አጼ ሀይለስላሴ እና አትሌት ሀይሌ በ”እንቁ” የአፍሪካ ልጅነት ተመረጡ በታምሩ ገዳ (ለንደን)

December 29th, 2010 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት ቀዳማዊ ሀይለስላሴ እና ታዋቂው አትሌት ሀይሌ ገ\ስላሴ በአፍሪካ አሕጉር ውስጥ ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱት ወይም በመጫወት ላይ ከሚገኙት ሃምሳ “እንቁ” የአሕጉሪቱ ልጆች መካከል ስማቸው ተካተተ፡ለንደን ውስጥ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው ወርሃዊው ፎክስ ኦን አፍሪካ መጸሔት በቅርቡ በመላው አለም ለሚገኙ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ አምባቢዎቹ ባወጣው የአህጉሪቱ “የሁል ጊዜ ታላልቅ ሰዎች ” የምረጡ ማስታወቂያ መሰረት አፍሪካ ውስጥ ቀደም ሲል በተካሄዱ ወይም በመካሄድ ላይ ባሉ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ እንዲሁም ኢኮነሚያዊ እንቅስቃሴዎች አኳያ አጼ ሀይለስላሴ እና አትሌት ሀይሌ ገ\ስላሴ ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት በመልካም አርያነት ሊጠቀሱ ከሚገባችው ሃምሳ(50) የአፍሪካ ታላላቅ ስዎች ተርታ የስም ዝርዝራቸው ሰፍሯል፡:

አጼ ሀይለስላሴን በተመለከት ይከተሉት የነበረው የዘውዳዊ አገዛዝ እጅግ ሃላቀር ከመሆኑ አልፎ በአገር ውስጥ
የተለያዩ የመብት ረገጣዎች መፈጸማቸውን በምሪት የሚናገሩ ወገኖች አልታጡም ፡፡በሌላ በኩል ንጉሱ ኢትዮጵያን ወደ ዘመናዊ ሰልጣኔ ለማሸጋገር የትምህርት ፣ የጤና ፣የመንገድ ፣ የኢንዱስትሪ … ወዘተ ተቋማት እንዲስፋፉ በማድረግ ረገድ የማይናቅ ሚና መጫወታቸውን የሚመስክሩ ወግኖች በርካታዎች ናቸው ::
በለንደን የአፍሪካ እና የኦሪንታል የጥናት ዮኒቭርስቲ ውስጥ በምስራቅ አፍሪካ ዙሪያ ተመራማሪ በመሆን ወደ ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዚያት ጎራ እንደሚሉ የተናገሩት ሚስተር ካርል (ትክክለኛ ስማቸው አይደለም) ከዚህ ጸሐፊ ጋር ባደርጉት ቃለ ምልልስ ” አጼ ሀይለስላሴ ኢትዮጵያ በውጪው አለም እንድትታወቅ ከፍተኛ ጥረት ካደረጉ ጥቂት መሪዎች መካከል በቀዳሚነት ሊጠቅሱ ይችላሉ ፡፡

የፓን አፍሪካ ፍልስፍናን በማንገብ በአፍሪካ ውስጥ በቀኝ ግዛት ቀንበር ስር የወደቁ አገሮች ነጻነታቸውን እስካላገኙ
ደረስ የተቀረው አለም የሰላም እንቅልፍ ሊተኛ እንደማይችል በማስገንዘብ ፣ የተቃረኑ ወገኖችን በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ በማስታረቅ ፣የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫውን በአ\አ አንዲያደርግ መሪዎችን በማሳመን ረገድ…ወዘተ የንጉሱ ተጋድሎ ቀላል አልነበረም ፡፡ ዛሬ የአለም መሪዎች አብይ የመነጋገሪያ ርዕስ የሆነው የኒዩክለር እና የጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያዎች መወገድን በተመለከተ አጼ ሀይለስላሴ ቀደም ብለው በተለያዩ የአለም አቀፍ መድረኮች ላይ በጽኑ ሲሰብኩ የነበሩ ብርቱ መሪ ናቸው” ብለዋል፡፡ እያንዳንዱ መሪ የራሱ ጠንካራ ጎን እንዳልው ሁሉ የራሱ የሆነ ደካማ ጎን አያጣውም ያሉት እኚሁ ምሁር በወቅቱ ተነስቶ የነበረውን የመሬት ለአራሹ ጥያቄ፣ የድብቁ ረሃብ ፣የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ… ወዘተ ቀደም ብለው ወይም በጊዜው ለመመለስ ያለመቻላቸው ለውድቀታቸው መፋጠን ዋንኛ መንስኤዎች ከሆኑት መካካል ጥቂቶቹ አንደነበሩ ጠቅሰዋል ፡፡ አስተያየታቸውን በመቀጠልም ” ከንጉሱ ውድቀት በሁዋላ ያ የኢትዮጵያ ገናና ታሪክ ተነዶ አገሪቱ ሆነች ህዝቦቿ በረሃብተኛ ፣በሰደተኛ፣ለተለያዩ በሽታዎች እና የርስ በርስ ግጭቶች ምሳሌነት ለመጠራት በቅተዋል” ሲሉ ምሁራዊ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡በአጠቃላይ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ለኢትዮጵያ ሆነ በማደግ ላይ ላሉት የአፍሪካ ፣የላቲን አሜሪካ እና የካሪቤያን አገሮች ካደርጉት አስተዋጽኦ አኳያ “በእንቁ ሰዎች” ተርታ መመረጣቸው ተገቢ መሆኑን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

አጼ ሀይለስላሴን በተለያዩ መድረኮች ላይ እንዳዩዋቸው የሚናገሩት አቶ ማን ከለክሎት አድማሱ የተባሉ አዛውንት በበኩላቸው ለዚህ ጸሐፊ ሲናገሩ ” ግርማዊነታቸው ህዝቡ ሃይማኖቱን፣አንድነቱን እና ባህሉን ጠብቆ እንዲቆይ ከማድረጋቸው የተነሳ በአካል የማያውቋቸው ወጣት ኢትዮጵያዊያን ሆኑ የሌሎች አገር ዜጎች ዛሬ የንጉሱን ስም እና ምስል ያለባቸውን ካንቲሪዎችን ፣ጃኬቶችን እና ኮፍያዎችን … ወዘተ በማጥለቅ ታዋቂ አርቲስቶችም ቢሆኑ ሰለ ንጉሱ ገናናነትን የሚያወድሱ ዘፈኖችን በማቀንቀን ለንጉሱ ያላቸውን ልዩ ፍቅር ሲያሳዩ ይታያሉ፡፡ሌላው ቀረቶ በሃይማኖት ረገድ እንኳን በአሁኑ ወቅት የግርማዊነታቸው ስም በሁሉም የኢ\ኦ\ተ\ቤ\ን የዕለት ጽሎት ፣የወር እና የአመት ክብረ ባዕላት ላይ በክብር ከሚጠሩት ጥቂት የቀድሞ ደጋግ የኢትዮጵያ መሪዎች መካከል አንዱ መሆናቸው በራሱ ዛሬ ድረስ ከአርባ ሚሊዮኖች በላይ ከሚቆጠሩ ምዕመናን ጋር ያላቸውን ቀጥተኛ የሆነ የመንፈሳዊ ቁርኝትን ያመላክታል” በለዋል፡፡
በዚህ የመጽሔቱ የአምባቢዎች ነጻ ምርጫ ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት ስማቸው ከተካተተው ሁለት ኢትዮጵያዊያን አንዱ የሆነው አትሌት ሀይሌ ገ\ስላሴ ሲሆን ሀይሌ የተለያዩ ሃያ ሰባት ሪኮርዶችን በመስበር እና የወቅቱ የማራቶን ሪኮርድ ባለቤት በመሆን በአፍሪካ ሆነ በአለም የአትሌቲክስ የውድድር መድረኮች ላይ ለረጅም አመታት አሸናፊ በመሆን ለአድናቂዎቹ ጥሩ አርያ የመሆኑ ጉዳይ የብዙዎቹ የመጽሔቱን አምባቢዎች ቀልብን ለመሳብ አንዳስቻለለት ተገምቷል፡፡ከሩጫው ሜዳ ባሻገር በኢንስትመንት መስኩ በለስ የቀናው ሀይሌ በቅርቡ በአንድ የገዢው ፓርቲ አመታዊ ስብሰባ ላይ በመገኘት “ፖለቲካዊ አንድምታ” እንዳለው የተገመተ አስተያየት በመስጠቱ ሳቢያ ” እንዴ ሀይሌም እጅ ሰጠ ?” የሚል ጥያቄ ከበርካታ አድናቂዎቹ ዘንድ አስከትሎ አንደነበር አይዘነጋም፡፡በተጨማሪም በንግዱ መስክ ከአቶ መለስ ባለቤት ወ\ሮ አዜብ ጋር ሸሪክ እንዲሆን ፖለቲካዊ ጫና እየተደረገበት መሆኑን እና የተንቀሳቃሸ ስልኩ (ሞባይሉ) በኢሀዲግ የደህንነት ሰዎች የጠለፉበታል… ወዘተ ለሚሉ አስተያየቶች በተመለከተ ሀይሌ ማስተባበሉን ሮይተርስ የተባለው የዜና አገልግሎት ሰሞኑን ዘግቧል፡፡

