ዶር ነጋሶ ሲናገሩ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ በባሀር ዳር ስቴዲየም በፊጨትና በሆታ ደስታዉን ገለጸ !

January 11th, 2010 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

አቡጊዳ – ጥር 3 ቀን 2002

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ በባህር ዳር ከተማ በሚገኘዉ ስቴዲየም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ባሉበት ታላቅ ህዝባዊ ስብሰብ ትላንት ጥር 2 ቀን 2002 ማድረጉን ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያመለክታል። የክልሉ የገዢዉ ፓርቲ ባለሥልጣናት ህዝቡ ወደ ስብሰባዉ እንዳይሄድ በጥቅም ላይ የተመሰረቱ ስብሰባዎች በየቀበሌዉና በየትምህርት ቤቶቹ መድረኩ ህዝባዊ ስብሰባ በጠራበት ቀንና ሰዓት አዘጋጅተዉ እንደነበረም የደረሰን ዜና አክሎ ገልጿል።

በስብሰባዉ በርካታ የመድረክ አመራር አባላት ንግግር ያደረጉ ሲሆን በተለይም በቅርቡ የአንድነት ፓርቲን የተቀላቀሉትና የአንድነት ፓርቲ የዉጭ ጉዳይ ሃላፊ ሆነዉ የተመረጡት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ለመናገር በቀረቡ ጊዜ የታየዉ የህዝቡ ስሜት እጅግ አስደናቂና ስሜታዊ እንደነበረም ለማወቅ ችለናል። በፉጨትና በጩኸት ሕዝቡ ደስታዉን እየደጋገመ በመግለጹ ዶር ነጋሶ ንግግራቸዉን ደጋግመዉ ለደቂቃዎች ያቋርጡ እንደነበረም ከስፍራዉ ይደረሰን ዜና ያመለክታል።

ትላንትና የብሄር ፖለቲካ ያራምዱ የነበሩና አሁን ያለዉ ገዢ ፓርቲ ከፍተና አመራር የነበሩት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ይህን ያህል ከፍተኛ ድጋፍ ከሕዝቡ በፉጨትና በጩኸት ማግኘታቸዉን የታዘቡ በስፍራዉ የነበሩና ለአንድነት ፓርቲ ቅርበት ያላችዉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ «ዶር ነጋሶ ሕሊናቸዉን ሽጠዉ፣ እንደ አቶ ግርማ ብሩ፣ አባ ዱላና ኩማ ደመቅሳ የነመለስ መጠቀሚያ ሊሆኑ ይችሉ ነበር። ነገር በባደመ ጦርነቱ ጊዜ በመርህ ላይ በመመርኮዝ ከገዢዉ ፓርቲ ተለይተዋል። ያንን ህዝቡ አልረሳም። በዚያም ምክንያት ለዶር እንጋሶ ከበፊትም አክብሮት ነበረዉ።፡ አሁን ደግሞ ለአሥራ ሰባት አመታት ወያኔ/ኢሕአዴግ ሲያራምደዉ የነበረዉን የዘር የብሄርና የመከፋፈል ፖለቲካ ላይ ጩቤ ሰክተዉ ወደ አንድነትና ሕብረ ብሄራዊነት ፖለቲካ መመለሳቸዉና የአንድነት ፓርቲን መቀላቀላቸዉ ህዝቡን የበለጠ ስላስደሰተዉ ነዉ ይሄ ሁሉ ፉጨትና የደስታ ጩኸት የተሰማዉ» ሲሉ የባህር ዳሩ ሕዝባዊ ስብሰባ ከዶር ናጎስ ጊዳዳም በላይ ሕዝቡ በአንድነቱና በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ስሜታዊነትን አልፎ አጥንት የዘለቀና ሥር የሰደደ ጠንካራ አቋም እንዳለዉ ያንጸባረቀበት እንደሆነ ያስረዱት።

የመድረኩ ከፍተኛ አመራር አባላት ከባህር ዳሩ ህዝባዊ ስብሰባ በኋላ የተወሰኑት ወደ ደብረ ማርቆስ፣ የተወሰኑት ወደ ጎንደር የተቀሩት ደግሞ ድርጅታዊ ስራ ለመሥራትና ህዝቡን ለማስተባበር ወደ ትግራይ እንዳመሩ የተገለጸልን ሲሆን ሰኔ ጥር ዘጠኝ ቀን ደግሞ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ በሚይዘዉ በአዲስ አበባ የኮንቬሽን ማእከል መድረኩ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርግም ለማወቅ ችለናል።

የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ አንድ አመት በእሥር መቆየቷን ለመቃወምና ለርሷ ድጋፍን ለመስጠት የአንድነት ፓርቲ በመስቀል አደባባይ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥር-ዓት ለማዘጋጅት አቅዶ ለለበረዉን ዝግጅትና ታህሳስ 25 ቀን መድረክ በዚሁ አደባባይ ኢትዮጵያዉያንን ለማነጋገር ላቀደዉ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰበ የገዢዉ ፓርቲ የአዲስ አበባ ሃላፊዎች ፣ ሕገ መንገስቱን በመናድ ፍቃድ አለመስጠታቸዉ ይታወቃል።

በዚህ ምክንያት የሻማ ማብራቱ በአዲስ እበባ በክልሉ ባሉ የአንድነት ጽ/ቤቶች የተከናወነ ሲሆን፣ የመድረኩ ስብሰባ ግን ከላይ እንደዘገብነዉ በኮንቬሽን አዳራሽ እንዲደረግ ገዢዉ ፓርቲ ፍቃድ ሰጥቷል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በአቶ አንዱዓለም ድራጌ የአንድነት ፓርቲ ወጣት ዋና ጸሃፊ የተመራዉ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራርም በሆሳዕና ከተማ በአንድ ትልቅ ል ሆቴል አዳራሽ ከአባላትንና ከደጋፊዎች ጋር ሰፊ ዉይይት ማድረጉንም ዘጋቢዎቻችን ገለጹ። የሆቴሉ አዳራሽ የሞላ እንደነበረ የደረሰን ዜና ሲዘግብ የሕዝቡ ስሜት በጣም ከፍተኛና የጋለ እንደነበረም ለማወቅ ተችሏል።

በአካባቢዉ የነበሩ በብሄር ተደራጅተዉ የነበሩ ድርጅቶች ድርጅታቸዉ አክስመዉ በሕብረ ብሄራዊነትና በኢትዮጵያዊነት ጥላ ሥር ለመታገል ወደ አንድነት ፓርቲ በብዛት እየተቀላቀሉ እንደሆነ የገለጹት አቶ አንዱዓለም በተለይም የሆሳናዉን ስብሰባ አስመልክቶ ሲናገሩ «በሕዝቡ ይንጸባረቅ የነበረዉ ጠንካራ አቋምና ቁርጠኝነት በጣም የሚያስደስታን የሚያኮራ ነዉ» ሲሉ የአንድነት ፓርቲ ጠመንጃ ሳይታጠቅ በሰለጠነ ፖለቲካ ህዝቡን የማረከ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከሆሳእናዉ ስብሰባ በፊት በደቡብ ክልል የአንድነት ፓርቲ በአዋሳ በቅርቡ ሕዝቡን ማነጋገሩ ይታወሳል። በዚህ ስብሰባ ከገጠር ቀናት በእግራቸዉ ተጉዘዉ የመጡ ሁሉ ሳይቀሩ «ያቺ ጀግና ሴት የምትመራዉ ድርጅት አሳዩን» እያሉ በአንድነት ስብሰባ ብዙዎች መገነታቸዉን መዘገባችን ይታወሳል።

  1. Simabelewe
    | #1

    God bless Negasso and his family. Viva Ethiopian unity.

  2. Yikerbelen
    | #2

    well done UDJP. WELL DONE MEDEREK. WELL DONE d

  3. Yikerbelen
    | #3

    Ethiopia’s nationalism will win over the adwa’s narrow minded and foreign agents didvide and rule policy. well done UDJP, well done medereke. well done Dr Negasso. dele le ethiopia’s hizb mote le TPLF ena le ashikerochu [ MEAD AND LIDETU] AMEN

  4. DOWN WITH HODAM AND BANDA
    | #4

    WELL DONE UDJP. WELL DONE Dr negasso. down with TPLF and it’s servants like MEAD and lidetu.

  5. አንድነት
    | #5

    መድረክ ?

    መድረክ የጎሰኛ ስብስቡ ?

