አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፤ በአዲስ አበባ ሕዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ ሊጠራ ነው።

January 26th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

አቡጊዳ / ጥር 19 ቀን 2001 ዓ.ም.

በእስር ላይ ያሉትን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ለማስፈታት የተደረገው ሙከራ በሙሉ በገዢው ፓርቲ ስራ አስፈፃሚዎች አማካኝነት ተገቢውን ምላሽ ባለማግኘቱ ሰለማዊ ሰልፍ ለመጥራት በመዘጋጀት ላይ መሆኑን ፓርቲው አስታወቀ፡፡ የታሰሩበትን አንደኛ ወር አስመልክቶም በርቲው ጽ/ቤት ውስጥ የሻማ ማብራት ስነስርአት ይካሄዳል፡፡

የወ/ሪት ብርቱካን ጠበቃ ደንበኛቸውን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ወደ ማረሚያ ቤት ቢሄዱም ፍቃድ አግኝተው ደንበኛቸውን ለማነጋገር ባለመቻላቸው፤ የሊቀመንበሯ ዘመድ፣ ወዳጅና ደጋፊ እንዲጎበኛቸው አለመፈቀዱ፤ እስካሁን ሁለት በሁለት በሆነ ቆርቆሮ ቤት ውስጥ ለብቻቸው መታሰራቸው ፓርቲውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት እንዳስገደደው ያገኘነው መረጃ ያለመክታል፡፡

የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶ/ር ሀይሉ አርአያ ስለጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ እንዳስታወቁት ሰልፉን ለመጥራት መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው ‹‹ሰልፉን የምናደርገው ህጉን ጠብቀን ይሆናል›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም የወ/ሪት ብርቱካን ጠበቃ ደንበኛቸውን እንዳያገኙ መከልከላቸውን አስመልክቶ የፍትህ ሚንስቴር አስተዳደራዊ እርምጅ እንዲወስድ ለመጠየቅ ማሰባቸውን ገልፀዋል፡፡

ወ/ሪት ብርቱካን ከታሰሩበት ጊዜ አንስቶ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ለመነጋገር ጥረት ሲደረግ ቢቆይም እስካሁን የሀገር ሽማግሌ ተብዬዎቹንም ሆነ ተወካዮችቸውን አግኝቶ ለማነጋገር አልተቻለም፡፡ የሊቀመንበሯ መታሰር በሀገር ውስጥና በውጭ ሚዲያዎች ሽፋን ያገኘ በመሆኑ እንዲሁም የፓርቲው አመራሮች ከሽማግሌዎቹ ጋር ለመነጋገር ሙከራ ማድረጋቸው እየታወቀ ምንም ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆናቸው አሁንም መነጋገሪያ እንደሆነ ነው፡፡ ፓርቲውም በዚህ በኩል እንዳልተሰዳካለት በተደጋጋሚ አስታውቋል፡፡

 1. Temelkach
  | #1

  በጣም ትልቅ ውሳኒ ና መሆን ያለበት ነው:: እግዚያብሂር ከናንተ ጋር ይሁን::

  በርቱ እናሸንፋለን!!!

 2. መይሳዉ
  | #2

  የአንድነት ፓርቲ እየሰራ ያለዉ በጣም የሚያስደስትና የሚያኮራ ነዉ:: ያለዉን ሕግ በመጠቀም በርግጥ ወያኔን እየሸረሸሩት ነዉ:: የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰር ያልተጠበቀዉን ትልቅ ድጋፍ ስላመጣ ነዉ የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት የደፈረዉ::

  እንግዲህ ኳሷ በወያኔ በር ላይ ትገኛለች:: አለም አፍጥጦ እያያቸዉ ባለበት መልኩ ሰልፉን ለመከልከል ይከብዳቸዋል:: ከከለከሉ ሌላ የፖለቲካ ድል ይሆናል:: ይኸዉ ሕገ መንግስቱ የሚደነግገዉን ሰልፍ የማድረግ መብት ተነፍገናል ይላሉ:: ወያኔ የብርቱካን ጉዳይ የሕግ ጉዳይ ነዉ ብሎ እንደቀባጠረዉ የሕግ ነገር ሊያነሳ አይችልም::

  ከፈቀደ ደግሞ አራት ሚሊዮን ህዝብ ሊሰበሰብበት ነዉ:: ጉድ ፈላ !!!!!!!

