ይሁዳም ስለ ድሆች ሞግተዋል! በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

December 29th, 2010 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ
 1. አባይ
  | #1

  ሰልምን አንደሆነ አልገባጘም

 2. ስንሻው
  | #2

  “ጥያቄው እውነት ስለ ሕዝባቸው የታገሉ፣ ደማቸውን ያፈሰሱ፣ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ ሕዝብን አፍነው፣ ረግጠው፣ አንቀጥቅጠውና ውጠው ለማበጥና ለመግዛት ነው እንዴ? በውኑ ሀገሬ! ሕዝቤ! እየተባለ በሕዝብ ስም ጩሆው የሚያጫጭኹና ጮቤ የሚረግጡትስ ቢሆኑ (ሕዝብ ባያውቃቸውም) ደማቸው ቢመረመር (እግዚአብሔር ቢገልጣቸው) እውነት ሀገራቸውና ሕዝባቸው ግድ ብሎአቸው ይሆን? ሀገሬ ሆይ! ይሁዳም ስለ ድሆች ሞግተዋል! ስለ ድሆች መሞገት በራሱ ኃጢአት ሆኖ ሳይሆን ያስወቀሰው በልቡ ሌባ ስለ ነበር ነውና ስለ ነገ ቢጠየቅ በመልሱ የማይሳሳት እግዚአብሔር ይሁንሽ። በኪነ ጥበቡም ሰው ይስጥሽ እንጂ ሰውስ አልወጣልሽም። ክቡር ዜጋ ሆይ! የሚያብለጨልጭ ሁሉ ወርቅ አይደለም። ጉድ ነው! አንዳንዱ ብረት (ቆርኪ) በእሳት ውስጥ አልፎ እስካላዩት ድረስ ሲታይ ከወርቅም በላይ ነው።”

  “ሀገሬ ሆይ! የሀገር መሪም እንደሆነ ከድምጽም ያለፈ ነውና የተፈተነ ይጣልልሽ! በዕድሜም የሸነገለ፣ በትምህርትም ሰው ለሰው የሚሰጠውን ማዕረግ ያጠናቀቀ፣ ተኩሶም ዒላማውን የማይስት አልልም (ትምህርት መቃወሜ አይደለም ከማንም በላይ የማለት ድፍረቱ ባይኖረኝ ከማንም በማይተናነስ መልኩ በእውቀት አምናለሁ የተማሩ ትላላቆቼም አከብራለሁ) እያልኩ ያለሁተይ ከትምህርትም ከታጋይም በላይ ለሀገሩና ለሕዝቡ ልብ ያለው የተሰጠ የህዝብ ህመም ህመሜ ነው፣ የህዝብ ስብራት ስብራቴ ነው፣ የህዝብ ሀዘን ሀዘኔ ነው የሚል ለማለት ነው። በተረፈ ግን ተምሮ ለመብላት፣ ታግሎም ለጥፋት ከሆነ ትምህርቱም ሆነ ትግሉ ለምንሽ ሀገሬ? ለምንህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ?”

 3. ያሬድ
  | #3

  ይሁዳም ለድሆች ሞግቶዋል? ይሁዳ ማንን ሞገተ? አሳልፎ የሰጠውን ጌታን:: እና አንተ የማን ተማጓች ነህ የይሁዳ? አሁን ትክክል ቦታህን ያዝክ ቀድሞም እኮ አልሰማ አልክ ወይም ደግሞ ያዳቆነህ ሰይጣን ሳያቀስህ አልቅህም በሎህ እንጂ እኛማ ተናግረን ነበር ይሄ ሁሉ ድካምህ ያንተን ዘር የበላይነት ለማረጋገጥ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ በዙሃኑ ደግሞ ምንም ይሁን ምን በአንድ ዘር የበላይነት ከቶ አይኖርም እፍኝ የማይሞሉትን ጨካኝና ዘርኞችን ከማጠፋት ወደሁዋላ አይልም እድሜ ይስጠህ ታየዋለህ ሁሉንም

 4. Lucy in America
  | #4

  ebakeh ante sewuye ye egzabiheren kale yalebotawu eyasegebah menefesachinen atawukewu. enate tekem kagegnachihu monday, muslim, tuesday penete, wensday , orthodox, thur, catholic, friiday protestant saturday johova lemehone menem yemiwokese hilina yelachihu sewoch nachihu. zare kemanem belay penet , protestant cathilc eyehonu orthodox yemiyawogezu yemendereh sewoch nachewu be alem laye. ye dekik estofanose be 14 kz yekehedete enkesekase, be ethio Italy war gezeye yezemedochin tabot awutetewu ye italy general mawodese ena behualam wode lelawu akababi ke Italy worari gare teselefewu hitanat sayikeru sislebu mekoyet yemiyastemeren tekem eskagegnachi derese hageren, wegenen hayimanoten, bahelen lemelewota menem chiger endelelebachihu newu. selezih zeregna weyanen lemedekef ye anete deresha beye web situ layi tenchile wodiya kemezemez wodiya yehone neger eyetafeh gezeyachewun atefabachewu tebeleh kehone yemiyanebewum yelem. ene rase semehen ena titelun kalehone besteker ye anten zebazenki yemenebebet gezeye yelegnim. egzabiheren yemetefera kehone le pastor geberemdehn geberyohanse heden orthodox church lekeh wode protestanteh hedeh geba belewu, we know him very well.

