የኢፕርድፍ ልዑካኖች፦ ብዙ ጥያቅዮችን ይዘው ተመለሱ – በዘውገ ፋንታ (ስያትል)

April 23rd, 2010 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

መግብያ

እሑድ ምያዝያ 18 የኢትዮጵያ ገዥ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በስያትል ተገኝተው፣ “ከባንክ የተቀመጠ ዕንቁ” ካሏቸው የኢትዮጵያ ወገኖች ጋር የኢትዮጵያን አስከፊ ሁናቴ አስመልክቶ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። መልስ ያልተገኘላቸውን ብዙ ጥያቄዎች ልዕካኖቹ ወደ ሀገራችን ይዘው ተመልሰዋል። ትዝብትን ያተረፈ ንግግር ግን ተንጸባርቋል። በጣም ሳይጋነን የምትታወስ ትንሽ የታሪክ ቀን ነበረች ማለት ይቻላል።

ዱሮ በወያኔዎች በሚዘጋጅ ስብስብ ላይ ተግተልትሎ ይመጣ የነበረው የትግራይ ክፍለ ሀገር ተወላጅ በዚህ ስብሰባ አልተገኘም። ጠ/ም መለስ ዘናዊን አኩርፈው ወይም በወረት ወደ ሰየ አብርሃና ገብሩ አስራት የፖለቲካ ጎራ ዘው ብለዋል። አለበለዚይ ሠርግ አለብኝ ብሎ የማይቀረው ሀገር ወዳድ ጀግና ሁሉ አልታየም። በተጨማሪም፣ በተቀዋሚው ጎራ በሰላም ትግል ለዲሞክራሲ ለውጥ ቀልጣፋ አርበኞች የነበሩት ለግላጋ የትጎሉ ጀነራሎችም አልታዩም። ስለዚህ አዳራሹና ቃየው ጭር ያለ መሆኑ በወሬ መካከል ተነስቷል። እንደሚመስለው የጊዜው የፖለቲካ ቀዛፊዎችና ተከታዮች ያተኮሩት በየከተማው ለሚዞሩት ለክቡር ነጋሶ፣ ግዛቸው፣ ሰየና ገብሩ ወዘተ አቀባበል እንደሆነ ታውቋል። ቁጥራቸው ከሃምሳ የማይበልጥ በድብቅ ከተዘጋጀው ስብስብ ተገኝተው ከልዑካኖቹ ጋር አንዳንድ ጊዜ በመፋጠጥ፣ ሌላም ጊዜ በመገረም እኽ! እንዴ! እያሉ ሰዐቶቹ አለፋዋል።

ውይይቱ በሰላም ተካሂዷል። ልዑካኖቹ በዚህ ዲሞክራሳዊ ሥርዐትና ባሕል ተማርከው እንደተመለሱ አይጠረጠርም። ስለሆነም፣ ያዩትን የዲሞክራሲ ጸባይ ለማይበገሩት ጠ/ም መለስ ያስረዳሉ የሚል ተስፋ አለ። የዚህ ስብስብ ፍሬ ይኼ ብቻ ነው። ዳሩ ግን ስብሰባው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በሰላም ተካኼደ እንዳይባል፣ ካድሬው መኮንን ካሳ በስብስቡ ወቅት ያስነሳውን ቀውስ መጥቀሱ ተገቢ ነው። በአሜሪካ/ስያትል የወያኔው ዋና ተጠሪ መኮንን ካሳ በአኳኋኑ በር ጠባቂ ወይም የሴኩሪቲ ኃላፊ ይመስል ነበር። ይህንን ምግባሩን አላግባብ በመጠቀም አንዱን ተጋባዥ (አድማጭ) “ጥያቄ አትጠይቅም፣ ቁጭ በል!” በማለት በኃይለ ቃልና ትዕዛዝ በመናገሩ የከረረ እንካስላንቴ ተጀመረ። የመኮንን ካሳ ገጽ ደም የሚያፈላ ይመስላል፣ ሌሎች ሰዎች ተጨመሩበትና ስድቡ ስለተፋፋመ ውይይቱ ቆመ። ይኼም ጸሐፊ በር በሩን መመልከት ጀምሮ ነበር። ከልዕኳኖቹ መካከል አንዱ የተባረከ መኮንን ካሳን ከቦታው ስላስገለለው ውይይቱ በሰላም ቀጥሏል።