ይሄው ዘገባ በማከልም ሀይሌ የሩጫ ጫማውን በሰቀለ ማግስት ፊቱን ወደ ፖለቲካው በማዞር የጠ\ሚ\ርነት ፣የፕሬዜዳንትነት ወይም የሚኒስተርነት ቦታን ለመቆናጠጥ በመጣር ለእርሱ፣ለቤተሰቡ፣ለአገሩ እና ለአፍሪካ የሚሆን ታሪክ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡ከሩጫ ጋር በተያያዘ ሀይሌ በቅርቡ ለታዋቂው የጆኒ ዎከር ውስኪ መጠጥ ለአንድ አመት መቶ ሺህ (100,000 )ዶላር የሚገመት የማስታወቂያ ስራ መፈራረሙ ከቅርብ አትሌት ጓደኞቹ ሳይቀር የስፖርታዊ መርህ ከሆኑት አንዱ የሆነውን ሰፖርት ለጤንነት የሚለው መልዕክትን ይጻረራል በተጨማሪም ለታዳጊ ወጣቶች መጥፎ መልክት ያስተላልፋል የሚሉ ወቀሳዎች እና ብርቱ ቅሬታ ገጥሞታል፡፡ ይሁንና ሀይሌ በበኩሉ “ሰዎች መጠጥ ሲጎነጩ ሃላፊነት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባቸዋል፡፡ የማስታወቂያው አላማ ስለመጠጥ ጥሩነት ለመግለጽ ሳይሆን ስለጽናት እና ውጤታማነት ገላጭ ነው ” ሲል በሰራው የውስኪ መጠጥ ማሰታውቂያ ትክክለኛነት በአላማ ደረጃ መስማማቱን አፍሪካ ሪቪው የተሰኘው ድህረ ገጽ ሰሞኑን ሀይሌን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ይህን ምርጫ ተከትሎ ሌሎች በርካታ አስትያየቶች እየተሰነዘሩ ሲሆን ኢትዮጵያ የወራሪው የጣሊያን ጦርን በአደዋው ጦርነት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለጥቁር ህዝቦች የአትንኩን ባይነት ተምሳሌት እንድትሆን ያደርጉት ዳግማዊ ምኒሊክ ስማቸው ቢካተት ጥሩ ነበር የሚሉ ወገኖች ይገኙበታል ፡፡በሌላ በኩል በአንድ ወቅት የአፍሪካ “ብሩህ ተሰፋዎች” ተብለው በቀደሞው የአሜሪካው ፕ\ት ቢል ክሊንተን የተሞካሹት የኢትዮጵያው አቶ መለስ ዜናዊ፣ የኤርትራው አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የሩዋንዳው ፖል ካጋሜ እና የኡጋንዳው ዩኤሪ ሙሴቪኒ የፎከስ ኦን አፍሪካ መጽሔት አምባቢዎች ድምጽ ከመስጠት ከነፈጓቸው የወቅቱ መሪዎች መካከል የገኙበታል፡፡ከአምባቢዎች ከፍተኛ ድምጽ ካገኙት ሃምሳ “እንቁዎች” መካከል የቀድሞው የተመድ ዋና ጸሐፊ ጋናዊው ኮፊ አናን ፣የቀድሞው የደ\አፍሪካ ፕ\ት ኒልሰን ማንዴላ እና የቀድሞዋ ባለቤታቸው ዊኒ ማንዴላ ፣የአፍሪካ የሰነጽሁፍ አባት የሚባሉት ናይጄሪያዊው ቺኑኣ አቻቤ ፣ በ አፍሪካ ታሪክ የመጀመሪያዋ የሴት ፕሬዜዳንት የላይቤሪያዋ ኤለን ጆንሰን ፣ የጸረ አፓርታይድ ዋንኛ ተዋንያን ለቲቭ ቢኮ፣ የፓን አፍሪካ አርበኛ እና የቀድሞው የጋናው ፕ\ት ኩዋሜ ናኩርማ ፣ የደ\አፍሪካ የጸረ አፓርታይድ ታጋይ አቡነ ዴዜሞን ቱቱ ፣ እውቋ ደ\አፍሪካዊ ዘፋኟ ማሪያ ማኬባ እና አንጋፋው ካሚሮናዊው የእግር ኳስ ተጨዋች ሮጀር ሚላ ተጠቃሾች ናቸው ፡፡

የፎከስ ኦን አፍሪካ መጽሔት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ከሆኑት የአፍሪካ አገሮች ውስጥ በመሪዎች ፣ የኤኮነሚ እና የፓለቲካ ተመራማሪዎች፣የ ኪነጥበብ የስፖርት … ወዘተ አድናቂዎች ዘንድ ከፍተኛ ተነባቢነት ካላቸው መጽሔቶች መካከል በዋናኛነት የሚጠቀስ ነው ፡፡መጽሔቱን በተመለከተ ከ 21 ሚሊዮን በላይ ለሚቆጠሩ የቴሌቭዥን እና የራዴዮ ደነበኞች በተለያዮ ጊዜያት ማስታወቂያ በቀጥታ እንዲደርሳቸው ይደረጋል፡፡

 1. Sheger
  | #1

  Do they know Ethiopian is in this kind of Mess because of the faiure of Haile Selassie to leave his seat which he held mischeiveaously on time? Do they know he was a kind of silet dictator who killed his opponents one by one?

 2. TED
  | #2

  ህዪሊ ገ/ስላሰም መዘላበዱን ትቶ(አንደ አስታራኪ አንደ መሪ ልሁን ከሚል) ዪህ ዪበጀዉ ነበር ለወደፊቱ::
  የሰሞኑ ባህሪዉ አላማረኒም::

 3. ዘርኣያቆብ ያሬድ
  | #3

  የአፍሪቃ ምርጦች

  ታሪክንና ነጻነት አስመልክቶ:
  1. ሃኒባል
  2. ራእሲ አሉላ
  3. ማንዴላ
  4. ፓትሪስ ሉሙምባ
  .
  .
  .

  እፖርትን አስመልክቶ:
  1. አበበ ቢቂላ
  2. ምሩፅ ይፍጠር
  3. ሃይሌ ገብረስላሴ
  4. ቀነኒሳ በቀለ
  5. ብዙ የሩቅ ሩጫ ተቀላጣፊ ከንያዎች (ይቅርታ ስማቸውን አልያዝኩትም)
  6. ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ኮከብ ሴቶች
  7. አበዲ ፔሌ (የጋና የእግር ኩዋስ ተጫዋች)
  8. ጆርጅ ዌህ (የላይበርያ የእግር ኩዋስ ተጫዋች)
  9. ሳሙኤል ኤቶ(ካመሩን)
  .
  .
  .

 4. ዳዊት ከ የሩሳሌም
  | #4

  እስማማለሁ

 5. woye zandero
  | #5

  I agree with Haile G|Silase it is good done but who is Hilsilase…he was murder for us never and ever forget his job.this is a few nafitagna propoganda from London …Remember king is not charge and heavan is not caltivated….jazz

 6. woye zandero
  | #6

  woye zandero :
  I agree with Haile G|Silase it is good done but who is Hilsilase…he was murder for us never and ever forget his job.this is a few nafitagna propoganda from London …Remember king is not charge and heavan is not caltivated….jazz

  @woye zandero

 7. ze
  | #7

  we agree hile G/silase.

 8. ሚልኪያስ
  | #8

  ክሃይለ ይሊቅ አበበ ቢቂላ

 9. አበበ ተስፋችን
  | #9

  ሐይሌም ጃንሆይም በአህጉራችን በጥሩ መልኩ ዕውቅና ማግኘታቸው ሁላችንም
  ሊያስደስት የሚገባ ጉዳይ ነው::ሌሎቻችንም በሞያችንና በችሎታችን ከሌላው አለም እይተወዳደርን
  አግራችንን በጥሩ ገጽታዋ ለማሳወቅ ይልመድብን!

