የሕገ-መንግሥት ጥሰቱና ገደብ የለሽ አምባገነንነቱ እየጨመረና እየባሰበት ነው!! ከአንድነት ፓርቲ የተሠጠ መግለጫ
በመርህ ደረጃ የምናውቀውና በትምህርት ቤት የተማርነው ሰዎች ከታሪክ ይማራሉ በዚህም ስህተቶች እየታረሙ ይሄዳሉ፣ አይደገሙም የሚል ነው፡፡ ነገር ግን የሕይወት እንቆቅልሽና በተግባር ስናየው ታሪክ፣ የሚያስተምረን፣ ሰዎች ከታሪክ የማይማሩ መሆናቸውን መሆኑ የሚያስገርም ነው፡፡ ይበልጥ አስገራሚው ደግሞ ሰዎች እንኳን ከአለፈ ከታሪክና በፊት ለፊት ከሚያዩት፣ ከሚሰሙትና ከሚያውቁት እውነታም እንደማይማሩ ነው፡፡ በተለይም አምባገነኖች፤ ጥቂቱንና የቅርቡን ለመጥቀስ፤ የግብፁ ሙባረክ ከቱኒዚያው በንዓሊ አልተማሩም፡፡ የሊቢያው ጋዳፊ ከግብጹ ሙባረክ አልተማሩም፡፡ የየመኑ ዓሊ አብደላ ሳሊሕና የሶሪያው በሸር አልአሳድ ከጋዳፊ የተማሩ አይመስሉም፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ አንዱ ከሌላው የማይማር መሆኑ የቀጠለና የማያቋርጥ ክስተት እየሆነ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ከምንም በላይ ግልጽ ሆኖ የመጣው ጉዳይ ከአለፈ ታሪክ፣ እንዲሁም ከፊት ለፊት ከሚያዩትና ከሚሰሙት አለመማር የአምባገኖች አንዱ ዓይነተኛ ባህሪ መሆኑ ነው፡፡
ከላይ በመንደርደሪያ የጠቀስናቸው አስተያየቶች ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ በአገራችን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥትና የገዢው ፓርቲ እያደር እየታረመ፣ እየተማረ፤ እየሰከነና ልብ እየገዛ ይመጣ ይሆናል እያልን ስለ አገር፣ ስለ ሕዝብና ስለ ራሱም ብሎ የሕግ የበላይነት እንዲያስከብር ደጋግመን ሳንሰለች ስንጎተጉተው ብንከርምም ሰሚ ጆሮ አልተገኘም፡፡ እንዲያውም ይባስ ብሎ አምባገነኑ መንግሥት ሲፈልግ በየጊዜው በሚያወጣቸው አሳሪና አስፈሪ አዋጆች ከፈለገም ያለምንም አዋጅ በጠራራ ፀሐይ ሕገ-መንግሥቱን በጉልበት እየጣሰ ነው፡፡ ዜጎችን አክብሮ መከበር ለመንግሥት ባዕድ ነገር ሆኗል፡፡ መንግሥት በዜጎች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት ተጠያቂነት የለበትም፡፡ ‹‹ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው›› የሚለው የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 24 ተ.ቁ 1 የወረቀት ላይ ጌጥ ሆኖ ነው የቀረው፡፡ በመሆኑም መንግሥት ያለምንም ጥንቃቄና ማስተዋል ከጳጉሜ 2ዐዐ3 ዓም ጀምሮ የሠላማዊና ሕጋዊ ፖለቲካ አራማጆችንና ነፃ ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት ከሶ ወደ ወህኒ ቤት አውርዷቸዋል፡፡ ታሳሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ በአንድ በኩል በታክስ ከፋዩ ሕዝብ ገንዘብ የሚንቀሳቀሱት ቴሌቪዥኖች ሬዲዮኖችና ጋዜጦች በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 2ዐ ተ.ቁ 3 የተከሰሱ ሰዎች ‹‹በፍርድ ሄደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር . . . መብት አላቸው›› የሚለውን በመጣስ አሸባሪነታቸው የተረጋገጠ እንደሆነ በአደባባይ ሲገልጽ ከርሟል፡፡ አሁንም እየገለጽ ነው፡፡
