ግልጽ ደብዳቤ ለፕሮፈስር መስፍን ወ/ማሪያም
ውድ ፕሮፌሰር መስፍን፤ በመጀመሪያ የከበረ ሰላምታችን ይድረሰዎ።
ይህ ደብዳቤ የተፃፈው ከቀድሞ ተማሪዎችዎ፤ የሥራ ባልደርቦችዎ፤ ምሁራዊ ሥራዎችዎን ካነበቡና፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) መሥራችና መሪ ሆነው ላደረጓቸው ፈር-ቀዳጅ ሥራዎች፤ አድናቆት ካለን ሰዎች ነው።
ከዚህ በላይ ባጭሩ የገለፅነው ለእርሰዎ ያለን ክብር እንደተጠበቀ ሆኖ፤ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ከእርሰዎ ጋር ሆነን በኢትዮጵያችን ውስጥ ዲሞክራሲና ሰላም እንዲሰፍን አብረን ስንሰራ የነበርን፤ እርሰዎና ሌሎቹ የፖለቲካ እስረኞች ከእስር እንዲትፈቱ ሌት ተቀን የለፋን ወዳጆቸዎ በቅርብ ጊዜ በተፈጠረው ሁኔታ በመቆርቆር የተንሳ ይህንን ግልፅ ደብዳቤ ለመፃፍ ተገደናል።
ጉዳዩ እርሰዎ የሚመሩት “የአንድነት ፓርቲ” ቡድን ከመድረክ ጋር ተቀላቅሎ ከሚሰራው የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የሚያደርገውን ትንንቅ በተመለከ ነው። ግልጽ ለማድረግ ያህል፤ በቅርቡ በኮኮበ ፅባህ ት/ቤት በመጋቤት 29 ቀን 2002 ዓ/ም ያሳለፋችሁትን ውሳኔ በአንክሮ ተመልክተነዋል። እርሰዎም በዚህ እድሜዎ የወ/ሪት ብርቱካ “የወንበር ጠባቂ” ሆኜ ተመርጫለሁ ብለው ያስተላለፉትንም ዜና በመገርም አዳምጠናል። ይህንኑ በተመለከት በየጊዜው የሚጽፏቸውን ጽሁፎች አንብበናል። በእኛ አመለካከት ጽሁፎችዎና የሚሰጧቸው ቃለ-መጠይቆች በቆረጣ መልክ “ምርጫን ማሸነፍ” ተግባሩ ለሆነው ለገዥው ፓርቲ መጠቀሚያ ሆኗል። ይህንን በሚመለከትም እኛ “ምላሽ እናድርግ ወይስ አናድርግ” እያልን ከእራሳችን ጋር ስንሟገት ቆይተናል። እርሰዎና የእርሰዎ ተከታዎች በፀረ-ዲሞክራሲው መንግሥት ላይ ያነጣጠረ ትግል እንደማካሄድ፤ ደርሻችሁን ለጋራ ትግሉ እንደማበርከት ፋንታ፤ በአንፃሩ ግን በዲሞክራሲያዊ ሀሎች ላይ ያነጣጠረ ተኩስ መተኮሳችሁ ታሪካዊ ስህተት ነው።
ይህ በዲሞክራሲያዊ ሀይሎች መካከል የሚደረገው መጠላለፍ ከዛሬ ነገ ይበርዳል ብለን ስንጠብቅ፤ ጣልቃ ላለመግባት ስንልም፤ ታግሠን ቆየን። እርሰዎና ተባባሪዎችዎ እንደጠላት የምትቆጥሯቸውን ሀይሎች “ታገሷቸው” እያልን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ምክራችንን ስንለግስ ቆይተናል። ሆኖም ግን ሁኔታው ከዕለት ወደ ዕለት ተባብሶ፤ እንዳውም እስከ ምርጫው ዋዜማ ደርሶ፤ ምንም እንኳ እርሰዎና ተባባሪዎችዎ የምታደርጉት ከፀረ-ዲሞክራሲ ሀይሎች ጋር የሚደረገውን ትንንቅ ያዳክመዋል ብለን ባንጠብቅም፤ በአንድ በኩል በአሁኑ ጊዜ ከእርሰዎ የሚጠበቀው አደናጋሪና ከፋፋይ ተግባር ሳይሆን፤ ከፍተኛ ትግስትን ተመርኩዞ፤ የተጣሉትን ማስታረቅ፤ ያለተስማሙትን ማስማማት ስለሆነ፤ በሌላ በኩል ደግም በአሁኑ ጊዜ የዓላማ አንድነት ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶችና ቡድኖች የሚያደርጉትን የመፈላልግ እንቅስቃሴን እርሰዎና ተባባሪዎችዎ ይህንን መልካም ተግባር የሚቃረንም ስለሆነ፤ ይህንኑ ተገንዝበው በስቸቋይ እንዲያስተካክሉ እንጠይቃለን።
በመጨረሻም፤ ይህንን ግልጽ ደብዳቤ የላክነው ምሁራን ስማችንን አሁን በይፋ ለመግልፅ ያልፈለግንበት ዋናው ምክንያት ከላይ እንደገለፅነው፤ የእርሰዎ አጋሮች ስለሆንን፤ ጊዜውና ሁኔታው ባመቸ ጊዜ ከእርሰዎ ጋር ውይይት ለመቀጠል አንዲያመቸንና የኢትዮጵያ ሕዝብም የስህተቱ ሰለባ እንዳይሆን በማሰብ ነው።
