ለሚኮበልሉ የህወሃት/ኢህአዴግ ልዑካን በሙሉ፡-ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች እንወክለዋለን ያላችሁትን “መንግሥት” ዓላማ በማንገብ ስብሰባ ለማድረግ ስትሞክሩ እንደነበር በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ ይህ 52 ግለሰቦችን ያካተተው ቡድን ባሳለፍነው የሳምንት መጨረሻ በበርካታ የአሜሪካ ከተሞች የፕሮፓጋንዳ ዘመቻውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ በየከተማው የደረሰበትን ከፍተኛና ጠንካራ ተቃውሞ ከማንም በላቀ መልኩ የተመለከታችሁና በቅርበት የተከታተላችሁት እናንተ ናችሁ፡፡ በውጪ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ የመናገር፣ የመሰብሰብ፣ ሃሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱ የተከበረ በመሆኑ ይህንን ዓይነት ተቃውሞ አቀረበባችሁ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ወገናችን ከዚህ ዕድል ጥቂቱን ቢያገኝ ሊያሰማችሁ የሚችለውን ተቃውሞና ተግዳሮት ምን ያህል ጠንካራ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያቅታችሁም፡፡ የ1997 ምርጫና ለውጥ የናፈቀው ታሪካዊው “የሕዝብ ሱናሚ” የቅርብ ጊዜ ትዝታዎች በመሆናቸው በዚያን ወቅት የታየውን የሕዝባችንን ግልጽ ተቃውሞ የምትዘነጉት አይመስለንም፡፡
በአገራችን ውስጥ ላለፉት 20 ዓመታት የተካሄደው የመብት ረገጣ፣ ጭቆና፣ አፈና፣ ግድያ፣ ወዘተ አሁንም የቀጠለ በመሆኑ ይህ ደግሞ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ቀጣይነት እንዲኖረው እያደረጋችሁ ያላችሁት እናንተ መሆናችሁ አትዘነጉትም፡፡ የሥርዓቱ ደጋፊና አቀንቃኝ በመሆን እስካሁን ያደረጋችሁት አገር ቤት ያለው ሕዝባችንም ይሁን እኛ በውጪ የምንገኝ ጠንቅቀን የምናውቀው ነው፡፡ እንዲሁም የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ወደፊት በማስረጃነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ሰነዶች በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የሰበሰበ መሆኑንና አሁንም ከምንጊዜውም በበለጠ ሁኔታ በተቀናጀ መልኩ በእያንዳንዱ በኃላፊነት ላይ በተቀመጠ ግለሰብ ላይ እየሰበሰበ መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ሰላም፣ እኩልነት፣ አንድነትና ዕርቅ የሰፈነባትን አዲሲቷን ኢትዮጵያን ለመመሥረት የሚታገል እንደመሆኑ መጠን የዚያኑ ያህል ደግሞ ወንጀለኞችን ለፍርድ በማቅረብና መረጃዎችን በመሰብሰብ በኩል አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል፡፡ ስለዚህ በቅርቡ ይህ በአገራችን ላይ የሚካሄደው ግፍ ማቆሚያ በሚደረግለት ጊዜ የእናንተና የመሰል ጓደኞቻችሁ መጻዒ ዕድል ምን እንደሚሆን መገመት የሚያቅታችሁ አይመስለንም፡፡