 10. Lucy in America
  | #10

  No wonder if the west will announce the world that Haileslasie is the man of the century because 1.He was pro white colour, he said for one of america’s president USA” I am not negero” 2. He hanged ethiopian young hereo like Belay zeleke who chased away Italy from ethiopia. Haileselasie worked with british general and he advised to hang him to revenge. 3. He spolied ethiopian’s proud name by running away from africa by leaving his ppl and country in difficult times.4. He blocked ethiopia’s civilazation by not reforming or transporming power to the new generation, and as a result now ethiopia became a failed state under tegere’s thugs who have been giving to britain to looot ethiopia’s gold and sugar and any thing what they want.5. Haileselasie allowed to foreign baseless religion by saying ” hager ye gara newu hayimanot yegele newu”to divide our people .6. Haileselasie had stolen un known amount of money and hidden in the foreign banks and now they are using that money when our people are dyng.7. Haileselasie failed to prepared and armed the ethiopian’s people to defend his country as King menelik did in adwa because of that millions of ethiopians were killed by invader forces.9. He was the first repressive king who stay for a long time on power from africa and did very little for his country. 10. He killed the powerfull prince eyassu whom the westren countries were affarid of him. 11. He kept in secret the wollo srought and caused for the death of over 500,000 inncent ethiopians by the lack of coordination.12. He hanged and killed a well known general mengistu neway.13. he had done so many damages aganist poor ethiopia’s farmers. we can lists so many .

 11. ያለው
  | #11

  እያንዳንዳችን ስልጣን ላይ ብንሆንና ብንታይ እውን የኢትዮፒያን ህዝብ በሙሉ ማስደሰት እንችላላለን??? በጣም የሚግርመኝ ዝሆን የሚአክል መልካም ነገርን ማየት ተስኖን ጥንቸል የምታክል ሎዶሎ ነገር የምንቆጥር ሰዎች የራሳችንን ጎዶሎነት እያንጸባረቅን እንጂ በትክክል መፍረዳችን አይደለም. አገር መምራት ቀላል አይደለም. አንድ ቤተሰብ ሆነን እንኳን አለመስማማት አለ. አንድ ግሩፕ ሆነንም አለመስማማት አለ . እናም አገር መምራት ሁሉንም ማደሰት አይቻልም. ዋናው ከመቶ ከ60 በላይ ህዝብ ከመረጠ ደህና ነው. ክ 100 70 በጣም ጥሩ ነው ከ መቶ 80 ደሞ እጅግ ድንቅ ነው. እናም ማለት የፈለኩት ንጉስ ሃይለ ስላሴ እኛ አልደርስንባቸው ይሆናል ወይ ደሞ ህጻናቶች እንሆን ይሆናል ወይ ደሞ ትዝ አይለን ይሆናል . ስለዚህ ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይናገር የነበረ ነውና በዛን ስሃት የነበሩ ሲናገር በደርግም ሆነ ቢአዴግ ጊዜ ስጠየቁ የንጉሱን ዘመን እጅግ የሚያወድሱ ብዙ አሉ . ከደርግ ጋር ደሞ ኢአዴጝ ሲተያይ እያየነው ነው ይዘርኝነት ልክፍት,የአገር መሸጥ, የገንዘብ ማሽሽ, ሙስና, የተቃዋሚ እና ይህዝብ ጥላቻ ማየል, ከመልካም አስተዳደር ጉድለት የሚመጣ እርግጦ የመግዛት, ያምባገነንነት ስርሃት ….ብዙ ማለት ይቻላል.በተለይ እዚ ውስጥ ዪአዴግ ደጋፊ ካልችው እውነቱን ንገሩን በዚ ሰሃት ህዝብ እየተማረረ ያለበት ነገር ታቃላችው ይህ ነው የሚባል የንሮ ሰማይ መድረስ ምንም ተፈጥሮ አይደለም ለምን አልመረጥከኝም በሚል ሰበብ ደሞዝና ወጭ በማይመጣጠን ንሮን እንዲገፋና ብሶቱ እንዳይፈነዳ ብረሃብ ህዝቡን እያዳከመ እጅግ ብዙ ይሆነ የሆነ አጥያት እየሰራ ነው. እናም ንጉሱን እየጠላን ያለን አንድ ተናገሩ ብንባል ይህ ነው የምንለው ነገር የለም ኢአዴግና ደርግ የነፉትን ፕሮፓጋንዳ እንደገደል ማሚቱ ከማስተጋባት በስተቀር. ንጉሱ ጥፋት ይላቸውም ማለት አይደለም የሳቸው ጥፋት ወሎ ስለተራበ አፋጣኝ መልስ አልሰጡም መባል ነው አቤት አቤት!! ለውድቀታቸው ምክንያት የሆነው የወሎ መራብ ነው. አቤት!!!አቤት!! በወሎ ፋንታ አንድ የኦሮሞ ግዛት ወይም የትግራይ ግዛት ተርቦ ቢሆን አቤት ሞር ለፖለቲካ በተመቸ ግን ያው አማራው አምጾ ሳያስቡት ጣላችው. በተርፈ ሃይሌ ስለሮጥ የግል ክብርን አግኝቷል ኢትዮፒያ በርጫ ስሟ ድሮም የጠጠራ ነው እሱ እንኳን ግማሽ ልማት ግማሽ ጥፋት ነው.

 12. jegnaw
  | #12

  እኔ በሁለቱም ምርጫ አልስማማም;;በተለይ አጼ ህይለስላሴ በተለይ በ እርሳቸው የስልጣን ጥም በፊውዳል በርግጥ ከፊል ካፒታሊስት ስር አት ሀገራችንንወደ ዲሞክራሲያዊ ስር አት ሳታመራ ስልጣናቸውን የረባ ለውጥ ሳያመጡ የቀሩ ደካማ መሪ ናቸው;;ይሄ የምርጫ ሃሳብ የመጣው በውጭ ከሚገኘው የዘውድ አሰባሳቢ ምክር ቤት ከሚባል የስልጣን ጥም ካላቸውደካሞች የተጠቆመ ይመስለኛል;;እነዚህ ንጉሳዊ ቤተሰቦች አሁንም ሀገሪቱ እንደ እንግሊዝ royal familyክብርና ዝናን አግኝተው ለመኖር ያልማሉ;;የ እንግሊዝ ንጉሳዊ ቤተሰቦች ለሀገሪቱና ለህዝቡ ታላቅ እድገትን አምጥተዋል;;የኛዎቹ ግን ቆዳቸውን እያዋደዱ የህዝባችንን ደም ሲመጡ የኖሩ ተባዮች ናቸው;;የሚገርመው ነገር ሀይለስላሴ በደርግ እጃቸው በተያዘበት ወቅት አንድ ጠቆር ያለ ወታደር የጎንደር ሰውን አንተም ኢትዮጵያዊ ነህ ብለው እንደሳቁበት በነበር መጽሀፍ ግጽ 141 ተጠቅሶ ይገኛል;;ሌላው ደካማነታቸው ተራ ሰው ማች መሆናቸውን ረስተው የጃማይካን ህዝብ እርሳቸውን ሳይሆን ፈጣሪን እንዲያመልክ እንኩዋን አንዲት ቃል አለመተንፈሳቸው የመያሳዝን እና የሚያሳፍር የታሪካቸው አካል ነው;;
  ሀይሌን በተመለከተ ግን የወያኔ ተጽ እኖ በጣም ሳይበረታበት አልቀረም;;ይሁን እንጂበዚህ ክፉ ጊዜ ከኢትዮጵያውያን ጋር ስላልቆመ አይገባውም

 13. ቅፍጣናው
  | #13

  ይህ የነፍጠኛ ቅዥት ወይም ህልም ስለሆነ ይሚሰማችሁ የለም::ወራዶች አትስሩና አውሩ ወሬ አይሰለቻችሁም ህይለስላሴ የስንቱን ሰው ደም ጠጥቶ ያለፈን ሰው እያነሳችሁ የምታሽቃብጡማ ክሆነ መለስ ዜናዊንም መውቀሱ ባላስፈለገ ነበራ? የጥቂት የነፍጠኛ ርዝራዥ ፕሮፓጋንዳ ስለሆነ ብዙም አይገርምም::

 14. ማይክ
  | #14

  ብስለት የተምላበት ኣና የምስማማበት ነው. እመስግናለሁ

 15. m.k
  | #15

  i agree with hile g/silase and meles zenawie i think you all agree too.