ካክብሮት ጋር፤
በሁኔታው የተቆረቆርን በውጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ምሁራን።



000000የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳችሁ::00000000
ፕሮፌስር መስፍን ወ/ማርያም ሐቅ ይዘው ብዙ ይዘገያሉ ::ባህርያቸው እና እድሜያቸው ሆኖም ንግግራቸው የሚጎተትና ነገራቸው የሚዘገዩ ናቸው::በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ደግሞ ዕጥን ምጥን ያለች የበሰለች ደብዳቤ በመፃፋችሁ ልቤን ነክቶታል::
ጉዳዩን አይዘነጉትም ብዬ አምናለሁ::ሆኖም በአስታራቂነት በውስጥ ሽማግሌዎች በውይይት መፍታት እንጂ “የሁለቱ ዝሆኖች…”የጥፋት ውጤት እንዳይሆን ፀሐፊዎቹ ሶስተኛ አካል ሆነው እንዲንታገሉ ሃሳቤን ያዙልኝ::
በሌላ በኩል መድረክ ከወዳጅም የሚሰነዘሩትን አፍራሾች ከጠላትም እየተዋጋ ደም እና ሕይወት እየከፈለ በሚገኝበት ወቅት የግንቦት ሰባት እንደአጀማመሩ በአሁኑ ወቅት በእጅጉ እንቅስቃሴአቸው አይታይም እና የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳችሁ !!!በርቱ::
አቢይ ኢትዮጵያዊ::
Can any ethiopian save prof mesfin before he committes a grave mistake? Kidetu ayalew and shilu hailu shawul have killed the popular party [ Kinijit] in support of TPLF .By doing such a crime , both kidetu and hailu will pay at the end of the day. TPLF gave kinijit for ayele chamisso. I have never ever expected that prof mesfin can go down to earth to kill the wish of ethiopia’s ppl for freedom and democracy. Even prof mesfin said in weyane’s paltalk room [ kinijit swizerland room] ” EPRDF is far better than medrek” So shame.
የፕሮፈስር መስፍን ወ/ማሪያም የፖለቲካ አመለካከት ግልጽ ያልተምታታ እንደሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቀዋል አደናጋሪና ከፋፋይ ተግባርም ፈጽመው አያውቁም!!!!!!!!!!!!!!!!!
በተጨማሪ እንደማንም ሰው በሀሳብ የመለየት መብታቸው ሊጠበቅ ይገባል ይህ ደግሞ እናንተ ምሁራን በምትኖሩበት አገር ያለ አንድ ይዲሞክራሲያዊ መብት መሆኑ መዘንጋት የለበትም ደግሞ ሀስብን ማቸንፍ እሚቻለው በመወያየት ብቻ እንጂ በዘለፋ መሆን አይኖርበትም:: ለመሆኑ ፕሮፈስር መስፍን ወ/ማሪያም ወያኔ ሲባሉ እናንተ ተቆረቆርን በውጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ምሁራን ምንው አንዳች ንገር አላላችሁ ደግሞስ ዜናው ምን ያስገርማል የወ/ሪት ብርቱካንን መሪነት መቀበል ያቃታቸው ሰዎች አይደሉ እንዴ የአንድነት ፓርቲ እየመራ ያለው? ለማንቸም ለወያኔ ከፕሮፈስር መስፍን ወ/ማሪያም እነ ስየ አብርሃ ዶ/ር ነጋሶ ፕሮፈስር በየነ ቅርብ መሆናቸው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ያውቀዋል::
አምልክ እኝህን ታላቅ ሰው ይጠብቃቻው!!!!
