ግንቦት 2ዐ እና የጠፋው 8.5 ቢሊዮን ዶላር እስክንድር ነጋ (ካለፈው ሳምንት የቀጠለ)
ቅዳሜ ረፋዱ ላይ ጀምበር ለመጥለቅ ዳር ዳር ትላለች፡፡ የግንቦት አናት ሰርሳሪ ፀሐይ ዘንድሮ በደመና ለዝቦ ነው የሰነበተው፡፡ ከእኩለ ቀን አንስቶ የከተማዋ አየር ቀዝቀዝ ብሎ ውሏል፡፡ አንዳንዴም መለስተኛ ካፊያ መጠት ሄደት ይላል፡፡
የብሥራተ ገብርኤል ሰፈር ነዋሪ እንደወትሮው የግቢ በሩን ቀርቅሮ በየቤቱ ውስጥ ተከቷል፡፡ ትናንሽም ትላልቅም ቤቶች በረዣዥም የአጥር ግንብ የተከለሉ ናቸው፡፡ በቁራሽ የእርሻ መሬት ደም ሲቀባባ የኖረ ሕዝብ፣ ከቤቱ ይልቅ አጥሩን አጥብቆ ይሰራል፡፡ ውጤቱ ጥሩ አልሆነም፡፡ ረዣዥሞቹ አጥሮች በነባሩ የኢትዮጵያዊያን ማሕበራዊ ሕይወት ላይ የቆሙ ግድቦች ሆነዋል፡፡ የሰፈርተኛው ትስስር እንደ ፈረንጆቹ የላላ ለመሆን ትንሽ ነው የቀረው፡፡ የጥንቱ አብሮነት ለአዲሱ ባይተዋርነት ሸብረክ ብሏል፡፡
እንዲህም ሆኖ፣ ኢትዮጵያዊያን አሁንም በሰርጎቻቸው፣ በለቅሶቻቸውና በአምልኮታቸው እንደተሳሰሩ ናቸው፡፡ የጥንቱ ዕድር አልተበጣጠሰም፡፡ የብስራተ ገብርኤል ነዋሪ አብሮ ይሰርጋል፣ ተደጋግፎ ይላቀሳል፣ ተሰባስቦ ፈጣሪውን ያመልካል፡፡
የቅዳሜው የእድር ጡሩንባ ግን፣ ሰፈርተኛውን በእጅጉ ግራ አጋባ፡፡ ሰዓቱ ተዛብቷል፡፡ ጥሩምባው አየሩን የሰነጠቀው ከረፋዱ 12 ሰዓት ገደማ ነው፡፡ ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ የእድር ጥሪ ከሌሊቱ 11 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት ነው፡፡ ዛሬ ምን ተፈጠረ? ነዋሪው በጉጉት ከየቤቱ ብቅ አለ፡፡
«እድርተኞች፣ ነገ፣ ግንቦት 2ዐ፣ ከጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የሕዳሴውን ግድብ አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ ስለሚደረግ እንድትገኙ ተብላችኋል፣» እያሉ አደበላለቁት የእድሩ ለፋፊ፣ ትከሻቸው ላይ ባንጠለጠሉት የድምፅ ማጉያ፡፡
ኧረ፣ እድር ከቶ ስለሕዳሴው ግድብ (የዓባይ ግድብ) ምን አገባው? ሰልፉስ እውነት ለግድቡ ነው ወይስ ለኢሕአዴግ ድል? ማን ይጠየቅ? ማንስ ይመልስ? የብስራተ ገብርኤል ነዋሪ ከንፈሩን በቁጭት እየመጠጠ ወደየቤቱ ገባ፡፡ ነውር የጠፋበት ዘመን፡፡
ቀበሌዎች በበኩላቸው፣ እያንዳንዱን በር እያንኳኩ ወረቀት በትነዋል፡፡ «ከ18 ዓመት በላይ የሆነ እንዳይቀር» ብለዋል፡፡ በግዴታ ይሁን በውዴታ አልለየም፡፡ በትምህርት ቤቶችም ሲቀሰቀስ ሰነባብቷል፡፡ ተማሪዎቹ ግን ከ18 ዓመት በታች ናቸው፡፡ ግንቦት 2ዐ አልተነሳም፡፡ ለዓባይ ግድብ እንዲወጡ ነው የተነገራቸው፡፡ «ገለልተኛ» የሴቶችና የወጣቶች ማሕበራት ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ ረጭተዋል፡፡ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አባላት በቡድን እንዲወጡ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡ የቀረ ወየውለት፡፡ ለእነዚህ ምክንያት መንገር አላስፈለገም፡፡ በቀጭን ትዕዛዝ ግልብጥ ብለው ይወጣሉ፡፡ ዝንፍ ቢሉ ጉሮሮዋቸው እንደሚዘጋ ያውቁታል፡፡ ለጥቂት ቀናትም የመንገድ ለመንገድ ቅስቀሳ ተደርጓል፣ ትርፉ ከሕዝብ ግልምጫ ብዙም ባያልፍም፡፡ ሆኖም፣ አንድም ሰው ትርጉም አለው፡፡ በእንጥብጣቢ በርሜል ይሞላል፡፡ ስለዚህም፣ በአራቱም ማዕዘን ተወጥሯል፡፡
