መድረክ ከቅንጅትነት ወደ ግንባርነት እንዲሸጋገር ምክር ቤቱ ወሰነ !

July 31st, 2010 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

አቡጊዳ – ሐምሌ 24 ቀን 2002

ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ እንደሚገልጸዉ ከእያንዳንዶቹ የመድረክ አባላት፣ ሰባት ሰባት ሰዎችን የያዘዉ የመድረክ ምክር ቤት፣ መድረክ ከቅንጅት ወደ ግንባር እንዲሸጋገር ወሰነ።

የመድረክ አባል ድርጅቶች ከመቼዉም በበለጠ በመከባበርና በመግባባት የሚሰሩ መሆናቸዉን የገለጹት አንድ ያነጋገርናቸዉ የፖለቲካ ተንታኝ መድረኩ ወደ ግንባር ለመሸጋገር ያደረገዉን ዉሳኔ «ከኢትዮጵያ ህዝብ ትርታ ጋር አብሮ የሚሄድ» ሲሉ አድንቀዉታል።

የመድረኩ ወደ ግንባር የመሸጋገር ዉሳኔን ቀጥሎ ፣ የመድረኩ አባል ድርጅቶች ከዚህ በፊት የመድረኩን መለስተኛ ፕሮግራም ሲያዘጋጁ ያስቀመጧቸዉን አንዳንድ ልዩነቶች የበለጠ ያጠቧቸዋል ተብሎም ይጠበቃል።

መድረኩ ዛሬ ባደረገዉ ስብሰባ፣ የአንድነት ምክትል ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸዉ የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ሆነዉ የተመረጡ ሲሆን ፣ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ገብሩ አሥራት የፋይናንስ ሃላፊ ሆነዉ ተመርጠዋል።

በተያያዘ ዜናም ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ እንደሚጠቁመዉ፣ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከሚመራዉ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጋር አብሮ ለመስራት ብሎም ለመዋሃድ የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት፣ በድርጅቱ ዉስጥ ሰፊ ዉይይቶች እየተደረጉ መሆናቸዉን ለማወቅ ችለናል።

በተለይም በየወረዳዉ ያሉ የመኢአድ ደጋፊዎችና አባላት በምርጫዉ ወቅት አብረዉ ከአንድነት ፓርቲ ደጋፊዎችና አባላት ጋር የታሰሩ፣ የተቆሳቆሉና ወከባ የደረሰባቸዉ እንደመሆናቸዉ «በኛና በአንድነት አባላት መካከል ምንም ልዩነት የለም፤ የፖለቲካ ፕሮግራሞቻችን አንድ ናቸዉ። አላማችንና ራእያችን አንድ ነዉ» በማለት ከአንድነት ፓርቲ ጋር አብሮ የመሥራት ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸዉና ግፊት እያደረጉ መሆናቸዉን ዘጋቢዎቻችን ይገልጻሉ።

መኢአድ ከምርጫ 2002 በኋላ ከመድረክ ጋር ተመሳሳይ አቋም ይዘዉ ይንቀሳቀሱ እንደነበረና የ2002 ምርጫ ዉጤትንም እንዳልተቀበሉ የሚታወቅ ነዉ።

  1. ሔውዞ
    | #1

    ዛሬ ደግሞ አዲሱ አርእስተ ዜና መድረክ ግንባር ሆኛለሁ ነው ለሚቀጥለው ምርጫ እያሉ ሊያጃጅሉን:: ግንባር ማለት በረሃ ለበረሃ ጠመንጃ ይዞ ከጠላት ወያኔ ጋር የሚዋደቅ የተደራጀ ሃይል ማለት አይደለም እንዴ:: እነ ነጋሶና ስየ ህዝቡ ሲተፋቸው ምንድነው የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ በማለት ህዝቡን ሊያምታቱት ይሞክራሉ እንደ እባብ ቆዳችሁን አትቀያይሩ ህዝቡ ደም መጣጩን ወያኔ ለመጣል ጡረተኛ ግንባር አያስፈልገውም ጥጋችሁን ያዙ ገለል በሉ አታምታቱ ስራ ካላቹ ከስራ መልስ Part time ጠጃችሁን ላሱ ጠጃም ሁሉ::

