የመኢአድ ደጋፊዎች ክፍፍል በፓልቶክ – ሕዝቅያስ ፍቅሬ

January 26th, 2010 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

በመሰረቱ ዛሬ በአገራችን የሚታየው በፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ያለው የመከፋፈል አባዜ በመኢአድ አመራሮች ውስጥ አለመታየቱ ምን ያህል በመሪዎቹ መሀከል ያለውን መተማመን ያመላክታል። ምን ያህልም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ መሆናቸውን ይገልፃል።

ይሁን እንጂ፤ በአገር ውስጥ ባሉት የመኢአድ አመራሮች ያልታየው ክፍፍል በ “ፓልቶክ” ተደራጅተው የመኢአድ ደጋፊዎች ነን በሚሉ ወገኖች መሀከል የሚታየው የእርስ በርስ ሽኩቻ ከግዜ ወደግዜ እየተባባሰ መምጣቱ አብዛኛውን ለመኢአድ ቀና አስተሳሰብ ያለውን ወገን እያሳሰበ ያለ ጉዳይ ነው። እነዚህ በፓልቶክ ተደራጅተው የመኢአድ ደጋፊዎች ነን የሚሉ ወገኖች አብዛኛዎቹ አሁን በቅርብ መኢአድ የወሰደውን የ “ምርጫ ስነምግባር” ስምምነት ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደግፋለን የሚሉም ናቸው። እንግዲህ እነኚህ በ “ፓልቶክ” ተደራጅተው የመኢአድን አቋም ካለምንም ማንገራገር እየደገፉ ያሉ ሰዎች፤ የመከፋፈላቸው መንስዔ ከምን የተነሳ ነው? የሚለው ሀሳብ ሁሌም በአህምሮዬ የሚንከባለል ሀሳብ ነው።

በመሰረቱ ዛሬ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፤ በአለም ላይ የተበታተነውን ወገናቸውን ለማሰባሰብ ሲሉ “ፓልቶክ” የሚባለውን ፈጣን የመገናኛ ማዕከል ሲጠቀሙ ይታያል። ይህም የመገናኛ ማዕከል ከምርጫ ዘጠና ሰባት ጀምሮ ሲያገለግል የነበረ ነው። የቅንጅት አመራሮች ቃሊቲ ታስረው በነበረበት ሰዓትም ከፍተኛ የዲፕሎማሲያዊና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። በዚህ የመገናኛ ብዙሀን በመደራጀትም ቆራጥ የኢትዮጵያ ልጆች ለህዝባቸው የሚደርስ የሚዲያ አገልግሎት አበርክተዋል።

ይህ እንዳለ ሆኖ፤ የገዢው መደብ ካድሬዎችም ይህንን የሚዲያ አገልግሎት በከፍተኛ ሁኔታ ሲጠቀሙበት ይታያል። የገዢው መደብ ካድሬዎች የሶሻል ክፍሎችን በመክፈት የወጣቱን አእምሮ ሲያጠምዱበት፤ የሀይማኖት ሰዎችን ደግሞ፤ የሀይማኖት ክፍሎችን በመክፈት አመለካከታቸውን ለማስቀየር ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። በዚህ አጋጣሚ ሳልገልፀው የማላልፈው ነገር ቢኖር፤ ሻቢያዎችም ይህንን ሚዲያ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። ሻቢያዎች ፓልቶክን የሚጠቀሙበት፤ ኢትዮጵያውያኖችን ለመሳደብ እና ለማዋረድ ነው። ሻቢያዎች ፓልቶክን የሚጠቀሙበት፤ በኢትዮጵያ ላይ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲነሳ ቅስቀሳ በማድረግ ነው። ሻቢያዎች ፓልቶክን የሚጠቀሙበት፤ በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ የተቃዋሚ መሪ እንዳይፈጠር ነው። ሻቢያዎች ፓልቶክን የሚጠቀሙበት፤ የተቃዋሚ ድርጅቶች ደጋፊ በመምሰል በኢትዮጵያውያኖች መሀከል ሰርጎ በመግባት፤ ከፍተኛ ክፍፍልን በመፍጠር ነው። በጥቅሉ ሻቢያዎች ፓልቶክን የሚጠቀሙበት፤ በመሪያቸው የተነገረውን “የመቶ አመት የቤት ስራ” ለመተግበር ነው።

