በሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ሰጭ ማኅበር መግለጫ

September 23rd, 2011 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባርና ግብረ አበሮቹ በተቃዋሚዎች ላይ በሚያካሂዱት የእሥር ዘመቻ
ከሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ መግለጫ
(መስከረም 11፤ 2004 ዓ ም)

የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባርና ግብረአበሮቹ በተከታታይ በተቀዋሚ ድርጅቶች አመራርና አባላት፤ በግል ጋዜጠኞችና አርቲስቶች ላይ ባጠቃላይ በተቃዋሚ ድርጅቶች አባላት ላይ እያካሄዱ ያለውን የማሰርና የአፈና ዘመቻ በጥብቅ እናወግዛለን። በቅርቡም ያለአንዳች ማስረጃ በፍርሃት ላይ በተመሠረተ ስሌት ብቻ የግል ኑሮአቸውን በሰላም ከሚያከናውኑበት ቦታ በሽብርተኝነት በመወንጀል በግፍ ያሰሯቸውን፤
1. ኣቶ ደበበ እሽቱ፤ አርቲስት፤
2. አቶ አንዱአለም አራጌ፤ የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ም/ፕሬዘደንትና የሕዝብ ግኑኝነት ሃላፊ፤
3. አቶ በቀለ ገርባ፤ የተቃዋሚ ድርጅት ሥራ አመራር አባል
4. አቶ ኦልባና ሌሊሳ፤ የተቃዋሚ ድርጅት ሥራ አመራር አባል
5. አቶ ናትናኤል መኮንን፤ የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ አባል
6. አቶ ዘመኑ ሞላ፤ የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ አባል
7. አቶ እስክንድር ነጋ፤ ጋዜጠኛ
8. ወ/ት ርዕዮት ዓለሙ፤ ጋዜጠኛ
9. አቶ ውብሸት ታዬ፤ ጋዜጠኛ
10. አቶ ስለሺ ሃጎስ ፤ጋዜጠኛ
ሌሎችም እንደዚሁ በሥር ላይ የሚገኙ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ እንዲለቅ በጥብቅ እናሳስባለን። እነዚህን ግለስቦች የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርና የዓለም ሕብረተስብም ጭምር በተለይም የዓለም አቀፍ ስብአዊ መብት አስጠባቂ ድርጅቶችና የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ደህንነት ማህበር ለሀገሪቱ ደህንነት ተቆርቁረው በነፃ ሃሳባቸውን ከመግለጽ ሌላ በሽብርተኝነት የሚያስከስስ ወንጀል እንደሌለ ባወጡአቸው መግለጫዎች አስታውቀዋል። የዘረኛው አምባገነን መንግሥት ዓይን ባወጣ መልኩ ፈጥሮ ያቀረበው ክስ የሚያስገርም ከመሆኑም በላይ በዓለም ሕዝብ እይታም አሳፋሪ ተግባር ነው። ዋነኛ ዓላማው ግን በተቃዋሚ ድርጅቶች፤ አባላትና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ፍርሃት ፈጥሮ ብሶቱን እንዳይገልጽና ለዘረኛና አምባገነን አገዛዙ እንዲንበረከክ ለማድረግ እንደሆነ አያጠራጥርም።
በመሠረቱ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር በመሣሪያ ሀይል በሕዝባችንና በሀገራችን ላይ የተጫነ ሲሆን እነሆ ላለፉት ሀያ ዓመታት እንደፈለግው ሲያስር፤ ሀገር ቆርሶ ሲሸጥ፤ ሕዝባችንን በረሀብ ሲቀጣ፤ ለዘመናት ተሳስረው የኖሩ ወገኖቻችንን በዘር ከፋፍሎ ለዘመናት የሚቆይ ውዝግብ ውስጥ ለመክተት ያላሰለስ ጥረት እያደረገ ፤ያለ ሀይሉን በመጠቀም የሕዝቡን የምርጫ ድምጽ በጉልበት በመንጠቅ በሥልጣን የቆየ ነው።
በትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር የሚመራው አምባገነን መንግሥት የሚያወጣቸው ሕጎች፤ የሚፈጥራቸው መ/ቤቶች የጦርና የፖሊስ ሀይሎችን ጨምሮ ሁሉም የአገዛዙን ደህንነት የሚጠብቁና ዕድሜውን የሚያራዝሙ ተግባሮች እንዲፈጽሙ ታቅደው የተፈጠሩና የተዋቀሩ መሆኑን ለአንድ አፍታም መዘንጋት የለብንም።
ስለሆነም በሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ማህበር፤
1. ከፍ ብሎ ስማቸው የተጠቀሱትና ሌሎችም በየክፍለ ሀገሩ የታሰሩ የፓለቲካ እሥረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እየጠየቀ ለዚህም መሠረተ ቢስ ክስና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደረግ የስብዓዊ መብት ረገጣ መለስና ግብረ አበሮቹ ተጠያቂ መሆናቸውን በጥብቅ እናስታውቃለን።