    ለመሆኑ አንድነት እና የተቀሩት መድረክ ውስጥ ያሉት ፓርቲዎች እንዴት ሊግባቡ ይችላሉ ?
    በጣም ታላቅ ልዩነት አላቸው, ማለትም የፓርቲያቸው ፕሮግራም በስየ ግፊት እስካልተቀየረ ድረስ
    ያም ልዩነት አንድነት ፀረ-ጎሰኝነት ሲሆን የተቀሩት የመድረክ አባል ፓርቲዎች ልክ እንደ ህወሃት ወይም ኢህአዴግ ጎሰኞች ናቸው
    ይህ ታላቅ ልዩነት ነው
    እና አንድነት ከሌሎች የመድረክ ፓርቲዎች ጋር ሆኖ የምርጫ ድምፅ ለማግኘት መስራቱ መራጩን ማታለል አይሆንም ?

    ይህን ታላቅ ልዩነት የሚያሳይ ፅሁፍ አቡጊዳ ለጥፏል
    http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2009/05/paper_-on_-medrek.pdf

  6. ባልቻ
    | #6

    Good job Dr.Negasso! God bless you and your family! Go UDJ !Damn TPLF!!

  7. ሞላ
    | #7

    ለአቶ አንድነት ዘረኝነት እስካሁንም ያለቀቀህ አንተው ነህ እንጂ መድረክ የጎስኞች ሳይሆን ሁሉንም ብህር ያቀፈቡድን ማለትና ጎሰኝነት የተለያዩ ስለሆነ በመድረክ ስም ዘረኝነት ለማራመድ አትሞክር በተረፈ በዘረኝነትየታወርውን አይንክን ክልማረህ ይውሰድህ መርዝህ ሌላውን ስለምበክል!!
    መድረክ የህዝብ አለኝታ ነው::

  8. ባልቻ
    | #8

    @አንድነት,
    እንዳንተ አይነት መሃይም እያለ የኢትዮጵያ ትንሳኤ እንዴት ሊፋጠን ይችላል?? ጠርብ መሃይም!

  9. ዎቻዮ
    | #9

    የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ይሄን ነው:ጎሰኝነት የትም አያደርስም: እኛም ደጋፊዎች የየራሳችንን ንጉስ ለማንግስ መታገላችንን ትተን ለአንድ ኢትዮጵያ ኢንታገል: አንዳንድ ተማርን ባዮችና የጎሳ ተጠሪ ነኝ የሚሉትን በሃያኛዉ ክፍለ ዘመን እንዳለን እናስረዳቸዉ:

    ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ!!::

  10. ግርማ
    | #10

    በአንድነት ስም ከላይ የጽኣፉት ወገኔ, ስምዎትን ቢቀይሩት ጥሩ ነበር:: አንድነትን የሚፈልግ ሰዉ በመድረክ መመስረት መደሰት ነበረበት:: አንድነት ማልት ልዩነቶች የሉም ማለት አይደለም::በአንድ ቤተሰብ ዉስጥ እራሱ ልዩነቶች አሉ:: በኢትዮጵያ የተለያዩ አስተሳሰቦች አሉ::ነገር ግን ዜጎች በልዩነታቸዉ ተከባብረዉና ተቻችለዉ በሚያስማማቸዉና አንድ በሚያደርጋቸዉ ጉዳዮች ላይ አብረዉ ሲሰሩ ያ “አንድነት” ይባላል::

    መድረኩ ዉስጥ ያሉ ድርጅቶች ብዙዎቹ ከአንድነት ጋር እንደዉም መዋሃድ የሚችሉ ናቸዉ::ጥቂቶቹ ወንድሜ በለጤፉት የአቡጊዳ ዘገባ ላይ እንዳለዉ ልዩነቶች ያሉዋቸዉ አሉ:: ነገር ግን እነዚህ ልዩነቶች ቢኖሩም ልዩነቶች የበለጠ እንዲጠቡ በመሥራት አሊያም ልዩነቶች እንዳሉ ተግባብቶ በመከባበር በሚያስማሙ ነገሮች ላይ በአንድነት መሥራቱ አይበጁም ?????

    ሌላ ደግሞ አንድ ነጥብ ላንሳሎት::የመድረኩ ሰነድ ወደ ስድሳ ማናምን ገጾች ነዉ:: እነዚያ ሁሉ የመድረክ ድርጅቶች የሚስማሙባቸዉን ነጥቦች የያዙ ገጾች ናቸዉ:: ያያሉ …. የሚስማሙበት እጅግ እጅግ በጣም ብዙ ነዉ:: ኢትዮጵያ አንድ መሆንዋን ይሳማማሉ:: ኢትዮጵያ የባህር ወደብ እንደሚያስፈልጋት ይስማማሉ:: መገንጠልን አጥብቀዉ ያቃወማሉ::በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አወቃቀር እንደሚያስፈልግ ይቀበላሉ::በኦትዮጵያ ሊበራል ዲሞክራሲን ይደግፋሉ ……

    እግዜር ይስጥላኝ

  11. ድር ቢአብር
    | #11

    ድል ለአንድነት ሀይሎች!!!
    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!

