የሰው ልጅ ተከበረ!

January 26th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ዘካርያስ ጌታቸው / ጥር 19 ቀን 2001 ዓ.ም.

ቀኑ በጣም ነበር የራቀው። የራቀው ለኔ ብቻ ሳይሆን ለመላው አለምም ነበር። ቀኑዋ በቀናት በሰአታት በደቂቃ እንዲሁም በሴኮንድ እየተቆጠረች ደረሰች። አለማችን ብዙ ታላላቅ ቀናቶችን በእድሜዋ ብታሳልፍም የአሁኑ ግን ልዩ ሆኖባታል። የተደነጋገረችም ትመስላለች በውስጡዋ ግን ታላቅ እረፍትና ደስታ የተሰማት ይመስላል። ቀኑ በሰላም በፍቅር እንዲያልፍ በምድር ላይ ያሉ አባቶች እናቶች እንዲሁም ህፃናትም ጭምር ከፈጣሪያቸው ጋር የልመና ግኑኘነት ከጀመሩ ቀናቶችን አሳልፈዋል።

ቀኑዋ ሮጣ አታመልጥም እና መድረስ አይቀርም ደረሰች። እኔም ፈቃዱ ሆኖ በዚች ታሪካዊ ቀን ለመገኝት እግዜር ወዳደላት መዲና ወደዋሽንግተን ጉዞዬን ጀምሬአለሁ። በአይሮፕላኑ ማረፊያው ሆነ በአውሮፕላኑ ውስጥ የሚወራው ወሬ ስለዚቹ ቀን ነው። በእንቢልታና በነጋሪት ተነፍቶ እንደታወጀ አዋጅ የሰው ዘር ከየቦታው እየተሰባሰበ ነው። በዚች ቀን ወንድም ባራክ ኦባማ የአሜሪካ 44ተኛው ፕሬዘዳንት ሆኖ በህዝብ ፊት ወንበሩን ይረከባል።

ፈጣሪ አምላካችን የሰውን ልጅ በተለያየ ጊዜአት ትሁት እንዲሆን፤ እንዲከባበር፤ እንዲፈቃቀር እና እንዲረዳዳ በተለያዩ መንገዶች ሲያሳየን እና ሲያስተምረን አልፎአል። ዘመኑ ግን ሰው የሚከባበርበት ሳይሆን እንደአውሬ የሚበላላበት፤ የፍቅር ሳይሆን የምቀኝነት መንፈስ የተላወሰበት ተተኪ ትውልድ ግራ የተጋባበት ዘመን ነው። መቼም እናት ልጁዋን በስህተቱ እንደማትጠላው ሁሉ ፈጣሪም ምንም እንኳን በዚች አለም መርመጥመጥ ቢያዝንም ይቅር እያለን መልእክተኛን በመላክ ሊያድነንና ለያስተምረን ይፈልጋል።

በእለተ ማክሰኞ Jአnuአry 20, 2009 ዓ.ም መልእክተኛውን ፕሬዘዳንት ሲሆን ለማየት ወደ በአሉ ቦታ በግር ስጓዝ ከዚህ በፊት አይቼው እማላቀውን ክስተቶችን እያየሁ መጓዜን ቀጠልኩ። መረዳዳት መፈቃቀር ትሁትና እንደምግብ ወደሰውነቴ ሲገባ ይሰማኝ ነበር። ወታደሩ በፈገግታ ሰላምታን እየሰጡ ፖሊሶቹ ምን ልርዳችሁ እያሉ እንደጉንዳን የሚፈላውን ህዝብ በእንክብካቤ ይዘውታል። በጉዞ ላይ ያለውም ህዝብ ለብዙ አመታት አብሮ አደግ እነደነበሩ ጓደኛማቾች ታሪካቸውን እያወሩ በጉዞ ላይ ናቸው። ለቦታው ሰላም መከበር መለዮ ለባሹ ብቻ ሳይሆን ህዝቡም ትልቅ ሃላፊነት የተረከበ መስሎ ይታይበት ነበር።