 5. b.b.
  | #5

  ዲያቆን ሙሉ.. አሳብክን ጠቅለል አርገክ ማሳጣር ስትችል ቅዳሴም የነስልካል መሰለኝ በጣም ታሟዝዘዋለክ .ጹሁፍክን ማንበብ በጣም ይሰለቻል. እጅግ በጣም ከመንዛዛቱ የተነሳ. አዜብ አንተ በሞለጭካት ጉዳይ ላይ የሰጠችውን መልስ አነበብኩት ECADF ላይ አሁን ተነስቶ እንድሆን አልቅም ለዛ ሁሉ አዲስ ዘመን ለሚያክለው የስድብ ናዳ እሷ የአንተን የእሩብ እሩብ ያህል መልስ አልሰጠችም .ያውም ከስድብ የነጻ የመልስ ምት ነበር አድቄላታለው ያውም በሴትነቷ ሳታንዛዛ. ምናልባት ላንተ ከተሰጠ መልስ ትምህርት ወስዳ ይሆናል. አንተ በመሳደብክ እና ጹኡፍክ ሙዝዝ ያለ ነው የሚል አስተያየት ስለጎርፈልክ ይሆናል ጹፏን ያላረዘመችው እናም ያልተሳደበችው. ብልጥ ሰው በሚደርስበት አይቶ ይማራል. ሞኝ ግን በራሱ ደርሶ እንኳን አይማርም የሚባለው ነገር ይህ ነው. በተርፈ ወያኔ ብቻ አይደለም ስንት ግለሰብ አለ ምድረ ይሁዳ ያልከውና ሁሉም ለስልጣን ነው ለራሱ ነው ያልከው አሁን ደሞ ነብይ መሆን አማረክ???????????? ማንንም ማዳከም አትችልም!!! መንፈሳዊ እንዳልሆንክ ፍሬክ እኮ ተገልጦ ታይቷል. ለጥቅስ ጥቅስማ ዲያቢሎስም ጥቅስ ይጠቅሳል. ስላንተ ምልህክቶችን ያዛል እንኪያስ የግዚሃቤር ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስክን ወርውር ብሎ ዲያቢሎስ ጌትን ተፈታትኗል 3 ጊዜ. እንዲ ተብሎ ተጽፏል እያለ. እናም ህዝብ ወያኔን የጠላበት ምክንያት ዋናው ስለመዝረፍ አይደለም ዋናው ንጹዓኖች መገደላቸው, ቢትዮፒያ አንድነት የሚያምኑትን ማሳደዱ, አገር ያለወደብ ማስቀርቱ, ጎሳን ከጎሳ ጋር ማባላቱ, አገር የመከፋፈል አላማው, ልህዝብ አለማሰቡ , የርዳታ ገንዘብ እያሸሸ ዜጋን በረሃብ መጨረሱ,በማእከላዊ እና በድብቅ እስር ቤት አሰቃቂ በደል መፈጸሙ, የድብቅ ጄኖሳይድ ምካሄዱ….. ነው ገባክ??? እናም ማንም ተቃዋሚ ሃይሎች ስልጣን ብይዙ ይህን ሁሉ ያረጋሉ???? መልሱን እራስክ መልሰው. ስለዝህ ነው የተሻለ የምንፈልገው.የፈለገ ቢመጣ እንደዚህ መንግስት ጠባብና ሆዳም ባለጌ አይመጣም.

 6. Shotellaw
  | #6

  Diakon Mulugetta

  Even Yihunda was not as RUD as you are!!! Qebatari balege!

 7. Mulu ken
  | #7

  ወገኖች የዚህን የ ዘረኛ: በሽተኛ ዲያቆን ዝባዝንኬ ትታችሁ: በ ይሄይስ አይምሮ የተጻፈውን: የ እውነተኛ አባቶች ትምህርት አንብቡ:: ይሄንን ዲያቢሎስ መዝጋት ነው::እኔ መቼም አንባብያንን ይቅርታ ካልጠያቀ የሱን ቅራቅንቦ ላለማንበብ ለ ራሴ ቃል ገብቻለሁ:: ወያኔ የማይኖርበት ቦታ የት ይሆን??

 8. አባይ
  | #8

  ዲያቆኖቹን ምን ንካቸዉ ?

 9. በቀለ ለማ
  | #9

  “እኔ አውቃለሁ፣

  እናውቅላችኋለን”

  ማለት ግን ባርነትን የሚያጸና ዕንቅፋት ከመሆኑ በላይ ኃያላን መንግሥታት እርስ በርሳችን ስንናከስና ስንጨፋጨፍ ተሽከርካሪ ወንበራቸው ላይ ተቀምጠው መነጸራቸውን ዝቅ አድርገው (ደም መፋሰሳችን በደንብ ጥርት ብሎ እንዲታያቸው ማለት ነው) እንደሚመለከቱን ሁሉ የእግዚአብሔርም አሰራርና ማንነትም እንደሆነ ከዚህ የተለየ አይደለም። ዋናተኞች አንድ የሰመጠውን ሰው ለማውጣት ኃይሉን እስኪ ጨርስ ድረስ ጠብቀው ለመታደግ ጣልቃ እንደሚገቡ ይህንንም እርምጃ ለመውሰድ የሚገደዱት ያ ሰው በራሴ እተርፋለሁ ማለቱ ሲያቆም እንደሆነ ሁሉ ወደድንም ጠላንም የእግዚአብሔር አሰራርም እንዲሁ ነው። በተረፈ ገና አሁንም ራሴን አተርፋለሁ በሚል እሳቤ በኃይል መንፈራገጡ ያልተወና ያላቆመ እንደሆነ አድናለሁ ብሎ የገባ ሰውዬም ጨምሮ መጥፋቱ ስለማይቀር ማንም የሚታደገው አይኖርም።

 10. Anonymous
  | #10

  diro diro yibal neber
  “diaqon kezefene fiel ke…”

  tadiya ahun egnas binl
  “diaqon ke tybe(type)qum tsihufun tito
  McDonalds ke wale Zekewin resto
  belut be mequamiya
  lemanim aybejim
  tatochu yiqoretu dagim enday tybe”

 11. ሰላም
  | #11

  ከእባብ ባህሪ መልካሙን ብንማርስ???