ይህ እንዳለ ሆኖ ወደፍሬ ሀሳቤ ስመጣ፤ ፓልቶክ በከፊልም ቢሆን በውጭ ያለውን የመኢአድ ደጋፊ ለመከፋፈያ መንስዔ ሆኗል። ምክንያቱም፤ በፓልቶክ ላይ የሰዎችን ፖለቲካዊ አቋም ማወቅ ካለመቻልና፤ ከላይ እንደተገለጸው አንዳንድ ሀይሎች በፓልቶክ ውስጥ ደጋፊ በመምሰል የፖለቲካ ሀይሎችን በቀላሉ ሊከፋፍሉ ስለሚችሉ ነው። በእርግጥ ችግሩ ከአገር ቤት ተወክለው በመጡ አመራሮችም እንደሆነ ነው የሚነገረው። ከአንዳንድ ወገኖችም እንደምንሰማው ከሆነ፤ ከአገር ቤት ተወክለው የመጡት የተከበሩ አቶ አባይነህ ብርሀኑ ወገንተኝነት አሳይተዋል የሚል ነው። የተከበሩ አቶ አባይነህን ወገኝተኝነት ሲገልጹም፤ በእኛ ፓልቶክ ሲጋበዙ አልመጣም አሉ፤ ነገር ግን የሌላኛው ወገን ሲጋብዛቸው ይሄዳሉ የሚል ነው። ለግንዛቤ ያህል << እነኚህ፤ የአቶ አባይነህ ተቃዋሚዎች፤ ከቅርብ ግዜ በፊት መኢአድ ከፍተኛ የተቃውሞ ምት ሲገጥመው፤ ግንባር ቀደም ሆነው ድርጅቱን ሲከላከሉ የነበሩ ወገኖች ናቸው።>>
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ አቶ አባይነህ ብርሀኑ፤ የቅንጅት መሪዎች <<እሳቸውንም ጨምሮ>> ከመታሰራቸው በፊትም ሆነ በሁዋላ፤ በታማኝነት ድርጅታቸውን ያገለገሉ ታላቅ መሪ ናቸው። የተከበሩ አቶ አባይነህ ብርሀኑ፤ ኢንጅነር ሀይሉ ሻውል፤ ለህክምና ውጭ በቆዩበት ግዜ ውስጥ፤ የወያኔ ወከባና ዛቻ ሳይበግራቸው መኢአድን በውክልና ሲመሩ የቆዩ መሪ ናቸው። ቢሆንም ቅሉ፤ እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው አብይ ጉዳይ፤ አቶ አባይነህ ብርሀኑ ውጭ ከመጡ በሁዋላ ስህተት አልሰሩም ለማለት አይደለም። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ስህተት ሰርተው ሊሆን ይችላል። ወገኝተኝነትም ወስደው ሊሆን ይችላል። በነገሩ ላይ እርግጠኛ መሆን ባይቻልም። በእርግጥ እኔ ስህተት ነው ብዬ የማልፈው፤ የተፈጠረውን ልዩነት ገና ሳይሰፋ በፊት መድፈን ይችሉ ነበር የሚል ነው። ነገር ግን፤ እያንን አላደረጉም። `

ስለዚህ የመኢአድ አመራሮች፤ ነገሮች እየተባባሱ ከመሄዳቸው በፊት፤ ለጉዳዬ አስቸኳይ እልባት ሊሰጡ ይገባቸዋል። ምክንያቱም አኩራፊው ሀይል፤ ከዚህ በፊት ለመኢአድ ከፍተኛ እገዛ ያደርግ ስለነበረ ብሎም ነገሮች በመድበስበስ ከታለፉ ልዩነቶች ይመጣሉ ከሚል ስጋት ነው። ሌላው ደግሞ፤ የመኢአድ አመራሮች ሰዎችን ወደውጭ ከመላካቸው በፊት፤ ከአድልዎ እና ከወገንተኝነት የነጹ መሆናቸውን አጥንተው መላክ ይኖርባቸዋል። ይህ እንዳለ ሆኖ፤ የክፍፍሉ መንስዔ ፓልቶክ ሆኖም ከተገኘ፤ ከደጋፊዎች ጋር ያለውን ግንኙነት፤ ባቋቋሟቸው ቻፕተር ብቻ እንዲወስኑ ወገናዊ ምክሬን እለግሳለሁኝ። ችግሩንም ባቋቋሟቸው ቻፕተሮች በኩል፤ ባስቸኳይ ሊፈቱ ይገባቸዋል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ሕዝቅያስ ፍቅሬ
Agere_ethiopiaa@yahoo.com

