አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ በደራሲ ተስፋዬ ገ/አብ አይን በገላነው ክራር

March 11th, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ
  1. አዜብ
    | #1

    ጣይቱ ሚንሊክ ከጣሊያን ቢዋጉ::
    የኔድርሻ አለበት ሲደረመስ ደርጉ::
    ስንቱን ተጋዳላይ ያጋደልኩ እኔ ነኝ:
    ጠይቅ: መኮንን ን: እኔን ካላመንከኝ::
    ስንቴ: በአጥር ዘሎ እዳላዘለለኝ:
    ሚስጥሩን: አውጥቶ: በ ኢሳት ያጋለጠኝ ::
    እኔ ሞኝ አይደለሁ ላገር የምሞተው:
    በዘሬም: የለብኝ :ነገም አላስበው::
    አያት: ቅድም አያቴ : ታሪክ ያቃቸዋል:
    ከጣሊያን ተዋጉ ሲባል ሰምታችኋል??
    ያልዘሩት: አይበቅልም: ነውና ተረቱ:
    አዜብም: አዜብ :ናት ጣይቱም ጣይቱ::
    የኔ ፍላጎቴ ላገሬ የምመኝው:
    ለሀገር: ከመሞት: ሀገርን መግደል ነው::
    ቢዝነስ: ነው: ሆቢዬ: ቢዝነስ :እወዳለሁ:
    ሀገሬን: በመሸጥ: እተባበራለ ሁ::
    በ ኤ ፈርት :ጉዳይ :ከመጣችሁብኝ:
    ህይወቴን :ለመስጠት :ሁሌም: ዝግጁ ነኝ::
    ኢኮኖሚው: በጥፍ: በያመቱ :የሚያድገው:
    የማታቁ: እወቁ : ሀገር ተሸጦ ነው::
    በእርግጥ: አደንቃለሁ :የጣይቱን ነገር:
    ጣሊያን: ወስዶት:ቢሆን :ምን: እንሆን ነበር?
    ልመና: ያልተው ነው:ከጫካ ጀምሮ
    የ ኤ ፈርት ከረጢት ተቀዳዶ ኖሮ::
    ለወባና ለኤድስ የሚላከው ሁሉ:
    እኔ ልብ: ሳልል :ተንጠባጥቧል አሉ::
    ጥሩ ቢዝነስ ናቸው:በሽታና :ችጋር:
    ያሰተዳድሩናል:እኔን :ከባሌ ጋር::

  2. አለም
    | #2

    ስለ ተስፋዬ ሲነገር ሁሌም አጻጻፉ ይደነቅለታል:: ከበአሉ ግርማ ጋር ይስተያያል:: አንዳንዴም ነሸጥ የሚያረጋቸው ከጸጋዬ ገ/መድኅን ጋር ያገናኙታል:: ይህ የሚያስረዳን አድናቂዎቹ ስለ በአሉ ሆነ ስለ ጸጋዬ ብዙ እንደማያውቁ, ሌሎች ጸሐፊያንም እንዳሉ እንዳልተረዱ, ስለ ሥነጽሑፍም ያላቸው መረዳት ግምታዊ እንደሆነ አስረጅ ነው:: በተረፈ, ተስፋዬ የሚጽፋቸው ድርሰቶች ይዘት ሁሌ በጥርጣሬ ይታያሉ:: ተስፋዬ ስለ ታሪክ ጻፈ ማለት የታሪክ ተመራማሪ ነው ማለት አይደለም:: እንደ ማንም ሰው የመሰለውን አሰማምሮ ግን በርዞ የማቅረብ ችሎታ አለው:: እስቲ የዓለማየሁ ገላጋይን “ቀንዳም ኑሮን በቀልድ ቀንበር” [ፍትህ መጽሔት]ያንብቡ:: አመለካከትዎ እንደነበረ ከቀጠለ ችግሩ ያለው እርስዎ ጋ ነው ማለት ነው! ወይም የአቤ ቶኪቻውን ምጸት ያንብቡ:: ወይም …ስንቱን ዘርዝሬ ልጨርስ? ሚዛንዎ በጓደኝነት ከሆነ ችግር ይገጥምዎታል:: ለሚሰማዎም ችግር ፈጣሪ ይሆናሉ!!