ጉዞ…

ቀኑ በጣም ብርዳማ ነበርና አንዲት ጥቁር አሜሪካዊ በእግሩዋ ውስጥ የገባውን ብርድ ልትቆጣጠርው ባለመቻሉዋ አንዲት ነጭ አሜሪካዊት ለራሱዋ የያዘችዉን ጫማ ውስጥ የሚገባውን ማሞቂያ ለጥቁር አሜሪካዋ ስትሰጥ ሳይ በካንፔኑ ስሰራ ብዙውን ጊዜ ፍቅርን እና መረዳድትን ባያትም ይህን ሳይ ግን ይህ መልእክተኛ መሪ ምን ያህል ፍቅርን ለሰው ልጅ እንደሰጠ ለመገንዘብ በታላቁ ችዬአለሁ።

ፈጣሪ ይህቺን ምድር ሲፈጥር የሰውን ልጅ በህግ እንዲመራ አድርጎ ነው የፈጠረው። በዚህ በዘንድሮ በአሜሪካ የፕሬዘዳንት ምርጫ የአሜሪካ ህዝብ ምን ያህል በህግ መገዛቱን ለአለማችን ያሳየበት እና አሜሪካ ከሜቼውም በበለጠ ተከብራ እንደትታይ ያደረገበት ጊዜ ነበር። በአሜሪካ የፖለቲካ ርእዮተ አለም ውስጥ ብዙ ያልነበረ፤ በልጅነቱ ከአሜሪካ ውጪ ያደገ፤ በአባቱ ጥቁር በናቱ ነጭ፤ በእናቱ አሜሪካዊ በአባቱ ኬኒያዊ፤ በእናቱ ክርስትያን በአባቱ እስላም የሆነውን ከህዝብ አብካር የወጣውን ባራክ ኦባማን የአሜሪካንን ፖለቲካ ሆነ ኢኮኖሚ ሲፈልጡ እና ሲቆርጡ የነበሩ ሁሉ ጎንበስ ብለው እጅ ሲነሱለት ስናይ ምን ይሆን አለማችን የተማረችው?

ለኔ የሰው ልጅ በገንዘቡ፤ በትምህርቱ፣ በዘሩ፤ በቀለሙ ሳይሆን በማንነቱ ማለትም የሰው ልጅ በመሆኑ መከበሩን አይቼአለሁ።

አዎ የሰው ልጅ ተከበረ!
ይቻላል> ተችሎአል!

 1. ጣሳ ቁርጥ
  | #1

  እውነት ትቆያለች እንጂ መውጣቷ አይቀርም ከወጣች ደሞ አንዴ ነው ውሸትን ክፍንኝ ታሰከፈዋለች :: ይሄንንም በ አገራችን ለማየት ያብቅን god bless obama!!!

 2. ጣሳ ቁርጥ
  | #2

  እውነት ትቆያለች እንጂ መውጣቷ አይቀርም ከወጣች ደሞ አንዴ ነው ውሸትን ክፍንኛ ታሰከፈዋለች :: ይሄንንም በ አገራችን ለማየት ያብቅን god bless obama!!!

 3. ሊሊ
  | #3

  አሜሪካ ምንግዜም አሜሪካ ነች
  እስቲ አስቡት ኢትዮጲያ ውስጥ እንደ ኦባማ ለኢትዮጲያ የሚያስብ ህዝብን ባአንድነት የሚያይ በምርጫ የመጣ በምርጫ የሚያምን የዚህ አይነት መንግስት ቢመጣ እሱ የመጣበት ቀን ምን ይመስል እንደነበር ያ ቀን አስቡት ህዝቡ ከዳር እስከዳር ወጥቶ ደስታውን ሲገልጵ የዛ ቀን ሰለብሬሽን ሲታሰብ ምነው አሁን በሆነ ያስብላል ግን በየት በኩል ወያኔ እያለ የወያኔን መጨረሻ ያሳየን አሜን “”

 4. ጣሳ ቁርጥ
  | #4

  ሊሊ ኦባማ ሰለሽ ወደፊት የምናየወን አስተዳደር በ ኢትዮጵያ ላይ ማለቴ ነው:: መጀመሪያው ንግግሩ ላይ ያለወን የሰማሽ የመስለኛል:: የ ቡሽ ን አየነው አይደል እንዴ ሶማለያ ላይ ያሳየውን ተፅኖውን:: ለስራው ጊዜ ስለሚያሰፈልገው ትንሽ እንጠብቀው::

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።