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ሕገ-መንግሥቱን የማሰከበርና የማስጠበቅ ኃላፊነትን በቃለ-መሀላ የተቀበሉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጥቅምት 9 ቀን 2ዐዐ4 ዓም ፓርላማ ተገኝተው በአደረጉት ንግግር በሽብር ተጠርጥረው ከተያዙት ተከሳሻች መካከል አንድም ሰው ማስረጃ ያልቀረበበት የለም ብለዋል፡፡ አልፈው ተርፈውም ሁሉም ተከሳሾች በበቂና በአሳማኝ ሁኔታ ወንጅለኛ ሆነው ስለተገኙ ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት በማለት በሕግ በሚያሰጠይቃቸው መልኩና በተለመደው ማንአለብኝነት የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ ጥሰውታል፡፡ የሚገርመው ጉዳዩ ግን እንዲህ ዓይነቱ ማረጋገጫ ከተሰጠባቸውና አለአግባብ ከተንገላቱት ሰዎች መካከል አራት ሰዎች በቅርቡ መፈታታቸው ነው፡፡ የተነገረውና እውነታው ሰማይና ምድር ያህል የተለያየ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የሌሎቹም ተከሳሾች ጉዳይ ከዚህ የተለዬ አይደለም የሚል እምነት አለ፡፡ ተከሳሾቹን እኛ የምናውቃቸውና የምንመሰክርላቸው በሠላማዊ ትግል ተምሳሌትነታቸው ነው፡፡ ዛሬም ድምፃችንን ከፍ አድርገን እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
ህዳር 9 ቀን 2ዐዐ4 ዓም በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች (ቃሊቲ) የተፈፀመው የአምባገነኖች የሕገ-መንግሥት ጥሰት ደግሞ አንድ ሌላ ተጨማሪ ማስረጃ ነው፡፡ በእለቱ የማረሚያ ቤቱን ሕግ መሠረት በማድረግ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበርና ሁለት ም/ሊቀመናብርት፣ የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚና የብሔራዊ ም/ቤት አባላት በቃሊቲ በመገኘት በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የታሰሩትን የፓርቲውን አባላት፣ የመድረክ አባል ፓርቲ አባላትና ጋዜጠኞችን ለመጠየቅ 6፡ዐዐ ሰዓት ላይ በቃሊቲ በመገኘት ከሕዝብ ጋር ተራ ይዘው ወደ ግቢው ቢገቡም በእስር ቤቱ ኃላፊዎች የተለመደ የማንአለብኝነትና የአምባገነንነት መንፈስ የሕገ-መንግሥቱን አንቀጽ 21 በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች መብት በሚለው ስር ተ.ቁ 2 ‹‹ ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው ከጓደኞቻቸው (ስርዝ የተጨመረ) . . . ጋር ለመገናኘትና እንዲጎበኛቸውም እድል የማግኘት መብት አላቸው›› የሚለው ተጥሶ ጥየቃውን ተከልክለዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ ጥሰት ተገቢ አይደለም በማለት ከኃላፊዎቹ ጋር የተሞከረው ውይይት ሊሳካ አልቻለም፡፡ ምናልባትም የዓይናችሁ ቀለም ስለአላማረን ነው የማትገቡት የሚለው አባባል እዚህም ሊጠቀስ ይችል ይሆናል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ የሕገ-መንግሥት ጥሰት አዲስ አይደለም፡፡ ከዚህ የባሱ የሕገ-መንግሥት ጥሰቶች በከፋና በሚጎዳ ሁኔታ እየተፈፀሙ ነው፡፡ መንግሥት በሕዝብ ስም በአደራ የያዘውን ሥልጣን ለሕዝብ ማጥቂያ እየተጠቀመበት ነው፡፡ በሕግ ሽፋን ሕዝብን የማጥቃት ዘመቻ እያካሄደ ነው፡፡