  3. አዲስአበባዊ
    | #3

    ጸሃፊው ቀና እና አስተዋይ በመሆናቸው ሳላመሰግናቸው አላልፍም ለአቶ ተስፋዬም ጥሩ የውንድም ያህል መክረዋል አበጁ ሰው ከጥፋቱ ተምሮ እድሜም ሲያስተምረው እርሶ እንዳሉት ቀና አሳቢ ከሆነ በተለይ ጸሃፊዎች ለአንድ መሃበረሰብ መልካም ጎዳና አመላካቾች ይሆናሉ

  4. ኤርምያስ
    | #4

    አቶ ገላው በጣም አመሰግናለሁ እኔም ያልኩት ያንን ነው መጀመሪያ ባለፈ ክፉም ሆነ ደግ ታሪክ ሲጨቃጨቁ መዋል ምንም ትርጉም አያመጣም እንዳልከው ደራሲ ሁሌ ሰውን በጽሁፉ ማስደሰት አይችልም ታዲያ አንዳንድ የሚያስከፋ ጽሁፍን ሲያወጣ በዘሩ አንስተን ከፍና ዝቅ አርገን መስደቡ ተገቢ አይደለም አንተም ለዚህ ማብራሪያ መስጠትህን ወድጄዋለሁ

  5. kemal
    | #5

    ተስፋዬ ገ/አብ ፍላጎቱ ካለው ተደማጭነቱን ለበጎ ነገር ሊጠቀምበት ይችላል በቅርቡ ባደረገው ቃለምልልስ ግን ስለ መሬት መያዝ ግን ተስፋዬ አንድ እውነት ተናግሯል ተቃዋሚዎች ሃገራችንን ከውድቀት ላማዳን የታጠቀ ሰራዊት ማደራጀት ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ ነው ካስፈለገም ሶማሊያ ይሁን ወይም የኦጋዴን ሃይሎች በሚንቀሳቀሱበት ቦታ መሬት መያዝ ግድ ነው ያን ጊዜ ይሄ የተገፋ ህዝብ አንድ መንደርደሪያ አገኘ ማለት ነው! ይህ እስካልሆነ ወያኔ በሰላማዊ ትግል ይለቃል ብሎ ማሰብ ለህዝባችን ያለውን ጥላቻ አለማወቅ ነው!