2. የኢትዮጵያ ሕዝብ እየደረሰበት ስላለው መራራ የኑሮ ሁኔታና ለዚህም መፍትሄ የሚላቸውን ሀሳቦች በሰላማዊ መንገድ በአደባባይ ወጥቶ ለመግለጽ የጠየቀው ጥያቄ እገዳው ተነስቶ ብሶቱን መግለጽ እንዳለበት እናምናለን። ሰልፍ የማድረግ መሠረታዊ መብቱ ስለሆነም ከማንም ፈቃድ አያስፈልገውም እንላለን፤ በነቂስ በአደባባይ ወጥቶም ብሶቱንና ፍላጎቱን መግለጹን የምንደግፍ መሆኑን እንገልጻለን። ይህ መብቱ እስኪረጋገጥለት ድረስ በሚቻለን አቅም ባገኘነው መድረክ ሁሉ ካለማሰለስ የምንታገል መሆኑን እንገልጻለን።
ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር
በሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ሰጭ ማህበር

  1. ኩማ
    | #1

    መቼም በወያኔ ያልተለጠፉትን ይበልጥ እንድናቃችው እይተደረገ ነው. ተለጣፊዎቹማ ጭራሽ ጥበቃ እይተደረገላቸወ ነው. በሳቅ የሚገል ነገር አቶ ልደቱ(ክህደቱ) ለስሙ ተቃዋሞኢ ናቸው ነገር ግን በጥበቃ ይንቀሳቀሳሉ አይታያችወም እወነተኛ ተቃዋሚ ቢሆን ክፉ እንዳይነካው ሲጠበቅ አይታየንም????? እወነተኛ ተቃዋሚ ወደ እስር ቤት እናም ነጻነት አይቀረም ህሏም የስራዋን ታገኛለች. እንዚህ ንጽሃን ግን ሰላማዊ እና አገሪቱ ውስጥ እይተደረገ ያልወን ነገር እያዩ ስለተናገሩ ሽብረተኛ አለ ይህ ደረቅ ውሸት የማይሰለቸው መንስት እራሱ ሽብረተኛ ዘራፊ እና ሌባ. እናንተ ሰዎች አይዟችው. ታሪክ የማይረሳችው ልጆቻችው ቀና ብለው የሚሄዱበትን ተከብረው እና ተወደው የሚኖሩበትን ትልቅ ስራ ነው የሰራችወት መላው ህዝብ እንደው ሽብረተኛወን በደንብ ያውቃል. ፍርሃታቸው የፈጠረባችው ሽብር ነው. እናንተ ግን የሰላም ታጋዮች ናችው.

  2. በራ በብራቱ
    | #2

    እንሰሳው የበረቱን በር ሰበረ:
    ኩማም እነድሰው አስቦ እስይ መናገር ጀመረ:
    ድምክራሲያችን ዳበረ:
    መብታችን ተከበረ::
    አገራችን ለማች በለጽገች:
    ስሟንም አችመለስች::
    ኩማም ይመልከት ወድ በሩ:
    እንድመለስ ወደ አገሩ::

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።