ውይይቱ ሰፊ ጥያቄዎች የተሰነዘሩበት ነበር። ልዑካኖቹም ሁሉንም ጥያቄ መልሰዋል። ዳሩ ግን ለአስራ ዘጠኝ ዓመቶች አጥብቆ የሚያውቀውንና የተረዳውን ሕዝብ “የምትሉት ውሸት ነው” በማለት ለማሳመን ልዑካኖቹ ያደረጉት ጥረት ከንቱ ሆኗል። ታሪክ በንግግር ሊቀየር የሚቻል ቢሆን፣ የልዑካኖቹ ሙከራ በቀየረው ነበር። ጥያቄው ሲከር፣ ከመልስ ይልቅ አንድ ሰው ኢትዮጵያን በአይኑ ካላየ ለማመን እንደማይቻል ተጠቁሟል። የ”ባንኩ ዕንቁ” የተባለው ወገን በናት ሀገሩ ላይ ያለውን አስጊና አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ከባድ ጥያቄዎች ማቅረቡና ውሸት ፕሮፓጋንዳ አልቀበልም ማለቱ፣ ለሀገሩ ያለው ፍቅርና ናፍቆት አገሩን በቅርቡ በዐይኑ በማየቱና ባለማየቱ አንጻር ስለተመዘነ ይኼንን ጸሐፊ ጭምር አስቀይሟል። የወያኔ አገዛዝ ፍልስፍናና ምግባር ጥያቄዎችን ፈጥሮ እንጂ መልስን ወልዶ አያውቅም። ልዑካኖቹ እንኳን ስያትል መጥተው አይተውን ሄዱ። ከውይይት በኋላ ጨዋታና ግብዣ አልነበረም፣ በወያኔ ዘመን ኑሮም አያውቅም። በሽሽግ ግብዣ የሚያደርጉላቸው ካድሬዎቻቸው መጨረሻውን አላሳመሩላቸውም። የስብሰባው መልካም ውጤት ልዕካኖቹ መጥተው ተናግረው መመለሳቸው ብቻ ነው።

የልዑካኖቹ የጉዞ አላማ

የኢፕርድፍ (EPRDF)ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ጉብኝት ምክንያት የአስራ ዘጠኝ ዓመታት ውጤታማ ስራቸውን በውጭ ላለው የኢትዮጵያ ወገን የማያውቅ ካለ ለመግለጽ እንደሆነ ታውቋል። ከፍተኛ ባለሥልጣኖች የተላኩበት ምክንያት፣ ወያኔ በሚመጣው ምርጫ ከሥልጣን እንዳይወርድ ባይሰጋም፣ የደነገጠ ስለሆነ ከምርጫው በኋላ ለሚሆነው ደጋፊ ነፍስ ለመፈለግ ይመስላል። ዳሩ ግን፣ ከሰፊው ስደተኛ ሕዝብ የፖለቲካ አካል ከሆነው፣ ከፊሉ ለመላው ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲና ኢዲፓ፣ ሌላው ለመድረክ፣ የቀረው ደግሞ በሁለገቡ ፖለቲካ ድርድር የተከተተ ስለሆነ፣ የወያኔው መንግሥት እንደለመደው ደልሎ እንኳን የሚወስደው የተረፈ ነፍስ የለም። ወያኔ በሀገር ውስጥ ከሕዝቡና ከተቀዋሚው ፓርቲዎች ጋር በሰራው ኃጢያቱ ላይ እየተከራከረና እየተፋተገ ሳለ፣ በሀገር ውጭ ደግሞ፣ የመድረኩ ክቡር ነጋሶ ጊዳዳና፡ ሰየ፣ ገብሩ፣ ግዛቸው ወዘተ የገንዘብ ዕርዳታና የፖለቲካ ድጋፍ ከሚሰበስቡት ጋር ለመሻማት ፈልጎ፣ በውጭም መቦጫጨቅን አትርፏል። የመድረክ ልዑካኖች የወያኔን ሰፊ የጥፋት ጉዞ እኛም ነበርንበትና አጥብቀን እናውቀዋለን እያሉ፣ ስለ ዲሞክራሲ መዳኽና መንፏቀቅ፣ ስለ ኢኮኖሚው መንጎዳጎድ፣ በቋንቋ ልዩነት ላይ ስለተመሰረተው ፌደራሊዝም ቅጠወጥነትና አደገኛ ሂደት፣ ስለ ምርጫው ሰለባዎች፣ ለሱዳንና ለሌላ ሀገሮች ስለተዳረጉት የኢትዮጵያ አድማስ ምድርና ወደብ፤ በግፍ ያለፍርድ ስለታሰረውና ስለተገደለው “አትንኩን፣ አትግፉን እናወጣዋለን” እያሉ የአዲስ አበባን ወያኔ መሪ እያጋለጡ ይገኛሉ። እነዚህን የውስጥ አዋቂዎች ለመስማት የዱሮ ወያኔዎች ሩጫቸውን ወደዚያ አዳራሾች አድርገዋል። መለስን የከዳው ወይም የሸሸው ካድሬ አሁን ሠንጋም ቢጣልለት ወይም ሄክታር መሬት ቢመራ ከአዲስ አበባ ከመጡት ባለስልጣኖች ስብስብ መራቃቸው መለስ ዘናዊ የሚመራው የወያኔ መንግሥት ያበቃለት መሆኑን ያሳያል። የዚህን ሥርዓተ ግባት ለማሳየት ይች ጽሑፍ ባጭሩ ቀርባለች።

