ማህበረ ቅዱሳን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል የሚሉ ተሃድሶዎች በተስፋ አዲስ

January 8th, 2011 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ክፍል አንድ

ተሐድሶዎች እነማን ናቸው?

ብዙ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ስሄድ የስብከት ካሴት ሳዳምጥ፤ የተለያዩ ሥነ ጽሑፎችን ሳነብ ፡ተሃድሶዎች ተሐድስዎች፡ የሚል ጩኸት እሰማለሁ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሥር የተቋቋመው ማህበረ ቅዱሳን የሚባለው ድርጅት አባላቱም ሆኑ አመራሮቹ ስለተሃድሶዎች በስብከታቸው እና በጽሑፋቸው ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ ሳያነሱ አያልፉም።

እኔም ተሐድሶዎችን ለማወቅ ብዙ ጥረት አድርጌአለሁ ምን ዓይነት አቋም እንዳልቸውና የት ዕንደሚገኙ፤ አላማቸው ምን እንደሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቅ ፈለግሁ እነርሱ ግን ተሃድሶ የሚለውን አይቀበሉትም እኔ ተሃድሶዎች ስል አንባቢ በሚገባው ቋንቋ ለመጠቀም እንዳሰብሁ ይረዳልኝ። ማህበረ ቅዱሳን የሚባለው ማህበርም ከተሐድሶዎች ጋር ያለውን ቅራኔ ለማቅረብ እሞክራለሁ አንባቢ የራሱን ተቃውሞም ሆነ ድጋፍ እንዲሠጥ አንዳችም ሳልቀንስ እና ሳልጨምር ትክክለኛውን መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ። መነሻየ ግን ከማህበረ ቅዱሳን እና ከተሐድሶዎች ሥነ ጽሑፎች ነው። የሁለቱንም ቡድን እንቅሥቃሴ በተከታታይ አቀርባለሁ መልካም ንባብ።

ተሀድሶ ማለት ይላሉ ቤተ ክርስቲያን መታደስ አለባት የሚሉ ወገኖች ማደስ፣ መጠገን፣ ማጽዳት፣ ማለት ነው ይላሉ።ለምሳሌ ቤት ከተሠራ በኋላ ሳይታደስ ብዙ ከቆየ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሊፈርስ ይችላል ስለዚህ ከመፍረሱ በፊት የሚደርግለት እንክብካቤ ቤቱን ያጸናዋል። እንደሸረሪት ድር፤ የጢስ ጠቀርሻ ያሉ ነገሮችም ከቤቱ ላይ ሊጠረጉ ይገባል። ማደስ ማለት ማፍረስ አይደለም በቤቱ ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፤ ማስወገድ እና በፈረሰው በኩል መጠገን ነው በሌላ አነጋገር መሠረቱን ሳይነኩ እና ሳያናውጡ ጥንታዊነቱን እንደያዘ ቤቱን ማሳመር ማለት ነው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም ብዙ ዘመን ከመኖሯ የተነሣ ብዙ ስሕተቶች ይገኙባታልና መጽዳት አላባት ባህሉን ከሃይማኖቱ፤ ውሸቱን ከውነቱ፤ ክፉውን ከደጉ መለየት አለባት የሚል ራእይ ያላቸውና ለዚህ ሌት ተቀን ያለ እረፍት የሚሠሩ ናቸው።

የሚገኙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው ጳጳሳት፤ ቀሳውስት፤ ዲያቆናት፤ መምህራን፤ የድጓ፤ የቅኔ የቅዳሴ መምህራን የሰንበት ተማሪዎች፤ እንዲሁም ምእመናን ሁሉ ያሉበት ነው የታወቀ ማህበር ግን የላቸውም አንዳዶች ማህበር መሥርተዋል። ኑራቸው እና ሥራቸው በዚያው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ሲሆን በተለያየ ቦታ ጽ/ቤት እና በርካታ ማሰልጠኛዎች አሏቸው። በርካታ መነኮሳት እና ሰባኪዎች በነዚህ ቦታዎች ይሰለጥናሉ። ይህን ሁሉ እንቅሥቃሴ የሚያደርጉት ግን ቤተ ክህነቱ ሳይውቅ ነው። ቀሳውስቱ ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ በየቤተክርስቲያናቸው ሌሎች ቀሳውስት በመመልመል ያሰልጥናሉ አንዳድ ጳጳሳትም ለዚሁ ሥራ የሚውል በግላቸው ከፍተኛ እርዳታ ያደርጋሉ። ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ቁልፍ ቦታ አላቸው በተለይ በአሁኑ ሰዓት በየአብያተ ክርስቲያናቱ በብዛት ይገኛሉ። በገጠር አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት ሁሉ አሉ። ደሞዛቸውን የሚያገኙት ከዚያው ከቤተ ክርስቲያኒቱ ነው። ግን ከሌሎች የእምነት ድርጅቶችም እርዳታ ያገኛሉ ተብለው ይታማሉ። ተሐድሶዎች እራሳቸውን ተሃድሶ ብለው አይጠሩም ስማቸው በሥራቸው ምክንያት የተሰጣቸው ነው። በቤተ ክርስቲያን ባሕላዊ ትምህርት ጥልቅ የሆነ ዕውቀት ያላቸው ስለሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሁለንተና ደካማ ጎንም ሆነ ጠንካራ ጎን ለይተው የሚያውቁ ሊቃውንት ናቸው። የተሃድሶዎች እንቅሥቃሴ ከባድ እንቅሥቃሴ ነው ምክንያቱም እስከሞት ድረስ የቆረጡ ሲሆኑ ታላቅ እራዕይ ያላቸው ናቸው።

የተሃድሶ እንቅሥቃሴ በኢትዮጵያ መቼ ተጀመረ?

የተሃድሶ እንቅሥቃሴ በኢትዮጵያ የቆየ ታሪክ አለው። በጣም ጎልቶ የወጣው ግን በአስራ አምስተኛው መቶ[1430] ክፈለ ዘመን ነው። በአሥራ አምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደቂቀ እስጢፋኖስ የሚባሉ ኃይለኛ የሃይማኖት ሰዎች ተነሥተው ነበር እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በዘርዓ ያዕቆብ የሚካሄደውን አምልኮ፤ ባዕድ አምልኮ አለበትና ይህን ሁኔታ አንቀበልም ብለው ለማስወገድ የተነሡ ነበሩ።

አባ እስጢፋኖስ የሚባሉት መነኩሴ በምሥራቅ ትግራይ በአጋሜ አውራጃ ስቡሐ በተባለ አውራጃ የተወለዱ ናቸው። አባታቸው በልጅነታቸው ስለሞቱ አጎታቸው አሳድገዋቸዋል። አባ ስጢፋኖስ በግና ፍየል በሚጠብቅበት ወቅት መንፈሳዊ ስሜት አደረበትና ያደገበትን መንደር ለቆ ቤተ ኢየሱስ በተባለች ሥፋራ መንፈሳዊ ትምህርቱን ጀመረ። ቤተ ሰባቸው ደግሞ ወታደር እንጂ ቄስ እንዲሆንላቸው ስለአልፈለጉ ከሄዱበት አመጧቸው እርሳቸው ግን እንደገና ተመልሰው ለዲቁና የሚያበቃቸውን ትምህርት አጠናቀው በ18 ዓመታቸው ዲቁና ተቀበሉ። አባ ስጢፋኖስ ቤተ ሰባቸው ያወጣላቸው ስም ሀደገ አንበሳ ሲሆን መምህራቸው ግን ትጋታቸውን እና ትህትናቸውን አይተው እስጢፋኖስ ብለው ሰየሟቸው።

ከዚያም እናታቸው እርሳቸውን ለመዳር ስታወጣ ስታወርድ ባለችበት ሰዓት የሚከተለውን ቃል ተናግረው ወደ አባ ሳሙኤል ገዳም ሄደው ምንኩስናን ተቀበሉ። አባ ስጢፋኖስ ለእናታቸው የተናገሩት“ አባቴ በልጅነቴ ስለሞተ እግዚአብሔር አባት እና እናት ሆኖ አሳደገኝ ስለዚህ ሰው ሁሉ ወልዶ ላሳደገው ይገዛል እኔም ከልጅነቴ ጀምሮ ወልዶ ላሳደገኝ ለእግዚአብሔር እራሴን ማስገዛት ስለምፈልግ ከዛሬ ጀምሮ እኔን ማየት አትችይም እራስሽን ለእግዚአብሔር አስገዢ በሰላም ኑሪ” የሚል ነበር።[ ከገድለ እስጢፋኖስ]

አባ ስጢፋኖስ ብሉያትን እና ሐዲሳትን ከተማሩ በኋላ ነገሮችን ሁሉ ማስተዋል ጀመሩ መምህሩንም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት “ ሃይማኖት መጻሕፍት እንደሚናገሩት ነው? ወይስ እደ ሰው ልማድ” የሚል ነበር። መምህሩም ሃይማኖትማ መጻሕፍት እንደሚሉት ነው ብለው ሲመሉስላቸው ታዲያ ይህ ሃይማኖት የሚመስል የሰው ልማድ ከሄት መጣ ብለው ሲጠይቁ ይህማ ከራሱ ከሰው የመጣ ነው ብለው መለሱላቸው። ከዚህ በኋላ አባ ስጢፋኖስ የእግዚአብሔርን ቃል ከሰው ልማድ እየለዩ ውሸቱን ከእውነቱ እያበጠሩ በማስተማር የራሳቸውን ደቀመዛሙርት ለብቻ ማደራጀት ጀመሩ ያስተማሯቸው ደቀ መዛሙርት በራሳቸው ወዝ ሠርተው እንዲበሉ እንጂ ከሰው እንዳይቀበሉ ሥራ እያስተማሯቸው አትክልት እና ፍራፍሬ በማልማት ከራሳቸው አልፈው ለሌላው ህዝብ መትረፍ ጀምረው ነበር።

