መለስ ሞቱ ታየዉ መሰለኝ- በሸንቃጣዉ ዘካሊፎርኒያ

December 9th, 2010 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

አምባገነኑ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለብዙ ጊዜያት ህክምና ከዱባይ እያገኘ ሳለ ድንገት ስትሮክ (strokeየጭንቅላት ዉስጥ ደም መፍሰስ ማለትም ዋገምት የማያድነዉ) መቶት የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ህክምና የሚያስፈልገዉ መሆኑ ስለታወቀ እ. አ. አ. በነሀሴ ወር 2009 ዓ. ም. የቤልጂየም ዋና ከተማ ወደ ሆነችዉ ወደ ብራሴልስ በአስር ታጣቂዎች ታጅቦ በጥድፊያ ተጓዘ። የተቀላጠፈ የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ህክምና ባይደረግለት ኖሮ ይሄኔ መለስ ቆሞ ባልሄደም ነበር። ከዚህ ህክምናም በፊት የአእምሮ መታወክ በተደጋጋሚ ደርሶበት እንደሆነ በሰፊዉ ባይዘገብም ተወርቷል። እንደ በረከት ስምኦን ደቡብ አፍሪካ ለአእምሮ መታወክ ህክምና ባይሄድም በአገር ዉስጥ ባሉት የታወቁ የህክምና ባለሙያዎች እንደታከመም ተሰምቷል።በስትሮክና በአእምሮ መታወክ ተደጋግሞ መከሰት መለስ የሞት እምቢልታዉ ሳይሰማዉ የቀረ አይመስልም። ይህ ከሆነ ደግሞ በትረ-መንግቱን ለሚቀጥለዉ ግለሰብ ለማስረከብ በምርቃና ሳያስብበት እንደማይቀር አልጠራጠርም።

መለስ የህወሀት ነባር መሪዎችን በዘዴ ጥግ ያስያዛቸዉ እሱ ከሞተ ከእሱ ቤተሰብ ዉጪ ማንም ስልጣን ላይ እንዳይቀመጥ ለማድረግ ያቀደዉ ፕላን ሳይሆን ይቀራል እንዴ? መለስ እንደሚለዉ ወጣት ምሁራንን ለማስገባት ነዉ ወይ የስልጣን ሽግሽግ ያደረገዉ? ከስልጣን ድልድሉ እንደታየዉ ከሆነ የአመራር ልምድ የሌላቸዉና ፍጹም ታዛዦች የሆኑ እንጂ ለምን ይህ ነገር ወይም ያ ነገር ተደረገ ብለዉ የማይጠይቁ “አቤት ባዮች” እንደሆኑ ነዉ የምንረዳዉ። ከድሮዎቹም የህወሀት አመራር አካላት ቢሆን 47% የሚሆኑት በተለያየ የስልጣን ደረጃ ተመልሰዉ የተመደቡት ለቁልፍ ስልጣን አስጊ በማይሆኑበትና የመለስንም ስልጣን በአይነ ቁራኛ መጠበቅ በሚችሉበት ሁኔታ ተደርጎ የተመደቡ እንደሆነ ነዉ የሚገባኝ። የጦር ሀይሎችንና የደህንነት መዋቅሩን በሚተማመንባቸዉ ሰዎች አመራር ስር እስካደረገ ድረስ መለስ ለስልጣኑ በአሁኑ ወቅት ማንንም አይፈራም። የተጠናከረና የተደራጀ ተቃዋሚ በሌለበት ምድር ሊያስፈራዉ የሚችለዉ ምናልባት የዉስጥ ወታደራዊ ተቀናቃኞች ካልሆኑ በስተቀር አሁን በህወሀትና በኢህአዴግ አመራር ላይ ያሉት እንኳ አይደሉም። እነዚህ የታዘዙትን አቤት ጌታዬ እያሉ ከመስራት በቀር ምንም ማድረግ የማይችሉ መሆዶዎች ናቸዉ። ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአልጋ ወራሽነት ያለች ትመስላለች እንደ አዲሱ የስልጣን ድልድል ከሆነ። መለስ ድንገት ስትሮክ መቶት ቢሞት ያለምንም ጥርጥር ወ/ሮ አዜብ ስልጣን ላይ ጉብ እንደምትል አልጠራጠርም።

ዊኪሊክስ ከሰሞኑ ባጋለጠዉ የዲፕሎማቲክ ኬብል መረጃ መሰረት የመለስ ጤንነት እያሽቆለቆለ እንደሆነ ነዉ የምንረዳዉ። የዩናይትድ ስቴትና ምዕራባዉያን አገሮች የወደፊቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ሳያሳስባቸዉ እንደማይቀር እገምታለሁ ከዚህ መረጃ አኳያ ስመለከተዉ። መለስ ፊቱን ወደ ቻይና እንዳዞረ በሚገባ ሁኔታ በተለይም ዬዩናይትድ ሰቴትስ መንግስት እንደተረዳዉ መገመት አያዳግትም። በስልጣን ሽግሽጉ ስዩም መስፍንን በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለማድረግ መለስ ሞክሮ የተሰጠዉ መልስ ቢኖር ነባር አብዮተኞችን አንፈልግም የሚል ነበር። ይህ ሙከራ ለመለስ በቂ መልስ ሊሰጠዉ ይችል ነበር።ሆኖም ግን ምናልባት አባይ ጸሀይን ከተቀበሉልኝ ብሎ እንደገና ሲሞክር ነባር አብዮተኞችን አንቀበልም የሚል መልስ ነበር በድጋሚ ከስቴትስ ዲፓርትሜንት የተሰጠዉ። ዶ/ር ግርማ ብሩን ግን እንደሚቀበሉ ስቴት ዲፓርትሜንት ጨምሮ ገልጾ ነበር። ይህ የስቴት ዲፓርትሜንት መልስ የሚያስረዳን ነገር ቢኖር መለስ ፊቱን ወደ ቻይና መልሶ እርዳታ ከምዕራቡ ለማግኘት የወጠነዉን ስትራቴጂ ለመቃወም እንደተደረገ በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል። የመለስ ስትራቴጂ ሳይሰራ ቀረና ስዩም መስፍን በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ሲሆን አባይ ጸሀይ ደግሞ በኢትዮጵያ የስኳር ሚኒስትር ሆነ። ጉድ ያሰኛል! አባይ ጸሃይ “ጓል አስመራይ ጓል አስመራይ ማለት ሹቓር ነሽ” እያለ በአደባባይ እዳይዘፍን ብቻ ፍሩልኝ።