ከተለያዩ አቅጣጫዎች እንደምንሰማውም ሆነ አንዳንዶች በግልጽ ለጋራ ንቅናቄያችን እንደሚነግሩን በኢህአዴግ ውስጥ በአባልነት የተመዘገቡ የሥርዓቱ አራማጆች የሚፈጽሙት ተግባር በሙሉ አምነውበት እንዳልሆነ ነገር ግን የእንጀራ ጉዳይ በመሆኑ ወይም አማራጭ ከማጣት የተነሳ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ከእናንተም ውስጥ ከዚህ ጎራ የምትሰለፉ ጥቂቶች እንዳልሆናችሁ እናምናለን፡፡ መውጫ መፈለግ ተገቢ ነገር ቢሆንም መውጫውን ማግኘቱ ደግሞ አስፈላጊም ነው፡፡ ስለዚህም ነው ይህንን ዕድል እንድትጠቀሙበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ልናሳስባችሁ የምንወደው፡፡ እስካሁን የፈጸማችሁትን ስህተት መሰረዝ አይቻልም – ጊዜው አልፏልና፡፡ ከዚህ ወዲያ ያለው ግን በእጃችሁ ያለ በመሆኑ አሁን የሚሰጣችሁን ዕድል ሳትጠቀሙበት ቀርታችሁ ወደቀድሞው ሥራችሁ በመመለስ ሕዝባችንን ለመበደል የምታደርጉት ቀጣይ ሥራ በዕርቅ ብቻ ለማለፍ የሚያስቸግር ያደርገዋል፡፡ ለዚህም ነው የጋራ ንቅናቄያችን ይህንን ዕድል ተጠቅማችሁ አሁን ማቆሚያ እንድታበጁለት ጥሪ የሚያደርግላችሁ፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ስትመለሱ ሳይሆን እዚሁ እያላችሁ ይህንን የተቀደሰ ውሳኔ በማድረግ ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍትሕ እና አንድነት የሚሰፍንባትን አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመመሥረት የሚደረገውን ትግል ዛሬ ለመቀላቀል ውሳኔ አድርጉ፡፡
በመሠረቱ አኢጋን የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ከየትኛውም የፖለቲካ ቡድን ጋር የወገነ ባለመሆኑ ነገር ግን “ከዘር ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ የሚሰጥባት” አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመመሥረት የሚታገል በመሆኑ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በዕኩልነት መነጽር የሚያይ ስለሆነ እናንተንም ከሌላው ኢትዮጵያዊ ለይቶ የሚያይበት ምንም ምክንያት የለውም፡፡ ከጋራ ንቅናቄያችን መሠረታዊ መርሆዎች መካከል አንዱ በአገራችን ዘላቂነት ያለው ዕርቅ መስፈን እንደመሆኑ ለዚህ ተግባር ራሳችሁን በመስጠት እየሞተ ያለውን አገዛዝ ትታችሁ ለራሳችሁና ለሌሎች ነጻነት በአንድነት መታገል እንድትችሉ ነው ይህንን ጥሪ የምናቀርብላችሁ፡፡
በተለይ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ በተለያዩ የሰሜንና የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች እየተካሄደ ባለበት ወቅት ይህ ለውጥ ወደአገራችን መዛመቱ የማይቅር እየሆነ የመጣ ሃቅ ነው፡፡ ጥያቄው ይህ አሁን የተሰጣችሁን ዕድል ንቃችሁ ለውጡ እውን በሚሆንበት ጊዜ ሕዝቡ ከያላችሁበት እያደነ ሲያወጣችሁና ያላሰባችሁትና ያልጠበቃችሁት በሙሉ ሲከሰት “እኛ እኮ ሕዝቡን ለማስተዳደር ኮንትራት የፈጸምን መስሎን ነበር?” ልትሉ ነው ወይስ የተለመደችውን “እኔ እኮ ትዕዛዝ ፈጻሚ ነኝ፤ የታዘዝኩትን ነውን’ጂ የፈጸምኩት ምንም ያደረኩት ነገር የለም“ ልትሉ ነው? በአገራችን ንጉሣዊው ሥርዓት እንዲሁም የደርግ አገዛዝ በወደቁበት ጊዜ የሆነውን መለስ ብሎ ማሰቡ ትልቅ ትምህርት የሚሰጣችሁ ይመስለናል፡፡ አንድ በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው ነገር “ታሪክ ራሱ ይደግማል ከዚያ የማይማሩ ግን ደንቆሮዎች ናቸው“ የሚለው አባባል እውን እንደሚሆን ሲሆን እናንተ ግን ከታሪክ ተምራችሁ ተገቢውን ውሳኔ የማድረግ ቁርጥ እርምጃ እንደምትወስዱ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