ፕሮፓጋንዳዎችና የሀገር ጉዳዮች ጥያቄዎች

ልዑካኖቹ ንግግራቸውን ጀምረው በየተራ ስያቀርቡ ተጋባዡ ሳይሰለች ጥያቄውን በልቡ እያሰላሰለ ፕሮፓጋንዳውን ረግቶ አዳምጧል። ልዕካኖቹ ስለ ከተማዎች መስፋፋት፣ ብዙ የአውራ ጎዳናዎች መዘርጋት፣ ስለ ኤሌክትሪክ መስፋፋትና ከኩራዝ ወደ አምፖል ዘመን መሸጋገር፣ ስለ ትምሕርትና ጤና አገልግሎት መዳበርና ሐኪም ከማያስፈልግበት ደረጃ መደረሱን፣ በኢኮኖሚ መዳበር ኢትዮጵያ ከዓለም ታዳጊ ሀገሮች የሚነጻጸር የዕድገት ርምጃ ማሳየቷን በቁጥር አማካይነት አኩሪ ኢትዮጵያን አድምቀው አስቀምጠዋታል። እኽኽ! እያለ እየተንቆጠቆጠ ያዳመጠው ወገን ትዕግስቱ ስላላለቀ፣ የተረጋጉት ልዑካኖቹ በመቀጠል ስለ ፍትሕና ዲሞክራሲ ከውጩ ከሰለጠነው ዓለም ጋር እያወዳደሩ አስቀመጡት። የጥያቄ ጊዜ እንዲጀምር በአዳማጩ መሰልቸትና መለዋወስ ምልክት ንግግሩ ተቋጭቶ ሞቅ ወደአለው ወደ ጥያቄና አስተያየት ጊዜ ተገባ። በዚህ ወቅት ነው የወያኔው ልዑካኖች ከተሰበሰበው ወገን ጋር ሆድና ጀርባ መሆናቸው የተረዱት።

አነድ ጠያቂ በጋለ መንፈስ ስለ ጋምቤላ ሕዝብ ጭፍጨፋና አሁንም በእስር ቤት ስለሚሟቅቁት የፖለቲካ እስረኞች ስም እየጠራ ቅንጣት የዲሞክራሲ አሰራር በወያኔ አገዛዝ እንደሌለ በመግለጽ፣ ይኼ ዓለም ያወቀው የሰባዊ መብት ገፈፋ ስለሆነ ወያኔ ከዓለም ሕብረተሰብ ህሊና ውጭ እስከመቸ ድረስ ሊቆይ ያስባል ሲል ተገርሞ ጠየቀ። ሌላው ደግሞ በየክፍለ ሀገሩ የተገደሉትንና የታሰሩትን እንደ ዳኛ ብርቱካን መደቅሳን ጨምሮ በመጥቀስ አሉ የተባሉት የዓለም ሰብዐዊ መብት ጠባቂና ተመልካቾች የወያኔውን መንግሥት ያወገዙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ በአምባገነንነት ቢገዙም አንድ ቀን ተጠያቂነት እንደሚመጣባቸው እያመለከተ ልዑካኖቹ ምን መልስ እንዳላቸው ጠየቀ። ልዑካኖቹ በየተራ በመናገር፣ በጥያቄ የቀረበው ሁሉ ሀሰት ነው አሉ። ልዕካኖቹ ለመናዘዝ ወይም ጥፋቱን አምነው ይቅር ለማለት መጡ የሚለው ፈጽሞ የማይተሰብ ሃሳብ ነው። ከአቋማቸው ፈንከች ሳይሉ፣ የፖለቲካ እስረኛ በኢትዮጵያ እንደሌለና ዳኛ ብርቱካንም በወንጀል ስራ የታሰረች መሆኗን ጠቅሰው ታሪኩን ተናገሩ። የዘነጉት ነገር ግን በቅርቡ የተቀዋሚው መኢአዲ ፓርቲ ከሁለት መቶ በላይ የሆኑትን በእስር ቤት ያሉትን የፖለቲካ እስረኞች ማስፈታቱና በሺ የሚቆጠሩ አሁን በእስር ቤት እንደሚገኙ እነሱንም ለማስፈታት እየታገሉ መሆናቸውን ነው። መቸም ዕውነትን መቀበልና ማመን እንደ ኃጢአት የሚቆጥር እንደ ወያኔ ያለ መንግሥት በዓለም የለም። ይኽ ባህል በሰራተኞቹ ሁሉ ደም ስር ገብቷል። የአገዛዙ ስልት ሆኗል። በዚሁ የተነሳ፣ ዱሮም ባይኖር፣ በልዑካኖቹና በአድማጩ መካከል መተማመንና መግባባት ጠፋ።