መለስ አንድ ቀን ወይም አንድ ጊዜ እንኳ “እናት አገራችን ኢትዮጵያ” ሳይል ለኢትዮጵያ ልዑልና ከልብ የተቆረቆረ ለመምሰል ከግብጽ ጋር እንካ ሰላንትያ ተያይዟል። የአባይ ወንዝን ጉዳይ ሳያንቀሳቅስ ሞተ እንዳይባል ነዉ ወይንስ ለሌላ ነገር ? ይህ እንኳን በእኔ ግምት ዲያስፖራዉን ሊያታልል ወይም የምርጫ 2010 ማረሳሻ እንዲሆን የወጠነዉ ስትራቴጂ ይመስላል። መሞቻዉ የታየዉ ሰዉ ቀና ቀና ያሳስበዋል፣ ይቅርታም የመማጸን ሁኔታ ይታይበታል። መንግስቱ ሀይለማርያም በቀይ ሽብር ወቅት መሞቻዉን ሳያዉቅ እንኳ አብዮት ልጅዋን ትበላለች እያለ በቀይ ሽብር ለተጨፈጨፉት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቋል። መለስ ግን ፍንክች አይልም ሞቱ እየተቃረበ ሲመጣ።

መለስ ሌት ተቀን እንዴት አዜብዬ በ2015 ምርጫ እርሱን ተክታዉ እርሱ ደግሞ ቤተመንግስት ተቀምጦ በሪሞት ኮንትሮልና በምርቃና ብርታት አመራር መስጠት እንደሚችል የሚጨነቅ ይመስለኛል። የ”አልሸሹም ዞር አሉ” ፖለቲካ አይደለም ብሎ እነደሚከራከር አልጠራጠርም። ምክንያቱም አንድ ነገር ትክክል ሆነ አልሆነ መረጃ መፈለግ አያስፈልግም መለስ አንድ ነገር ከተናገረ። ልክ 99.6% ድምጽ በማግኘት ምርጫዉን አሸንፈናል እንዳለዉ ሁሉ አዜብዬ ደግሞ ስትመረጥ ሌላ ወቅታዊና ተስማሚ ሊሆን ይችላል የሚለዉን ምክንያት ይሰጠንና ከተቀበላችሁ ተቀበሉ፤ እምቢ ካላችሁ ደግሞ ገደል የመግባት መብታችሁ የተጠበቀ ነዉ ይለናል። ልጆቻቸዉ ወይም የቤተሰብ አባላቸዉ የተኳቸዉ አምባገነኖች በተራቸዉ ልጆቻቸዉን ከመተካት ወደሗላ አይሉም። ምክንያቱም ስልጣን፣ ገንዘብና ሙስና የጥማሉና። “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” የሚባለዉን ተረት መለስና አዜብ በሚገባ የተረዱት ይመስላል።

እስከ ምርጫ 2015 ድረስ ወ/ሮ አዜብዬ ብዙ ሴሚናሮችን በምርቃና ልትከታተልና ልታጠና ነዉ፣ በህወሀትና በኢህአዴግ የፖሊት ቢሮዎች አባልነት እንዲሁም በትግራይ ልማት ድርጅት መሪነት በቴልቪዥንና በሬዲዮ እየቀረበች መግለጫዎች ልትሰጥ ነዉ፣ ድስኩሮችንም ልትደሰኩር ነዉ፣ ብዙ አገሮችን ደግሞ ከመለስ ጋር አብራ በመጎብኘትና ከአገር መሪዎች ጋርም በመገናኘት የዉጪ ፖሊሲ ልምዷን ልታስፋፋ ነዉ ልክ ሂለሪ ክሊንተን ለፕሬዚደንነት ስትሮጥ የስራ ልምዷን እንደገለጸችዉ። እስከ ምርጫዉ ድረስ ወዲ አርማጭሆኢቷ አዜብዬ ብዙ የስራ ልምዶችን ታከማቻለች ማለት ነዉ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፑበሊክ ሴት መሪ ለመሆን።

