ቃሌ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ ፤ ሰላማዊ ሰልፍም በዚህ ወር መጨራሻ ላይ ይጠራል።

January 29th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

አቡጊዳ / ጥር 21 ቀን 2001 ዓ.ም.

የብርቱካን መታሰር የአንድነት አባላት፣ ደጋፊውችና የነፃነት ናፋቂዎች ሁሉ እስር ነው ሲሉ ኢ/ር ግዛቸው ገለፁ፡፡ ትላንት ማምሻውን የወ/ሪት ብርቱካንን በግፍ መታሰር አስመልክቶ ፓርቲው ‹‹ቃሌ›› በሚል ስያሜ የሻማ ማብራት ስነ ስርአት አካሂዷል፡፡

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በግፍ የታሰሩበትን አንደኛ ወር ለማስታወስ በተዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም ላይ ከ300 በላይ አባላትና ደጋፊዎች የተገኙ ሲሆን ግጥሞች፣ መጣጥፍና ለእርሳቸው የተዘጋጁ ሙዚቃዎች ቀርበዋል፡፡

ፕሮግራሙን በንግግር የከፈቱት ዋና ፀሀፊው አቶ አስራት ጣሴ ሲሆኑ ‹‹የብርቱካን መታሰር የአንድነትን፣ የህግ የበላይነትንና የሰላማዊ ትግል ተስፋን የሚያቀጭጭ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም በትኩረት እናየዋለን ያሉ ሲሆን፡፡ ስለ ወ/ሪት ብርቱካንም የሚከተለውን ብለዋል፤ ‹‹ብርቱካን የመጀመሪያዋ ሴት፣ ወጣትና የትልቅ ፓርቲ መሪ ናት፤ የግል ህይወት የላትም፤ ህይወቷ አንድነት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ይጠራ ከተባለ የምትመጣው ህፃን ሴት ልጇ ሀሌ ናት፡፡ ህይወቷ ለህግ የበላይነት መከበር የተሰጠ፤ የነፃነትና የህግ የበላይነት ምልክት ናት፡፡››

ቃሌ የሻማ ምሽት ዝክረ ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ ወጣት ሀና ዋለልኝ ‹‹ዳኛዋ ዳኛ አጣች››፤ ወጣት ስለሺ ‹‹ይድረስ ላንቺው›› የሚሉ ግጥሞችን ለታዳሚው አቅርበዋል፡፡በመጨረሻም የሻማ ማብራት ስነስርአቱን ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው እንዲያስጀምሩት ወደ መድረክ ወጥተው አጭር ንግግር አድርገዋል፡፡ ኢ/ር ግዛቸው ብርቱካንን ለማሰብ የመጡትን እንግዶች ካመሰገኑ በኋላ ‹‹ቃሊቲ በነበርን ጊዜ የነበረንን ነፃነት ሳስበው ያኮራኛል፡፡ ያኔ የታሰርነው እኛ ብቻ ሳንሆን ህዝቡ ጠቅላላ ነበር፡፡ ዛሬም ብርቱካን ለዲሞክራሲ፣ ለነፃነት ስትል እስር ቤት ገብታለች፡፡ የታሰረችው እርሷ ብቻ አይደለችም፤ የአንድነት ደጋፊዎችና አባላት ጭምር እንጂ፡፡ እኛም ከህሊና እስር የምንፈታው እርሷ ስትፈታ ነው፡፡ የብርቱካን እስር የነፃነት፣ የኢትዮጵያዊነት ምልክት ነው›› ብለዋል፡፡ አክለውም ይህ ፕሮግራም የመጀመሪያው እንጂ የመጨረሻው አይደለም፤ ቢያንስ በየወሩ ለማክበር ቃል እንገባለን፡፡

የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ዶ/ር ሀይሉ አርአያ ብርቱካን የተያዘችበት ሁኔታ ምንም የህግ ድጋፍ የሌለው ስለመሆኑ ከባለሙያዎች ጋር ተነጋግረን ትንተና እየሰራንበት ነው፤ ግርድፍ የሆነ ውጤት አግኝተናል ያሉ ሲሆን፤ ‹‹ጉዳዩ እርሷን ከማስፈታት በተጨማሪ ለታሪክም የሚቀመጥ ነው›› ብለዋል፡፡ ዶ/ር ሀይሉ ብርቱካን እስካሁን ለብቻዋ እንደታሰረች፣ ጠበቃዋን ለማግኘት እንደተከለከለች፣ ከእናቷና ሴት ልጇ በስተቀር ማንም እንዲጎበኛት አለመፈቀዱን አስታውሰዋል፡፡ ‹‹አንድ እስረኛ በሀይማኖት አባቶች፣ በቤተሰብ፣ በጠበቃ የመጎብኘት መብት እንዳለው በህግ ተደንግጓል፡፡ ቢሆም እኛ ይህን መብት ተነፍገናል፡፡ ማረሚያ ቤቱ እምቢ ስላለ ለፍትህ ሚንስትር በደብዳቤ እንጠይቃለን፤ በዚህም የማይቻል ከሆነ ወደ ፍ/ቤት እንወስደዋለን ሲሉ ስለ ወቅታዊ ሁኔታው አስረድተዋል፡፡ በቅርቡም ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን፤ ለዚህም የሚያስፈልገውን የህግ ፎርማሊቲ እያሟሉ እንደሆነና በዚህ ወር መጨረሻ ለማካሄድ እንዳቀዱ አስረድተዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ባለፈው ሳምንት አጋማሽና መጨረሻ ላይ የስራ ጉብኝት ለማድረግ የተንቀሳቀሱት ቡድኖች በአብዛኛው የተሳካ ስራ ሰርተው መመለሳቸውን ዶ/ር ሀይሉ ገልፀዋል፡፡ ቀድሞ የተነሳውና በአቶ ተመስገን የሚመራው የደቡብ ልኡክ ከ3000 ኪ.ሜ በላይ አካሎ 17 ቢሮዎችን ጎብኝቶ የለመሰ ሲሆን አብዛኞቹ ስራቸውን ባግባቡ እያከናወኑ እንደሆነ፤ ነገር ግን በቦዲቲ ከተማ ያለው ቢሮ በአካባቢው ባለስልጣናት አማካኝነት እንደተዘጋ አስታውቀዋል፡፡ አቶ ተመስገን ስለሁኔታው ሲናገሩ ‹‹በቢሮው ውስጥ የነበሩ እቃዎች ወጥተው፣ ታፔላውና ሰንደቃላማው ወርዶ ነው የጠበቃቸው፡፡

ወደ ሰሜን የተጓዘው በዶ/ር ያቆብ የሚመራው ቡድን ጉብኝቱን ከደብረ ብርሀን የጀመረ ሲሆን ሰባት አዳዲስ ቢሮዎችን ከፍቶ እንደሚመለስ ይጠበቃል፡፡ ቡድኑ በመርሳ አካባቢ ሲደርስ ለሰአታት ታስሮ እንደነበር የሚገልፁት ዶ/ር ሀይሉ ‹‹የመንግስት ካድሬዎች ካላቸው ጠባብ ግናዛቤ የተነሳ፤ አልያም ሆን ብለው ስራችንን ለማደናቀፍ በሚመስል ሁኔታ አባላቶቻችንን ለሰአታት አስረውብናል›› ብለዋል፡፡ ዶ/ር ያቆብን ጨምሮ አቶ ይልቃል፣ አቶ ብሩ ብረመጃ፣ አቶ አለባቸው ከዚህ የተላኩ፤ አስር ከአካባቢው ከመጡ አባለቶች ጋር ስብሰባ በማድረግ ላይ እያሉ በፖሊስ ‹‹የምታደርጉትን ስብሰባ አላሳወቃችሁም›› በሚል ተይዘው ለሰአታት እንዲታሰሩ ተደርጓል፡፡

አቶ ብሩ በርመጃ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው መታሰራቸው የሚያመለክተው ለምክር ቤቱ አባላት የሚሰጠው የህግ ከለላ እንደማይከበር ነው፡፡ ከዚህ በፊትም በደንደጫን ወረዳ አ/ር ግዛቸውን ጨምሮ የተወካዮች ምክርቤት አባላት መታሰራቸው አይዘነጋም፡፡