  1. አለቱ
    | #1

    በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ አስተያየት ለመስጠት ባልችልም ሓሳብህና አነሳስህ ወጥ ለማቅጠን የምትሄድ ይመለኛል::በትክክል ጉዳዩ በሚመለከታቸው ክፍሎች የተነገረውን መግለጽ ሲገባህና በራሳቸው መረጃ መደግፍ ሳትችል በስማስማ ታጋዮችን መዝለፍና መካሪ መስሎ መቅረብ እራሱ ሻቢያነት መሆኑን አቶ ሕዝቅያስ ፍቅሬ የተገነዘቡት አይመስለኝም::

  2. milat
    | #2

    It is not in paltalk we consider ETH people.
    It is the people at home land we consider The people involve in Politics.
    You guys play on Computer you see AEUP win the coming election By the people with the people.
    Watch!!

  3. ለመለስ ንገረው
    | #3

    milat :It is not in paltalk we consider ETH people.It is the people at home land we consider The people involve in Politics.You guys play on Computer you see AEUP win the coming election By the people with the people.Watch!!

    Don’t waste your time. We know what we do.

  4. ለመለስ ንገረው
    | #4

    የድርጅቱ ደጋፊ ከሆኑ በድርጅቱ ድህረ-ገጽ ላይ አስተያየት መስጠት ይችላልሁ:: ከዚያ ውጭ ለኛ ምንም ጥቅም አይሰጥም ጽሁፍዎ::ምክንያቱም ስለድርጅቱ ውስጣዊ ችግር ሊያወያየን የሚችል መረጃ የለንምና! ድርጅቱ ይጨነቅበት:: እዚህ መነጋገር የምንችለው በአጠቃላይ ጉዳዮች ላይ እንጂ ስለአንዳንዱ ተቃዋሚ ተብየእ አይደለም::

  5. Sekokaw Beza
    | #5

    አቶ ሕዝቅያስ ቁም ነገር ገና በመጀመሪያው አረፍተነግርዎት ስለተናገሩ በዚያው ቢያበቅ ጥሩ ነበር ዋናው እኮ አመራሩ ካልተከፋፈለ ውጢእት ሊመጣ ይችላል ፓልቶክ ላይ እኮ የርሶ መሰሉም የሚአሓድ ደጋፊ ነኝ ብሎ ሊያወራ ይችላል እባክዎ ሕዝቡን አይከፋፍሉት አርፈው ቢቀመጡ ጥሩ ነበር ልድገመውና አመራሩ ካልትከፋፈለ በቂ ነው አመሰግናላሁ

  6. ናደዉ አስማማው
    | #6

    ለምን ይህን ያህል አሳሰበህ !!! ሁሉም ሆዳም ናቸዉ::

  7. jeru
    | #7

    milat yes, after a copel of whisky i have the same openion with u. haha a, aeup win hahaaa..what a dream!!or ቅኽ ት
    ful me once shame on u ful me twice shame on ME!!

  8. ዕያሱ
    | #8

    አቶ ሂስክያስ ሚን አለፋ አለፋህ ትንበሪካኪዎችህ ናችሁ ለዎያነ አድራችህዋል ብካ ኩቲር ሁለት ዎያነ

  9. Down with all hodam bandas
    | #9

    AEUP’s supporters divided in paltalk !!!!!!!!!!!! kkkkkkkkkkkkkkkkkkk Of course AEUP’s “leadership” can not be splited because they have one strong leader that is melese zenawi. Melese considers hailu as his baby sitter. whqat melese says to Hailu he will do it. IN the first place , Hailu did not send Shaleqa abayihen berhanu to USA. Melese sent shaleqa abayihen berhanu as melese sent shaleqa admase to divide ethiopians in diaspora. Secondly, Hailu assigned Shaleqa Abayihen Berhanu not as AEUP’s leader, but as CUDP’s leader. Your bower hailu has never been against TPLF, he was the first to sumitt work application for