  2. ኪሮስ ግርማይ
    | #2

    የህንንንን ቀን የተባረከ ቀን ነው ለኢትዮፕያ ህዝብ

  3. አባተ
    | #3

    መልም በርቱ እስየው

  4. ስለሞን
    | #4

    ይህየአድነት!ጉዳይ ሀዝቡ የሚፊልግው በመሆኑ አውን አዲሆን በታም እመኝ ለሁ አግዝ አብህር ይርዳችሁ

  5. አል
    | #5

    ውሻው የጮኽው ጅቡ ካለፈ ቢሆንም ለላ ጅብ መምጣቱ ስለማይቀር ተዘጋጅቶ መቀመጥ አይክፋም

  6. Helen
    | #6

    መድረክ ከቅንጅትነት ወደ ግንባርነት እንዲሸጋገር ምክር ቤቱ ወሰነ !እጅ እጅ ያለና የታከተ ዜና ነው ። መድረክ፣ ቅንጅት፤ አንድነት፤ በአጠቃላይ እንኚህ ኦፖዚሽን ፓርቲዎች ነን ብለው እራሳቸውን የሚጠሩ ድርጅቶች ለመሆኑ ማንን ነው ኦፖዝ የሚያደርጉት ? በአጭሩ የኢሃድግ ልጥፍ ፓርቲዎች ብለው እራሳቸውን ቢጠሩ አይሻልም ፤ ስም እየቀያየሩና ስልጣን እየተከፋፈሉ በዚህ ድሃ ህዝብ ደም ከሚጫወቱ ፤ ይሄንን ባንዳ መለስ ዜናዊ እስከነቡችሎቹ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሱትን ግፍና ሰቆቃ አልቀበልም እቃወማለሁ ብላ የቆመች የራስዋን ኑሮና ህወት ለመሰዋት የተነሳችና የምትፈጽም ውነተኛ ተቃዋሚ ብርቱካን ሚዴቅሳ ነች፤ ደሞ አይታፈርም እንደኢንጂነር ሃይሉ ሻወል አይነት ከሃጂ ቀበሮ በህዝብ ደም የተጫወተ አሁንም እንደገና በኦፖዚሽንነት ስሙ ይጠራል ፤ ይሄንን በዜና መልክ የምታቀርቡትስ ጋዤጠኞች ለመሁኑ በዜናችሁ ስለምትጠቅሷቸው ግለሰቦች ትንሽ ትንታኔ መጨመር በጋዜጥኝነት ከሚጠበቅባችሁ ስራ አንዱ አይደለምን ? ትላንትና ስለስየ አብርሃ ከወያኔነት በአንድ ጊዜ ዘሎ ወደተቃዋሚዎ ጎራ ገባ ሲባል ሁሉም እንደበግ እየተነዳ ሲከተለው ነበር ፤ይሀውና የምርጫው ጊዜ አለፈ አሁን ድምጹም አይሰማም ለምን ቢባል የተላከበትን ስራውን ጨርሶአል ኦፖዚሽኖች የተባሉትን ትንሽ ጩሀት ሲያበዙ እንደስየ አብርሃ አይነት አስመሳይ ቀበሮ እየተላከላቸው የተቃዋሚውን ሃይል ከውስጥ እየገባ የማኮላሸት ስራውን ይሰራል ፤ በዜናው ላይ እንደተጻፈው “የመድረክ አባል ድርጅቶች ከመቼዉም በበለጠ በመከባበርና በመግባባት የሚሰሩ መሆናቸዉን የገለጹት አንድ ያነጋገርናቸዉ የፖለቲካ ተንታኝ መድረኩ ወደ ግንባር ለመሸጋገር ያደረገዉን ዉሳኔ «ከኢትዮጵያ ህዝብ ትርታ ጋር አብሮ የሚሄድ» ሲሉ አድንቀዉታል” የፖለቲካ ተንታኝ! እንዲህም አድርጎ ተንታኝነት የለም ፤ ለመሆኑ ምን ለማድረግ ነው የህዝቡን ትርታ ማዳመጥ የህዝቡ ትርታ እኮ ሲባል የክራር ወይንም የማሲንቆ ቅኝት የሚአዳምጡ መሰላቸው እንዴ ፤ ይሄ ህዝብ የሚደርስበትን ሰቆቃና ግፍ ጩሀት እኮ ነው የሚያዳምጡት እና ምን አይነት መፍትሄ ለማቅረብ ወስነዋል ፤ህዝቡን ና ተነሳ አደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ እናድርግ እንተባበር እንውጣ ሊሉት ነው ወይስ እንደተለመደው ህዝቡ ስቃይ ላይ ለማላገጥ ነው ።

  7. koster
    | #7

    What does it mean, does it mean uniting with MEDREK too?