  ትግል ማለት ይሄ ነዉ:: ዶ/ር ብርሃኑ ዝም ብለዉ ከሚያዉደለድሉ እንደዉ እዚያዉ ኢትዮጵያ ቢሆኑ ኖሮ ይሻል ነበር:: ይኸዉ እነርሱ አመጽ እያሉ አመት ሊሆናቸዉ ነዉ:: እነ በርቱካን በሰላም ወያኔን እያርበደበዱት ነዉ::

 3. ክብሮም ከኢትዮጵያ
  | #3

  የሰላማዊ ሰልፍ ጥሩ ነው::እኔም ሁሉም ይሳተፋል ::

  ውድ ወገኖቸ እባካችሁ እነዚህን ሰዎች የሀገር ሽማግሌዎች አትበሉ አቸው:: እንዲህ አይነት ቃለ በላ ሽማግሌ በኢትዮጵያ ታሪክ ና ባህል ተሰምቶም ታይቶም አይታዎቅም:: ስለዚህ እነዚህ ሰዎች የሀገራችንን ባህል ያጎደፉ ና ያዋረዱ በሀገር ሽማግሌዎች ስም የተሰየሙ የወያኔ ካድሪዎች ናቸው::
  ከዚህ በሃላ ላጠፉት ጥፋት ምንም አይነት ማስተባበያ ቢያቀርቡ ልንቀበላቸው አይገባም::

 4. sam
  | #4

  it is time to say enough is enough for woyanne . we gave them time to learn but they are not willing to learn .
  the peopple must show that the woyanne regim can not
  continue like it does now /

 5. ዳናአል
  | #5

  Great move! Go ETHIOPIANS. TIME FOR WEYANES(TPLF) TO BE DESTROYED FROM FACE OF ETHIOPIA. THE DAYS IS NEAR AND CLOSE. WE SHALL SEE JUSTICE SOON.

 6. አኮራቺኝ
  | #6

  በጅቦች በታጠረች አገር እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ማምጣቱ እራሱ ለነጻነትና ለፍትህ ምን ያህል ቁርጠኝነት እንዳለ ያሳያል::

  ይሁንና ለሰላማዊ ሰልፉ ፈቃድ ማግኘታቸው ግን ያጠራጥራል :: አገዛዙ ስለመታሰር እና መፈታት በማሰብ ብቻ የአንድነት ፓርቲ ግዜውንና ሃብቱን እንዲያጠፋ ፍላጎት እንዳለው ጥርጥር የለውም:: ሆኖም በዚህ ወቅት የሊቀመንበርዋ መታሰር ለአገዛዙ ከምንጊዜውም የበለጠ ፈተና ዉስጥ እንደሚከተዉና የውድቀቱም የመጀመሪያው ምእራፍ ሊሆን እንድሚችል የሚያመላክቱ ብዙ ነገሮች እየታዩ ነው:: ዉጤቱን በቅርብ ጊዜ እንያለን:: እዳር ለማድረስ ግን አሁንም የእያንዳንዳችን አስተውጽኦ በጥብቅ ያስፈልጋል::

 7. አንድ ለናቱ
  | #7

  የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲያችን ይህንን የሰላማዊ ሰልፍ ማዘጋጀቱ ተገቢ ነው

 8. አለሚቱ
  | #8

  በርቱ. YES. Demo must be called in Addis. If the leaders have the gut and go on the street, atleast 50,000 people will follow them!

 9. አቢይ፡ኢትዮጵያዊ
  | #9

  )))))))))))))ውጣ ለነጻነት!!!((((((((((((
  ይሄ ነው መተግበር
  እንዲህ ነው መጀመር::
  በዘዴ በመላ
  ይህን ሆዳም ሁላ::
  ወየውልህ!!! በለው
  ልብሕን አስለው::
  ሞርደው ባንድነት
  ውጣ ለነጻነት::
  ሆኖም ግን ተጠንቀቅ
  ድምፅህ እንዳይሰረቅ::
  በየአደባባዩ
  አንተአንቺን እያዩ::
  ደግሞም በነጋታው
  ይመጣል ጉተታው::
  ይመጣሉ ቤትሽ
  ምናባትክ ምናባትሽ::
  እያሉ ለማሰር
  በስመ መጠርጠር::
  እናም አትጋለጡ
  እንዲያ ስትወጡ::
  ፓርቲው ለሰልፈኛው
  ይሄንን ገምቶ
  መላ ብዙ መትቶ::
  ከባንዶች ለይቶ
  ጥበብ ዘዴ አይቶ::
  መፈየድ አለበት
  ሕዝብ እንዲኮራበት::
  ከሰልፎች በሳሉ
  እንዲሆን ታገሉ::
  እንታገል ዛሬ በዘዴ በመላ
  ይሄን ደም የጠማው ለከስካሳ ሁላ::
  ወየውልህ!!!እንበለው
  አምርረን እንሳለው::
  ጥርሳችንን ፈጭተን
  በወኔ ተነፍተን::
  እንትመም ባንድነት
  ውጡ ለነጻነት::
  ውጪ ለነጻነት
  ውጣ ለነጻነት!!!!!!

