እንዳንዘነጋ፤በድቡሽት ላይ የተሰራ ቤት ምን እንደሚሆን አናውቅም የሚሉ ሰዎች ሁሉ፦ እነሱ ልባቸው ድንጋይ አይናቸው ግንባር ሆኖ በቁማቸው ሞተዋልና ሕሊና የላቸውም።
ቀጥታ ወደ ወቅታዊ ጉዳይ መግባት አለብንና አገራችን ኢትዮጵያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የዲሞክራሲ ሥርዓት ለመመስረት የመሞት ወይም የመዳን አሊያም ወደባሰ የእርስ በእርስ ጦርነት:- አንድዬ ይብቃት ካለ ደግሞ የዓለም መድኅኒት ልትሆን ከገዳይ ልጆቿ ጋር የሞት ወይም የሽረት ትንቅንቅ ላይ ትገኛለች።
ኢትዮጵያ የሰላም እጆቿን ዘርግታ ለዘመናት ለተፈራረቁባት ጠላቶቿ ውድ ተተኪ የሌላቸውን ልጆቿን በመሰዋት በደም ጎርፍ ስትታጠብ በመከራ አሳልፋለች።ዛሬ ይህን የመከራ እሣት እያቀጣጠለ አምርሮ ሊገድላት የመጣን ጠላት የሰላም እጅን በመዘርጋት ልቡ ይራራላታል ማለት፣በሚሊዮን የሚቆጠር ሃብትህን ትተህ ወደ ነበርክበት የቀድሞህ ኑሮ ተመለስ ማለት ስለሆነ ምላሻቸው”መግደል ወይም መሞት”መሆኑ እየታወቀ ይሻላቸው ይሆናል ብሎ መገመት በሌላው ተራ ሕዝብ ሕይወት መቀለድ ነው።ይህንንም በቀላሉ እንመልከት እነዶክተር እንትና፣እነፕሮፌሰር እንቶኔ ወይም የታወቁ ሰዎችን መንግስት ይዞ በግዱ እንዲፈታ ይደረጋል፤በሺህ አሊያም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምን እንደተደረጉ እናውቃለን፤የመለስን የተናጠል”ሊያስገድሉህ”ነው ወኔ መስለቢያ ጥገኛ ሐረግ ትተን።
እናም ስለአንድ የኢትዮጵያ ጉዳይ በየግላችን በሰብዓዊነት ወይም በሰውነት ለማድረግ ፈልገን ስንጀምር የችግሩ መፍትሄ ላይ ለመድረስ ጥረታችን ከቀላል ወደ ከባድ እየተወሳሰበ ሊሄድብን ይችላል።በተለይም የቤት መሥራት አገርን ከመገንባት የተለየ አይደለምና ጉዳይ ቀላል አይሆንም። ከዚህ አንፃር እንደኢትዮጵያችን ያሉት በችግርና በፈተና የተወታተቡ አገሮች መፍትሄአቸው በቀላሉ የማይገኘው ከዜጎቻችን መካከል ሕሊናቸው ድንጋይ የሆነ ብቻ ነው። ይህንን እውነታ በቀላል አቀራረብ ለመረዳት እንችላለን።በቅድሚያ የቤትን በኋላም የአገርን ግንባታ እንመልከት።
ምናልባት ይህ አቀራረብ ተራ ሊሆን ይችላል፣መርሳት የሌለብን ግን ያንን ጥሩ የእጅም ሆነ የግድግዳ ሰዓት በተገቢው እንዲሰራ የምታደርገው ከትንሿ ብሎን ጀምሮ መሆኗንም አለመዘንጋት ነው።የአንዲት ብሎን መጓደል ሰዓቷን ቀስ በቀስ ዋጋቢስ እንደሚያደርጋት ሁሉ ቤትም ስንሰራ ለምን እና እንዴት እንደሚያስፈልገን ከመሰረቱ ማወቅ ይኖርብናል።ለዚህም በቅድሚያ ቤት መሰራት ያለበት በድቡሽት ላይ ወይም በአሸዋ ላይ ሳይሆን መሰረቱ በጠብቀ አለት ወይም ድንጋይ ላይ ነው።ይህን ሐቅ በዛሬው ጊዜ በሰው የዕድሜ ደረጃ የምንገኝ ሁሉ አንዘነጋውም ብዬ አምናለሁ።እውነትንቱን የማይቀበሉት ግን በዚህም ሆነ በዚያ ምክንያት አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከእነ ሕሊናቸው ዘቅጠዋል።