የግንቦት 2ዐ እለት፣ የማይናቅ ቁጥር ያለው ሕዝብ በመስቀል አደባባይ ተገኝቷል፡፡ አንድ ሚሊዮን ተብሎ የታለመው ግን ቅዠት ሆኖ ቀርቷል፡፡
ግልፅ ባልሆነ ምክንያት፣ ሰላማዊ ሰልፉን በቶሎ ለመበተን ጥድፊያ ነበር፡፡ በሁለት ዓረፍተ ነገር የምትዘጋ ጥያቄን ግማሽ ሰዓት የሚያላዝኑባት መለስ ዜናዊ፣ የአምስት ደቂቃ ብቻ ንግግር አደረጉ፡፡ በ2ዐ ዓመታት ውስጥ አጭሩ ንግግራቸው መሆኑ ነው፡፡ አዲስ ክብረወሰን፡፡ (ብዙዎች ልምድ እንዲያደርጉት ተመኝተውላቸዋል፡፡) በጥቅሉ፣ ሰላማዊ ሰልፉ ሁለት ሰዓታት እንኳን አልቆየም፡፡
ለምን?
ተቃውሞ ስለተፈራ፡፡ መጀመሪያውንም፣ ፈራ ተባ እየተባለ የተጠራ ሰልፍ ነበር፡፡ ሕዝብ ወደ አደባባይ ገብቶ አልለቅም ቢልስ? የግብፅ ታሂርር አደባባይ ተፈጠረ ማለት አይደለም እንዴ? ዘንድሮ ሕዝብን በመጨፍጨፍ መበተን አይቻልም፡፡ በአረብ ሀገራት አይተነዋል፡፡ አደባባይ የተቀመጠ ህዝብን ደግሞ መጨፍጨፍ አያመችም፡፡ ኢሕአዴግ መውደቂያውን አመቻችቶ ነበር፡፡ አደጋው እነመለስን አልጠፋቸውም፤ ብዙ ያውቃሉ፡፡ በሕልውናቸው ቁማር የተጫወቱት፣ አጋጣሚውን መጠቀም የሚችል የተደራጀ ሕዝብ የለም ብለው ስላመኑ ነው፡፡ አልተሳሳቱም፡፡ የሞከረ እንኳን አልነበረም፡፡ ሰልፉ ቶሎ የተበተነው ለምናልባቱ መሆኑ ነው፡፡ ማንም ስለምንም መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን አይችልም፡፡ ያቺ ቀዳዳ መደፈን ነበረባት፡፡
ኢኮኖሚዬ 11 ከመቶ አደገ የሚል መሪ ፈገግታ ከፊቱ ሊጠፋ አይችልም፡፡ ከዚህ በላይ ብዙ ሊፈልግ አይችልም፡፡ የመለስ ፊት ግን ብዙም ሳይፈታ ነው ሰላማዊ ሰልፉ የተጠናቀቀው፡፡ ሐሳባቸው ሌላ ቦታ የሄደ ይመስላል፡፡ እርግጥ፣ የሀገር መሪ ሆኖ የሚታሰብ አይጠፋም፡፡ ቀልብን የሚሰልብ ጉዳይ የሚያጋጥመው ግን፣ አልፎ አልፎ ነው፡፡
ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጋር ሰሞኑን ተጋፍጦ የሚገኘው ጉዳይ ቀልብን ሊስብ የሚችል ብቻ ተብሎ ሊታለፍ የሚችል አይደለም፡፡ አንድ ደረጃ ከፍ ይላል፡፡ ቅሌት ቢባል ይመጥነዋል፡፡ ፈረንጆች Scandal ይሉታል፡፡ መለስ ጭው ብለው የጠፉ ቢመስሉ አይገርምም፡፡
8.5 ቢሊዮን ዶላር ከባድ ገንዘብ ነው፡፡ ዘንድሮ እንኳን ለኢትዮጵያ ለአሜሪካ ይከብዳታል፡፡ ላለፉት 5 እና 6 ዓመታት በኢኮኖሚው ተዓምር አስመዝግበናል እየተባለ፣ ሐገራችን በዚህ ዓመት ወደ ውጭ ከምትላካቸው ምርቶች የምትጠብቀው ከ2 ቢሊዮን ዶላር ትንሽ ነው ከፍ የሚለው፡፡ 8.5 ቢሊዮን ዶላሩ ከ4 ዓመታት ድምር ልፋታችን ጋር የሚስተካከል ነው፤ እንደ ሐገር ሆነን፡፡ ታዲያ፣ ይሄ ቅሌት መባል ይነሰው እንዴ?
