የሕወሃትና የአንድነት ሰላማዊ ትንቅንቅ- ዶር ያእቆብና ሌሎች ታስረዉ ነበር

January 27th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

አቡጊዳ / ጥር 20 ቀን 2001 ዓ.ም.

በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ምክትል ሊቀመናበርት የሚመራ ቡድን ህዝብን ለማነጋገር፣ የተከፈቱ ቢሮዎችን የሥራ ሂደት ለመገምገምና ሌሎች ቢሮዎችን ለመከፍት እንዲሁም በዋናነት የፓርቲዉ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ሕገ ወጥ እሥር ለሕዝብ ለማስረዳት ተጉዞ ሥራዉን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ መዘገባችን ይታወሳል።

ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የተጓዘዉ መርሳ ተብሎ በሚታወቀዉና ከደሴ ጥቂት ኪሎሜትር ወጣ ብሎ በሚገኘዉ ቦታ ዛሬ ጥር 18 ቀን 2001 ዓ.ም ዶር ያዕቆብ ወልደማሪያም፣ አቶ ይልቃል የድርጅት ጉዳይ ጸሃፊ፣ አቶ ብሩ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሰብሳቢና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንዲሁም 10 የሚሆኑ የአካባቢዉ የአመራር አባላትና የስብሰባዉን አደራጆች በቁጥጥር ስር በማዋል ለሰዓታት መታሰራቸዉን ከፓርቲዉ ቅርበት ካላቸዉ ምንጮቻች የደረሰን ዜና ያመለክታል።

ከምንጮቻችን እንደተረዳነዉ በመርሳ ከተማ በገዢዉ ፓርቲና በአንድነት ፓርቲ መካከል የተደረገዉ ፍጥጫና ሰላማዊ ትንቅንቅ እንደሚከተለዉ አቅርበነዋል።

የዲሞክራሲ እንቅስቃሴ በጣም አስቸጋሪ በሆነበትና የገዢዉ ፓርቲ ካድሬዎች ዛቻና ማስፈራራት እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ በአዳራሽ ዉስጥ ስብሰባ ለማካሄድ አስፈላጊዉ ዝግጅት ከተሟላና ሕጉ በሚፈቅደዉ መሰረት የሰላማዊ ትግል አካል የሆነዉን፣ ኢትዮጵያዊያንን ሰብስቦ ስላለዉ የወቅቱ ሁኔታ ለማስረዳት በተጠራዉ ስብሰባ ላይ ለመካፈል ሳይፈሩ በድፍረት እጅግ በጣም በርካታ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

የአካባቢዉ የገዢዉ ፓርቲ ባለሥልጣናት በስብሰባዉ ቦታ ተገኝተዉ ስብሰባ ማድረግ እንደማይቻል ህዝቡም በዚህ ስብሰባ ላይ መካፈል እንደሌለበት ይናገራሉ። የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላትና ለስብሰባ የመጣዉ ሕዝብ መሰብሰብ በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸዉ መብት መሆኑንና በአዳራሹ ስብሰባ ማካሄድም መከልከል እንደሌለበት ለማስረዳት ቢሞክሩም የገዢዉ ፓርቲ ታጣቂዎችና የደህንነት አባላት ለመስማት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ለጥቂት ጊዚያት ከፍተኛ ጭቅጭቅና የሃሳብ ክርክር ከተደረገ በኋላ የሕወሃት ባለስልጣናት ወደ ለመዱት የጡንቻ ታክቲክ ይሄዳሉ። በጉልበትና በጠመንጃ የስብሰባዉን አዳራሽ ወረዉ ይይዛሉ። ዶ/ር ያዕቆብ ወልደማሪያምን፣ አቶ ይልቃልም አቶ ብሩንና 10 የክልልሉ የአንድነት አመራር አባላትን ከአዳራሹ እንዳይወጡ ለሰዓታት በቁጥጥር ሥር ያዉሏቸዋል።