በምሳሌ አስደግፈን የአገራችንን የኢትዮጵያን እውነታ ስንመለከት ድቡሽቱ ዘረኝነት ነው። ግንባታ፣ልማት፣ነፃነት፣እኩልነት፣አንድነት፣ወዳጅነት፣ጥምረት፣ዲሞክራሲ፣ዳኝነት እና ሰብዓዊነት እንዲሁም ሌሎች የእግዚአብሔር ሥጦታዎች ሁሉ ሰው በመሆናችን ሊኖሩን የሚገቡን ናቸውና ማንም ግለሰብ እንደፈለገው ሊሰጠን ወይም ሊከለክለን ሥልጣን እንደሌለው ይታውቃል፤መሰረቱ በዘረኝነት ላይ ከተመሰረተ ድቡሽቱ ይሄው ነው። እነዚህን የነፃነት መብት ለማስጠበቅ ደግሞ ለእኛ አሁን ላለነው ኢትዮጵያውያን ለማቆየት ያለፉት ወገኖቻችን ምን ያህል ደምና አጥንት ለጠላቶቻችን እንደገበሩ በቂ ምሥክራቸው ስለ እኛ እየተሰቀሉ፣እይታረዱ፣እየደሙ እና እየተፈጁ፣ የእኛን የዛሬ ሕላዌ መፈጠር ነው።
****ታዲያ ዛሬ ግንባታ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው ብለን ያውም “አስፋልት”ተብሎ ያደጋ መቆጣጠሪያ መብራት እንኳ ሳይኖረው ያለ ጥናት በመሰራቱ በሺህ ለሚቆጠሩ የመኪና አደጋዎች ሕዝብ ለሞት የተጋለጠባቸው ከተማዎች ተደርተው፤በሺህ የሚቆጠሩ ሕንፃዎች ውሃ እና መብራት የሌላቸው ሆቴሎችን ጨምሮ ተራ መፀዳጃ እንኳ የሌላቸው።የግንባታዎቹስ ባለቤትነት የማን ንብረት ናቸው፣የሕዝብ ግን አይደሉም።የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን የማን ንብረት የቱ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል።ቁምነግሩ ታዲያ የተሰራው ግንባታ በድቡሽት ላይ ነው ወይስ አይደለም ለሚለው ዕውነቱን ማወቅ ነው።አዎ ሕሊና ካለን ሐቁን ልባችንም ያውቃል አይናችንም ያየዋልና ሳናውቀው ነገ ታሪክና ሕዝብ ከጎናችን ሆነው በሰብዓዊነታችን ሲወድሰን እና ሲያመሰግነን ይኖራል።
****እስኪ ልማታችንን እንመልከት፤የተፈጥሮ ድርቅ አገራችንን መታት እናም የዓለም ሕዝብ አዘነልን ገንዘብ ሰጠን ምግብም እረዳን። እኛም በዚያ እየቆየን ከእጅ ወደ አፍ ልማትን ተያያዝነው።ድንገት የመንግስት አካል ነኝ የሚል ባዕድ ግለሰብ አጠገባችን መጥቶ በሰለጠነ የእርሻ መሳሪያ የኔንም መሬት ጨምሮ እያረስ ያመረተውን እህል ማጋጋዝ ተያያዘው።እኔም በድህነቴ እና በአቅመ-ቢስነቴ የበይ ተመልካች እንድሆን የተደረግኩት በልማት ሥም ነውና በኢትዮጵያዊነቴ ጊዜዬን እጠብቃለሁ።ነገ ብረት ባነሳስ አይገባኝም???
****ነፃነታችንንስ ብንመለከተው የመጨረሻ ጣሪያው በመሸማቀቅ እንደተቋጨ ስንቶቻችን ተረድተንዋል???ሆን ብለን አይደለም ተሳስተን ድንገት ለምንናገረው ወይም መስሎን ለምንጠይቀው የሕይወት ዋጋ ሞት የሚያስከፍለን እንደሆነ ተገንዝበናል???የመንግስት አካል ነኝ የሚል ሁሉ ጥፋትን የማይታረም ስህተት ለመፈፀም ወይም ለማድረግ ሥልጣን እንደተሰጠው በትክክል ተጨባጭ መረጃዎች ማቅረብ ይገባኛል?ምክንያቱም አልተፈፀሙም የሚሉ ግለሰቦች ስላሉ?ሐቁን ግን ምንጊዜም ማየት እንችላለን።
እኩልነት በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብለን ለማመንም ሆነ ላለማመን ዋናው እኩልነታችን በሕጉ መሰረት ከለላ ማግኘቱ ወይም አለማግኘቱ ነው።በእርግጥ እኛነታችን የሕግ ከለላ አለው???ወይስ የሕግ ከለላ ያለው የሚመስል ሽፋን አለው???እንንቃበት!!!