ሟርተኛ እንዳትሉኝ እንጂ እኔ እየታየኝ ያለዉ ነገር ቢኖር ይህ ነዉ። መለስ መሄጃዉ የታየዉና የተቃረበ መሰለኝ። መልኩም በቴሌቪዥን ሲታይ እንደ በፊቱ አይደለም። የሆነ የሚያጠራጥር ገጽታ ፊቱ ላይ የሚነበብ ይመስላል። መለስ ድንገት ካመለጠ ልንፈራ የሚገባን ስለአዜብ ስልጣን ላይ መዉጣት አይደለም። ስለወታደራዊ ብጥብጥ እንጂ። እግዚኦ እናት አገራችንን ከመጥፎ አደጋ ጠብቃት እያልን እንጸልይ። አሜን!

shenqatawu@yahoo.com

  1. ያደታ
    | #1

    ደንድር እውነት ብለካል አማራ የዘር በሽታ የለበትም. ይህን የሚክድ ካለ እውነት ማውራት የማይወድ ዎያኒ ነው. አማራ በስልታን ላይ በነበረበት ዘመን ይን እንደ ትግሪዎች ይህን ተምረው ቢኖር . ዎያኒም አይገባም ነበር. በቅንነት ይደርግ ስርሃት ሰለመረረው ብቻ ዎያኒ አግዞታል. ውለታ የማይውቅ ቅሊታም ዎያነ ግን አሁን ከመረቱ እያፈናቀለው ነው.አሁን የጊዘ ነገር ሆነና ትግሪም አማራን ይስደብ???? ጥቂት የማይባሉ ኦሮሞችም ብንሆን እይደነፋን ነው ለአይምሮዪ ዋጋ ለመስጤት ስል እውነት እናገራለው.የአማራ ባለስጣኖች ደንፍተው ይሆናል ግን ተራው ህዝብ ከማንም ጋር ተመሳስሎ ነበር የሚኖረው. አሁን ትግራዮችን እዩ. ምንም የማይጤቀሙት እንኩአን እንደት እንደሚያረጋችው እዩ.ግን አማራው አሁንም ቢሆን የ ዘር በሽታ አይያዘው. እነሱ በዚ ነገር ላይ ከተነሱ ነገሩ ሁሉ ከባድ ነው ለዚ ነው ዎያኒ በዚ ነገር ሊበክላችው ሞክሮ አልተሳካለትም. የሂትዮፕያን አንድነት ስለማይፈልግ . በተረፈ የዚች የበረሃ አይጥ ልክስክስነት የማይገርመው አበሻ የለም ምን ታርግ ያለቦታዋ ገብታ አይ አቢብ መለስ ለ ሰማይ ቢትሽ ነው የምትስንቂው.በተረፈ ድል ኦሮሞ, ለአማራ እና ለጉራጊ ህዝብ (ለኢትዮፒያ ህዝብ) ሸንቃታው ቀጥል በርታ ዎያኒም ይቃተል አንተም በርታ

  2. የገረመው
    | #2

    እናንተ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር የመንግስቱ ሚስት (ውባንቺ ) አንድም ግዚ በተለያየ ነገር ስትታማ አትሰማም ያው ደርግ እንደ ዎያኒ ደም አፍሥአል . በተረፈ ሚስቶቻቸውን ስንመለከት እውነትም ይቺ የበርሃ አይጥ በየንግዱ ስትልከሰክስ ትታያለች. ደሞ የሰው መውደድ የለላት ወዘ ቢስ ደርቅ ነገር ነች.መለስ ግን ብልጥ ነው ስልታን እንደያዘ አዚብ አትታይም ነበር የመቸረሻ ሃግሊ ነበረች በዛ ላይ 2 አስተማሪ ነበር በፈረቃ የሚአስተምራት. ትንሽ እቢት ውስጥ ከተማረች በዋላ መታየት ጀመረች. ብልጥ ነው እዚ ላይ. በተረፈ ነጋዲ መሃል እየገባች መፎካከር ሆኖል ስራዋ. የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ቀረጥ አለመክፈላ ነው. የደርግ ሚስት ክብራን እንደተበቀች ሂደች. ጥሩ አረገች. ይቺ ደሃ የደሃ ዘር የት ልትበላው ይሆን ?? የህዝብን ገንዘብ እየዘረፈች. የርዳታ ገንዘብ ያሸሻሉ ህዝብ በረሃብ ያልቃል.በተረፈ ሸንቃታው በርታ በርታ!! በርታ! አበበ አንተ ስምክ አበበ ሳይሆን ከሰመ ነክ. የሰው ሞት የምተምኝ እናንተን ብሎ ዲሞክራሲያዊ ላልከው አንድ ጥያቂ ልተይክክ አንተ የምትደግፈው መንግስት ድምሲ ይከበር ብሎ ሰላማው ሰልፍ ያረጉት ላይ ውሃ ዎይም የሚያስለቅስ ችስ መርቸት ሲችል ደብተር ለያዘ ተማሪ መሃል ከተማ ታንክ ያስገባና 199 ዘጎችን በእንሥሶች (በ አጋዚ ) ያስቸረሰ መንግስት ነው. ታዲያ ይን መንግስት እስከደገፍክ ድረስ ዲሞክራሲ የሚለውን ዎርድ መተቀምም የለብክም .ለአንድ ጂኖሳይድ ለሚያካይድ መንግስት ሞትን መመኝት የሚገርም አይደለም. ለሰው ነፍስ የምታዝን ከሆነ ደሞ ዕድሚውን ላገባደደ ሳንባው ጉበታችው በመጥጥ እና በቻት የላሸቀ, አይምራቸው ደሞ ያፈሰሱት ደም ለሊት በህልማቸው አስም እየመታ እና እያባነናቸው ለታመመ አይምሮ የሰሩት ስራ እንቅልፍ ነስታቸው በሽተኝ አይምሮ ላላቸው ሳይሆን ምንም ሳያዩ ላለቁ ሰዎች,እኒን ለምን አልደገፍክም ተብለው በእስር ለሚማቅቁ, በየክፍለ አገሩ የውህ ሽታ ሆነው ለሚቀሩ, የ 97 ምርቻ ጊዚ 60 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በረሃ ሲወስድ በአውረ ለተበሉ …. የ ዎያኒ ጉድ ብዙ ነው. እናም ማዘን ካልብክ ለነዚ ነበር.ግን አልፈርድብክም የሚወረወርልክ ፍርፋሪ እያነቀክ እንዲት እውነት ትናገራለክ? ውሻ በበላበት አይደል የሚቾህው. ደሞ ዎያኒን ተቃዋሚ አትምሰል አሰመሳይ ውሻ ሳይሆን ታማኝ ውሻ ሁን. ሸንቃታው በርታ! ይ መንግስት ለምን ተዋረደ የሚሉትን እናቃቸዋለን. ሞት ለወያኒ እና ለወሾቹ. ድል ለኢትዮፒያ ህዝብ!!!!