 1. ሊሊ
  | #1

  አው የብርቱካን መታሰር ምንም ለሶ ሌከብዳት ቢችልም ከትግል ውስጥ አንድ ነው የሶ መታሰር በተዘዋዋሪ ለሶ እውቅናና የሚሰጥ ነው ወያኔ ሳያውቀው የተሳሳተው እዚህ ላይ ነው ::
  ከመታስር በላይም ሊመጣ ይችል ነበር ያ አልሆነም ቢሆንም የትግል ውጤት ነው “”
  አሁን እሶን ምንም ሊያረግ አይችልም በውጭም በውስጥም እውቅና አግኝታለች በተለይ የውጭ ምንግስታቶች ስለሶ መፈታት መግለጫ ማውጣት ለብርቱካን ትልቅ ድል ነው በተዘዋዋሪ ወያኔ እየታሰረ ይገኛል ወያኔውች ነገሮች እየከበዱባቸው ነው አሁን አልተፊሻል ፊክ እየሆኑ ነው ::

 2. ወጌስአው
  | #2

  እነሱ:መች:ታስረው?

  ብርቱካን መች ታሰራ;
  ክቡር መስፍን መደብደቡ የተወራ?
  ወጥኣቱም ተዲ እንደ ብርሃኑ እንዳበራ;
  የሀዝቡን ልብ ከልቡ እንዳኮራ;
  አይነጋም ወይ ሌቱ ብሎ እየተጥኣራ;
  አይ መብዛቱ የኢትዮጵያ መከራ::

  ብርቱካን አልታሰረች ይብላኝ ለሆድ አደሮች;
  ህሊናቸውን ክደው ለሆኑ ደላሎች;
  አምበሳው መስፍንስ መች ተዋርዶ? ቢመታ በምች;
  ውርደትማ ነው ለነፍስ አጥፊዎች
  አይዞን ከአዘቅት ሃገር ትወጥኣች::

  ምነው ባገራችን መከራው መብዛቱ;
  ረሃቡ በስታው ሰደት ጥኦርነቱ;
  የናት ጥኡት መንከሱ ሌብነት ከህደቱ;
  አስራት ወልደየስም በገዳይ እጅ ሞቱ?

  የኢትዮጵያ ልጆች ተነሳሱ በርቱ;
  ሃገር አፍረታለች ብርቱካን ከጥንቱ;
  ካሳ ዮሃንሱን ምኒሊኩን ጥኣይቱ;
  ያገር እንባ ይድረቅ በመስዋእትነቱ::

  ብርቱካን ለህዝብ ብላ “ቃሌን አላጥፍም”;
  ተዲም ተቀብሎ “ከቡር ሰው አልገድልም”;
  ህዝብ አራጅ ማን እንደሁ እያወቀው አለም;
  ሳታመህኝ ብላኝ ነገሩ ቢሆንም;
  እስረኝኣ እራሱ ጼረ ሕዝብ ስላም::

  ብርቱካን መች ታስራ ነገሩ እንዼት ነው;
  ገፍ ደም አፍሳሶች በህዝቦች ተከበው?
  መስፍን መች ተዋርዶ ህዝብን ባስተማረ;
  ከሱማሌ ምድር አጅሬ ሲባረር;
  ህዝቡ ባልፌቀደው ጥኦርነት ሲማገር;
  እናንተው ፍረዱት ማን አለበት ማፈር?

  ተዲ ምን አጥፍቶ በሃሰት ታሰረ;
  በመረዋ ድምጽኡ እውነት ባበሰረ?
  ምን ጉድ ነው ዘንድሮ ኢትዮያ ሃገረ
  ምርጥ ልጆችዋን ከይሲ ተጽኣረረ?
  ትንሳኤው ቅርብ ነው ገዳይዋም ይረር::

  አንዲት ኢትዮጵያ:ደግሞ እንደ ትላንት;
  አንዲት ኢትዮጵያ:ዛረም የሁሉ ናት;
  አንዲት ኢትዮጵያ:ለዘላለም ውህደት
  ተነስ ኢትዮጵያዊ:ሕዝብ አድን ባንድነት!