እሚገርመው ነገር አገራችን ሀብታም ከሆነች የመሰደድ ፍላጎት የልን ኢሃእዲግ ለራሱ ስለተመችው ለላ የከፋው አይመስለው ይሆናል ስለ አረብ አገር ሰት ግፍ ግታ ይወከው በአእለም ያላቹ ሙህራን አዕምለምናቹህ ይህ ጉዳይ አሳዛን ነገር አኢያይን አንለፍ
በዚህ የስደቱ ጉዳይ እንበል የአረብ አገር ኑሮ ያየ ይፍረድ
በውጭ ሀገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን እነማን ናችሁ? ስንት ናችሁ? አይን ያወጣ ድርቅና ማለት ይሄ ነው:: የመልዕክቱ ግድፈትም ከዚህ ይጀምራል:: በጎ ሀሳብ በጠቃሚነቱና እውነት በመሆኑ ብቻ ነው የሚመዘነው:: አንድም ሁለትም: ሺህ ስውም ይፃፈው ምንም አይደለም:: ምናለ ከዚህ ሁሉን አውቃለሁ: እኔ አውቅላችኅለው ከሚል አባዜ ብንወጣ!!
Pro.Mesfin must go to Amanuel Hospital.
ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወገጥ!
የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም የቀድሞ ተማሪዎች፣ የስራ ባልደረቦች፣ ምሁራዊ ስራዎቻቸዉን ያነበባችሁ እና የኢሰምጉ መስራችና መሪ ሆነዉ ላደረጉዋቸዉ ፈር-ቀዳጅ ስራዎች አድናቆት ያላችሁ፤ ለፕሮፈሰር መስፍን ወ/ማሪያም የፃፋችሁላቸዉን ግልፅ ደብዳቤ አነበብሁት። ተረዳሁ አንድምታዉንም ሳይቀር-እናም ገፋፋኝ አንዳንድ እንድል።
የግል አስተያየትየን እንጂ መልስ መስጠት ቃጥቶኝ አይደለም – ምን ቅብጥጥ አድርጎኝ። አስከንድተዉ መመለስ የሚችሉ ባለጉዳዩ እያሉ። ያዉም ካስፈለጋቸዉ ይመስለኛል። አንድ ጉዳይ ልጨምር። ፕሮፈሰሩ፣ ካስተማሩዋቸዉ መካከል የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እንደ መገኘታቸዉ፤ ለኢትዮጵያ አይን ናጫ የሆኑባትም አሉ። አብሮ በመስራትም ረገድ ከሆነ ካልሚዋም፤ ከአምካኝዋም ሆነ ካፋሽ አጎምባሹ እና ለመጣው ኃል ሁሉ እስክስታ ወራጁ ጋር መስራታቸዉንም አታዉቁም አልልም። ፕሮፍሰሩ፤ ሰንየ እና ሰኞ የሰመረላቸዉ ዘረኞቹ እየተናዱ አዲስ አበባ ሲገቡም ልጆቻችን መጡ፤ ምንድን ነዉ የምትሉት፣ ጊዝየ ይሰጣቸዉ እንጂ ባዮችም ጋር አብረው እንደነበሩ አታጡትም።
ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ልመለስ እና፣ ፕ/ር መስፍንን እንየም ስለማቃቸዉ ነዉ ያን ያልኩት፤ ግን ተማሪያቸዉ አልነበርኩም። የስራ ጉዋደኛሞችም አይደለን። በእድመም አንገናኝ። ስራዎቻቸዉን አዉቃለሁ-የቻልኩትን ያህል። ከአድናቂዎቻቸዉ እና ከአክባሪዎቻቸዉ መካከል ነኝ ብየ አምናለሁ። እንኩዋን እንየ፣ ነፍጠኛ የአምሃሩ ምሁር ባዮቻቸዉ እንኩዋ ሳይወዱ በግዳቸዉ፤ እየጎመዘዛቸዉም ቢሆን የሚቀበሉት ጉዳይ ለመሆኑ አንድ እና ሁለት የሚያስብል ላለመሆኑ ክርክር ታንሳላችሁ ብየ አልገምትም።
