ሞረሽ

December 31st, 2008 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ከየሺእመቤት መንገሻ(ከለምበስ ኦሃዮ) / December 31, 2008

ሞረሽ፤ በይ፤ አረ፤ ሞረሽ

ካድማሱ ባሻገር አገርቤትም ያለሽ

በድል ችቦ፤ በድል፤ ጮራ፡

አገር ካገር ሲጠራራ።

ሞረሽ በል ወንድም

ባገር ቀልድ የለም

ሞረሽ በይ እቱ

ለፍትሀ ለነጻነቱ

እሀት ወዴት፤ ወዴት መቀነትን ጠበቅ

ወንድም ተስፋ አትቁረጥ ቀበቶህን ጠበቅ

አይሰማሽም ውይ ይሀ ሁሉ መከራ

አይስማሀም ውይ ይህ ሁሉ መከራ

ኢትዮጵያን እናውጣት ከዚህ ከደንቃራ

ከእንግዲህ በሓላ የለም ወለም ዘለም

በሐገርና በሚስት በባልም ቀልድ የልም

መጀመሪያ ሐገር

ከዚያ ፍቅር

አገር ሳትኖር

የለም ትዳር

አታልቅስ ወገኔ

አትዘን ወገኔ

አሻፋረኝ በለው ለዚህ ለወያኔ

ማንቀላፋት የቅር መተኛቱ ይብቃ

ተሎ መላቀቅ ነው ከማንም ጨቅጫቃ

ተነሳ ከእንግዲህ አታብዛ ቀጠሮ

ያለፍው ይበቃል ሐዘን እንጉርጉሮ

በልመና ስንዴ ይገፍል ወይ ኑሮ

የሚበላ ጠፍቶ አንጀትህ ተሳሰሮ

አንተን እያሰራበ አንተን እያስጠማ

ጭራሹን ሊያጠፋህ ነገር እያቅማማ

ግጥሙ ይቀጥላል 2ኛው ገጽ ያንብቡ

ካገርም እዳትኖር ነገር አቀጣጥሎ

ስብእናህን ገፎ አዋርዶና ጥሎ

የጥጋቡ በዛት

ህዝብን ማስቃዬት

ታዲያ ለምን መፍራት

ዝምታ ሲበዛ ፍርሃት ይመሰዋል

በቃ ለወንበዴ ትግስታችን አልቓል

በላይ፤በታች እሳት አገር ስትጠፍ

ምን ይመጣል ብለን እንጠብቅ በተስፍ

ነቃ በል ወገኔ ብዙ አናመናታ

ለሃገር እንድረስ እንሁን መከታ

ሞረሽ በይ በጋራው ሞርሽ በይ በዱሩ

እንደ አባት አደሩ

አልኖርም ከእንግዲህ እያልኩ እሽሩሩ

አንበሳው ተነስ ተነሽ ነብሬቱ

ያቆማል ዛሬ መንገላታቱ

ጥሪ ጋሻውን መከታየ ብለሺ

ተኝቶ እዳይቀር ሊሆን አጎንባሺ

ቀና በል በይው ቀጥል መንገድክን

ቁርጥ ቀን መጥቶአል ዘብ እንድንሆን

የምን ማፋግፍግ ማየት ወደሓላ

ግራ ተጋብቶት ህዝብ ሲብላላ

ቀይስ ዘዴውን መታገያውን

አንድ በል ዛሬ ምራን መንገዱን

ጠመዝማዛው መንገድ አጭርና ረዥም

ውሽት ተሽክሜ አልኖርም ዘላለም

ሞረሺ በይ በጀግናዋ እናትሽ በቴጌ ጥይቱ

አብሰሪ ፍትህ ነጻነት ቀና በይ እቱ

ሞርሽ በይ ሂጅ ብረሪ

ለወገኖችሽ ሐቅን አብስሪ

ጋሻውን አንሳ ይሁን ባብቶችህ

ዳግም እንዳትተኛ አድራውን በልተህ

ሶስትኛውን ገጽ ያንብቡ

በቅድም አያቶቸህ

ይሁን በ ቴዎድሮስ

ይሁን በዮሐንስ

በጀግናው አባትህ በአጼ ሚኒሊክ

ነገር አያይዘው ሲገፉህ በእልክ

እስከ ዛሬ ድረስ ምክንያት እያበዛህ

ከዚህ የበለጠ ምን ትጠብቃለህ

ሐገር ስትጠፍ ተጠያቂ አንተ ነህ

ስምተህ እንዳልስማህ ጀሮ ልበስ

የህጻን ጨዋታ ነገር ምለባበስ

አንትም እንደሱ ወንድ አይደለህም

አገር ስትሞት አንተም የለህም

ጎራው በል ጀግና ጎራው ብይ እቱ

ገልብጠህ ጣለው ይሂድ ባናቱ

አገርም እንደ እቃ አዬነ ተሽጠች

በኛ ትክሻ ላይ ኑሮውን ሲያመቻች

ወዴት ዘው፤ ዘው ውዴት ዘጭ፤ ዘጭ

ከአናትህ ወጥቶ አንተን ሲያበሳጭ

ያዝ እንዳትለቀው ባገር ቀልድ የለም

ከአሁን በሓላ አንበረከክም

ወገን ተስባስብ ድምጽህን አስማ

ከሞትች በሓላ እንዳትል ማማ

ወገን ተስባስብ

ያልፈውን አስታውስ ያሁኑንም እስብ

አገር ውስጥም ሆነ ውጭ አገር ያላችሁ

የኢትዮጵያ ልጆች አንድ ሁኑ እባካችሁ

በምሥራቅ በምእራብ በደቡብ በስሜን

በአራቱ ማህዘን

በቃላችን ፅንተን

እንድረስ ለወገን

አገርን ለማዳን።

  1. ይሰማ
    | #1

    የሚያይ ዓይን.. የሚሰማ ጆሮ..ዓዕምሮ ያለው የሚያገናዝብ
    ልብ ያለው ቆራጥ… ይህ ነበር ፍሬው የቃሉ መነሻ
    ከተወለደች ወኔ መቀስቀሻ
    ሴቷ ተናግራለች የክብር መንገሻ::

  2. kegutema
    | #2

    ቦሮፉት መሊ ኢንትሊሎፍቱ ብለ ናል

  3. koster
    | #3

    There will be more imprisonment and killing as long as the opposition is divided and weak. Leaving power means for woyane a lot and do whatever possible not to give up power.

    If Meles/woyane were willing to give power, accepting the result of the May 2005 election was an opportune time. Unfortunately the result was dramatic and was not desired by woyanes and their supporters including the Anglo-Americans. Their Choice is either Meles/woyane or other Anglo-American friendly like Dr Berhanu/Andargatchew not engineer Hailu Shawel.

  4. Anonymous
    | #4

    “ይሄ ዝም ማለት ለበግም አልበጃት
    ሃምሳ ነፍሱዋን ሆና አንድ ነብር ፈጃት”
    ይባላል. በተልይ የአሁኑ የሞረሽ ጥሪ በጣም ወቅታዊ ነው. “ዘቦ እዝን ስሚአ ለይስማእ” ይላል መጽሀፉ. ጆሮ ያለውና የተደናገረው ሁሉ ይህን ጥሪ ይስማ. ምክንያቱን አያብዛ. አንድ ሁነን ብንችል
    ጠላታችንን መጣንብህ እንበለው ያም ቢያቅተን
    ድምጻችንን ሳንከፋፈልን, ስንንዘላዘል እናሰማ.

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።