ከኢትዮጵያ ላይ ስለተዘረፈው 8.5 ቢሊዮን ዶላር ዛሬ ብዘረዝር የቀባሪ አርጂ ያደርገኛል፡፡ ሁሉም ያውቀዋል፡፡ ዘረፋው ዜና አይደለም፡፡ ዜናው በተባበሩት መንግሥታት በኩል ለመውጣት መብቃቱ፡፡ ጥርጣሬያችን አሁን በማስረጃ ተደግፏል፡፡ ኢሕአዴግ ከዚህ በኋላ ማስረጃ ሊጠይቀን አይችልም፡፡
ከ8.5 ቢሊዮን ዶላሩ ላይ ከ6ዐ እስከ 65 ከመቶ የሚሆነው ገንዘብ ከሀገር የወጣው ከውጭ ንግድ ጋር በተያያዘ መልኩ እንደሆነ በተመድ ሪፖርት ተቀምጧል፡፡ የነጋዴዎች እጅ አለበት ማለት ነው፡፡ ይሄ ብዙ አያከራክርም፡፡ ብዙ ሚሊዮን ዶላሮች የሚያወጡ መኖሪያ ቤቶች በአሜሪካ የገዙ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ንግዳቸው ግን ሙሉ ለሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ገንዘብ እንዳሸሹ ግልፅ ነው፡፡ ድምር አቅማቸው ግን እምብዛም እንደሆነ የአደባባይ ሚስጢር ነው፡፡ (የአላሙዲንን አቅም አያካትትም፡፡) በጣም ተለጥጦ ከ2 እና ከ3 መቶ ሚሊዮን ዶላር አይዘልም፡፡ እንዲያውም፣ 4ዐዐ ሚሊዮን ዶላሩን እንኳን በእነሱ ላይ ብናሳብብ፣ 8 ቢሊዮን ዶላር ይቀራል፡፡ ለዚህ ገንዘብ ተጠያቂዎቹ በስልጣን ላይ ያሉት አንዳንድ የኢሕአዴግ መሪዎች ናቸው፡፡ ሌላ ተጠርጣሪ የለም፡፡ ያለ ቀይ መስመር ደሃ ሀገራቸውን አድምተዋል፡፡
ግንቦት 2ዐ እለት የመለስን ቀልብ የሳበው ይህ ጉዳይ ነበር ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ መንግሥታቸው ብዙ ብዙ ጥያቄዎች አሉበት፡፡
ፀሐፊውን ለማግኘት serk27@gmail.com



We expect reconciliation of figures with our ‘The Federal ethics and anti corruption Commission of Ethiopia ‘.
I invite every body to read the commission report for the year 2009/2010 on their website .They haven’t even done anything worth covering their annual budgetary expendture(15.3 mio birrs for salary and operating expenses)
ወያኔ ከመነሻው kleptocrat መሆኑ በግልጽ የሚታወቅ ነው the rule of thieves
As usual, u are great & honest. We will never ever forget your contribution.