ወገኖች፣ ማንነታችሁን ገለፃችሁ አልገለፃችሁት፣ አትስጉ፤ በእራችሁ፣ ተግባራችሁ ገልፆአችሁአል – ስም ተምግባር፣ ምግባር ተስም ይሉየል። እንግዲህ፣ እንድፅሁፋችሁ ከእናንተ ጋር የሚለየኝ የፕሮፈሰሩ የፖለቲካ አካህየድ ጉዳይ ነዉ። ይህን ደግሞ አሳምርየ ስከታተለዉ የቆየሁት እና አሁንም የምከታተለዉ፤ አሳምርየም የማዉቀው ጉዳይ ነዉ። ይሀዉ፣ በሶስቱም አምባገነኖቻችን ዘመናት ሁሉ ፕሮፈሰሩ እንዳሉ አሉ። የእድምየ ለዉጡን ተውትና። ፕሮፈሰሩ፣ ከይሁን ይልቅ፣ አይሆንንም የሚያስቀድሙ፤ አይሆንም ሲሉአቸዉ፣ ይሆናልንን የሚለጥጡ፤ እሳቸዉ የጀመሩትን እንጂ ልየላዉ የጀመረዉ/የሚጀምረዉ የማይጥማቸዉ ናቸዉ እንየ ሳዉቃቸዉ። ቅልብጭ ባለዉ፣ እሳቸው የለሉበት ሁሉ እርኩስ ከአርዮስ ነዉ – ተደምሞ የሚሆንብኝ ግን እሳቸዉ ያሉበት/የነበሩበት ሁሉ ሲናድ ማደሩ ነዉ።
ኤናም ፕሮፈሰሩ፣ በመድረክ/አንድነት ወይንም Forum/UDJ ላይ የወሰድቱን አቁዋምን እማየዉ ከዚህ አኩዋያ እንጂ መድረክ/አንድነት ወይንም Forum/UDJ በመለስ ለሚመራዉ ወያነ ድጋፍ ሰጭ ወይም በሰየ ለሚመራዉ ልየላኛዉ/አዲሱ ወያነ እንቅፋት ሁዋኝ አድርግየ አይደለም። እንደ እንየ እነስየ ከመለስ የከፉ፣ ያፈጠጡ ዘረኞች ለመሆናቸዉ መፅሀፍ ማገላበጥን የሚጠይቅ አይደለም። ከስልጣናቸዉ የተባረሩትም መለስ ለትግራይ/ኤርትራ የሚሰራ/እየሰራ የነበረ/ያለ ሲሆን፤ እነሰየ ደግሞ ለኤርትራ በመስራት ረገድ ባርነት/ነፃነት እስከሚለዉ ሪፈረንደም ድረስ ከእነመልየ ጋር አብረዉ የሰሩ፤ በሁዋላ በሁዋላ ግን በምንም ይሁን በምን የትግራይ የበላይነት ብቻ ነዉ መጠበቅ ያለበት ባይ እየሆኑ መምጣታቸዉ [(ለነገሩ ሲጠነሰሱም ለዚያዉ ነበር) ከስልታናቸዉ መልየ አባተንኮሉ የፈነገላቸዉ ለዚህ ነዉ] – ይህ ነዉ ልዩነታቸዉ፣ ወደዳችሁምትም ጣላችሁ።
ከዚህ አኩያም፣ እነ ፕሮፈሰር በመድረክ/አንድነት ወይንም Forum/UDJ መቃወማቸዉን የማየዉ ኢትዮጵያን ከምታደግ አንፃር ሳይሆን፣ አንድነት በልፍስፍሶቹ፤ በእነ እንጂንየር ግዛቸዉ፣ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ እና መሰሎቻቸዉ አመራር ጉድለት፣ አንድነት በተኩላዎቹ መጠለፉን በመቃወም የወሰዱት አቁዋም አድርግየ ነዉ። ይህም ሊደገፍ እንጂ፤ የቅርየታ/የምክር ወይም የተማፅኖ ደብዳብየ የሚያፅፍ ሆኖ አላገኘሁትም። ይልቅየ፣ እነ ፕሮፈሰር ሳይሆኑ፤ እናንተ ናችሁ ደብዳብያችሁን መሳብ የሚኖርባችሁ – ካፈርኩ አይመልሰኝ ካላላችሁ እንደ ስዩም መስፍንየ። አበቃሁ።
ቸር ይግጠመን።
Tekuale፣ የአቡጊዳ Admn፣ ይቅርታ ስምየ ከመለክትየ ጋር አልወጣም እና “ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወገጥ” የሚለዉ የእንየ፣ የTekuale ነዉ። ከምስጋና ጋር።
ግሩም ድንቅ መል እክት ነው ተስፋ እናደርጋለን የጀመሩት ስራ ለማን እንደሚጠቅም ተረድተው ሃሳባቸውን ለውጠው ጉዳዩንም በውይይትና በመመካከር በመቻቻል እንደሚፈቱት
ደደብ : መስፊንን : ለመናገር: ሞራል: የለህም:የወያነ: ወገነህ: ነህ::
ዲሞክራሲ: አንተ: እደምታስበው:ከሆነ: ሳይመታ:ይክር::
መከባበር:ከለለ: ዲሞክራሲ: የለም::
ጝዛችው: ዝምአንልምን: ተባራዋል: የሚለው: እሱ:ማነው?ለምን: ተክላላጉባየው:አያባርራችውም::
ከውያነ: በምን: ይለያል?