  10. Down with all hodam bandas
    | #10

    Ofcourse the” AEUP’ Can not split because it has a very strong leader behind, that is melese zenawi. Hailu is melese’s baby sitter. What melese tells him , he will do with out forwarding any question. LOOK all what hailu has done since he was in qality by mistake untill now. Melese has arranged a publice meeting in mekele, Hailu was there. What is very interesting here, when the former Tgeray’s president and the current arena’s leader geberu asrat had a publice meeting in tegeray, the same question raised to gebru from the people. 1. why do you work with dergs , CUDP and nefetegnas?, but when the derg agriculture minister, EWP’s member . and CUDP leader hailu shawul had a meeting in mekele, you can not hear such a question from the publice, because Hailu is running from one corner to another 1. to save TPLF .2. To work with TPLF and give ethiopia’s fertile land to sudan .3. To loott ethiopia together. 4. to keep the aparthied system in ethiopia[ oneminority ethnice group over others] 5. To share TPLF crime against all ethiopians.6. to keep divide and rule TPLF’s policy in ethiopia.7.To arrange preconditions for the creation of greater tegeray by lootting an Amharas land from gonder and wollo by displacing Amharas farmers. When hailu shawul bowed and shocked melese hand, he should know that he has shared all the evil doing of melese from dedebit untill now including a merciless killing of prof asrat. What is very interesting, AAPO was founded to stop the killing of innocent Amharas farmers in different parts of ethiopia. Those who were accusing TPLF for the killingt of their families members , brothers, sisters and others , now they are supporting Hailu’s dinning with bereket and melese shamelessly. WHEN those who are from the majorities are bowing to the minorities, that is the end of a history. But those who are dancing with hailu should know that melese killed prof asrat ,but they are killing prof asrat’s goal. if prof asrat refused to bows for melese and work with him for the destruction of ethiopia that is why melese killed him. IN spite of the fact that AAPO founded by genuine ethiopians to save the brothers, sisters . mother, fathers and other families’s members of the current Hailu’s supporters, these hodams are giving their back to us when TPLF gives the fertile land of ethiopia in gonder. Finally, Hailu shawul did not send shaleqa abayihen berhanu. As melese sent shaleqa admasse, melese did shaleqa Abayihen berhanu to divide ethiopians in diaspora. almost all in all those who claim them selves as a leaders of AEUP were well known derg’s criminals, for that reason they are the hostages of TPLF.IF they refuse to work for TPLF, it will send them in qality for their crimes which they had commiitted during derg’s era. So AEUP is another mini TPLF’s branch in shoa. AEUP is not only mini TPLF’s branch in shoa, but also it has one common thing with TPLF. TPLF from tegeray= adwa and it sounds like a families club , AEUP from shoa , and the same families club from one village. Just check all the so called AEUP’s supporters, they are all from shoa [ particularly from hailu’s village. what is good at the end of the tonneel there is a light always and we will find all hodams one by one at the end of the day. GOD bless ethiopia amen. down with bandas and hodams. amen

  11. Abiy Ethiopiawe
    | #11

    Hesikias,
    It is a good article to show the truth in political view,but it is a matter of meaning.Weyanee can’t and will not understand you try in the other way like this.