እናስ ይህ ሁሉ ጥፋት መኖሩን እናውቃለን በአንፃሩም በጎሥራዎች በስፋት እየተሰሩ ነው ብለን እንናገር፤ዳሩግን በቅርፃቸው መልካም የተባሉት በይዘታቸው ግን በድቡሽት ላይ የተመሰረቱትን በጥልቅ የተገነዘብን ስንቶቻችን ነን?????
ማጠቃለያ:- ****እንዳንዘነጋ፤በድቡሽት ላይ የተሰራ ቤት ምን እንደሚሆን አናውቅም የሚሉ ሰዎች ሁሉ፦ እነሱ ልባቸው ድንጋይ አይናቸው ግንባር ሆኖ በቁማቸው ሞተዋልና ሕሊና የላቸውም። *****
ችግሩን ያወቅንስ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል???
እያወቁት የሚዋጉን እነሱ ልባቸው ድንጋይ አይናቸው ግንባር ሆኖ በቁማቸው ሞተዋልና ሕሊና ስለሌላቸው የለየላቸው ጠላቶቻችን ናቸው።
በጉዳያችን ስለኢትዮጵያ ሁኔታ በአደባባይ ስንቆስል፣ስንደማ እና ስንገደል አልግባንም ብለው
በትግል መሃል የሚገኙ ደግሞ ምርጫቸውን ከሕዝብ ወይም ከጉጅሌው የትግራይ አጋዚ ቡድን ጋር ለመቀላቀል አሁን መወሰን አለባቸው።
ይህም ትግል በአደባባይ የወጣ እና ሕዝብ የሚያውቀው አሰላለፍ ነው።
ልዩነቱን ለማወቅ ብዙ መመራመር አያስፈልግም።ከዚህ በታች ያሉትን ቀላሉን የትግል ስልቶች መፈፀም ነው።
1ኛ/የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ሆኖ በመሃሉ አምባሻ(ኮከብ)ያለበት አይደለም፤መያዝም የለበትም።
2ኛ/ግፍ፣ጭቅቆና፣ዘረኝነት፣ኢ-ሰብዓዊነት፣መገደል፣መታሰር፣መገዛት እና ሌሎችም ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ለማቆም የትግራይ ጉጅሌው አገዛዝን “በቃ!!!በቃ!!!በቃ!!!”ብለናል ይህንንም በግል በተለያዩ አልባሳት ማሳየት አለብን።
3ኛ/በቴክኒዎሎጂ በመታገዝ ኢንተርኔትን ጨምሮ ለሕዝብ የምናውቀውን ማጋለጥ ይገባናል።መለስና አዜብን ጨምሮ በሰንደል አዲስ አበባ ገብተውና ባዶ እጅ የነበሩት ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በረገፉበት ሥርዓት ውስጥ ያግኙት የደም ገንዘብ እና ንብረት መሆኑን እስከነ አገልጋዮቻቸው ማጋለጥ ይገባል።
4ኛ/ከሬዲዮና ከቴሌቪዥን ሁኔታዎችን በየጊዜው እየተከታተሉ መልዕክቶችን ማስተላለፍ በፈጠራ የትግል ስልት መሳተፍ።
5ኛ/አቅም የፈቀደውን ሁሉ በገንዘብ ከአንድ ዶላር ጀምሮ ለማጠራቀም ኤንቨሎፕ አዘጋጅቶ ሲሞላ መላክ።
6ኛ/በአደባባይ ለሚደረጉ ሰልፎች ቅድመዝግጅት ስብሰባ ሲጠራ በስልቱ ላይ ለመነጋገር መገኘት በሰልፉ ወቅትም መዋጮ ሲደረግ ማዋጣት ።