ለ40 ዓመታት የጋዳፊን ሥርዓት ሲደግፉና ሲያራምዱ የነበሩት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጊዜያቸው በደረሰ ጊዜ ከሕዝባቸው ጋር እንደቆሙ ሁሉ እናንተም ውስጥ እንዲህ ያለው ከሕዝብ ጋር አብሮ የመሰለፍ ፍላጎት ዳብሮ ፍሬ የሚያፈራበት ወቅት አሁን በመሆኑ ዛሬ ውሳኔያችሁን እንድታደርጉና “ከእንግዲህስ በቃ“ በማለት ራሳችሁን ነጻ አውጥታችሁ የእናንተን አርአያ ለመከተል ለሚሹ ሁሉ ፋና ወጊ እንድትሆኑ በጥብቅ ልናሳስባችሁ እንወዳለን፡፡ በአገራችን “ስም ከመቃብር በላይ ይውላል“ እንደሚባለው ዛሬ ይህንን ውሳኔ ብታደርጉ በታሪካችሁ ላይ የሚዘከረው እስካሁን ያደረጋችሁት ብቻ ሳይሆን ከዚህ በኋላ የምታደርጉት በመሆኑ ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለልጆቻችሁና ለቀሪው ዘራችሁ በማሰብ ይህንን ቁርጥ ውሳኔ የምታደርጉበት ጊዜ አሁን ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚ በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የምናስተላልፈው መልዕክት ቢኖር እነዚህ ግለሰቦች ወደእኛ ለመምጣት ውሳኔ በሚያደርጉበት ጊዜ እነርሱን ለመቀበል የቅድሚያ ዝግጅት እናድርግ፡፡ ከስሜት እና ከደመኝነት ባለፈ መንፈስ ጉዳዩን እንመልከተው፡፡ ለአገራችን የሚበጃትን በሰከነ ሁኔታ በማሰብ ለዘላቂ ሰላምና ዕርቅ ራሳችሁን እንድታዘጋጁ የጋራ ንቅናቄያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
በመጨረሻም እናንተ በዚህ የልዑካን ቡድን ውስጥ የምትገኙ በሙሉ ይህንን ጥሪ ተቀብላችሁ ከብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ጋር ለመቀላቀል ውሳኔ በምታደርጉበት በማንኛውም ጊዜ ከጋራ ንቅናቄያችን ጋር በስልክም ሆነ በኢሜይል ልትገናኙ እንደምትችሉ በግልጽ እናሳውቃለን፡፡ ከዚህ ሌላ አሁን ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ አገዛዙ የሚወገድበትን መንገድ በህቡዕ ለመሥራትና እንቅስቃሴውንም ከውስጥ ሆኖ ለመደገፍ የምትፈልጉ ከእናንተ መካከል እንዳላችሁ የማይካድ ሃቅ በመሆኑ ይህንን ሥራችሁን እንድትቀጥሉና ከጋራ ንቅናቄያችን ጋር የዘወትር ግንኙነታችሁን በመቀጠል መረጃ በማቀበልም ሆነ ሌሎች ምስጢራዊ ሥራዎችን የመሥራት ተግባራችሁን እንድትገፉበት እናሳስባለን፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ይህንን ጥሪ እምቢ በማለት የማንአለብኝነት ተግባራችሁን ለመቀጠል የምትወስኑ ሁሉ በተገቢው ጊዜ ለፍርድ የምትቀርቡ ብቻ ሳይሆን ይህ ጥሪ ራሱ ለእምቢተኝነታችሁና ጸረ-ሰላም ለመሆናችሁ ማስረጃ ሆኖ የሚቀርብባችሁ መሆኑን እንድታውቁት በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ፈጣሪ አገራችንን ይባርክ፤ ለእናንተም ድፍረቱና ልቦናውን ይስጣችሁ፡፡



Whey the tyrants at last give up their power dead or alive, it is the supporters who have to live with their guilt with their brothers and sisters whom they are now terrorizing. I hope you will take this opportunity and say no to state terrorism in ETHIOPIA. BEQA/GAYE
ተማር ልጄ…..ተማር ልጄ…..ተማር ምዽረ ሆዻም አጋሰስ የወያኔ ደጋፊና አቀንቃኝ ሁላ !!!