«ይህ ድርጊት በሕገ መንግስቱ ላይ በግልጽ የሰፈረዉን የዜጎች በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ መብት የሚጻረር ነዉ። ስብሰባዉ ሕጋዊና ሰላማዊ ነዉ። ሕጋዊና ሰላማዊ ያልሆነዉ የእናንተ እኛን ማገትና ስብሰባዉን መከልከል ነዉ» በማለት ዶ/ር ያዕቆብና የትግል አጋሮቻቸዉ በታሰሩበት ቦታ ሆነዉ ለማስረዳት ሞክረዉ የነበረ ሲሆን የአገዛዙ ባለሥልጣናት ግን «ሕገ መንግስቱ ላይ የሰፈረም ቢሆን የሚፈቀደዉና ሥራ ላይ ሊዉል የሚችለዉ እኛ ስንፈቅድ ብቻ ነዉ» በሚል ስሜትና ማን አለብኝነት እንደ ተራ ወንጀለኛ ያለአንዳች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስረዉ ስብሰባዉን ለማደናቀፍ ችለዋል።

ከአምሳ ሰዉ በላይ አይመጣም ብለዉ የሕወሃት ባለሥልጣናት የገመቱት በሜክሲኮ አደባባይ በሚግኘዉ 3000 ሺህ ሕዝብ በሚይዘዉ የመብራት ኃይል አዳራሽ ጊቢዉ ሁሉ ሞልቶ እስኪዘጋና ከዚያ በኋላ የሚመጣዉ ሕዝብ እንዲመለስ እስኪደረግ ድረስ ወደ 5000 ሺህ ኢትዮጵያዉያን መገኘታቸዉ፣ የአዲስ አበባ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ከመደረጉም ጥቂት ሳምንታት በፊት የአንድነት አመራራ አባላት በየክልሉ ጽ/ቤት ለመከፈትና ህዝቡን ለማዳራጀት ባደረጉት የመስክ ስምሪት ከአዲስ አበባ ዉጭ ባሉ ከተሞችና ገጠሮች ከፍተኛ ድጋፍ መገኘቱና ወደ 35 የሚሆኑ ጽ/ቤቶች እንደተከፈቱ የሚታወስ ነዉ። በተለይም በደንበጫ ጎጃም የአንድነት አመራር አባላትን ባንዲራ እያዉለበለበ ሕዝቡ ሲቀበላቸዉና ለነርሱም ክብር ሙከት ማረዱን ያዩ የአካባቢዉ ባለሥልጣናት ኢንጀር ግዛቸዉንና አብረዋቸዉ ያሉት ለአራት ሰዓት እንዳሰሯቸዉ በወቅቱ ተዘግቧል።

ይህ ከአዲስ አበባም ያለፈ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ የሕወሃት ባለሥልጣናትን እጅግ ስላስደነገጠ ተልካሻና እነርሱን ትልቅ ግምትና ዉርድት ዉስጥ የሚከት አስቂኝና አሳፋሪ ምክንያት በማቅረብ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን በግፍ የታሰሩ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሕወሃት እያደረገ ያለዉ ሕገ ወጥ ድርጊት ገዢዉ ፓርቲ በራሱ የመተማመን አቀም እንደሌለዉ የሚሰራዉን እንደማያዉቅን በርግጥ እንደተደናበረ ያሳያል የሚሉ በርካቶች ናቸዉ።

«የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰር ዓላማዉ ድርጅቱን ለማፈን፣ ሕዝቡን ለማስፈራራትና እንደለመዱት በጉልበት ለመግዛት ነበር።” ያነጋገርናቸዉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ « ሊሳካለት ግን አልቻለም። የጉልበት እርምጃ ድርጅቱ ላይ በተወሰደ ቁጥር ድርጅቱ እየኮሰሰ ሳይሆን እያደገ ነዉ የመጣዉ። የድርጅቱ አባላት በታሰሩ ቁጠር ሌሎች በርካቶች ትግሉን እየተቀላቀሉ ነዉ። አገዛዙ አላወቀዉም እንጂ አሁን እያደረገ ያለዉ አፈና ለአንድነት ፓርቲ ትልቅ ገጸ በረከት ነዉ የሰጠዉ» በማለት የአንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለዉ ሰላማዊ ትንቅንቅ ትልቅ ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ገልጸዋል።