የዚህ መግለጫ ዋና ዓላማ ምንም ቢዘገይ የመንግሥትን ሥልጣን የያዘው ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ በሰከነ አዕምሮ ስለአገርና ስለ ሕዝብ፤ ስለ ሕገ-መንግሥታዊነት እንዲያስብበት ለማሳሰብ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊን እንደ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ጉልበተኝነትንና ጥቃትን አምርረን እንጠላለን፡፡ እንታገለዋለንም፡፡ ትግላችንም ጥቃትንና ጉልበተኝነትን ከአገራችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ነው፡፡ ኢህአዴግአዊያን ግን ጉልበተኝነትን፣ አምባገነንነትን፣ ጥቃትን፣ እንቃወማለን ሲሉ ‹‹ብሶት የወለደን ነን ሲሉ›› ጉልበተኝነትን፣ አምባገነንነትን፣ ጥቃትን ከአገር ለማጥፋት ሳይሆን እራሳቸውን አዲስ አጥቂዎች፣ አምባገነኖች፣ ጉልበተኞች ለማድረግና ሌሎችን ለመበደልና ለማጥቃት ነው፡፡ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ብሶት የወለዳቸው መሆናቸው ቀርቶ ብሶት የወለደው ሕዝብ እየፈጠሩ ነው፡፡ በእኛ በኩል ኢህአዴግ ከታሪክ ባይማርም ከራሱ ታሪክ በመነሳት ብሶት የወለደው ሕዝብ አምባገነኖችን እንደሚያስወግድ እንገነዘባለን፡፡
ትግላችን ለእኩልነት፣ ለነፃነት ለእድገትና ብልጽግና ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ለሕጋዊነትና ለሕገ-መንግሥታዊነት ነው፡፡ የነፃነቶችና መብቶች መከበር ለእድገትና ብልጽግና ቁልፍ ናቸው፡፡ የነፃነት በርን ጠርቅሞ ዘግቶ ሕገ-መንግሥትን እየደፈጠጡ ስለ ልማት መለፈፍ ትርጉም የለውም፡፡ ሂውማን ደቨሎፕሜንት ኢንዲክስ እንደሚያሳየው ከሆነ በ2ዐ11 ኢትዮጵያ ከ185 አገሮች መካከል በእድገት 174ኛ ደረጃ ላይ ነች፡፡ በዓለም ላይ በእድገት የምትበልጠው 11 አገሮችን ብቻ ነው፡፡› በብልጽግና ደረጃም ቢሆን ኢትዮጵያ ለግምገማ ከቀረቡ 11ዐ አገሮች መካከል 1ዐ4ኛ ነች፡፡ ከዓለም በብልጽግና የምትበልጣቸው 6 አገሮች ብቻ ናቸው፡፡ በዴሞክራሲ ደረጃም የለየላት በአምባገነን ሥርዓት ሥር ያለች አገር መሆኗን ጥናቱ ያሳያል፡፡ ወደድንም ጠላንም እውነታው ይህው ነው፡፡ አውቀን እንታረም፡፡ ይህ በተሳሳተ የታሪክ ጎዳና መጓዝ ለአገርም፣ ለሕዝብም ለኢህአዴግም ከባድ ዋጋ የሚያስከፍል እንዳይሆን እንጠንቀቅ እያልን ባንደማመጥ ደግመን ደጋግመን እንናገራለን፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ህዳር 14 ቀን 2ዐዐ3 ዓም
አዲስ አበባ



I appreciate that UDJ are trying their best to convince Tigre People Liberation FRONT to come to their senses, and UDJ have presented some figures to show that TPLF are actually failinfg Ethiopia. However, what they do not seem to get the grasp of , after 20 years , is the fact that TPLF are not willing to listen or compromise. What ever logical reasoning is presented to the Tigre People Liberation FRONT, it has fallen on deaf ears.
The nature of Tigre People Liberation FRONT is such that they donot understand what democracy or justice means. It is an organisation born out of and surviving through violence and murder. It is a criminal gangster organisation responsible for the death of 100s of 1000s of innocent people over the last 30 years.
