እሪ በይ ሀገሬ! – ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

September 24th, 2010 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ስማ ወገኔ! ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ከዚህ በላይ ክፉ ቀን የለም!! ቀን ሳለ የጨላለመብን፣ የህይወት ጣዕም ጠፍቶብን ምሬትና ሐዘን ሲፈራረቁቡን፣ በገዛ ምድራችን ባሮች በስደትም ባሮች፣ በገዛ ምድራችን ምጻተኞች በእንግድነት የሰፈርንባት ምድርም እንዲሁ ስደተኞች፣ በገዛ ምድራችን ተገፍተን እና አልቅሰን በስደትም በኃሳብ ማቀን እስከመቼ ነው?

እንግዲህ እሪ በይ ሀገሬ! የሕዝብሽ የርሀቡ ጽናት፣

የልጆችሽ ጉስቁልናና ሰቆቃ፣
ባርነት – ዋይታና እሪታ።

እሪ በይ ሀገሬ! መሬትሽ ተቸብችቦ ልጆችሽ በስደት ሲንከራተቱ
በአንጻሩ በዕዳን በጉያሽ ሲርመሰመሱ።

እሪ በይ ሀገሬ! አንድ ሳለን የለያየን የፖለቲካ መሪዎችሽ የልብ ጥመት፣

ክፋትና እልከኝነት።

እሪ በይ ሀገሬ! የእናውቅላችኋለን ፖለቲከኞችሽ ክህደትና ዲስኩር – ሲጠብሰን፥

ራስ ወዳድነታቸው – መንገድ ላይ ሲያስቀረን፥

መራራነታቸው – ሰላማችንን ስያሳጣን፥

ጥላቻቸውና ንቀታቸው – ጾማችንን ስያሳድረን።

እሪ በይ ሀገሬ! የኃይማኖት መሪዎችሽ ድንቁርና – ከፈጣሪ ሲለያየን፥

ሌብነታቸው – እጃችን በአፋችን ስያስጭነን፥

አድርባይነታቸው – እንደ እሳት ሲፈጀን፥

ምንደኝነታቸውና ነፍሰ ገዳይነታቸው – ከሀገር ሲያስኮበልለን።

እሪ በይ ሀገሬ! ልጄ ስትዬ በታሪክ ያስተዋወቅሽን ፈላስፋው እነ ዘርዓ ያዕቆብ ታሪካቸው በሰማንባትና
በተመላለሱባት ምድር ኑሮአቸው ሲቀርባቸው ለቁራሽ ዳቦ ሲባል ወሬኞች፣ ሐሜተኞችና
አሉባልተኞች ከለባት ልጓማቸው ፈትተው ባልተገራ አንደበታቸውና ብዕራቸው ሲሳለቁብሽ፥

እሪ በይ ሀገሬ! ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያውያን ይተዉልን ዘንድም እሪታሽን አስተጋቢልን።

እሪ በይ ሀገሬ! የማጸንሽ ፍሬዎች ከጣላቶሽ አብረው ሊያወድሙሽ ሲመክሩ፥ እሪ በይ ሀገሬ! ጩሆትሽን አሰሚ ቸሩ መድኃኔአለም አይቶ ቢራራልሽ፣

እሪ በይ ሀገሬ! እንግዲህ አምላክ አባ አይደለም ሰምቶና አይቶ ዝም አይልሽ!!

የሰው እርዳታ የማይሻ በወጀብም በአውሎ ነፋስም መንገድ ያለው መንገደ ብዙ እግዚአብሔር ይርዳን! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

  1. Anonymous
    | #1

    በደርግ ግዜ የትኛህ እስከአሁን ድረስ በህልም ነው ያለሀው መሰለኝ? እርይ የሚባልበት ግዜ አልፈናልና ወንድሜ ነቃ በል.

  2. Anonymous
    | #2

    እባክሕ ወገኔ! ዲያቆን የሚለውን ስም ትተህ ሌላ ማእርግ ብትፈልግ! ለምሳሌ ዲያቆፖለቲከር!!

  3. jegnaw
    | #3

    I know Annonymous from where you are coming.you have the origin.your birthplace is Dedebit.you are the termite.God is not like aba diabilos.Derg is 100%much better interms of maintaining the national soverginity and unity of the country.ነቃ ማለት የሚገባህ አንተ ወያኔ ነህ::አንድ አባባል ልንገርህ በራስ ኣሊ ጊዜ የደነቆረ ሁልጊዜ ራስ አሊ ይሙት ይላል:አትጠራጠር እግዚአብሄር ለፍርድ ያበቃችሁአል

  4. ሳሙኤል ጎሽ
    | #4

    ይህንን ግፍ በዝምታ መሸከም ስብ እናን ማዋረድ ብቻ ሳይሆን ከእንሥሳ በታች መሆን ነው!!!!!!!!!! እረ በጋራ እሪሪሪሪሪሪሪ !!!!! እንበል! እንነሳ ! እናሸንፍ !! እስከመቼ እንዲህ ተዋርደን?

    http://www.ethiopianreview.com/content/29535

  5. አበሻው
    | #5

    እሪ አንልም ጀግና እሪ አይልም የሚመስለው ነገር ያረጋል እንጂ እሪ እሪ ለወያነ እሪ ለሻብያ ወዳ ጀግና አገር እሪም አትልም አታቀውም

  6. spoiled eggs
    | #6

    Anonymou, Your time is numbered, just wait untill the sword touchs your neck. Ethiopians are united against aparthied system in ethiopia . Criminals and their co will not have a single place to hide them selves. because the world became a small village at this time.

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።