የፖለቲካ ተንታኙ የነዶር ያዕቆብን በመርሳ መታሰር በተመለከተ ሲናገሩ « መርሳ የምትባል ከተማ መኖሯን ድንገት በወሎ አካባቢ የሚኖርና የጂኦግራፊ ጠበብት ካልሆነ በቀር ብዙ ሰዉ የሚያወቅ አይመስለኝም። አሁን ግን መርሳ ታወቀች። ስብሰባዉ ቢደረግ ኖሮ ከሚኖረዉ ጉዳት ስብስባ አለመደረጉ ለሕወሃት ትልቅ ጉዳት የሚያመጣ ይመስለኛል። ይኸዉ መርሳ ዉስጥ የሆነዉ ነገር ከዚህ በፊት ደንበጫ እንደሆነዉ ትልቅ ዜና ሆነ እያነጋገር ነዉ። » ነበር ያሉን።

የአገዛዙ ባለሥልጣናት «ሕገ መንግስቱ ላይ የሰፈረም ቢሆን የሚፈቀደዉና ሥራ ላይ ሊዉል የሚችለዉ እኛ ስንፈቅድ ብቻ ነዉ» ማለታቸዉ ደግሞ ከነ አቶ መለስ የተሻለ ያደርጋቸውዋል ያሉን ተንታኙ «ቢያንስ ቢያንስ እዉነቱን ተናግረዋል። ሕግ ሕግ እያሉን እንደነ አቶ መለስ አልቀባጠሩም። የሕግ የበላይነት በኢትዮጵያ እንደሌለም በግልጽ አሳዉቀዋል።» ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ አስተያየታቸዉ ደምድመዋል።

 1. | #1

  በርቱልን

 2. ቶኪቻው
  | #2

  ያቺ ቀን ትመጣለች !!

 3. ሞትባይኖር ዘመድ ኩን
  | #3

  ወያን መች እንደሚገባው ኣእግዚያር ነው የሚያቅ ::

  ሙጋበ እንካን ከተቃዋሚ ጋር መነጋገር ጀምርዋል(የነበረከት አለቃ).

 4. ሊነጋ ሲል ይጨልማል
  | #4

  መርሳ ሆነ ደንበጫ,ሆነ ሰለለክላካ የትም የቢገኘው ህዝብ የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ ነው ደፍሮ እንደዚህ ወደታች መውረድ መጀምር ቀዳሚው የትግል ምእራፍ ነው ወያኔ በድቡሽት ላይ የተሰራ ቤት ነው ህዝብን ማደራጀት ከተቻለ ወያኔ የአንድ ቀን የቤት ስራ ነው በርቱ አንበሶች
  ማሰር,መግደል,ወከባ መፍጠር የትግል ሂደትን ያፋጥናል እንጅ የአቆመበት ታሪክ የለም

 5. ዮናሰ
  | #5

  ወያኒ እግዚአብሂር ማስተዋልና ልቦና ይስተው.
  እናንተም እግዚአብሂር ይርዳችሁ.

 6. Habtegebriel
  | #6

  I am really apreciate the peoples decsion and their hate against the woyane,Woyane is now at the last moment,Woyane is a dying wounded Hyena,that is why they are trying to terrorize the peoles as wel as the opositions.Now is the time all ethiopians to stand united and fight for the final removal of this fascist regime.
  God bless Ethiopia!

 7. ሊሊ
  | #7

  ወያኔ ትግሉ ወደ ህዝቡ ውስጥ እንዳይገባ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ህዝብ ውስጥ መግባት ያስፈልጋል ተቃዋሚውች ህዝብ ላይ የተቀናበረ ስራ አልሰሩም እንዳይሰሩም ወያኔ እንቅፋት ይፈጥራል ህዝቡ አንዴ ከተነሳ የመጨረሻቸው እንደሚሆን ያውቁታል ህዝብ ግን አንድ ጠንካራ ተቃዋሚ ይፈልጋል የራሴ የሚለው እነኚህ ለኛ ያስባሉ ብሎ ካል መመለሻም የለውም
  የኢትዮጲያ ህዝብ የሚወደውን ይፈልጋል ብርቱካን ይህን እያሳየች ነው ህዝብ የሚፈልገውን እያየ ነው ብርቱካን እያንዳንዱ ዚጋ ልብ ውስጥ እየገባች ነው የማሸነፊያ ጅማሬውን ከፍታለች ::

 8. TEZEBETYE
  | #8

  woyne mewdikyiaw tekerboal …selizhi yehn le mafaten ye tekawmi politca derjtoche ena degafiwch ..mewkasenena mewgagezen teten meserat ye migban be adenet …..ETHIOPIAN le madan mensat aleben

