዮጵያ አይደለም።) የኤሌና መልስ ግን ያናድዳል። ግን ብልጥነቷንም ያሳያል እንዲህ አለች፡ ለቾቼስኮ። ሀዜብ ለመለስ መሆኑ ነው። አቃቤ ሕግ “እስካሁን 34 ሰው ሞቷል” ሲል፡ ኤሌና፡ በሹክሹክታ፡ “ተመልከት፡ ያንን የዘር ማጥፋት ወንጀል ይሉታል።” (አይገርምም፡ እስካሁን መልስ ሳትሰጥ፡ አሁን ክፍተት አገኘች። እሷ ያስጨነቃት የሰላሰ አራት ሰው መሞት አይደለም። የ34 ሰው ሞት የዘር ማጥፋት መባሉ ነው። እና ስለተኩስ ሲጠየቁ ሳትመለስ፡ ክፍተት ስታገኝ፡ ክሱን ለማጣጣል ብቻ ተነሳች። የዘር ማጥፋት ሙከራና የዘር ማጥፋት የማይለይ ችኩል ስርአት ስለ ዘር ማጥፋትና ሰው ማጥፋት ሲከራከር አይገርምም። እነ መለስ፡ የቅንጅትን አመራር በዘር ማጥፋት ወንጀል ሲከሱ፡ “ አረ ተዉ ይሄ ነገር አያዋጣም፡ ባይሆን “ሙከራ” በሉት እንጂ ብሎ የመከራቸው አንድ የአሜሪካ ምሁር ነው። እና ዛሬ ስለዘርማጥፋት ወንጀል ሌክቸር ሊሰጡ ነው።)

አቃቤ ሕግ ቀጠለ፡ “በሁሉም ከተሞችና ወረዳዎች፡ ተኩስ እንደቀጠለ ነው። ሕዝቡ በባርነት ቀንበር ተይዞ ኖረ። የሀገሪቱ ምሁራን ሁሉ ተሰደዱ። ማንም ከናንተ ጋር መስራተ አልፈለገም።” እነሆ አመጽ ፈነዳ። ተሸነፋችሁ። ህዝብ አሸነፈ።

አንድ ያልታወቅ ጠያቂ ጣልቃ ገባ፡ “የተከበሩ ፕሬዚዳንት፡ አንድ ነገር ማወቅ እፈልጋለሁ። ተከሳሹ እነዚህ ሕዝብ ላይ የሚተኩሱ ቅጥረኞች እነማን እንደሆኑ? ማን እንደሚከፍላቸውና እንዴት ወዳገሪቱ እንደገቡ እንዲነግርን እፈልጋለሁ።”
አዎ ልክ ነው። መልስልን ተከሳሽ። መልስልን አለው አቃቤ ህግ። ቾቼስኮ ግን ያንኑ የመጀመሪያውን መልስ ደገመ። “አልመልስም፡ ከአብዩ ብሄራዊ ሸንጎ ፊት ብቻ ነው የምናገረው” አለ። ቾቼስኮ እንደ ጅብም አደረገው። እሰው አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አይነት ነገር። እነደ ቃሪያም አደረገው፡ በሁዳዴ ተግዝታ ሁልግዜ ሁዳዼ እንደሚመስላት። ኤሌናም ማንሾካሾኳን ቀጠለች። ሾካካ።

አቃቤ ሕግ፡ በሀዜብ ሹክሹክታ ተበሳጨ መሰል ይሄንን አለ። ኤሌና ቁርጥ ሀዜብን ነው። ሀዜብ መስፍን ጎላ።
“ኤሌና ድሮም ምንም የማታውቅ ቀባጣሪ ነች። እኔ ራሴ፡ ምንም በቅጡ ማንበብ እንኳን የማትችል ነግር ግን ራሷን እንደ ዩኒቨርሲቴ ምሩቅ የምትቆጥር ሴት መሆኗን አስተውያለሁ። አቃቤ ሕግ ከዚያ ቀጥሎ ወ/ሮ ኤሌና አለኝ የምትለውን የዲግሪ መአት ደረደረው። (የሀዜብና የኤሌና መመሳሰል ግርም ይለኛል። ወ/ሮ ሀዜብ ታጋይ ነበረች። ሻይም ታፍላ ጠላ ትጥመቅ፡ ባንድ ወቅት ከታጋዮች ጋር የኖረች ታጋይ ነች። እስኪ አስቡት፡ ይህቺ ታጋይ የኢትዮጵያ ጸረ-ኤድስ ምናምን ፕሬዚዳን፡ የኤፈርት ምክትል ስራ አስኪያጅ፡ የዚህ ድርጅት ሀላፊ፡ የተዋካዮች ም/ቤት አባል፤ እሷም እንደነ መለስ የተልእኮ ድግሪ ትያዝ አትያዝ አላውቅም። ግን ማይ ይከለክላታል። ገንዘብ ካለ…. እነሆ ሀዜብ ለመለስ በጆሮው ታንሾካሹካለች።)