  8. Adunga
    | #8

    Please go together.

  9. Anonymous
    | #9

    ይሁን እስቲ ድጋፋችን አይለያችሁም:: ነገር ግን አንዳንድ ነጥቦችን ግልጽ ማድረግ አለባቸው
    1- ስላለፈው ምርጫ ጠንካራ የሆነ አቋም አልወሰዳችሁም:: ምርጫውን የተቀበላችሁት አይነት ሁኔታ እየታየ ነው :: ለምሳሌ በስብሰባ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞ እንዲኖር እንኳ አልተሞከረም::
    2- ብሩህ የሆኑ ወጣት አባላትን አመራሩ ውስጥ ማሳተፍ አለባችሁ
    3-የህዝብ ግኙነት ክፍል የፓርቲው ልሳን ነውና ቀልጣፋ አንደበተ ርቱእ የሆነ በንግግር ህዝቡን ከጎን ማሰለፍ የሚችል ሰው ያስፈልጋል የፖርቲውን አስተዳደር ላይ ያሉ /የነበሩ ሰዎች ፓርቲውን መምራት ላይ ያተኩሩ
    4-ውስጣዊ የማጥራት ስራ መሰራት አለበት:: ደካማውን በጠንካራ ዓላማውን ለይቶ በሚያውቅ የመተካት ስራ በአባላት መሰራት አለበት
    5-ፍርሃትን እናስወግድ በልምምጥ የሚገኝ የፖሊቲካ ድል አይኖርም

  10. MATEWOS
  11. Helen
    | #11

    as long as ato hailu shawel and his power and money monger friends are removed from MEAD, both udj and mead can merge and work together.

  12. ቲ ደብሩ
    | #12

    ወደፊት በርቱ ግን ለምን አትቀናጁም ? ምክንያቱም ወደ አንድ ለመምጣት የፓርታዎች መክሰም አስፋላጊ ነው ::

  13. ሞላ
    | #13

    ሔለን እግዚአብሀር ይባርክሽ አስተያየትሽን ወድጀዋለሁ::እነዚህ የባንዳና የሰርጎገብ ቡዲኖች በየትኛውም መስፈርት የወያኔን እድሜ ከማራዘም ውጭ የሚፈይዱት ነገር የለም!!!!!!!!!!!!!!!!::ኢትዮጵያን እግዚአብሀር ይጠብቃት.ሺህ ግዜ ቢቀናጁ ቢውሉ የሚፈይዱት ነገር እንደሌላቸው አንዘንጋ በመጀመሪያ እነዚሰዎች እነማን ናቸው ? እውነት ተቃዋሚዎች ናቸው? እነዚህን ጥያቄዎች ከልብ ማያት ያስፈልገናል ዝም ብለን ተቃዋሚ ነኝ ላለው ሁሉ ከማጨብጨባችን በፊት,እባካችሁ እናስተውል::

  14. Action speaks louder than words
    | #14

    well done medrek.The ethiopia’s people want to live together as usual. fragemenation for TPLF, fOR OLF AND For the former siedbare military and the current ONLF.UNity for ethiopia’s people.Even AEUP is far better with our selfish and iegoeists hailu shawul, still there is some thing fishy. getachew mengist and mamushet are the right hands of TPLF. so unity is brings strength.

  15. ሞላ
    | #15

    ተቀናጁ ነበር ጨዋታው አሁን ደግሞ ግንባር ፈጠርን በሚል ሌላ አስር አመት ህዝቡን ለማታለልና በቀላሉ ለገዢው መደብም ጥቃት እንዲጋለጥ የተነደፈ/የታለመ/ ከመሆን የተለየ አላማ የለውም::የግንባሩ ተዋናይ የሆኑት ግለስቦች የፈጠሩት የማዳከሚያ ስልት መሆኑን ልንገነዘብ ያስፈልጋል::እትዮጵያን እግዚአብህር ይጠብቃት!!