ታዲያ: ለዲሞክራሲ: መሰለፍ: ይህ:ከሆነ: ወያነ: ይኑር::
የፕሮፌሰር መስፍን ጉዳይ ለሰሚው ግራ የሚሆነው ለዘመናት የሰራቸውን ስራዎች በቅርበት ያላዎቀ ነው:: ሰውየው በዚሀች በእኔ በትንሽ እድሜየ እንደታዘብኩት ሁኔታው ሁሉ የመርዝ ብልቃጥነት አለው:: መቸውንም ቢሆን እንደ ገመድ ጉተታ በተቃራኒው መሄድን ይመርጣል::ጥሩ ነገር ባለበት ያንን ጥሩ ነገር ያመነጨው ራሱ ካልሆነ አይቀበለውም::እንደማንኛውም ዲሞክራሲያዊ ስርኣት አንድነት ፓርቲም ያደረገው በድምጽ ብልጫ የነርሱ ሃሳብ ወደቀ; ይህንን ራሳቸው ፕሮፌሰሩ በድምጽ ተበልጠን እንድንወድቅ ተደረገን ንው ብለዋል:: በዚህም በድምጽ ብንበለጥም የእኔ ሃሳብ ብቻ ተቀባይነት ማግኘት አለበት በሚል እድምታ ከድርጅቱ ደንብ ውጭ በመንቀሳቀሳቸው ተባረዋል:: ያልው አማራጭ ድርጅታቸውን እንደ አኢሃዴጉ አባይ ይቅርታ መጠየቅ ወይም እንደነ ሰየ ሌሎች በሃገራችን ዲሞክራሲን ለማምጣት የሚታገሉ ድርጅቶችን መቀላቀል::እንጅ ለዎያኔ ሚዲያዎች አዲስ የአየር ጊዜ ሽፋን መሆን ለማንም አይጥቅምም::
MESFIN WOYANE NEW
ለኒ ብዙም ግልት
ሰሚን ሽዋ፣ ፕሮፌሰሩ በቀኝ ሲሉአቸዉ በግራ፣ በግራ ሲሉአቸዉ በቀኝ የሚረግጡ ለመሆናቸዉ ምንም ክርክር የሚያስገባ ጉዳይ የለዉም። ውዮን ለመሆን ግን ትግሬ መሆንን የግድ ስለሚላቸው ባሆን ለወዮ አጎንባሽ ቢባሉ እስማማለሁ። ከአንተ በታች ህሳቡን ያስቀመጠው ሰዉ ስለተጠቀመበት ነው – ይቅርታ!
ወንድሜ/እህቴ ግን አትሞኝ/ኚ፡ አንድነት ሌላዉ ኢህድን ነዉ። መድረክ ኢሀዴግ ሲሆን፣ አርና ደግሞ ወያኔ ነዉ። ስለዚህ ፕሮፌሰሩ ተሳስተው ወይም ወያኔን ያስደሰቱ መስሎአቸዉ የወያኔን ግልባጭ ቤት ነው የሰበሩት የሚረዳችሁ ከሆነ። እናም በዚህ አድራጎታቸዉ ሊደገፉ ይገባል – ፕሮፌሰሩ። ስየ ምንም ምንም ቢሆን ከመለስ የባሰ በዘር የሰከረ፣ ከእግር ጥፍሩ እስከ እራሱ ጠጉር ድረስ በኢትዮጵያዊያን ደም የተዘፈዘፈ፤ ለህዝብ ፍርድ እንጂ፣ በአደባባይ ሊታይ የሚገባዉ ፍጡር አይደለም – ተወደደም፤ ተጠላ። አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ እንዲህ በቀላሉ ወዶ-ገብ ተቃዋሚዎች እና አንዳንድ የሚረግጡት የጠፋባቸዉ እነ ስም አይጠሬ ቁርጠኛ ተቃዋሚ ነን ባዮች እንደ እሚያናፉት አይምሰላችሁ። ሁሉንም በሁሉም አቅጣጫ አገላብጦ ማየትን ይጠይቃል። ለምን ብትሉ ወያኔ/ሻእብያ ቫይረሶች – ግን በሀቀኛ የኢትዮጵያ ልጆች፣ እንደ እነደብተራው፣ ፀጋዬ ገ/መድህን የኢህአፓው ባሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ትግል የሚረክሱ – ናቸዉ። ጎበዝ ልቦናችንን ብናሰራዉ የተሻለ ይመስለኛል – አይበቃችሁም። ቸር ይግጠመን፡ ልቦናዉንም ይባርከን – አሚን በሉ!