 16. ናደው
  | #16

  እሪ ማለት ዪብጃል ወዪስ ዪህን ላፕቶፔን በቦክስ እንከሚአስነጥሰው ድረስ ላናፍጠ!! አንድ ሰው እንዳዪገላግለኝ ትዝ አለኝ ያግራችን ፊውዳል በቅሎዋ መቸም ስትሰግር እንድ እንዝርት ነው የሚያሽከረክራት አለያም እንደሞቃት ኮረዳ መቀምጫዋን “እንጃባህ እንጃባብ” እያናግረች የምትሄድ ነው የምትመስለው አንድ ቀን አልቀረም አሽከር የብቅሎዋን ግላስ አስክር በደንብ አላሰረዉም ኖሩዋል ገታ ከመደራቸው ወጥተ ወንዙን እንደወረዱ ሳይስቡት ግላሱ ተፈታና ጌታ አንድ እግራቸው እርካቡ ላይ እንደተወተፈ ከብቅሎዋ ጉያ ወስጥ ገቡ ብቅሎም በመደንገጥ ጌታን እየጎተተች በርግጫ ነፍሳችሀውን ስትጠፋቸው ጌታ ከመሞት መስንበት ብለው ሺጉጣቸውን ከወገባቸው መዥለጥ ያደጉና በቁሎዋቸውን ኩኩዋን አስተካክለው ነፍሳቸውን አዳኑ ተሸክሙዋቸው የነበረን ኩርቻ ተሸክመው ወደቤታቸው ተመለሱ እኔም ዪሄ ላብቶፕ መጥፎ ወሬ እያሰማ ስላስቸገረኝ ኩኩን ልለው ተነስቻለሁ አሁን አጤ ኃይለስላሤንና ሀይሌን አንድ ላይ ማወዳደር አገሪቱ ምን ያህ ተዋርዳለች ማለት ነው

 17. ወያኔ
  | #17

  ይህ ትውልድ ካለፈው ትውልድ በዘርነቱ ሳይሆን በአስተሳሰቡ ትንሺ መሻል አለበት::ወቀሳ ትችትና ስድብ አሁን በህይወትና በተግባር ላይ ባሉት ዘንድ ይሁን:: ምክንያቱ መሻሻል ባይችሉም የምንናገረውን ከሞላጎድል የሰሙ ይሆናልና::ሙት አይወቀስም እግዜር የፈቀደለትን ተግብሮ ገሎም ይሁን አስሮ ሰርቆም ሰርቶ ከዚህ ዓለም ተለይቷል:: ከዚህ አንጻር እኛ ሳንሆን ሌሎች ለሚስጡት አስተያየት የምንሰጠው አወንታዊ ያልሆን አስተያየት የራስን ማንነትና ደካማነት ከምስገመት ውጭ ፋይዳ የለውም::በጣም በምወደና በማከብረው ታዋቂው አትሌት ሀይሌ ገ\ስላሴ ላይ የሚደረግ ትችትን አልቃወምም ምክንያቱም በሕይወት አለና::ሁሉም የሚመስለውን ሲተች እሱም ማንነቱንና አካሄዱን ለመመርመር እድል ያገኛል::ሌላውን መታለፍ የሌለበት ግን ይህ ትውልድ ምንም ይሁን ምንም ጠቃሚ ነገር ለሐገሩ ሳይሰራ በወሬ ብቻ ከዚህ ዓለም ለመለየት ተቃርበናል::ለነፍስ ጥያቄ መልስ የሚሆን በጎ ተግባር የለም::በዚህ መድረክ እንኽውን በአግባቡ በወጉና ባህላዊ አንደምታ ያለው ነገር መጻፍ እከበደን ነው::ታዲያ አገርና ሕዝብ እንዴት ይደጉ?

 18. ወያኔ
  | #18

  ይህ ትውልድ ካለፈው ትውልድ በዘርነቱ ሳይሆን በአስተሳሰቡ ትንሺ መሻል አለበት::ወቀሳ ትችትና ስድብ አሁን በህይወትና በተግባር ላይ ባሉት ዘንድ ይሁን:: ምክንያቱ መሻሻል ባይችሉም የምንናገረውን ከሞላጎድል የሰሙ ይሆናልና::ሙት አይወቀስም እግዜር የፈቀደለትን ተግብሮ ገሎም ይሁን አስሮ ሰርቆም ሰርቶ ከዚህ ዓለም ተለይቷል:: ከዚህ አንጻር እኛ ሳንሆን ሌሎች ለሚስጡት አስተያየት የምንሰጠው አወንታዊ ያልሆን አስተያየት የራስን ማንነትና ደካማነት ከማስገመት ውጭ ፋይዳ የለውም::በጣም በምወደና በማከብረው ታዋቂው አትሌት ሀይሌ ገ\ስላሴ ላይ የሚደረግ ትችትን አልቃወምም ምክንያቱም በሕይወት አለና::ሁሉም የሚመስለውን ሲተች እሱም ማንነቱንና አካሄዱን ለመመርመር እድል ያገኛል::ሌላውን መታለፍ የሌለበት ግን ይህ ትውልድ ምንም ይሁን ምንም ጠቃሚ ነገር ለሐገሩ ሳይሰራ በወሬ ብቻ ከዚህ ዓለም ለመለየት ተቃርበናል::ለነፍስ ጥያቄ መልስ የሚሆን በጎ ተግባር የለም::በዚህ መድረክ እንኳን በአግባቡ በወጉና በባህላዊ አንደምታ ያለው ነገር መጻፍ እየከበደን ነው::ታዲያ አገርና ሕዝብ እንዴት ይደጉ?

 19. Lucy in America
  | #19

  The westren countries have worked day and night to destroy ethiopia, and they have used different forces, one of their forces was hailselasie and now Meles. The west had never pushed that dictatorial and cruel king to reform or to give political power to the young generation. The damages which his repressive and dictatorial regime had done could not repaire still now. Derg was the direct product[ son] of hailselasie and meles is haileselasie’s grand son. If that cruel and selfish king gave power to his son and push for a quick reform, derg could not come to menilik’s palace with it’s military uniform and ethiopia could not fall on the hands of tegeres’ lootters. So the whole messes now are becuase of his greediness and his greediness took him towards such a shamfull death. What is a cursed for haileselasie is his entire grand children became now TPLF’s slaves and they are preparing them selves for the second time death penality like their father. His grand son ” prince ‘ mekonen endalekachew has brought wabishebe hotel from weyanes not long time ago. Which is really sham for ethiopia. The crown families whom supposed to stand with ethiopia and it’s ppl and lead the struggle to save ethiopia are now working for ethiopia’s canncerious enemies. The man has paid millions of dollars for weyanes and weyanes are going to invest that money for the killing and torturing and for their destructive action aganist ethiopia. . His another grand daugther [ king hailu shawul's daughter-in law ] has been working for weyanes as key person in their protocol office. His grand son, mulugeta asrat has been working for weyanes in different places and right now he is working in TPLF’s embassy in Irland.His brother is living in germany and he is neutral from politics that is another sham for ethiopia. When the nation is calling for help , these greedy the so called crown families are hidding everywhere . dog’s crown families.

 20. ዘርኣያቆብ ያሬድ
  | #20

  Now i got it! Thank you, ‘Lucy in America’:
  “His another grand daugther [ king hailu shawul's daughter-in law ] has been working for weyanes as key person in their protocol office.”

  ለካስ ያ ሁሉ የኢትዮጵያ ‘ሁቱዎች-ሞቡቱዎች’ መጨባበጥ, መከዳዳትና አሁን ደግሞ እንደገና ተገናኝቶ ለመጨባበጥ ያመች ዘንዳ,ወደ ሊቀመንበርነት ለመመለስ መቸባቸብ ሚስጥሩና ብልሃቱ ሁሉ የሚቀነባበረው እዚሁ “የ’shawul’s daughter-in law” ቢሮ ውስጥ ኖርዋል!! ይሀንን እስከ ዛሬ ድረስ አላወቅኩም ነበር!! በትግርኛ’አነስያ ክምርዖሞ ክሓልፈለይ በለት ዓባይ ጝል’ እንዲሉት አይነት ነገር መሆኑ ነው. ኢትዮጵያ ለካስ በሁለመናሽ ተተብትበሽና ተሳስረሽ ተይዘሻል! ቂቂቂ!!!!ኪኪኪ!!!!!

