አቡጊዳ – አፍቃሪ ሕወሃት የትግራይ ተወላጆች በሻእቢያ ላይ ጦርነት እንዲከፈት ጠየቁ !
ገዢዉ ፓርቲ በአፋር ክልል ተፈጸመ ባለዉ የሽብር ተግባርን አስመልክቶ፣ አፍቃሪ ሕወሃት የሆነዉ የትግራይ ተወላጆች ማህበር በሰሜን አሜሪካ፣ በሰጠዉ መግለጫ የመለስ አገዛዝ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ።
የገዢዉ ፓርቲ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታዉ ምክር ቤት በሻእቢያ መንግስት ላይ ተገቢዉን እርምጃ የማይወስድ ከሆነ ኢትዮጵያ እርምጃ እንድምትወስድ መግለጹን ያስታወሰዉ የማህበሩ መግለጫ፣ የተባበሩት መንግስታት ማእቀብ ቢጥልም የሻእቢያን እኩይ ተግባር የሚለዉን ለማስቆም እንዳልቻለም ይገልጻል።
“መንግስታችን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የማስከበር መብቱን በመጠቀም ይህንን የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ስጋት የሆነዉን ኃይል ሽብራዊ ተግባርና ጥቃት ለማቆምና የሕዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያረጋገጥ» በመግለጫቸው የጠየቁት የማህበሩ አባላት፣ ገዢዉ ፓርቲ በሻእቢያ ላይ ለሚወስደዉ እርምጃ በሙሉ አቅማቸው እንደሚደግፉት አረጋግጠዋል።
የኢሕአዴግ ድጋፍ ማህበር በሰሜን አሜሪካ የሚባለዉ ማህበር እያለ፣ ለምን የትግራይ ተወላጆች ብቻ ይህንን መግለጫ እንዳወጡ ብዙም የሚታወቅ ነገር ባይኖርም፣ በብዙ አፍቃሪ ኢሕአዴግ የትግራይ ተወላጆች ዘንድ፣ በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ ትልቅ ጥርጣሬ እንዳለም ከውስጥ አዋቂዎች የሚደርሰን ዘገባ ያለመለክታል።
ከዚህ በፊት የተለያዩ ቅሬታ ቢኖራቸዉም ዉስጥ ዉስጡን ከመናገር ዉጭ በይፋ ከገዢው ፓርቲ የተለየ አቋም አንጸባርቀዉ የማያወቁት የአገዛዙ የትግራይ ተወላጅ ደጋፊዎች ፣ አሁን ይሄን አይነት ከአቶ መለስ ፖሊሲ የተለየ፣ አቋማቸዉን ይፋ ማድረጋቸዉ፣ አቶ መለስ በኤርትራ ላይ ባላቸው አቋም፣ ከብዙ የሕወሃት ታጋዮችና ደጋፊች ጋር መሰረታዊ ልዩነቶች እንዳላቸው የሚያሳያ ነዉ።
አቶ መለስ ዜናዊ፣ በባድመ ጦርነት ወቅት፣ ሻእቢያ በመቀሌ ትምህርት ቤት ላይ ቦምብ አፈንድቶ ብዙ ሕጻናትን ሲገድል፣ ኢትዮጵያ እራሷን እንዳትከላከል፣ በኤርትራ ላይ ጥቃት እንዳይሰነዘር ፍላጎት እንደነበራቸውአን ሲያከላክሉ እንደነበረ ይታወቃል። ከርሳቸዉ ፍላጎት ውጭ፣ ጦርነቱ ተጀምሮ ፣ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ቢጠናቀቅም ፣ የአልጀርስ ስምምነትን ተሯሩጦ በመፈረም፣ በአሥር ሺሆች የኢትዮጵያን ደም የተገኘዉን ድል ማስቀልበሳቸው ይታወሳል።
«የትግራይ ተወላጆች ያወጡትን መግለጫ የሚያነብ አይኖርም» ያሉን በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ አንድ የፖለቲአክ ተንታኝ «አቶ መለስ ሻእቢያ ላይ ጦርነት መቼም አይከፍቱም። በየጊዜዉ የሚሰጧቸው አስተያየቶች ፣ የሚያወጧቸዉ ማስፈራሪያዎች፣ የትግራይ ተወላጆችን በሻእቢያ ላይ ጠንካራ እንደሆኑ ለማሳየትና ለማታለል ሲሉ የሚያደረጉት ነዉ» ሲሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።



በመጀመሪያ ወያኔም ሆነ አፍቃሪ ወያኔወች ኢትዪጵያን በታሪክ የማይረሳ የባሀር በር አልባ ወይም ለማኘ አደረጎት ከዛ በሓላ ደግሞ ስንት የአማራና የኦሮሞ ልጆችን አስጨፈጨፉ ካስጨፈጨፉም በሓላ ወያኔ መልሶ አፈገፈፈ ወያኔ የሀገር ጠላት አሁን ደግሞ የወያኔ ተቀጥላ አሜሪካ ቁጭብሎ መግለጫ አውጭ ያውቀዋላ ሄዶ እንደማይዋጋ የሚዋጋው የሚዋጋው ጭቁኑ አማራና ኦሮሞ ነው ሳይበላ ወያኔ ከባላሱ እስከጭፍራወቹው ያማረ እየበላ እየጠጣ ወረቀት ላይ ያወጣል የኢትዪጵያ ነገር ገዶት እንዳይመስላችሁ ቢገደውማ እንደመጣ ተቻኩሎ አይገነጥላትም ነበር
They can go and fight with out us.!!! Or let only Meles and Essayas fight each other. !!!! We will never with the people of Ereterians.!!!!!