7ኛ/አጋዚን ለመጋፈጥ በጣም ጥቂት ሰዎች የሚገኙበት ዋናው ምክንያት አለመተዋወቅና በሚተዋወቁ የግልጥረት ታጋዮች የሚካሄድ በመሆኑ ብዙዎቹ ሃሳቡን ቢደግፉትም “ያ ሰው” የመንግስት ሰላይ አለመሆኑን ምንም መረጃ ስለሌለ ፍራቻ እርስበ እርሳችን ላይ ይኖራል።መፍትሔው ግን ሁላችንም ከላይ የተገለፁትን ይዘን ከተገኘን በእለቱም የገንዘብ እርዳታ ካደረግን፤ጠላቶቻችን ሳይወዱ በግድ ውስጣቸው ጠላት ቢሆንም ይሰለፏታል።ይህን የሚያስተባብሩ እንደታማኝ በየነ(መገኘት የለባቸውም) ባሉ የሚታወቁ መሆን እና ለዚሁም እነሱ ልዩ አርማቸውን አድርገው የሚያስተባብሩ መሆን ይኖርባቸዋል። ለምን ከታምራዊ ፓርቲ ማስተባበርን አንጠብቅምና።ምንጊዜም በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ተሳታፊዎች ቢገኙ ከሥራ ሩጫ ጋር እንድንታገል ይረዳናል።
ስለዚህ በየሳምንቱ ትግላችንን እየተፈራረቅን በመቀጠል እንዳይቋረጥ ማድረግ ይጠበቅብናል። በአንድወቅት “ከኮዞፎዎች” የተማርኩት የትግል ስልት ነውና ይህ አጋጣሚ ኢትዮጵያ የራሷን የትግል ስልት እንድታቀጣጥል እግዚአብሔር ያደላትም ነው ብለን ከ”በቃ”አልፈን “አምርረን እንነሳ!!!።
****እንዳንዘነጋ፤በድቡሽት ላይ የተሰራ ቤት ምን እንደሚሆን አናውቅም የሚሉ ሰዎች ስለአሉ፦ እነሱ ልባቸው ድንጋይ አይናቸው ግንባር ሆኖ በቁማቸው ሞተዋልና ሕሊና የላቸውም።********
የኢትዮጵያ ሕዝብ በመራራ ትግሉ የሥጋ ትሎችን ይዋጋል፤በመጨረሻም ያቸንፋል!!!!
ድል ለኢትዮጵያ!!!



1ኛ/የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ሆኖ በመሃሉ አምባሻ(ኮከብ)ያለበት አይደለም፤መያዝም የለበትም።
2ኛ/ግፍ፣ጭቅቆና፣ዘረኝነት፣ኢ-ሰብዓዊነት፣መገደል፣መታሰር፣መገዛት እና ሌሎችም ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ለማቆም የትግራይ ጉጅሌው አገዛዝን “በቃ!!!በቃ!!!በቃ!!!”ብለናል ይህንንም በግል በተለያዩ አልባሳት ማሳየት አለብን።
3ኛ/በቴክኒዎሎጂ በመታገዝ ኢንተርኔትን ጨምሮ ለሕዝብ የምናውቀውን ማጋለጥ ይገባናል።መለስና አዜብን ጨምሮ በሰንደል አዲስ አበባ ገብተውና ባዶ እጅ የነበሩት ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በረገፉበት ሥርዓት ውስጥ ያግኙት የደም ገንዘብ እና ንብረት መሆኑን እስከነ አገልጋዮቻቸው ማጋለጥ ይገባል።
4ኛ/ከሬዲዮና ከቴሌቪዥን ሁኔታዎችን በየጊዜው እየተከታተሉ መልዕክቶችን ማስተላለፍ በፈጠራ የትግል ስልት መሳተፍ።
5ኛ/አቅም የፈቀደውን ሁሉ በገንዘብ ከአንድ ዶላር ጀምሮ ለማጠራቀም ኤንቨሎፕ አዘጋጅቶ ሲሞላ መላክ።
6ኛ/በአደባባይ ለሚደረጉ ሰልፎች ቅድመዝግጅት ስብሰባ ሲጠራ በስልቱ ላይ ለመነጋገር መገኘት በሰልፉ ወቅትም መዋጮ ሲደረግ ማዋጣት ።
7ኛ/አጋዚን ለመጋፈጥ በጣም ጥቂት ሰዎች የሚገኙበት ዋናው ምክንያት አለመተዋወቅና በሚተዋወቁ የግልጥረት ታጋዮች የሚካሄድ በመሆኑ ብዙዎቹ ሃሳቡን ቢደግፉትም “ያ ሰው” የመንግስት ሰላይ አለመሆኑን ምንም መረጃ ስለሌለ ፍራቻ እርስበ እርሳችን ላይ ይኖራል።መፍትሔው ግን ሁላችንም ከላይ የተገለፁትን ይዘን ከተገኘን በእለቱም የገንዘብ እርዳታ ካደረግን፤ጠላቶቻችን ሳይወዱ በግድ ውስጣቸው ጠላት ቢሆንም ይሰለፏታል።ይህን የሚያስተባብሩ እንደታማኝ በየነ(መገኘት የለባቸውም) ባሉ የሚታወቁ መሆን እና ለዚሁም እነሱ ልዩ አርማቸውን አድርገው የሚያስተባብሩ መሆን ይኖርባቸዋል። ለምን ከታምራዊ ፓርቲ ማስተባበርን አንጠብቅምና።ምንጊዜም በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ተሳታፊዎች ቢገኙ ከሥራ ሩጫ ጋር እንድንታገል ይረዳናል።