ሌላው ጠያቂ ይኽ የወያኔ መንግሥት ኢትዮጵያውያንን በአገር ውስጥም በውጩም ዓለም እያዋረደ መሆኑን እና ታሪካችንንና ክብራችን እያወደመ መሆኑን በምሳሌ አድርጎ ገለጸ። በተለይ የወያኔ ካድሬ ሁሉ የገንዘብ ፍቅሩ ጣራ የሌለው መሆኑንና በዚሁም ምክንያት ለምንም ያልበቁ ሴቶችን በገንዘብ እንደ በግ እየሸጡ በአርብ ሀገሮች በውርደት የሚኖሩት ሰቀቀኑንና ውርደቱን አልችል እያሉ እራሳቸውን የገደሉትን እየጠቀሰ አሁንም የወያኒው መንግሥት US$14,000 በራስ እየተቀበለ በህፃን የሚነግድ አረመኔ መሆኑን በተጨበተ ማስረጃ አስረዳ። በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዚህ ጉዳይ ክፍል ሀላፊ ነኝ ያሉት ከልዑካኖቹ አንዱ ለዚህ ጥያቄ መልስ ሲሰጡ አንድ ሰው ወደ አረቦች አገር ለስራ ልሂድ ሲል ሁሉን ካሟላ አትሄጂም/አትሄድም ለማለት በህግ የማይቻል ነው አሉ። ድርጊታቸውንም ከአሜሪካና ሌሎች ሀገሮች ህግና ስራ ጋር አነጻጽረውታል። ይኼን የህፃን ልጅ ሽያጭ የሀገር ጠንቅነቱንና አደጋውን የሚያውቅና የሚረዳ ሌላ መንግሥት እንጂ ወያኔ እንዳልሆነ ግልጽ ሆኗል።

አንድ ጠያቂ ወያኔ እራሱን ከአጼ ሐይለሥላሴና ደርግ ጋር እያወዳደረ ይኼን አሻሽያለሁ ይላል። ዳሩ ግን ኢትዮጵያ በሁሉ ረገድ ወደ ኋላ እንጂ ወደፊት እየሄደች አለመሆኗን ገልጾ፣ በድህነት ወደ ኋላ፣ በዲሞክራሲና በሰው መብት ወደ ኋላ፣ በሽታና ችግር ያጠቃት የምጽዋት ሀገር እየተባለች መሆኗን ወገንም የውጩም ዓለም አምኖ የተቀበለውን እንዴት ብላችሁ የደኽየችውን ኢትዮጵያን ከዳበሩት ሀገሮች ግስጋሴ ጋር ታነጻጽራላችሁ ብሎ ጠየቀ። የተሰጠው መልስ ኢትዮጵያን ሂዶ ስላላየ ለማመን መመዘኛውን ቁጥር ለመቀበል እንደሚያዳግተው ተነገረው። ምናልባት እነሱም የዲሞክራሲን ጉዳይ ለማወቅ የብልጽግናን ሂደት ለማየት አሜሪካና አውሮፓ መጥተው ስላላዩ ነው ብሎ በሰጡት ምሳሌ መገመት ይቻላል። በ19 ዓመቶች የሰሩትን ማድነቃቸው በ5 ዓመቶች የኢትዮጵያኖች ሰፊ ጉልበትና የኢትዮጵያ በርካታ ሀብት ምን ሊያሰራና ከምን ብልጻጌ ደረጃ ሊያደርስ እንደሚችል ፈጽሞ ሊያውቁትና ሊረዱት ባለመቻላቸው ስለሆነ መሆኑ ዕውቅ ነው። አዲስ መንግሥት ሲቋቋም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ሲመሰረት፣ ድህነት ሲጠፋና ብልጽግና ሲስፋፋ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተደስቶ መኖር ሲጀምር ለማየት ሁላቸውንም ሌላ ሃያ ዓመት ያኑራቸው ማለቱ ተገቢ ነው።

ሌላው ወገን በእስላሞቹ ኢትዮጵያኖች ላይ የሚደርሰውን በደል ከነማስረጃው ተንትኖ በማቅረብ፣ ለምን የኢሀደግ መንግሥት ሆነ ብሎ በወገኖች መካከል ጠብ እንደሚጭርና አንዱ ዜጋ ሌላውን በኃይማኖትና ጎሳ እንዲጠላላ እና በደል እንዲፈጽም ያደርጋል? ለምንስ እራሱ ሰው እየላከ ግጭት እየፈጠረ በሌላ እያሳበበ የባሰ ግጭትና በደል እንዲፈጸም ያደርጋል? በማለት ጠይቆ፣ የተፈጸመው ግድያ የወያኒ እጅ እንዳለበት የተረጋገጠ ስለሆነ ኃላፊነት መውሰድ አለባችሁ ሲል አሳሰበ። እንደተለመደው መንግሥት ይህንን ዕክል የማይፈጽም እንደውም የሚከላከል መሆኑን በመግለጽ፣ ኃጢአቱን በሌሎች ላይ ወይም በሞተ ሰው ላይ ማውረስ የተለመደ ዘዴ ሆኗል።

