ፍትህ – የፍትህ ጋዜጣ ከወቅታዊ ዘገባዎቿ ጋር
የፍትህ ጋዜጣ አገር ዉስጥ የምትታተም ነጻ ጋዜጣ ናት። የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዮት አለሙ ፣ የፍትህ ጋዜጣ ዘጋቢ ሂሩት ክፍሌ፣ ለአሥራ አራት እና ለአሥራ ዘጠኝ አመታት ኢሰብዓዊና ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ መሰረተ ቢስ በሆነ የሽብር ተግባር ተሰማርታችኋል በሚል በቃሊቲ እሥር ቤት እየተሰቃዩ ነዉ።
ከነዚህ ጀግና ወገኖቻችን ጎን እንቁም። የፍትህ ጋዜጣን እንዲሁም በጽሁፍን እና ንግግር የሚደረግን ሰላማዊ ትግልን ይደግፉ !



በሕገ-አራዊት የሚመሩት ጉጂሌዎች የአሃዝ ስሌት ግድፈት ብቻ ሳይሆን ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም እንዳስቀመጡት የሕሊና ዳኝነት የሌላቸው ለመሆኑ ከሃያ ዓመታት በኋላም መቼም አይማሩም::በዚህ አጋጣሚ ፕሮፌሰሩ ቢያንስ ብዕራቸው መተኮስ በመጀመሩ ሊበረታቱ ይገባል እና ይቀጥሉበት::እኔም ለወንድሞቼ እና ለእህቶቼ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንደግንቦት ሰባት የግሌን ወንድማዊ ምክሬን በሥነ-ግጥም ላካፍል ወደድኩ::
ሃያ ዓመታት ሙሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየደማና እየሞተ አንደቅጠል በረሐብ እየረገፈ አይናችን እያየ ጆሯችን እየሰማ በጥቅምና በፍርፋሪ ለሥልጣን ተገዝተን ሕሊናን የምትሸጡ ሁሉ “አጠገቡ ሲታረድ እንደሚያመነዥግ በግ አትሁኑ::እነበረከት ስምኦን ወይም እነመለስ ዜናዊ አሊያም ሌሎች የፍርፋሪ ባለሥልጣኖች ለማምለጫቸው የገንዘብ እና የሰው ኃይል በጥሩ ሁኔታ አዘጋጅተዋል::ማምለጥ የሚቻለው ግን እግዚአብሔር ሲፈቅድ ብቻ ነው::እንኳን ኢትዮጵያውያን የአምባገነን ባለሥልጣኖችን ይቅርና የናዚ ወንጀለኞች እስከዛሬም እየታደኑ ሰባ ዓመታት ጊዜአቸውን አስቆጥረዋል::ዛሬም የኢትዮጵያ አምባገነን ባለሥልጣን ወንጀእለኞች የትም አገር ማምለጫ የላቸውም:-ዳሩግን ዛሬም ኢትዮጵያ ሕዝቦቿ እየረገፉ”ልማቷን እዩ:መንገዱን ተመልከቱ:ቻይናዎች የሚገነቡትን አስተውሉ:ሕንዶች የሚያለሙትን አድንቁት ይሉናል::በእግዚአብሔር የማያምኑ ሁለቱ ሃገሮች የራሳቸውን ሕዝብ በግፍ አፍነው ይዘው ወደ አፍሪቃ የዘመቱ የአምልኮተ-አጋንንት ተከታዮችና የአምባገነኖች መከታዎች ናቸውና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ንቁ::
******በደም አትፈርሙ!!!*****
ሕሊናን ካወቅነው:-
ደም ውስጡ ረቂቅ ነው::
እናም የደም እሣት ረመጥ ቀለሙ:-
ሕሊናን ይበላል በደም አትፈርሙ::
አትፈርሙ ፍፁም እንዳትሳሳቱ:-
የደም-ዕዳ መምጫ ብዙ ነው ዓይነቱ::
አንዳንዱ በገንዘብ ሌላው ደግሞ ሥልጣን:-
ግፍና ወንጀልነው የሚወርድ ከሰይጣን::
ሁሌም ፍትወትን ክፉ-መንፈስ ይሻል:-
ሕሊና እያደማ ልብን ያቆሽሻል::
ሁሌም ለፈጣሪ እኛ እንዳንታዘዝ:-
ሥጋችን ይያዛል በድንገት በሚያፈዝ::
ግና በፀሎት ነው:-
ርኩስ የሚበነው::
አይተን እንዳላየ:-ሰምተን እንዳልሰማ:-
ሁሌም ያደርገናል ከሃዲ ጠማማ::
በጥልቅ ያደመጡ ልቡና ያላቸው:-
በቁም ከመገደል የሚድኑ ናቸው::
እናም የደም-እሳት ረመጥ ቀለሙ:-
ሕሊናን ይበላል በደም አትፈርሙ::
አሜን!!!