  6. ሙሴ ሙላቱ
    | #6

    መጻፍ የመቻል ያለመቻል ጥያቄ አይደለም የሚያምሰን::
    እደበዓሉ ግርማ የብዕር አጠጣል የማደንቀዉ እሰከንድር ነጋ ነዉ:: እስክነድር እነደበዓሉ ይፅፋል:: እስክንድርም አንዳንዴ ያነጫንጨኛል:; እንኩዋን እስክንድር ፕሮፌሰር መሰፍንም አነጫንጨዉኛል:: የተራገምኩቸዉን ርግማን ራሴ አዉቃታለሁ::
    ፕሮፌሰሩን በሰደፍ ስመቱ አጥንቴን ዘልቆ ማመሙ ብቻ ሳይሆን መሰፍኔን እንዴት አፍርካዊ መምታት ቀርቶ የሚዳፈር ቃላት ልወጣዉ እንደሚችለዉ ይገርመኛል:: የተሰፋዬ የበዓሉን የመምሰል ያለመመስሉ አላከከኝም:: ተሰፋዬ በትልልቅ ስራዎች መከከል የሚያስተናግዳቸዉ ትናንሽ ነገሮች ይረብሻሉ:: ከዚህ ቀደም የፃፋቸዉን ፅሁፎች የሚያዉቁት ስንገሸገሹ እናያለን:: የጋዜጠኛዉን ማስታወሻ መፀሀፍ ከማሳተሙ አስቀድሜ ተስፋዬ የሚባል ሰዉ ስለመኖሩ አላዉቅ ስለነበርና በቡርቃ ዝምታ ብዙ ቁጣዎች ተነስተዉበት ስለነበር የቡርቃ ዝምታን ለማንበብ ሞክሬ ስለሰለቸኝ አንብቤ አልጨረስኩትም:: ተሰፋዬ የግለሰቦችን ስብዕና ያጠነጠነ አፃፃፍ መተዉ ቢችል የሚጎዳዉ ያለ አይመስለኝም:: ስዬ አብረሃን: ነጋሶ ግዳደን: ዛሬ ደገሞ አፄ ምኒልክን አፄ ምኒልክን ክርስቶስ አይደሉም:: እንደ ተሰፋዬና እንደኛ ሰዉ ናቸዉ:: የሚርባቸዉ: የሚጠማቸዉ: የሰዉነት ፍላጎት ያላቸዉ የታመሙ: ታመዉ በሞት የተደፈ ናቸዉ::ዘሬ ያለዉ ኢትዮጲያዊ ስለ አጼ ምኒሊክ ማዉቅ የሚፈልገዉን ለመገመት የማይችል ደራሲ ሊሆን አይችልም:: ጋዜጠኛ ሊሆንም አይችለም:: አፄ ምንልክ የሰሩት ስራ ለመላዉ አፍርካ አብነት የሆነበትንና በአጼ ምንልክ ላይ ስለምሰነዘሩት ክሶች ምርምርን መሰረት ያደረገ አስተሳሰብ ላይ ፀሃፊዉም አንባበቡዉም ጊዜያቸዉን ዘርተዉ እንድያምረቱ በሚጠበቅበት ሰዓት ለዚህ ዓይነት ጨዋታ ይመለመላሉ ተብለዉ ከሚጠበቁት አንዱ መሆን የሚችለዉ ተስፋዬ በአልባልታ መሰል አበባሎች ባይጠመድ ይመከራል:: አፄ ምንልክ ነጨች በጥቁሮች ላይ ዛሬም ያልሰረዙትን ወስጣዊ ንቀት የሚያሽር መጫዋት የመቻሉን ለማሳዬት የቻለ ጎበዝ ነዉ ልጅ ነዉ:: ደካማ ጎን ያልነበረዉ ፍፁም ሰዉ ነዉ ብለን አልተከራከርንም:: የዚህን ሰዉ ደካማ ጎን ማወቅ እንፈልጋለን ወይ የሚለዉን ጥያቃ ደራሲ ነኝ የሚል መገመት መቻል አለበት:: በሕይወታችን ሁሉን ነገር ለማወቅ እንደማንችል የታወቀ ነዉ:: ስለዚህ ነዉ ገለባዉን ከፍሬ ለይተን አስፈላጊ በሆኑነና በትላልቅ ጉዳዮች በአጭር ዕድሜያችን
    መጠመድ የምንፈልገዉ:: ታዳሚ የማይፈከልገዉን ያበደ ትዓትር የከዉነ አርትዕስት አደራሹን አይቶ ችሎታዉን ራሱን መጠዬቅ ያለበት ይመለኛል:: ተስፋዬ የራሱን ስሜት ሳይሆን መፃፍ ያለበት የአድማጮቹን ስሜት ለመከተል ያለመቻሉ ትልቁ ድክመቱ ይመስለኛል:: በኢትዮጰያችን የማይድን ነቀርሳችን ለመናገር የምንችለዉን ያክል አንድ መቶኛዉን ያክል እንኩዋን ለማዳመጥ አንችልም:: መለስ ዜናዊ ለመስማት ትንሽ ጆሮ አምላክ ቢለግሰዉ ድርጊቱ ከመወገዝ የሚወደስ ይሆን ነበር:: ሀይሉ ሻዉል: ልደቱ አያለዉ: መንግሰቱ ሀ/ማሪያም ፈተናቸዉ ምንድነዉ?
    ተስፋዬም ማዳመጥ አይችለም:: በጣም ያሳዝናል:: ደጋግመን ለመምከር የሞከርን ይመስለኛል:: ለማዳመጥ ቢችል የግለሰብን ስብዕና የመንካት ጨዋታ ልጅነት ለማለት ቢችልና ከዚያ መማር ቢችል ደስ ይለናል:: በአጼ ምኒሊክ አፃጻፉ ያስተላለፈዉ አንድም መልዕክት የለም:: ጊዜ ካጠፋ አይቀር ጉልበቱን ያጠፋበት ለገለባ መሆኑን መገንዘብ መቻል አለበት ደራሲ ነኝ ካለ:: ተስፋዬ ትልቅነትን ከትንሽነት መለዬት መቻል አለበት:: በምኒልክ ላይ የመፃፍ ማንዴት የለዉም ኢትዮጲያዊ ነኝ ካለ:: ኢትዮጲያዊነትን አልፈልገዉም ካለ እንደመለስ መናገር ይችላል አንከራከረዉም:: ምንልክን ለማጥቃት በቅቶ የተረፈ ጊዜ የለንም:: ጋዜጠኞቻችንና ደራሲዎቻችን ቀፍድዶ የያዘን ችግሮቻችን ዙሪያ ቀን ከሌሊት ቢያነጋግሩን ደስታዉን አንችለዉም:: ችግራችን ያለሆነዉን ጉዳይ ጊዜችንን መሻማት ከጀመሩ የኛ ጋዛጠኞችና ደራሲዎች የመሆን መብት የላቸዉም:: ችሎታዉ ኖራቸዉ አልኖራቸዉ::
    መስፍኔ ሰዉ ነዉ::በስህተቶቻ ድፍርን ልንከራክር እንችላለን::
    እሱም በዘህ ችግር ያለበት አይመስለንም:: ስዬንም ነጋሶንም በአንተነት ድፍረን ለሚንናገረዉ አባባል ችግር ያለባቸዉ አይመስለኝም::ለነጋሶ እንደቦርስ የልስን በመለስ ታንኮች ላይ መዘጋጀት እንዳለበት እየነገርነዉ ነዉ:: የፋሺስቱ መለስ ታንኮች ወደ ነጋሶ እተጠጉ ብቻ ሳይሆን ነጋሶም ወደታንኮቹ ጥሪዉን ተቀብሎ በትልቅ ጅግንነት በመጉዋዝ ላይ ነዉ:: ነጋሶን ስዬም በዘህ ሰዓት ከናችን ሆነዉ ለድሮ ለማጥቃት መነሳት ቅመኝነት ነዉ:: መለስ ድሮ ያደረገዉ ሳሆን የሚረብሸን አሁንም አያደረገ ያለዉ ብቻ ሳይሆን ለማድርግ በመዘጋጅት ላይ ያለዉ የወደቀና የበከተ አስተሰሳቡ ነዉ:: መለስ ሊያድረስ የሚችከለዉን ጥፋት ለመግታት በሚናድርፈገዉ ትንቅንቅ እስከስብዕናዉ ሊንዘለቅ እንችላለን:: ከዘህ ባሻግር በጥፋቱ ተፀፅቶ ተጨማሪ ጥፋት ከማድረስ ቢታቀምብ ቢያንስ አገሪቱን የመቸብቸብ ብልግና ቢያቆም ከመለስ ስብዕና ጋር ጊዜ ማጥፋት አስፈለጊ አይደለም::
    ኢትዮጲያ ለዘለዓለም ትኑር!