ሌላው በወያኔው መንግሥት ኢትዮጵያ ወደብ ማጣቷን፣ የአድማስ ምድሯን መቀማቷን፣ ሕዝቦቿ መሰደዳቸውን፣ የደንና የእርሻ ለም መሬቷ እየተመረጠ ለባዕድ ሀገሮች መሸጡን፣ ሀገሪቱ ያልታወቀ የአየር፣ ውሃና አፈር መመረዝና መጥፎ ጥፋት ላይ እየተዳረገች መሆኑን፣ ወያኔ ሀገሪቱንና ሕዝቡን ለማውደም ቆርጦና ታጥቆ መነሳቱን የተሰማውን ቁጭት ገልጾ ወያኔ በኢትዮጵያ ላይ ያልፈጸመው በደል አለወይ? ሲል ጠየቀ። የተሸጠው መሬት እጅግ አነስተኛ መሆኑን እና ዓለም የሚያደርገው የልማት ዘይቤ መሆኑን ገልጸዋል። ሆኖም በማያውቁት የምድርና አየር መበከል ጣጣ አደጋ ውስጥ ኢትዮጵያ መግባቷን ባያውቁም፣ ቢያውቁምፈጽሞ የማያሳስባቸው ስለሆነ፣ በጥበቧ እንኳን ልትነጻጸር ቀርቶ ልታውቅ ከማትችለው የአሜሪካ እጅግ ከረቀቀና ከተወሳሰበ አስተዳደርና የንግድ ደንብና ሕግ ጋር የዲክታተሩ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚፈጸመውን የጥፋት ስራ በዚያ ማነጻጸሪያ ሊሸፍኑ ይሞክራሉ። አሜሪካ የንግድም ሆነ የአስተዳደር ሕጎቿ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካና ሌላ ኃይሏ ሁሉ ከንግዱ ጋር አብሮ ይሰራል። የወያኔ መሪ ከዚያ በታች ላሉት ሀያል ሀገሮች ጥቅም እየሰራን ቢል ይሻላል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም እየሰራን ነው ማለት ዘበት ሆኗል። ወደ ውጭ የሚጎርፈው የኢትዮጵያ ሀብት በሀገሪቱ ውስጥ ቀርቶ በስራ ቢውል እርሻውን ለማካሄድ የግብጽና ቻይና ገንዘብና ጉልበት ባላስፈለገ ነበር። ስለተወሰደው ዳርቻ መሬት ልዕካኖቹ ለሱዳን የተሸጠ ወይም የተሰጠ መሬት የለም በማለት በሁለቱ መካከል የተደረሰበት ስምምነት አልተፈረመም በማለት ለጥያቄው ቁልጭ ያለ መልስ ስለሰጡ፣ በዚህ ንግግር የተነካው ይኽ ጸሐፊ እጁን አውጥቶ ልዕካኑን ሊጠይቅ ተገደደ።

ከዚህ ቀጥሎ ላለው ጽሑፍ ይኽ ጸሐፊ ከማለት ይልቅ፣ ለአንባቢና ለመጻፍ እንዲመች “እኔ” በማለት እጽፋለሁ። ከወያኔ ልዕካኖች ስብሰባዎች ስገኝ ይኽ ሁለተኛው ምናልባት ሶስተኛው ጊዜየ ነው። በአስራ ዘጠኝ ዓመቶች ውስጥ ብዙ ተካሂደዋል። በመጀመሪያው ስብሰባ ላይ አስተናጋጆቹ የራሴ ጓደኞች የነበሩት ያሁኖቹ ከፍተኛ ካድሬዎች ሰለሞን ታደሰ፣ እዝራ ተሾመና ተስፋየ ነበሩ። እነሱ አሁን በሌላ አገልግሎት ላይ ስለሆኑ መኮንን ካሳ ቦታቸውን ተረክቧል። በዚያ የመጀመሪያየ የስብሰባ ተሳትፎ ላይ፣ እጅግ አንጸባርቀው በበር የቆሙት አስተናጋጆች ከላይ የተጠቀስኳቸው ሲሆኑ፣ ከበሩ ላይ ስደርስ “እንዳትረብሽ” የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጡኝ። ለአመላቸው እንጂ የኔን ጸባይ ሳይረዱ ቀርተው አይደለም። ከውስጥ የነበረው ታላቁ እንግዳ አምባሳደር ብርሃኔ ገ/ክርስቶስ እንደ አሁኖቹ ማራኪ ተናጋሪ አይደለም። ንግግሩን ጨርሶ ጥያቄ መቀበል ሲጀምር፣ ለመጠየቅ እጂን አወጣሁ። እየታለፍኩ ስብሰባው ሊያበቃ ሲል አንድ የትግራይ ሴት በትግርኛ ይህ ሰው ብዙ ጊዜ እጁን አውጥቶ ለምን አለፋችሁት ብላ ጩኸ ጠየቀች። በሷ አቤቱታ እንድጠይቅ ስለተፈቀደል ጥያቄየን አቀረብኩ። አምባሳደሩ ጥያቄን ለመመለስ ባለመፈለጉ ፍቱን ወደ ሌላ ስላዞረ፣ ሌላ ጥያቄ ያለው ሰው ተባለ። ለሌሎች የተሰጠውን መልስ ግማሹን ሰምቸ ወጣሁ። ከበሩ አጠገብ የቆሙት ከላይ ጓደኞች ያልኳቸው ሰዎች ደስ እንዳላቸው በግሩም ፈገግታቸው አሳዩኝ። ከብዙ ዓመቶች በኋላ ሌላ የወያኔ ስብሰባ ሂድኩ። አሁንም ጥያቄ ለመጠየቅ እጄን አውጥቸ ሌላ ጠያቂ ቢጠፋ ጊዜው አለቀ ተብሎ ሳልጠይቅ ስብሰባው አለቀ።