  3. አብነት
    | #3

    የማነህ ባክህ ዘር ከዘር ጋ እያባላህ አንድ ነን የምትል እንዳንተ አይነት ጭንቅላት የሌላቸው ሰዎች ለማስተማር ነው የኢትዮጵያ ህዝብ የሰለቸው በጥቂት ፖለቲከኞች አገር ሙሉ እምትሰድበው መጀመርያ የጻፍከው ቃላት መልሰህ አንብበው ፊደል ተማር

  4. ደንድር ሙስተፋ
    | #4

    በመጀመርያ ደረጃ አሪፍ ጽፈሃል ግፋበት. ዎያኒን አቃጥላቸው. ሽንቃታው. በተረፈ እነ የሚገርመኝ አማራ ለአመታት ሲገዛ እንዲ አላነፋም. ትግሪዎች ምነው?… የደሃ ነገር ሆነና. የጉራጊ ህብረተሰብ ለአማራው ህዝብ አክሮት አለው. እውነት ለመናገር አስተዳደር ያቁበታል. ጥቂት ጥፋት ሊኖር ይችላል .ዎያኒን ማየት ነው. ከ መቶ 90% የተበላሸ ነው ምን ያርጉ ያለቦታቸው ገብተው.እነሱ ለሹፍርና አሪፍ ናቸው. በነሱም ብሶ የአማራን አስተዳደር ጥቂት ጥፋት ይቆጥራሉ. የነሱ ተራራ የሚያክል ጥፋት አይተው የሚያሰላስል አይምሮ የለላቸው የህዝብ ፍቅር እና መውደድ የለላቸው ናቸው.የጉራጊ ህብረተሰብ ለአማራው ትልቅ አክብሮት አለው. አማራዎች የዘርኝነት በሽታ የለለባቸው አርቆ አሳቢ ህዝብ ነው ዛሪ የጊዘ ነገር ሆነና የማንም መሃየም አፍን ሊከፍትባቸው የገርመኛል. በዘር ነገር ከተነሳባቸው ደሞ በታም መጥፎ ነው. ይህ ከነሱ ይራቅ!!! በተረፈ አዘብ መስፊን የ ኢትዮፒአን ህዝብ መዝረፍ ብታቆም ይሻላታል የደሃ ነገር አልተግብ ብላላች የት አባታ ልትበላው?? ነው ዎይስ በሰማይ ቢት የሚተቅማት መሰላት ይቺ አስቀያሚ አጋሚ.

  5. ትግል
    | #5

    እኢትዮፐያ እወድሻላሁ

  6. ጃርሶ
    | #6

    አሁንኮ የተቸገራችሁት አማሮች ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል እምትልዋት ነገር ናት አሁን አማራ ቢገዛም አታስቀምጡትም ለምን ሁላችሁም መግዛት ትፈልጋላቹ አታገኙትም እንጂ አለፈባቹ ከንግዲህ ህዝብ ነቅታል ኦሮሞም ዳግም በናንተ ላይገዛ ትግሬውም ጉራጌውም ቤንሻንጉሉም ኩናማው አፋሩ ሌላውም ጎሳ ነቅቶባቹሀል እንደገና ረግጦ ለመግዛት ነው አላማቹ የለም ለምን አማራ ግዝቶን ጥሩ ነገር አላየንም አሁን ሰው በቓንቓው መጻፍ ማንበብ በጀመረበት ሳአት ዳግም አማራ ይገዛል ብላቹ አትገምቱ የራሳችሁን ክልል መግዛት ትችላላቹ ኦሮምያ ግን ዳግም ባማራ አትገዛም ከተገዛች ባገርዋ ልጅ ኦሮሞ ነው እምትኖሮው አሁን አማራ ዘር ከዘር አይለይም አላቹ ወደ ሓላ ዞር ብላቹ ታሪክ አንብቡ ለማታለል አትሞክሩ ስማቹ እየቀየራቹ እኛ ኦሮሞዎች ከአማራ ጋር ምንም ጸብ የለንም አንድ ነን ካማራ ጋ ከመች ወዲህ በኦሮሞ ህዝብ አትቀልዱ የተቀለደብን ጊዘ በቂ መሰለኝ አሁን ለትግሬ እምትሰድቡት እምታዋርዱት ስልጣን ስለወሰደባቹህ እንጂ በክፉ ስራ ከሄድን አማራ የሰራው ይብሳል