 21. የታዘበው
  | #21

  ያለው እና አበበ ተስፋችን ያሉት ትክክል ነው እስማማለው. በተለይ አበበ ተስፋችን ብስለት ያለው ንግግር ነው . ያለው የተናገርው ነገር በጣም ገረመኝ ” ብዙዎቻችን ስለጃንዮ ደርግ እና ወያኔ የነፋውን እንደገድል ማሚቶ ከማስተጋባት በስተቀር የምናቀው የለም” ልብ በሉ THE SAME THING ዘረ ያህቆብ የጻፈውን ካነበባችው 10 ኪው ሉሲ ከአሜሪካ ይህም አለ እንዴ ለካ አላቅም ነበር አለ. እናም ይህ ሰው አሁን ልክ እንድሚያውቅ ለሌላ ሰው ሌላውም ለሌላ እያለ ያላዩትንና በጥላቻ ፈጠራ እንደገደል ማሚቶ ማስተጋባት ይሉሃል እንዲህ ነው አያቹ. የሚገርመኝ ሉሲ ሁሌ ስለምንም ይጻፍ ስለምን ስለፖለቲካም ይሁን ስለግለሰብ ብጭ ስለምንም ይሁን በተጻፈው ነገር ሁሉ 100%100 አጌይንስት መሆኗ ይገርመኛል. ሌሎቻችን ወያኔን በተመለከተ ተመሳሳይ አስተያየት አለን በሌላው ነገር ደሞ የመደገፍ እና የመቃወም ነገር እናሳያለን ይቺ ሴት ግን ምን ይሁን ምን ምንም ድህና መልስ የላትም አንድም እንኳን?? ማንም ፐርፌክት የለም. እናም እስቲ ከራስሽ ጋር ታርቂ መጀመርያ. ነፍተኛ ሲባል እራሱ ያስቀኛል የሰማናትን ኮፒ እያረግን ስልሆነ ነፍተኛ ማለት በጊዜው ስልጣን የያዘ ማለት ነው ደርግ በጊዜው ነፍጠኛ ነበር አሁን ደሞ ወያኔ ነፍጠኛ ይባላል. ይሀ ነው ትርጉሙ. እናም ከማናቸውም ከስማነውም ካየነውም መቶ ጊዜ ጃንዮ ይሻላሉ ባይ ነኝ .

 22. Lucy in America
  | #22

  I gave my personal vote and voice for the voiceless and fearless the ethiopian’s heroe who punished fascist Italy and Adolf Hitler in their own soil with their own weapon , the man of the century in human’s history. enjoy reading. Ethiopia has been a hell for it’s heroes and dancing palace for bandas.Abdissa Aga
  Colonel Abdissa Aga was born in Welega. His
  father lost his temper and killed his own
  brother when Abdissa was about 12 years old.
  Though he went as far as Addis Ababa to
  appeal for the release of his father, he was
  executed. Sad and embittered, he joined the
  Ethiopian Army around the age of 14 and
  fought against Fascist Italy in 1936 in Ethiopia.
  He was captured and imprisoned in a
  concentration camp in the island of Sicily in
  Italy. There he met Captain Julio, a Yugoslav
  hero.

  The two became friends and made a daring
  escape from the concentration camp taking
  with them a dozen prisoners to the woods.
  They returned to the camp a few days later, at
  night, led by young Abdissa who was terribly
  feared by the Italians. Abdissa choked and
  silenced the guards. He and Julio took off the
  uniforms of the guards. Two of the former
  prisoners wore the uniforms, held the guns of
  the dead soldiers, and stood at the gate of the
  camp pretending to be Fascist watchmen.
  Abdissa and Julio, followed by the other
  partisans Penetrated the camp, released all of
  the prisoners, fought with some of the Fascist
  officers, robbed them off their ammunitions
  and supplies, as well as trucks full of
  weapons, and drove back to the woods.

  They continued to fight in that manner freeing
  prisoners and robbing concentration camps,
  banks, government warehouses, etc. until
  their number grew to an army, and until the
  Italian Government battled with them fiercely.
  The partisans chose Abdissa to be their
  leader and called him Major. The Italian
  Fascists were terrified since they knew how
  brave Ethiopians were recalling the Battle of
  Dogali, Ambalage, Adwa, Maichew and
  remembering the bravery of Zerai Deres,
  whom later, Abdissa tried in vain to see and
  hug. Taking advantage of the fear of the Italian
  people, Italian gangsters painted their faces
  cook and started robbing banks and pillaging
  villages imposing as Abdissa and other
  Ethiopians who were also partisans together
  with him. Abdissa caught these awe-inspiring
  gangsters and executed them, since they
  were discrediting his name by their atrocious
  acts. The Italian Government did all it could to
  catch Abdissa by force. As they failed to do
  so, they tried to cajole and allure him by
  promising him a big post and by begging him
  to stop fighting and join their ranks. If I recall
  correctly, Abdissa shot the Italian officer who
  brought him the letter from the Italian
  Government.

  Finally, the Second World War broke out. The
  Allied forces, Britain, the USA, France and
  Russia recognized Major Abdissa, Captain
  Julio and the rest of the partisans and began
  to supply them with arms and provisions.
  Major Abdissa Aga was chosen to lead the
  international army of partisans (former
  prisoners) which consisted of Americans,
  English, French, Ethiopians and other
  nationals. Captain Julio became the
  commander of the Yugoslav partisans. This
  way the partisans weakened Italy and
  contributed to their defeat. Major Abdissa Aga
  was the first hero who entered and captured
  the city of Rome sitting in a jeep, waving first
  and foremost the flag of Ethiopia, which was
  also tied around the arms of his international
  soldiers including Americans, French and
  English. When the armies of the allies
  reached Rome, they honored Major Abdissa
  Aga highly. The British made him the
  Commander of the British Military Police and
  sent him to Germany to fight against the
  German Army. He battled with the German
  Nazis in different cities, defeated them,
  controlled the cities and villages, and entered
  Berlin triumphantly again waving Ethiopian
  and British flags. He was in the spot light all
  over the world.

  At the end of the war, the British, the
  Canadians and the Americans wanted him to
  join their armies promising him high ranks. He
  refused adamantly saying that though his
  motherland, Ethiopia, was poor, he would still
  return to her and see the face of his Emperor
  whom he had missed for so long. This
  incensed the Allies, and believe it or not, they
  accused him of ravaging the Italian Fascists
  when he was a partisan. The French, the
  British, the Americans, even the Russians to
  some extent condemned him. Fortunately, a
  noble British general who had decorated him
  with medals previously fought for his release
  changing the prison sentence to financial fine,
  which was paid by Abdissa himself and the
  British Government.

  The great Ethiopian hero finally returned to
  Ethiopia longing to see his country and
  Emperor. The Emperor welcomed him and
  sent him to Ras Abebe Aregai, the then
  Minister of Defense so that he would employ
  him. Ras Abebe and some of the most
  important patriots Ethiopia were scared of
  Abdissa’s valor and feared
  for their own positions. So, instead of
  promoting him to a general, Ras Abebe sent
  Major Abdissa to the Holeta Military Academy
  as a simple cadet. After several months of
  hardship in Holeta he graduated as a first
  lieutenant, to the surprise of the British
  officers whom Abdissa used to command
  when they were in Europe. Abdissa was
  oppressed in the Ethiopian Army. He was sent
  to the Ogaden and fought against the Somali
  invaders displaying incredible courage and
  military tactics. In spite of what he did to raise
  the pride of Ethiopia and to safeguard her
  territorial integrity, he didn’t rise above the
  rank of a captain for many, many years until
  somebody (they say Captain Julio and
  Marshal Tito) drew the attention of the
  Emperor towards the end of the Emperor’s life
  and regime. The Emperor raised his rank to
  colonel and made him his bodyguard. Colonel
  Abdissa Aga the great died a few years after
  the 1974 Ethiopian Revolution

 23. በለው!
  | #23

  አበበ ተስፋችን ያለው የታዘበው ያገኘውን ሐሳብ እኔም በአድናቆት አንብቤዋለሁ ተገርሜአለሁም በለው !
  ከሀገረ ካናዳ…ከምስጋና ጋር በቸር ይግጠመን!

 24. ያደሳ ገለታ
  | #24

  እውነቱን እንነጋገር የደርግ ዘመን የደም መፍሰስ ዘመን , ይትህቢት ዘመን አንድ ኡለት ነገር ጥሩ ሰርቷል የአገር አንድነት አስጠብቋል መሃይምነትን ላይ ዘምቷል. ወያኔ ደስ ይበለውና ኢአዲግ ልበለውና ይችጋር ዘመን, የዘርኝነት ዘመን, አገር የመሸጥ ዘመን, የዘረፋ ዘመን, ይጥላቻ ዘመን, አገር የመክዳትና የባንዳ ዘመን, የሙስና ዘመን ደም የማፍሰሰ ዘመን, የጄኖሳይድ ዘመን,( የኦሮሞና የአማራን ህዝብ) የማፈናቀል ዘመን… አንድ ጥሩ ነገር አርጓል እሱም የሐይማኖት እኩልነት. እሱንም አመሪካንን ለማስደሰት. የሐይለስላሴ ዘመን የጥጋብ ዘመን, የአንድነት ዘመን, ደግ እና መልካም ዘመን የመፋቀር ዘመን, የመከባበር ዘመን, ባቅማችወና በጊዜያቸው የጥሩ ዲፕሎማሲ ግንኙነት, የአንድነት ዘመን,ያለአድሎ የማስተዳደር ዘመን, የስልጣኔ በር ከፋች ዘመን, እናም ማወዳደር ያለብን ካለፈውና ከነበረው ጋር ከሆነ ይገባችዋል!!!!! ንጉስ ሐይለ ስላሴ ይገባቸዋል እንድውም ሲያንሳችው ነው. ሃይሌ ፈርጣጩ ግን አይገባውም ባይ ነኝ ለሆዱ ያደረ አትሌት ከገዳይ ጋር ያበረ ባንዳ ውድያ ባይሆን ለህዝብ ክብርና ፍቅር ዋጋ የከፈለች ብርቱካንን ብትሉ ይስማማኛል.