  አንድ በእንስሳት ባህሪ ላይ በቂ ጥናት ያደረገ የቅርብ ወዳጄ ስለ እባብ ባህሪ:- ‘እባቦች እንደማንኛውም እንስሳ እርስ በርሳቸው ይጣላሉ አንዱን አንዱ ለመጉዳትና ለማሸነፍም ብዙ ትግል ያደርጋሉ:: ነገር ግን በዚህ ሁሉ ፍትጊያቸው ላይ አንዱ በአንዱ ላይ መርዙን በጭራሽ አይረጭበትም’ አለኝ:: እኔም ይህን ጉዳይ ልብ ብዬ በመደነቅ ሃሳቡን ሳወጣ ሳወርደው:- ምናልባት ለዚህ ይሆን ጌታ በቃሉ/በወንጌሉ ‘እንደ እባብ ብልህ እንደ ርግብ ደግሞ የዋህ ሁኑ’ ያለው? ብየ እራሴን ለመጠየቅ ተገደድኩ::

  አስተዋይ የሆንክ ወገን ሁሉ በእውነት ፍረድ ከዚህ በላይ የግል ሃሳባቸውን በዲያቆኑ ጽሑፍ ላይ ከሰነዘሩት ከያሬድ ከሉሲና ከቢቢ መልእክቶች ላይ ከግል ጥላቻ በስተቀር የምንማረው ምንድነው? ይኸ ሰው በጽሑፍ ችሎታው የወገኑን ብሶት በሚያመልከው አምላክ ቃል ተመስርቶ በመረጃ ነው ያቀረበው:: ታዲያ ምን አድርግ ነው የሚሉት? ችሎታ ያለው ሰው እንዲህ ሲገኝ ለምንድነው እባብ ከእባብ ጋር ምንም ቢጣላ በሌላው ጠብኛ ወገኑ ላይ የማይረጨውን መርዝ እነዚህና መሰሎቻቸው ምድራችን ባፈራቻቸው ጸሓፊዎቻችን ላይ የሚረጩት?? ወይ ጭብጥ ባለው መረጃ ላይ ተመስርተው የተሻለ ጽሑፍ ካላቸው ያቅርቡና ያስነብቡን? ወይም ችሎታው ከሌላቸው ዝም ብለው እንደሁላችን ይማሩ እላለሁ::

  አዎ!! እኔም በዲያቆኑ ሃሳብ እስማማለሁ:: ዘርፈ ብዙ ለሆነው ለምድራችን ችግር መፍትሄው ዛሬ ተመስርቶ ነገ የሚፈርስ የጮሌዎች ስብስብ ሳይሆን ከሁሉም በላይ በምድራችን/በሕዝባችን ላይ እውነተኛ ፈሪሃ እግዚአብሔር ሲመጣ ብቻ ነው:: አምላኩን በቃሉ ላይ ተመስርቶ የሚያውቅ ሕዝብ ባለስልጣንን በተገቢው መንገድ ከማክበር በስተቀር አይፈራም:: የራሱና የሌሎች መብት ሲጣስም ዝም አይልም:: ወደ ላይም ወደታችም እንዲሁም ወደግራና ቀኝ በጋራ በመጮህ የጋራ መፍትሄ ባለቤት ይሆናል:: ምናልባት አንዳንዶቻችሁ ምነው ፈሪሃ እግዚአብሔር አሁን በምድራችን ላይ የለም ነው እንዴ የምትለን? ትሉ ይሆናል:: እቅጩን ልንገራችሁ መልሱ አዎ! አዎ! አዎ! ነው:: ምክናያቱም ቢኖርማ ኖሮ ወንድም ወንድሙን ለጥቅም ባልሸጠ/ባላስገደለው ወይም ሕዝባችን በድግምትና በአስማት እንዲሁም በጥንቆላ ያጋንንት መጫዎቻ ባልሆነም ነበር:: እንዲሁም በጉልበቱ ሕዝቡን የሚገድልን መንግሥት ሃይ የሚሉ የሃይማኖት መሪዎች አጥተን የልቅሶአችን ዘመን ባልረዘመ ነበር:: ለተባለው ነገር ከዚህ በላይ መረጃ ካስፈለገ ከትክክለኛው ታሪካችን ተነስተን በተጨባጭ መረጃ ማለት ይቻላልና ለዛሬው እዚህ ላይ እንዳበቃ ልወገኔ ያለኝን የሲቃ ስሜቴን ለጊዚው ተቆጣጥሬ እንዳቆም እገደዳለሁ::

  በተረፈ የሚያስፈልገን የሚራራ የሚያዝንና ለችግሩ ተግባራዊ መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል እንደ ጌታ ኢየሱስ ያለ ሥጋን ፈውሶ ነፍስን የሚያረሰርስ እውነተኛ ተምዋጋች/ጠበቃ እንጂ የራሱን ጥቅም ለማስከበር ዓላማው ሲል ለድሆች የሚሞግት ይሁዳ አይደለምና ሁላችንም ብንፈታተሽ መልካም ይሆናል:: በጠላት ላይ እንጂ በወገን ላይ መርዙን እንደማይረጨው እንደ እባብ ብልህ እንደ ርግብ ደግሞ የዋህ ያድርገን አሜን::

  ሙሉጌታን ግን በርታ ሳልል ባቆም ህሊናዬ ይወቅሰኛልና ባላውቅህም አውቄሃለሁና ጽሑፍህ እንዳይነጥፍ በርታ ልልህ እወዳለሁ:: አቡጌዳዎችንም እጅግ አመሰግናለሁ በርቱ አፋጩን አንድ የምንፈልገውን መልካም ውጤት እስከምናገኝ ድረስ::

