ፍኖት ጋዜጣ – ኢትዮጵያዊነትኔን ማንም ሊነግረኝ አይችልም !

August 31st, 2011 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

በህይወቴ የማንነት ጥያቄ ችግር ኖሮብኝ አያውቅም፡፡ነገር ግን ክፉዎች፣ የሀገር መምራት ሥልጣነ-መንበሩን ከተቆናጠጡት በኋላ (እግዚአብሔር የሥራቸውን ይስጣቸው) በሚመቻቸውና ሥልጣናቸውን ለማርዘም ሲሉ ብቻ ከፋፈሉን፡፡ ለያዩን፡፡ እኛ ግን እግዚአብሔር ይመስገን እስካሁን አለን፡፡ ወደፊትም ሳንከፋፈል እንኖራለን፡፡

ይህን ያለምክንያት አላነሳሁም፡፡ በአንድ ወቅት በ”ኢህአዴግ” የወረደ አስተሳሰብ እና ብልሹ አመራር ተበሳጭቼ ኑሮዬ የኋሊት ሲጐትተኝ ስደት ተመኘሁ፡፡ ለዚህም ይረዳኝ ዘንድ ፓስፖርት ማዉጣት ስላለብኝ በቅድሚያ መሟላት ከሚገባቸው ነገሮች አንዱ የቀበሌ መታወቂያ ነው፡፡ ነዋሪነቴም፣ ተወልጄ ያደኩትም አዲስ አበባ ሲሆን፣ ወደምኖርበት ቀበሌ መሄድ ነበረብኝና በዕለተ ሰኞ ሄድኩኝ፤ ከዚያም መሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች አሟልቼ ለማክሰኞ እንድመጣ ተነገረኝ፡፡

በነጋታው የተነገረኝን አሟልቼ ስመጣ አንድ አስደንጋጭ ነገር ገጠመኝ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ብዙዎቻችሁ የቀበሌ መታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማውጣት ስትሄዱ እንደኔ ገጥሟችኋል ብዬ አስባለሁ፡፡ ምን መሰላችሁ? ጉዳዩ የመታወቂያ ካርድ ቅጹ ላይ፣ ስም ከእነ አያት፣ የእናት ስም፣ የትውልድ ቦታ እና ቀን፣ በአደጋ ጊዜ ተጠሪ፣ አድራሻ ይላል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ለየት ያለብኝ ነገር ደግሞ «ብሔር» የሚል ጥያቄ ቀረበልኝ፡፡ ግራ ገባኝና ዜግነት ማለትህ ነው? አልኩ፡፡ ‹አይ ብሔር› አለኝ፡፡ እኔም ‹አልገባኝም ምን ማለት ነው?› ብዬ ጠየቅሁ፡፡ ምክንያቱም ድሮ ዜግነት ነበር የሚጠየቀው፡፡ በተለይ እኛ ሰፈር የውጭ የሶማሊ፣ የቻይና፣ የህንድ ዜጐች ስለሚበዙ ግልፅ ነው፡፡ በነገራችን ላይ እኔ በወላጆቼ፣ በዘመዶቼና በዜጐቼ የምኮራ ቀብራራ ሀበሻ ነኝ፡፡ አዎ ነኝ! ያውም ኩሩ ኢትዮጵያዊ፡፡ የዛን ቀን ግን መልስ ለመስጠት ተደነባበርኩ፡፡

እስካሁን በተለያዩ ሁለት የሀገራችን ዩኒቨርስቲዎች የተለያየ ሙያ ተምሬያለሁ፡፡ በኃይማኖት ተቋማትም እንዲሁ፡፡ ግን እንደዚህ ጥያቄ ከብዶኝ አያውቅም፡፡ የማላውቀውን መልስ መስጠት አልወድም፤ ከቻልኩ እመልሳለሁ፡፡ ካልቻልኩ እንዲነግሩኝና እንዲያሳውቁኝ ጠይቄ ለማወቅ እሞክራለሁ፡፡

የዛን ቀን ግን አያምጣው፡፡ ለምን መሰላችሁ? ስም ከነአያት፣ የልደት ቀንና ቦታ ከመሳሰሉት ውጭ ያሉ ቅፆች ደስ ካለዎት ይሞላሉ፤ አሊያም በስረዝ ይታለፋል፡፡ ብሔር የሚለው ግን የግድ ነው ስለተባልኩ፤ የቃሉን ትርጉም ፍቺ ጠየቅሁ፡፡

እነሱም የተወለድክበት ቦታና የምትናገረውን ቋንቋ ነው የሚገልፀው አሉኝ፡፡ እኔም መልስ ሰጠሁ፡፡ የተወለድኩት አዲስ አበባ፣ ያደግኩት ምስራቅ ሸዋ፤ በትምህርት ምክንያት አዋሳ፣ ሰሜን ኢትዮጵያ፣ ከዚያም እስከ አሁን አዲስ አበባ ነው አልኩት፡፡ የምችለው ቋንቋ ደግሞ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሀድይኛ፣ ትግርኛ፣ ሲዳምኛ (በትንሹ) እና ከውጭ በትምህርት ያገኘሁት እንግሊዘኛ፣ፈረንሳይኛና አረብኛ (በትንሹ) አልኩት፡፡

ወላጆችህስ? አለኝ፡፡ አባቴ ደግሞ ከሲዳምኛ ውጭ እኔ የምችለውን ሁሉ ይችላል፣ ከውጭ ግን ሩስኪ (የራሺያ)፣ ጀርመንኛ እና እንግሊዘኛ ይናገራል፡፡ እናቴ ግን የሀገር ውስጥ እኔ የምችለውን ከሲዳምኛ በስተቀር መናገር ትችላለች ስል በጣም ይደነቅና ሊፈትነኝ ሞከረ፡፡