  7. ለማ
    | #7

    ያደታ እውነት አንተ ኦሮሞ አይደለህም አንዴ አማራ በዘር ከተነሳ አለቀልን ትላለህ አንዴ ኦሮሞ ና አማራ ፍቅር እንደሆኑ ታወራለህ ባይገርምህ አማራ ነህ ኦሮሞና አማራ በምንም መልኩ ፍቅር ሊሆኑ አይችሉም በህዝቡ ብቻ ሳይሆን ገዢዎችም ጭምር ኦሮሞን እንደ ሰው ሳይሆን ሲታይ የነበረው እሱን ታቀዋለህ አሁን እዚህ መግለጹ አስፈላጊ አይመስለኝም; በዚሁ ቂሙ ህዝቡ ዘንድ አለ አገራችን ውስጥ ወደ ሁላ ያስቀረን ነገር ቢኖር እርስ በራስ መናናቁ ነው አማራ ኦሮሞ ይላል ትግሬ አማራ ኦሮሞም ትግሬም አማራም ጉራጌም ሁሉ የየራሱ ዘር ማወደስ ይወዳል አገራችን ባለን አንድነት አምነን አንተ አማራ ትግሬ ኦሮሞ ጉራጌ አፋር ኩናማ ምናምን ሳንባባል ብንኖር ከሁሉም የበለጠ አድገን ነበር ያማራ ትቢት ነው ለዚህ ሁሉ እሚያበቃው እና እባካቹ እርስ በራስ እንከባበር ማንም ከማንም አይበልጥም አናስበልጥ አማራ ምን ስለሆነ እሚገዛው ሌላው ዘር ምንድንነውና የማይገዛው ከየትኛውም ዘር ይሁን አድልዎ በሌለው ሳይከፋፈል አንዲት ኢትዮጵያ እኩል አርጎ እሚገዛ ይሁን ብቻ መከፋፈል ይቅር እኔ ከሌላው ዘር እበልጣለሁ ይቅር ቸር ይግጠመን

  8. ኩማ
    | #8

    ጃርሶ ጥሩ የሚያመዛዝን አይመሮ አለክ ቂቂቂቂቂቂቂቂቅ ስማ ኦሮሞ እንደዚ ግዚ የተሰቃየበት እና የተዋረደበት ዘመን የለም አንተ ታሪክ አንብቡ አልክ? የዎያኒ ታሪክ አሁን ስልታን ላይ ሆኖ የሰራው እውነተኝ ታሪክ ሊወታ የምተብክ ሞኝ ነክ. ስማ አንተ ኦሮሞ አትመሰለኝም ከሆንክም ደሞ ለሆዳቸው ተገዝተው የህዝባቸውን መከራ እና ስቃይ ከሚያራዝሙት አንዱ ነክ. እሱ መብትክ ነው.ስማ ሚስጥር አይደለም ኢ.ቲ.ቭ ላይ ሁሊ የሚታይ ነገር ነው. ኦነግ እንዲ አረገ ኦነግ…. እያሉ ስንቱ እንደተገደለ በየቢቱ የሚያነባውን , በእስር የሚማቅቀውን, መታሰር ሳይበቃ ዎንዶች ብልታቸውን እየተቀተቀቱ, ሰቶች እየተደፈሩ,…ዘግናኝ ነገር ይህን በደንብ ታውቃለክ.እናም ይህን በተለቭዝን ለማየት ተተብቃለክ?? ድሮ አማራ ገዛ በለካል አሁንማ ኦርሞ እየገዛክ ነው? ሊላው በታም የዋሸከው ነገር ቢኖር የዘረኝነት ነገር የመታው በዎያኒ ስርሃት ነው.ሰው በቕንቕው ስለሳፈ ስለተናገር ብለካል, ድሮ ክልክል ነበር እንዲ? ዎለጋ ሂድ ድሮም በቕንቕቸው ነበር የሚናገሩት.አንድ ያልገባክን ነገር ልንገርክ አንዲት አገር የተለያየ ብሂረሰብ የሚኖርባት ከሆነች የግድ አንድ አገር አቀፍ ቕንቕ ያስፈልጋታል. ሊገርምክ አይገባም አሁን ምን እየተደርገ ነው ኦርሞ አገር አቀፍ ቕንቕ ኦሮምና እንዲሆን ይፈልጋል ትግሪም በአቅሙ እንዲው. አማርናን ለማጥፋት ይታታራሉ. ግን እየተተቀሙበት ነው.በተረፈ ሲሻር ያልበላ ላልከው ዎያኒ የስልታን ጥማቱ መዝረፍ ነበር .እየዘረፈ ነው. ደርግም ከደርግም በፊት እርዳታ እንደዚ መንግስት የሚያገኝ የለም ታሪክ አቃለው ብለካል ከአውሮፓና ከአሚሪካ የሚያገኝው ገንዘብ እረጂ እንጂ ተረጂ ባልነበር. እስካሁን የለምናል ማፈሪያ መንግስት. የሚገርመው ባሁን ሰህት ያለው ርሃብ ታይቶ አይታውቅም. ለምን ? የሚገባው የርዳታ ገንዘብ የት እየገባ ነው? ያንተ ነገር ይህንንም እትዮፒያ ተለቭዥን ላይ ልትሰማ የምትብክ አዋቂ ነክ. ሲሾም ያልበላ ካልክ ንጉሱ በጥጋብ አስተዳደረዋል.ጥቂት ስህተት ተከስታል.ገንዘብ እየዘርፉ ከአገር ማሽሽ አልነበረም. ደርግም ስልታን ያዘ ሲሾም ያልበላ ….ብሎ ሲዘርፍ አልታየም አገርን ያለወደብ አላስቀረም አሁንም እትዮፕያን እይሸነሸነ አልሸተም አማራ ሲገዛ የውንብድና አመል የለበትም ተማሪም የሚበላው አጥቶ ትምርቱን አላቕረተም. የዎያን ጉድ ስልታኑን ሲለቅ ጉዱን ትሰማለክ. በተረፈ ምንም እንኩአን ኦሮሞ ብሆን ሃቅን መናገር የቆተርኩት ፊደል ግድ ይለኝሃል. እውነት ለመናገር አስተዳደር አማራ ተሽሎ ታይታል. የ ኦሮሞን አላየንም ለማንናውም መልካም እድል በዎያን ወታደር ስቃይ ለሚያዩ ዎገኖቺ እግዚአበር ይርዳቸው እላለው. ዎያኒ እያደረገ ያለውን ህብረተሰቡ መሃል ግቡና እዩት ለሆዳችው የተገዛቹ አማራ እና ኦሮሞዎች እባካቹ እባካቹ ዎያኒ ዘርና ቕንቕን ለማጥፋት ተነስታል ከባዶች ናቸው የሚዘሩት ፕሮፓጋንዳ ቀላል አይምሮ ጋገኝ እና ሆዳም ባንዳን ካገኝ ዘር ለማጥፋት ተነስታል. እሺ ተሳካለት እንበል እና መቸረሻ የ እናንተ እድል ምንድነው??? ??? ከሱ ዘር ሊላ ማየት የማይፈልግ የዘር በሽታ የተተናወተው መቸረሻ ምን የሚላቹ የመስላችዋል?? እናንተ ባለውለታዎቺ ናቹ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙልዋት ነው , ዎይስ እናንተ ከሃዲዎች ስራችውን አተናቃችዋል ከዚ በዋላ ስራ የለም ብሎ እንደሚቸርሳቹ ሃታውቁ ይሆን? እግዚአበር ኢትዮፕያን ይባርክ እኒ በበኩሊ ኦሮሞ አማራ ጉራጊ ትግሪ ደቡብ …. ሁሉንም በ እኩል አይን የሚያይ አገር እና ህዝቡን የሚወድ ህዝብም የሚወደው ባልተቸበረበረ ምርቻ ያሸነፍ ማቹርድ የሆነ በ እትዮፒያ አንድነት የሚያምን ,ከ ጎረበት ጋር በሰላም እና በጥበብ መኖር የማይችል ላደጉ አገሮች አሽከር ያልሆነ ኩሩ እና አዋቂ መንግስት ይስተን አሚን!!