 25. ጥሩ ነው
  | #25

  ቆፍጣናው አትቀባጥር ደም ያፈሰሱት ደርግና ወያኔ ነው ጃንዮ ተማሪዎች ሲያምጹ ውሃ ነበር የሚረጩት ወያኔ ደም ጥይት እናም የግል ጥላቻ ሌላ ነገር ነው ግን ያለቦታ አትቀላቅል እናም 1000000000000000000 ጊዜ ጃንዮ ጃንሆይ!!!!!!!!

 26. ዘርኣያቆብ ያሬድ
  | #26

  ከፍ ብሎ በቁጥር 21 ኮሜንት ላይ ለመጻፍ የሞከረው ተሳታፊ,እኔን,ጽሁፍህ ሁሉ የገደል ማሚቶ ነው የሚልውንና እንደ ባልፉት 35 አመታት ሙሉ የማውቀውን አይነት መያዣ መጨበጫ የሌለውን ማለሊታዊ ጭንጋፍ እርኩስ “ባህል” ሊጭንብኝ ቃኝቶታል: አንባብያን ይገመግሙ ዘንዳ ይሄው በቅርቡ ከጻፍኩዋቸው ኮሜንቶች ሶስቱን ከዚህ በታች ተራ-በተራ በማከታተል አሰፍራለሁኝ.የገደል ማሚቶ ይመስላሉን?

  1ኛ

  የአፍሪቃ ምርጦች

  ታሪክንና ነጻነት አስመልክቶ:
  1. ሃኒባል
  2. ራእሲ አሉላ
  3. ማንዴላ
  4. ፓትሪስ ሉሙምባ
  .
  .
  .

  እፖርትን አስመልክቶ:
  1. አበበ ቢቂላ
  2. ምሩፅ ይፍጠር
  3. ሃይሌ ገብረስላሴ
  4. ቀነኒሳ በቀለ
  5. ብዙ የሩቅ ሩጫ ተቀላጣፊ ከንያዎች (ይቅርታ ስማቸውን አልያዝኩትም)
  6. ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ኮከብ ሴቶች
  7. አበዲ ፔሌ (የጋና የእግር ኩዋስ ተጫዋች)
  8. ጆርጅ ዌህ (የላይበርያ የእግር ኩዋስ ተጫዋች)
  9. ሳሙኤል ኤቶ(ካመሩን)
  .
  .
  .

  2ኛ
  ዘርኣያቆብ ያሬድ December 31st, 2010 at 11:52 | #20 ይመልሱ | ይጥቀሱ Now i got it! Thank you, ‘Lucy in America’:
  “His another grand daugther [ king hailu shawul's daughter-in law ] has been working for weyanes as key person in their protocol office.”

  ለካስ ያ ሁሉ የኢትዮጵያ ‘ሁቱዎች-ሞቡቱዎች’ መጨባበጥ, መከዳዳትና አሁን ደግሞ እንደገና ተገናኝቶ ለመጨባበጥ ያመች ዘንዳ,ወደ ሊቀመንበርነት ለመመለስ መቸባቸብ ሚስጥሩና ብልሃቱ ሁሉ የሚቀነባበረው እዚሁ “የ’shawul’s daughter-in law” ቢሮ ውስጥ ኖርዋል!! ይሀንን እስከ ዛሬ ድረስ አላወቅኩም ነበር!! በትግርኛ’አነስያ ክምርዖሞ ክሓልፈለይ በለት ዓባይ ጝል’ እንዲሉት አይነት ነገር መሆኑ ነው. ኢትዮጵያ ለካስ በሁለመናሽ ተተብትበሽና ተሳስረሽ ተይዘሻል! ቂቂቂ!!!!ኪኪኪ!!!!!

  3ኛ
  Comment from: Zerayakob Yared [Visitor]
  Thee X [Visitor],

  for your information: 60% of the agazi recruits are SAWA RUN AWAY DEQI HATINOTAT. It is also the same thing with the so called new scholars in AXUM and MEKELLE.

  Fathers were FIRMATORIES by Haileselassie, and sons are by MALELIT “tribalist agazi securitys”, who are Keeping “Ethiopia in darkness .”(your own words)
  If you want more information, ask (the gang of four) Meles, Bereket and (those ‘Rabittas’) Teodros(es), who were sending war-jets on the people of Tigray during the so called election 2010. And i am sure, those Teodroses are from your village, like all the other DEQI HATINOTAT, including the 60% of the agazi recruits SAWA RUN AWAY DEQI HATINOTAT and the new Scholars in AXUM and MEKELLE.

  As i said it many times before, MIKIR LE’HULACHIHUM: WEY EMIYE ETHIOPIA HOY! YIQIR BEYIGN! BILO TTEQLILO METTITO ……, ALEBELEZIAM WEDE DIRSHACHIHU YE’….. ZENDA TTEQLILO MEHED NEW!

  I am tired of this ZELALEMAWI YE’ERGO-ZINBINET. LEMAWENABED YAKIL YE’OROMO TTEBEQA MEMSELUN, ISSAYAS’M TITOTAL!! SILE TIGRAY’M ATITCHENEQ, LELOCH KANTE YEKEFU TTELATOCH ALIWATNA!!

  12/30/10 @ 13:00

 27. the mountain man
  | #27

  December 30th, 2010 at 01:49 | #1

  The following statement is made by some one who called himself/herself as SHEGER
  “Do they know Ethiopian is in this kind of Mess because of the faiure of Haile Selassie to leave his seat which he held mischeiveaously on time? Do they know he was a kind of silet dictator who killed his opponents one by one”

  I do not think Sheger really knows what he is talking about, regarding Emperor Haile Selassie. I can tell you what he did very briefly. The Emperor was a visionary leadership who believed the coexistence of Ethiopians who came from all walks of life A man who put Ethiopia above everything else. A man who worked hard to protect the sovereign integrity of Ethiopia, by modernizing its armed forces ,( the Air Force, the Navy, the Army) as well as the police force. Under the Emperor’s reign soldiers had never been ordered to shoot and kill students and civilians alike in cold blood as we saw in recent years. Under the Emperor many schools were built around the country, and the quality of a given education in all provinces were compatible. A transfer student from other provinces can enroll in any schools in Addis Ababa can easily manage the courses without difficulty. But to day no way under this clear blue sky a transfer student from remote part of Ethiopia can compete with students in Addis Ababa or Mekele.

  The Emperor was a great believer in Education. He opened boarding schools in and around Addis Ababa so students from all walks of life, be it from the north, south, east or western part of the country can come together and learn and assimilate with one another. Having seen English and French were very important subjects , he hired foreign teachers from English and french speaking countries to teach Ethiopian students from elementary to college level. By the way can this person named Sheger tell me if English or French languages are being taught in Ethiopian schools these days beginning at the elementary level. I don’t think so. Does he know that the Ethiopian educational system was under intensive care unit when the Emperor was overthrown, and dead now for good under the current regime.

  when the Emperor ruled over Ethiopia the best and the brightest students were selected from all walks of life and given scholarship opportunities to go to school overseas. Do you know after graduation how those Ethiopian students were eager to go back home and serve their country. Where as nowadays on the contrary no one wants to go back home.

  But these days who actually go overseas for education. Not the best and the brightest any more, but spoiled brats , who do not even know to distinguish between later and letter when writing an essay. They are only being sent because their parents inherited huge sums of money by robbing, killing, begging, and diverging more money from its originally intended use .

  I guess that is quite enough for Sheger to open his eyes and see the Emperor was not a bad person, as he or she claimed on the comment.