በዚህ ጊዜ የራሳቸው ጓደኞች መነኮሳት ትምህርታቸው ከእኛ የተለየ ነው፤ ልማዳቸውም የኛን የሚቃወም ነው በማለት ይከሷቸው ጀመር።ይህንም ክስ በዘመናቸው ንጉሥ ለነበረው ለዘርዓ ያዕቆብ አቅርበውት ነበር። ዘርዓ ያዕቆብ ከአጼ ዳዊት ቀጥሎ የነገሠ ሲሆን በልጅነቱ ግሸን ላይ ታሥሮ እንደኖረ ይነገርለታል ከዚያም ወደ ገዳም ገብቶ ከመነኮሰ በኋላ ምንኩስናውን ትቶ አግብቶ የነገሠ ሰው ነው።

ንጉሡ የተማረ ሰው ስለነበር ድርሰት መድረስ ዋና ሥራው ነበር። ከደረሳቸው ድርሰቶች ውስጥ ታምረ ማርያም እና መጽሐፈ ብርሃን፤ የታወቁት ናቸው ማህሌተ ጽጌ እና መጽሐፈ ሰዓታት በርሱ ዘመን የተደረሱ ድርሰቶች ናቸው። በኢትዮጵያ በ30ው ቀናት ውስጥ በርካታ በዓላት እንዲከበሩ አዋጅ ያወጀው አፄ ዘራዓ ያዕቆብ ነው የእመቤታችን 33 በዓላት እንደ እሑድ ሰንበት እንዲከበሩ፤ የመስቀል በዓል ብሔራዊ በአል ሆኖ እንዲከበር እና ስለ መስቀል ክብር የሚናገሩ ድርሰቶች እንዲደረሱ ያደረገው ዘርዓ ያዕቆብ ነው።

ለማርያም ስእል እና ለመስቀል[ለመስቀለኛ እንጨት] ስግደት እንዲደረግ አዋጅ ያወጣው ዘራዓ ያዕቆብ ነው። አንድ ቀን ዘራዓ ያዕቆብ ታምረ ማርያምን ጽፎ ከአባ እስጢፋኖስ ገዳም በየሳምንቱ እሁድ እሁድ እንዲነበብ ከሚል ጥብቅ ትእዛዝ ጋር ይልከዋል። አባ እስጢፋኖስም መጽሐፉን በጥንቃቄ ካነበቡት በኋላ ይህ መጽሐፍ ከገዳማችን አይገባም መጸሐፉ ደቀ መዣሙረቴን የሚያሰንፍ ነው። ድንግል ማርያምንም አያከብርም በማርያም ስም የተነገረ ባዕድ ትምህርት ነውና አልቀበለውም ብለው መልሰው ላኩለት።

በዚህ ጊዜ ዘርዓ ያዕቆብ በመጀመሪያ ይሰማው ከነበረው ክስ ጋር የሚመሳሰል ነገር አገኘና እጅግ ተቆጥቶ እስጢፋኖስን አስጠራቸው። ደብረ ብርሃን ላይ ትልቅ ጉባኤ ተደረገ ሊቃውንት ምእመናን እና መነኮሳት ከየገዳሙ ተሰበሰቡ። አባስጢፋኖስ እና ደቀ መዛሙርቱ በአንድ በኩል ተቃዋሚዎች እና አፄ ዘራአ ያዕቆብ በሌላ በኩል ቆመው ክርክር ተደረገ።

አፄ ዘራዓ ያዕቆብ እና ተከታዮቹ የሚሉት፦

ለማርያም እና ለሥእሏ ስገዱ

ለመስቀል[ለመስቀለኛ እንጨት] ስገዱ

ለእኔም ለንጉሡ ስገዱ

ታምረ ማርያምን ተቀበሉ ነው

አባ እስጢፋኖስ እና ደቀመዛሙርቱ የሚሉት፦

“ኢንሰግድ ለባዕድ ዘእንበለ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ” ትርጉም ለአብ ለወልድ እና ለምንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር ለአራተኛ አካል አንሰግድም።

የሰው እጅ ለሠራው ለስእልም ሆነ ለመስቀለኛ እንጨት ባዕድ አምልኮ ስለሆነ አንሰግድም አሉ። በዚህ ጊዜ አባ እስጢፋኖስ ከባድ ግርፋት ከደረሰባቸው በኋላ ታስረው በነበረበት ቤት አረፉ።ደቀ መዛሙርቱም ለብቻ እምነታቸውን ቢጠየቁ አባታችን ካስተማረን ንቅንቅ አንልም አሉ። እጅግ ከተገረፉ በኋላ እስከ አንገታቸው የሚደርስ ጉድጓድ ተቆፍሮ በዚያ ገብተው ፈረስ እና ከብት በጭንቅላታቸው ላይ ተነዳባቸው። ይህን ታሪክ በታምረ ማርያም ም 12 ላይ እና በግድለ እስጢፋኖስ ማግኘት ይቻላል። በተለይም ፕሮፌሰር ጌታቸው በሕግ አምላክ በሚል እርስ የደቂቀ ስጢፋኖስን ገድል ስለ ተረጎሙት እርሱን በማንበብ በቂ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

ሌሎች ተደብቀው የቀሩት ያአባ እስጢፋኖስ ደቀ መዛሙርት ከያሉበት እየተፈለጉ እጅ እና እግራቸውን ተቆረጡ፤ አፍንጫቸውን ተፎነኑ፤ ሴቶች ማህጸናቸውን በእሳት ተጠበሱ። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በፕሮፌሰር ጌታቸው መጽሐፍ ላይ በሰጡት አስተያየት በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ የተፈጸመውን ግፍ ሂትለር በአይሁድ ላይ ከፈጸመው ግፍ ጋር አመሳስለውታል።

ደቂቀ እስጢፋኖስ ደቅ እና ቆራጣ የሚባል በጣና ደሴት አካባቢ መታሰቢያ አላቸው በትግራይ ደግሞ ጉንዳጉዴ የሚባል ገዳም አላቸው ይህ ገዳም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚተዳደር ሲሆን ታምረ ማርያም ግን እስከ አሁን ድረስ አይነበብበትም።

ደቂቀ እስጢፋኖስ በቤተ ክርስቲያኒቱ እስከ አሁን ድረስ እንደ መናፍቅ የሚወገዙ ሲሆን ምሥጢሩን የሚያውቁ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰዎች ግን እንደ ሰማእታት እና እንደ ቅዱሳን ይቆጥሩአቸዋል።

ይህ የነ አባ እስጢፋኖስ እንቅሥቃሴ በጊዜው በነበረው የፖለቲካ የበላይነት ተዳፍኖ ቢቆይም ውስጥ ውስጡን ግን ሲሄድ እና ቀስ ብሎ ሲጓዝ የኖረ እንቅሥቃሴ ነው። ይህን ውስጣዊ እንቅሥቃሴ በርካታ ሊቃውንት በሥዉር ሲሳተፉበት ኖረዋል። ለምሳሌ ከነዚህ ሊቃውንት ውስጥ ጥቂቶች ከመጻሕፍቶቻቸው መረዳት እንደሚቻለው አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ አለቃ ታዬ፤ አለቃ ብላቴን ጌታ ሕሩይ፤ ፤ አለቃ ገብሩ ደስታ፤ ዘመንፈስ፤ የሚባሉ ሊቃውንት ሲሆኑ በደንብ ወደ አደባባይ ካወጡት እና ከቤተ ክርስቲያን ከተገለሉት የቅርብ ሊቃውንት ውስጥ አለቃ መሠረት ስብሐት ለአብ እና ጓደኞቻቸው ይገኙባቸዋል። የአለቃ መሠረት ስብሐት ለአብ ጓደኞች አሁንም በሕይወት ስለአሉ ስማቸውን መጽሐፍ አልፈለግሁም እነርሱም ስማቸው እንዲወጣ አይፈልጉም ዛሬም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በተለያዩ ሥራዎች ተመድበው ይገኛሉ። ከላይ ስማቸውን የጠቅስኋቸው ሰዎች የአባ እስጢፋኖስ ሐሳብ ነበራቸው። ይህን ለማለት ያስቻለኝ አሁን ያሉት ቤተ ክርስቲያን መታደስ አለባት የሚሉት ወገኖች ከሚያራምዱት አላማ ጋር መጻሕፍቶቻቸውን በማስታያየት እና የሕይወት ታሪካቸውን በማገናዘብ ነው።

የታሐድሶዎች ዓላማ ምንድን ነው?

ተሐድሶዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሻሻል አለባት ይላሉ። ራእያቸውም ቤተ ክርስቲያኒቱ በሐዋርያት እምነት ላይ የተመሠረተች በመሆኗ፤ የሐዋርያትን ትምህርት መከተል አለባት። አሁን የሚታዩት የሕዝብ ልማዶች እንደ ሃይማኖት ሆነው የሚታዩት ከዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ጀምረው በኃይል እና በፖለቲካ የበላይነት የተጫኑብን እንጂ እውነተኛው እና ጥንታዊው የኦርቶዶክስ እምነት አይደለም ባይ ናቸው። እውነተኛውን ኦርቶዶክሳዊ ትውፊትንም ሆነ እምነትን የሸፈነ ልማድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አለ። ይህን ቀስ በቀስ ሕዝብን በማስተማር መሰረቱን ሳያፈርሱ ውሸት የሆነውን ሁሉ እናስወግዳለን የሚል ራእይ አላቸው።

ተሐድሶ እንዲደረግ የሚፈልጉትም፦

1ኛ በአምልኮው ላይ 2ኛ በመጻሕፍቱ ላይ 3ኛ በአስተዳደሩ ላይ ተሐድሶ እንዲደረግ ይፈልጋሉ ለዚህም መጻሕፍቶቻቸውን ማንበብ ይቻላል በርካታ መጻሕፍት አሏቸው። በገድላት፣ በድርሳነ ሚካኤል እና በድርሳነ ገብርኤል በድርሳነ ኡራኤልም ላይ በጠቅላላ በድርሳንቱ እና በግድላቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ትችታቸውን ጽፈዋል ወደ ፊት እናቀርበዋለን።

በአስተዳድር ላይ የሚያነሱት ጥያቄ ከማህብረ ቅዱሳን ጋር ተመሳሳይ ነው። አስተዳደሩ መንፈሳዊ ካልሆኑ ሰዎች ተላቆ በተማሩ እና ፈሪሃ እግዚአብሔር ባላቸው ሰዎች ይመራ ባይ ናቸው በአስተዳደሩ የሚፈጸሙ የዘረኝነት እና የሙስና አሠራርን አጥብቀው የሚቃወሙ ሲሆን በየቤተ ክርስቲያኑ በበዓል ቀን መንፈሳዊ ያልሆነ አሠራር እይተስፋፋ ነው ይህም የንግድ ሥራ እንጂ የእምነት ሥራ አይደለም በማለት አጥብቀው ይቃወማሉ። ጠንቋዮች በቤተ ክርስቲያኒቱ መታቀፍ የለባቸውም ጠንቋይ የሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ባዕድ አምልኮን በማስፋፋት ትልቁን ሚና እየተጫወቱ ስለሚገኙ ይወገዱልን ባይ ናቸው በዚህ እረገድ ማህበረ ቅዱሳንም ጠንካራ አቋም አለው። የቀረውን የእንቅሥቃሴያቸውን ታሪክ በሚቀጥለው አቀርባለሁ። ከኔ የቀረውን አንባቢ ቢያስተካክለው ድስ ይለኛል።

ክፍል ሁለት

ማህበረ ቅዱሳን

ማህበረ ቅዱሳን በደርግ ዘመን ለውትድርና እንዲሰለጥኑ በተመለመሉ የዩንበርስቲ ተማሪዎች ብላቴን ላይ የተመሰረተ ማህበር ነው ይላሉ። ማህበሩ በተለያዩ የጻድቃን እና የቅዱሳን ስም በየአካባቢው የጽዋ ማህበር ሆኖ የቆየ ሲሆን ሁሉም ማህበራት ዝዋይ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ዘንድ እየተሰበሰቡ ይማሩ ነበር። ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በሞቱ በዓመቱ የተለያዩ የጽዋዕ ማህበራት አባላት ሙት ዐመት ለማሰብ ተሰበሰቡ ከተሰበሰቡት አንዱ የስማቸው መታሰቢያ የሚሆን ማህበር እናቋቁም የሚል ሐሳብ ሲያመጣ ሁሉም የማህበራት አባላት በነገሩ ይስማማሉ። ነገር ግን ስም አወጣጡ ላይ አልተስማሙም ነበር አንዱ ማህበረ ማርያም፤ አንዱ ማህበረ ተክለ ሃይማኖት፤ አንዱ ማህበረ ጊዮርጊስ፤ ሌላው ማህበረ ሚካኤል ወዘተ በማለት ሲከራከሩ፤ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ሁላችሁም በቅዱሳን ስም ነው የተመሰረታችሁት ለምን ሁሉንም ትተን “ማህበረ ቅዱሳን አንለውም” አሉ። ሁሉም ማህበራት በዚህ ተስማምተው ጸሐፊ እና ሊቀ መንበር መርጠው መሥራት ጀመሩ።

አባላቱ በብዛት የዩንበርስቲ ተማሪዎች ሲሆኑ በዘመናዊ ሙያ የበለጸጉ ዶክቶሮች፤ ሎዌሮች፤ ኢንጅነሮች፤ የተሰበሰቡበት ማህበር ነው። ከቤተ ክርስቲያን ባለሙያዎችም ጳጳሳት፤ ቀሳውስት፤ መምህራን፤ ዲያቆናት፤ በአባልነት አሉበት።በአባላት ብዛት፤ በአደረጃጀት፤ በኢኮኖሚ አቅም፤ የሚወዳደራቸው የለም።

ማህበሩ በተለያዩ ሀገሮች እና ከተማዎች ታላላቅ የንግድ ማዕከላት አሉት እያንዳዱ አባል አሥራቱን ለማህበረ ቅዱሳን ዋና ማዕከል ይክፍላል፤ የራሱ ሊቃውንት ጉባኤ፤ የልማት ክፍል፤ የትምህርት ክፍል፤ የራሱ ጽሕፈት ቤት፤ በየሀገረ ስብከቱ የራሱ ማዕከል አለው።

የማህብረ ቅዱሳን አባላት በዘመናዊ ትምህርት እንጂ በመንፈሳዊ እውቀት ብዙ የሚመሰገኑ አይደሉም። ነገር ግን ከማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን በብዙ ይሻላሉ። በቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ እውቀት በኩል ከተሃድሶዎች ጋር ሲወዳደሩ የሰማይና እና የምድር ያክል ይራራቃሉ። ነገር ግን ለባህል ፤ ለቅርስ፤ እንዲሁም ለሀገራቸው እና ለአባቶች ወግ ያላቸው ቅናት ከፍተኛ ነው። ማንኛውም የማህበረ ቅዱሳን አባል ሥልጠናውን ከጨረሰ በኋላ ሦስት ዓይነት ከለር ያለው ክር ባንገቱ እንዲያደርግ ይሰጠዋል የማህበረ ቅዱሳን አባል መሆኑ የሚታወቀው በዚህ ነው። ይህን ሁኔታ የተመለከቱ ሰዎች ወደፊት ማህበረ ቅዱሳን የራሱን ቤተ ክርስቲያን መመሥረቱ የማይቀር ነው ይላሉ።

በአምልኮ ወደ ነፍሳት፤ ወደ መላእክት፤ መጸለይን፤ ለቅዱሳን እና ለመላእክት ሥእል መስገድን አጥብቀው ያስተምራሉ፤ ይጽፋሉ። በመጻሕፍተ አዋልድ አንዳድ ስሕተቶች እንዳሉባቸው ቢያምኑም ይህን ማሻሻል ያለበት ሲኖዶስ እንጂ እኛ አይደለንም ይላሉ። ይህን የሚሉት ጥቂት የማህበረ ቅዱሳን መሪዎች እንጂ ሌሎች ተራ አባላቶች ምንም ስሕተት የለባቸውም ብለው የሚያምኑ ናቸው።

ማህበሩ ዓላማ

ቤተ ክርስቲያንን በሙያቸው በነጻ ማገልገል፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪክ በተለያዩ መንገዶች ለምሳሌ በኢግዚብሽን ማስተዋወቅ፤ ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት ወጣቱ በቤተ ክርስቲያን እንዲታቀፍ ሥልጠና መስጠት የሚል ነው። በመንግሥት ውስጥ ታላቅ ቦታ አላቸው እስከ አምባሳደር የደረሱ የማህበረ ቅዱሳን አባላት አሉ። በሥራቸው ትጉህ ናቸው፤ በገዳማት እና በተለያዩ ያሉ መምህራንን የገንዘብ እርዳታ ለመስጠት ጥረት ያደርጋሉ የአብነት ትምህርት ቤቶችን እንደገና በዘመናዊ መልክ ለማደራጀት ይታገላሉ፤

ሌላም ከዚህ ያለፈ ዓላማ እንዳለው ይታማል።

ማህበሩ የሚታማባቸው ዋና ዋና ነገሮች

የማህበሩ መሪ የነበረው — አንዱ ሰው ናዝሬት ላይ በሰይጣናዊ አሠራር ሰው ሊገድል ሲል በፖሊስ ተይዞ በመታሠሩ በማህበሩ ላይ ጥላ አጥልቶበት ነበር። ይህ ሁኔታ እስከ አሁን ድረስ ማህበሩን ጥያቄ ላይ የጣለው ነገር ነው። የማህበሩ መሪ ማርያም መሥዋዕት አቅርቡልኝ ስላለች አንድ ሰው ታንቆ መሞት አለበት በማለት አንዲትን ሴት አሳምኖ ኖሯል በገመድ ተንጠልጥላ በመንፈራገጥ ላይ እያለች ፖሊስ ደርሶ ከሞት አትርፏታል።

ይህ ድርጊት በፖሊስ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ተሌቭዥን በተከታታይ ሲቀርብ ነበር። ታሪኩ በመጽሐፍም ተጽፎ ይገኛል። በኋላ ግን ማህበሩ እንደምንም ብሎ ስሙን አደሰ መንፈሳዊ ዝግጅት እያዘጋጀ መንፈሳዊ ጉዞዎችን እያደረገ አባላትን መስብሰብ ጀመረ። ይህን እንቅሥቃሴ በትኩረት የተመለከቱ አቡነ ቴዎፍሎስን ያስገደለው የታላጉ ጉባኤ አባላት ትኩረታቸውን ማህበረ ቅዱሳን አባላት ላይ በማድረግ ስድስት ኪሎ በሚገኘው ምስካየ ሕዙናን መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ግቢ እየነጠሉ በመሰብሰብ አላማቸውን አስቀይረዋቸዋል ይባላል። ማህበሩ የታላቁ ጉባኤ አባላት ከገቡበት ጀምሮ አቡነ ጎርጎርዮስን ለማሰብና ቤተ ክርስቲያንን ለመርዳት የነበረውን አላማውን ትቶታል የሚሉ አሉ።

ከተመሠረተ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ለምሳሌ ሃይማኖተ አበውን ለማፈርስ ያደረገው እንቅሳቃሴ እና ለአባላቱም የሚሰጠው ስልጠና በዋናነት “የመናፍቃን ምላሽ” የሚል ሆነ። በጽሑፉም ሃይማኖተ አበውን የሚያጥላላ ጽሑፍ እያሠራጨ ቆይቶ በደንብ ከተዘጋጀ እና እውቅና ካገኘ በኋላ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ቡድን በማደራጀት የሃይማኖተ አበውን አባላት እና ተሃድሶ ናቸው ያላቸውን ሁሉ በመደባደብ በማሳደዱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከ60 ሺህ በላይ አባላቷን አጥታለች እይተባለ ይተቻል።