አቶ መለስ አፍቃሪ ወያኔወችን ሲያታልሉዋቸው በመጫኛ ጣሉዋቸው !!!!!!!!!!!!!!!!!!
ለገሰ ዘናዊ ኤርትራን የሚነካበት አይዎድም: ምክንያት የናቱ አገር ነች: ለገሰ ቢቻል ኤርትራን መገንባት እንጂ
መዋጋት አይፈልግም: የለገሰ ዘናዊ ዋና አላማ ኢትዮጵያን ከነታሪኩዋ ማጥፋት,ሕዝቡን ማስራብና ማሰደድ,ማሰርና
ማሸበር,የአገሪቱን ሀብት መበዝበዝ ወይም መዝረፍና እርቃንዋን ማስቀረት,በተለይ አማራንና ኦሮሞን በተቻለ መጤን
ማይም ማድረግ, ትግራይን በሁሉም ዘርፍ ማሳደግና ሌሎች ለትግራዮች ተገዥ እንዲሆኑ ማድረግና ሌሎችንም በግድ
እንዲተገበሩ ማድረግ ነው:ይህም የአፓርታይድ አገዛዝን በኢትዮጵያ ማስፈን ነው: አሁን መሰረቱ ተጥሎአል,ወደፊት
ግን 100% ማረጋገጥ ነው የለገሰና ተከታዮቹ ዐላማ::ስለዚህ ይህንን የአፓርታይድ አገዛዝ ማስዎገድ የሁላችንም
ኢትዮጵያውያን ሃላፊነትና የጋራ ትግል ነው::
Woyane and Shabia fighting eachother is not a bad news. It’s just two wild donkeys fighting each other which is non of my business.
Meles will never and ever conduct a war against Eritrea. Those who think so are nave.
በምንም ምክንያት ለኢትዮጵያ ጤኦርነት አያስፈልጋትም ምንም ጥቅም አያስገኝላትም በውጊያ የሰው ልጅ ይሞታል መሞት መጋደል እንስሣዊ ባህሪ ነው:: ይብቃን በአለፈው ጤኦርነት ስንት የድሃ ልጅ አለቀ:: የሃብታም ልጅ ወይም የባለስልጥኣን ልጅ ወይም ዘመድ አልሞተም:: አሁንም የሚጎዳው ድሃው የኢትዮጵያ ልጅ ነው:: ይብቃን!!! እናት አባት ወንድም እህት ዘመድ አዝማድ ማስለቀስ ይቁም ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው እንዲሉ እኝኣ ተደላድለን ቁጭ ብለን ተዋጉ ማለት አሁንም የመለስና የኢሳያስ ዕድሜ ማርዘም ነው:; ለኢትዮጵዮጵይ ምንም አይጤቕምም በአለፈው 70,000 ኢትዮጵያዊ ወጥኣት አለቀ ይደገም የሚል ካለ ኢትዮጵያዊ ይለቅ ማለት ነው:: ያውም ድሃው! በደንብ ማሰብ ያስፈልጋል:: እናስብ ሁላችንም ራሳችን እዛ ውስጥ ሆነን እንየው:: መጋደል ውስጥኣችን ያለው ችግር ነው!!!!!!!
What Abugida calls “natives of Tigray” are in fact false Tegaru. A Tigray man or woman is necessarily one who is very respectful of the patriotic and heroic heritage of Ezana, Kaleb, Yohanes, Alula, etc. The Tigray association in north America is a collection of traitors in the pay of the TPLF, the organization responsible for the death of millions of Tegaru between 1975 until today.
ኢትዮጵያውያን በሙሉ እርስበራስ መናከስን አቁመው Unity in diversity የሁላችንም መፈክር ነው, ያሉ ዕለት ችግሮች በሙሉ ይቃለላሉ!! እስከዚያን ጊዜ ድረስ ግን በማሌሊት በታኝነት ‘ከአፍቃሪም’ ሆነ “ፀላኢ” የሚሰነዘረው የቃላትና የቋንቋ ጨዋታ ሁሉ, እያወናበዱ የስልጣን ዘመናትን ለማራዘም ብቻ ነው የሚያገለግለው:: ጦርነት ብቻውን ደግሞ ምን ጊዜም መፍትሄ ሆኖ አያውቅም::
Let us pray for Peace not war.Lemasmesel endezih eyesafu sewun masasat biker’s minale yihene gibana tewaga bibal yet gigegnalna …America ey tewugn
ጦርነት መመረጥ የሌለበት የሰላም መፍጠር አማራጭ ነው።ተገደህ ከገባህበት የድሉ ባለቤት መሆንህ አያጠራጥርም።ስለዚህ አገራችን ወደ ጦርነት እንድትገባ እየገፋፋት ያለ ቀዌ ዳግም ካልተፈወሰ ሰላማዊ ንሮና ዕድገት ብሎ ማሰብ ዘቨት ነው።
አልማዝ,
ምን እያሉን ነው !? ሊገባኝ አልቻለን!!