 28. the mountain man
  | #28

  I do not think Sheger really knows what he is talking about, regarding Emperor Haile Selassie. I can tell you what he did very briefly. The Emperor was a visionary leadership who believed the coexistence of Ethiopians who came from all walks of life A man who put Ethiopia above everything else. A man who worked hard to protect the sovereign integrity of Ethiopia, by modernizing its armed forces ,( the Air Force, the Navy, the Army) as well as the police force. Under the Emperor’s reign soldiers had never been ordered to shoot and kill students and civilians alike in cold blood as we saw in recent years. Under the Emperor many schools were built around the country, and the quality of a given education in all provinces were compatible. A transfer student from other provinces can enroll in any schools in Addis Ababa can easily manage the courses without difficulty. But to day no way under this clear blue sky a transfer student from remote part of Ethiopia can compete with students in Addis Ababa or Mekele.

  The Emperor was a great believer in Education. He opened boarding schools in and around Addis Ababa so students from all walks of life, be it from the north, south, east or western part of the country can come together and learn and assimilate with one another. Having seen English and French were very important subjects , he hired foreign teachers from English and french speaking countries to teach Ethiopian students from elementary to college level. By the way can this person named Sheger tell me if English or French languages are being taught in Ethiopian schools these days beginning at the elementary level. I don’t think so. Does he know that the Ethiopian educational system was under intensive care unit when the Emperor was overthrown, and dead now for good under the current regime.

  when the Emperor ruled over Ethiopia the best and the brightest students were selected from all walks of life and given scholarship opportunities to go to school overseas. Do you know after graduation how those Ethiopian students were eager to go back home and serve their country. Where as nowadays on the contrary no one wants to go back home.

  But these days who actually go overseas for education. Not the best and the brightest any more, but spoiled brats , who do not even know to distinguish between later and letter when writing an essay. They are only being sent because their parents inherited huge sums of money by robbing, killing, begging, and diverging more money from its originally intended use .

  I guess that is quite enough for Sheger to open his eyes and see the Emperor was not a bad person, as he or she claimed on the comment.

 29. daniel
  | #29

  10 Q THE MOUNTAIN MAN ያለ ምንም ማጋነን እና መቀነስ ለሰጠከው አስተያየትክ ስንት መልካም ነገር አርገዋል ንጉሱ እሳቸው መታማት የሚችሉት በደርግ እና በወያኔ አይደለም. እስቲ ማንም ወላጁን ይጠይቅ? የቱ ስርሃት እንደሚሻል. አንዳንዶቹማ ነፍጠኛ ሲሉ እራሱ እኔ ስለእነሱ በጣም አፍራለው. ወያኔ ነፍጠኛ ሲል ሰምተው እኮ ነው ነፍጠኛ ማለት ከላይ አንድ ሰው እንደገለጸው ባለጊዜ ማለት ነው ይ ማለት ደሞ በወቅቱ ስልጣን ላይ ያለ ገዢ ማለት ነው. አሁን ወያኔ ነፍጠኛ ይባላል ወያኔዎች እራሱ ትርጉሙ አልገባቸውም ቢገባቸው የሚሉት አይመስሉኝም በሰላማኢ ህዝብ ላይ ጥይት ያወረዱ ከነፍጠኛም ነፍጠኛ ማለት እነሱ ናቸው ነፍጣቸውን ብስርሃት እና ያለቦታ የተጠቀሙ ማለት ነው ባጭሩ ነፍጠኛ ማለት ጠመንጃ(ነፍጥ ያነገበ )ይባላል ያሁኑ እና ይደርግ ደሞ ታንከኛ ሊባል ነው ማለት ነው እናም ማስተዋል ይሻላል በንጉሱ ጊዜ የተበደለ የለም ማለት አይደለም ግን ዘርን ታርጌት ያረገ አስፋሪን አጸያፊ ስራ በጭራሽ አልነበረም. ጥቂት የተከፉ ነበሩ በደርግ እጅግ በጣም ሰው ተበድሏል በወያኔጽ ከወያኔ በስተቀር ሙልውን ህዝብ ዳር እስከዳር ተበድልሏል. ከነዚህ ስዎች ጋር በጭራሽ ንጉሱ አይወዳደሩም ወይም እጅግ በጣም ሲበዛ መልካም ናቸው!!!!በተረፈ ሃይሌ ግ/ስላሴ ያለኝ አስተያየት ነፍጥ ይዞ ባይተኩስም የተኮሱትንና የገደሉትን ማልያ የሸለመ የታሪክ አተላ!!!!!!

 30. Lucy in America
  | #30

  Yes, If our comparism is from three messers, So Haileselasie was better than all other odds. But if we compare from all ethiopians who had served and defended his country, we have so more internationally well known hereoes like Colonel Abdiss Aga. Read his biography from one of above posted my comments. Let us not be biased one. what is our ceretierias to give credite? What about atse menilik who defeated the foreign invaders and told the whole black people that you can fight against your colonizers and win and get your freedom? Guys haileselasie was on power over 48 years. he was the first african’s leader who stayed on power longer time and it was relatively peacefull time to build ethiopia.Atse menilik built schools, hotel, tel, rail way and he made the farmers from paying taxes for those who sent their children to school and he charged more taxes for those who refused to send their children. you see how he addressed the use of education and the way he pushed the people to send their children to school?

 31. በረከት
  | #31

  ዘረ ያቆብ የታሪክ ደብተርክን አምጥተክ አንብብ አልተባልክም ለ ራንክ ያህል ነውና እስከ 3ስት መጥቀስ ትችላለክ. ከዛ መዘርዘር ማን አቃተው መስለክ? ሉሲ ደሞ ነገር ማንዛዛት ትወጃለሽ አንዳንዴም የማይገናኝ ነገር ታገናኚያለሽ. ለምሳሌ አብዲሳ አጋ አልሽ. አብዲሳ አጋ በተሰማራበት ቦታ ገዳጁን በጀግንነት የተወጣ ነው ስራው አገር መምራት አልነበረም. መንግስትን ከመንግስት, ዶክተርን ከዶክተር,አስተማሪን ከአስተማሪ,ገበሬን ከገበሬ,አትሌትን ከአትሌት,ተማሪን ከተማሪ አርቲስትን ከአርቲስት ጋር በየፊልዳቸው ነው እንጂ ማወዳደር ያለብሽ,መንግስትን ከዶክተር ጋር አመሳክረሽ ይሀው ዶክተሩ ሰው አዳነ መንግስትስ??? እንደማለት ነው እያልሽ ያልሽው.ትልቅ የተሳሳትሽው ነገር አይለስላሴ ትምህርትን አስፋፍተዋል የሚገርመው ነገር ወጥ ቤት ድረስ ባጃቢዎቻችው እይገቡ ወጥ ቀመስ እያደርጉ ወጥ ብቶችን ይወቅሱ ነበር አጣፍታችው ስሩላቸው እንጂ የጎደለ ነገር አለ እንዴ??? ምንድነው ይህ በደንብ ይሰራ ስጋ በደንብ ይግባ አይቅጠን ብለው አንዳንድ ተማሪ እየተጠራ ይጠየቃል. ከዛም ወጥ ቤቶች ተደናግጠው ልዪ አክብሮትና ለውጥ ነበር የሚያሳዩት . ተማሪ ሲመረቅ ግንባራቸውን በአባታዊ ፍቅር እየተሳሙ ነበር የሚሸለሙት.በጊዜይቸው ሰርተዋል አንድን መንግስት መገምገም የሚቻለው ከዘመኑ ጋር ነው. አሁን በወያኔ ስርሃት ደርግ እንኳን በ 10 ዓመት የሚያገኝው ወያኔ በአንድ ዓመት እንደሚያገኝ ነው ይህው 20 ዓመት ምን ሰራ?? ፎቅ ?? እሱንም የ 97 ምርጫ ውጠት ነው. ያሁሉ ሰልፍ ቅንጅትን ለመደገፍ አገር ሁሉ ግልብጥ ብሎ ሲወጣ ይሁሉ በዓለም ሚድያ ታየ አፈረ መዝረፉን ጋብ አርጎ መንገድ ሰራ. እንዲ ተጠልቻለው ለካ ብሎ ቁጭቱንም በምስኪን ህዝብ ላይ አወረደው. መንገድ ሰራ. ፎቁም ቢሆን ብህዝብ ላብ በጉቦ የተገኝ ነው ፎቁም የወያኔ ነው. ይህ መንግስት እንደሚያገኘ እርዳታ አንድ ከአደገ አገር ጋር በተመሳሰለ ነበር የአህያነቱ ብዛት እስካኡን ስንዴ ይለምናል . ማፈርያ ለማኝ መንግስት እናም ዋዋዋዋዋዋዋዋዋው!!!!!!! ጃንዮ የፍቅር ዘመን, የጥጋብ ዘመን, የአንድነት ዘመን, የደግ እና የለዛ ዘመን,የበረከት ዘመን…. ደርግ አረመኔ ሳያስቡት ሳይጠረጥሩት ከጃቸው ተምሮ ጉድ አረጋቸው ስራ ለሰሪው እሾህ ለአጣሪው ነውና ይሀው የጁን አገኝ. የወያኔ ደሞ የከፋ ነው. ሰው ቢጠፋ ሁሉ ባንዳ እና ሆዳም ቢሆንና ሰው ቢጠፋ የለም ያሉት እግዚሃብሄር መኖሩን ያሳያቸዋል. በተርፈ ሃይለ ገብረስላሴ ያው በውጭ ዓለም ሪክርድ መስበሩን አይተው በስራው መርጠውታል እዝህ ጉዱን አያውቁ. ንጉሱም ደሞ በሰላማዊነታቸው , በዲፕሎማሲያዊነታችው, በአገር ማሳደግ ጥረታቸው, በመልካም አስተዳደራቸው ……. በውጪው ዓለም ይታወቁበት ነው . ትክክል ብለዋል የሃይሌን ግን የውጭ ጀግንነቱን እንጂ የውስጥ ባለጌነቱን አያውቁም . እናም ንጉሱን ከመውቀስ በቅናት የሚቃጥለውን የጥላት ፕሮፓጋንዳን ማመን ሳይሆን በጊዜው የነበሩትን መጠይቅ ዝም ብሎ ከመቀባጠር ያድነናል.