ኤሌና መስፍን፡ የዚህ አገር ምሁራን በኛ ላይ የምታቀርበውን ክስ እየሰሙ ነው። ይታዘቡሀል አይነት ነገር ተናገረች።

አቃቤ ሕግ፡ ቀጠለ፡ “አቶ ኒኮላ ዜናዊ፡ ጥያቁያችንን ለምን እንደማይመለስ ሊነግረን ይገባል? ምንድነው ምክንያቱ?”

መለስ ቾቼስኮ ለምን መልስ እንደማይመለስ እንዲህ ሲል መለሰ። “ማናቸውንም ጥያቄ እመልሳለሁ፡ ግን ከሰራተኛው መደብ ተወካዮች ከታላቁ ብሄራዊ ሸንጎ ፊት ከሆነ ነው። ለሕዝቡ ሁሉንም ጥያቄውን እንደምመልስ ንገሩት። ዓለም እዚህ ምን እየተሰራ ምንስ እየተደረገ መሆኑን ማወቅ አለበት። የማውቀው፡ የሰራተኛውን መደብና፡ የብሄራዊ ሸንጎውን ብቻ ነው፤ ሌላ ማንንም አላውቅም።” (አራት ነጥብ አላለም እንደ መለስ። ያ በቻይና ቴክኖሎጂ እየታገዘ አገሪቱን አፍኖ የገዛና መተንፈሻ ያሳጣ፡ ያ መገናኛ ብዙሀንን ዘግቶ የራሱን ልሳን ብቻ የከፈተ አምባገነን፡ ያ ዓለም ረሀባችንና መታረዛችንን እናዳያውቅ ያደረገ ስርአት መሪ፡ ዛሬ በወደቀ በሶስተኛው ሌሊት እዚህ ኢትዮጵያ የሚደረገውን ዓለም ይወቀው ይላል። አይገርምም። እኛም እሱን፡ መለስንና ፓርቲውን ያወቅነው በግድ ነው። መርጠን አይደለም። ወደንም ፈቅደንም አይደለም። እነሆ ያ ጊዜ መጣ፡ እሱም እኛን በግድ የሚያውቅበት)። አቃቤህጉም አለው ለመለስ ቾቼስኮ፡ “ዓለም በዚህ በሮማኒያ የሆነውን አውቋል።” በኢትዮጵያም እንደዚያው። ስለዚህም መለስ አድምጥ፡ አለም እኛን አላዳነንነም፡ ዓለም አንተንም አያድንህም።

መለስ ቾቼስኮ፡ በብስጭት እንዲህ አለ “እናንተ አመጸኞችና ሴረኞች፡ መንግስት ገልባጮች፡ ለናንተ መልስ አልሰጥም።”

አቃቤ ሕግ፡ “ብሄራዊ ሸንጎው ፈርሷል”።

መለስ ቾቼስኮ፡ “ይህ ሊሆን አይችልም፡ ማንም ብሄራዊ ሸንጎውን ሊያፈርሰው አይችልም።” (አይገርምም፡ የአምባገነኖች ሁሉ ጸባይ አንድ ነው። መንግስታችን በአለት ላይ የታነጸ ነው። የሲኦልም ደጆች ሊያናውጿት አይችልም አይነት አነጋገር። ለሰማያዊ ፈጣሪ ብቻ የተሰጠውን ቋንቋ ለራሳቸው ይጠቀሙበታል። መለስ ሕገ መንግስታችንን ማንም ሊነጥቅ አይችልም እንደሚለው መሆኑ ነው። ከፊታቸው ነጥቀው የመጡትን ሕገ መንግስታት ይዘነጋሉ። ተመልከቱ፡ አምባገነኖች ልብና አእምሮ ይነሳቸዋል ካልተባለ በስተቀር፡ መለስ የደርግን፡ ደርግም የጃንሆይን ህገ መንግስት አፍርሰው እዚህ እንደደረሱ ካልረሱ በስተቀር፡ እንደምን ማንም ሊነቀንቀን አይቻለውም ብለው ይናገራሉ?) የሆነ ሆነና ቾቼስኮ እንደዚያ አለ። እንደ መለስ።