  ሰላም ሁኑ ሰላም ይግጠመን!!
  ሰላም ነኝ

 12. ማተቡ
  | #12

  ሰላም=ሙሉገታ= የወያኔ/ድያብሎስ መንፈስ ደቀ-መዝሙር/ራን::

  የጽሁፋችሁ/የጽሁፍህ ዓላማና ግብ ምንድን ነው??:: ሕዝብን ሓይማኖት ለማስተማር? ምናይነት ሓይማኖት? ራሱን ነቢይ/መሲህ ብሎ የመጣውን ሙሉ-ጌታን ለመቀበል?የትኛውን ሕዝብ ለማስተማር? ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለውን ሕዝብ? በውጭ ያለውን ሕዝብ?::
  ጉድ ነው!!:: የወያኔ የእንጀራ አባቶች ጣሊያኖች/እንግሊዞች “ሓይማኖት/ሲልጣኔን ልናስተምር” እንዳሉት በዘመነ ቅኝ ግዛት::
  ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከብዙሺህ ዘመናት በፊት እውነተኛ ፈጣሪውንና ያወቀና የሰለጠነ ሕዝብ መሆኑ ሃቅ ሆኖ ሳለ::
  ጉድ ነው እናንተ?!!::
  ወያኔ ንጹህ ዜጋ ያስራል “ምሕረት” ጠዪቅ ዪላል::ዪገድላል,ያሰቃያል, ዪዘርፋል ::አይኑን በጨው ታጥቦ ምንም እንዳልሰራ አድርጎ ዝንጀሮ ፊቱን ኩዋኩሎ “የዓለም ተራማጅ” ዪሆናል!!::ይህም ደቀ-መዝሙር ዪሳደባል!!, እንደገና ሰደባችሁኝ ይላል!!:

  እናም አንድም ሁለትም ሆነህ የምትዘላብድ “ካህን/ድያቆን” ይሁዳ አንተ ነህ!!,ሌላ ማንም አይደለም::

  ማተቡ

 13. ሰላም
  | #13

  ለማተቡና ማተቡን ለመሰሎች ወገኖቼ!!!

  ነጻነትዋን ጠብቃ የኖረች አገር እየተባለ የሚዘመርላት አገራችን ሰው ከሚያውቀው ኮሎኒያሊዝም በባሰ መልኩ ለ1600 ዓመታት በ111 የግብጽ ጳጳሳት (እስላሞች ሳይቀር ያሉበት) መንፈሳዊ ቅኝ ተግዥዎች የነበርንና እስከ አሁን ድረስ ጠባሳው ያለቀቀን መሆኑን ታውቁ ይሆንን??? መፍትሔ ያጣንለት የአባይ ችግር ከየት የመጣ ነው?? እነዚህንስ 111 ጳጳሳት ተቀብሎ ያስተናግደ ባንዳ ማን ይመስላችሁአል? መልሱን ታሪክ ይመልሰዋል እየመለሰውም ነው:: ታታሪው አርሶ አደር እንዳይሠራ 30 ቀናትን ባእል አድርጎ እየገዘተ ሕዝባችንን ድሃ ያደረገ ማነው? ከዚህ ዓለም መንግሥት ጋር ተጋብቶ ሕዝብን ሚስጥሩን በማያውቀው መስቀል እያስፈራራ ያስበዘብዝና የበዘበዘ ማነው? ከማርቲን ሉተር በፊት የመንፍስ ቅዱስን ሪቫይቫል በምድራችን ያስነሱትን የእምነት አባቶቻችንን አሰቃይቶ ያስገደለና የገደለ ማነው? ምንው በባዶ ማንነታችን መኩራራቱንና መንጠራራቱን አቁመን የተበላሸውን በጋራ አርመን ትክክለኛ ታሪክ እንዲኖረን ብንጥር? ለነገሩ አልፈርድባችሁም ያደግነው ኩራት እራት ነው:: ካልረባባ ግልድም ሙልጭ ያለ ቂጥ ይሻላል:: ምንም ሳይኖር ለምለሚቱ ኢትዮጵያ:: በሚል ኩፈሳ ያደግን ስለሆን ውጭ አገርም ሳይቀር ማንነታችን ከሌሎች ጋር አላስማማ ብሎናል:: ደግሞም ያደግነው ዓይንህ ይፍሰስ:: አፈር ብላ:: ጥይት ይምታህ:: ወዘተ በሚል እርግማን ስለሆነ መልካም ቃል ከየት ታመጣላችሁ ጭራሽ ያልበቀለባችሁን????
  እስቲ ታሪክ ያመጣብንን ማንነት በተጨባጭ አውቀን ለእውነተኛው የችግራችን ምንጭ መፍትሔ በጋራ ለመሻት እንችል ዘንድ የታሪክ መዛግብትን እናገላብጥና ((ለምሳሌ ደቂቀ እስጢፋኖስ በፕ/ር ጌታቸው ሃይሌ የኢትዮጵያ ቤ/ክ(ሁላችንንም ወንጌልን ሳታስተምር ክርስቲያን ያደረገችንን)ታሪካዊ ሂደት በመምህር ጌታቸው ምትኬ ወዘተ)) ለማንበብ እንሞክር::

  አይደለም በባዶ ማንነት መምካት ጳውሎስ በእውነተኛ ማንነቱ ላይ ሳይቀር በቅዱስ ቃሉ(ፊልጵስዩስ 3:3-11) ያስቀመጠልንን ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወታችንና ለሕዝባችን ፈውስ እንጠቀምበት እላለሁ:: ደግሞም በገላትያ 5:15 ላይ ”ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትንካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ” ለሚለው የአምላካችን ቃል ብንታዘዝ መልካም ይሆንልናል::(በእውነት በቃሉ መሰረት እውነተኛ ክርስቲያኖች ከሆን ማለቴ ነው)