10Q
እኔ የሚገርመኝ እስክንድር ለመሆኑ እንዲህ እንዳንተ ልበ ሙሉነትን የተቸረ ጀግና አለ? በዛ ላይ የጽሁፎችህ ሃቅ እናም አዝናንኝነታቸው::ስለስርዓቱ ዘራፊነት መቸም ዓይናችንም ሆነ ጆሮአችን ያቅለሸለሸው ቢሆንም ዝርፊያውን ከማስቆም እና ይገባናል ከማለት ይልቅ በርሃብና ፈርሃት መሞትን መርጤን ሞቶልን ነጽ የሚያወጥንና ሃብታችህንን የሚያካፍለንን የህልም ጀግና እየናፈቅን እንደመሸብን መጭለሙ ነው::ባለጊዘወች እንደሆኑ እንኩአንስ ሰውን እግዘእብሄርን አላፍርና አልፈራ ብለው ስድብም ምክርም የሚሰሙ አልሆኑም:: ለነገሩ እነዚህ ባለጊዘወች በታሪካችው ችግር ርሃብና ፈተና ይችላሉ እንጅ የጥጋብ ነገር አይሆንላቸውምና መጭረሻውን ያሳምርላቸው ብለን እንጥፅልይላቸው:: ካልሆነ ርሃብና ስደት ታሪኩ የሆነ ህዝብ እንዴት የወገኑ ሰቆቃ አይገባውም? እንደነበረ ያለፈና የሚያልፍ የልምና ማስተዋል እምቢ ካሉ ከቀደመው ታሪካቸው ወደባሰ ፍዳ የሚገቡበት ቀን ሩቅ አይሆንምና ለሁሉም እግዘእብሄር ይማራቸው
Dear Brother,
I wish I could comment in Amharic but I couldn’t type, it needs more time to learn. But I would like to pass my appretiation and thank you note.
You write several issues which really has potential to lead us to one focus than any other thoughts which are comming up here. I really agree with my friends comment you need to take care of yourself because we have no such brave people now a days who are willing to pay their life on such a wild government being there and confronting them with no mask. Really we need you my bro that is the only thing what I would like to say because I am Christian and the Bible says Money is lord for the person who choose it equivalent to our Almight Lord. Therefore, we can not take it as a simple example becaues it is Jesus who says this not any ordinary person. Therefore if someone choose money like his god what do you expect nothing can be taken of for the sake of worship his god. I promis to pray for you.
Blessings,
ለመሆኑ የአዲስ አበባ ህዝብ አለ ? ምኑ ነው እንዲህ ያደነዘዘው ? ያሳዝናል ግብጾች እንኽዋን ታሪክ ሲሰሩ ሃበሾች ተኝተው ያንቀላፋሉ::
God Bless You Eskender
አቶ እስክንድር እንደምን ሰነበትክ ምናልባት የቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቻይና የሔዱት ከደሃው ሕዝብ የዘረፉትን ገንዘብ ቦታ ቦታ ለማስያዝ ይሆን::
If we had few more like Eskinder, we would have our “rage” bursting on weyane. Thank you, Eskinder. Ethiopia will never forget the courage you have shown against the enemy, and the contribution you have made for the struggle.
In fact, I believe the UN estimate of $8.4 billion appears understated. Weyane has strolen more than that.
ይህ መንግሥት የተባለው በገንዘብ ብቻ ሳይሆን የዘቀጠው:-በደም የተጨመላለቀ ለመሆኑ አይደሉም ኢትዮጵያውያን ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ያደባባይ ሚሥጥር ነው::ሚሥጥር ሊያደርጉት የሚፈልጉትም ፍርፋሪ የሚበሉትና ደሙን የሚልሱት ጀሌ ሆዳሞች ናቸው:-ለሁሉም ግን ጊዜው እየከዳቸው ነውና በትግል ፀንተን ያንን የተስፋ ቀን እንጠብቅ::አቶ እስክንድር ነጋም የሳለው ብዕርህ ይባረክ::
ኾሮቦኦ
You do not have to ask Eskender where the money is .If you are not one of those go-betweens of Azeb Mesfen and money laundering off- shore companies,Please ask your kins.
As to priorities,that is all we are concerned with.Free from starvation for all Ethiopians.Self-sufficiency in food production.The rest will follow.