  7. በለው!
    | #7

    ከድንፋታው አሁን በተግባር መሆን ያለበት
    የወንድ አልጫን በሴት ሚጥሚጣ መተካት!
    አዎን በወሬና በቃላት መደረደር
    ከመለስ በላይ የሚደነፋ ማን ነበር ?
    መቶ ዓመት አልፎ ሃምሳ ቢጨመር
    ለውጥ ካልመጣ ሁሉን አቀፍ
    ያስተዛዝባል በዓመት አንዴ መለፍለፍ !
    የሌላውን እንጃ የእኛ ቤት ልዩ ነው
    ወንዱ እንኳ ሲሞካሽ በሴቷ ነው
    ይባል ነበር!”እከሌ እኮ ወንድ ናት”
    ትንሽም ቢሆን የእጅ አመል ያላት
    አዜብ ጠላች አሉ ‘ቀዳማዊ እመቤት’
    አትበሉኝ አለች የእከሌ ሚስት
    ሴትየዋ ከሱዳን ነች? ከወልቃይት?
    ትርጉሙ እንዴት ገባት ?
    ተታኩሳለች አሉ አስደግፋ ድንጋይ
    ይሻላል ያለችው እንድትባል ታጋይ !
    ለገሠ ፈርቶ ሲደበቅ ሲፈረጥጥ
    ባንክ ሊያዘርፍ ሰው አለቀ እሱ ሲያመልጥ
    የታጋይ ምግባር አጉል ሆነ
    ቡና ሳትቆላ ሳትወቅጥ ተባነነ
    ልጆች አሉኝ አለች የመንገድ ዳር
    ሳይሞቱ የተረፉ ከባሕር ዳር
    እራቁታቸውን የተኙ የተደገፉ ጠጠር
    አዜብን የሚጠብቁ አፋቸውን የከፈቱ
    የወለደቻቸው ውጪ ሀገር ተከተቱ
    ቅቤ በርበሬ ቅመም ምጥንና ቋንጣ
    እንዳይጎልባቸው ይላካል በሻንጣ
    የሀገር ትዝታቸው እንዳይጠፋ
    በዚያውም ይቀራሉ ቀን ከከፋ
    የሴትማ ክብር ታሪክን ክፈቱ
    መልካም ነበረች ብጡል ጣይቱ
    ምነው ውብበአንቺ ድምጽ አልነበራት
    በሙያዋ ኮርታ ነው ሰው ያላያት
    መብቷ ተነፍጎ ይሆን የናቀችን
    መኖሯ ሳይሰማ ሄድኩ ያለችን ??
    የእኛ ቀዳማዊት ሁለገብ ዘማች
    ለገሠ መለሰ እሷም ሰብሳቢ ነች
    ከእኔ በላይ ተኳሽ ! እያለች
    በስንቱ ሰፍሳፋ ላይ አነጣጠረች
    ገና አልገባችም ብቅ ጥልቅ ትላለች
    ከጎኑም ተኝታ ከጎኑ ተቀምጣለች
    ልቧ ትልቅ ነው ከፊት አድርጉኝ ትላለች
    ይመቻል ወይ ?ያዋጣል ወይ ?ተይ በሏት
    መግደልና መምራት እንዳይምታታባት
    ጋዜጠኛዋም ዳኛይቱም አላገኙት
    አዎን እንታገላለን ለሴቶች መብት
    ንግዱንም ፓርላማውንም ይሳተፉበት
    ግን አያድርጉት የቤተሰብ እርስት::!
    ክብር ለሴቶች ይሁን እንረዳዳ
    ቃል ይከበር በለው! ከሀገረ ካናዳ
    >>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>