በነገራችን ላይ የሚያስተናግደኝ ሰው በትግርኛ አናገረኝ መለስኩለት፤ ከአማርኛ እና ከትግርኛ ውጭ አልቻለም መሰለኝ የቋንቋው ፈተና አበቃ፡፡ ከዚያም የትኛውን ብሔር ልሙላልህ? አለኝ፡፡ እኔም ኢትዮጵያ ስል ተናደደና አትቀልድብኝ አለኝ፡፡ እኔም የምሬን እንደሆነ ነገርኩት፡፡ ከዚያም ግራ ገባው፤ ተጨነቀ፡፡ ግን የግድ መሞላት አለበት የሚል መመሪያ እንዳለ እሱም ይህን እንደማያምንበት ነገረኝ፡፡

የሚገርመው እኔ ከእናትና ከአባቴ ብቻ ሳይሆን በአያቶቼም እጅ አድጌአለሁ፡፡ የእናቴ የትውልድ ሀረግ ሲዘረዘር የጐንደር፣ የአምቦ፣ የደብረማርቆስ፣ የተንቤንና የመራቤቴ ቤተሰብ ግንድ አለባት፡፡ አባቴ ደግሞ የሀድያ፣ የጉራጌ፣ የቤተእስራኤል፣ የጅማ እና የጐንደር አካባቢ ግንድ አለባቸው፡፡ የተለያየ ቋንቋም ይናገራሉ፡፡ ፍረዱኝ እንግዲህ … እኔ የየትኛው ብሔር አባል ነኝ ልል ነው? ወይንስ እንደ ዶሮ ብልት አካሌን ልበልት? ለመሆኑ ማነው የኔን ኢትዮጵያዊነት የሚነግረኝ? ምንስ አገባው? እሱ ማነውና? 2ዐ ዓመት ተጉዘን እንኳን አይበቃንም? እኔ ግን ትናትም፣ ዛሬም፣ ነገም፣ ወደፊትም፣ ብሞትም በአጽሜ ሳይቀር ኢትዮጵያዊ ነኝ።

የፍኖት ጋዜጣ እትይም 5 ሙሉዉን ለማነበብ ወደ አንድነት ፓርቲ ድህረ ገጽ ይሂዱ።

  1. zenebe
    | #1

    fantastic! this has become our fate, it is absolutely irritating. We are damned to the extreme. I TOO FACED THIS PROBLEM, EVERYONE faces the same mindboggling trouble of such kind. How could I know whether I am Oromo or Amhara or anybody else? yezemnu gugmangugoch endih aderegun. egzer yiyilachew. I think they do this to know identify ‘their’ people and to give them the utmost advantage and to harm others when any mishap comes to the political scene of the country. Any how this practice is beyond our capacity to endure. yigelagilen.

  2. Anonymous
    | #2

    ወንድነህ የኢትዮያ አምላክ ይርዳህ
    መለስ ዘር ማንዘሩ ባንዳ ሰለነበሩ ሰለ ኢትዮፒያዊነት ኢንዲነሳ አይፈለገም

  3. ዳኒ
    | #3

    ዳግም ተሸወደክ ምነው በሁለት ስም አንድ አስተያየት????? ይገርማል ቀብሌ እናም ገጥሞኛል በጣም ገርሞኝ ነበር ያየኡት አዲስ ነገር ብሄር እና ሐይማኖት እናም በጣም ያሳዝናል. ምናልባት ትግሬ ያልሆነውን ለጄኖሳይድ ታስቦ ይሆን???? ጥሩ ታዝበሃል. ግን ኢትዮጲያ ውስጥ ሁሉም ያዘኑበት ነገር ነው እናም ወደፊት የታሰበች ነገር ስላለ ነው.ጠንቀቅ ነው. ይህ ዘረኛ አምላክ ይንቀለው.

  4. አዲስአበባዊ
    | #4

    ጥሩ ጽሁፍ ፍኖት ጋዜጣ አስነበበን እንደ እኔ ብሄር የሚለው በተለይ ከገዢውቻችን ዘር ላልመጣን ሁል ግዜ የምንቆጭበትና እንደውም የተበደልንበት ሆኖ ይሰማናል ትክክልም ነው ሊሰማን ይገባል ግን ምናልባት ለነሱ ልዩ ጥቅም የሚያስገኝ ነው ምክንያቱም ከህግ አስከባሪ ጀምሮ በየመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች አገልግሎት ለማግኘት ሲሄዱ መታወቂያ ተጠይቀው ሲያቀርቡ በምንም መልኩ ትግሪኛ የሚለውን ያየ ሰራተኛ ላይ በተለያየ ሁኔታ ትጽእኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው ታዲያ ከመታወቂያ ላይ ብሄር የሚል እንዳይኖር ቢባል ያንን አይነት ጥቅም ሲያገኝ ለኖረ ሰው እንደ መለስ ዜናዊ ጸጉሬን ያስነጨኛል ነው የሚሎት ዞሮ ዞሮ ጥቅሙ ለነሱ ነው ይህም የሚጠውፋው ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ብሆንም ብሄር ሲሉኝ አዲስአበባዊ ነኝ የምላቸው ስለ አዲስአበባዊነት በሰፊው ሌላ ግዜ በአስተያየቴ ላይ ላብራራ እሞክራለሁ::

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።