አቶ ታተት ለመሆኑ ፕሮ.መስፍን ለእት. አንድነት ምንየስሩት ነገር አለ ? አንድን ቀን እንኮ እኢህድግን በወጉ ሲቃወሙ ሰምተው ያቃሉ
ለግል ጥቅማቸውና ለወንበር ከመሻማት እንድሁም የአንድን ጎሳ የበላይነት ለማስጠበቅ እለት ተእለት የሚተጉ ናቸው ህቁን ለማወቅ ከፈልክ.ግለሰቡ ተፍጥሮ የበደላቸው የፊውዳል አስተሳሰብ እስክሁን እላያቸው የሰፈር ጸረ ሀገር ,ጸረ ህዝብ ናቸው::እስካሁንም ከርሱ ጋር የወጣ ሰው በሰላም ተመልሶ የማያውቅ ኮተ ደረቅ ናቸው ልገረህና.ሌሎች አንተ የሚትቃወማቸው ስየ,ነጋሶ ወይም ግዛችው ሌትዮ.አንድነት ህብረብህራዊ በሆነ መልኩ አምባገነኑን መለስ ለማበርክክ እይገፉ ናችው ብተርፈ የወጉትን የትዮ.ህዝብ ለመካስ ትግሉን እያፈፋሙ ባለበት ያንተው መስፍን እነርሱ የገነቡትን አንድነት ለማፍረስ የወያነ ተባባሪ ሆነዋል ስለዝህ ጸረ አንደነት ጸረ ዲሞክራሲ ናቸው ወደድክም ጠላህም:: ስየም ሆነ ሌሎች የመድረክ አብላት በዝቦች መሃል መስፍንና መለስ የረጩትን ለማጥፋት መስራታቸው ምኑ ላይ ነው ስህተቱ ይለቅስ ሳትቆይ በዘር የሰከርውን ወንድምህን ታደገው ካልሆነ መቀመቅ ይወርዳታል!!!
ወንድም ሰሜን ሽዋ በዝሁ ቀጥል ያገር ልጅ .
Forget about crazy old guy keep on to destroy Melese and crazy Mesfine.He is Ertirian agent,he is working for his wife country.Wake up !
ፕሮፌሰር መስፍን ተቃዋሚ ናቸው ተወደደም ተጠላ ተቃውሞአቸውንም በማካሔድ ላይ ናቸው የመድረክ መዘምራንና ነጭ ለባሾች ለህዝቡ የምታመጡለትን ለውጥ በሚቀጥለው ወር እናያለን የምን መቸኮል ነው
ጠርጥረዉ፣ ፅሁፌን መረዳት ቀርቶ በወጉ ለማንበብህ(ሽ)እጠራጠራለሁ። እንደወያኔ ያልተባለዉ ማለት እና ማምታታቱን ማቆም እና በወጉ ሃሳብን ማቅረቡ አይሻልም ይልቅ! ጥያቄዉ ስየ ወንጀለኛ ነው። ዘር ያሰከረዉ ነዉ። ለህዝብ መድረክ መቅረቡ ቀርቶ በህይወት ለመቆየቱ ራሱ ዕድለኛ መሆኑ መታወስ አለበት። ሀገርን ሲበድሉ ኑሮ፣ በህዝብ ደም ሲታጠቡ ኑሮ፣ አሁንም ሀገር ህልዉናዋ እየተናጋ እንዳላዩ እየተሆነ፣ ሂሳብ ልናወራርድ አይደለም ከህዝብ ፊት የቀረብነው እየተባለ፣ ህዝባችን ይቅርታ ለመጠየቅ አልበቃም እየተባለ፣ እነመለስ ባይጫኑን ይሻላል፡ ከተጫኑን የምናውቀዉን ሚስጥር እናወጣዋለን እየተባለ ነው የበደለዉን ሀገር ለመካስ ቆርጦ ተንስቶአልና ደግፉት የምንባለው? ሰየ ራሱ የበደልኩትን ሀገር እየካስኩ ነዉ ያላለዉን – ከየት ነዉ የምታመጡት። እረባካችሁ እፈሩ! ለዕቡይ አቮካቶ አትቁሙ። በሰማንያ ሚልዮን ህዝባችን መተማመን ቀርቶ በግለሰቦች – ያዉም እንደ እነሰየ ደም ጢምብራቸዉን ያዞረዉን መተማመኑ ይብቃ! ወይ ደግሞ እንደ እነ አብራሃ በላይ፣ እስክንድር ነጋ፣ ድ/ር ተኮላ ሀጎስ፣ … ዘረኛ ከሆንክ ቀጥ ብለህ፣ ራስክን ችላችህ ና እጂ ታኮ አትሁን። በዝብ እየተተፋችሁ መሄዳችሁ እየታያችሁ መራወጡን አብዛችሁ። ቀናችሁ ሩቅ አይደለም። ጭጋጉ ነግ ፍንትዉ ይላል። ይብቃኝ አይደል! ልቦናዉን ይስጠን – አሚን በሉ።