እውነት ነው
ይህ ሀሳብ ግሩም ሀሳብ ነዉ::
መለስ ወርቃማ ጊዜ አመልጦታል::
ወያኔ ለኢትዮጲያ አስቦ አያዉቅም::
መለስ በምርጫ 97 ስልጣን በክብር ለአሸናፊዉ
ማስረከብ ቢችል ኖሮ ከዘያ በፊት ለተሰሩ ወንጀሎች
ይቅርታ ለማግኘት ይችል ነበር::
ከትላልቆቹ ወንጀሎች ኤርትራን ማስገንጠል
በኢትዮ ኤርትራ የተሰረዉ ክደትና የጋምቤላ
ጭፍጨፋ ይገኙበታል::
መለስ ዜናዊ በብዙ ይቅር በማይባሉ ወንጀሎች
የተጨማለቀዉ ከምርጫ 97 ወዲህ ነዉ::
በምርጫ 97 የተሰራዉ ወንጀል ብቻዉን የሰዉን ልጅን
ለማጥፋት የተወሰደ መንጀል ነዉ::
ምርጫ 97ን ተከትሎ ነዉ ሶማሌን በመዉርር 3 ትላልቅ
ወንጀሎች የተፈፀሙት::
► ለኢትዮጰያ ህዝብና ሰረዊት ከፍተኛ ውርደትን
የሚያመለክት ወክልና ጦርነት ሱማሌን ወረዋል::
► በወረራዉ ወቅት የጦር ወንጀላ ተፈፅመዋል::
● የደሃዉ የኢትዮጲያ ልጅ ወታደር አስከሬኑ
እንደወረቀት እየተቃጠለ መሬት ላይ ስጎተት ዓለም
በቴሌቢዥን የተከታተለዉ ነዉ::
● በወቅቱ ሰራዊቱን ላለማሰወጠት ላሳዬዉ እቢሪት
ያሰጠይቀወል::
► በኦጋዴን የተፈፀመዉ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ወንጀል
ከምርጫ 97 በሁላ ነዉ::
ተቆጥረዉ የማልቁ ወንጀሎች ተፈፅመዉል::
► የአገር ሀብት ተዘርፎ ወደ ዉጭ በመሸሽ ለይ ነዉ::
► የአገርቱ ለም መሬት ተቆርሶ ለሱዳን ስለሚሰጥበት
ከኢትዮጲያ ህዝብ ጀርባ ክህደት ስፈፀም ቆይተዋል::
► አሁንም ደቡብ ኢትዮጲያ መዓት እየወረደበተ ነዉ::
● ደኖችዋ አይተጨፈጨፉ ነዉ::
● 500 ሺ ሄክታር መሬት በላይ ከመዠንገር ህዝብ
ተቀምቶ ለህንድ ባለሀብቶች እንድሸጋሸግና
የጥንታዊት ኢትዮጲያ የአከባቢዉም ተፈጥሮ
እንደበለት ተፈርዶበታል::
● ለህንድ ባለሀብት $6 ዶላር ለሚቀጥሉት 50 ዐመታት
የመቸብብ ወንጀል በማን አለብኝነት አይተሰራ ነዉ::
► ከአድስ አበባ ዩኒበረሲት ከፍተኛ ዝርፊያና ሙስና የመለስ
የቅረብ ሰዉ በሆነዉ አንድርያስ በቡድኑ አሳፋሪ ወንጀሎች
እየተፈፀሙ ናቸዉ::
የታወቁና በመረጃ የተደገፉ የመለስ አገዛዝ ወንጀሎች ተዘርዘረዉ የሚያልቁ አይደሉም::
ሕዝባዊ አመፅ ቢነሳ የሚሰራዉ ወንጀል እሰካሁን የተሰሩትን
ከማጠፍ ወደሁላ አይልም:: በአሁኑ ሰዓት በመለስ ሳንባ
በመተንፈስ ላይ ያሉት መልዕክተኞቹ ይህን ጥሪ ለመቀበል ቢችሉ
እስካሁን ከተሰሩ ወንጀሎች ለመተረፍ ዕድል ባይኖራቸዉም
በመደገስ ላይ ካለዉ መጠነ ሰፊ ወንጀል እጃቸዉን በመታጠብ
ቢያንስ ቤተሰቦቻቸዉ ባልበሉት ዕዳ ሳይጠየቁ መልካም ዕንቅልፍ
እንድተኙ ራሳቸዉን አሳልፈዉ ሊሰጡ ይችላሉ::
ይህ አያስጨንቀንም:: ከፈለጉ በፕሮፌሰር መስፍን ቁዋንቁዋ
በወንድ በር መዉጣት ይችላሉ::
ለራሳቸዉ ይወቁበት!