    ትርጁማን ፈልጉ!!!
    አዋጅ! አዋጅ !አዋጅ!፤
    ለኢትዮጵያ የሚበጅ።
    የሰማም ላልሰማ፤
    ያልሰማም እንዲሰማ።
    መፍትሄ ነውና ለአገር ‘ምትጓጉ
    የሾህ ፊደል የሚያውቅ ትርጁማን ፈልጉ።
    የጉምዝ የሽናሻ የኮንሶ የሌላም፤
    የትግሬ የኦሮሞ በፍጹም አይደለም።
    የወያኔን ቋንቋ ገልብጦ የሚያጠና፤
    ባለሙያ ሆኖ አለሁ የሚል ጀግና።
    ፈልጉላት ዛሬ፤
    ለውዲቱ አገሬ።
    ሕዝቡማ ለአንድነት ይሞታል ላገሩ፤
    ለሰንደቅ-ዓላማ ለነፃነት ክብሩ።
    ኢትዮጵያዬ እያለ ላብ ደሙን አፍስሦ፤
    በዲሞክራሲ ሥም ከአፈናው ተንፍሶ፤
    መገንጠልን ሲያወግዝ ዘረኝነትን ሲያጥላላ፤
    በተስፋ ኑሮውን ቋጥሮ ጊዜውን
    በትዕግስት ሲያሰላ
    ወያኔዎቹ ሳቁበት ተንከተከቱ በአገሩ፤
    መገንጠልን እያጋቱት ዘረኝነት እየዘሩ።
    እኮ ምንድን ይባላል ትርጉሙ?
    በየአደባባይ ሲደፉት ከንቱ ሊቀር ደሙ።
    የሕዝብ ሕሊና ሲሸረሽሩ፤
    እስከመቼ ነው እሽሩሩ???
    እየተገፋን በችግሩ፤
    በሞት ሰቀቀን ማደሩ።
    እናም የወያኔን ቋንቋውን ያጠና፤
    እያስተረጎመ የሚያስተምር ጀግና።
    መፍትሔ ነውና ላገር የምትጓጉ፤
    የሾህ-ፊደል የሚያውቅ ትርጁማን ፈልጉ።
    ቀን በየመድረኩ ተናግሮ አናጋሪን፤
    ለወያኔ ያደረ ሲመሽ አማካሪን።
    እያርበደበደች ቀንዱን የምትመታ፤
    ኩሩዋ ኢትዮጵያዊት ልቧ ‘ማይረታ፤
    ቅን ልቧ ሲሰበር፤
    ግንባሯ ‘ሚቋጠር።
    ለሆዱም ያደረውን፤
    አይታ የማትምረውን።
    ቋንቋዎች የምታውቅ ተርጓሚ ናት እሷ፤
    ወኔ-ቢስ ያልሆነች ሱሪ ነው ቀሚሷ።
    መፍትሔ ናትና ላገር የምትጓጉ፤
    በቃኝ ለእኔ ‘ምትል ትርጁማን ፈልጉ።
    አፈላልጓት ዛሬ፤
    ለኢትዮጵያ አገሬ።
    ምሁራንም ቢሆን ውይይቱ ይብቃ፤
    ዘመኑ ተቆጥሯል ሕዝብ’ኮ ከነቃ።
    መሳሪያ አትሁኑ ሂዱ ወደ ሙያችሁ፤
    የወያኔ ቋንቋ መቼም አይገባችሁ።
    አስራስምንት ዓመት ስትከራከሩ፤
    ኑሮ እየሞተ ምጥ ሆኗል ችግሩ።
    በሕዝብ ደም መፍሰስ ዕድሜ ስትገብሩ፤
    በሠላም ሥም ሐቁን ይብቃና ቅበሩ።
    ዛሬም አታበቁም?
    መራር ሕዝብ አትውቁም???
    ዲሞክራሲውን አይታችኋል፤ሕጉንም በባዕዳን አፅፈው፤
    በማን አለብኝ ሲመርሹ ጠመንጃቸውን ታቅፈው።
    በአፈ-ሙዝ ተንጠልጥለው ቁልቁል እያዩት ሕዝቡን፤
    በዚህ አንቀፅ ተነዳ ሲሉት፤ሲያመለክቱት ደንቡን።
    ትዕቢቱ ባጥንት ቆዝሯቸው፤
    ካለኛ ሲሉ ማን ነካቸው???
    ይልቅ ልብ በሉ፤
    የቋንቋ ሆኗል ትግሉ።
    የኦሮሞ የአማራ የጉራጌ የሌላም፤
    ባጠቃላይ የብሔሮች ክቡር ቋንቋም አይደለም።
    የወያኔን ቋንቋ በደሙ ያጠና፤
    እኔስ በቃኝ የሚል በሾህ ነቃይ ጀግና።
    መፍትሔ ነውና ለአገር የምትጓጉ፤
    የሾህ ፊደል የሚያውቅ፤
    ትርጁማን ፈልጉ።