 10. Seqoqaw Beza
  | #10

  ተገቢና ወቅታዊ ነው ሁሉም ፓርቲ ድጋፉን የመስጠት ኢትዮጵያዊ ህላፊነት አለበት የብርቱካን ወይም የአንድነት ብቻ አይድለም

 11. ቀናው
  | #11

  እኔ የምለው ከውሸታም ጋር የተጎዳኘን ሽማግሌን ሽማግሌ ,
  ሽማግሌ እያላችሁ የምታወድሱትና ,ብንጠራቸው አልሰማ አሉን ብላችሁ የምትገረሙበት ጉዳይ በፍጹም ሊገባኝ አልቻለም

 12. ሊሊ
  | #12

  እስቲ ይሁን ግን ?

 13. አግደው
  | #13

  ለዎያኔ መልሱ ይዬ ነው :
  ህዝብ ድምጹን በሃይል ማሰማት አለበት;
  አንዳለፈው ጊዜ ሚልዮን ሰው ተሰለፎ ቢወጣ ነገሩ ባለቀ ነበር : ይተቀሩት ፓርቲዎች ከአንድነት ጋር ይተባበራሉ ብዬ ተስፋ አረጋለሁ:
  ለወይዘሮ ብርቱካን እጸልያለሁ :

 14. አግደው
  | #14

  መኢአድ ከአንድነት ጋር አብሮ የህዝብ ሰልፍ
  መጥራት አለበት :

 15. እውነቱ
  | #15

  መይሳው አትዘባርቅ! ዶር ብርሃኑ የበኩሉን እየሰራ ነውና!

 16. andnet
  | #16

  if all of us in Ethiopia go out and displace every unit of weyane at a time in all over ethiopia, we may die but after that we will get rid of this mindless,non ethiopian and stupid devil weyanes.weyane yiwdem keweyane ye italy werari yishalenal,melkam edil le selfu.ye Ethiopian nesanet lijocwa enaregagitalen ..birtukan,tedi,bekele jirata and other political prisoners amlak yirdacchu nesa tiwetalachu bekirbu.Ethiopia lezelealm tinur!!!!!!!!!

 17. Anonymous
  | #17

  እፍኝ የማይሞላ ወያነን ለማስወገድ ይቻላል ያስቸገረን ሆዳም አማራና ኦሮሞ ነው

 18. ኢያሱ
  | #18

  መይሳው ስም አትጥራ አትሳደብ ስድብ የጨዋነት ምልክት አይደለም ሁሉም በራሱ መንገድ ይሂድ ለራስህ ነጻነት እንዳለሕ ሁሉ የስው መብት አትንካ እንከባበር አይመስልህም

 19. work_amanuel
  | #19

  SELAM EMF:

  I have read this report first on Abugida. It is the same report. Which website is the originator of the news ?

  Here I read ” Written on Monday, January 26th, 2009 at 5:15 am by ethioforum”.

  If this is correct then Abugida must indicate that it got the news from EMF. If EMF copied from abugida then EMF must give credit to Abugida and not take the credit for itself.

  I am sure this correction will be made from the part of EMF.

  I am not writing this because it is a big deal. It isnot a big deal; however “honesty is the best policy”. Unless we establish truth and integrity with little staff it will grow and may end being a big problem.

  As to the event that will be held in Addis Ababa, I have no other words but admiration to UDJ leaders. May god be with them.

  AZ

 20. በርቱ
  | #20

  ጎሽ ወገኖች ሁላችንም መጀመሪያ አገራችንን እናድን ልዩነታችን በህዝብ መንግስት ይፈታል:: ወያኔ ማንንም ወገን ሲያጠቃ አብረን መቆማችንን ይሄንን ወንበዴ ቡድን መውጫ መግቢያ እናስወጣዋለንን::

  ተጠንቀቁ ሲቸግረው ባልና ሚሲት ያጋጫል:: ሰሞኑን ደግሞ እንደገና በሃይማኖት እየሞከረ ነው::

  ይሄንን የሚያደርጉ ቡችላዎቹንን ለፍርድ እንዲቀርቡ ተከታተሉ::

 21. ተፈሪ መኮንን
  | #21

  ለምን ግን My lord, ’tis not the sable suit I wear;
  No, nor the tears that still stand in my eyes,
  Nor the distracted ‘havior in the visage,
  Nor altogether mixt with outward semblance,
  Is equal to the sorrow of my heart;
  Him have I lost I must of force forego,
  Thes, but the ornaments and suits of woe.