አቃቤ ሕግ፡ “ያ ሆነ፡ ብሄራዊ ሸንጓችሁ ፈረሰ። የተወካዮች ምክር ቤት የፌዴሬሽን ምክርቤት የሰራተኛ ምደብ የገበሬው ግንባር፡ ኢህአዴግ ምናምን የምትሏቸው አካላት ሁሉ ተበተኑ። አሁን ሌላ መሪ አካል አለ። የብሄራዊ መድህን ግንባር ነው አገሪቱን የሚመራው”።

መለስ ቾቼስኮ፡ “ማንም ያንን የሚቀበል የለም። ለዚህም ነው ሕዝቡ ባገሪቱ ሁሉ የሚፋለመው። ጋንጎች ናቸው ይህን መፈንቅለ መንግስት ያስተባበሩት። ይሄ ጋንግ ይደመሰሳል።” (አሁንም የአምባገነኖች ሁሉ ቋንቋና ጅልነት አንድ አይነት ነው። እየሞቱ ሁሉ እየወደቁ፡ ቋንቋቸውን አይለውጡም። ምንም ነገር የህዝቡ ነው ብለው አያምኑም። የጣልቃ ገቦች፡ የአመጸኞች፡ የዱርዬዎች፡ የምናምኖች …..። መለስም ያለው ይሄንን ነበር። የቦዘኔዎች፡ የዱርዬዎች፡ የተቃዋሚዎች። ቢሆንስ? እነሱስ ባንድ ወቅት ሽፍቶች አልተባሉም? ወንበዴዎች አልተባሉም? ቤተ መንግስት መግባታቸውና ልብስ መቀየራቸው፡ ከቁምጣ ወደ ሱፍ፡ ማደግ ሁሉንም ነገር ይለውጣል ማለት ነው?

አቃቤ ሕግ፡ “ህዝቡ የሚዋጋው እናንተን ነው፡ ሕዝቡ የሚዋጋው አዲሱን መንግስት አይደለም።”

መለስ፡ “ኖ ሕዝቡ የሚዋጋው ለነጻነቱ ነው። የሚዋጋውም አዲሱን አመራር ነው። ይሄንን ፍርድ ቤት አላውቅም።

አቃቤ ሕግ፡ “ይቅርታ እስኪ ድገምልኝ፡ ዛሬ ሕዝቡ የሚዋጋው ለምን ይመስልሀል? እስኪ ምን ታስባለህ?”
(ምን ያስባሉ አቶ መለስ? በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡለትን መብቶች ለማስጠበቅ ነው እንደሚሉ ነው አቶ መለስና ቤተሰባቸው። መቼም ልጆቻቸውን አንጨምርም አዚህ። ግን በሕግ መንግስቱ የተረጋገጡትን መብቶች የሚጥሱት ህገ መንግስቱን የሰጡት ሲሆኑስ?)

ቾቼስኮ ዜናዊም መለሰ፡ “ቀደም ብዬ እንዳልኩት፡ ሕዝቡ የሚዋጋው ለነጻነቱና ይሄንን መፈንቅለ መንግስትና የስልጣን ንጥቂያ ተቃውሞ ነው።” ቾቼስኮ የሚለው ይሄ መፈንቅለ መንግስት የተቀናበረው በውጭ ሀይሎች ነው አይነት ነገር ነው። (ይሄ ተለመደ ነው። የህዝብንና የተማሪዎችን አመጽ የተቃዋሚዎችና የዱርዬዎች አድርጎ መሳል የነመለስ የዘወትር ስልት ነው። ግን ያ አይሰራም። ማንም ይቀስቅሰው ማን፡ ዋናው ነገር ማሸነፍ ነው። ካሸነፍን ፍርድ የኛ ነው። ከተሸነፍን፡ ከተነቃብንም፡ ይፈረድብናል። እንዲህ እንዲህ እያለ ክርክሩ ይቀጥላል …….. ይቀጥላል። የፍርድ ሂደቱም በቀጥታ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ይተላለፋል። ትንቢተ ሮማኒያ ይቀጥላል …..