ሌላው ማህበሩ የሚታማበት ነገር ብዙ የሚያጠራጥር ነው በመጀምሪያ ቤተ ክህነቱን መቆጣጠር ሲሆን ቤተ መንግሥቱንም ማለፍ አይፈልግም ይባላል። የታላቁ ጉባኤ አባላት እንደ የበላይ ጠባቂ ሁነው የማህበሩ አማካሪ ናቸው፤ ማህበሩ አካሄዱን እንዲያሳምር ያደረጉት እኒህ የታላቁ ጉባኤ አባላት ናቸው አንዳዶች የሞቱ ሲሆን የተወሰኑት አሉ።[በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚዘጋጀው ጋዜጣ ዜና ቤተ ክርስቲያን እንደዘገበው]።

ማህበረ ቅዱሳን ምሥጢራዊ የሆነ የሥለላ ቡድን አለው ይህ የስለላ ቡድን በዋነኛነት የሚሰልለው ተሃድሶ እና ተቃዋሚዎቼ የሚላቸውን ነው ተቃዋሚዎቹን ሁሉ ተሃድሶ ይላቸዋል ነገር ግን ብዙዎቹ በከንቱ ነው ስማቸው የጠፋው ይባላል። ከዚህ በተረፈ ጳጳሳትን፣ ካህናትን፣ መነኮሳትን፣ ዲያቆናትን ኑሮአቸውን ሕይወታቸውን ይሰልላል የእያንዳዱ ጳጳስና መነኩሴ የሕይወት ታሪክ፤ በቴፕ እና በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ ይሰበስባል። ባማህበረ ቅዱሳን ላይ ያመጸ አገልጋይ ቢኖር ይህ መረጃ ይሰጠውና አፉን እንዲይዝ ይደረጋል።

እያንዳዱ የደብር ጸሐፊ እና አስተዳዳሪ ሒሳብ ሹም፣ ቁጥጥር፣ ገንዘብ ያዥ፤ ሰባኪ፤ ወዘተ በሙሉ በማህበረ ቅዱሳን የመረጃ መረብ ውስጥ የገባ ነው። ከማህበረ ቅዱሳን ማምለጥ የማይቻል ነው። ሆኖም ተሃድሶዎችን ግን አልቻሏቸውም ከማህበረ ቅዱሳን አቅም በላይ የሆኑ ቢኖሩ ተሃድሶዎች ብቻ ናቸው። ምክንያቱም ተሃድሶዎች እጅግ በጣም ቁጥብ በሙስና የማይገኙ ከመሆኑም በላይ ሥራቸውንም በዝግታ ስለሚያካሂዱት ውስጥ ለውስጥ የሚቀጣጠሉ እና የተዳፈኑ እሳቶች ናቸው። አሁን አሁን ማህበረ ቅዱሳን እንደተሃድሶዎች ሆኖ ተሃድሶውችን እየሰለለ ቢሆንም ተሀድሶዎችም በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ በስፋት ገብተው አንዳድ ማዕከላትን ተቆጣጥረው ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት የተሃድሶዎች እና የማህበረ ቅዱሳን ሁኔታ አሳሳቢ ነው ነገሩ እየከረረ መጥቷል። ይህ ሁኔታ በቶሎ በሲኖዶሱ ሊፈታ ይገባል በማለት አስተያየታቸውን የሚሰጡ ብዙዎች ናቸው።

ክፍል ሦስት

በክፍል ሦስት የምናያቸው ደግሞ መሃል ሰፋሪ አገልጋዮችን ነው። እነዚህ መሃል ሰፋሪ አገልጋዮች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ እውቅና ያላቸው መድረኩን ተቆጣጥረው የሚኖሩ፤ ዋና ዋና የገንዘብ ቦታዎች ላይ የተቀመጡ ጸሐፊዎች ሒሳብ ሹም ገንዘብ ያዥ፤ አስተዳዳሪዎች ናቸው። ማህበረ ቅዱሳንንም ሆነ ተሃድሶዎችን ይቃወማሉ የሚቃወሙትም ከጥቅማቸው የተነሣ እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ስለተቆረቆሩ አይደለም።

እነዚህ ክፍሎች ምንም ዓይነት እራይ የላቸውም ማህበረ ቅዱሳን ወይም ተሃድሶ አይደሉም። ነገር ግን ጥቅም ካገኙ የማንኛውም ጥገኛ ሊሆኑ ይችላሉ የሚያስቡት ለሆዳቸው ብቻ ነው አንዳዶች የፖለቲካ [የኢሀዴግ] ጥገኞች ናቸው በዚም ጥገኛ የሆኑት የኢሃዴግ አላማ ግበቷቸው ሳይሆን ጥቅም ስለአገኙ ብቻ ነው። እነዚህ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኘውን ጥቅም አግበስብሰው ዘወር ለማለት የሚሠሩ ደሞዝተኛ ናቸው። በቤተ ክርስቲያን የሚደረገውን ማንኛውንም መንፈሳዊ ነገር አያምኑበትም እራሳቸውን እንደ ሠራተኛ ስለሚመለከቱት መንፈሳዊ ነገር ጉዳይ አይሰጣቸውም።

በዝማሬ እና በስብከት ካሴት የሚታወቁ አንዳድ ሰዎችም ከዚህ ጎራ የሚመደቡ ናቸው። ስብከታቸውም ሆነ ዝማሬያቸው የሰውን ስሜት በመኮርኮር ብዙ ገንዘብ ለማግኘት የታሰበ እንጂ በሊቃውንት የተመረመረ እግዚአብሔርን ለማክበር የታሰበ አይደለም። እነዚህ ሰዎች ሕዝብ በብዛት ለሚወደው ጻድቅ፤ ቦታም ሆነ ታሪክ ይዘምራሉ ይህ ገንዘብ የሚያገኙበት ዘዴ ነው። እነዚህ ወገኖች ምንም ዓይነት እራዕይም ሆነ አላማ ፈጽሞ የላቸውም የሕዝቡን ልብ እና አእምሮ ቆልፈው የያዙት ግን እነዚህ ወገኖች ናቸው። በስብከታቸው ነቀፋ እና ስድብን ስለሚያበዙ፤ በተዛዋሪ ሕዝብ መናገር የሚፈራውን የልቡን ብሶት በአደባባይ ያለምንም ሐፍረት ስለሚናገሩ በቃላሉ እውቅና ያገኙ ናቸው አስተዋይ ሲመዝናቸው ግን እውቀትም ሆነ መንፈሳዊ ሕይወት የላቸውም እግዚአብሔርንም አይፈሩም። በነዚህም ላይ ጽሑፎችን እናቀርባለን! የኢትዮጵያ ሕዝብ ከነዚህ ውዥንብር ፈጣሪዎች ዘወር ብሎ፡ ማህበረ ቅዱሳንን እና ቤተ ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል የሚሉ ሰዎችን ማዳመጥ አለበት እነዚህ ወገኖች ባለራእይ ናቸው።

መልካም የውይይት ጊዜ ይሁንልን!

 1. አንድነት
  | #1

  እምዬ ምኒሊክ የፋሽስቱን ጠላት የጣሊያንንን ጦር ሲያርበደብዱ ጦርነቱን በማግስቱ ጦርነቱን ሊያደርጉ ሌሊቱን አድዋ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እንዲቀመጥ ባደረጉት ጽላት ፊት ቅዳሴ አድርገው ስለእምነታቸው ፈጣሪ ረድቷቸውና በዚያን ጊዜም የነበሩት ካህናት ስለሃገር አንድነትም ይሁን ነጻነት የሚገነዘቡ ሆነው ሳለ የአሁኖቹ ከነፍሳቸው ይልቅ ለአለም ሕይወታቸው ባማስቀደም ወያኔዎችን በዝምታ ማቀፋቸው ይገርማል::
  ሃገርህን የማታድን ውጉዝ ነህ ማለት ቀርቶ ወንጌሉን ሽፋን በማድረግ…..

 2. Saba
  | #2

  I read this article yesterday and there wasn’t any comment at the time. It is good that at least somethings needs a debate. On the other hand, I would ask Ato Tesfa Addis to write his true identity. People who believe have truth to their side, should state who they are. One recent example of writing clearly supported by facts is Kesis Asteraye Tsige. Those who comment or jot down a barrage of attack would not help.

  If Ato Tesfa does not disclose who he is, he might Woyane who has launched enormous campaign on EOTC particular in the Diaspora. The reason why I am saying this is because there are havoc in London, Dallas, Denver, in Kansas etc.