 9. ESKMECHE
  | #9

  YE WEKTU TEYAKE ENE EBELET NE AYDELEM ..ETHIOPIAN LE MADAN BE ANDNET ..YE TEKAWMI POLITICA DERJETOCHE ENA DEGFAWIWOCH MENSAT ALBEN

 10. ሲራክ
  | #10

  ጠይና ይስጥልኝ:: ለሙከራ ነው የጻፍኩት:; ይሄ ካለፈልኝ የምላቸው ቡዙ ነገሮች አሉ:: ሲራክ እባላለሁ::

 11. ዶክማስ
  | #11

  በታም የሚገርምነው እንዚህ ስዎቸ ከናያለውን አትዮፒያዊሁሉ አንገት ልማሰድፋት ክሰሙንበመስበር ሰለኅገሩ እንዳያሰብ ብእትዮፕያዊነት ላይ ገልስእ ቶርንተ አወጀዋል ማለትነው ?

 12. ዳካ
  | #12

  በርቱ ወገኖች

 13. ዶክማስ
  | #13

  ከኢቲዮፕያና ኢትዮፒያዊነተ ጋር ወድፊት ወያኒ እና ሆዳደር ባንዳዎች ወደመካአብራቻው አሚን

 14. እውነቱ
  | #14

  የዛች ሃገር እታ ፋንታ ምን ይሆን?

 15. ታሪኩ
  | #15

  ሲራክ ሲራክ ሲራክ በርታ በጣም ጥሩ ነው ግፋበት እንይህ!

 16. አባዳማ
  | #16

  በሁሉም አቅጣጫ: በሁሉም መንገድ ትግሉ ይቀጥላል:: አንድነት ፓርቲ በስላማዊ: የታጠቁት ደግሞ በመስሪያ: ሃይማኖተኛዉ በጸሎት: ሃገራችን ፍትህ እኩልነት እስኪስፍን እንዲሁም ዳር ድንበራችን እስኪከበር ትግሉ አይቆምም::

  ወያነ ያለዉ አማራጭ አንድና አንድ ቢቻ ነዉ:: የህዝብን ድምጽ ማዳመጥ:: አማራጭ ይዝው የሃገራችን ጉዳይ ያገባናል ለሚሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፍት ቦት ምልቀቅ::

 17. ታሪኩ
  | #17

  so what i need to do

 18. ተክሉ
  | #18

  ወያኔ ቢፍጭረጨር ትግሉ በምንም አይነት ወደሁአላ አይልም

 19. sam
  | #19

  Victory will be to the peopple and the peopple will win
  At the end . soon it will be Democracy in Ethiopia

 20. ሲራክ
  | #20

  አላማችን ምንድነው ? ግባችንስ ወዴት ነው ? ማነን ? ምንድነን ? ከየት ነን ? ወዴት ነን ? ……..!!!!
  ፍላጎታችን ምንድነው ? ስልጣን ነው ? የህዝብ ስቃይ ጩሀትና እንግልት የተሰማን ብሶተኖች ነን ? የዲሞክራሲ መረገጥ ያስቆጨን የመናገር የመጻፍ መብት በባለጊዢዎች መዘረፍ ያስቆጣን ፋኖዎች ነን ? ባቌራጭ ቤተ መንግስት ለመግባት የምንዳክር ተስፈኖች ነን ? ስርአቱ ሲለወጥ የካቦርታችንን ቀለም እየለዋወጥን የፊት ወንበር ላይ ለመቀመጥ የምንሻኮት ጊዜ ላነሳው ባለስልጣን ፖሎቲካዊ ንስሀ እየገባን ትንፋሻችንን ለማቆየት የምንተጋ ልምስምሶች ነን ? ወይስ የመጻፍ የመናገር የግልጽነት እሴቶች አገራችንን ውስጥ እንዲያብቡ የምንናፍቅ ለዘጎች መብት እዳር እስከ ዳር መከበር ራሳችንን ጭዳ ለማድረግ ያዘጋጀን ስልጣን በዘር በውልደት ባካባቢ ልጅነት ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ብቻ የተማከለ ሀላፊነትን ግልጽነትን ታማኝነትን ምርኩዙ እንዲያደርግ ለመጮህ የቆረጥን አንበሶች ! ነን ?? ማነን ? ፍላጎታችንን አውቀንዋል ? ራሳችንን ፈልገን አግኝተንዋል ? አላማችን ምንድነው ? ግባችንስ ወዴት ነው ? እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ ማንነታችንን እንመርምር …..ለየት ያለ አስተሳሰብ ሲመጣ ታዲያ ሳንበረግግ ሃሳብ እንለዋወጥ…ያ ነው ዲሞክራሲ !! ያ ነው ብስለት…ያ ነው እድገት:: ወንድም ታሪኩ ሰላምታህን ተቀብያለሁ:: እመለሳለሁ::
  _________________