ይህ ጽሁፍ፡ ከዚህ http://www.ceausescu.org/ceausescu_texts/revolution/trial-eng.htm የተወሰደና ለኢትዮጵያ ሁኔታ እንዲስማማ ትንሽ ማስተካከያ የተደረገበት ነው። ቀጣዩን ክፍል ሰሞኑን ይዘን እንቀርባለን።

ልጅ ተክሌ፡ ካናዳ፡ ታህሳስ 2009፤

 1. ወይ ነዶ መሞት
  | #1

  አይ ውድ ልጅ ተክሌ:

  በጣም ይገርሙኛል: ለመሆኑ ስንቱን ጀግኖችና ውድ የሆኑ ኢትዮጵያንቹን በውቀትም ሆነ በድሜ የበለጸጉትን አንተና አንቺ ይሏቸዋል: ሌባና ከሃዲ የሆነውን ወንጀለኛ ትንሽ የደም ትስስር ወይም የፍራቻ ነገር ይመስላል አንቱና ክቡር ይሏቸዋል: ለምን? አሁን መለሰ አንቱ የሚባል ሰው ነውኝ? አንቱና አንተ የሚያስብለው ምን እንደሆነ ያውቃሉ? በጣም አፈርኩ::

  መለሰ ዜናዊ የበላው የሰው ስጋና ደም ያስመልሰውና ፍርድ ቤት ይቅረብ እንጅ ተናገረ አልተናገረ ምን ችግር ይፈጥራል? መጀመሪያ በጠራራ ጸሃይ የገደላቸው የንጹሃን ልጆች ደም: ሁለተኛ የደርግ ወታደር ናቸው ብሎ በሜዳ ተጨፈጨፋቸው አርበኞች: ሶስተኛ ኤርትራን ገንጥሎ በስጦታ ማስረከቡ: አራተኛ በአደባባይ በአማራ ህዝብ ላይ በአዋጅ መጨረስ አለበት ብሎ ማዘዙ: አምስተኛ; ሌላውን ብሄሮች አደህይቶ ስልጣኑንና የሀገሪቱን ሀብት ለትግራይ ልጆች ማከፋፈሉ: ወዘተ የሱን ሀጢአትና የክስ ብዛት ለመዘረዘር ጊዜም ሆነ ለጠበቃ ኢትዮጵያ የምታወጣው ገንዘብ አይኖርም: አንኳር አንኳር በሆኑት ወንጀሎች ብቻ ኢትዮጵያኖች ብቻ ሳይሆኑ የአለም ህዝብ የሚያውቀውን ወንጀል ጠቅሶ መፈረድ እንጅ ሌላ እንካ ስላንቴ የምንገጥምበትና ለሱ ብለን የምንደክምበት ምክንያት የለም::

  ከዚያ በፊ ግን ለክሱ የምንጠቀመው ህግ ራሱ ባወጣው ህግ ሲሆን ምርመራውም የሚጠናቀቀው በራሱ መርማሪዎችና ራሱ ባዘጋጀው እስር ቤት ይሆናል: ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ብቻ ሳይሆን ሌባና ሽፍታ በነበረበትም ጊዜ የገደላቸውና ያጠፋቸው ልጆች ደም እስካሁን ይጮሃል: ከዚያ 1ኛ/ እሱ እጁ እንደተያዘ ወንድ ልጆችን የሰንጋ ከብት ይመስል ብልታቸውን እንዳስቀጠቀጠው በሚስቱ ፊት ብልቱ ይቀጠቀጣል: ከጭካኔው ብዛት ሴቶች ልጆችም እስር ቤት አምጠውና ያለህክማ እንደወለዱትና ክቡር በሆነው ማህጸናቸው ውስጥ እንዳልተወለደበትና ሚስቱም ሆች ልጁ ማህጸን እንደሌላቸው እጅግ ዘግናኝ የሆነ ቅጣት እንዳስፈጸመባቸው በተመሳሳይ መልኩ በራሱ ህግ ሚስቱና ልጁም ይቀጣሉ? ወደደም ጠላውም ባላደረጉትና ባልሰሩት ወንጀል በቅጣቱ አሰቃቂነትና በስቃዩ መክበድ የተነሳ ሳያደርጉ አድርገናል እንዳስባላቸው የግድ ይከፍላታል::