 3. ሰላም
  | #3

  የተከበሩ የአቡጊዳ ኢዲተር:

  ከዚህ በላይ እንደ ኢትዮጵያዊ ያሉ አስተያየት ሰጭዎች ይህን የመሰለ ያገር ጉዳይ አጀንዳ ban እንድታደርጉ ያቀረቡትን ሃሳብ እቃወማለሁ:: ይህ ማለት በዚች አብዛኞቻችንን ባሳደገችና የፖለቲካ መሳሪያ በመሆን ጌታን እያሰደበች ባለች ‘ቤተ ክርስቲያናችን’ ውስጥ በእነዚህ በተጠቀሱት ሁለት ወገኖች/ቡድኖች መካከል እየሆነ ያለውን እንቅስቃሴ ሕዝቡ በግልጽ እንዳያውቀውና የሚጠቅመውን እውነት እንዳይዝ ተዳፍኖ ይቅር ማለት ነው:: በሌላ መንገድ ደግሞ ይህ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት/እኔን ጨምሮ የሌለው ሕዝብ እንዲደናገርና አስፈላጊ ላልሆነ መጠላላት/መጨፋጨፍ እንዲዳረግ ከመሻት የተነሳ የተሰነዘረ አስተያየት ይመስላልና የኢትዮጵያዊን ባን የማድረግ ሃሳብ ማስተናገድ ያለባችሁ አይመስለኝም:: በእርግጥ ለሁላችንም የጋራ ችግር መፍትሄ ሊሆን የማይችል ስድብና ዘለፋ የሆነውን በንጽሑ አእምሮአችሁና ሙያዊ ግዴታችሁ ሳትወግኑ ገለባውን ለነፋስ ብትሰጡት የደንበኞቻችሁን ብዛትና ጥራት ያሳድግላችሁአል::

  ከዚህ በተረፈ የእነዚህን ሁለት ተፋላሚዎች ማንነት የከዚህ በፊትና ያሁኑ ሥራቸው ፍሬ ደህና አድርጎ ስለሚገልጻቸው ሁላችንም እያንዳንዱን ለይቶ ለማወቅ ብዙም የምንቸገር አይመስለኝም
  ይህ ሃሳብ ለሃሳብ የመፋጨታችን ሁኔታ ግን የበለጠ የሚጠቅመው:-
  1) ያለ እውቀት በጭፍን ስሜት ተነድቶ አባል ለሆነ ቆም ብሎ እንዲያስብ ያነቃዋል
  2) ሁለቱ ‘አንበሶች’ ሲፋተጉ ሳሩ ጉዳት እንዳይደርስበት ለመከላከል ይጠቅማል
  3) ያለ ወንጌልና ያለ ክርስቶስ ኢየሱስ ክርስቲያን ተብለን የተጠራን እንድናስተውል ይረዳናል
  4) ጥላቻ ቂም በቀልና እንዲሁም በለው ያዘው ልቀቀው አሳደው ግደለው የሰይጣን ሥር መሆኑን
  5) የምድራችን ዘርፈ ብዙ ችግር ዋና ምንጩ መንፈሳዊ መሆኑን እንድንገነዘብ ያደርገናል
  6) ይችን ባለቤት ያጣችና ከባልዋ የተፋታች ቤ/ክ የቃሉና የመንፈሱ ለማድረግ ያስችላል
  7) በጎ የሆነውን በእውነት የመከባበርና የመተሳሰብ ባህላችንን እናሳድጋለን/ ስድብን ትተን

  ስለዚህ ወገኖች ይህ ጉዳይ ያገር ጉዳይ ነውና እንደ ቀላል ነገር ባናየው መልካም ነው:: ሌባውን ከታማኙ የምንለይበትና የሚጠቅመንን ይዘን የምንጉአዝብት መልካም የመለየት መድረክ ነውና ልባችሁን አስፍታችሁ አወያዩን::

  ”ይህን ብታውቁ ብታደርጉትም ብፁአን ናችሁ” (ዮሐ 13:17)

  ሰላም ይብዛላችሁ

  ሰላም ነኝ

 4. meta
  | #4

  ሰላም
  I checked your IP address, you are the writer of this article. Do not lie

 5. ያእኮብ
  | #5

  Dear All,

  Doctrinal conflict is not a new thing to EOTC. We had a lot of problems in previous times. As recently as the rein of Atse Yohannes, we had seious splits in the church and Emperor Yohannes had to call for a debate between the Tewahedo and the opponent group in a public place where the former won the debate while the latter had to get a deserved punishment. I also believe in a spirited discourse instead of propagating rumors and backdoor dealings. So, the Tehadso group should make itelf public and its agenda clear and the MK group should be willing to partake in such discoures if they truely care for the church. It is amazing that our forefathers were more strategic, tactful and visionary than us, the so-called current generation. Constant accusation can only benefit those who gain from raising the dust and creating confusions and animosity. As alleged, the Tehados group could be anti-EOTC and by extension anti-Christ; however, this will remain a simple allegation until these folks are allowed to come public with their agenda and show their leadership and structure. I know that the protestant group has inflitrated the church in their attempt to weaken it, but it is futile to blame all the tehadso movement, if any, on the pentes. I believe there are things that need to be cleaned up.

  I also want to say that the author of the article appears to be favoring the Tehados group; he could as well be “a wolf in a sheep hide.” However, the point is: IS IT NOT TIME NOW FOR THE CHURCH TO CLEAN UP ALL CONTROVERSIES ONCE AND FOR ALL AND FOCUS ON SPIRITUAL REVIVAL,INSTEAD OF LETTING THE PROBLEMS PERPETUATE AND MAKE THEM IRREVERSIBLE? What does the church want to pass over to the next generation? A church with lots of controversies or a chuRch that shines from top to bottom? Just to confess, I strongly oppose protestantism because I dont believe in it, but I believe we need to do our job and sift out the good from the bad.

  Folks, even during the time of the Apostels, many people wrote Gospels, Epistels (letters)and different spiritual stories, but our forefathers sifted the true gospels and epistels and bound them in the form of the Bible while rejecting and burning those that they found to be unauthentic with the help of the Holy Spirit. Likewise, a number of good and bad books were written by different monks and Kings after the time of the Apostels, and I suspect some of the bad ones infiltrated the EOTC church so that we have now all these controversies when people start reading them. Even at this time, many people are writing controverisial things in the name of EOTC; unless we correct them now, the next generation will consider them as true books of the church and the fire will become bigger and eventully burn the church to the ground. Folks, I don’t belong to any of the groups and nor do I want to be one. I am commenting this because I love my church and want it to be the shining star on earth without any tainted teaching and with multitudes of followers.

  Does anyone have a different idea for the way forward and resolving the controversies?

  Does anyone believe all the books and writings of the church are absolutely true without any problem?

  Please address me by name when you respond so that I don’t miss any points you guys may make. Thank you,

 6. ተሽመ
  | #6

  ወንድም በታም ብልት ተሃድሶ ነህ:: ክታብህ 10% ውነት 90% ሃሰት ነው:: ግን እኮ ዐንት ተሃድሶ መሆንህን ተናግረህ የምታምንበትን ማስረዳት:: ያናንተና የመሀበረ ክዱሳን ልዩነት ዪሂ ነው:: ዐንተና መሰሎችህ ተልኮአችሁ በፈለገው መንገድ
  ይሁን (ዐሁን ኢንዳረከው በሃሰቲም)ቤተ ክርስቲያንን እና ሃገርን ማዳከም አና ማትፋት ነው:: ማህበረ ቅዱሳን ዓባቶችን ይወዳሉ ብልህ ደግሞ የራሳችውን ቤተክርስቲያን …. . መችም ቢሆን የናንተ አላማ አይሳካም. ለመኮነን እኮ ሃሰት በኪ ትፋት ነው::

 7. Libona yisten
  | #7

  Be sime silase, Amen!

  my brother, you said, you are neutral but obviously you are up to damage ‘Mahbere Kidusan’ and grandize ‘tehadiso’. Well, i happen to know both. Not all members of Mahbere Kidusan are Saints. However, the intension of the association is well meaning and they did encredible justice to the Church and the Nation. If you mean well, let’s engage them constructively and help them perfect their activities.

  Please don’t mix the bagage of our confused diaspora politics with the spiritual matters.
  Libona Yisten!

 8. ዲያቆን
  | #8

  ኪኪኪኪኪኪኪክኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኢኪ

  ”ተልባ እያረረ ይስቃል”አሉ:: ሁላቸውም ስራቸውን ከ እግዘር ያገኛሉ

 9. Baby
  | #9

  በጣም እስማማለሁ:: ሰይጣንና ጭፍሮቹ በተክርስቲያናችንን ሲያዩ ደማቸው ይፈላል::ምንም ልናደርጋችሁ አንችልም::
  @አባይ

 10. Anonymous
  | #10

  @meta
  if this is the case why ? you let posted. this is really bad Ethiopian any body can believe any this is right. it is not place to debt about issue. any body can’t Judge. if Selam is really the writer of this article. There is a massage she can try to send. please live alone be a good person of what you believe.

  If you have him in you(GOD) you can’t speak this bad to any body.

  respect one another millions of way to express Love for God.

 11. belay
  | #11

  @meta
  if this is the case why ? you let posted. this is really bad Ethiopian any body can believe any this is right. it is not place to debt about issue. any body can’t Judge. if Selam is really the writer of this article. There is a massage she can try to send. please live alone be a good person of what you believe.

  If you have him in you(GOD) you can’t speak this bad to any body.

  respect one another millions of way to express Love for God.