Tigre People Liberation FRONT marched to Addis Abeba carrying their guns, violently smashing and murdering anybody that they found in their way. It is therefore futile to expect any common sense out of such a brutal organisation.
Tigre People Liberation FRONT have been sowing the seed of ethnic hatred, division and animosity and inciting violence and pitting people who have lived in peace for generations, one against the other in order to divide and rule.
TPLF can not be expected to bring freedom, democracy and justice to the people, because it is not some thing they know, it is an alien idea to them that only exists in western countries. their leader meles zenawi even said it will take 100 years to introduce democracy in Ethiopia. What he meant is he will not leave power and that he wants his kith and kins to continue his brutal dictatorship.
UDJ please wake up and see the reality as it is, for 20 years you have been hoodwinked and you still do not seem to understand what TPLF mean.
What should happen is that practical measures should be taken by all poltical opposition to help the people to reach the goal of freeing themselves from the grip of Tigre People Liberation FRONT.
for example on the economic front, many people have been suggesting to organise a boycott on EFFORT companies/TPLF businesses. I am sure there are many other ways peaceful struggle could be waged.
UDJ should concentrate on formulating some practical steps to advance the peaceful struggle rather than snding out letters to the Tigre People Liberation FRONT CHIEF ASKING HIM TO DO THIS OR THAT. THIS IS A WASTE OF TIME.
“ከታሪክ የምንማረው ነገር ቢኖር ምንም የማንማር መሆኑን ብቻ ነው” ስማቸው ጠፋኝ የእንግሊዝ ምሁር
What is your role in Dawro people’s drama , Are you a spectator or on the side of the people ?
Thank you Dawit. You were the voice of the voiceless. you spoke through your press about the people who were denied nearly all democratic rights and converted in to mere breathing creatures. you survived under a regime which is an outgrowth of what once was a minor terrorist organisation with narrow tribal-based ideology blessed to become a completely rude and blatantly cruel mafia-dictatorship. Through your newspaper we were able to connect with our country and its dire politics. you laboured to reach us with your media information with the only hope that ethiopia will become a better place to live tomorrow. You carry a heart that beats the painful life of the ethiopian people under an arrogant and cynical dictator. i am sure your effort will never be in vain.
ተክላይ :
“ከታሪክ የምንማረው ነገር ቢኖር ምንም የማንማር መሆኑን ብቻ ነው” ስማቸው ጠፋኝ የእንግሊዝ ምሁር
ውድ ኢዴፓዎች መልካም ብላችዋል:: ብሶት የወለደው ሕዝብ አምባገነኖችን እንደሚያስወግድ ሁላችንም አይተነዋል:: ልብ ያለው ግን ልብ ይበል::
god is love
ግፍ ይብቃን መላ እንፈልግ አንድ እንሁን ወያነ ይወገድ:: ኢትዮጵያ አንድ ናት:: አንፍራ ሞት አንድ ነው:: ሲገሉን ዝም ብለን አንይ!!!
ወድ አንነድነቶች!