 21. ውብሸት ግቅሬ ከለደን ከስደተና ካምብ
  | #21

  መልካም በአል ለሁላችን ይሁን ለመላዉ ለኢትዮጲያ በሙሉ መልካም በአል ይሁንልን

 22. ጌታ
  | #22

  ሲራክ ምን ማለትህ እንደሆነ አልገባኝም ስለዚህ ግልጽ አድርገው

 23. ሲራክ
  | #23

  አላማዬ ግልጽ ነው:: ወንድም ጌታ:: ይሀውልህ አላማውን ሳያውቅ ጦር ሜዳ የወረደ ተዋጊ ጥይት ሳይተኩስ እጁን ይሰጣል:: አላማ ይኑረን:: ዘዴ እንዘይድ:: ስሜታዊ አንሁን:: ተኩሰን ሳንገድል ፋኖ ነን እያልን አናቅራራ:: ጠላት ብለን ልንገጥመው ያሰብነውን አንድ ሃሙስ እንደቀረው መጻጉዕ አድርገን አንይ:: ስሜታዊነት ሳይሆን በመሬት ላይ ባለው ዕውነት እንመራ:: ይሄንን እያልኩ ነው ወንድም ጌታ::

 24. ሲራክ
  | #24

  የተጻፈ ነገር ማስተካከል(edit) እንዴት ይቻላል? እባካችሁ አስረዱኝ:: ለዚህ ፎሩም አዲስ ነኝ::
  አመሰግናለሁ:: ሲራክ ነኝ::

 25. ሲራክ
  | #25

  ከላይ ሳነብ “”ቻ”" በሚል ኒክ የጻፈው ወንድም (እህት) በርቱልን ይላል ወይንም ትላለች:: ምን ማለት ነው? ትግል ካምቦሎጆ ውስጥ የሚካሄድ የኳስ ግጥሚያ ነው እንዴ?
  ሲራክ ነኝ::

 26. ሲራክ
  | #26

  አንድነት ፓርቲ ወደሃገር ውስጥ ገብቶ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ በመወሰኑ ውሳኔአቸውን አከብራለሁ:: እደግፋለሁ:: የምድብለ ፓርቲ ስራአት እንዲዲመሰረት አንድነት ፓርቲ ፋና ወጊ ሆኖአል:: ታላቅ እርምጃ ነው:: የስራት ለውጥ ተራራ ላይ ተቀምጦ በሚጸላይ ጸሎት አይመጣም:: ጭጉጥ እየተደነገነበትም ቢሆን የሚታገል የሰላም ፋኖ ግን ቀኑ ይርዘም እንጂ የህዝባዊውን ስራት ቀንዲል እንደሚያበራ አይጠረጠርም:: ኢንችሃአላህ::
  ሲራክ ነኝ::

 27. ሲራክ
  | #27

  እንዴት ነው (SH) ባማርኛ መጻፍ የሚቻለው? ለምሳሌ
  SHጉጥ ብዬ ለመጻፍ ፈልጌ አቃተኝ::
  አመሰግናለሁ::
  ሲራክ ነኝ::

 28. አሰተዋይ
  | #28

  Popular democracy shall prevail in Ethiopia with the sacrifice you are making. The people of Ethiopia has been sending the message loudly and and clearly since May 2005. We shall overcome!! UDJ leaders we are proud of you!!

 29. ማስተዋል
  | #29

  Truth will prevail, it may take time.
  God bless Ethiopia.

 30. Anonymous
  | #30

  ሽፍት የምትለዋን ያዝ አድርጋትነ xተጭኣን

 31. gutema
  | #31

  AS far as iknow not only ethiopia but the whole africa is changing if we look back to 2005 the ppl of ethiopia voted for change but their vote was stolen by the ruling elites of woyane so the nation is yearning for democracy justies for all that is andinet for thatis why pplare rallying behind this party

 32. ሲራክ
  | #32

  Anonymous , አመሰግናለሁ:: “” ሽ”" ን መጻፍ ችያለሁ::
  ሲራክ ነኝ::

 33. Abebe gelaw
  | #33

  I don’t want to spread false news,and hand out unrealistic hope like some of you here, when infact weyane is getting stronger by the day as the opposition is fragmented than ever and in total disarray.
  Be objective, and not emotion ridden, that is the only way we can prevail!