  ለዛሬ ይብቃኝ

  የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ
  ሰላም ነኝ

 14. ዮሃንስ
  | #14

  ዻያቆን ከዘፈነ ፍየል ከቀዘነ መዳኛም የለው አሉ አባቶቻችን
  በዚህ በተገላበጠ ዘመን ደግሞ ዳያቆን ካድሬ ከሆነ መለስ ከመነነ ነገር ተበላሸ ብንልስ?
  ይህ ዳያቆን ነኝ ባይ ፖለቲከኛ ወይ የግዜሩን መንገድ አልሄደበት ወይ ፖለቲካው አላማረበት ስለ ይሁዳ ይጽፋል::
  ይሁዳው ራሱ ሆኖ በልቡ ለወያኔ አድሮ ሌላውን አላዋቂ ራሱን ሊቅ አድርጎ አንዴ ራሱን ከጌታና ከሃዋርያቶች ሲያመሳስል
  አንዴ ወያኔን አትታገሉ ሲል ይሁዳ ጌታን እንደሸጠ ይህ ዳያቆን ነኝ ባይ ዳያስፖራውን እንዳይሸጠው ስጋት አድሮብኛል::የተላከውም ለዚህ በመሆኑ ይህን የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ለደህንነታችን ከመሃከላችን እንዳይገባ መከላከልና መታገል ይኖርብናል
  ጽሁፉ ደርዝ የሌለው የሚለው የተምታታበት የአእምሮ ህክምና ወይ ጠበል የሚያስፈልገው ያበደ የወያኔ ውሻ ነው:: ጤናውን አግኝቶ የይሄይስ አእምሮን “እውነተኛ አባት እንዲህ ነው!!” ቢያነብና ቢረዳው እርሱ የመርዘኛ የወያኔ ዲስኩሩን ያቆም ነበር:: ልቦና ይስጠው ለዚህ ይሁዳ ዳላስ ከተማ ነዋሪዎችን አሸብሮ ወደሌላ ዘምቶ አሁን ደግሞ በኢንተርኔት መርዝ ፕሮፓጋንዳውን እየረጨ ይገኛል

 15. ማተቡ
  | #15

  ሰላም = ሙሉጌታ::

  “ካልረባባ ግልድም ሙልጭ ያለ ቂጥ ይሻላል::”!!?:: አይ ድያቆን!!::እንዲህ ነው የዘመማናችን/የወያኔ ድያቆን!!::

  እናም ላስተምራችሁ!!, ነው የምትለን??:: ምክንያቱም “ሳይኖረን በኩራት ብቻ” ነው ያድግን!!:: ኩራተቢስ!!/አሁን ልክ ተናገርክ !!:: ያሳደገህ ወያኔ/አንተም ጭምር በሺህ ዘመናት የሓገራችን ታሪክ አትኮሩም!!::”ኢትዮጵያ 100 አመት” ታሪክ ብቻ ነው ያላት በናንተ በክንቱዎቹ!!::አዎ “ኢንኮራለን” በታሪቻችን!!, ኢንኮራለን በኛነታችን, ኢንኮራለን በማተባችን!!::

  ያንተ ኩራት ግን ታሪክን በጥቁር ቀለም በዳጥ!!:: የሴቶችን ጡት , የወንዶችን ብልት መቁረጥ:: ያንተ ኩራት ሓገርን መሸጥ!!:: ያንተ ኩራት ድንጋይ ሆነህ ስገዱልኝ!!::
  በል ቀጥል አንማር ካንተ!!:: ምንነትህን!!::
  በውነት ቅዱስ ቃሉን በዚህ ቦታ መጠቀም አልፈለኩም :: “ግፍን በግፍ ላይ ማታለልንም ብማታለል ላይ እየጨመሩ ይህሔዳሉ” ኤርምያስ 9:6::

  ማተቡ ሶስትቀለሙ::

 16. ሰው
  | #16

  @ሰላም
  መጀመሪያ የት እንደቆማችሁ ማሳወቅ:: ለእውነት እና የእውነት ጌታ ለሆነው አምላክ ያመናችሁበትን እውነት ማሳየት:: በተሓድሶ ቆዳ
  ተጠቅልላችሁ ትዋሻላችሁ:: ይሁዳ እኮ አስመሳይ ውሸታም ነበር አምላኩን የከዳ ከናንተ የሚሻለው ራሱን ማጥፋቱ ነው::
  አንተ/አንቺ ስለ ግብጾች የጻፍከው አለ:: አባቶቻችን ውሸታሙን ሁለ ያምኑ ነበር [እስላም ሁሉ ተልኮ የለ] አሁን ደሞ ተራው የውሸታም ጴንጤ መሆኑ ነው?? ቢያንስ እምነትህን በግልጽ ተናገር:: ያለፈው ጊዜ ታቦተ ጽዮን የለም ብሎ ቅርሻቱን ያቀረሻ ነበር:: አሁን ደግሞ አንተ በተራህ ታቀረሻለህ:: እንኩዋን ሰለ ፖለቲካ እና ሃይማኖት ቀርቶ ስንት ሰዓት እንደሆነ አለጠይቀውም::
  በትንሹ ያልታመነ ማለት ይሄ ነው::

