አንጋፋውና ዝነኛው የስፖርት ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ – ከናደው አምባዬ

December 31st, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ከአንጋፋዎቹ ዝነኛና ታዋቂ የአገራችን የስፖርትጋዜጠኞች ሰለሞን ተሰማ ነጋ ወልደስላሴና ፍቅሩ ኪዳኔ ቀጥሎ በ1962 ዓ.ም. ከድሬ ደዋ በአማተር የስፖርት ዜና ዘጋቢነት ለ ሰባት አመታት በመቀጠልም በኢትዮጵያ ሬድዮ ድርጅት እስካሁን ለ33 ዓመታት ባጠቃላይ ከ40 ዓመት በላይ የስፖርት ጋዜጠኛ በመሆን ያገለገለ ታዋቂና ዝነኛው ውድ የኢጥዮጵያ ልጅ ደምሴ ዳምጤ -

በሞስኮ ፤ በሎሳጀለስ ፤ በሴኦል ፤ በባርሴሎና ፤ በአትላንታ ፤ በሲድኒ ፤ በአቴንስና በቤጂንግ የኦሎምፕክ ጨዋታዎች ባቀረባቸው የስፖርት ዘገባዎች፤

በዓለምና የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ባስተላለፈው የእግር ኳስ ቀጥታ ስርጭት፤

በዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮንና በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች፤

በምስራቅና መካክለኛው የአፍሪካ የእግር ኳስ ውድድሮች በተለይም በ1980 ዓ.ም ኢትዮጵያ ባስተናገደችው የ15ተኛው የምስራቅና መካክለኛ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የኢትይጵያና ዝምባብዌ በሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች ያደረጉትን የፍፃሜ ጨዋታ ከአዲስ አበባ ስታድዮም በቀጥታ ሥርጭት ሲተላለፍ ደምሴ ዳምጤ ያስተላልፍ የነበረው የይቤ ምንግዜም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የማይረሳ ትዝታ ጥሎ ያለፈ መሆኑ፤

በተለያየ ግዜ ባቀረባቸው ሌሎች ልዩ ልልዩ የስፖርት ዜናዎች እንዲሁም ፕሮግራሞች በሚያቀርበው የሚጥምና ቀልብ የሚስብ ስርጭት የስፖርት አፍቃሪውን ህዝብ ስሜትና ፍላጎት ያረካ መሆኑን፤

በአጠቃላይ ባቀረባችው የስፖርት ዜናዎች ቀጥታ የእግር ኳስ ጨዋታ ስርጭት በኢትዮጵያ ህዝብና በስፖርት አፍቃሪዎች ዘንድ ዝነኛና ታዋቂ የሆነው የአገር ቅርስ ደምሴ ዳምጤ በአይኑ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ችግር ፡

ሕመም በውጭ አገር ከፍተኛ ሕክምና ካልተደረገለት በሁለቱም ዓይኖቹ ሙሉ በሙሉ ማየት እንደሚሳነው በሕክምና ዳሬክተሮች ቦርድ የተረጋገጠ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትብብርና እገዛ እንዲድረግለት በጠየቀው መሰረት በሙያ አጋሮቹ ዓለምነህ ዋሴና ታምራት ኅይሉ አማካኝነት ኮሚት ተቋቁሞ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም የስፖርት አፍቃሪው ህዝብ የሰጠው አፋጣኝ ምላሽ በሕዝብ ዘብንድ መወደድ ምን ያህል አርኪና ለወግን ለማግለፅ ቃላት የማይገኝ እርካታ እንደሚያስገኝ የታየና ወገን ለወገን ደራሽ መሆኑ በአጭር ጊዜ በአስተማማኝ መልኩ እየትየ ነው።

በሌላ በኩል ከገቢው ማስገኛ ፕሮግራም ቀደም ብሎ አቶ ተክለ ብርሃን አምባዬ የተባሉ የስፖርት አፍቃሪ የሆኑ የኤድና ሞልና የተክለብረሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ባለቤት በራሳቸው ተነሳሽነት ደምሴ ቤት በመሄድ በሁኔታው በጣም በማዘን በግላቸው ከሰጡት 50 ሺ ብር በተጨማሪ 6 ጓደኞቻቸውን በማስተባበር ከኢትዮጵያ ውጭም በመደወል 180 ሺ ብር ለደምሴ እንዲስጥ ማድረጋቸው እጅግ ባጣም የሚያስመሰግናችው ሲሁን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በተደረገበት ወቅት ሼህ መሐማድ ሁሴን አላሙዲ የደምሴን ሙሉ የህክምና ወጪ ለመሸፈን በተወካያቸው ቃል መግባታቸው ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነቤተሰቡ የትራንስፖርት ወጪ ለመሸፈን ቃል መግባቱና ቢጂአድ ካምፓኒ/ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፤ ባቲና ካስትል ቢራ ፋብሪካ ሌሎች ልዮ ልዩ ወጪዎች ለመሸፈን ቃል መግባታቸው የሚያስማሰግናቸው ሲሆን በአገር ውስጥና በውጪ አገር የተጀመረው ትብብርና እገዛ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመተማመን ደምሴ በቅርብ ግዜ ድኖና ተፈውሶ እንድናየው የእግዚአብሔር ፍቃድ ይጨምርበት።