  16. አንበሴ
    | #16

    እናንት ተቃዋሚ ነን ባዮች ቀላጆች: ምንም ምንም አላችሁ እዚያ ፓርላማ ተብዬ አዳራሽ ውስጥ ተቀምጣችሁ ድመዛችሁ አይቀርባችሁ ነገር: ፋሽስቱን ወያኔ አጅባችሁ በነዚያ ምስኪን ወጣቶችና አረጋዊ ኢትዮጵያውያን መቃብር ላይ ተቀማጣችሁ ለዳግም የወያኔ ሚዜነት መጋለባችሁ ይቅር የማይባል የፋሽስት ወያኔ ተባባሪነታችሁ የሚያስገርም ሳይሆን የሚያናድድ ተግባር ላይ ስለመሆናችሁ ግብራችሁ ሁሉ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በግልጽ በመታየታችሁ ከፋሽስት ወያኔ በበለጠ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን በድላችኋል:: የሚከተላችሁም ሁሉ ፋሽስት ወያኔ ነው:: ውጉዝ ከመ አርዮስ ሁሉ ተብሏል በፓርላማ ተቀምጦ የሚበላ የወያኔ አጃቢ ሁሉ::
    ኢትዮጵያውያን በሚገባ አውቀዋችኋልና ከናንተ ጋር የሚጃጃል ከእንግዲህ በኋላ አይኖርም:: የሚከተላችሁንም ሁሉ ከሃሽስት ወያኔ ጋር ፈርጀናችኋልና ባዶ ቤት ብትንጫጩ የሚሰማችሁ የለም::
    ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ለፍትህ ለነጻነትና ለዲሞክራሲያዊ መብት ከግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አባሎች ጋር በመጀመሪያው ረድፍ ላይ አንድነታቸውን ክንዳቸውንና እውቀታቸውን አስተባብረዋል::

    ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!!!

  17. Anonymous
    | #17

    የእ ሂዝብ ገንግኑንት ሓልፍ ይ

  18. Anonymous
    | #18

    BEYEN PETROS AS PUBLIC RELATIONS OFFICER. WHAT A JOKE. HE IS TONGUE TIED. SEIYE WAS BETTER. WE NEED AN ORATOR WHO CAN BOLDLY SPEAK WITH A DEEP VOICE LIKE MENGIE THE WOYANNE GERAFIW OR OBAMA.
    I SEE NO BUSINES WITH THE TURETEGNA GROUP. WE NEED FRESH HORSES NOW.

  19. Lafiw
    | #19

    WE NEED FRESH HORSES- ORATORS OF SOUND MIND FOR THE PUBLIC RELATIONS. NO BUSINESS WITH THE TURETEGNA GROUP.
    TELL BEYEN PETROS TO GO. HE PARTIED WITH MELES AT ONE TIME. HE IS A LOSER AS LIDETU DID

  20. Anonymous
    | #20

    ፕልስ ትንሽ ከመናገሩህ በፈት አስብ@ሔውዞ

  21. አንበሴ
    | #21

    ግምባር በሚል ቃል ኢትዮጵያውያንን ማታለል አይቻልም:: ግምባር ቃሉን ብቻ ሳይሆን: ግምባር የሚለውን ቃል በፓርላማ ወንበር ሳይሆን: ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግምባር ብላችሁ ስለኢትዮጵያ ሃገራችሁ ወገናችሁ ስቃይና እንግልት ግድያና አፈና ወደነጻነት ጎዳና እንድታመርሩ የመላው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ወቅታዊ ጥሪ ነው::
    በፓርላማ ወንበር ተቀምጣችሁ ወያኔን በትያትሩ በተውኔቱ ጩኸት ማስደሰት: እውነታውን ለዓለም መንግስታትና ሕዝብ እንዳናጋልጥ መጋረጃውን ከዘረጋችሁላቸው: ወያኔነታችሁን በግልጽ አረጋገጣችሁ ማለትና የኢትዮጵያውያን ሌላው ቀንደኛ ጠላቶች መሆናችሁን በራሳችሁ ጊዜ መሰከራችሁ ነውና ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ ከመሆናችሁ በፊት ለማሰብ ምንም ወደኋላ መሄድና ብዙ ማሰብ የሚጠይቅ አይደለም::
    ትግሉ ይቀጥላል::

    ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!!!

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።