  ስለዚህ ይህን በተመለከተ ልጅ ተክሌ አይድከሙ: ከአሁኑ አስበንበትና ተዘጋጅተንበት እንጠባበቃለን: እርስዎ በሞያዎ የሚያውቁትንና የሚችሉትን ይስሩ ይህን ለኛ ይተውት:: ምን ያህል ጨካኝ ነህ ሊሉኝ ይችላሉ? መለሰ ህዝብን የሚያሰቃየውና የሚገድለው በህግ ስም እየተጠቀመ መሆኑን አይርሱት: ይህ ጭካኔ ሳይሆን በጥርቃሞ ባንዳ የባንዳ ልጆች ምክር ቤት የጸደቀ ህግ ስለሆነ የራሱን ህግ በራሱ ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል:: ቅጣት እንደወንጀሉ መክበድና መቅለል ምርመራ ይካሄድበታል::

  ለመሆኑ በጣም ጨካኝና ደፋር እርስዎ ነዎት እንጅ: መለሰና ቻቸስኮ በምን መልኩ ይመሳሰላሉ? በጨካኝነታቸው ከሆነ እሽ: ሁሉም ይቅር ለመሆኑ ቻቸስኮ አሀሩን ለባዕዳን ሀገር ሲሸጥ አይተዋል? ለመሆኑ ቻቸስኮ የሀገሩን ወታደር የሀገሬ ወታደር አይደለም ብሎ በበረሃ ላይ ሲረሽን አይተዋል? ለመሆኑ ቻቸስኮ ወደብ ሀገሬ አያስፈልጋት ምን ጊዜም ቢሆን በልመናና በምጽዋት እየተረዳን እንኖራለን እኔ የማስተዳድረው በቅኝ ግዛት እንጅ ሀገሬ አይደለም እንዳለው መለሰ ቻቸስኮ ብሏል ነው የሚሉት? በጣም ይገርሙኛል: እውቀት ከሚገባው በላይ በዝቶበወታል ወይም ከውቀቱ ብዛት በጣም እሩህሩህና አዛኝ ሆነዋል ማለት ነው: ገና እጁን ሳንይዘው መሆኑ አይቀርም ብለው ማለሳለሱን እባክዎ ያቁሙ? ስራውንና ትግሉን ተከፋፍለን ሁሉም በሞያው ለመስራት ይሞክር ብየ ምክሬን እለግሰዎታለሁ: አለበለዚያ እንደመለሰ የከፋ ስህተት ልንሰራ መሆኑ ነው: ቅድስት ወይዘሪት ብርቱካንን ሊገድላት ይችላል: በህይወትም ላትኖር ትችላለች ብለው ተንብየዋል: አያስቡ መሆን ያለበት ሁሉ ይሆናል: ያደርገዋል የሚል ምንም ጥርጣሬ የለኝም: የኢትዮጵያን ብርቅየ የሆኑ ጀግና ልጅ ገድሎ ለሱ ነው ተጨንቀውና ተጠበው ከአሁኑ ሰላም ነስቶዎት ጽሁፍ ለመጻፍ የበቁት? አንድ ጸጉራቸውንም አይነካቸውም: ወንድ እንደሌለ አውቆ እንጅ ለማሰርም ባልደፈረ ነበር: ብርቱካንን ግገድሎ ፈርድ ቤት መቅረብ ልጅና ሚስቴ ማለት ይችላል: ወደፊት ለሚሆን ነበር መቃጠልና መበሳጨት አልሻም::

  ስለአዜብ ይተውት ለውይይትም የሚቀርብ ነገር አይደለም: አዜብ ማለት ማን ናት ብለው በደንብ ገና ሽፍታና ጫካ በነበሩበት ጊዜ ጠይቀው ይረዱ? ከሴት ልጅ ስለተወለድኩና ሴቶች እህቶችም ስላሉኝ የግል ሀጢአቷን መግለጹ አያስፈልግም: በአጠቅላይ ከጽሁፍዎ እንደተረዳሁት ጊዜዎን ለማባከን የፈለጉ እንጅ የሚያስፈልግና የሚያደክመዎትም አልነበረም: ለሁሉም ይሁን::
  በቸር ይግጠመን::

 2. Firdu
  | #2

  I was student in neighbouring Bulgaria during that time. It is difficult to compare Romanian dictator Chao Chesko with Super dictator Melesse. Chesko was doing good for his country. At the end of his power the country has no loan from the world bank. The economy of Romania was in good condition. Look what Melesse doing? The country is surviving ( if we call it surviving) with foreigner loan. No democracy.He is totally killing the country and its people.No justice.Every where the security people are working for him not for the country and its people.

 3. koster
  | #3

  It is very unfortunate we does not learn from our mistakes or the mistakes of others. Sooner or later Meles will end up either like Chechesko he will be dragged out of office by angry Ethiopian crowds/forces or end up like Saddam Hussien. Meles missed the chance to give

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።