 12. ኢትዮጵያዊው
  | #12

  ያገር ልጆች፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ በወገናችን ላይ ያላት ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው። ከወገናችን ቢያንስ ከ50% በላዩ የዚህችው ቤተኃይማኖት ተከታይ ነው። በዚህች ቤተክርስቲያን ትምህርት ላይ የእግዚአብሔርን አሳብ የተከተል ትምህርትና አምልኮ እንዲሰፍን መወያየት መልካም እንጂ የክፋት አይመስለኝም፤ በግሌ። ቤተክርስቲያኒቱ በአገራችን ሕዝብ መንፈሳዊ ሕይወት ላይ ብቻ ሳይሆን በማህበራዊና ኢኮኖሚ ሁኔታዎችም ላይ ቀጥታ ያልሆነ ጠንካራ ተጽዕኖ አላት።

  አንድ የወያኔ ካድሬ ከሚናገረው በላይ አንድ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ዲያቆን የሚናገረው ትልቅ ተሰሚነትና ተቀባይነት አለው (የግሌ አስተውሎት ነው)። ይህቺ ቤ/ክ የጌታችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን በቅጡ ብታስተምር፤ ቃለ-አምላክ ያልሆነውን ነገር ህዝባችን እንዲጥል ብትመክር፣ ለሥራ እንዲነሳ የባህል ትብትቦችን በቃለ-እግዚአብሔር ትምህርት ብትቆርጥ… ወገናችን ከረሃብ፣ ከበሽታ፣ ከድንቁርና እስራት ሰርቶ ሊላቀቅ ይችላል።

  ስለዚህ በዚህ ስፍራ ላይ በጨዋነት ብንወያይ ልናመጣ የምንችለው በጎ ነገር ይኖራል። እንዲያው ዝም ብሎ እንደበቀቀን መጮህ ብቻ ከሆነ ግን ዋጋ የለውም። በእውነት ለአገርና ለወገን አሳቢዎች ከሆንን የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጉዳይ ሊያሳስበን ይገባል። ከዚህ አንጻር ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን፣ ተሃድሶ፣ ማህበረ በኹር፣ ሃይማኖተ አበው… ወዘተ የሚባሉትን ሁሉ በጥንቃቄ መፈተሽ ያስፈልጋል። በጊዜ ካልተፈተሹ ግን በግሌ እንደተገነዘብኩት ከሆነ እንደማህበረ ቅዱሳን አይነት አጉል ጥፋት ሊመጣ ይችላል። የማህበረ ቅዱሳን ትምህርቱ፣ ዓላማው፣ አሰራሩ እና በጠቅላላው አደረጃጀቱ እጅግ ምስጢር ሆኖ ቆይቶ ሁሉም መፈንዳት የጀመረው ከፖሊስት ፕሮግራም ዘግናኝ ዘገባ በኋላ ነበር። ይሄ ደግሞ ስንት ጥፋቶች ተደብቀው እንደቀሩ ቤቱ ይቁጠረው። ይህ ለመንፈሳዊውም ሆነ ለምድራዊው ኑሮ የማይበጅ ተልካሻ አካሄድ እንዳይደገም ነው መነጋገርና መረጃ መለዋወጥ ያለብን።

  ምናልባት እዚህ በመወያየታችን በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ላይ ጉድ ይፈላል ብሎ የሚያስብ ካለ በጣም ደካማ አእምሮ ያለው ነው። ነጻ ሆነን ብንነጋገር ግን በቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች ላይ ልናሳረፈው የምንችለው በጎ የሆነ ተጽዕኖ፣ ተስፋ ያለው እና ለወገናችን የሚጠቅም ነገር ማበርከት እንችላለን።

  መልካም ውይይት፤ ቸር ሰንብቱልኝ።

 13. UU
  | #13

  Please Elaborate with evidence! a href=”#comment-15637″>@አባይ

 14. Misgana.
  | #14

  Thank you for your comment. Well, we can’t deny the fact that we are facing now in our church. You might have some degree of truth. I was not intending to elaborate,criticize,appreciate any fact or grouping. I am sorry about the “non categorized church goers” We are so thrilled by the privilege of these groups, and yet at the same time we know that we have to let it go. “I learned long ago, never to wrestle with a pig, you get dirty; and besides, the pig likes it.” Every one of them is fighting the church. Some of them are conquering the church and pinching the people in all their battles. Others are trying to break the resistance of the church without fighting.
  If these groups are merely opponents of the church or allies, that would be no problem. However, they torn between a desire to improve (save) the church and a desire to fulfill their hidden agenda. This makes our church sink in thorny situation. Dangerous situations always come to us in beautiful color combinations that are but skin-deep. We believe in God. Believers please, don’t let your mind depend on what people say about our church. Self-important Pharisees and Sadducees, Darwinists or the progeny of Judas will not remain evermore. They have never been successful. The blood of Jesus Christ is going to heal the double-cross of our church. God be with us always. God bless.

  Misgana.

 15. ያበጠው ይፈንዳ
  | #15

  አንዳንድ ሰዎች በውያኔ ጭንቅላት የመዘናሉ እንዳነበብኩት ከሆነ እንዴት ብትሉ ለምሳሌ ወያኔ እፈለገ ቢያጠፋ ጎበዝ እንጂ እርምትን መስማት አይፈልግም አሁንም ጭራሽ አንዳንድ አስተያእት ሰጪዎች እዚህ ፕሮተስታንት እያሉ ያልበላቸውን ሲያኩ ይታያል እስቲ ንገሩኝ ይኛስ ሐይማኖት እኛ ሌላውን ለማማት የትኛው ፍጹማዊነታችን ነው??????? እናም ያለውን ምፍቴ መነጋገር እና መወያየት ማለት የሚያምጣው ነገር ቢኖር ለውጥን’, ተሐድሶን, ህድገትን ,እርምትን,ነው እንጂ ምንም ክፋት የለውም ተሐድሶ በጣም ያስፈልጋል ጥርት እና ቁልጭ ያለ ወንጌል እያለ ምድረ ኮተት ሰብሰበን ይስም ሐይማኖት ምን ያደርጋል????? ይህ ከበሰበሰና ከዋላቀነት አስተሳሰብ እንውጣ . የታዘብኩት ነገር ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስ ይዘን መታየት እንኳን እንደነውር ነው ብሱ ፋንታ ሰኔ ጎለጎታ, ፍካሬ ዘጻድቃን, ዳዊት,…… ዳዊትም ቢሆን ከመዝሙረ ዳዊት የወጣ ይሁን እንጂ ብዙ ከስጋ ለባሽ እና በስጋ የተጨመረ ጽሁፍ ይበዛበታል መጸሔፍ ቅዱስ አነሰ????? በመንፈስ ቅዱስ የተጻፈ የከበረው የግዚሐቤር ቃል ይታረማልን???????? አሳዛኝ እና አሳፋሪ .መጸፍ ቅዱስ የያዘ እንደ ጰንጠ እየታየ እኛም ሆንን አባም ሆኑ አባት ተብዬዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ በሰው የተጻፉ ሰው ደረሶችን ይዘን ስንታይ ደስ የሚላቸው የሚለንም እጅግ በጣም አሳፋሪ እና አስቀያሚ ነገር. ጭራሽ በኛም ብሶ በኛም ብሶ ጥረት ያለች መጸፍ ቅዱስ የሚጠቀሙትን የተበረዘ መጽሐፍ ይጠቀማሉ እያልን ወዝና ለዛ የሌለው ውሸት ስንዋሽ ትንሽ አናፍረም እኛ ነን ዋናው አንድና አንዱን የአምላካችንን ቃል ወድያ ብለን ምድረ ኮተት የምንሰበስበው ይህን መናገሬ ይብዙዎች ምህመኖች መፍለስ ስለሚያቃጥለኝ ነው!!! ይህ ነው ትልቁ ምክንያት. እናም ያበጠው ይፈንዳ እንጂ እውነቱን እናእራለው ሰዎች ለምን ይህን ሐኢማኖት ይተዋሉ???? እውነቱን ተነጋግረን መፍቴ ማምጣት ይሻላል ዎይስ ከፈጠርን ፈጣሪ በላይ ለራሳቸው ሐጥያታቸው ከግር ጥፍር እስከ ጸጉሩ የተዘፈቀውን ቄስ,አባ,ፓትሪአክ ድያቆን.አብነ እያልን ለንሱ ማሸርገድ??????ለዚህ ነው እውነት እንዳናውቅ ማንበበ ያለብንን የሚበራረዙብን ለዚ ነው ስለንዚህ ሰዎች ጌታችን ሲናገር በገበያ መሐል እረዣዥም ቀሚስ እየለበሱ ክብርን እይሚፈልጉ እንዛ ግብዞች ያለው . በጣም ክብር ይፈልጋሉ . አናክብራቸው አይደለም የሐይማኖት አባት አይደለም ማንም ሰው ስርሃት ባለው መንገድ መከበር አለበት. አልሽቆጠቆጠም ለፈጠረኝ አምላክ እሽቆጠቆጣለው!!! የትኛውንተውነት ሲያስተምሩ. ሁላችንም እኩል መብት አለን ቃሉን ማንበበ ነው በቃ የፍርድ ቀን ማንም ለማንም አይደርስም ሊደርስም አይችል ወድያ ብለን ችላ ላልነው በሙሴ በመንፈስ ቁዱስ የተጻፈውን እውነተኛ መጸፍ እናንብብ የተረት መሐት ተተን እናም ተሐድሶ ጥሩ ነው እጅግ በጣም ጸሐፊው በርታ በርታ!!!!!

 16. Misgana.
  | #16

  @Peace
  Hi #39 Tobia
  If you are still in old Germany hotel, I want to send a wake-up message. Or may be you just wake up in the middle of nowhere in Ethiopia. If your heart is on your native land you need to bind to all problems. If you afraid of God or doing mistakes or if you don’t believe in institution, just calm down. Otherwise, this is burning issue. Thanks.