 34. ደምበጫ ከለንደን
  | #34

  ሲራክ

  መግቢያ ጥሁፍህ ላይ ጠለቅ ብሎ የሚያስብና የሚያሰላ ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ ሃሳቦች ትንሰነዝራለህ ብዬ ገምቻለሁ ተስፋም አለኝ ግን ኋለኛው መልዕክትህ (ጸሎት የሚል ቃል ያዘለው) የአጋጭነት ጠባይ ስለሚያንጸባርቅ, ቀደም ሲል ብዙ ስለተባለበት ብዙ ስለሚታወቅ በጥያቄ መልክ ያስቀመጥከውን ቀደመት መልካም ሃሳብ እንዳደመስስብህ (ስለሚጣረሰው) በዚያ ሰፋ ባለው አመለካከትህ ምክር ብትለግስ የተሻለ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ:: የመጨረሻዋ አቀራረብህ አላማረችኝም ማለት ቅሬታ የለኝም አይደለም ግን በድረ ገጽ ማናፈሱ መፍትሄ አይሆንም::

  ካስመሳዮች ከስርጎ ገብ አጥፊዎ ይሰውረን::

 35. ሲራክ
  | #35

  ጥሩ ነው ወንድም ደምበጫን የለንደኑ:: አስተያየትህ መልካም ነው:;እኔ ይቺን ሳይት ያገኝኋት ትናንት ነው:: በቀላሉ ባማርኛ እንደዚህ ሃሳቤን መግለጽ በመቻሌ ስለተመቸኝ ነው መለስ መለስ ያልኩት:: አንተ እንዳስቀመጥከው አይነት ለመሆን ሃሳብም አቅሙም የለኝም:: የኔ እምነት ይሄም አይደለም ወንድም ደምበጫን :: ግን ነጻ በሆነ ዲሞክራሲያዊ ውይይት አምናለሁ:: በምንሰራው ስራ ግልጽ ስንሆን ታማኝነትን እናገኛለን:: ታማኝነት እውነተኛነትና transparacy ይፈጥራል:: ይሄንን ያማከለ የሰዎች ስብስብ ራሱንም አካባቢውንም ሀገሩንም ይለውጣል:: ደምበጫን የአንድን የፖሎቲካ ድርጅት አቋም የምትድገፈው ለምንድነው?? የምታውቃቸው ሰዎች ድርጅቱን ስለመሩት ነው? በአንደበተ-ርቱእነታቸው ተስበህ ነው? ወይስ በኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ ዲሞክራሲን ያሰፍናሉ ብለህ ስላመንክባቸው ነው? ዲሞክራሲ በኔ እምነት የምተፈልገውን ነገር ብቻ ቻናል እየቀየርክ የምትሰማው ሙዚቃ አይደለም:: የማትፈልገው ሃሳብም ሲመጣ የምታስተናግድበት መድረክ ሊሆን ይገባል:: የተለየ ሃሳብ ይዞ የመጣን ሰው “” ሰርጎ ገብ አስመሳይ”" ማለት መፍትሄ አይደለም:: ሃሳቡን እየው መዝነው ላገር ይዞ የመጣው ፋይዳ ካለ ፍትሸው…..ምርቱን ከገለባ የምትለይበትን መንሽ ያዝና አጥራው:: ሳንተያይ ነጻ ውይይት exersise ማድረግ ካልቻልን ባካል ከተገናኘን በጥይት እንዳንጠዛጠዝ ያሰጋል:: ዲሞክራሲዊ ባህላችን ከኛነታችን ጋር አብሮ መቀየር አለበት ደምበጫው ወንድሜ:: ” A spade a spade” ማለትንም መማር አለብን:: አንተ የምትለውን እኔ እያዳነኩ (apperciate) እያደረኩ የምደግምልህ ከሆነ የገደል ማሚቶ ሆኛለሁ ማለት ነው:: እኔ በዚህ አላምንም ::የተለያየ ህሳብ ይምጣ ይንሸራሸር::ብስሉን ከጥሬ እንለይ::ነጥሮ የወጣውን ለሀገራችን እንስጥ:: እንደዚህ አይነት ውይይት ለማድረግ ይሄ መድረክ የሚፈቅድልኝ ከሆነ አብሬአችሁ አለሁ:: “ይ እኛ የምንለውን ስማ “ከሆነ ግን አንብቤአችሁ ሹልክ እላለሁ:: ቅቅቅ:: ሰላም ሁኑ::
  ሲራክ ነኝ:: ከሞት ሃገር::