  8. በለው!
    | #8

    ‘ይቅርታ’ ብያለሁ ሳላቀርብ ሰላምታ
    ሙዳችሁ ነውና ሳያጠፉ ማስጠየቅ ይቅርታ
    ቀዳማዊት አዜብ ከቶ እንደምን አሉ
    ምነው ቀደም ብለው ባልዎን ወከሉ?
    ባልዎን ጥሩልኝ ጊዜ ካላቸው
    የሚወዱት ክራር እረገበ ብለው
    ቅኝት ቢያደርጉት በቸሩ እጃቸው
    ጭብጫቦው ቀለጠ በዚህ በመለስ
    ባለውለታችሁ ሲካብ ሲሞገስ
    የሥራችሁ ውጤት ነው ይበላችሁ ደስ
    ተልኮውን አጧጡፎታል ሁሉን በማዳረስ
    በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ
    በባዶ ቆርቆሮ ክራር ተደምሮ
    ይሄ ቧልት ምንድነው የከፋ ለጆሮ ?
    ተስፍሽ የብሸፍቱ አራዳው
    ኢትዮጵያ ከኤርትራ ተደናገረው
    የአቶ ቡልቻን ብሄር ምነው አጣጣለው ?
    ውስጥ አዋቂ ሌባ መውጫው ብዙ ነው
    ይተረተረዋል ያልገባበት የለ የማያውቀው
    ያልተሳተፈበት ስብሰባ እሱ ያላወያየው
    ተስፋዬ ገብረአብ ለመሆኑ ማነው ?
    እኮ ማነው ? እሱን ፈራጅ ያደረገው
    ጸሐፊ ጋዜጠኛ ምሁር አንባቢ ያለው
    ይህ ሁሉ ዝና አድናቆት የተቸረው
    የወቅቱን አይጽፍም አይተችም
    ከሰው ሥራ ዓረፍተ ነገር ከሚቃርም
    ጨልፈው ቆርጠው ነው የሚያምታቱት
    ለገሥንህ ይሉሃል መልሰው ወስደውት !!
    ጎበዝ ንቃ በድፍን ቅል ትል አለበት::
    ላለፉት አርባ ዓመታት የወጣች ሕትመት
    እንደገና ተሰብስቦ መፈተሽ አለባት
    የእያንዳዱ ግለሰብ ሥራ ይመሳከርበት
    ማን ሰርቶ ማን ገድሎስ በላባት
    እንማን ቆርጠው ሞቱ እነማንስ ቆረጧት
    ይህ ትውልድ እርሃም ጥማቱ ሳያንሰው
    አዕምሮውም ተበክሏል እናክመው
    ለዚህ ነው ሃያ ዓመትን እንደቀላል ያየው
    አፍ ያለው እየቆላ በምላሱ እያቃለጠ
    አጉል ተሞካሽቶ በጣም አላገጠ
    በተናጠል ከምትዋረድ ከምትገመገም
    ልዩነትን አስወግደህ ግንባር ግጠም
    በር ከፍቶ ሰው ሌባ ከማለት
    ለገሰና መለሰ እያሉ ከማማት
    በቃህን ከናቀው እንቢኝ ነው ማለት
    ክብሬ መብቴ ስብዕናዬ ናቸው አሸባሪነት
    አይ የእኔ ነገር እንቢ አልኩ ደገምኩት!!
    በ*************ለ********ው !

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።