 17. Kinfe Gebriel
  | #17

  I honestly believe that this article was not neutral, it is a fact that it sides with the Tehadiso groups. If the tehadiso groups have authentic reasoning to “refurbish” the Church, it would be this time while most people are open for challenges and scholarly debate since Ethiopia is now led by a secular government that would actually favor differences in a very important and powerful institution in Ethiopia as EOTC believers. But the only reason why the tehadiso enthusiasts don’t come out in public with their point of view is for the mere reason that they can stand the ultimate truth the Church is founded upon, i strongly support the idea that there are elements in the Church with strange traditions attached with the Church but those elements are not endorsed by Mahibere Kidusan, EOTC Administration and EOTC members who have basic knowledges of the Church. Even though, as a large organization, Mahibere Kidusan has some problems within itself, it has never allowed the bad seeds to grow, infiltrate the very founding principles of it and at last destroy it but has successfully rejected them out everytime they show up, its vigilante attitude and intelligence gathering systems are very important to help protect the Church from venoms like Tehadisos. Emperor Zera Yacob was a simply one of the best leaders Ethiopia ever had, he is widely respected in all of the Oriental Orthodox Churches and specially in the Coptic Orthodox Church that never makes the mistake of accepting a murderer and an enemy of the Church in her “Hall of Fame”. Emperor Zera Yacob might have persecuted Aba Estifanos and his students but the story is entirely exaggerated. And the only “mistake” one can find in Te’amire Mariam” book would the very idea of magnifying the glory of the Mother of God, and this is a mistake if its only seen with the eyes of Satan and his followers. In the first place, this book was co-authored by Aba Michael and Aba Gebriel, two of the most respected scholars of the Coptic Orthodox Church of Alexandria. The other point the author of this article just raised was about bowing down for the Holy Cross, in our Churches case, genuflecting towards the Holy Cross and Holy Images depicting the life of the Lord and His Saints, I can never understand why one would oppose the idea of bowing for the Cross, the article said “Man made cross”, Jesus Christ didn’t put the Cross together to be crucified on but enemies did and He gave His Blessed Life on It and we, without any regret , will bow down for the image of the Cross and will be definitely saved by doing so. The only creature that hates the guts of bowing down for the Holy Cross would be Satan and its followers. So, by only taking this point into consideration, I and other Ethiopian Orthodox Tewahido Church members along with Mahibere Kidusan denounce the tehadiso motive to detroy our Church, History and Heritage. May the God of Zera Yacob give you the common sense of real Christianity. If the Emperor did that to the dekike Estifanos, it might have been a punishment from God, as for me, Zera Yacob was a true servant of God who was blessed by God Himself and i know that because He became the first in our History to be entrusted by God of the Holy Cross. Many Kings including his father have tried to be blessed by doing so, but it was Zera Yacob, who was the chosen one. May His Blessings be upon us for He was a righteous King Blessed by the Holy Trinity.
  God Bless Ethiopia

 18. ሰላም
  | #18

  በጎ ነገር ሳይኖረኝ እንዲሁ በወደደኝ ጌታ ስም የምወዳችሁ እግረ ቀጫጭን ወገኖቼ!!!

  እስቲ እንደማመጥ እንስሳይቱ አህያ ሳትቀር የእግዚአብሔር ቃል መልእክተኛ በመሆን የሳተውን ነቢይ ከሰህተቱ መልሳለች:: ታዲያ እኛ በአምሳሉ የተፈጠርንና ማመዛዝን የምንችልበት ህሊና የተቸረን ሰወች ምን ነክቶን ነው ሊያስተምርና ሊያንጽ የሚችል ቃል ድሆች በመሆን የአፍራሽና የአስጸያፊ ቃላት ጎተራ የሆነው??? እባካችሁ እውንቱን ተነጋግረን ለችግራችን የጋራ መፍትሄ እንፈልግለት:: እስቲ አንድ መሰረታዊ ጥያቄ እንድጠይቅ ይፈቀድልኝ:: እሱም የቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ በመጀመሪያው ጳጳሳችኝ በከሳቴ ብርሃን መልካምና መንፈሳዊ ጅማሬ ጀምራ ሳለ ከዚያ በሁላ በዮዲት ጉዲት በግራኝ ሙሐመድ በንጉሥ ዘራይቆብና በነገሥታት ጣልቃ ገብነት አልተቃጠለችም? አልተመዘበረችም? አልተቀላቀለችም?/ሲሦ መንግሥት/ የያዘችውን የወንጌል እንቁ እንድትጥል አልተደረገችም? እውነተኛ የእምነት አባቶች የተበረዘውን አንቀበልም በማለታቸው አልተገደሉም?/በፕ/ር ጌታቸው ሃይሌ የተተረጎመውን ደቂቀ እስጢፋኖስ መጽሐፍን ያንብቡ/እረ ለመሆኑ ድግምቱ አንደርቡ አስማቱ ክፋቱ ተንኮሉ ምንጩ ከየት ነው? ታዲያ ነቢዩ በአሃያቱ ከተመለሰ እንዲሁም ሓጢያተኛው በንስሓ እንዲመለስ ጌታ ራሱ ከፈቀደ ቤተ ክርስቲያናችን በዘመናት በተፈራረቁባት ችግሮች ምክናያት የጣለችውን ብታነሳ የዘነጋችውን ብታስታውስ የግብጽ ጳጳሳት ያሸከምዋትን ባእድ ሸክም ብታቃልል የተነሰነሰባትን አብዋራ ከላዋ ላይ ብታራግፍና እንደገና ባላት መልካም ነገርዋ ላይ ውብት የሚያጎናጽፈውን ወንጌል ብቻ በመስበክ ሕዝብዋ በመንፈሳዊና እንዲሁም በሥጋዊ ነገሩ እንዲባረክ ከርስቶስ ኢየሱስን እንድትለብስ ብትደርግ ምን ላይ ነው ክፋቱ??

  ብዙ ብዙ የሚባል ስላለ ከጅምሩ በጦር አንወጋጋ:: የዘመናት ችግራችንን ምንጭ ካወቀን መፍትሄው ቀላል ይሆናልና ትእግስት ይኑረን

  ማንም ይጽፍ ቁምነገሩ ፍሬ ሃሳቡ ነው::

  ሰላም ሁኑልኝ

  ሰላም ነኝ

 19. Anonymous
  | #19

  I found this article and more at http://www.abaselama.org. The writer of this article may be maintaining this website. Interesting anyway.

 20. ፋሲል
  | #20

  @ኢትዮጵያዊው
  መጀመሪያ አንተ ራስህ ስርአት ይኑርህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አንተ ብለሃት ወይም ጸልያህላት የምትኖር አይደለችም ያለች የነበረች ወደፊትም እስከ እለተ ምጽአት የምትኖር ነች መንግስት ይመጣል መንግስትም ያልፋል ቤተክርስቲያኒቱ ግን Against all odds ዘላለማዊት ናት ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ እንደሁልጊዜው ቤተክርስቲያኒቱም በራሱዋ ልጆች ጭምር ስትፈተን ኑራለች አሁንም እየተፈተነች ነው በአሁኑ ሰአት ሊኖርባት የሚችል ፈተና ምሳሌ ልጥቀስልህ ብለው ብለው ያቃታቸው ጴንጤዎች አሁን ተመሳስለው እየቀረቡ ነው ተሃደሶ ብለው ራሳቸውን ማለት ነው ሌላው የዘር ክፍፍል ነው አንተ የእከሌ ነህ ያኛው የሌላ የአሁኑ የቅርቡ ደግሞ የጥንተ አብሶ ጉዳይ ነው ይሄ ሁሉ ከንቱ ነው ቤተክርስቲያኒቱን ንቅንቅ አያደርጋትም በክርስቶስ ደም በመመስረቱዋና የማእዘን ራሱዋም ራሱ ባለቤቱ በመሆኑ:: ሌላው ቢቀር ጌታ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የኔ የሚላቸው በጎች አሉ ስለነሱ ሲል ቤተክርስቲያኒቱን ይጠብቃታል ብቻ ሳይሆን ይዋጋላታል አሸናፊውን ደግሞ ስናይ ነበር አሁንም ወደፊትም እናያለን የዲያቢሎስ መልእክተኞች ግን ለጊዜው ፈንጩ

 21. UU
  | #21

  ያበጠው ይፈንዳ
  wow ! Great comment! By the way, I am a pentey. There are few true Orthodoxes in our church like you who were from kes family. They have vast knowledge of the Bible and I have great respect to them. Example, professor Tilahun Adera is one of matured and well respected Bible teacher. http://nazret.com/blog/index.php/2009/01/18/ethiopia_prof_tilahun_adera_named_dean_o

 22. አይ ክርስትና!!!
  | #22

  አይ ይህ ዽንጠ ተቸገር እንሱ ከነመፈጠራችንም አያነሱን እኛ ዘፈናችን ሁሉ ዸንጠ ሆነና አረፈው አሳፋሪ ነው እነሱ እይገሰገሱ ነው እኛ ደሞ ቼልሲዎችን እየደገፍን አብረን እዬተንገዳገድን ነው የተወሰኑ ሰዎች ለመፍቴያችን ጥሩ አድሎ የሌለበት ነገር ጽፈዋል ይህ ከስህተት ይመልሰናል ወንጌል ወንጜል በቃ ከአባባ ተስፋዬ የማይተናነስ ተረት ይቁም!!! የራሳችንን አንድ ሺ ጥፋት እንፈትሽ የሚገርመኝ ያለዸንጠ የሚያባነነ የለም እንዴ ሼም ስንትና ስንት ሐይማኖት እያለ አንቅና እንደንሱ መሆን ካልሆነ ዝም ይሻላል አንድ አምላክ ያመልካሉ እኛ ደሞ 30 አምላክ እግዚዖኦ 30 ቀን መቀነቱን እያላላ ሆዱን እያሽ ሲያስደግሰን ከረመ አሁንም እንድያ ቁልጭ ያለውን ውነት ካወቅን ጉዱ ይፈላላ እናም እኛ አናውቅ ዝም ብለን አባ መጡ ኦ በሉ በዚ ወጡ ያ በሉ እይተባልን ስንሰግድላቸው ኖረናል እኔ በእመቤቴ ቀልድ የለም ባይ ነኝ ግን የቕሶች አድራጎት ያበሽቀኛል አሁን አህንማ ሰው ሲያፈነግጥባቸው አስቂኝ ድራማ ጀምረዋል 5ሺ አንዳንዴም 3ስት ሺ እይከፈሉ የፔንጠ መንፈስ ጩህ እያሉ መፎገር ጀምረዋል በደንብ እያሰለጠኗችወ በየንግሱ ድራማው ይካሓዳል ማፈርያዎች የአንድ ሰሃት ስብከት ቢሰጣቸው 45 ደቂቃው ዽንጠ ነው የሚታይበት 15 ደቂቃ ቃሉ በለው!!!!!ይህቺ የፔንጠ መንፈስ ድራማ በቅርቡ 3ስት ሰዎች ታያላችው ስልጠና ላይ ናቸው. እኔ ለጰንጠ ማገዜ አይደለም ነገር ግን የራሳችን ስንት ጉድ እያለ በፈጠራ ስም አናጥፋ ማምላክስ እንዸት ከኛ መሃል ይገኛል???? እንዴት ያስማን እመቤታችንስ እንዴት ትማጼነን!!!!!!የጠንቕያ ታምራት ገለታ ፉገራ እኮ ሲጋለጥ ምድረ ቄስ ጥምጥሙን እይፈታ እንደገባ አትውቁም ይህ ነው አጋንንትን በግዚሃቤር መንፈስ የሚያስለቅቀው???? እራሱ ይጮህ ይሆናል እንጂ ብዙ እል ነበር ደከመኘ እመቤቴ እንደማትኮንነኝ እርግጠኛ ነኝ አልዋሸውምና በቃኝ አንድ ሁለት ቢራዬን ቋ አርጌ ለጥ ደና እደሩ.