 32. ሱሌይማን
  | #32

  ቴንኪው!!!!!!! በረከት ተባረክ ስለ ገዛ ህሊናችን ,ስለገዛ ማንነታችንስንል, ስልክብራችን ስንል,ስልክራችን ስንል,ስለስማችን ስንል,ከምንም በላይ ውሸት ስለሚጠላው ፈጣርያችን ስንል እውነት መናገር ህሊናን ያሳርፋል ከጥላቻና ከስማ በለው የጸዳ አስተያየት ቢሆን ጥሩ ነበር የንጉስ ሐይለ ስላሴ ዘመን ደሞ እግዜር ካልታረቀን ይህ ዘመን አይመጣም . ወያኔ እንኳን በደርግ ግዜ የመጣ ነው. ሻብያ ደሞ 10 ዓመት ቀደም ብሎ. እናም በጦርነቱ ጊዜ እጅግ ልዝብ ያለ እርምጃና ጦርነት ነበር ሰራዊቱ ሲናደድ እሳቸው ተው ዎንድሞቻችው ላይ እንዲ አታምሩ አለመብሰል ነው ተዋቸው ነበር የሚሉት. የተማረኩ እንኳን በደንብ ተይዘው ነበር የሚሸኙት. ይህን ክራሳቸው የተሰማ ነው .በጣም ነበር ያዝኑላቸው የነበረው. ሁሁሁኡሁኡሁሁ ንጉሱ እጅግ በጣም የሚወደድ ነገር ነበራቸው.ይህዝብ ፍቅር የአገር ፍቅር ህዝባቸውን እንደ ልጅ ነበር የምያዩት ይህው ግፍ አይቀር ደርግ መጣ ጃንዮንን ያልተበደለ ሁሉ ከምጣው ጅብ ጋር አስልፈው ሰጣቸው ይፈለጋሉ ተብለው ሲወሰዱ ይሆነ ቅጠል ነገር በጠስ እያረግ ይጥሉ ነበር ካጀባቸው ወታደር አንዱ ጃንዮ ምን እያረጉ ነው ሲላቸው አይ አዝኛለው ምን አጥፍቼ እንደወንጀለኛ እንዲ የደርግ አጃብዎች እና ከነፈሰው ጋር የሚነፍሱ እይተከተሉ ሲሰድቧቸው እየበጣጠሱ ይዘው የነበረውን ቅጠል ይሆን አበባ ወደ ዋላ ወደ ሚጮሁት በተኑት ምንው ሲባሉ ይህ ትውልድ ምን አርኩት??? ልጄ ባልኩት? በሳሳውለት? ጮማ ባበላው ባስተማርኩት??? እንዲ ያውርዱኝ እንግድያውስ እንደዚህ አበባ ሲረግፉ ይታየኛል አሉ. ነገሬም ያለ አልነበር ከዛ ደርግ ተቆናጠጠ የስንቱ ተማሪና ወጣት ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰ.የጥጋባችን እና የግፋችን ብዛት ይህው የባሰ እንጂ የተሻለ መች መጣ ” አገሬ ኢትዮዽያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርት ይገደለሽ በላ” ተባለላት ወያኔም ትግራይን ሊገነጥል መጣ እድሜ ለደርግ ባለስልጣን ባዶ አገኝ ገቡ ስንቱን ወጣት አረገፉ አገር ገድለው አሁን እውነትኝ ዜጋ በስደት ባንዳ ወያኔ በስርቆት ተያያዛት. ኅይለ ስላሴ ይማሩን እጅግ በጣም የዋህ, አሳቢ, ሩኅሩ, አዛኝ, ሰላማዊ ,የተባረኩ ንጉስ ነበሩ. የማይካድ ሐሰት.

 33. ሱሌይማን
  | #33

  ይቅርታ መጨረሻ ላይ የማይካድ እውነት ተብሎ የነበብልኝ.

 34. Lucy in america
  | #34

  Bereket,No body denied that haileselasie did not do any thing for our ppl and country.But my point is he could do more because he stayed on power over 48 years, there was relatively peace and ethiopiawinet had high momentum after adwa war. And you should know that his regime how treated the poor ethiopian’s farmers. And more over derg and TPLF is the direct result of haileselasie’s repressive regime. If he could transform power to the new generation, derg could not come to menelik’s palace and TPLF could not follow derg.

 35. ይድረስ ለሉሲ(ለኤርትራዊዋ)
  | #35

  ሉሲ በኤርትራዊነትሽ ኪትዮፒያውያኖች የበለጠ መሳተፍሽና መድረክ ማጣበብሽን እናመሰግናለን . ብዙ ግን ባትደክሚ ጥሩ ነው. የማንም ኢትዮፒአዊ ድህና ነገር ስትገልጪ አትታይም ሰው ሁሉን ነገር አላርጂክ ይሆናል እንዴ???? እስቲ ስለእብዱ እሳያስ ስለሚያንገላተቸው እስረኞች ጀባ በይና. የሐይለስላሴ 50 ዓመት መግዛት አሁንም እያቃጠለሽ ነው አስሬ 50 ዓመት ገዙ ትያለሽ. ገበሬውም ጃንዮ ይማሩን እያሉ ነው ምን ይዋጥሽ??? አንቺ አይደለሽም ለኢትዮፕያዊ ገበሬ የምታስቢው. ስለ 50 ዓመት ታሪክ እንደ ዳዊት ከምትደጋግሚ አሁን አስመራ ውስጥ ያለው ገበሬና ህዝብ በድሎት ነዋ!!! ብዙ አስተውዬሽ ነው ይህን ልጽፍ የተገደድኩት ስለማንኛውም ኢትዮፒያዊ ድህና ነገር አንድም ጊዜ ስትጽፊ አልታየሽም ከዚህ በዋላ አፍረሽ የሆነ ነገር ትይ ይሆናል ሰው አልገባውም ማንነትሽ. እናም ብዙ ማለት ያለብሽ ስለኤርትራ ውስጥ ስለሚደርገው ጉድ ነው. ለነገር እኛ እዚህ ስለራሳችን እንጂ ስለማንም ጉዳይ ለመቀበጣጠር ጊዜ የለንም. እናም ፕሊስ ኮሜንት አታብዢ . ያልተረዳሽው ነገር 50 ዓመት መግዛቱ አይደለም ቁም ነገሩ መልካም አስተዳደር እስከሆነ ድረስ ለምን ለዘላለም አይሆንም ህዝብን አክብረው አፍቅረው አገርን ከመበጣጠስ ታግደው በመልካም ስርሃት እስክሆነ ድረስ ማንም አይጠላም. የህው መለስና የናንተው ቀውሱ ኢሳያስ 20 ዓመት ህዝብ ን እያስራቡ እያፈኑ ከነንፍሳቸው ኮንቴይነር እየከተቱ በማያምኑበት ሐይማኖት እያሰገዱ ገንዘብ እያሸሹ …..ብዙ ጉድ እየሰሩ አይደል?? በዓለም ዙርያ በዚህ ሰሃት ኤርትራዊና ኢትዮፒያዊ ነው በስደት አንደኛ ለተቀባይ አገር እስኪሰለቹ እናም አፍ አውጥተው በቃን እስኪሉ እንዳሸን የፈላው ስደተኛ በጃንዮ ጊዘ ነበር??????? እናም ዋናው ዘመን መቅጠር አይደለም .

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።