በመርህ ደረጃ ሰዎች ከስህተታቸዉ ይማራሉ:: በመርህ ደረጃ የሚታዉቁትና በትምህርት ቤትም ከተማራቸሁት የተለዬ ነገር መኖሩ የማይቀር ነዉ:: የኢትዮጲያዉ አፋኝ አገዛዝ ከስህተቱ የተማረበት ወቅት አልነበረም:: የመማር ችሎታ የለዉም:: ስለሆነም ዛሬ በተዓምር ይማራል ብሎ መጠበቅ አይቻልም:: በማይድን በሽታ የታመመ አይድንም:: ይህ አገዛዝ በማይድን በሽታ እንደታመመ በሽተኛ ስለሆነ ይማራል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነዉ::
አፄ መለሰ የፃፈዉን ህገ መንግስት አያዉቀዉም:: ካድሬዎቹም እንደዚሁ::
መለስ ዜናዊ የሚይዘዉን የሚጨብጠዉን ሲያጣ ወደ ሱማሌ ዘሎ ይገባል:: የኢትዮጰያ ወታደር ሱማሌ ግባ ስባል ትዕዛዙን ተቀብሎ ሱማሊያ ይገባል:: የሱማሌ ሜዳ ላይ እንደወረቀት እየተቃጠለ አስከሬኑ ይጎተታል:: ለ24 ወራት በደረቱ ላይ የዕቶን እሳት አስተናግዱ ወዳገሩ ለተመለሰዉ ሰራዊት አፄ መለስ ስለደረሰበት ማብራሪያ ለመስጠት ያለመገደዱን በትዕብት ባደባባይ ነበር የተናገረዉ:: ይህ መሳረያ ተሸካሚ ማሺን ሙት ስባል ሞዋች ግደል ስባል ገዳይ መሆኑን ባለፉት 20 ዓመታት ያስመሰከረ ስሆን የሚገርመዉ ልዩ ጀግንነታቸዉን የሚያስመሰክሩት ደግሞ በአቅመ ደካሞቹ ላይ መሆኑኑ ነዉ::
ለሁለት ዓመት ከዘለቀ ታርካዊ አሳፋሪ ጦርነት ሳይማር ተቀርቶ ለተመሳሰይ ጦርት እንደገና ተዘሎ እየተገባ ነዉ::
ሺ አንሽታይኖችን ከፊት ከሁላ ብናቆምላቸዉም ሰዎቹ የማመር ችሎታ የሌላቸዉ ስለሆኖ ድንጋይን ለማስተማር እንደመታገል ነዉ:: ባለፉት ሃያ ዓመታት ሰዎቹ በእንግሊዘኛ ማፉዋጨት ችለዋል:: ይህንን አያዩ ሰዎቹ ሁሉንም መማር የሚችሉ እየመሰላቸዉ እንዴት አይማሩም ይላሉ::
የሰዉ አንጎል የተወሳሰበ በመሆኑ አንዳኛ መደቡ ለም ሌላዉ በረሃ መሆኑ የሚደንቅ አይደለም:.
የመለስ በረከት አገዛዝ እግዚአብሄር እንደሰዶም የማጥፋት ዕቅድ ቢያወጣ እንኩዋን ለመማር የታደለ አይደለም:: እጅግ በጣም ትናንሽ ጉዳዮች ታርክ ሳያገላብጡ መማር የሚገባቸዉን
በተዓምር ለመማር ያልቻሉ ትልልቁን እንዴት ልማሩ ይችላሉ?
እንኩዋንነ ታርክ እንተዉና ቢያልፍም አሁንም የመዝሙራችን አዝማች የሆነዉን ጋዳፊ እንርሳና የኔሰዉ የከፈለዉን መስዋዕትነት መማር ለሚችል ሰዉ ስንት ነገር ያስተምራል::
የኔሰዉ ሰዉ የከፈለዉን መስዋዕትነት ዕብድ ነዉ በሚል ለመሸፋፈን መሞከር በራሱ ነገ ሌላ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን የተገነዘቡ አይመስልም:: ለኢትዮጰያ ወጣቶች እጅግ ብዙ ነገር አስተምሮ አልፈዋል:: ለመለስ አገዛዝና ለስመጥሩዉ የማስፈራራት ዘዴዉ መማር ቢችሉ መጨረሻ የለሌዉ ትምህርት ሆኖ አልፈዋል:: ካሁን በሁላ የራሴን ህይወት ራሴ ማጥፈት ችሎታ ስላለኝ ገለሃለሁ ብለህ ልታስፈረራኝ አትችልም የሚል ያልተፃፈ ህግና ትምህርት አስቀምጦ አልፈዋል:: ከዚህ የተማሩት ነገር ያለ አይመስልም::