ከዛሪው ስብሰባ ለመጠየቅ አስቤ አልሄድኩም። ውሳኔየ እንዳልጠይቅ ነብር። ብጠይቅም የማገኘው አጥጋቢ መልስ እንደሌለ በመረዳት ነበር። ዳሩ ግን ከልዕካኑ አንዱ ኢትዮጵያ ለሱዳን የሰጠችው፣ የለወጠችው ወይም የሸጠችው የለም ብለው በመናገራቸው፣ መጠየቅ ግዴታ ሆነብኝ። እጄን አወጣሁ። በተሰጠኝ ዕድል፣ አንደኛ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን መሰጠቱ በካርታ ገና ባያሳዩትም፣ በመሬቱ ላይ ለብዙ ዘመን ኗሪ የነበርው የተፈናቀለና የተሰደደ መሆኑ እንደማይካድ፤ ሁለተኛ፣ መለስ ዘናዊ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያላትን የወሰን ዳርቻ እንደማታውቅ አስረድተው፣ ዳሩ ግን፣ ከሱዳን የወሰድነውን መሬት ለሱዳን መልሰናል ማለታቸው እጅግ የተዛባ ጉዳይ መሆኑን አመልክቸ፣ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን የተሰጠ መሆኑ ይኽ ማስረጃ እንደሆነ ገለጽኩ። ቀጥሎም፣ ልዑካኖቹ ስለ ሀገር ግንባታ የሰጡትን ሰፊ ትንተና ጠቅሸ፣ ግንባታው በ”ኤትኒክ ፈዴራሊዝም” አስተዳደር የተመሰረተ ስለሆነ ቤትን በአሸዋ ላይ እንደመስራት ነው ብዬ በምሳሌ ገለጽኩ። ቀጥየም አስተዳደር የአፈርን ሀብት፣ የመሬትን አቀማመጥ ሁኔታ፣ የወንዝና የባህርን፣ የሕዝብን አሰፋፈር በመሳሰሉት ላይ ሲሆን አፋኝ የሌለው ሰፊ ልማት ይቻላል፣ ለኢትዮጵያም ተገቢው ይኽ ነው በማለት ገለጽኩ። በንጉሡ መጨረሻ ዘመን ላይ በሱዳንና ኢትዮጵያ የተደረገውን ስምምነት ካርታውን የሰራሁ መሆኔን በመግለጽ ውል ወይም ስምምነት የለም የሚባለው ኢትዮጵያን ከጉዳት ላይ ለመጣል ካልሆነ በስተቀር፣ ስህተት መሆኑን የታሪክ ምስክር መሆኔን ገለጽኩ። ለዚህ መልስ በዚሁ ስራ ዐዋቂ የተባሉት ከልዕካኑ አንዱ በቦታው ስለነበሩ መልስ እንዲሰጡ ተደርጎ በንጉሡ ዘመን የተፈጸመውን ሳያስተባብሉ ገለጻ አድርገዋል። በተጨማሪም ሌላው ባለሥልጣን ስለ ፌደራል አስተዳደሩ በቋንቋ ላይ መሆኑ መልካም ነገርና ለጎሳዎች ዕድገት ጠቃሚ መሆኑን አብራርተው በመሬት አቀማመጥ ቢሆን ዕድገትን እንደሚያግድ አስረዱ። ባለሥልጣኑ አጥበቀው የተረዱ አለመሆናቸውን የሚያጠራጥረው፣ ቋንቋ ፈሰሽ እንደሆነና ድንበር ሊደረግለት እንደማይችልና አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ ወዘተ ከሰሜን ዳርቻ እስከ ደቡብ ዳርቻ፣ ከምስራቅ ሀገር ዳርቻ እስከ ምዕራብ ዳርቻ ሊነገርና ሊስፋፋ የሚችል መሆኑንና አጥር እንደሚያስፈልገው፣ አስተዳደር ግን ዳርቻው የሕዝብ አሰፋፋር፣ የመሬት አፈጣጠር፣ አቀማመጥ እንዲሁም የወንዝ፣ ባህር፣ የሸለቆ፣ የተራራ፣ የደን የመሳሰሉት የሚያስተካክሉት መሆኑን ዕውቅናን ይጠይቃል። በተጨማሪም፣ በኢትዮጵያ የተጠነሰሰው አስተዳደር በዓለም ዙሪያ ተመሳሳይና አኳያ የልተገኘለት ልዩ አስተዳደር እንደውም የሕዝብ ብጥብጥን መፈተኛና መመዘኛ ወይም መከፋፈያ መሆኑን መረዳት የሕዝቡ ኃላፊነት መሆኑን ማሳወቅ ይገባል።