ካልፈለጉ በሕዝባዊ ማዕበል መወገድ አለባቸዉ::
የመለስ በረከት ወንጀለኛ አገዛዝ ይወገዳል!
መከባበር ጠፍ በስነ-ስርአት መወየት የለም ማለት ነው…….ወይ ሐበሻ ሲባል መናቖር ሲወድ
ተምረህ ሙተሃል ጉርኛ ኢብሪተኛ ብትማርማ ኖሮ ባልተሳድብክ ነበር :
በርግጥ ወያኔ ተምሮ ህገር የሚመራበት ጭንቅላት ነው ያለው አንተግን አልተማርክም እንጂ ብትማርም ሀገርን መምራት አይደልም ቤትህ መምራት አትችልም::
ውዽ የእትዮፒያ ህዝብ ሰላም ለሁላችኁም ድል በክርብ እና መታለን መለስ መሞችህ ደርሳል
በቃሉ አይጥ-ና የወየ ደጋፊወች low IQ ያላቸወንደሆኑ ነው የኒታወቀው እነዚያ “ኮረኔል ጀነራል” እይለ ቆርቆሮ ምሳይ ትክሻቸው ላይ የለጠፈላቸው በደንብ ባማርኛሆነ በትግርኛ በደንብ ማንበብና መጻፍ የትማሩት አዲስ አበባ ከገቡ በሁዋላ ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የምትለው ስሞኦን ኢሃፓም ሲቀላቀል ገና የከፍተኛ ደረጃ አዲስ ምልምልል ነበር መለስ የኮሌጅ የገና ምሩቅ ነው አቶ አይጥ-ና ለምን ጺው–ጺው –ጺው ትላለህ
@በቃሉ ይጥና
በቃሉ ወያኔማ ተማርኩ በሎ ከኤርትራ ጋር የድንበሩ ጉዳይ ፍርድ ኮምሽኑ ብይኑን ሲያወጣ ማንበብ ያቃታቸው መሪዋችህ በተለይ
ስዩም መስፍን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ህዝባችንን ከማሳሳት ለጭፈራ ዳርገውታል እሱም አልበቃ ብሎት ለሬድዮና ለቴለቭዥን
ያንን ሲናገር ምን ያህል የእውቀት ችግር እንዳለ አንተም ምትክደው አይደለም:: ሌላው ደግሞ በምርጫ 97 በነበረው በወያኔና
ቅንጅት የሚዲያ ዲቤት ህዝባችን በመሃይሞች አንመራም ብሎ ነው ቅንጅትን የመረጠው ስለዚህ ወደን አይደለም ምንሳደበው
የናንተ አላዋቂ ሳሚነት ስላስጠላን ነው:: ደግሞም ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ ነውና ወይ ለሙህራን ቦታውን መልቀቅ
ወይም ስድብ ና ወቀሳን መቀበል መቻል አለብህ::