ሰላም ሰላምን ለምትናፍቁ ሁሉ ይሁን!
ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አሉ ያገራችን ሰዎች: ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ከልጅነት እስካሁኑ ያዛውንትነት እድሜያቸው ድረስ “መርሕ ይከበር” እንዳሉ አሉ:: በዓጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት እውቁ የመልክአ ምድር ምሑር አውራጃ አስተዳዳሪ ተብለው ወደግዞት ተላኩ:: ፕሮፌሰር መስፍን ከአላማቸው ፍንክች አላሉም በደርግ ጊዜም እንዲሁ እሳቸው ለእውነት አምባገነኖች ለአምባገነንነታቸው ቆመው ሲፋለሙ ኖሩ:: በዘመነ ወያኔ የሕዝብ መብት ጥሰቱ እየበዛና እየሰፋ በመሄዱ ኢሰመጉን አቆቁመው ያደረጉትን አስተዋጽኦ የማያውቅ የሚኖር አይመስለኝም:: እንዲያው ልታወር ካላለ በስተቀር ማለት ነው:: በቅንጅትም ወቅት ሚዛናዊ ሆኖ የሕዝብ አለኝታነቱን እንዲወጣ ብዙ ታግለዋል:: ጥረዋል: ታስረዋል: ተዋርደዋል: ተንጓጠዋል:: ያላዩት የመከራ አይነት የለም:: “ግልጽ ደብዳቤ” ጸሓፊዎቹ ምሁራን ባሕር ማዶ የነጻነት አየር እየተነፈሳችሁ እንደ እናንተው አባባል ምሑራን ከሆናችሁ ሀገራችሁን ገብታችሁ እንደማገልገል እራሳችሁን ኮፍሳችሁ ሃገራችን በምትሏት ኢትዮጵያ ላይ በደል ትፈጽማላችሁ:: ብዙዎቻችሁ ሳታስቡት ራስ ወደድነታችሁ እንኳን ሳይታወቃችሁ ሕይወቱን ለመስጠት የተዘጋጀን ጀግና ትሸረድዳላችሁ ምክር አይሉት ተግሳጻችሁ አሳፋሪና ነውርም ነው:: አዎ! ወያኔ እኩይ ነው! አዎ ወያኔ መሰሪና የሀገር ጠላት ነው:: ታግሎ ማስወገዱ ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ መተው አለበት? ወይንስ እንደ እናንተ “በውጪ የምትኖሩ ምሑራን” በወሬ ቅምዝምዝ ልታርበደብዱት ነው? አዎሮፓና አሜሪካ እንኳን ሆናችሁ “ግልጽ ደብዳቤያችሁን” በስማችሁና በፊርማችሁ ማቅረብ ያልቻላችሁ “ቡከኖች” ናችሁ:: በዚህ በአረጋዊ እድሜያቸው እረ መርህ ይከበር! የአንድነት ፓርቲ የማዕዘን ድንጋይ የሆነው “የግለ ሰቦች መብት” የሚለው በእነ አቶ ሰየና ነጋሶ ጊዳዳ ተቀልብሶ ሳይመከርበትና በጉባኤ ሳይጸድቅ “የቡድንም” የሚል ድሪቶ ሲከተትበት: ለምን? በማለታቸው: አካሄዳችንን እንምከርበት ግልጽ ውይይት ይደረግበት በማለታቸው ተባረሩ:: ያ ትክክል ነው ነው የምትሉት የተከበራችሁ ምሑራኖቻችን? በአንድ በኩል ወያኔ አሁንም አስሮ እያንገላታቸው (የመርህ ይከበር አባላት) በሌላ በኩል መደገፉ ቢቀር በአግባቡ ማወያየት እየተቻለ ለምን “የእብድ ገላጋይ…” መሆን መረጣችሁ?