 17. ይድረስ ለዞረባት ሰላም
  | #17

  ያሬድ ቢቢ እና ሉሲ አስተያየቶቻችው ከግል የተነሳ ጥላቻ ብለሽ ያልሽው አንቺ በግል ታቂዋለሽና ሁሉም ያቀዋል ማለት ነው??? ይህን ዲያቆን የሚታወቀው በጻፈው ደባሪ እና አምላክን በመዳፈሩ ነው. የሱ ምልምልም መሆንሽ አያዋጣሽም ካሁኑ ንስሃ ግቢ ባለፈው በጻፍው ደብዳቤ ላይ እጅግ ብዙ ናዳ ነው የወረደበት በሰራው ስራ እንጂ በግል ስለሚአውቁት አይደለም . ከላይ የጠቀሻቸው ስዎች አይተሻችው ሳትውቂ የግል ጥላቻ ነው ማለትሽ ዝም ብሎ ማንነትሽን ያሳይል.ስለአስተዳደግ ያልሽው አበሻ ወላጁን እያፈረና እያከበረ ነው ያደገው እንጂ እንደሰለጠነው አገር ተብየ ወላጆቻቸው ፊት ውንዱ ከሴት ሴቱ ከዎንድ ጋር ውላጆች ፊት የሚጋደም ህዝብ አይደለም .እግዚሃቤርን ተዳፈረ እንጂ እውነት አልተናገርም ይህ ዲያቆን የተሟዘዘውን ጹፉን ማንበብ ሰልችቶሽ ሳትረጂ ነው አስተያየት የሰጠሽው ማለት ነው.

 18. Lucy in America
  | #18

  selam, penete sikenata hagerun ata. yibalale, ye diyabilose feresoch penetewoch egna bemeder laye hager yelenem yegna hager besemaye bete newu yuluhal. simotu gene genzeb eyetesebeseb yebesebese atemachewu wode ethiopia silake tayaleh. yeyetem hager menefesawi abate le hullum orthodox hayimanot teketay hizb keretian newu. ante hayimanotehen le senede ena aroge lebese yelewoten ye seyitan ferese be ethiopia wust 30 kene beale ayikeberem. belayih laye yeseferewu sheborere– sheborere – sheborer yemilewu menefese newu yemiyanagereh.

 19. ሰላም
  | #19

  እነያሬድ!

  አዎ እውነት ነው! የወንዶች ትምክሕተኝነት በጎላበት ህብረተሰብ ያደግን በመሆናችን የአገርዋና የሕዝብዋ ሁለንተናዊ ችግር በሚያሳዝናትና በሚያስለቅሳት ሴት የተጻፈ እውነት አልዋጥላችሁ ብሎ ሊያስቸግራችሁ ይችላል:: አሁንም ይህ ማንነታችን በአስተሳሰባችን ላይ ገና ልንሠራው የሚገባን ብዙ ሥራ እንዳለን የሚያመላክት ነውና በመጀመሪያ እያንዳንዳችን በራሳችን አስተሳሰብ ላይ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ዘመቻ እናድርግ:: ከዚያም የተለወጠ የበሰለና በእግዚአብሔር ቃል የተለወጥ/የተፈወሰ ልብ/አእምሮ ወንድሙን/እሕቱን መቀበል አይከበደውም:: ቢሳሳትም በፍቅር ሊመልሰው ይሞክራል እንጂ የስድብና የነቀፌታ ቃል አይሰነዝርበትም::

  ስለዚህ ፈቃዳችሁ ቢሆን እባካችሁ መነቃቀፉን አቁመን ለሕዛባችን ችግር መፍትሄ ማምጣት በምንችልበት ጉዳይ ላይ እንድንነጋገር በእግዚአብሔር ፍቅር እጠይቃችሁአለሁ:: በእኔ ላይ የተሰነዘረውን ስድብ በፍጹም አላስበውም:: በእናንተ ላይ ግን ሳላውቀው የወረወርኩት መጥፎ ቃል ካለ /ያለ ግን አይመስለኝም/ ይቅር እንድትሉኝ ከሀጢአት መርዝ ሊያድነን እራሱን ለመስቀል ሞት አሳልፎ በሰጠልን ጌታ ስም ተንበርክኬ እጠይቃችሁአለሁ:: ጌታ ምስክሬ ነው በጌታ ፍቅር እናንተንም ዲያቆኑንም እወዳችሁአለሁ:: ይህ ማለት ግን ‘ኩን ከማሆሙ’ ለማለትና በእውነት ላይ ለማመቻመች ፈጽሞ እንዳልሆነ ተረዱልኝና በአገራችን ጉዳይ ላይ እውንቱን እንድንነጋገር መበረታት አለብንና በዚህ ጉዳይ ላይ እንትጋ::

  ለምሳሌ:- 1) የፖለቲካችን የኢኮኖሚያችንና የማህበራዊ መሰረታዊ ችግራችን ምንጭ ምንድ ነው?
  2) የመልካም አስተዳደርና ሕዝብን የሚወድና ለሕዝብ የሚሠራ መሪ ድሆች የሆነው
  ለምንድነው? መሪዎች ከሕብረተሰቡ ወጥትው ለምንድነው በራሱ ላይ የሚከፉት?
  3) የክርስትና መለያ ባህሪ ፍቅርና አንዱ ለሌላው ሕይዎት መስዋእት መክፈል ማለት
  ነው:: ታዲያ ክርስትናችን በዚህ መስፈርት ያልፋልን? ለምን?
  4) በአጠቃላይ ታሪካችን ሁሉ የተመሰረተው በምን ላይ ነው? ጠንካራ ጎናችንና ደካማ
  ጎናችን ምንድን ናቸው? በማንኛውም መልኩ የመሰረትነው ህብረት ዘለቄታዊ
  ውጤት የማይኖረው ለምድን ነው?

  እነዚህን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ለምን አንነጋገርና መልስ ለማግኘት አንሞክርም???