አዎን ማጋለጥ ይገባል!!!ማሳየት አለብን።
“… ኢትዮጵያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የዲሞክራሲ ሥርዓት ለመመስረት …ከገዳይ ልጆቿ ጋር የሞት ወይም የሽረት ትንቅንቅ ላይ ትገኛለች።
…” የሚለው መል’ዕክት አንዳንድ ጥያቄዎችን እንዳነሳ አስገድዶኛል:: በምንም መልኩ መተኪያ የሌላትን እናትን ልጆቿ ለምድን ነው ሊያጠፏት የሚፈልጉት? (ጸሃፊው እንደሚሉት) ይህ ጥያቄ ተገቢዉን መልስ ማግኘት አለበት:: አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ለዚህ ጥያቄ የራሱን መፍትኸ መልስ ሰጥቷል:: መፍትኸ የሚለውንም እርምጃ ወስዷል:: ብዙዎች ይህንን የገዢውን መልስና መፍትኸ አላመኑበትም ወይንም አልተቀበሉትም:: ከዚያም አልፈው የትጥቅ ትግላቸውን ቀጥለዋል:: ከፊሎች ጊዚያዊም ቢሆን ያገኙት ጥቅም እንዳለ ይገነዘባሉ::ያቺውኑ እንዳያጡ ሲሉ ሥልጣን ላይ ካለው መንግሥት ጎን ይሰለፋሉ::
ይህንን የተበታተነ የዜጎች ኃይል እንዴት ነው ወደ ትግሉ ማምጣት የሚቻለው? ለሚለው ጥያቄ ጸሀፊው መልስ አልሰጡም::የፈጠራም ይሁን ታሪካዊ መሰረት ይኑረው አይኑረው በሕዝባችን መካከል በዘር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር ለችግራችን እንደ መፍትኸ ተወስዶ እየተሰራበት ይገኛል:: …የምንታገልለት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የያንዳንዱን ዜጋ ያልተሸራረፈ መብት የሚያስከብር መሆኑን እና ይህ ደግሞ የብሄር ብሄሰቦችን መብት የበለጠ የሚያስከብር እንጂ የሚጋፋ አለመሆኑን በግልጽ ዜጎች ሁሉ አውቀው ለዚሁ እንዲዋጉ በሰፊው መብራራትና አንዴትስ ሥራ ላይ አንደሚዉል መታወቅ አለበት..”
ሌላው ጥያቄዬ ችግራችን የውስጥ ችግር ብቻ ነውን? (ጸሀፊው አንደሚሉት) የሚል ነው:: ሀገሪቷ ካለችበት ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ የተነሳ በርካታ የውጭ ጠላቶች አሏት የሚል አምነት አለኝ:: ዛሬ ሥልጣን ላይ ያለውን ቡድን ለዚህ ያበቁት የውጭ ኃይላትም ከፍተኛ አስተዋጽ’ኦ አድርገዋል:: አናም ይህንን የውጭ ኃይል መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም:: ቢቻል ይህንን ኃይል ከጎናችን ማሰለፍ ካልተቻለ አጁን “ሰብስቦ” የሚቀመጥበትን መንገድ መተለም አለብን:: የትግሉ ፋና ወጊዎች ይህንንም ቢያስቡበት የሕባችን ትግል መና አንዳይቀርና በቀላሉም ካሰበው ግብም ይደርሳል የሚል አምነት አለኝ::