 36. ደምበጫ ከለንደን
  | #36

  ሲራክ ያስብልሀል ማለት ነህ አይደለም ባጭሩ:: ግን ሰው ያወቀውን ጠሐይ የሞቀውን መደጋገሙ ለመከራችን መፍትሄ አይሆንም:: በጠቆምከው እኔም ያዝንክበትና ቅር የተሰኘሁበት መሆኑን እወቅልኝ:: አንድ ያላየህልኝ ቢኖር ባፈ ምላጮች እማልደለል መሆኔን ሲሆን ግምትህ ከእውነቱ የራቀ ነው እያልኩ አካፋን አካፋ ማለቱን እየተስማማሁበት ሊባሉ የሚገባቸው ሀገር አጥፊዎች ላይ የጋራ ጠላቶቻችን ብናተኩር ይሻላል ብዬ ነው:: ካልመሰለህ በሃሳብህ ብትገፋበት ለኔ ችግር አይፈጥርም የምመኘው ነጻነት ነውና::
  እኔም ትንሽ ሳቅ ብያለሁ::
  ቸር ይግጠመን::

 37. ላጤው
  | #37

  ወንድም ሲራክ
  ከላይ የጻፍካቸውን አነበብኩ:: ሆኖም ሃሳብህና አቀዋምህ ሊገባኝ አልቻለም:: ኢህአዴግን መደገፍም ሆን ከአንድነት ፓርቲ ጋር መቆም የግል መብትህ ነው:: እኔም ይህንን ልነግርህ አይገባኝም ብዙ የምታውቅ ነህና::
  እኔ የአንድነት ፓርቲ ደጋፊ ነኝ:: ፓርቲውን የምደግፈው የምወዳቸው ሰዎች ስላሉበት አይደልም:: በሰላማዊ ትግል NON VIOLENCE ፍልስፍና ስለማምን ነው:: በዚህ በኩል የሚመጣው ደግሞ ዘላቂነት ያለውና ለሁሉም የሚበጅ ነው:: የአንድነት ፓርቲ ዋናው መመሪያም ይሀው ነው:: ከዚያ በላይ ደግሞ የድርጅቱን የፖለቲካ መመሪያ ሄደህ ብታነበው ግልጽ በሆነ መንገድ ተቀምጦ ታግኘዋለህ:: ጉዳዩን ለማሳጠር የኔ የፖለቲካ አመለካከት እና የምደግፈው ፓርቲ ይህንን ይመስላል:: አንተስ? ሃሳብህን እንደዚህ ግልጽ ብታደርገውስ ምን ይመስልሃል? ከዚያም ውይይቱን በየፈርጁ መቀጠል እንችላለን::

  ሰላም ሁን!!!

 38. Yikerbelen
  | #38

  Be united , and stand together,and firmly and push one step forward hard, TPLF will be overthrown. Only through strong unity we can free our selves from cancer. No one will free from TPLF’s oppression untill we all free together.