መቼም ሁላችሁም የቱጃር ልጆች ሆናችሁ አውሮፓና አሜሪካ ፊድል እንድትቆጥሩ የተላካችሁ አትመስሉኝም:: ያ ካለ መጫሚያ አፈር ገፍቶ ቁርና ሐሩሩን ተቋቁሞ ግፍም በገዢዎቹ እየተፈጸሙበት በከፈለው ግብር የተማራችሁ መሰለኝ:: ፕሮፌሰር መስፍንና መሰሎቻቸው ያንን ወሮታ ለመክፈል መከራውንም አብረው እየተቀበሉ ያ የዕለት ከዕለት መከራ ያነሳቸው ይመስል በፈርጣጮች ምን ማድርግና ማለት እንዳለባቸው ሊነገራቸው ይገባል? በአጭር ታጥቆ አይዞህ እኛ ልጆችህ አለንልህ- ደረስንልህ ማለታችሁ ይሆን?
እረ እንዲያው ለመሆኑ ፓርቲዎን የመሰረቱትን በሐሳብ ልዩነት ስላላቸው ከፓርቲው አስወግዶ ትናንት ምን ሲያደርጉና ሲሉ የነበሩትን ሁለቱን የወያኔ ትራፊዎች ለሥልጣን ለማብቃት ብቻ ሲባል የተሰራው ስራ አያሳዝናችሁም? የብርቱካንስ ጉዳይ? በቃ ታሰረች ታሰራች ነው ነገሩ?
ለ ሕዝባችሁ የምትቆረቆሩና የምታስቡለት ከሆነ ገብታችሁ እንግልቱን እየተጋራችሁ- ሞቱን እየሞታችሁ አጋር ለመሆን ባትታዳሉም መከራውን የሚጋራውን እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ያሉትን ልጆቹን አትንኩበት::
መቼም አታደርጉትም, ምሁርም አይሳሳትም ብዮች ትሆናላችሁ:: ግን ወኔ ከፈነቀላችሁ ለፕሮፌሰሩ የይቅርታ ደብዳቤ ይጻፍላቸው::
መተራረሙን- መቻቻሉን እናንተ ምሑራኑ ካላስተማራችሁን እኛ ከየት እንማረው?
ወሮታው አዘነ
ሰውን እድሜ ያስተምረዋል ሲባል እሰማ ነበረ ምነው ፕሮፌሰር መስፍንን አናስተምር አለ?
ሰው ተወያኔ መጠቀምያ መሆን አለበት እንዴ?
ደደብ በክት ሁላ እናንተ ልካችሁን አታቁም ወያነ ካስችህገራችሁ ልክ እሱ እንዳደረገው ታግሎ ማውረድ ነው እዚጋ መለፍለፍ ለማንም አይበጅም ካልሆነ ደግሞ ዝም ማለት ነው.ወያነም ቢሆን ማንም ካደረገው በላይ ደሙን ተፍቶአል እነ ልደቱ እና በየነ ፐትሮስ ኮለጅ ሲዝናኑ ወያነዮች ደማችቸዉን እያፈሰሱ ነበር ራሳችንን ከ አመሪካ ጋር ባናነጽጽር መልካም ይመስለኝል አመሪካ 200 አመት ሙሉ ዼሞክራሲን ዼቨሎፕ ስታደርግ የቆየች አገር ነች. እና ደግሞ እናንተ ዉጭ ነዋሪ ተብየዎቹ ወንድ ከሆናቹ እዚህ መቶ መታገል ወይ አፋችሁን ዚጉልን ያልተማረውን ህዝብ ለማይሆን እና ለማይበጀው ነገር አትገፋፉት እዚህ የምንጤበሰው ዪበቃናል
it is my first day here and am sick of all u guys bullshiting specially those hu live in europe and USA we don want ur shit here we have enough pain we have seen here we don want to see how u are enjoying democrase there wen the times comes things might change at the time being u are reminding us our pain so shut z fk up and let us live our life