  12. ጋሻ መከታ
    | #12

    ተስፋችን በመድረክ (በተለይ በ UDJ) ላይ ነው:: የጠባብነት ካባ ጥለው የአንድነትን ካባ ለደረቡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ ስዬ አብርሃ ይበል ያሰኛል:: እባካችሁ ለአንድነት በተግባር እንስራ ጸጉር መሰንጠቁ ሓገራችንን አይጠቅምም::

  13. አንድነት
    | #13

    ሞላና ባልቻ,
    አይ የናንተ ነገር ምን አይነት ክብር የሌላችሁ ናችሁ
    ተቆጣችሁ አልተቆጣችሁ እኔ ግድ የለኝም
    እና እደግመዋለሁ,
    መድረክ ጎሰኛ ነው ከአንድነት በቀር
    ይህን ግልጽ ነገር ማየት የተሳነው ሰው ወይ እውር ነው አለያም አውቆ የተኛ ነው
    እላይ የተጻፈው ጽሁፍ ላይ መድረክ ጎሰኛ መሆኑ ቁልጭ ብሎ ሰፍሯል
    መድረክን (አንድነትን ሳይጨምር) ጎሰኛ ወይም ወያኔ2 የሚያስብለውም ልክ እንደ ወያኔ በጎሳ ላይ የተመሰረተ ክልሎች አላማው ስለሆነ ነው, ታዲያ ከወያኔ ልዩነቱ ምንድን ነው ?
    ወያኔ በስልጣን ላይ ነው
    መድረክ (ካለ አንድነት) ስልጣን ላይ መውጣት የሚፈልግ ነው
    እና ጤነኛ የሆነ ሰው ሁለቱ ከዚህ ሌላ ምንም ልዩነት የላቸውም ይላል

    እና ዋናው ጥያቄዬ መድረክ ውስጥ ያሉት ጎሰኞች አንድነትን መሃከላቸው እንዲኖር የፈለጉት መራጩን ሊያታልሉ አስበው ይሆን ነው
    ማለትም መራጩ አንድነትን በማየት ጎሰኛ ያልሆነውን የመረጠ መስሎት መድረክን ቢመርጥ እኮ ተታለለ ማለት ነው
    ሁላችንም እንደምናውቀው ጎሰኛ ፖርቲዎች በብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ የተጠሉ ናቸው,
    ስለዚህም ነው በ2005 ወያኔ እና የእንደነ መራራ ጉዲና ያሉት ጎሰኞች ፓርቲዎች የከሰሩት እና ጎሰኛ ያልሆነው ቅንጅት ያሸነፈው

    እና አንድነት ፓርቲ የሚመርጠውን ሰው ለማጭበርበር ባይሞክር ጥሩ ነው
    ይህንንም ማድረግ የሚችለው በእሱ እና በሌሎች መድረክ ውስጥ ባሉት ጎሰኛ ፓርቲዎች መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ ለመራጮች በማሳወቅ ነው
    በተለይ መድረክ እንደ አንድ ቡድን ሆኖ እጩዎቹን በስሙ የሚያሰልፍ ከሆነ ነው

    ለመድገም ያህል አንድነት እና ሌሎች መድረክ ውስጥ ያሉት ጎሰኛ ፓርቲዎች ያላቸው ታላቅ ልዩነት
    አንድነት የጎሳ ክልሎችን የሚቃወም በመሆኑእ
    እና ሌሎቹ መድረክ ያሉት የጎሳ ፓርቲዎች ልክ እንደ ወያኔ የጎሳ ክልልን የሚደግፉ በመሆናቸው
    ነው

    This is like if two groups were in kansas and one group wants to travel to new york the other group to los angeles, both groups can not sit in the same train !

  14. አለቱ
    | #14

    እኔስ ጥርጣሬየ ብዙ ነው ግን ተስፋ አልቆርጥም

  15. Anonymous
    | #15

    Yikerbelen :
    Ethiopia’s nationalism will win over the adwa’s narrow minded and foreign agents didvide and rule policy. well done UDJP, well done medereke. well done Dr Negasso. dele le ethiopia’s hizb mote le TPLF ena le ashikerochu [ MEAD AND LIDETU] AMEN

    @አለቱ

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።