  አቢሲንያዊው:ከኢውሮፕ (05/01/2009)

 3. ዓቢይ
  | #3

  “እንደገና አበራ! እንደገና አበራ! የብርቱካን ስራ! እያልን እንዘምራ. ጎበዝ ታሪክን ብቻ እንፍራ. ማድረግ የሚገባንን ሳናደርግ ቀርተን
  እንዳይፋረደን የታሪክ አሻራ. በያለንበት የብርቱካንን ስም እንጥራ.
  የውያኔን መርበድበድ ብገሀድ የምገልጽ አንድ አስቂኝ ፊልም ዛሬ በውያኔው ቱልቱላ በአይጋ ፎረም
  ተምልክቻለሁ. ፊልሙ, ባንጋፋው ፕሮፌሶር መስፍን, በኢንጅኔር ሃይሉና በአርቲስት ደበበ እሸቱ
  ላይ ያተኮረ, በቅጥር ስም ገዳዮች የተዘጋጀ ለፈፋ
  ነው. እነዚህ ይሰሩትን ያሳጣቸው ወያኔዎች ወገኖቻችንን የበለጠ እንዲወደዱ እድርገዋቸዋል. የሚቀርብባቸው ስሞታ ሁሉ የሚባረቅ ነው. ለህዝብ መቆማቸውን ያረጋግጣል እንጅ ከህዝብ ጋር ይሚያጣላ አይደለም. ቶሎ ካላጠፉት አይቶ መሳቁ
  ወያኔ ምን ያህል እንደከሰረ ያረጋግጣል. ለመሆኑ ምን አስበው ይህን ቅስቀሳ አዘጋጁ? ለምስቦካት? ማነን? አይውቁአቸውም ማለት ነው?

 4. ታዛቢ
  | #4

  አዲስ ኮሚክ ነገር የአዉሮጳ ሕብረት የኢትዮጵያን የልማት ፕሮጄክቶች ለማስፈፀሚያ 251 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 322 ሚሊዮን ዶላር ረዳ,,, ድሮስ ክፈረንጅ ምን ይጠበቃል, ጀርመን
  http://www.dw-world.de/dw/0,,611,00.html

 5. Yikerbelen
  | #5

  SHAME ON EU.LET GOD PUNISH YOU. YOU ARE SHAMEFULL PEOPLE. YOU ARE CONDOMNING MUGABE AND SUPPORT ONE OF THE WORST EAST AFRICAN’S ADOLF HITLER WHO COMMITTED A CRIME AGAINST ETHIOPIA’S PEOPLE EVERY WHERE.YOU ARE CONDOMNING MUGABE, BECAUSE MUGABE HAS TAKEN THE LAND FROM BRITISH FEUDALS AND DISTRIBUTED TO LANDLESS ZIMBABWEANS. THAT IS MUGABE’S CRIMES.SUPPORTING MELESE ZENAWI MEANS SUPPORTING HITLER’S ACTION AGAINST 6M JEWISHES SOME 65 YEARS AGO. BUT BE SURE YOUR PUPPET MLESE WILL LEAVE ETHIOPIA WHETHER YOU LIKE IT OR NOT. YOUR 251M EUROS WILL BE INVESTED FOR KILLING OF INNOCENT ETHIOPIANS.

 6. tesfu
  | #6

  My Brothers…This is Mr. Idiot… wherever you are, We will hunt you. You are fighting for Power. We know clearly that your intention IS to share power with your croni bastard(Issayas Afeworki); THE PARASITIC WOYANE.

  Death for baneda(Solomon Tekaligne)
  Death to woyane(parasite)
  Death to OLF
  Death to tplf
  Death to Ethiopian review(Shabia)
  Death to onlf
  Death to hodamoche(talkatives)

  VIVA TRUE ETHIOPIANS WHO ARE FIGHTING FOR TRUE DEMOCRACY!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
  Viva UDJP!!

 7. Anonymous
  | #7

  እግዚአብሂር ይርዳችህ!!!!!!!!! ምንም እንኩዋን እኒም እንደእናንተ እስር,ድብደባ,የግድያ ሙከራ የደረሰብን ብሆንም መቻል ሲያቅተን ሃገረንትቸ በስደት እገናለሁ የኢትዮ አምላከ ሀዝብዋን መሪወችዋን ከእስር ያሰፈታ!!!

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።