መደምደሚያ
ስብስቡ በዚህ ዓይነት ውይይት የተካሄደ ነበር። ተሳታፊው ተናጋሪዎቹም ሊደሰቱ ምክንያት አላቸው። ማን በምን መደሰት እንዳለበት ወይም መደሰት እንደሌለበት መፍረድ ወይም መበየን አይቻልም ወይም አይገባም። በዚህ ጸሐፊ አስተያየት ግን፣ ባለሥልጣኖቹ ከተናገሩት ይልቅ ከሰሙት ዕውቀትና ምርምር ሊማሩ ይገባቸዋል። ከዚህ ላይ ያልተጠቀሰ ብዙ ክርክርና የውይይት ነጥቦች ነበሩ። ሁሉም አሳሳቢ ናቸው። ይኽን ጽሑፍ ለማቅረብ ሀሳብም ዕቅድም አልነበረም። ስለዚህ ከዚህ የጠቀሳቸው ሊያስታውስ የቻለውን ብቻ ነው።

ጥያቄ ወይም ሀሳብዎን ለጸሐፊው ለማካፈል ከፈለጉ በሚከተለው ኢ.ሜል ይላኩ።

zegfantam@aol.com

  1. መስፍን
    | #1

    እንዲህ ዓይነት ዘብዛባ ፅሑፍ አንብቤ አላውቅም!!!

  2. wakyo
    | #2

    Very interesting it must be a culture to go to some of woyanne meetings and tell them that they dont have no rabbit hole to hide in the planet,
    as they are very backwards they dont even know that we have each and every information about our beloved motherland unlike their primitive
    cadres who have sold their concious for a stolen Ethiopian money in this case.I would like to thank the writer for exposing their lies other
    wise we had have the other way by the woyanne sponserd Aiga forum as if it was a success and for the writer i would like to tell you it doesnot matter who he is woyanne can never learn change as it goes to its goal
    and that is to disintigrate Ethiopia slowly but surely

  3. Anonymous
    | #3

    me too, endih aynet zebzaba anbebie alawuqem

  4. Da
    | #4

    hi Mesfin it is better tocomment on the content

  5. ይነጋል
    | #5

    ምነው መስፍኔ አመመህሳ!!! ጸሃፊው ያዩትን ቁልጭ አርገው ነው ያቀረቡት: ካልጣመህ ዝምታ እኮ ወርቅ ነው!!!የሰሞኑን የጠ/ሚ ጸባይ እንዳስታውስ አረግኝ

  6. ወይ ነዶ መሞት
    | #6

    መስፍን አባባልህ ትክክል ነው:

    ከከሃዲውና ከባንዳው ወያኔ ወገን ስለሆንክ አንገብግቦህ ስለሆነ አይፈረድብህም: አነበብክ አላነበብክ ምንም የምታመጣው ለውጥ የለም:: እኔስ ይህ ጽሁፍ በጣም አስደስቶኛል::

  7. ሎሎ
    | #7

    የጽሁፉ ዋና ነጥብ ምንድን ነው ? አልገባኝም:: መልእክቱ ግልጽ አይደለም::

  8. ከ ሃጋራ
    | #8

    እናንተህ ሳዎችሂ ዋያና እኮ ዋገናችሂን ነው ምነው ወራዊን የምታገኑት ዋያና ተላታችሂን አይደለም እናንተ መታፍ የሚገባችኡ ወይ ደግሞ ለዊቲ እንፈልጋለን ብቱሉ እንሳማማለን ጊን እናንተ የምቲሉትን ወደ ዘራጊነት የሚያዳላ ኒግጊር ነው ዋያናዎችሂ እኮ መስዋህትት ከፍሎ የመትሱ ናችሀው እንደናንተ ዊችሂ ሃገር ተከምትሶ ዋራ ማባዛት ሳይሆን በተግባር ያሳን መኒጊስት ነውሀና የሚገርመግ የመኒጊሲት ደጋፊ ከሆኒክ እትሂኦፒአዊ አይደልህም ማለት ተገምርዋል ወዳችወይደግሞ የ ቲግራይ ተዋላግ ከሆነ ዋያና ነው ዪባላል ከ ሚገርማችሁ እና ለምሳላ የሚካወሞ የነበርክ ሳው ነግ ግን እንግላድ ከመትሳው ገሚራ አሳበግ ከየሩክ ሚኪኒያቱ እና የ ቲግራይ ተወላግ ጋር አሲተያያታችሀዊ ቲሩ አይደሉም እና ደግሞ ህለህ ሂዞግ የ ወያና ደጋፊ ሁጋለው በ ተርፈ ችሃው