  9. ሰላማዊት
    | #9

    አንድ አንድ ሰው እንድ አንድ ሰው እንደት እንደሚያስብ ይገርመኝል.ለማ ያንተ ትንሽ ሳታስብ የጽኣፍክ ትመስላለክ. እንደት ብትል ኦሮሞ ሆኖ ኦሮሞን የሚቃወም የለም?? ዎየስ ሆሮሞ ሆኖ አማራን ዎየም ትግረን የሚደግፍ የለም?? ጉራገ ሆኖ አማራን የሚደግፍ የለም?? ዎየስ ጉራገ ሆኖ ትግረን የሚቃወም የለም?? … እናም ያደታ ኦሮሞ ሆኖ የሆሮሞን እና የአማራን የትግረንም ድክመትና ብርታት ተናገረ ማለት አይገርምም ትግረን እይ ትግረን ተመልከት. አረና ነን ብለው ሽፍተው እየተዋጉ ነው. ኦሮሞን እይ እይተዘጋጀ ነው.ደቡብን እይ ሸምቛል በንሻጉን እዩ. አርበኛ ግንባርን እዩ.የኦሮሞ የሚያናድደው መከፋፈላቸው ነው.ጃርሶ ይህ ደሞ ለአንተ ትምህርት ይሁንክ. አማራ ቀጥቅጦ ገዛ ላልከው የውያኒ ፕሮፓጋንዳ ነው.በ አማራው ግዚ የስልጣን ድልድል ተመልከት ሁሉም አለበት የዎያኒን ተመልከት ከሀ-ፐ ትግራዮች ናቸው. ሲ!!!! አሁንማ ተንቀባረን ነው የምንኖረው?? አሳዛኝ እና አሳፋሪ ግዚ ላይ አይደለን? አንተ ምንክም አልተነካ ይሆናል . ይህ ሁሉ የሸፈተ ብሂር ብሂረሰብ አገዛዙ ስለተስማማው ነው?? በተረፈ አንተ ስለትግራይ ህዝብ ማን ይግዛን የሚለውን የራስክን መምረጥ ትችላለክ. የሊላውን ጎሳ ማን ይግዛ ለሚለው አትመርጥልንም. እኒ ለምሳሊ አባቴ የጅማ ኦሮሞ ነው እናቴ ደሞ ጉራጌ ናት. ይን አገዛዝ እጅግ ያማርራሉ. ምክንያታቸው ከበቂ በላይ ነው. ምርጫ 97 ተመልከት ያሁሉ ህዝብ አይተካል ዎያኒ የተዋረደበት ግዜ ነበር. ከዚም የተነሳ በቂም በቀል የኑሮን ሁኔታ ሰማይ ሰቀለ እግዚሃብሄር ግን ህዝቡን በታምር ያኖራል. እኔ አሁን ማን ይግዛ ማን አይደለም ሰው ሳይሆን እግዚሃብሄር ይምረጥ. ግን ማንም ከዎያኔ የሚጠቀም ካልሆነ ዎይም በጭልምተኝነት ዘሬ ይግዛ ካልሆነ ማንም ብሄር ዎያኔን አይመርጥም.