  12. ቴወድሮስ
    | #12

    ሲለዚሂ ነገር እነሱ በደኒብ ቢዎያዩበት በጥኣም ጥሩ ነዉ እላለሁ

  13. Down with all hodam bandas
    | #13

    Dear hesikias, would you tell us which paltalk rooms are hailu’s supporters? But do not include swiss kinjit and diaspora . they are typical weyanes’ rooms . they are not divided , but they are spreading lies over lies,spreading misinformation among ethiopians are their job. we are going to post all the names of the so called hailu’s supportters.because these people will be equally responsible for the suffering of ethiopia’s people, the giving away of ethiopia’s land to sudan , the destruction of kinijit and other crimes which TPLF has committed. bowing for TPLF is a crime by it self. Dinning with melese and bereket is a crime by it self because these two criminals are responsible for the disappreance of millions of AMharas since they are in menilik’s palace illegally.The so called Hailu’s supporters are the killers of prof asrat’s goal and his saccrifice in his life for the unity of ethiopia and ethiopians. Prof asrat refused to bow for TPLF and work with TPLF to destroy ethiopia and ethiopia’s nationalism. for that reason the tegers’ criminals revenged by locking him in one small room . Those who claimed them selves as the main followers of prof asrat , now they are telling us that the dinning of hailu with melese and bereket in menilik’s palace like GOD’s blessing, even they are trying to tell us that melese and bereket decided to dinning with hailu because TPLF’s mini-branch in shoa ” AEUP” forced THEM TO DO SO. It is a sham of the year when the former BADM members abandoned TPLF and joined the armed struggle in defence of ethiopia’S LAND FROM GONDER UNTILL GEMEBELLAS, Our ” AEUP” doesn’t have any problem about TPLF’s land giving to sudan. Most of “AEUP’ members are the hostage of their crime which they had committed during derg for 17 years as a head of EWP’s seceratray in different parts of ethiopia.

  14. Down with all hodam bandas
    | #14

    well done debereberhan’s heroes. The hidden TPLF’s agent [ Hailu's ]car is being smashed in deberberhan after returning from mekele,

  15. Down with all hodam bandas
    | #15

    hodams will never escape from ethiopia’s people muscle and they will be ssmashed at the end of the day like hailu’s car.

  16. አንበሴ
    | #16

    መኢአድ ማለት የወያኔ ዋናው አጃቢ ነውና የነቃ ዘግቶዋቸው ለፍትህ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ከሚታገሉት ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ጋር መሰለፍ እውነተኛ አማራጭ ነውና ከልብ ያስቡበት::

  17. death to surrenders
    | #17

    In a normal procedure there could be a surnders in the battle field. But AEUP which made in TPLF’s Fabrice has never been in the battle field after prof asrat’s imprisonment. According to prof Tecola’s witness, Hailu shawul was in Tecola’s office after the downfall of hailu’s ex boss [ mengistu] and told tecola that he wants to work with TPLF, but Tecola did give him any attention at that time , but weyanes gave him long time home work around AAPO, and later AEUP and now he is doing his job in support of TPLF against the wish of ethiopia’s people for freedom and democracy. Hailu is one of the killers of CUDP again in support of TPLF against the wish of our innocent people. He must grab more wealths from the throat of poor ethiopia’s ppl. ye abateh bere sizeref abereh zeref newu negeru. The question is here, why did others decide to surrender for TPLF at this crucial time? IS not TPLF which is directly responsible for the disappreance of millions of innocent Amharas all party of ethiopia?

  18. ዛሬ ነው
    | #18

    ኤርትራም አገሬ ሱማሌም አገሬ
    ማደርያ አልጣም እኔ ዞሬ ዞሬ
    ኢትዮጵያዊ ነኝ ጥቁር’ነት ነው ዘሬ
    ስራ’አጥም ሁን አረ ወዝአደሬ
    ታጠቅ ተማሪ ተነሳ ገበሬ
    ነገን ስትጠብቅ እንዳትሞት ዛሬ

  19. አቶ እስኪያስ ፍኪረ
    | #19

    አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ ነዉና ነገሩ ማንነትዎትን ለማወክ ያስችግራል መጀመሪይ የት ላይ እንደኮሙ ያስተዋሉ አይመስለግም እራስወን ያሳዉኩ

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።