  9. Anonymous
    | #9

    ሎሎ

    ዋናው መልዕክት – እኔ እንደገባኝ – “ወያኔዎቹ ለፕሮፓጋንዳ በጠሩት ስብሰባ ላይ ተሰብሳቢው በጥያቄ አጣደፋቸው: እኛን በፕሮፓጋንዳችሁ የምታሳምኑን መስሏችሁ ከሆን አትድከሙ አላቸው” ነው::

    እንደዚህ በስብሰባቸው ላይ እየተገኘን ሪፖርት ብናደርግ ጥሩ ነበር::

  10. Ethiopia first
    | #10

    Abugida, why do delete my comment? if some body does not support seye 100%, is that person is enemy? WE WILL SEE THE NEXT COMIUNG WOYANE ELECTION. what ever woyane will not give power by peace full struggle. Melese and his group pretend stand shabyia side the other ex- woyane are anti shabiya and to return Assab port for Ethiopia that means Shabye have to work with Melese,and than woyane get other friend, please we Ethiopian have to weak up and smell the coffe, this is woyane game. they try to control power for ever. our big enemy is woyane , we have to stand togeather to rid of woyane after that we will discuuse with shabyia.

  11. ታየ ፈካዱ ፋንታየ
    | #11

    አሳፋሪ ነው

  12. ጼሌምኦኝ
    | #12

    WEYANE COME FROME BUSH ,THEY THINK LIKE THE BUSH THE GREAT PEOPLE OF ETTHIOPIA NEVER EVER LIKE WEUYANE (THE GOV). IS DEAD FISH IT MUST BE DAMPT
    SO ON THIS ELECTION ANY KIND OF OPPONENT EXCEPT DEAD WEYANE

  13. Ethiopiawinet
    | #13

    Thank you very much Zewge Fanta.
    Well done.

  14. Anonymous
    | #14

    Since ethiopians boycotted woyane meeting all over the world ,I wonder why Zeg was there .

  15. ዘመን
    | #15

    ኣቶ ዘውገ,
    በጣም ግሩም ዘገባ ነው ይቀረብክልን, በጣም ላመሰግንህ እዎዳለሁ. ልቡ በዘረኛው ዎያኔ የተሰለበው ሆዳም ሁሉ, በሆዱ ነው የሚአስበው, ብጭንቅላቱ አይደለም. በቀረበው ዘገባ በሁዋላውም በፊቱም ሆድ ያዎጣውን ሆዳም ተዋርዶ ከስብሰባ መባረሩን ተገንዝበናል. ይህ ዎራዳ ግለሰብ,የበቀልበትን ምድርም አሳፍሮአል!!!. አቶ ዘውገ ሰለ እውነት የምታደርገውን ጥረት አደንቃለሁ!, ለገርህም ያለህ ፍቅር ለሁላችንም ትልቅ ምሳሌነት አለው.

  16. ለላ
    | #16

    አቡጊዳ ዉሸታኦቺ እዊነት አዊሩ አቲከፋፊሉ

  17. lEMLEM AMARE
    | #17

    TPLF ia doing phase by phase what they ought and vow to do from day one.To ENRICH ONE ETHNIC AT THE COST OF LOOTING THE WHOLE ETHIOPIA BY ANY MEANS NECESSERY.WHAT I DONOT UNDER STAND IS THE SO CALLED “OPPOSITIONS”WHO FORM A NEW ORG. NEW COMMITTEE AND NEW WEB SITE AND NEW RADIO AND TV STATIONS EVER 3 MONTHS,AS IF RADIO,TV,WEB SITES OR CHAT ROOMS CAN RESOLVE TO HELP ETHIOPIA FREED FROM TPLF ALMOST 20 YRS TYRRANICAL AND BRUTAL RULE .I SEE THE TPLF’S CRIME AND MISRULE OF ETHIOPIA AND I WORRIED MORE AND SADENED BY THE OPPOSITIONS FAILURITY TO FORM SOLID UNITED AND VISIONFUL ORGANIZATION WHICH INCLUDES ETHIOPIANS OF ALL WALKS OF LIFE .THE BURDEN OF PROOF IS LAID ON THE OPPOSITIONS TO PROVE ETHIOPIANS AND THE WORLD THAT THEY ARE READY AND CAPABLE OF LEADING A NATION ,I’M WONDERING WHERE DID THEY GOT THE IDEA OF RULING THE NATION OF 80 MILLION PEOPLE WHILE THEY PROVED US AGAIN AND AGAIN THEY CAN NOT EVEN RESOLVED THEIR ORGANIZATIONS OR GROUPS PROBLEM WITH CIVIL DISCUSSIONS AND FOCUSING ON THE BIGGER PICTURE -TO LIBERATE ETHIOPIA FROM TPLF NARROW ETHNICALLY BASED BRUTAL RULE

  18. ኣጥእ
    | #18

    ግሩም

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።