  10. HELELE HANBABE
    | #10

    ጃርሶ :
    አሁንኮ የተቸገራችሁት አማሮች ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል እምትልዋት ነገር ናት አሁን አማራ ቢገዛም አታስቀምጡትም ለምን ሁላችሁም መግዛት ትፈልጋላቹ አታገኙትም እንጂ አለፈባቹ ከንግዲህ ህዝብ ነቅታል ኦሮሞም ዳግም በናንተ ላይገዛ ትግሬውም ጉራጌውም ቤንሻንጉሉም ኩናማው አፋሩ ሌላውም ጎሳ ነቅቶባቹሀል እንደገና ረግጦ ለመግዛት ነው አላማቹ የለም ለምን አማራ ግዝቶን ጥሩ ነገር አላየንም አሁን ሰው በቓንቓው መጻፍ ማንበብ በጀመረበት ሳአት ዳግም አማራ ይገዛል ብላቹ አትገምቱ የራሳችሁን ክልል መግዛት ትችላላቹ ኦሮምያ ግን ዳግም ባማራ አትገዛም ከተገዛች ባገርዋ ልጅ ኦሮሞ ነው እምትኖሮው አሁን አማራ ዘር ከዘር አይለይም አላቹ ወደ ሓላ ዞር ብላቹ ታሪክ አንብቡ ለማታለል አትሞክሩ ስማቹ እየቀየራቹ እኛ ኦሮሞዎች ከአማራ ጋር ምንም ጸብ የለንም አንድ ነን ካማራ ጋ ከመች ወዲህ በኦሮሞ ህዝብ አትቀልዱ የተቀለደብን ጊዘ በቂ መሰለኝ አሁን ለትግሬ እምትሰድቡት እምታዋርዱት ስልጣን ስለወሰደባቹህ እንጂ በክፉ ስራ ከሄድን አማራ የሰራው ይብሳል

    JARSO: YOU ARE NOT AN OROMO. FROM WHAT YOU WROTE I COULD TELL THAT YOU ARE WEYANE. WHERE IN THE HISTORY OF AMHARA RULE DID AMHARAS PERSECUTE OROMOS MORE THAN WEYANES? WHERE IN ETHIOPIA’S HISTORY AMHARAS PROHIBITED OROMOS FROM EXERCISING THEIR CULTURE, RELIGION, LANGUAGE AND CUSTOMS? WEYANES ARGUE THAT AS LONG AS OROMOS WRITE IN QUBE AND EXERCISE THEIR CULTURE, THEY HAVE MORE FREEDOM THAN AMHARA’S RULE. THIS ARGUEMENT IS CLASSICAL BRITISH COLONIAL POLICY KNOWN AS CULTURAL AUTONOMY. THE POLITICS AND ADMINISTRATIVE AUTHORITIES ARE LEFT TO THE BRITISH COLONIZERS, JUST AS WEYANES ARE DOING NOW. YOU ARE A WOLF IN SHEEP’S CLOTHING.

  11. ጃርሶ
    | #11

    ኩማ እንዳንተ መሳደብ አልፈልግም; ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ ሆይ እኔ ያልኩት አማራ ኦሮሞ እንዳይማር ከሚኒሊክ ዘመን ጀምሮ የነበረው ታሪክ ነው ያወሳሁት; ኩማ ያልከው በእውነቱ አንተ የኦሮሞ ቅንጣት ያህል የለህም አማራ ነህ; አማራም ብትሆን ወንድሜ ኢትዮጵያዊ ነህ ;ይህ አይደለም ችግሩ እውነት ማውራት ስለማንችል እንጂ እውነቱን ሳናውቀው ቀርተን አይደለም;ኦሮሞ አልተጨቆነም ካልክ ተሳስተሀል በጣም ተጨቁነዋል እንዳይማር ተደርጋል ;አሁን ግን እሃዴግ የራሱ ችግሮች አሉት የሉትም አይደለም ባንድ በኩል ለህዝቡ በቓንቓው እንዲጽፍ እንዲያነብ አርጋል; የብሄር ብሄረሰብ መብት አስከብራል ;አሁን ላለው ችግሩ ግን አገራችን ውስጥ ያስቸገረው ነገር ቢኖር; እንደሰለጠኑት አገሮች ስልጣን ካንዱ ወደ አንዱ በሰላም የማስተላለፉ ጉዳይ ነው ;ሁሉም ያቺን ቦታ ከያዘ ቡሀላ በሰላም መልቀቅ አይፈልግም; ኢሃደግ ደሞ ስልጣኑን በዴሞክራሲ አምኖበት በየ አምስት አመቱ ለውጥ ብናይ ሁላችንም ደስ ባለን; በተረፈ እውነት ላወራ ሰው አንተ የነሱ ፍርፋሪ በላህ አሽከር ነህ አይባልም ;የመሳደቢይ ቦታ አናርገው ያለንን መወያያ ይሁን ሰላም ለኢትዮጵያ ህዝብ ይሁን