  //

 23. Ethiopian
  | #23

  I am not a memmber of EOTC but I am very happy to see atleast the Theadsos. No one wants EOTC to go away or destroy why? I just want to see the true gospel preached ::

 24. ተባረክ
  | #24

  ተሃድሶ አያስፈልግም የምትሉ እራሳችሁ ተሃድሶ ያስፈልጋችሁአል

 25. ገረመው ዘበርጋ
  | #25

  አረ ለመሆኑ ማደስ፣ መጠገን፣ ማጽዳት የሚያስፈልጋቸው ዕመነታቸን ነው ወይስ ስር አታችን ነው? የተሃድ ሶ ተክታዮች አነዚህን ሁነታዎች ግልጽ ማድረግ አለባችው. አነኚህ ሁነታዎች በግልጥ ክኣልታወቁ በስተቀር የተሃድሶ አንቅስቃስ የፕሮተስታንቶች ስውር ደባ መሆኑና ዐለመሆኑ ሊታወቅ ዐይቻልም. የሸረሪት ድር፤ የጢስ ጠቀርሻ የተባሉት ምን አንደሆኑ በግልጥ ይነገረን.
  ወሰበሃተ ለአግዚዐብህር

 26. ኩሉሉ –
  | #26

  በጣም የሚገርም በ እሪት የተለወሰ ጣፋጭ መርዝ ነው ;; እንወያይበት አልክ ! እኮ ወድይት –ወድይት ? በተሃድሶ ፈረስ ማንን ልትጎትት ? እኛም ነቅተናል —– ምሰናል
  እግዚአብሒር ኢትዮጵያን ይባርክ

 27. ተዋህዶ
  | #27

  የሸረሪት ድር የጢስ ጠቀርሻ ከሆኑት ለምሳሌ፦ በቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍ (ዚቅ በተባለው)ሚያዚያ 25 በሚዜመው ገጽ 170 ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዲህ ይላል “ስለ ሰው ልጆች ፍቅር በመታገስ መከራን የተቀበለ በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሰማይን እንደዋልታ የዘረጋና በከዋክብት የሸፈነ መርቆሬዎስ የሾኽ አክሊልን በራሱ ላይ ደፋ ስለዚህ ቸርነቱና ትህትናው ደግነቱን እንናገራለን” ይሄ ነው የጥንታውያን ኦርቶዶክሳውያን ትምህርት? መርቆሬዎስና ክርስቶስ አንድ ሆኑ? ይህንን ሲያነብ የማይዘገንነው ኦርቶዶክሳዊም አይደለም መጽሀፍ ቅዱስንም አይቶ አያውቅም። እንደዚህ አይነት የቤተክርስቲያንዋ ያልሆኑ ኮተቶች ስላሉ እነዚህ ይስተካከሉ የሚሉ ወገኖች እንዳሉ አንዘንጋ። አንዳንድ የፕሮቴስታንት ድርጅቶች ግን በእንደዚህ አይነት ጤናማ ውይይት ውስጥ ገብተው እንቅፋት መሆናችወ ግልጽ ነው እኛ ግን ብልጠት ያስፈልገናል።

 28. ሰው
  | #28

  አይ ተስፋi
  አንድ ሰሞን ደጀ ሰላምን አምሰኃት ነበር:: the truthfigter እያልክ ሙሉጌታ መሆንህን አስፎግረህ ነበር አሁንም በተስፋ ከች አልክ?
  እውነትን ተዋግተህ አታሸንፋትም እውነቴን ነው ከምር::
  አንዱ የግብር ወንድምህ ጴንጤ ኢትዮጵያ የነበረ አሁን ኬንያ ነው በዚህ ጉዳይ ሲፅፍ(ማህበረ ቅዱሳን ና ተሃድሶ) ምን አለ መሰለህ “Deception, even in the name of Christ, is still deception. These sorts of tactics are being reproduced elsewhere in Ethiopia.” ለዚህ ነው ማስመሰል ሳይሆን መሆን ነው አምላክን የሚያስደስተው::

  [One group of American missionaries has insinuated themselves under misleading premises (claiming to be business people when in fact they are missionaries from a Western grouop) into the area near one of the reformists theological colleges. By drawing into their circle some of the reformist leaders and students, they have had some success in persuading some to the Protestant perspective on salvation and the baptist perspective on baptism. The intention of these missionaries is to remove these leaders from the Orthodox Church and from the reformist movement and to set up (of course) their own baptist church. Deception, even in the name of Christ, is still deception. These sorts of tactics are being reproduced elsewhere in Ethiopia.]

  እውነት:: በነገራችን ላይ ይህን ያለው ሰው(ፓስተር ዊሊያም ብላክ)ጥቅሱን ስፈልግ ፅሁፉን ሰርዞታል::ደስ አይልም??? አይ የናንተ ነገር ያመናችሁበትን የማትናገሩ አስመሳዮች::

 29. ያእኮብ
  | #29

  Tewahedo,

  You mean it? This is much worse than a spider’s web. This is taot amliko or fetishism. Your point proves my earlier argument that bad writings have infiltrated the church over the years. I think that the pentes need to be restrained by all means not to divert such health dialogues to clean up our church…

 30. ኧበበ
  | #30

  ሁላችን እንደ እግዚአብሂር ቃል እንጂ እንደ ሰዎች የፍልስፍና ድሁፍ መሂድ የለብንም በእግዚአብሂር ቃል ብቻ እንመን አሚን

 31. groom
  | #31

  This is very annoying generation. First of all, it was better to read more about our history both in religion and our origin. We were the descendent of melke tsedic the present of king solomon. we know how to senve God. We don’t need any modification. who told you that all modifation is made by king Zereyakob? Who told you that the bible you have the right one? How do you trust others while still you have hard time to beleive in with all the materials that are preserved by your families? do you have all reasonable idea how all all thing that are availble all things that your reject? The tahadso people, your families were serving your lord satan, but didn’t get a chance to speak like you before. So you guys are talking such a trush idea? Why I am believing a such a modified association if it does not save my soul? I can live by myself with out you guys. Go to the wilderness and watch out what our great father are doing? Enjoying with holy spirit. They are not like yours who are wandering up and down in the cities with very nasty women hiding them selves in big coat and big Cross. Because they have already tide up and blinded with the bad spirit, they don’t have any peace in their mind unless they have changed our brothers and sisters who are dedicated to the right direction. Dresssing a big coat and hanging a big cross is not the criteria to be the church leader, but it requires a also practical life based on the bible. Otherwise, leave us alone, go to the protestinat church as you did it befoer or join with paster dawit, the cursed man, enjoy ensulting other for the time being. God will pay you back one day.

 32. ዘጌ
  | #32

  በጣም የሚግርም ነው ‘…ውስጡን ለቄስ ያአሉት ወደው አደለም
  ለጸሃፊው እግዜር ይስጥልን
  ቃለ ህይወት ያሰማን

 33. በርታ!!!!!
  | #33

  ጸሐፊው በርታ ይኛ ችግር ችግርን በውይይት ከመፍታት ይልቅ ከነችግሮቻቻን ወደ መቃብር እንወርዳለን እንጂ አነታራኪ እና ተውቃሽ ማጣት አንፈልግም . እውነት ተነግሮ ችግርን ከማጥፋት ወነትን ማድበስበስ እንወዳለን እጅግ ጥሩ ነገር ነው በበኩሌ አድንቄያለው በርታ!!!!!!

 34. ያእኮብ
  | #34

  SOLUTIONS

  Alternative 1:

  1. The true Tehadso wing needs to clean itself from any Penete element and needs to break any ties with them.

  2. Tehadso group needs to come up with a comprehensive Tehadso agenda and need to make that public by presenting the agenda to the EOTC leadership. They should spell out the suggested changes in amlikot, book revisions, traditions, beliefs, admin, etc…

  3. If the church leadership, MK and the likes are not listening and don’t want to partake in a dicourse to address the problems, then

  4. The Tehadso wing should establish its own Reformed EOTC with clear faith statement, accepted books or revised books, tradition, leadership, etc… My fear is that the Tehados group is highly fragmented without any common voice; some are elements of Pente as alleged and some are genuine people who want to clean up the dirt from our church.

  5. Establishing a genuinely reformed church will create pressure on the EOTC leadership to slisten and clean up the dirt. The tehados wing should not be tempted to join the Pente group because of pressure to do so from the opposing group. If they do, then the opposing group will win and i would say the Tehadso group does not have a genuine agenda, but they are extension of our enemies, the Pentes.

  6. If the Tehadso group has a genuine reform agenda and is not another arm of pente, they will definitely win in the end as there are lots of areas that need some clean up. I have talked to many priests and preachers in the church, they fully acknowledge the problems, though at different magnitudes.

  7. One last thing is that, the Tehados group should compare the faith and practices at EOTC to those of other Orhtodox churches. Certainly we have differences with the Eastern Orthodox churches on the Nature of Christ, but the rest should be comparable. However, there should not be substantive deviation from the Coptic Orthodox Church and the other sister churches. Of course, differences in traditions should be expected among all.

  I am just trying to forward my one cent advice if that can help. I pray that God help all those who have a loving heart for our church, EOTC.

አስተያየት መስጫ
አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።