የአጼ መለስ ካድሬዎች ሌሎቻችሁም ራሳችሁን አቃጥሉ
በሚል በመለሳዊ መንገዱን ጨርቅ ያድረግላችሁ ቆንቁዋ ሲያላዝኑ እያን ነዉ::
ሳርኮዚ ደጅ ሄዳችሁ ራሳችሁን አቃጥሉ ነዉ ያሉት:: የኔ ሰዉ አሙዋሞት ለለሚገባዉ ሰዉ ከመለስ የበለጠ የሚያስፈራዉ ልኖር ባልቻለ ነበር::
በአሁኑ ሰዓት ዕብድ ነዉ ብሎ ጉዳዩን ለማፈን እየተፍጨረጨሩ ነዉ:: ችሎታ በጊዜ መስረመር ላይ የሚጉዋዝ እንጂ ባንድ ነጥብ ላይ ብቻ የቆመ አይደለም:: ዛሬ መቻል የነገንም መቻል ለማልከት ካልቻለ ከንቱ መፍጭርጨር ነዉ:: ቦልካኖ የሚፈነዳበት ቤት ካለወቅንበት ስንደነስ ይነጋ የለ::
ስልጣን የተቆጣጠሩት ሰዎች ከማሳዘን ያለፉ ጅሎች ናቸዉ:: ብልጥ ለመባል ግን ይፈልጋሉ::
የአጼ መለስ ወያኔ ህገ መንግስቱን ከሌላ አገር በአማርኛ አስተርጉሞ ሕገ መንግስት ነዉ ከማለቱ በስተቀር በህገ መንግስት ተብዬዉ ህዝብ ተወያይቶበት ይህ አንቀፅ ይዉጣ ይግባ ይህ ይሻሻል ያላበት አይደለም:: ተፅፎ በወረቀት ላይ የተቀመጠ ዴዚ ደራታ ነዉ:: ሕገ መንግስት የህጎች ሁሉ በላይ የሆነዉ በህዝቡ ደምና ሥጋ የተዋደ መሆን አለበት::
በአገርቱ ተጨባጭ ሁኔታ ስንት አኩሪ ያልተፃፉ ሕጎች አሉ::
በህግ አምላክ ባብድራ አምላክ ከተባለ መነቃነቅ የለም የሚል ህግ ቢኖር መፃፍና ማንበብ የማይችለዉ ሳይቀር አንቀጹ ጠቅሶ የሚተገብረዉ መሆን በቻለ ነበር::
ባነድራ ጨርቅ ነዉ ያለ በሃለፊነት ቦታ አይቀመጥም የሚል የህግ
ለመቅርፅ ብዙ ዕቀወቀት አይጠይቀም::
ህጉን ከህዝቡ ለማስተዋወቅ ብዙ ሀይል አይጠይቅም::
ኢትዮጲያን የሚታክል ታለቅ አገር ለ20 አንቅጥቅጦ የገዛ ሰዉ ባንድራዉ ጨርቅ ነዉ ያለበትን ይቅርታ ለመጠየቅ አልቻለም::
ይህ አባበል ነዉር መሆኑን ተገንዝቦ ይቅርታ ለመጠዬቅ
ሳይችል የባንድራ ቀን የሚል አዉጄ ሀጢያቴ ይሰረዪልኛል ብሎ ለሚያስብ ጅል: ሌሎች የተወሳቡ ከጀርመን የተተረጎመ ህግ ሸምድዶ ለመተገበር ከአፄ መለስ እሰከ ካድሬዉ በነርሱ ቦታ ሆነን ስናዬዉ ቀላል ኢይደለም::
ምናልባትም ጥቂት የህግ ሰዎች ካልሆኑ በስተቀር በዘህ ዓይነት ሁኔታ የተቀረፀ ሕገ መንግስት በትክክል የሚረዳና የሚተረጉም የለም:: ችገሩ ጠቅላይ ሚኒስተር ተብዬዉ የህገ መንግስት ፈተና ወጥቶ ቢፈተን 50% ለማምጣት እንደማይችል መወራረድ ይቻላል:: ጠቅላይ ሚንሰተር ህገ መንግስቱን ስጥስ ይህ የመጀመረያዉ አይደለም:: አንድ ሺ ጊዜ የራሱን ህገመንግስት ጥሶ አንድ ጊዜ እንኩዋን የተጠየቀበት ወቅት የለም:: ሌላዉን ሁሉ እንተዉና ቀላሉን ነገር እንወሰድና አንድ ተራ ሰዉ ፍረድ ቤት ቀረቦ ያየዉን አላየሁም ብል በዓለም ላይ ባሉት አገርች ሁሉ ይቀጣል::በአደባባይ ስለዋሸ! በኢትዮጲያ ወስጥ ግን ከጠቅላይ ጭራቁ እስከ ትንሹ ካድሬ ያለ ዉሽት አንዲት ምዕራፍ የጨረሱበት ቦታ የለም::
ደበበ እሸቱንና ሌሎችንም ለሶስት ወራት ካንገላቱዋቸዉ በሁላ የለቀቁዋቸዉ ሰዎች አሸባሪዎች ሊሆኑ እንደማይችሉ በግልፅ እየታወቀ ጠቅላይ ሚኒስተር ተብዬዉ የእስካሁኑ ዉሸቶቹ ሞልተዉ ተርፍ እያሉ በፓርላማ ያናፋበትን ለተከተታለ