  በሉ ሰላም ሁኑ
  ሰላም ነኝ

 20. ይድረስ ለሉሲ ከ ዳናኤል
  | #20

  ምን አይነት ባለጌ ሴት ነሽ????? ይብላኝ ለወለደሽ ያገባሽስ ይፈታሻል. በምትሰጭው አስተያየት ላይ ያለስድብ የማይቀናሽ ተራ ሴት ነሽ. 10 ኪው ሰላም ጨዋ የጨዋ ልጅ ለተሰነዘርብሽ ወቀሳ አንድም ጸያፍ ቃል ሳይወጣሽ አስቀይሜያቹ ከሆነ ይቅርታ ማለትሽ ከዲያቆን ተብዬ ያልሰማነው ጥሩ ንግግር ነው እስቲ ባልጌውን ሁሉ አስተምሪ እኔንም ጭምር ማለት ነው. ሉሲ የኦርቶዶክስ ሐይማኖትን እንዴዚህ አፍ እየከፈትን ነው የምናሰድበው. እስቲ አንቺ መጀመርያ ሐይማኖተኛ ከሆንሽ ከሐይማኖትሽ ምን ተማርሽ??? ስድብ?? አሁን ስለዼንጠ ከመናገርሽ በፊት እራስሽን አጥሪ. በኛ መሰናከል ስንቶቹ የጥንቷን ሐይማኖታችንን እይተው ሄደዋል. እኔ የምለው አንድም ዼንጤ እዝህ አይደለም ሲሳደብ ሲሳተፍ አላየውም. እነዚህ ሰዎች ብያንስ እይሱስ ክርስቶስን አምላክ እንድሆነ ያምናሉ ሉዩነታችን በማርያም ነው ማርያም ብጹህ ናት ቅድስት ናት ይላሉ ግን አታማልድም ያማለደን በመስቀል የሞተው ክርስቶስ ነው ክሃብ ማልዶ ያስታረቀን ነ የሚሉት ባልሳሳት. እስላሞች ደሞ ክርስቶስ አምላክ አይደለም የግዚሃቤር ልጅ (ያላህ ልጅ) አይደለም ይላሉ. እንዚህን ሙስሊሞች እንኳን ሳይደርሱብን መናገር አይደለም አንዲት ትንፍሽ የለም አጋድመው ያርዱሻላ ታቂያለሽ. እናም ሚዛናዊ እንሁን እኛ እራሳችን በግዚሃቤር መንገድ እንሁንና ከዛ ሌላውን እንተቻለን ሐይማኖታችንን አናሰድብ ብስርሃት እንደሰላም በጨዋ አንደበት እንማማር.ይራሳችንን ጉድለት እንመልከት እዚህ በሌሉ ሰዎች ከመቀበጣጠር. ለማለት ነው በትረፈ ሉሲ ተብየ አስተያየትሽ ሁሉ ይደብረኛል. አንደበትሽን ቀድሺ ሐይማኖት አታሰድቢ ዘመድ አጣሽ እንጂ ጸበል ሳያስፈልግሽ አይቀርም.

 21. ለተብርሃን
  | #21

  ሰው:: አንተ ሰው ከሆንክ እንደሰው አስብ ስለ ዼንጤ ከማንሳታችን በፊት እኛው እንታረም ለምን እንዲህ እንደምናብድ አይገባኝም በፖለቲካ ቀንተን ብሐኢማኖት ቀንተን በግለሰብ ቀንተን ምን ይሻለናል. አብናረጋይ ይቅር ይበሉን ዋይ ዋይ ምን ይሻለናል አሁን በሌሉበት እዚህ ምን አሳበደክ?? እኔ ዼንጤ መደገፍ መቃወም አይደለም ግን እኛ አሁን አገራችን እና ቤትክርስቲያናችን በዚህ አስከፊ ሁኔታና መከፋፈል እያለች እሮጠን ዼንጤን መሳደብ ወድያ እኛ በምን ተሽለን የስድብ ድግሪ ነው የተሸከምነው አንድ ዼንጤ እዚህ ቢኖር አፉን የሚከፍት የለም ጌታ ይባርክክ ብሎክ ነው ዞረ የሚለው እኛ እንደ አብነዘበሰማያት ስንደግም. እናም በማርያም ይዣችዋለው አትሳደቡ!!!!!!! ኤጭ አሁንስ በዛ ይራሳችንን ጉድፍ ሳናይ የሰው ጉድፍ አንመልከት.ዼንጤ ዼንጤ አትበሉ አስር እጅ ክኛ ትሽለው ተገኝተዋል. ብያንስ አይሳደቡም.እኛ ለአፋችን ዚፕ እናበጅለት.

 22. ሰላም
  | #22

  ወንድሜ ዳንኢል!!!

  ሉሲን ወይም ተሳዳቢን መስደብ አልተፈቀደልንምና በጌታ ፊት ፈጥነህ ንስሃ ግባ:: ለእህታችን ሉሱና ለመሰሎች መድሃኒዓለም ማስተዋልና እውነተኛ የፍቅር ልብ እንዲሰጣቸው ሁላችንም አጥብቀን እንጸልይላቸው:: ሊኖረን የሚገባው የፍቅር እዳ ብቻ መሆን አለበትና እንደ እግዚአብሔር ቃል እንዲናገሩ{‘ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር” 1ጴጥ4:11 ስለሚል)::

  ማንኛችንም ብንሆን አጥብቀን ልንረዳው የሚገባን ነገር ቢኖር በስድብና በጥላቻ ደስ የምናሰኘው ሰይጣንንና አጋንንቶችን ብቻ ነውና እባካችሁ እድል ፈንታ አንስጠው??? ደግሞም ያሳደገችን ቤ/ክ የወላድ መካን የሆነችውና ልጆችዋን እያጣች ያለችው በውስጥዋ ያለንና የነበርን ተከታዮች በምናሳየው ይህን መሰል ባህሪ ነውና ይልቁንስ እራቁትዋን እንዳትቀር በቃሉ እውነት ዘወትር እንቀደስ(ዮሐ17:17)::

  ”በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ
  ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ
  ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ
  ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ
  ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ
  መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ
  በጎነት ቢሆን
  ምስጋናም ቢሆን
  እነዚህን አስቡ’::(ፊልጵስዩስ 4:8)
  ይላልና በእጃችን የያዝነው መጽሐፍ ቅዱስ እንዳያቃዠን ከመንተራስና ከመሳለም አልፈን እንብላው/እናንበው:: የማይጠገብ የሕይወት እንጀራ ነውና:: እንበርታ! እንበርታ! ይህን በፍቅር እያደረግንና ስለሕዝባችን መከራ ወደ ሰማይ እየጸለይን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በጋራ ማድረግ ከቻልን በቅርብ ጊዚ ውጤታማ እንደምንሆን አምናለሁ::

  ሉሲን የምወድበት ንጽህ ልብ ከሌለኝ በእውነት ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነኝ:: ለአንተም እንደዚሁ ነውና ወንድሜ ዳንኢል በረከትህን እንዳታዘጋው ብልህ ሁን:: በርታ በርታ!!!!

  ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከእንግዲህ የተሳዳቢዎችና የክፎዎች ዋሻ አትሆንም:: አሜን::

  የሰላም አምላክ ሁላችንንም በምህረቱ በዚህ አዲስ ዓመት(በሰው ቆጠራ)ይጎብኘን:: አሜን::
  እወዳችሁአለሁ!!!
  ሰላም ነኝ

 23. ማተቡ
  | #23

  ወገን!!::
  ወያኔ የታሪክ ማሕደርና ለመልኮታዊ እምነት ምንጭና መሰረት ::በቅዱስ መጽሓፍ እንደ ክብርት ሕገራችን ስሙ የተጠራ ሓገር (ክእስራኤል ቀጥሎ) ሌላ የለም::

  የወያኔ ርኩስ መንፈስ እንደዚህ የሚያቅበዘብዘው:: የተነሳንበትን ጽንሰ-ሓሳብ (እኛ እየረገምን ያለነው አራዊቱን ወያኔን ነው)አስቶ ወደ የሓይማኖቶች ንትርክ ልያስገባን በመሞከር ላይ ያለው “አወቅንብህ”!!, ስላልነው ነው::ከሞላጫነቱ ብዛት የተነሳ:አንዴ እሴት (“ሰላም”)ዪሆናል::”እናንተ ወንዶች ሴት አታከብሩ” bla,,bla!! ዪላል::
  ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላ ሐይማኖተኛ ሆኖ “ኩራት ብቻ”, “ተቆንጥጣችሁ ያደጋችሁ” ዪለናል::

  ብሁሉም አቅጣጫ መጣ, የሁሉም ጭንቅላቱ አራዊቱ ወያኔ እንደጭቃ ጠፍጥፎ የሰራውና ድያብሎስ “እፍ” ብሎ እሳት የበላ አፉን የፈጠረለት ዘረኛ መጻጉእ ፍጥረት ነው::እናም በየሓይማኖቱ: በየማህበሩ ደቀ-መዛሙርቱን ሰግስጎ አንዱ ሲመታ ሌላው ሺፋን እየሰጠ “የጦር አበጋዝኔቱን” ነው እያስተማረን የለው ወያኔ (ካዎቅንበት!!)::ግን ብዙዎቻችን በዚህ ዉስብስብ ስልቱ እንደናገርለት ይሆናል:: ወያኔ ከዚህ በላይ አያድግም!!, ከዚህ በላዪም (ከድያብሎስነት በላይ)ጸረሰብ አይሆንም::

  ማተቡ

 24. ማተቡ
  | #24

  ወገን!!::
  የወያኔ ርኩስ መንፈስ እንደዚህ የሚያቅበዘብዘው:: የተነሳንበትን ጽንሰ-ሓሳብ (እኛ እየረገምን ያለነው አራዊቱን ወያኔን ነው)አስቶ ወደ የሓይማኖቶች ንትርክ ልያስገባን በመሞከር ላይ ያለው “አወቅንብህ”!!, ስላልነው ነው::ከሞላጫነቱ ብዛት የተነሳ:አንዴ እሴት (”ሰላም”)ዪሆናል::”እናንተ ወንዶች ሴት አታከብሩ” bla,,bla!! ዪላል::
  ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላ ሐይማኖተኛ ሆኖ “ኩራት ብቻ”, “ተቆንጥጣችሁ ያደጋችሁ” ዪለናል::

  ብሁሉም አቅጣጫ መጣ, የሁሉም ጭንቅላቱ አራዊቱ ወያኔ እንደጭቃ ጠፍጥፎ የሰራውና ድያብሎስ “እፍ” ብሎ እሳት የበላ አፉን የፈጠረለት ዘረኛ መጻጉእ ፍጥረት ነው::እናም በየሓይማኖቱ: በየማህበሩ ደቀ-መዛሙርቱን ሰግስጎ አንዱ ሲመታ ሌላው ሺፋን እየሰጠ “የጦር አበጋዝኔቱን” ነው እያስተማረን የለው ወያኔ (ካዎቅንበት!!)::ግን ብዙዎቻችን በዚህ ዉስብስብ ስልቱ እንደናገርለት ይሆናል:: ወያኔ ከዚህ በላይ አያድግም!!, ከዚህ በላዪም (ከድያብሎስነት በላይ)ጸረሰብ አይሆንም::

  ማተቡ

 25. ግሩም
  | #25

  እኔ እንካን ለዚህ ጽሁፍ የሚሆን አስተያየት የለኝም ጽሁፉ ሁሌም ስለማይመቸኝ አሁን አስተያየት መስጠት የፈለኩት ለ ሰላም ነው ለትህትናሽ እግዚአብሄር ይባርክሽ ጌታም ያለው ለሚሰድባቹ አውድሱ ነውና ላንቺ በሰጠሽ ማስተዋል ጌታን አመሰገንኩት ምንም ሁኚ ምን ሀይማኖትሽ ትልቁ ነገር የጌታን ቃል መያዝሽ ተባረኪ ለትውልዱ አርአያ ያርግሽ ለሌላው ምሳሌ ነሽ

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።