 39. ሲራክ
  | #39

  ሰላም ወንድሞቼ ደምበጫንና ላጤው እንዲሁም ሌሎች:: ላስተያየታችሁ አመሰግናለሁ:: እንወያያለን :; መወያየት መልካም:: ዲሞክራሲ በመወያየት ውስጥ አለች:: ትኖራለች :; ታብባለች:: ትበለጽጋለች:: ስንወያይ መፍትሄ አለ:: ስንወያይ የውስጣችንን ብቻ ሳይሆን የውጭውን አለም ድምጽ መስማት ማጣጣም እንጀምራለን:: ባለፈው እንዳልኩት ላገር የሚጠቅመውን አጥብቀን እንይዛለን:: የማይሆነውን እናጓልላለን:: መፍትሄው እሱ ነው:: እኔ በዚች ሃገር ዲሞክራሲ እንዲኖርና እንዲከበር እንዲሁም ያሉት ዲሞክራሲኢአዊ ኢንስትቱዩቶች ተግባራዊ ( functional) እንዲሆኑ ከሚፈለጉና ከሚተጉ ኢትዮጵያውያኖች አንዱ ነኝ:: የፓርቲዎች ደጋፊ ሳልሆን የዲሞክራሲ ደጋፊ ነኝ:: ዲሞክራሲ ቤቷ የት ነው? መልኳ ስንት ነው?? ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው ? እንደት ትፈቱታላችሁ? ኢንሳይክሎፖዲያ አያስፈልገንም :: የሮኬት ሳይንቲስት መሆንን አይጠይቅም:: ውስጣችንን ውስጥ የሚፍልቀለቀውን ዐምሮአችን የሚያንተከትከውን እናውጣና እንወያይ:: ላጤውና ደምበጃን ወንድሞቼ:: ሰሞኑን የኑሮ ጉዳይ ስለሆነብኝ ነው ቶሎ ቶሎ ብቅ ያላልክት:: ለመልሳችሁ አመሰግናለሁ:: ሃሳብ በመለዋወጥ ላገራችንና ለህዝቧ የሚሆን መፍትሄ እንደምናገኝ ተስፋዬ ነው::
  ሲራክ ነኝ:: ከምድር ጫፍ::

 40. ኣራዳ
  | #40

  የሲራክ ነገር አልጣመኝም……..

 41. ኣራዳ
  | #41

  እሺ ሌላ ግዘ ብቅ እላለሁ::

  ሰላም!!

 42. ሲራክ
  | #42

  ይጣምህ ይጣምህ ወንድሜ አራዳው:: ኢንዲጥምህ ግድ ነው:: የሚስማማንን ሙዚቃ ብቻ መስማት ዲሞክራሲ አይደለም:: ዲሞክራሲ በማይጥምህ ነገር ላይ መወያየትን መነጋገርን ብሎም መደራደርን ይሻል :: እኔና አንተን የሚያስማሙን ነገሮች ይኖራሉ:: ዲሞክራሲ በማያስማሙን ላይ የምናቀርበው አርጉዩመንትና ያንን አርጉዩኢምነት የምንፈታበት አካሄድ ነው :: የዲሞክራሲ ጥልቀታችን የሚለካው በምንጠቀምበት የአፈታት ስልት ነው:: እሱ ነው ቴርሞሜትሩ:: አራዳው ሰላም ሰላም ነው አባ:: አይዞህ:: እንደምታስበው አይደለሁም:: ግን እኔ የምለው ተቃዋሚዎች ሃላፊነት እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ የሚገባንን አድርገናል ወይ? የቤት ስራችንን ሰርተናል ወይ? በኢህዳግ ላይ ጣት ስለጠቆምን ብቻ የሀገሪቷ ፖሎቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ይፈታሉ ወይ? ለምሳሌ እኛ በህዝብ ምርጫ አሸንፈን ስልጣን ብንይዝ አንድ ባንድ የወያኔን ባለስልጣን እንደ ዶሮ እያነቅን ሲጥ እናደርጋለን ቢል አንድ የተቃዋሚ መሪ ስልጣኑን ለህዝብ በፍቃደኝነት ለመልቀቅ የሚፈልግ የሂሃደግ አባል አለ ወይ? በኛ በኩል ለሰላማዊ ሽግግር ያዘጋጀነው “” safe heaven “” ስ አለ ወይ? እኛስ እራሳችን ከNON VIOLANCE ሽግግሩ ጎን ለጎን ላሉት ባለስልጣናት smooth transtion እንዲካሄድ ያመቻቸነው ምን አለ ? ይሄ ጥያቄ ጊዜውን ያልጠበቀ ሊሆን ይችላል:: አንድ ቀን ግን መጠየቁ አይቀርም:: መወያየት መጥፎ አይደለም እንወያይበት :: እኔ የይሄንን የምለው የኢሃድግ አባል ሆኘ አይደለም:: ግን ይህ አይነት መንፈስ በነሱ መሃል እንደሚናኝ ይሰማኛል::
  ሲራክ ነኝ::
  ሞቼ ነበር ተነሳሁ::

 43. ቲዎድሮስ አበበ
  | #43

  እናግዛአችሃለን

 44. Tewodros Abebe
  | #44

  we gat your back

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።