እነዘህ ዕብዶች አማካሪም የላቸዉ ከመላት የዘለለ ያለዉ ያለ አይመስለኝም::
እስክነድር ነጋ: አንዱ ዓለም አራጌ: የዉብሸት ታዬ እና የርዖቴ ዓለሙ አሸባሪዎች በተዓመር ያለመሆናቸዉን የሚፅፉትን ፅሁፍ የሚከታተል ይመሰክርላቸዋል::
ፅሁፋቸዉን የሚከታተል ሊመሰክር እንደሚችለዉ እነርሱ እንደሚያስቡት 80 ሚሊዬን ሕዝብ ያስባል:: ልዩነቱ እነርሱ በድፍረት ሀሳባቸዉን ሲገልፁ ሌሎቻችን ሀሳባችንን ብንገልፅ
ለሚድረስብን መፍራታችን ብቻ ነዉ::
ከጠቅላይ ጭራቁ አስከ ሆዳደሮቹ የተወለዱበት: ያደጉበት: የሰለጠኑበትንና ወደ ጡረታም የሚያዘግሙበትን የተለዬ ችሎታቸዉ የሆነዉን ወሸት ቀብረዉ በአድሱ ዕዉቀት እዉነት
ለመተካት ለመቻል እንደገና መወለድ አለባቸዉ:: እንደገና መወለድ ይችላሉ ወይ?
እንደገና የ20 ዓመት ዕድል ቢሰጣቸዉም እዉነትን ለመናገር የሚያስችልበት ደረጃ ላይ በተዓምር አያድጉም::
ሃያ ዓመት ዝሪፊያና ሃያ ዓመት ወሽት ብቻ ነዉ የምናነበዉ::
ጋዳፊ 42 ዓመታት ካጨማለቀዉ የበለጠ የመጨሩዉዋን ደቂቃ ለማወቅ ያለመቻሉ ምን ያህል ትንሽ ሰዉ መሆኑን ለማሳዬት ችለዋል:: አጼ መለስም ትንሽ ሰዉ ነዉ:: የመማር ችሎታ የለዉም:: የመጨረሻዉን ደቂቃ ለመማርም የታደለ አይደለም::
In the first place, there is no such title for the party name as “andinet party”, andinet le democracy ina lefitifh”. Those two titles have different conotations and followed by its objectives. The parties objectives are democracy, human right and justice, a subset of unity, territorial integrity, sovereignity of Ethiopia and Ethiopians, which normally could be labeled as “yekotun awerd billa yebituan telech”. And these objectives are reflected in their press release during the split of split of CUD, which eversince have labled itself a prodemocracy movement, a slogan of “no change but durable democracy” and a credible alternative to Kinijit (CUD); which latter formed a coalition with the loyalist opposition parties (ethnic feralists) now identifying itself as “front”, with ethnic agenda, a political cofiguration, making the political arena more complex.