  12. HELELE HANBABE
    | #12

    ለማ :
    ያደታ እውነት አንተ ኦሮሞ አይደለህም አንዴ አማራ በዘር ከተነሳ አለቀልን ትላለህ አንዴ ኦሮሞ ና አማራ ፍቅር እንደሆኑ ታወራለህ ባይገርምህ አማራ ነህ ኦሮሞና አማራ በምንም መልኩ ፍቅር ሊሆኑ አይችሉም በህዝቡ ብቻ ሳይሆን ገዢዎችም ጭምር ኦሮሞን እንደ ሰው ሳይሆን ሲታይ የነበረው እሱን ታቀዋለህ አሁን እዚህ መግለጹ አስፈላጊ አይመስለኝም; በዚሁ ቂሙ ህዝቡ ዘንድ አለ አገራችን ውስጥ ወደ ሁላ ያስቀረን ነገር ቢኖር እርስ በራስ መናናቁ ነው አማራ ኦሮሞ ይላል ትግሬ አማራ ኦሮሞም ትግሬም አማራም ጉራጌም ሁሉ የየራሱ ዘር ማወደስ ይወዳል አገራችን ባለን አንድነት አምነን አንተ አማራ ትግሬ ኦሮሞ ጉራጌ አፋር ኩናማ ምናምን ሳንባባል ብንኖር ከሁሉም የበለጠ አድገን ነበር ያማራ ትቢት ነው ለዚህ ሁሉ እሚያበቃው እና እባካቹ እርስ በራስ እንከባበር ማንም ከማንም አይበልጥም አናስበልጥ አማራ ምን ስለሆነ እሚገዛው ሌላው ዘር ምንድንነውና የማይገዛው ከየትኛውም ዘር ይሁን አድልዎ በሌለው ሳይከፋፈል አንዲት ኢትዮጵያ እኩል አርጎ እሚገዛ ይሁን ብቻ መከፋፈል ይቅር እኔ ከሌላው ዘር እበልጣለሁ ይቅር ቸር ይግጠመን

    LEMMA: YOU ARE SO IGNORANT ABOUT THE RELATION BETWEEN AMHARAS AND OROMOS. I DO NOT BELIEVE THAT YOU ARE AN OROMO. EVEN IF YOU ARE AN OROMO, YOU MAY BE FROM WELEGA OR SOMEWHERE IN OROMO REGION WHERE OROMOS ARE BRAINWASHED BY WEYANE OR OLF PROPAGANDA AND HATEFULNESS. YOU ARE FEARFUL ABOUT AMHARAS AS I UNDERSTAND YOU FROM WHAT YOU WROTE. FASCIST ITALIAN GRAZIANI ASKED GENERAL JAGAMAKELO’S FATHER WHO IS MARRIED TO AN AMHARA WOMAN(GENERAL JAGAMAKELO’S MOTHER)TO KILL AMHARAS IN RETURN TO BE ADMINISTRATOR OF SHEWA PROVINCE. GENERAL JAGAMAKELO’S FATHER CAME THE NEXT DAY WITH A SACK FULL OF TEFF (SERGEGNA) AND EMPTIED THE SACK BY LETTING THE SERGEGNA TEFF ON THE GROUND AND ASKED GRAZIANI TO SEPARATE THE RED TEFF FROM THE WHITE TEFF. GRAZIANI THEN ASKED WHY THE FATHER DID. AND THE FATHER RESPONDED SAYING THAT I AM MARRIED TO AN AMHARA AND HAVE CHILDREN AND THERE ARE MILLIONS OF OROMOS AND AMHARAS INTEGRATED LIKE US AND YOU WANT ME TO KILL AMHARAS THAT ARE MY FAMILY MEMBERS? THEN, GRAZIANI UNDERSTOOD AND LEFT HIM ALONE. LEMMA, YOU ARE TELLING US THAT AMHARAS AND OROMOS CAN NEVER LOVE EACH OTHER 75 YEARS AFTER GRAZIANI UNDERSTOOD WHAT GENERAL JAGAMA KILO’S FATHER TOLD HIM. WHAT A SAD IGNORANCE YOU HAVE. YOU CANNOT EVEN MAKE THE SLIGHTEST DIFFERENCE BETWEEN AN ORDER(SYSTEM OF GOVERNANCE) AND ORDINARY PEOPLE. YOU SIMPLY GENERALIZE AMHARAS FOR ALL THE SINS MONARCHIAL GOVERNMENTS OF AMHARAS DID. BY THE WAY, DO YOU KNOW THAT HAILE SELASSIE WAS 75% OROMO AND 25% AMHARA? HAILE SELASSIE’S FULL NAME WAS tEFERI MEKONNEN GUDISA (DO YOU GET IT?)DID YOU KNOW THE HISTORY OF OROMOS? DO YOU KNOW THE HISTORY OF OROMO MIGRATION? DO YOU KNOW WHAT OROMO MIGRATION DID TO MINORITIES? DO YOU THINK THAT ALL OROMOS ARE LIBERATORS OR ARE AGAINST ETHNIC CHAUVINISM? YOU HAVE SO PATHETIC MENTALITY!!!!!!!

አስተያየት መስጫ
አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።