 22. መላእከ
  | #22

  እግአብሂር ዝም ብሎ አያይም የኢትዮፒያ አምላክ በቅንነት ይፈርዳል በስልታን የሚያስቀምት አምላክ ከስልታን ያዋርዳል እግዚአብሂር የህዝብ አምላክ ሩህሩህ አባት ነው እሱ እንደ ሰው ክፉ አይደለም ይልቅ በንስሃ ወደ እርሱ መመለስ ያስፈልጋል እላለሁ ተመለሱ`!!!

 23. መላእከ
  | #23

  ለምን?ቅድሚያ ሊሰተው ይገባል

 24. ስደተኝኣው like soale
  | #24

  መይሳው ወያነ ነሀ መሰል ለመከፋፈል ትሞክራለህ ተረጋጋ

 25. ደሞክራሲ
  | #25

  አቡጊዳ ሚናቺሁ አይታወቅም

 26. ደበበ
  | #26

  ሁላቺንም በአንድነት ሆነን ፓርቲና ዘር ሳይለየን የምርጫ ሳጥኑንና ቦታውን ከመለስና ካድረወቹ አርቀን በነትጻነት ለዘለአለም ሁላቺንም የምንገለገሊበት በተፈለገው መንገድ በአስቸኩዋውይ ለማዘጋጀት እኛ ውነተኛ አገር ወዳዶ ኢትዮጵያኖች አናጢና ቡልዶዘር ሆነን መገኘት ያስፈልገናል::

 27. ሳተናው
  | #27

  እግዚአብሄር ይህርዳቸው ሆኖም ቀልላላል ሊሆን እንደማይችል.ሳይረዱት ይቀራሉ ብዪ አላስብም….ጥበብና ስልት ብተሞላበት ሁኔታ ከስርጎ ገብ ዎያኔዎች ራሳቸውን ጠብቀው መንስቀስ ይገባቸውል…በሌላ በኩል ሰቆቃው በዛ እንዳለዉ”ተገቢና ወቅታዊ ነው ሁሉም ፓርቲ ድጋፉን የመስጠት ኢትዮጵያዊ ህላፊነት አለበት የብርቱካን ወይም የአንድነት ብቻ አይድለም”ስለዚህ ሁላቺንም የበክኩላቺንን በምንቺለዉ መንገድ ለስኬቱ ጥረት ማድረግ ይጠብቅብናል
  አምላክ ይርዳን

 28. ሳተናው
  | #28

  ሳተናው እንዳለ(ው/ችው): Your comment is awaiting moderation. Noting that Woyannes and Shabias are infecting our forum, we have decided to moderate every comment. Sorry for the inconvenience this may have caused you!
  ምነው ደጋገምችሁት ሃሳቤ የወያኔ ወይም የሻብያ ይምስላል?

 29. Seqoqaw Beza
  | #29

  መቼ ነው ሰልፉ ወያኔስ ይፈቅዳል? ወይስ እንዳለፈው ጊዜ እናጥለቀልቀዋለን? ቀኑ ደርሷል በርቱልን ቁርጠኛ ስዎች የብርቱካን አይነት ግን ያስፈልገናል:: እግዚአብሔር አምላክ ከናንተ ጋር ይሁን:: ብርቱካንና ቴዲን እንዲሁም በዚህች ሰአት በወያኔ እስር ቤት ያሉትን ሁሉ ጌታ ያበርታልን:: አመሰግናልሁ!

 30. ህይወት
  | #30

  አስተያየት ሁሉ መልካም ነው አይከፋም
  ለትግሉ መፋፋት እጃችሁ ምን ይዙአል??
  ደጋፊ አላት እኮ በአንድ የተደራጀ
  ትግሉን የሚረዳ እየተዘጋጀ::
  ብሶቱ ንዼቱ እንዲያፈራ ፍሬ
  እስቲ ተደራጁ ሁላችሁም ዛሬ::
  ለብርቱካን ሳይሆን ለአላማዋ ቁሙ
  እናት ኢትዮፒያ እንድትድን ከህመሙ::
  ለአላማዋ የቆመ ለሱዋ እንደቆመ ነው
  ነፍስን ከስጋ ላይ ነጥሎ መውስድ ነው::
  እስቲ ይፋ ውጥኡ በያላችሁበት
  ዝምታ ድጋፍ ነው እያለ ወያነ
  እስቲ አያላግጥበት::
  ይህንን ስላችሁ ድርሻን ፈጥሜ ነው
  ድልም የሚገኝው በመደራጀት ነው::

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።