The only difference between you and eskinder is that you are hodam and does not care about Ethiopia and Ethiopians while Eskinder Nega is sacrificing his life for the freedom of us all including the Tigreans who are equally languishing under woyane state terrorism
You woyane what are you doing here! This website is for the voiceless.you go to meles propaganda machine &dance.you woyane tail(kedengaye mamerecha yewetah)
@ኾሮቦኦ
ወንድሜ ኾሮቦኦ በእውነቱ በሃገራችን የሕግ የበላይነት ባለመስፈኑ ገዢው ቡድንም ሆነ ጀሌዎቹ አፍ አውጥተው ባይናገሩም የሕግ ጥሰት በሰፊው መኖሩ ጥሬ ሃቅ ነው ነገር ግን አሁን በዲምክራሲ የተንበሸበሹት አገራት እዚህ የደረሱት ብዙ ዘመናት ወስደው ነው ይሄም እውነት ነው ታዲያ እኮ ሕግም ሆነ ሕገመንግስት የምንቀዳው(የምንወስደው) ከእነዚሁ ሁገራት ሆኖ ሳለ በዚህ ላይ ስልጣኔም ጭምር ታዲያ በእኛ አገር ዲሞክራሲን ለማስፈን ምኑ ላይ ነው ችግሩ ዲሞክራሲን ለመገንባት ግዜ ይወስዳል የሚሉት አምባ ገነናዊ አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው የሚል እምነት አለኝ ዲሞክራሲንም እየሸራረፉ እንደ እነሱው ችሮታ ለህዝቦች የሚያድሉት በዚሁ አውቃላችሁአለሁ አስተሳሰብ የተወጠሩት ናቸው እንደኔ ዲሞክራሲ ለሰው ልጅ ከፈጣሪ የተሰጠው ጽጋ ነው ስንፈጠር ጀምሮ ፖለቲካም ቢሆን:: እነዚሁ ከሌሎች በአመለካከት በስተሳስብ እንበልጣለን የሚሉ አስተሳሰቦች ናቸው ሁለቱንም ያወሳሰቡአቸው ለዛውም ለግልና ለቡድን ጥቅም ሲሉ እንደኔ ፖለቲካ ማለት ሕዝብ ህዝብ ማለት ፖለቲካ ነው ይህን ስል የሰው ልጅና ፖለቲካ አይለያዩም እንደኔ እምነት ፖለቲካ እውነትና በ እውነት ላይ መመርኮዝ አለበት:: እውነትን ግልጽና ቀናን በማጣመም ፖለቲካ ማለት ፍጹም የሰይጣናዊ አስተሳሰብ ነው:: ይህ የእራሴ አመለካከት ነው::
እኔ በበኩሌ ያቺ የበርህ አይጥ አለችበት ባይ ነኝ አዜብን ማለቴ ነው .የት አባታቸው ሊበሉት ይሆን ??? ወያኔ መገርሰሱ አይቀረም.ይተፏቷል መለስ ሳያቅ የሚሆን ነገር የለምና ዋናው እሱ ነው.እስክንድር በርታ ታሪክ የማይረሳህ ጀግና ነህ.
My bro Horoboo/or the like,
I am surprised with what you are saying. Of course I also agree with what u said about Eskindir he is not like us he lives in it. But sometimes you can not feel when you are living in may be like you. I do not think that anyone wants to oppose any one, unless he feels something different. Peacefullness is the Human nature which we share from our Creator. But when you go out and see what democracy and freedom means that is the time when you realize how you were opperased. Ofcourse there are times some brave people could understand when they are living in… but may be the person like you couldn’t know easily what is going on. Because you are not willing to know, or oppen your heart positively to see what is going on. Otherwise the price of Coffee (The food and drink of our poor community)besides any others nothing else end the 8.5billon dollar coruption and “Our 1st lady business” + the comment of our prime minister lableing the opposing person as “Intelectual Revolutionist” then advise them to go out the country after investing that much money to bring them to “intelect” position and give them back for other smart countries welcomming the “skilled manpower” without any investment and spending a peny on them …. then stolen the money…..Oh my bro take time to think more than twice may be at the time you understood you are either forced to leave the country or being threthoned and waiting your days for being jelled. “DIASPORA”
Don’t you think so!!!!!!!!!!!
ESKE NEGA ARE YOU KIDDING IF ETHIOPIA EARNS LIKE YOU SAID 2BILLION AND IF THIS ETHIOPIAN OFFICIALS STILL BILLIONS WOW THAT MEANS WE ETHIOPIANS ARE BILLIONERS NO PROBLEM.I have friends like you who boast about ETHIOPIA RICHES.First of all let us admit we are poor nation.The reason Meles or this govt beg for money is because they are needy.As an ETHIOPIAN I CARE FORMY NATION BUT TO SACRIFICE ETHIOPIA because of my selfish political aim is old fashioned.
What are you talking about the Tazabi?
Do you have any administrative or any government/organization related experience? Where are you when the Economics brought up the amount of wealth in its report. Please we need to talk what we know or ask from others to learn more otherwise, comment without knowledge is very old fashioned. Now Thanks to our Lord we have so many knowledgable people who reads a lot and have much better wealthy of knowledge than what you are talking about poorness. Do you have any idea about transaction only “Chichilia road” in a single day overnight for drink and dance spending 5 million birr? this is a reaserch conducted by one organization which I am not willing to give you the name before 3 years. you can emagine how much could it be this time when the coffee price alone goes 110birr per kg whether you believe it or not. Can you calculate it the amount of many how much it could be invested for corruption then…. better to know more about the country you are talking about and what the defination of being poor ishi interms of politics!!!!!