በመጨረሻም ደምሴና ቤተሰቦቹ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

 1. መስፍን ተስፋዬ
  | #1

  የኢትዮጵያ ሕዝብ ውለታውን አይረሳም:: ለወደደው እና ላገለገለው በችግሩ ጊዜ ባፋጣኝ ይደርሳል::ደምሴ አይዞህ እግዚያብሔር ምህረቱን ሰጥቶህ ወደምትወደው ሙያህ እና ሕዝብህ እንዲመልስህ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ፀሎት ነው::ወያኔዎችም ትምህርት መውሰድ ከፈለጋችሁ ከደምሴ ተማሩ:: ደምሴ አገሩን እና ሕዝቡን በመውደዱ ያገኝውን ምላሽ ተመልከቱ::

 2. ወሰን የለ በላይ
  | #2

  እግዚያቤሄር ይማርህ:

 3. ወሰን የለ በላይ
  | #3

  እግዚያብሄእ ይማርህ እንደሁም ተሽሎህ ለማይት እንመኛለን ሁሌየሚናፍቀን ያንተን ዲምጺ መስማት ነዉ በገንዘብ እንኩዋን መርዳት ባንቺል በጸሎት እናስብሃለን አምልክ ምረቱን ይላክልህ

 4. ዳወዶ
  | #4

  የአገር ሃብት ነሀና ኑርልን
  ውዱ ዘጋቢ

 5. ሰለሞን ፈቀደ
  | #5

  ግሩም ድምጽህን ለመስማት እንናፍቃለን:: እግዚያብሄር መልካሙን ሁሉ እንዲያደርግልህ ምኞቴና ጸሎቴ ነው:: ርዳታ በማድርግ የተሳተፉትን ሁሉ እግዚያብሄር ይባርካቸው:: የስፖርት አፍቃሪውን (በአጠቃላይ ህዝቡን). . . እኛን በሞላ መልካሙን የምንሰማ ያድርገን – Amen! I am sorry that I couldn’t get acquainted with some of the Amharic features on the key board. That’s the main reason why I write ‘Amen’ in English. QUICK RECOVERY for Demisse Damte.

 6. Anonymous
  | #6

  እግዚያዓብሔር ይማርህ

 7. be ewinet
  | #7

  Egziabher cherso ymarh min enlalen hulu neger lebego new kalat yelegnm

 8. ተሰፋየ.. ተ/ ሰላሲ
  | #8

  ናደው እግዘአበሂር ይሁንህ

 9. Henok
  | #9

  God bless you

 10. Anonymous
  | #10

  አግዚያብሔር ከአንተ ጋር ይሁን።

 11. Anonymous
  | #11

  YE Ethiopia wude leje amelake keante gar yehune
  Nadew antem seleasabineteh geta yastawuseh
  Dereje Tess.

 12. Anonymous
  | #12

  Henok :God bless you

  Henok :God bless you

  Henok :God bless you

  Henok :God bless you

  መስፍን ተስፋዬ :የኢትዮጵያ ሕዝብ ውለታውን አይረሳም:: ለወደደው እና ላገለገለው በችግሩ ጊዜ ባፋጣኝ ይደርሳል::ደምሴ አይዞህ እግዚያብሔር ምህረቱን ሰጥቶህ ወደምትወደው ሙያህ እና ሕዝብህ እንዲመልስህ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ፀሎት ነው::ወያኔዎችም ትምህርት መውሰድ ከፈለጋችሁ ከደምሴ ተማሩ:: ደምሴ አገሩን እና ሕዝቡን በመውደዱ ያገኝውን ምላሽ ተመልከቱ::

  @Henok

  @Henok

  @Henok

  @Henok

  @Henok

  @Henok

 13. ሣተናዉ
  | #13

  የህገር አለኒታ ምህረት ይስትህ አሚን

 14. Analyst
  | #14

  The legend , Marin Taylor of Ethiopia

 15. binyam
  | #15

  God bless you

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።